cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን

Advertising posts
2 328Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

✝️ ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ ✝️ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡ ✞ ሰኞ- ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡ ✞ ማክሰኞ- ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ "ጌታዬና አምላኬ" ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ.፳፥፳፯-፳፱ ✞ ረቡዕ- አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥና የባህርይ አምላክ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡ ✞ ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡ ✞ አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ✞ ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡ ✞ እሁድ- ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀ መዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን፡✝️ @EOTC_tg
Show all...
✝ክርስቶስ ተንስአ እሙታን በዐቢይ ኃይል ወስልጣን አሠሮ ለሰይጣን አግዐዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍሥሐ ወሰላም "አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነስቷል ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኗልና፤ ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና" ፩ኛ ቆሮ ፲፭፥፳ ሰላም የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሣኤ በሰላም በጤና በፍቅር አደረሳችሁ አደረሰን። በዓሉን የሰላም የፍቅርና የበረከት ያድርግልን።           ✝ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ✝
Show all...
"እንሆ ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጉታላችሁ ተነሥቶል እንጂ በዚ የለም" ሉቃ 24-5 ክርስቶስ ተንስአ ሙታን በዓቢይ ኃይል ወስልጣን አሰሮ ለሰይጣን አጋእዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ካነ ፍስሀ ወሰላም እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ። @EOTC_tg
Show all...
ሰላም ውድ የተዋህዶ ልጆች እንዴት ዋላችሁ? ስርአተ ነግስ ምንድነው? ስርዓተ ነግስ ማለት ማህሌት ስቡዕ ከሚለው እስከ ዘጣዕሙን አልፎ መልክዕ መግቢያ ድረስ ያሉትን ያጠቃልላል። ነግስ የሚይዛቸው ነገሮች አሉ፦ 1.መልክዐ ስላሴ 2. መልክዐ ሚካኤል 3.መልክአ ኪዳነ ምህረት 4.የዚቅ ነግስ 5.ማህሌተ ፅጌ 7.ዘጣዕሙ ነግስ ልክ ስብዕ ሲያልቅ... ዳዊት ነቢይ በከመ ጸለየ...ብሎ እንዳለቀ ሰላም ለአብ ወለወልድ ቃሉ በማለት በተራ በተራ ይባላል። በጣም የተለመደው ብዙ ጊዜ ለቅዱሳን በዓል የሚባለው... ሰላም ለአብ ወለወልድ ቃሉ...ከተባለ በኃላ ሰላም ለአብ ገባሬ ኩሉ አለም...ነው።ይህ ከተባለ በኃላ ሰላም ለአብ ዘእምቅድመ ነጋሲ...የሚባል ሲሆን ለቅድስት ስላሴ በአል ነው። 🌿መልክዐ ስላሴ፦ ሰላም ለአብ ዘእምቅድመ ነጋሲ... ከተባለ በኃላ እንደየበዓሉ 1 ይባላል። ለምሳሌ፦ ሰላም ለጉርኤክሙ-በቅዱስ ሚካኤልና ገብርኤል ሰላም ለኩልያቲክሙ-በዕለተ መድኃኔዓለም(27)፣በዕለተ ማርያም፣በዕለተ መስቀል ሰላም ለገብዋቲክሙ፤ በዕለተ ዮሐንስ መጥምቅ ሰላም እብል ለንዋየ ውስጠ ምህረትክሙ-በዕለተ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወተክለ ሐይማኖት ይባላሉ። ያልተጠቀሱ አሉ፤  ይህ ለምሣሌ ነው። 🌿መልክዐ ሚካኤል፦ ለሕፅንከ-በበአለ ቅዱሳን ነቢያት፣ሃዋርያት፣ጻድቃን፤ሰማዕት ይባላል። ለአጽፋረ እግርከ-በበዓለ ስሉስ ቅዱስ (ስላሴ )፣እግዚአብሔር አብ።፤መድኃኔዓለም፣አማኑኤል፣በዓለ ወልድ ይባላል። በበዓለ ቅድስት ማርያም ና ሚካኤል ከሆነ ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል...ይባላል። 🌿መልክዐ ኪዳነምህረት፦ዘጣዕሙ ከመባሉ በፊት ይባላል። እግዚአብሔር ወሃቤ ብርሀን...- በበዓለ ስሉስ ቅዱስ (ስላሴ )፣እግዚአብሔር አብ፤መድኃኔዓለም፣አማኑኤል፣በዓለ ወልድ ይባላል። ሰላም ለአፉኪ አፈ በረከት ትሩፍ...-በበዓለ ማርያም እና አብዛኛውን ጊዜ ዘጣዕሙ ከመባሉ በፊት ይባላል። 🌿ዘጣዕሙ- ይህ ማለት ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ ነው። 🌿የዚቅ ነግስ፦ ከዚቅ የሚባል ነው። አብዛኛውን ጊዜ መልክዐ ሚካኤል ከተባለ በኃላ ንዌጥን ዝክረ ውዳሴዎሙ ከመባሉ በፊት ይባላል። ዘጣዕሙን ከዘለሉት ወይም ደግሞ ካልተጸነጸለ መጨረሻ ላይ ይባላል። 🌿ማህሌተ ጽጌ፦ ለዕለቱ የሚስማማውን ዘጣዕሙ ከተባለ በኃላ ይባላል። ለምሳሌ፦ በበዓለ ስላሴ ማህሌተ ጽጌ ተፈስሒ ማርያም እንተ ኢተአምሪ ብዕሲ....ይባላል። 💠አንዳንዴ ሊቀያየር  ይችላል። #share @EOTC_tg
Show all...
ዐቢይ ጾም ዐቢይ ለምን ተባለ ቢሉ ‹‹ዐበየ›› ማለት ከፍ አለ ማለት ሲሆን ከዚህም ግስ ዐቢይ የሚለው ቅጽል ይገኛል፡፡ዐቢይ ማለት ከፍ ያለ ትልቅ ማለት ነው፡፡ ዐቢይ ጾም የተባለበት ምክንያት፡- ፩. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ጾም ስለሆነ ፪. በቀኑ ቁጥር ከሌሎች አጽዋማት የሚበልጥ ስለሆነ ፫. ሦስቱ ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎች ማለትም              ➛ ትዕቢት              ➛  ስስት              ➛  ፍቅረ ነዋይ ድል የተመቱበት ስለሆነ ነው፡፡ በቤተክርስቲያን ስያሜ መሰረት በዐቢይ ጾም ውስጥ የሚውሉ ሰንበታት እያንዳንዳቸው መጠሪያ ስም ሲኖራቸው እነርሱም፡- ዘወረደ የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሰንበት ሲሆን ይህም ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን ፈጥሮ የሚኖር አልፋና ኦሜጋ ከሰማየ ሰማያት መውረዱንና ከእመቤታችን ከቅድስተ ቅዱሳን ከንጽሕተ ንጹሐን ከድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመለክት ሥያሜ ነው፡፡ ቅድስት ይህ የሁለተኛው ሰንበት ስያሜ ሲሆን የተባለበትም ምክንያት ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ስለሚያወሳ ነው፡፡ እንዲሁም ይህ ዕለት ዕለተ እግዚአብሔር የተባለች የሰንበት ክርስቲያን ቅድስናን ያመለክታል ምክንያቱም የዚች ዕለት ጌታ እርሱ ቅዱስ እግዚአብሔር ነውና ስለዚህም ዕለተ ሰንበት ቅድስት ተብላለች፡፡ ምኩራብ ይህ የሦስተኛው ሰንበት ስያሜ ሲሆን በዚህ ሰንበት ጌታ በመዋዕለ ትምህርቱ በምኩራብ ገብቶ ማስተማሩ ይነገራል፡፡ እንዲሁም ይህች ዕለት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምኩራብ ገብቶ እንዳስተማረ የሚታሰብበት ዕለት ነው፡፡ ምኩራብ ማለት የቤተ አይሁዳውያን የጸሎት ቤት ነው፡፡ መጻጉዕ ይህ የአራተኛው ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያንን መፈወሱ እውራንን ማብራቱ ለምጻምን ማንጻቱ ሽባዎችን መተርተሩ የሚያነሳ መዝሙር የሚዘመርበት እንዲሁም እነዚህ ሁሉ ድንቅ ገቢራተ ታምራቶች የሚዘከሩበት ዕለት ነው፡፡ ደብረ ዘይት ይህ የአምስተኛው ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ሆኖ ነገረ ምጽአቱን እንዳስተማረ የሚወሳበት ሰንበት ነው፡፡ ደብረ ዘይት ማለት ወይራ የበዛበት ተራራ ማለት ነው፡፡ ገብርኄር ይህ የስድስተኛው ሳምንት ሰንበት ስያሜ ሲሆን ይህም ዕለት ለጌታው ታማኝና በጎ የሆነው ባርያ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ ተብሎ እንደተመሰገነ የሚነገርበት ዕለት ነው፡፡ ኒቆዲሞስ ይህ የሰባተኛው ሰንበት ስያሜ ነው፡፡ ይህም ዕለት ኒቆዲሞስ የተባለው የአይሁድ መምህር በሌሊት ወደ ጌታው ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እየመጣ ይማር እንደነበረ ይታሰብበታል በዚም ዕለት የኒቆዲሞስን ታሪክ የሚያስታውስ መዝሙር ይዘመርበታል፡፡ ሆሳዕና ይህ የስምንተኛው ሳምንት ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት በነቢዩ በዘካርያስ ላይ የተጻፈው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ጌታችም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያይቷ እና በውርንጭላይቷ ላይ ተቀምጦ ሆሳዕና በአርያም ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ ተብ እየተመሰገነ ወደ ቤተ መቅደስ መግባቱ የሚተሰብበት ዕለት ነው፡፡ ሆሳዕና ማለት ‹‹እባክህ አሁን አድን አሁን ባርከን›› ማለት ነው፡፡በሰሙነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሃት ጸሎተ አስተስርዮ ስለማይፈጸም ጸሎተ ፍትሃትና አስተስርዮ የሚደረገው በዚሁ ዕለት ነው::                ጾሙን የበረከት ጾም ያድርግልን፡፡
Show all...