cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

አድስ ነገር #

አዳዲስ እና ትኩስ መረጃ ለማዳመጥም ሆነ ለማምበብ ቻናላችንን ይቀላቀሉን ..እናም ቻናላችን እዲያድግ እና ብዙ አዳዲስ ክስተቶች ለማግኘት linkun ሼር በማድረግ አብረን በጋራ እንደግ https://youtu.be/n3mhyc9RKzs 👇👇👇👇 https://t.me/what_is_newthing 👆👆👆👆

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
436Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት መዓዛ አሸናፊ በግጭት ወቅት የተፈፀሙ ወንጀሎችንና የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በሽግግር ፍትህ ጭምር ማየት እንደሚገባ ገለፁ፡፡ በግጭት ወቅት ወይም ከግጭት በኋላ የተፈፀሙ ወንጀሎችን እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ከመደበኛው የፍትህ ስርዓት ባለፈ በሽግግር ፍትህ ጭምር ማየት የፍትህ ስርዓቱን ለማረጋጋት ወሳኝ ስራ ስለመሆኑ ጠቁመዋል፡፡ የፍትህ ስርዓቱ ግጭቶች ሲከሰቱና ከተከሰቱ በኋላ ሊኖረው በሚችለው አዎንታዊ ሚና ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ የተካሄደ ሲሆን በተለይም በሽግግር ወቅት ስለሚያስፈልገው የሽግግር ፍትህ አተገባበርና ይህንኑ ከመደበኛው ፍትህ ጎን ለጎን ማስኬድ በሚቻልበት አግባብ ላይ ውይይቱ ትኩረቱን አድርጓል። በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሰለሞን አረዳ የተመራው መድረኩ ላይ፥ የአፋርና አማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም ከዳያስፖራው ማህበረሰብ የተውጣጡ የሕግ ባለሙያዎችና የሕግ ምሁራን እየተሳተፉ እንደሚገኙ ኢቢሲ ዘግቧል። (ኢትዮ ኤፍ ኤም)
Show all...
ጋዜጠኛ መአዛ መሃመድ ከእስር መለቀቋ ታወቀ!! የሮሃ ኦንላይን ሚድያ መስራች የሆነችውና ታህሳስ 2 ቀን 2014 ዓ.ም በቁጥጥር ስር የዋለችው ጋዜጠኛ መአዛ መሃመድ ከእስር መፈታቷ ታወቀ። ግልፅ ባልሆነ ምክንያት በቁጥጥር ስር ከዋለችበት ጊዜ ጀምሮ የመአዛ የእስር ምክንያት በፓሊስ ይፋ ተደርጎ ክስ ተመስርቶባት ፍርድ ቤት እንዳልቀረበች ባለቤቷ ለሚድያ በሰጠው ቃል አስረድቷል። ጥብቅና የቆመላት አካል ፍርድ ቤት አለመቅረቧን ተከትሎ ለፍርድ ቤት አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም ፓሊስ ጉዳዩን እንዲያስረዳ በተጠራበት ችሎት አልተገኘም። በአንፃሩ ፓሊስ ጋዜጠኛዋ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በተመለከተ በቁጥጥር ስር እንደዋለች በመጠቆም ፍርድ ቤት መቅረብ አትችልም የሚል ምላሽ እንደሰጠ ተነግሯል። ጋዜጠኛ መአዛ መሃመድ በአባይ ሚድያ፣ በራሷ ሮሃ ሚድያና በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን መንግስትን የሚሞግቱ ትንታኔዎችና አስተያየቶች በማቅረብ እንደምትታወቅ ይታወሳል።
Show all...
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጎንደር ገቡ!! ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የጥምቀትን በአል በታሪካዊቷ ጎንደር ለማክበር ዛሬ ማምሻውን ጎንደር ከተማ ገቡ። ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ወደ ጎንደር ሲገቡ በባህላዊ ስነስርዓት የክብር አቀባባል ተደርጎላቸዋል፡፡
Show all...
በሆሳዕና ከተማ የከተራ በዓል በድምቀት ተከበረ! በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን አማኞች ዘንድ የከተራ በዓል በሃድያ ዞን ዋና ከተማ ሆሳዕና በድምቀት መከበሩን የዞኑ ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ መረጃ ይጠቁማል።
Show all...
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላበረከተችው የ15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ምስጋና አቀረቡ *** ከንቲባ ዳነች አቤቤ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አዲስ አበባ አገረ ስብከት የቦሌ ክፍለ ከተማ አብያተ ክርስቲያናት በጦርነት ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች ያሰባሰቡትን 15 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያለው ድጋፍ ማስረከባቸውን በማህበራዊ ገፃቸው አስታውቀዋል። ከንቲባዋ ቤተክርስቲያኗ ላደረገችው ድጋፍ በተጎዱትና ለችግር በተጋለጡት ወገኖቻችን ስም አመስግነዋል። ድጋፉን በሁለቱም ክልሎች ለተጀመረው መልሶ ግንባታ በታማኝነት እንደሚውልም አረጋግጠዋል።
Show all...
"ጦርነቱ እንደቀጠለ ነው‼️‼️" ህወሓት በአፋር ህዝብ ላይ በድጋሚ እያካሄደ ያለውን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ በአስቸኳይ ማቆም አለበት ሲል የአፋር ክልል መንግስት አስጠንቅቋል። "አሸባሪው ህወሓት በኪልበቲ ረሱ / ዞን ሁለት / በአብአላ በኩል ከታህሳስ 10/2014 ጀምሮ በከፈተው አዲስ ግንባር በተከታታይ እየተኮሰ ባለው ከባድ መሳሪያ ንፁሀን ዜጎችን መጨፍጨፉን ቀጥሏል" ብሏል ክልሉ። "የትግራይን ህዝብ ከሁሉም ኢትዮጵያውያን ጋር ለማናከስ ቆርጦ የተነሳው አሸባሪው ህወሀት በትግራይ ክልል አዋሳኝ በሆነው በዚሁ አካባቢ የትግራይን ህዝብ ከጎረቤቱ ጋር በማናከስ፣ ጉርብትና እንዲሻክርና ጎረቤቶችን በማጣላት የራሳቸውን እድሜ ለማራዘም አፋር እና ትግራይ ጎረቤት ህዝቦችን እያናከሰ ይገኛል" ሲል አሳውቋል። "ጎረቤታሞች በሰላም ውሎ እንዳያድር ትልቅ ጥረት በማድረግ ላይ ነው" የሚለው የአፋር ክልል" የትግራይ ህዝብም ይሄንን የጀንታውን እብደት ሊቃወም ይገባል፤ በቃቹህ ሊሉ ይገባል" ሲል አስገንዝቧል። ቡድኑ በንፁሀን የአፋር ህዝብ ላይ በተለይም በኪልበቲ ረሲ ዞን አብአላና መጋሌ በኩል የከፈተውን በጥብቅ ሊያወግዝ ይባልም ብሏል። ህወሓት በትናንትናው እና በዛሬው ዕለት በተለየ መልኩ ተደራጅቶ በመምጣት ከባድ መሳሪያዎችን በመተኮስ በርካታ ንፁሀን ላይ ጉዳት አድርሷል፣ የህዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማት እና የግለሰብ የንግድ ተቋማት እና መኖሪያ ቤቶችን አውድሟል ሲል የአፋር ክልል አሳውቋል። አሸባሪው ህወሀት ካሁን በፊት ጦርነት በከፈተባቸው የአፋር አካባቢዎች በጣም በተደራጀ ሁኔታ ተደጋጋሚ እና ፋታ የማይሰጥ ጥቃት በመክፈት ወደ ፊት ገፍቶ ለመሄድ የሞት ሽረት ትግሉን እያደረገ ይገኛል " ሲል ገልጿል።
Show all...
የሶማሊያ መንግስት ቃል አቀባይ መሐመድ ኢብራሂም ሞአሊሙ የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው‼️ የሶማሊያ መንግስት ቃል አቀባይ መሐመድ ኢብራሂም ሞአሊሙ በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው አቅራቢያ የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው፡፡ መሐመድ ኢብራሂም ሞአሊሙን ለመቁሰል ለዳረገው የግድያ ሙከራ አልሸባብ ሀላፊነቱን ወስዷል፡፡ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት በሞቃዲሾ መስቀለኛ መንገድ ላይ የደረሰው ፍንዳታ በአጥፍቶ ጠፊዎች የተቀነባበረ ነው። @
Show all...
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተላለፈ መልዕክት ‼️ አሸባሪው የትግራ ወራሪ እና ዘራፊ ቡድን አማራ ክልል ላይ ባካሄደው ወረራ በክልላችን ሕዝብ እና መንግሥት ሃብት እና ንብረት ላይ ከፍተኛ ዘረፋ እና ውድመት አድርሷል። የወራሪውን ቡድን ዘረፋ እና ውድመት ተከትሎ ጉዳት የደረሰባቸውን የክልላችን ሕዝቦች ለማቋቋም በሚል የተለያዩ አካላት የድጋፍ ማሰባሰቢያ የሒሳብ ቁጥሮች እና የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች እያሰናዱ እንደሆነ እየተመለከትን ነው። ነገር ግን ይህ ድርጊት ለቁጥጥር የማይመች እና ከክልሉ መንግሥት እውቅና ውጭ በመሆኑ በዚህ አይነት ድርጊት በመሳተፍ ያሉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ የክልሉ መንግሥት ያሳስባል። በቅርቡም የክልሉ መንግሥት የማቋቋሚያ ገቢ ዝግጅቶች እና የሒሳብ ቁጥሮችን የሚያሳውቅ በመሆኑ ሕዝባችንን መልሶ ለሟቋቋምና ዐሻራችሁን ለማሳረፍ ዝግጅ እንድትሆኑ ጥሪውን ያስተላልፋል። ©ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት @Esat_tv1 @Esat_tv1
Show all...
የሽብር ቡድኑ በአፋር ህዝብ ላይ በድጋሚ እያካሄደ ያለውን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ በአስቸኳይ ማቆም አለበት ‼️ ©የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የህወሓት የሽብር ቡድን በሰላም ወዳዱ የአፋር ህዝብ ላይ በድጋሚ እያካሄደ ያለውን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ በአስቸኳይ ሊያቆም እንደሚገባ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አሳሰበ፡፡ ክልሉ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ መግለጫ አውጥቷል፡፡አሸባሪው ህወሀት በኪልበቲ ረሱ /ዞን ሁለት/ በአብአላ በኩል ከታህሳስ 10/2014 ጀምሮ በከፈተው አዲስ ግንባር በተከታታይ እየተኮሰ ባለው ከባድ መሳሪያ ንፁሀን ዜጎችን መጨፍጨፍ መቀጠሉን መግለጫው ያትታል... ሙሉ መግለጫው ከፋይሉ ጋር ተያይዟል @
Show all...
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የግላቸውን አቋም እንዳያንጸባርቁ ኢትዮጵያ ጠየቀች፡፡ ዶ/ር ቴድሮስ ትናንትና በሰጡት መግለጫ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል ላሉ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ እንዳይደርስ አግዷል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም መንግስት በራሱ ዜጎች ላይ ምግብ፣ መድሃኒት እና ሌሎች የህይወት አድን ድጋፎችን እንዳያገኙ እገዳ ጥሏል ሲሉም ነበር የገለፁት፡፡ ይህንም ተከትሎ በመንግስታቱ ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪ ጽህፈት ቤት፤ ፖለቲካዊ ውግንና አላቸው ያላቸው ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖምን ኢትዮጵያን ከተመለከቱ ጉዳዮች ራሳቸውን እንዲያርቁና ገለልተኛ እንዲሆኑ በትዊተር ገጹ ባሰፈረው መልዕክት ጠይቋል፡፡ ጽህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተሩ የተሰጣቸውን ዓለም አቀፋዊ ሚና ከመወጣት ይልቅ ከፖለቲካዊ እና ግለሰባዊ ፍላጎት የመነጨ ውግንናቸውን እያንጸባረቁ ነው ያለ ሲሆን፤ የተመድ ኤጀንሲዎች ሥራም በዚሁ ምክንያት እየተስተጓጎለ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡ ስለሆነም ዋና ዳይሬክተሩ ኢትዮጵያን ከተመለከቱ የትኞቹም ጉዳዮች ላይ ራሳቸውን እንዲያርቁ፤ በአምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ የሚመራው በተመድ የኢትዮጵያ ተልዕኮ ጽህፈት ቤት አሳስቧል፡፡
Show all...