cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

Maraki News

Addisababa, Ethiopia🇪🇹 News & Media Company® . . ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!! 👉 @MarakiAds ✔

Show more
Advertising posts
124 437Subscribers
-34824 hours
-3787 days
-79530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ስድስት ወራት "ሹገር ማሚ" እና "ሹገር ዳዲ" እናገናኛለን የሚሉትን ጨምሮ ከ166 ሺህ በላይ ህገወጥ ማስታወቂያዎች ተነሱ አዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ስድስት ወራት 166 ሺህ 875 ህገወጥ ማስታወቂያዎች እንዲነሱ መደረጋቸውን የከተማ ውበት እና የአረንጓዴ ልማት ቢሮ አስታውቋል። በቢሮው የከተማ ውበት ልማት ክትትል ዳይሬክተር ወ/ሎ አልማዝ ከበደ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ፣በአዲስ አበባ  በሁሉም  ክፍለ ከተሞች ሊባል በሚችል ደረጃ በርካታ ህገወጥ ማስታወቂያዎች ይለጠፋሉ።በተለይም ደግሞ የህብረተሰቡ ዋንኛ መዳረሻ በሆኑት እንደ ሜክሲኮ እና መገናኛ ባሉት የአዲስ አበባ ቦታዎች ይህ ሁኔታ በስፋት ጎልቶ ይታያል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
Show all...
👍 15🤣 8❤ 2
በታይታኒክ ሮዝ ህይወቷን ያዳነችበት የእንጨት ቁራጭ በ718 ሺህ 750 ዶላር ተሸጠ ታይታኒክ መርከብ ከሰጠመች በኋላ ሮዝ ህይወቷን ያዳነችበት አነስተኛ የእንጨት ቁራጭ በጨረታ ውድ በሆነ ዋጋ ተሸጧል። ተንሳፋፊው እንጨት በሆሊውድ በተለያዩ ፊልሞች ላይ አገልግሎት ላይ ከዋሉ መገልገያ ዕቃዎች፣ አልባሳት ሌሎች ቅርሶች ጋር ለጨረታ ቀርቦ በ718 ሺህ 750 ዶላር መሸጡ ታውቋል። 2 ነጥብ 4 ሜትር ርዝመት እና 1 ሜትር ስፋት ያለው እንጨት በሆሊውድ በተዘጋጀ ጨረታ የተሸጠ ሲሆን፥ በ’ኢንዲያና ጆንስ’ እና ‘ዘ ቴምፕል ኦፍ ዱም’ በተሰኙ ፊልሞች ላይ ጥቅም ላይ የዋለ ጅራፍም በ525 ሺህ ዶላር ተሸጧል። ‘በስፓይደር ማን’ ፊልም ላይ ዋና ገጸ ባህሪው የለበሰው ልብስ በ125 ሺህ ዶላር የተሸጠ ሲሆን፥ አጠቃላይ ከተለያዩ ፊልሞች ከተሰበሰቡ ዕቃዎች ሽያጭ 15 ነጥብ 68 ሚሊየን ዶላር መገኘቱን ሄሪቴጅ አጫራች የተሰኘው ድርጅት አስታውቋል። ሮዝ ህይወቷን የታደገችባት እንጨት ታይታኒክ መርከብ ከሰጠመች በኋላ ከመርከቧ ስብስባሪ በፍለጋ የተገኘ ነው ተብሏል። ታይታኒክ ፊልም በፈረንጆቹ ሚያዝያ 10 ቀን 1912 ከእንግሊዟ ደቡባዊ የጠረፍ ከተማ ሳውዝሃምፕተን ተነስታ ከአምሥት ቀናት በኋላ ከበረዶ ግግር ጋር ተጋጭታ በሰጠመችው የታይታኒክ መርከብ ላይ ተመስርቶ የተሰራ ልብ ወለድ ፊልም ነው።
Show all...
❤‍🔥 3👍 3
የኢትዮጵያ እና የኤምሬትስ አየር መንገድ አውሮፕላኖች ባለፈው እሁድ በሶማሊያ የአየር ክልል ላይ ከመጋጨት ለጥቂት መትረፋቸው ተገለጸ። ነጻ አገርነቷን ያወጀችው የሶማሊላንድ ሲቪል አቪዬሽን እና ኤርፖርቶች ባለሥልጣን ሁለቱ አውሮፕላኖች አየር ላይ ሊጋጩ ተቃርበው የነበረው በሶማሊያ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች አሻሚ እና የተሳሳተ ትዕዛዝ ነው ብሏል። እንደ ባለሥልጣኑ መግለጫ እሁድ መጋቢት 15/2016 ዓ.ም. ምሽት ላይ በሶማሊያ የአየር ክልል ውስጥ ሲበሩ የነበሩት አውሮፕላኖች ሳይጋጩ የቀሩት የሶማሊላንድ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪዎች በወሰዱት “ፈጣን እና ትክክለኛ እምጃ” ነው። የበረራ መቆጣጠሪያ ድረ-ገጽ በሆነው ፍላይትራዳር24 ላይ መመልከት እንደሚቻለው ክስተቱ ባጋጠመበት ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ከአዲስ አበባ ወደ ሕንዷ ቤንጋሉሩ በ37ሺህ ጫማ ከፍታ ላይ ሲበር ነበር። በተመሳሳይ ሰዓት የኤምሬትሱ ቦይንግ 777 አውሮፕላን መነሻውን ናይሮቢ ኬንያ አድርጎ ወደ ዱባይ በተመሳሳይ 37ሺህ ጫማ ከፍታ ሲበር ይታያል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ኢቲ690 በሶማሊያ የአየር ክልል ሲበር ከነበረበት 37ሺህ ጫማ ምሽት 21፡43 (ሌሊት 6፡43) ሲል በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ከፍታውን በፍጥነት ጨምሮ ወደ 39ሺህ ጫማ ከፍ አድርጓል። በዚህም ምክንያት በሁለቱ የመንገደኞች አውሮፕላኖች መካከል ሊከሰት ይችል የነበረን አሰቃቂ አደጋ ለማስቀረት ችሏል። ☑️ @Maraki_News ☑️
Show all...
👍 8
'ከሚደርሱኝ ጥቆማዎች በመነሳት ማረጋገጥ የቻልኳቸው የቤት ፈረሳ መረጃዎች' በኤልያስ መሰረት:- - አያት ዞን አንድ ውስጥ ያሉ በርካታ 'ዘመናዊ' ሊባሉ የሚችሉ መኖርያ ቤቶች ስፍራው ለሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች ግንባታ ስለሚፈለግ ተነሱ እንደተባሉ፣ ባለፈው እሁድ እለት በመንግስት አካላት ስብሰባ ተጠርተው ይህ በይፋ እንደተነገራቸው አረጋግጫለሁ። ይህ በአካባቢው ቤቶችን የማንሳት ጉዳይ ቀጣይ እንደሆነም ታውቋል። - በቦሌ ክ/ከተማ በተለምዶ ጉርድ ሾላ ንግድ ባንክ አካባቢ አስፓልት ዳር ያሉ የግል ቤቶች ተለክተው አንዳንዱ ቤት እስከ ሳሎኑ፣ አንዳንዱ ደግሞ እስከ መኝታ ቤት ድረስ እንዲፈርስ መደረጉ ታውቋል። እስከ ሳሎን ድረስ ብቻ በልኬት የፈረሰባቸው ቀሪውን መኝታ ቤታቸውንና ኪችናቸውን ዛሬ ለመሸፈን መግቢያና መውጪያ በራቸውን ሲሰሩ በድጋሜ አፍርሰውባቸው እንደገና ፍቃድ አውጡ እንደተባሉ ተረጋግጧል።
Show all...
👍 9😢 5🤯 3🤔 1
ብረት መዝግያ ባል! ምታዩት ልጅ በደ/ሱዳን ፕ/ሊግ ላይ ተጫዋች ነው።ታድያማ ሁሌም ከልምምድ ሲመለስ ማገዶ እየለቀመ ለሚስቱ ይዞ ይሄዳል። ይህ ድርጊቱ ያስገረማቸው የኣይ ራድዮ ሰዎች ታድያ ድሪጊቱን ለምን እንደሚፈፅም ሲጠየቅ ... "ለሚስቴ ምግብ ማብሰያ ከሰል እንዳልገዛላት ከሰል 10ሺ የደቡብሱዳን ፓውንድ (4350ብር) ነው።ይህን መግዛት ኣቅሜ ኣይፈቅድም። እንደዚሁ ደሞ ህፃን ልጃችንን በቤት ውስጥ እየተንከባከበች እንደገና ማገዶ ለቀማ እንድትወጣም ኣልፈልግም።ለዚህ ነው ብዙ ጓዶቼ ቢስቁብኝም እኔ ግን ሁሌም ከጨዋታና ልምምድ በሁውላ ማገዶ እየለቀምኩ ይዤላት ምሄደው ሲል ተናግሯል።
Show all...
👍 44❤‍🔥 8❤ 5😢 3🐳 3🤝 1🆒 1
ንግድ ባንክ አላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ያልመለሱ 565 ግለሰቦች የስም ዝርዝር እና የመጨረሻ ማሳሰቢያ ሰጥቷል። ባንኩ ቀደም ሲል ባስጠነቀቀው መሠረት ወደ ቀጣዩ ሕጋዊ እርምጃ ከማለፉ በፊት ገንዘቡን በአፋጣኝ እንዲመልሱ አንድ ተጨማሪ ዕድል የሰጣቸው ሲሆን እስከ ቅዳሜ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ድረስ ገንዘቡን በሚመልሱት ላይ በባንኩ በኩል ቀጣይ ሕጋዊ እርምጃ እንደማይኖር አረጋግጧል። ነገር ግን እስከተጠቀሰው ቀን ገንዘቡን የማይመልሱ ያሉ ግን የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ዘዴዎችን በመጠቀም ሙሉ ስማቸውን፣ ፎቷቸውን፣ በሕገ ወጥ መንገድ ገንዘብ በመውሰድ ወንጀል መጠርጠራቸውን በመጥቀስ ለሚመለከታቸው የሕግ አካላትና ተቋማት በማሳወቅ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ ፤ እንዲሁም ከሕግ አካላትና ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመተባበር ቀጣይ የወንጀል፣ የፍትሐ ብሔርና የአስተዳደር ሕጋዊ እርምጃዎች እንደሚወሰድባቸው ለመጨረሻ ጊዜ ባንኩ አሳስቧል።
Show all...
👍 10❤ 2
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሰሞኑ በተፈጠረው የሲስተም ችግር ሳቢያ ከ 9 ሚሊዮን ብር በላይ የወሰዱትን ወደ 567 የሚጠጉ ግለሰቦችን ማግኘት አለመቻሉን አስታወቀ! ንግድ ባንክ ባጋጠመው የሲስተም ችግር ምክንያት ከተወሰደዉ ከ 801 ሚሊዮን ብር  á‰ áˆ‹á‹­ ገንዘብ 622 ሚሊዮን ያህሉን ወደ ባንኩ ተመላሽ ማድረጉን የገለፀዉ እና ቀሪ 567 ግለሰቦች ደግሞ የወሰዱትን 9.8 ሚሊዮን ብር ማግኘት አለመቻሉን አስታዉቋል።መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ምሽት ላይ ከ 3 ሰዓት ጀምሮ እስከ 8: 45 ድረስ ባለዉ 25 ሺህ 761 ደንበኞች ብር 801.4 ሚሊዮን መወሰዳቸውን ገልጿል። ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ በሂደቱ ዉስጥ የተሳተፉ 15 ሺህ ያህል የሂሳብ ቁጥሮችን ማግኘቱን ያስታወቀው ባንኩ 14 ግዜ ግበይት ነበራቸው ብሏል።በዕለቱ 238 ሺህ 293 ግብይት መደረጉን እና አንድ የባንኩ ደንበኛ ከ 9 ጊዜ በላይ ግብይት መፈፀሙን የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ  ለሁለተኛ ጊዜ በሰጡት መግለጫ አስታዉቀዋል። በሂደቱ ላይ 57 በመቶ ተሳታፊ የነበሩት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መሆናቸው ተነግሯል። አቶ አቤ ሳኖ እንደገለፁት እስከ ትላንት መጋቢት 16 ፤ 2016 ዓ.ም. ድረስ ከተወሰደዉ ገንዘብ 78 በመቶ ወይም ከ 622.9 ሚሊዮን ብር በላይ ወደ ባንኩ ተመላሽ ተደርጓል ብለዋል።በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ዉስጥ በፍቃደኝነት ገንዘብን ተመላሽ ያላደረጉ ግለሰቦች ስማቸዉን ጨምሮ ማንነታቸውን የሚገልፅ ምስዕል ከዛሬ ጀምሮ በተለያዩ አማራጮች ይፋ እንደሚያደርግ አስታዉቋል። ☑️ @Maraki_News ☑️
Show all...
👍 11❤ 1🎉 1🤩 1
በጋምቤላ ሴት መስሎ ሲሰራ በፖሊስ ተይዞ የነበረዉ ግለሰብ ከስድስት ወራት በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ በሸካ ዞን በቤት ሰራተኝነት ሲሰራ በቁጥጥር ስር ዋለ  በደቡብ  ምእራብ ኢትዮጵያ ሸካ ዞን በአንድራቻ ወረዳ ጌጫ ከተማ ሴት በመምሰል ህብረተሰቡን ሲያታልል የነበረው ቢኒያም ከበደ የተባለ ግለሰብ  በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታውቋል። የደብቡ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ምክትል ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ግለሰቡ ቃልኪዳን ወርቁ በሚል ሀሰተኛ ማንነት በቤት ሰራተኝነት ተቀጥሮ በመስራት ላይ እንዳለ ጥርጣሬ የነበራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች  በመጠቆማቸው ፖሊስ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጸዋል። ህብረተሰቡ ከእንደዚህ ዓይነት ግለሰቦች ራሳቸውን እንዲጠብቁና በተለይም ሆቴሎች እና የምግብ ቤት ባለቤቶች ሰራተኛ ሲቀጥሩ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ተብሏል። ግለሰቡ ከዛሬ 6 ወር በፊት በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ ሴት መስሎ በአስተናጋጅነት ተቀጥሮ የቀን ስራ እየሰራ እንዳለ በሰራተኞቹ ጥቆማ መያዙን ብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን መዘገቡ አይዘነጋም። ወጣቱ በጋምቤላም ሆነ በሸኮ ዞን በቁጥጥር ስር በዋለበት ወቅት በተመሳሳይ ሀሰተኛ ስምን በመጠቀም እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።
Show all...
👍 22🤯 6❤ 5
💰 Notcoin ብዙዎቻችን በነጻ ገንዘብ ስለሚገኝበት መንገድ ሲነገረን "መስሚያችን ጥጥ" ነው። ትክክል ነው፤ በነጻ የሚባል ነገር የለም። በቴሌግራም #Notcoin የሚባል ዲጂታል ገንዘብ "በነጻ" ሰብስቡ ሲባል ጥቂት የማይባሉት ግድ ያልሰጣቸውም ለዛ ነው። ነገር ግን #Notcoin ነጻ አይደለም። #Earn የሚለውን ስትነኩት 100 ሺህ እና ከዛም በላይ Notcoin የሚያስገኙ ተግባራት አሉ። ማስታወቂያዎች ናቸው። በእነዚህ ማስታወቂያዎች ቴሌግራም ከመቶ ሚሊዮኖች የሚበልጥ ዶላር ይሰበስባል። እናንተ ማስታወቂያ ያሰራው ድርጅት የማህበራዊ ሚዲያ ገዖችን  #Follow ስታደርጉ በ #Notcoin ክፍያ ትቋደሳላችሁ። ቴሌግራም ደግሞ ለማስታወቂያ ገቢው ምክንያት በመሆናችሁ #Tab በማድረግ ተጨማሪ ዳረጎት ይለግሳችኋል። በቅድመ ግብይት ከ 2.1 ትሪልየን በላይ ለሽያጭ ቀርቧል። ወደዚህ ሽያጭ ለመግባት ቢያንስ 10 ሚሊየን #Notcoin ያስፈልጋል። አሁን አሁን ብዙ ኢትዮጵያውያን በቲክቶክ #ሾለNotcoin እየተወያዩና እየሰበሰቡ ነው። ይህ ትልቅ ለውጥ ነው። ነገር ግን መሰብሰቡ ቆሞ በመደበኛ ዲጂታል ገበያ ለሽያጭና ለግዢ ለመቅረብ ከ #10 ያነሱ ቀናት ብቻ ናቸው የሚቀሩት። በእነዚህ ቀናት የምትችሉትን ሁሉ በማድረግ ኮይን ሰብስቡ። ከታች ባለው ሊንክ ወደጨዋታው ስትገቡ premium ቴሌግራም ከሆናችሁ 50,000 በመደበኛው ደግሞ 2,500 ተጨማሪ #Notcoin ታገኛላችሁ። https://t.me/notcoin_bot?start=rp_29092082 ጨዋታውን ስትጀምሩ በምስሉ እንደሚታየው ነው የሚመጣላችሁ። ከዛ የcoin ምልክቱን ደጋግማችሁ በመጫን ኮይን መሰብሰብ ትችላላችሁ። TAP ከማድረግ በተጨማሪ በቀስት የጠቆምኩት ውስጥ በመግባት Taskኮችን በመፈፀም ኮይን መሰብሰብ ትችላላላችሁ። ግድ የላችሁም ፤ ችላ አትበሉት !!! Click ~ Join ~ Tab 👇👇 https://t.me/notcoin_bot?start=rp_29092082
Show all...
👍 15🤩 3😍 1
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰኔ ወር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ምዝገባ ማድረጋቸውን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) በቅርቡ መግለፃቸው ይታወሳል፡፡ የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች በስተቀር በአብዛኛው የአገሪቱ አካባቢዎች የተማሪዎች ምዝገባ መጠናቀቁም ተገልጿል። የፈተናው ሕትመት በቀጣይ ቀናት እንደሚጀመር ለኢሳት የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሰኔ ወር እንደሚሰጥም አረጋግጠዋል፡፡ ለ3ኛ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተናው፤ ዘንድሮ ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ለእያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት አይነቶች እንዲሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑ አይዘነጋም፡፡
Show all...
👍 19😢 4
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!