cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

አዛኤል

የተለያዩ ልብ የሚነኩ መዝሙሮችና ቃሎችን ጨምሮ የሚያያስተምሩ ነገሮች ያገኙበታል። ይቀላቀሉን ለተለያዩ ሀሳብና አስተያየቶች @Naffota

Show more
Advertising posts
348Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Gd
Show all...
🔷 አንዷ የክርስቶስ የፍቅሩ ጠብታ ነፍሳችሁ፣ መንፈሳችሁ፣ አጥንታችሁ፣ ሁለንተናችሁ በፍቅሩ እንዲነደፍ ያደርገዋል። 🔷 የመጨረሻ መንፈሳዊ ሰው ስትሆኑ በክርስቶስ አጋፔ ፍቅር ትነደፋላችሁ ሌላ ነገር እንኳን ማሰብ እስኪከብዳችሁ ድረስ ሁለንተናችሁን ይሄ አጋፔ ፍቅር ይቆጣጠራችኋል። 🔷 በህይወታችን ህልውናውን እና መገኘቱን መለማመድ ከፈለግን በመጀመሪያ ማድረግ ያለብን የኢየሱስን አጋፔ ፍቅር ማሰብና ማሰላሰል ነው። 🔷 የክርስቶስን ፍቅር ስናሰላስል ኢየሱስን አለመውደድ አንችልም 🔷 የኢየሱስን አጋፔ ፍቅር ስናስብ ለመፀለይ ቃሉን ለማንበብ ለማገልገል ለመዘመር ቀስቃሽ አንፈልግም ፍቅሩ እራሱ ልባችንን ያግለዋል ዝም እንዳንል እንደ እሳት በውስጣችን ይነዳል 🔷 የክርስቶስን አጋፔ ፍቅር ስናስብ ለእግዚአብሔር እብዶች እንሆናለን 🔷 ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ፥ እስከ እግዚአብሔርም ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ -----ኤፌሶን 3: 18-19                   Join👇&Share♻️              @enekegnlet
Show all...
የግድ ታስፈልገኛለህ!!😭🔥 @enekegnlet @enekegnlet
Show all...
“እኛ በእርሱ ሆነን #የእግዚአብሔር #ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።”   — 2ኛ ቆሮ 5፥21 👉አንተ #በክርስቶስ_የእግዚአብሔር_ፅድቅ ነህ        👉በክርስቶስ #ፃዲቅ ሰው ነህ #ኩነኔ_የለብህም የሚኮንንህም አካል የለም ም/ቱም ዋናው አካል አንተን አፅድቆሀልና      #አንተ_በክርስቶስ_ፃዲቅ_ነህ        #አንተ_በክርስቶስ_ፃዲቅ_ነህ “እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? #የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ #የሚኰንንስ ማን ነው?”   — ሮሜ 8፥33       አንተ በእግዚአብሔር #የተመረጥክ       እግዚአብሔር #ያፀደቀክ ሰው ነህ     ♻️ ይ🀄️ላ🀄️ሉን♻️ 👇👇👇👇👇👇👇 @enekegnlet @enekegnlet     ይ🀄️ላ🀄️ሉን
Show all...
. "አማላጄ" ዘማሪ በረከት ተስፋዬ 〰〰〰〰〰〰〰 የኢየሱስ ደም ዛሬም ትኩስ ነው 2x አማላጄ ነው የጌታዬ ደም ዛሬም ትኩስ ነው 2x አማላጄ ነው የሰው ዘር ሁሉ የአዳም ስህተት ይዞት ወደቀ ወደ ጥፋት 2x ማንም እንዳይድን ይሄን ቢረዳ ሊከፍለው መጣ ለሃጥያት እዳ የሃጥያት ደሞዝ ነውና ሞት ሞቴን ሞተልኝ ሰጠኝ ህይወት ሃጥያት ተሻረ ከኔ ላይ በፈሰሰልኝ ጎልጎታ ላይ ቀራንዮ ላይ በገዛ ደሙ እርቅ አወረደ የጠፋሁትን ስለወደደ ሃጥዕ ተብዬ ስም ለወጣልኝ በደሙ አንፅቶ ጻድቅ አስባለኝ ከደጉ አባቴ አሁን ታረቅኩ በቅዱስ ደሙ ስለታጠብኩ ሌላ አማላጅ ሳያስፈልገኝ በቀኙ ሆንኩኝ ደሙ አቀረበኝ የኢየሱስ ደም ዛሬም ትኩስ ነው 2x አማላጄ ነው የጌታዬ ደም ዛሬም ትኩስ ነው 2x አማላጄ ነው የኢየሱስ ደም ሳያስታርቀኝ የማን ጸሎት ነው የሚያስታርቀኝ የኢየሱስ ደም ያላነፃኝ የማን ጸሎት የሚያነፃኝ የኢየሱስ ደም ሳያስታርቀኝ የማን ምልጃ  የሚያስታርቀኝ የኢየሱስ ደም ያላጠበኝ የማን ምልጃ  የሚያጥበኝ ያስታረቀኝ ከአባቱ አማላጅ የሆነልኝ ስለሃጥያቴ ጥብቅና በአብ ፊት የቆመልኝ የኢየሱስ ደም ዛሬም ትኩስ ነው 2x አማላጄ ነው የጌታዬ ደም ዛሬም ትኩስ ነው 2x አማላጄ ነው ለሆንኩት ለኔ ለሞት ፍርደኛ በአብ ቀኝ ያለ አንዱ ብቸኛ ስለበደሌ እሱ ነው ዋሴ የሚቆምልኝ ልክ እንደ ራሴ መሰላል ያየው ያዕቆብ በህልሙ መካከለኛ ነው ክቡር ደሙ ሰማይ ከኔ ጋር እርቅ ያደረገው በማንም አይደል በኢየሱስ ደም ነው ያስታረቀኝ ከአባቱ አማላጅ የሆነልኝ ፣ ስለሃጥያቴ ጥብቅና በአብ ፊት የቆመልኝ 🎼🎼  𝙟𝙤𝙞𝙣 & 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼🎼 @truechristianitych @truechristianitych ─── ❖ ──  ✦ ── ❖----
Show all...
🔷“ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፥ አቤቱ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች።”   — መዝሙር 42፥1         ዋላ ናፋቂ እንስሳ ነው። 🔷የሚናፍቀው ጥሙን የሚቆርጥለትን እርካታውን ነው። ለዋላ ከውኃ በላይ ተወዳጅ ነገር የለውም። ዋላ ውኃን የሚናፍቀው አልፎ አልፎ አይደለም አሁን አሁን ነው። ጠጥቶ ሆዱ ይሞላል በቃኝ ብሎ ሊሄድ ሲል መልሶ ይጠማዋል ስለዚህ ውኃን አሁን አሁን፣ መልሶ መላልሶ ማግኘት ይፈልጋል። እየጠጣውም ይናፍቀዋል። 🔷ዳዊት ራሱን ከዋላ ጋር ያነጻጸረው ነናፍቆት ነው። የዳዊት ናፍቆት እግዚአብሔር ነው። ነፍሱ እግዚአብሔርን በማወቅ ለመደሰት እጅግ ትጓጓለች። ንጉስ ሳለ ናፍቆቱን ምድራዊ ነገሮች ላይ ሳይሆን የነፍሱን ጥም የሚያረካለት እግዚአብሔር አድርጎ ነበር።   🔷እንደ እግዚአብሔር የሚያረካን የለም። የነፍሳችን ጥማት በክርስቶስ እግዚአብሔርን ማወቅና መደሰት ነው። ዋላ ናፍቆቷ የሆነውን ውኃ በማየት ሳይሆን በመጠጣት ትረካዋለች። ነፍሳችን እግዚአብሔርን በማምለክ እርካታን ማግኘት ትፈልጋለች። 🔷በብሉይ ኪዳን በበረሃ ይጓዙ የነበሩት የእስራኤል ህዝቦች ይከተላቸው ይከተላቸው ከነበረው ከመንፈሳዊ ዓለት ጠጥተዋል።  ያ ዓለት ክርስቶስ ነበር ይለናል። (1ኛ ቆሮንቶስ 10፥4) 🔷እስራኤላውያን በበትር ከተመታው ዓለት ውኃን እንደጠጡ ሁሉ እኛም ከተመታው ዓለት ከክርስቶስ ቁስል የህይወት ውኃን ጠጥተናል። እንደ ዋላ የምንናፍቀው ውኃችን ክርስቶስ ነው። ክርስቶስ በወር አንዴ የምናከብረው በዓላችን ሳይሆን እንደ ዓየር ያለማቋረጥ የምንስበው ህይወታችን ነው።                🔷ናፍቆታችሁ ምን ይሆን? ትዳር መያዝ፣ ከሀገር መውጣት፣ ልጅ መውለድ፣........ሁሉ ይደረስበታል። ባንይዘውም አይቆጭም። ነገር ግን ክርስቶስን እለት እለት አለማግኘትና አለመቆራኘት ትልቅ ኪሳራ ነው። ቤተክርስቲያን የምንሄደው ልምድ ስለሆነብን ሳይሆን እግዚአብሔርን በእውነትና በፍቅር ናፍቆን ልናመልከው መሆን አለበት። 🔷አንድ ሰው ናፈቅሺኝ፣ ናፈከኝ ካለ ያለማቋረጥ እናንተን እያሰበ ነው ማለት ነው። አዕምሯቸውን የናንተ ሃሳብ ተቆጣጥሮታል። ልክ እንደዚሁ ሁሉ እግዚአብሔር አዕምሯችንን ሁሉ ማርኮና ተቆጣጥሮ ሌላ ምንም ማሰብ እስኪሳነን ድረስ ሊናፍቀን ይገባል። የምንናፍቀው በደንብ የምናውቀውን ሰው ነው ስናውቀው ደግሞ እጅግ እንወደዋለን። እግዚአብሔርን ለማወቅ እጅግ መትጋት ያስፈልጋል በማወቃችን ውስጥ የጠለቀ መውደድን እናገኛለን። እርሱን ለማወቅ በበረታን ቁጥር ራሱን ይገልጥልናል የፍቅር ጸጋውን ያፈስልገናል::               Join👇&Share♻️              @enekegnlet
Show all...
📚በስሙ_ለምኑ #አብ በወልድ እንዲከብር፣ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ፤ማንኛውንም ነገር በስሜ ብትለምኑኝ፣ እኔ  አደርገዋለሁ። [ ዮሐንስ 14፥13-14 ] #ለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ፣ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ፣ በሩም ይከፈትላችኋል። የሚለምን ሁሉ ይሰጠዋል፤ የሚፈልግም ያገኛል፤ ለሚያንኳኳም በሩ ይከፈትለታል። ከእናንት መካከል ልጁ ዳቦ ቢለምነው፣ ድንጋይ የሚሰጥ አባት አለ? ወይንም ዓሣ ቢለምነው እባብ የሚሰጥ ይኖራልን? #ታዲያ እናንት ክፉዎች ሳላችሁ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት ካወቃችሁ፣ የሰማዩ አባታችሁማ ለሚለምኑት መልካም ስጦታን እንዴት አብልጦ አይሰጣቸውም? ሌሎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ነገር እናንተም አድርጉላቸው፤ ኦሪትም፣ነቢያትም በዚህ ይጠቃለላሉና። [ ማቴ 7፥7 ] #እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ እንድት ሄዱና ፍሬ እንድታፈሩ ፍሬያችሁም እንዲኖር ሾምኋችሁ። ስለዚህም አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል።” [ ዮሐንስ 15፥16 ] #በእርሱም የሚያምን ሁሉ በስሙ የኀጢአትን ስርየት እንደሚቀበል ነቢያት ሁሉ ይመሰክሩለታል። [ ሐዋርያት 10፥43 ]     🔹 @enekegnlet  🔹     🔸 @enekegnlet  🔸
Show all...
ሕይወት በፍቅር የተሞላች ናት ። 1ቆሮ 13:1-13❤❤❤👬❤🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹👬🚶🚶🚶🚶🚶🚶 ሕይወቱ በፍቅር የተሞላ ሰው ታጋሽ ና ደግ  እንዲሁም ከመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች ተካፋይ የሆነ ሰው  ነው። ሕይወት በፍቅር ስትሞላ ፍቅር በትዕግሥት ትዕግሥት በደግነት ደግነት በመልካምነት በመገለጥ በሙሉነት ይኖራል ። እንዲም ይባላል ያለህ 👉...በገንዘብ ሚበልጥህን በእውቀት ብለጠው በእውቀት ሚበልጥህን በፍቅር ብለጠው በፍቅር ሚበልጥህን እርሱን አብልጠ ውደደው... ሕይወቱ በፍቅር የተሞላ ሰው በሌሎች አይቀናም ይልቁንም ሌሎች እዲደሰቱበት መንገድ ይሆናል እርሱም ራሱም  ይደሰታል እንዲሁም አይታበይም አይኳራም ይልቅስ ትሑት ነው። ምክንያቱም የሚታበይ ሰው ራሱን እንጂ ሌሌችን ሰዎችን  አይወድም በፍቅር የተሞላ ሰው ሥረዓተ ቢስ አይደለም በባህሪው ዘውትር የረጋና የሰከነ ሰው ነው። እዲሁም የራሱን ጥቅም ፈላጊ ብቻ አይደለም ይልቅ ስለሌሎች ግድ ይለዋል በበጎነትም ይገለጣል ።1ኛ ቆሮንቶስ 10 ²⁴ እያንዳንዱ የባልንጀራውን ጥቅም እንጂ አንድ ስንኳ የራሱን ጥቅም አይፈልግ። ²⁵ በሥጋ ገበያ የሚሸጠውን ሁሉ ከሕሊና የተነሣ ሳትመራመሩ ብሉ፤ ²⁶ ምድርና በእርስዋ የሞላባት ሁሉ የጌታ ነውና። ²⁷ ከማያምኑ ሰዎች አንዱም ቢጠራችሁ ልትሄዱም ብትወዱ ከሕሊና የተነሣ ሳትመራመሩ የሚያቀርቡላችሁን ሁሉ ብሉ። ²⁸ ማንም ግን፦ ይህ ለጣዖት የተሠዋ ነው ቢላችሁ ከዚያ ካስታወቃችሁና ከሕሊና የተነሣ አትብሉ፤ ²⁹ ስለ ባልንጀራህ ሕሊና እንጂ ስለ ገዛ ሕሊናህ አልናገርም። አርነቴ በሌላ ሰው ሕሊና የሚፈርድ ኧረ ስለ ምንድር ነው? ³⁰ እኔም በጸጋ ብበላ፥ በነገሩ ስለማመሰግንበት ስለ ምን እሰደባለሁ? ³¹ እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውን ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት። ³²-³³ እኔ ደግሞ ብዙዎቹ ይድኑ ዘንድ ለጥቅማቸው እንጂ የራሴን ጥቅም ሳልፈልግ በሁሉ ነገር ሰውን ሁሉ ደስ እንደማሰኝ፥ ለአይሁድም ለግሪክም ሰዎች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንም ማሰናከያ አትሁኑ። 👉👉👉👉 ሲቀጥል ቢጎዳም፣ ቢያጣም፣ ሁሉን ችሎ በፍቅር ያልፋል ምክንያቱም የክርስቶስን ሕይወት ስለተካፈለ  ለመኖርም ስለሚናፍቅ በፍጹም አይበሳጭም ፣በደልንም፣ አይቆጥርም፣ ቂምና ቁጣንም አይዝም፣ የአንድ ሰውን በደል ዘውትር አያስብም ለምን?🚶🚶🚶🚶🚶🚶🚶🚶ለምን የአንድ ሰውን በደል የማንተውና የማንረሳ ከሆነ ያንን ሰው መቀበል ይከብደናል ያኔ ግጭቱ ከበደለን ሰው ጋር ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር ይሆናል ። በመሠረቱ የሠው ልጅ መርሳት ካልቻለህ ጤናማ አይሆንም ያብዳል ሁላችንም ያላበድነው በደንብ አድርገን መርሳት ስለቻልን ነው ። ዳሩ ግን ሕይወቱ በፍቅር የተሞላ ሰው እውነት በሆነ ነገር ይደሰታል በእውነት መንገድም ይጓዛል ነገሮችን ሁሉ በእውነት ጓዳና ይመለከታል “ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤” ኤፌሶን 4፥15 👉👉👉👉👉👉👉የሰዎችንም ድካማቸውን፣ ጉድለታቸውን፣ ይሸከማል፣ ልቡም ንፁ ስለሆነ ዘውትር አሸናፊ ነው።   🚶🚶🚶🚶🚶እውነተኛም ወዳጅ ነው፤ የወዳጅን ያለፈ ታሪክ በማጥናት፣በመውቅስ በማሸማቅቅ ፣ በማሰፈር፣በማስደነግጥ እና ፊት በመንሳት የትላንት ወቃሽ  ሳይሆን ቀጣይ የሕይወት ምዕራፍን የሚያቀና ቅን የሆነ ሰው ነው🚶🚶🚶🚶🚶🚶🚶🚶። ምን ማለት ነው?  ድካሙን፣ ጉድለቱን እና ክፍተታቸውን ከሌሎች ክፍ እና ጎጂ ከሆኑ ዕይታ ይሰውረል በፍቅር ሁሉን ችሎ ይታገሳል። “ትጸልዩም ዘንድ በመጠን ኑሩ፤ ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናልና ከሁሉ በፊት እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።”   — 1ኛ ጴጥሮስ 4፥8   “ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤”   1ኛ ቆሮንቶስ 13፥4 ታድያ ፍቅር ቃል ካይደለህ ፍቅር ተግባር ከሆነ  ፍቅር በሕይወት ምትሞላም ከሆነ ምን ያስፈልገናል ?????? 1 እምነት🙏🙏🙏 :- ሚገርመው እምነት ለአማኙ ሳይሆን ለታማኙ እዳ ነው። ያመነውን ሰው ልባችንን የሰጠነው ሰው ሊከዳን ይችላለ ! ስብናችን ሊያቆሽ! ከሚባለውም በላይ ሊያሳምመኝ ይችላል! ደግሞም ጎርቶኛል !ከሚሉ ውዝግብ ወተን ማመን ስንጀምር ጉዳዩ የእኛ ሳይሆን  የእግዚአብሔር ይሆናል ከእኛም ሚጠበቀው እርሱ ታማኝ አድርጎ እንደቆጠረን ለአገልግሎቱም ለአዲሰ ሕይወትም እደሾመን ሰዎችን አመኖ መቀበል እንጂ መጠርጠር፣ መፍራት ፣መሸበር፣ መወዛገብ፣ ነገን እያሰብ መጨነቅ የማታ ማታ ጉዳትን መፍራት እና ባለማመን ለመውደድ መሞከር ራስን መሸወድ እና በእግዚአብሔር ላይ ማመፅ ይሆንብናል። ሕይወታችንም ከፍቅር ትጎላለች ወገኖች በማመን እኳ ቅጣት የለም አለማመን ግን ቅጣት አለው “ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም።”    1ኛ ዮሐንስ 4፥18 ስለዚህ 👉👉👉👉👉 የነቃም  አይቀጣም በማመንም ሕይወትን ወደ ተሻለ ምዕራፍ እናሸጋግራታለን ፍቅርም ሁሉን ያምናል እግዚአብሔር ከወደድን እንደ ሀሳብም ከኖርን ነገር ሁሉ ለበጎ እዲደረግ ስለምናውቅ   የእኛ ድርሻ ሰዎችን ማመን ነው።“እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።”   — ሮሜ 8፥28 👏👏 ባጠቃላይ ሰዎችን ያለጥርጥር ያለፍርሃት  ለማመን ጨርሶ መሰጠት ያስፈልጋል የምንሰጠውም  ለእግዚአብሔር ቃል መሆን አለበት እምነትን ምናገኘው ከእግዚአብሔር ቃል ስለሆነ  “እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።”   — ሮሜ 10፥17 2ተስፍ ምን ማለት ነው? አንድን ሰው ስንወደው በሳስት ነገሮች ተስፋ እናደርግበታለን 1,በሕይወቱ ሰላም እና ደስተኛ እዲሆን 2,ስኬታማ እዲሆን 3,ተፅኖ ፈጣሪ እዲሆን ተስፋ እናደርግበታለን ። ተስፋም ያየነው አይደለም ዛሬ ላይ በመቆም ነገ ላይ እዲሆንልን የምንፈልገው ሕይወት ነው ። ታውቃላቹ ያለተስፋ ሕይወት አትገፋም ጣምም የላትም ሙላትም አይኖራትም ፍቅር እና መልካምነትም አይገለጡባትም ማስመሰል ይገናል ። 👉👉👉ነገር ግን በሕይወት ብዙ ነገር አይተንባታል ደግሞም እናይባታለን ታድያ በተስፋ እንደዳነ ሰው ተስፋ ማድረግ የለብንም ሮሜ 8 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁴ በተስፋ ድነናልና፤ ነገር ግን ተስፋ የሚደረግበቱ ነገር ቢታይ ተስፋ አይደለም፤ የሚያየውንማ ማን ተስፋ ያደርገዋል? ²⁵ የማናየውን ግን ተስፋ ብናደርገው በትዕግሥት እንጠባበቃለን። 👉👉ተስፍ የነብስ መልቅ ነው በማመን መጠበቅ በመጠበቅ መታመን አለብን:: ዛሬ ላይ ጨለማ የሆነብን ነገር ብርሃ ይሆናል ብሏ ተስፋ ማድረግ መልካም ነው። 👉👉 ለቀን ክፋቱ ይበቀዋል ነገ ለራሱ ይጨነቅ ጊዜ ማይቀይረው ማይፈታው ነገር የለም  ወዳጆች እግዚአብሔር🚶🚶🚶🚶  በሰው ተስፍ አይቆርጥ እኛም በሰው ተስፍ አንቁረጥ ሰውንም ማመን እና ተስፍ ማድረግ የምንችልበት የልብ ፅናት ያስፈልገናል  ። 👉👉👉ስለዚህ እኛ ክርስቲያን የሆንን👬👬🚶👬🚶👬  በማመን እንኑር በተስፋም እንቁም ሕይወታችንም በፍቅር ሙሉ ትሆናለች ብዬ እመክራለሁ @enekegnlet
Show all...
ሕይወት በፍቅር የተሞላች ናት ። 1ቆሮ 13:1-13❤❤❤👬❤🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹👬🚶🚶🚶🚶🚶🚶 ሕይወቱ በፍቅር የተሞላ ሰው ታጋሽ ና ደግ  እንዲሁም ከመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች ተካፋይ የሆነ ሰው  ነው። ሕይወት በፍቅር ስትሞላ ፍቅር በትዕግሥት ትዕግሥት በደግነት ደግነት በመልካምነት በመገለጥ በሙሉነት ይኖራል ። እንዲም ይባላል ያለህ 👉...በገንዘብ ሚበልጥህን በእውቀት ብለጠው በእውቀት ሚበልጥህን በፍቅር ብለጠው በፍቅር ሚበልጥህን እርሱን አብልጠ ውደደው... ሕይወቱ በፍቅር የተሞላ ሰው በሌሎች አይቀናም ይልቁንም ሌሎች እዲደሰቱበት መንገድ ይሆናል እርሱም ራሱም  ይደሰታል እንዲሁም አይታበይም አይኳራም ይልቅስ ትሑት ነው። ምክንያቱም የሚታበይ ሰው ራሱን እንጂ ሌሌችን ሰዎችን  አይወድም በፍቅር የተሞላ ሰው ሥረዓተ ቢስ አይደለም በባህሪው ዘውትር የረጋና የሰከነ ሰው ነው። እዲሁም የራሱን ጥቅም ፈላጊ ብቻ አይደለም ይልቅ ስለሌሎች ግድ ይለዋል በበጎነትም ይገለጣል ።1ኛ ቆሮንቶስ 10 ²⁴ እያንዳንዱ የባልንጀራውን ጥቅም እንጂ አንድ ስንኳ የራሱን ጥቅም አይፈልግ። ²⁵ በሥጋ ገበያ የሚሸጠውን ሁሉ ከሕሊና የተነሣ ሳትመራመሩ ብሉ፤ ²⁶ ምድርና በእርስዋ የሞላባት ሁሉ የጌታ ነውና። ²⁷ ከማያምኑ ሰዎች አንዱም ቢጠራችሁ ልትሄዱም ብትወዱ ከሕሊና የተነሣ ሳትመራመሩ የሚያቀርቡላችሁን ሁሉ ብሉ። ²⁸ ማንም ግን፦ ይህ ለጣዖት የተሠዋ ነው ቢላችሁ ከዚያ ካስታወቃችሁና ከሕሊና የተነሣ አትብሉ፤ ²⁹ ስለ ባልንጀራህ ሕሊና እንጂ ስለ ገዛ ሕሊናህ አልናገርም። አርነቴ በሌላ ሰው ሕሊና የሚፈርድ ኧረ ስለ ምንድር ነው? ³⁰ እኔም በጸጋ ብበላ፥ በነገሩ ስለማመሰግንበት ስለ ምን እሰደባለሁ? ³¹ እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውን ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት። ³²-³³ እኔ ደግሞ ብዙዎቹ ይድኑ ዘንድ ለጥቅማቸው እንጂ የራሴን ጥቅም ሳልፈልግ በሁሉ ነገር ሰውን ሁሉ ደስ እንደማሰኝ፥ ለአይሁድም ለግሪክም ሰዎች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንም ማሰናከያ አትሁኑ። 👉👉👉👉 ሲቀጥል ቢጎዳም፣ ቢያጣም፣ ሁሉን ችሎ በፍቅር ያልፋል ምክንያቱም የክርስቶስን ሕይወት ስለተካፈለ  ለመኖርም ስለሚናፍቅ በፍጹም አይበሳጭም ፣በደልንም፣ አይቆጥርም፣ ቂምና ቁጣንም አይዝም፣ የአንድ ሰውን በደል ዘውትር አያስብም ለምን?🚶🚶🚶🚶🚶🚶🚶🚶ለምን የአንድ ሰውን በደል የማንተውና የማንረሳ ከሆነ ያንን ሰው መቀበል ይከብደናል ያኔ ግጭቱ ከበደለን ሰው ጋር ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር ይሆናል ። በመሠረቱ የሠው ልጅ መርሳት ካልቻለህ ጤናማ አይሆንም ያብዳል ሁላችንም ያላበድነው በደንብ አድርገን መርሳት ስለቻልን ነው ። ዳሩ ግን ሕይወቱ በፍቅር የተሞላ ሰው እውነት በሆነ ነገር ይደሰታል በእውነት መንገድም ይጓዛል ነገሮችን ሁሉ በእውነት ጓዳና ይመለከታል “ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤” ኤፌሶን 4፥15 👉👉👉👉👉👉👉የሰዎችንም ድካማቸውን፣ ጉድለታቸውን፣ ይሸከማል፣ ልቡም ንፁ ስለሆነ ዘውትር አሸናፊ ነው።   🚶🚶🚶🚶🚶እውነተኛም ወዳጅ ነው፤ የወዳጅን ያለፈ ታሪክ በማጥናት፣በመውቅስ በማሸማቅቅ ፣ በማሰፈር፣በማስደነግጥ እና ፊት በመንሳት የትላንት ወቃሽ  ሳይሆን ቀጣይ የሕይወት ምዕራፍን የሚያቀና ቅን የሆነ ሰው ነው🚶🚶🚶🚶🚶🚶🚶🚶። ምን ማለት ነው?  ድካሙን፣ ጉድለቱን እና ክፍተታቸውን ከሌሎች ክፍ እና ጎጂ ከሆኑ ዕይታ ይሰውረል በፍቅር ሁሉን ችሎ ይታገሳል። “ትጸልዩም ዘንድ በመጠን ኑሩ፤ ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናልና ከሁሉ በፊት እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።”   — 1ኛ ጴጥሮስ 4፥8   “ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤”   1ኛ ቆሮንቶስ 13፥4 ታድያ ፍቅር ቃል ካይደለህ ፍቅር ተግባር ከሆነ  ፍቅር በሕይወት ምትሞላም ከሆነ ምን ያስፈልገናል ?????? 1 እምነት🙏🙏🙏 :- ሚገርመው እምነት ለአማኙ ሳይሆን ለታማኙ እዳ ነው። ያመነውን ሰው ልባችንን የሰጠነው ሰው ሊከዳን ይችላለ ! ስብናችን ሊያቆሽ! ከሚባለውም በላይ ሊያሳምመኝ ይችላል! ደግሞም ጎርቶኛል !ከሚሉ ውዝግብ ወተን ማመን ስንጀምር ጉዳዩ የእኛ ሳይሆን  የእግዚአብሔር ይሆናል ከእኛም ሚጠበቀው እርሱ ታማኝ አድርጎ እንደቆጠረን ለአገልግሎቱም ለአዲሰ ሕይወትም እደሾመን ሰዎችን አመኖ መቀበል እንጂ መጠርጠር፣ መፍራት ፣መሸበር፣ መወዛገብ፣ ነገን እያሰብ መጨነቅ የማታ ማታ ጉዳትን መፍራት እና ባለማመን ለመውደድ መሞከር ራስን መሸወድ እና በእግዚአብሔር ላይ ማመፅ ይሆንብናል። ሕይወታችንም ከፍቅር ትጎላለች ወገኖች በማመን እኳ ቅጣት የለም አለማመን ግን ቅጣት አለው “ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም።”    1ኛ ዮሐንስ 4፥18 ስለዚህ 👉👉👉👉👉 የነቃም  አይቀጣም በማመንም ሕይወትን ወደ ተሻለ ምዕራፍ እናሸጋግራታለን ፍቅርም ሁሉን ያምናል እግዚአብሔር ከወደድን እንደ ሀሳብም ከኖርን ነገር ሁሉ ለበጎ እዲደረግ ስለምናውቅ   የእኛ ድርሻ ሰዎችን ማመን ነው።“እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።”   — ሮሜ 8፥28 👏👏 ባጠቃላይ ሰዎችን ያለጥርጥር ያለፍርሃት  ለማመን ጨርሶ መሰጠት ያስፈልጋል የምንሰጠውም  ለእግዚአብሔር ቃል መሆን አለበት እምነትን ምናገኘው ከእግዚአብሔር ቃል ስለሆነ  “እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።”   — ሮሜ 10፥17 2ተስፍ ምን ማለት ነው? አንድን ሰው ስንወደው በሳስት ነገሮች ተስፋ እናደርግበታለን 1,በሕይወቱ ሰላም እና ደስተኛ እዲሆን 2,ስኬታማ እዲሆን 3,ተፅኖ ፈጣሪ እዲሆን ተስፋ እናደርግበታለን ። ተስፋም ያየነው አይደለም ዛሬ ላይ በመቆም ነገ ላይ እዲሆንልን የምንፈልገው ሕይወት ነው ። ታውቃላቹ ያለተስፋ ሕይወት አትገፋም ጣምም የላትም ሙላትም አይኖራትም ፍቅር እና መልካምነትም አይገለጡባትም ማስመሰል ይገናል ። 👉👉👉ነገር ግን በሕይወት ብዙ ነገር አይተንባታል ደግሞም እናይባታለን ታድያ በተስፋ እንደዳነ ሰው ተስፋ ማድረግ የለብንም ሮሜ 8 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁴ በተስፋ ድነናልና፤ ነገር ግን ተስፋ የሚደረግበቱ ነገር ቢታይ ተስፋ አይደለም፤ የሚያየውንማ ማን ተስፋ ያደርገዋል? ²⁵ የማናየውን ግን ተስፋ ብናደርገው በትዕግሥት እንጠባበቃለን። 👉👉ተስፍ የነብስ መልቅ ነው በማመን መጠበቅ በመጠበቅ መታመን አለብን:: ዛሬ ላይ ጨለማ የሆነብን ነገር ብርሃ ይሆናል ብሏ ተስፋ ማድረግ መልካም ነው። 👉👉 ለቀን ክፋቱ ይበቀዋል ነገ ለራሱ ይጨነቅ ጊዜ ማይቀይረው ማይፈታው ነገር የለም  ወዳጆች እግዚአብሔር🚶🚶🚶🚶  በሰው ተስፍ አይቆርጥ እኛም በሰው ተስፍ አንቁረጥ ሰውንም ማመን እና ተስፍ ማድረግ የምንችልበት የልብ ፅናት ያስፈልገናል  ። 👉👉👉ስለዚህ እኛ ክርስቲያን የሆንን👬👬🚶👬🚶👬  በማመን እንኑር በተስፋም እንቁም ሕይወታችንም በፍቅር ሙሉ ትሆናለች ብዬ እመክራለሁ አገልጋይ አቤኔዘር ዳዊት👏👏👏👏 @enekegnlet
Show all...