cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Bekulu Entertainment

ትኩስ መረጃወች በየደቂቃ የሚለቀቁበት channel እዲሁም:- ፠ አጫጭር ታሪኮች ፠ስፖርት እና ወቅታዊ ጉዳዮች ይዘገቡበታል። https://t.me/joinchat/AAAAAEdTBZdXx8xrHyomTg ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info_bot

Show more
Ethiopia1 896Amharic1 529The category is not specified
Advertising posts
10 390Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
ከአርባ በላይ የአማርኛ ፊልሞች ላይ የተወነው ተዋናይ ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) በድንገተኛ ህመም ዛሬ ጠዋት አርፏል ። ተዋናዩ ካባለቤቱ የፊልም ተዋናይት ቃልኪዳን ጥበቡ ጋር ከተለያየ በኋላ ድብርት ተደጋግሞ ያጠቃው እንደነበር ፊደል ፖስት ከቅርብ ወዳጆቹ ሰምቷል። ዕድሜው በሰላሳዎቹ አጋማሽ የሚገኘው ተዋናይ ታሪኩ ተውልዶ ያደገው ተክለ ሐይማኖት አካባቢ ሲሆን የአንድ ልጅም አባት ነው። በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝናን አና በብዙዎች ተወዳጅነትን ያተረፈ ተዋናይ ነው። በጉዳዬ ፊልም ላይ ደግሞ በድርሰት ፣ በዳይሬክተርነት እንዲሁም በትወና ተሳትፎበታል። ከተወነባቸው ፊልሞች መካከል :- 300ሺ፣ የፍቅር ABCD ፣ ብላቴና፣ ቦሌ ማነቂያ ፣ እንደ ባል እና ሚስት ፣ ኢንጂነሮቹ ፣ እርቅ ይሁን ፣ ኢዮሪካ ፣ ጉዳዬ ፣ ሀገርሽ ሀገሬ ፣ ሕይወቴ ፣ ህይወት እና ሳቅ ፣ ከባድ ሚዛን ፣ ፍቅር እና ፌስቡክ ፣ ከቃል በላይ፣ላውንድሪ ቦይ ፣ ኮከባችን ፣ ማርትሬዛ ፣ ይመችሽ-የአራዳ ልጅ 2 ፣ ሞኙ የአራዳ ልጅ ፣ ትዳርን ፍለጋ ፣ አንድ ሁለት ፣ ብር ርርር ፣ ወደው አይሰርቁ፣ ወፌ ቆመች፣ ወንድሜ ያዕቆብ ፣ እንደ ቀልድ ፣ ወቶ አደር፣ አባት ሀገር፣ የሞግዚቷ ልጆች፣ ይዋጣልን ፣ ዋሻው፣ ወሬ ነጋሪ ፣ ወጣት በ97 ተጠቃሽ ናቸዉ። #የኔቲዩብ ለአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ወዳጅና አድናቂዎች መፅናናትን ይመኛል። ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
Show all...
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በነገው ዕለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማብራሪያ  ይሰጣሉ! ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በነገው ዕለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጥያቄዎች ማብራሪያ  እንደሚሰጡ ምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ ነገ ኀዳር 06 ቀን 2015 ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት 4ኛ መደበኛ ስብሰባውን እንደሚያካሂድ የምክር ቤቱ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ለኢዜአ ገልጿል፡፡ በመደበኛ ስብሰባው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መስከረም 30 ቀን 2015 ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ተመላክቷል። በዚህም ምክር ቤቱ የመንግስትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑን ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጿል፡፡ በዕለቱ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙም ተገልጿል። ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
Show all...
ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ከአምባሳደር ኢቶ ታካኮ ጋር ተወያዩ ********************** የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ከሆኑት ኢቶ ታካኮ ጋር ተወያዩ። የጃፓን ህዝብ እና መንግሥት ለክልሉ ልማት እያደረጉት ያለውን ድጋፍ እንደሚያደንቁ ዶ/ር ይልቃል ለአምባሳደሯ ገልፀውላቸዋል። አምባሳደር ኢቶ ታካኮ በበኩላቸው በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ የሰለጠነ ብቁ የሰው ኃይል ለማውጣት ላለፉት 7 ዓመታት ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል። የጃፓን ዩኒቨርሲቲዎች ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር በመስራት በትምህርት ዘርፍ የቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ከሚያበረክቱት አስተዋጽኦ በተጨማሪ የሀገሪቱ መንግሥት ባህርዳር ከተማን ጨምሮ በአማራ ክልል በግብርና፣ በንፁህ መጠጥ ውሃ እና በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ላይ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል። አምባሳደሯ በቆይታቸው በክልሉ የጤና ተቋማት የካይዘን ትግበራ ያለበትን ደረጃ ጨምሮ በመንግሥታቸው የሚደገፉ ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶችን እንደሚመለከቱ ይጠበቃል። ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
Show all...
በኮሜዲያን እሸቱ መለሰ አማካኝነት ከ1.5 ሚልዮን ዶላር በላይ ተሰበሰበ! ኮመዲያን እሸቱ መለሰ "በሀገረ አሜሪካ ለሚቋቋመው ግዙፍ ስፋት ያለው ገዳም ቦታ መግዣ" ከ 1,500,000 የአሜሪካ ዶላር በላይ በአንድ ቀን መሰብሰብ ችሏል። ሰሞኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በአሜሪካ ካሊፎርኒያ በመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወቅድስት አርሴማ ገዳም ሥም ከ1497 ሄክታር በላይ ስፋት ያለው መሬት ልትገዛ እንደሆነ ማስታወቋ ይታወሳል። ይህን ተከትሎ ለገዳሙ መግዣ የሚሆነው ቅድመ ክፍያ ገንዘብ ለማሰባሰብ ኮሜዲያን እሸቱ በትናንትናው እለት ባዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ ከ15ሰአት በላይ በላይቭ(live) በመቆየት በአጠቃላይ ከ1.5ሚሊዮን ዶላር በላይ በማሰባሰብ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው የሆነውን ፈጣን የገቢ ማሰባሰብ ስራን አከናዉኗል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የሰሜን ካሊፎርኒያ፣ ኔቫዳ እና አሪዞና ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ቴዎፍሎስም የገቢ ማሰባሰቡን ያካሄዱትን ኮሜዲያን እሸቱን እና የዶንኪ ቲዩብ አባላቶችን ከልብ አመስግነዋል። በዚህ ሰፊ ይዞታ ላይም የአብነት ትምህርት ቤት፣ መንፈሳዊ ኮሌጅ፣ ዘመናዊ ዩኒቨርሲቲ፣ ሆስፒታል እንዲሁም ሌሎች በርካታ ተቋማትን ለማቋቋም እንደታቀደ የገለጹት ሊቀ ጳጳሱ፣ ለቦታው መግዣ የሚሆነውን 8 ሚሊዮን ዶላር ከምዕመናን ለማሰባሰብ እንደታሰበም ተናግረዋል። Via:- Fidel Post ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
Show all...
ለአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ የኮማንደርነት ማዕረግ ተሰጣት! የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ለአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ልዩ የኒሻን ሽልማት እና የኮማንደርነት ማዕረግ አበርክቶላታል፡፡ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በተሰማሩበት የሥራ መስክ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ 78 የኮሚሽኑ ስፖርት ክለብ አባላት የማዕረግ፣ የገንዘብና የልዩ ኒሻን ሽልማት አበርክቷል፡፡ በሽልማት ፕሮጋራሙ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ልዩ የኒሻን ሽልማት የተበረከተላት ሲሆን በኮሚሽኑ የኮማንደርነት ማዕረግም ተሰጥቷታል፡፡ ኮማንደር አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በተሰጣት ሽልማት መደሰቷን ገልጻ በማረሚያ ቤት ስፖርት ክለብ ትንሽ ልጅ ሆና በመቀጠር አሁን ለደረሰችበት ደረጃ መብቃቷንም አንስታለች፡፡ ሽልማቱ የማረሚያ ስፖርት ክለብ ወጣት አትሌቶች ጠንክረው እንዲሰሩ፣ እንዲበረታቱና የተሻለ ደረጃ እንዲደርሱ ያደርጋል ያለችው አትሌቷ በተለያዩ የውድድር መስኮች የኮሚሽኑ አትሌቶች ውጤታማ መሆናቸውን ገልፃለች፡፡ ኮሚሽኑ ለ34 ስፖርተኞች ከረዳት ሳጅን እስከ ኮማንደር ድረስ የማዕረግ ዕድገት ሲሰጥ ለ19 ስፖርተኞች ደግሞ የገንዘብ እና ለ13 ስፖርተኞች የእርከን ጭማሪና የገንዘብ ሽልማት ሰጥቷል፡፡ ለአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ የተበረከተው ልዩ የሜዳሊያ ሽልማት ከረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ቀጥሎ ለ2ኛ ጊዜ መሆኑን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡ ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
Show all...
በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጸሙ "የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ምርመራ እንዲጀመር እና አጥፊዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ" አሜሪካ ጥሪ አቀረበች። የኢትዮጵያ ተፋላሚ ኃይላት ግጭት ለማቆም፣ ለተቸገሩ ሁሉ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦትን ለማፋጠን፣ የሰላማዊ ሰዎችን ደሕንነት ለመጠበቅ እና መሠረታዊ አገልግሎቶችን መልሶ ለማስጀመር የደረሱበትን ስምምነት ሊያከብሩ እንደሚገባ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ጥሪ አቅርበዋል። ኔድ ፕራስ ትላንት ቅዳሜ ባወጡት መግለጫ ጥሪውን ያቀረቡት የሁለቱ ተፋላሚ ኃይላት የጦር አዛዦች የፕሪቶሪያውን ሥምምነት ተግባራዊ የሚያደርግ ሰነድ ከፈረሙ በኋላ ነው። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ እና የትግራይ ኃይሎች አዛዥ ጄኔራል ታደሰ ወረደ ሰነዱን ከፈረሙ በኋላ የአፍሪካ ኅብረት ባወጣው መግለጫ በትግራይ እና አጎራባች ክልሎች ለተቸገሩ ሁሉ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ያለ ገደብ ለማመቻቸት ከሥምምነት መደረሱን አስታውቋል። ሁለቱ የጦር አዛዦች የተፈራረሙት ሰነድ በፕሪቶሪያ በተደረሰበት ግጭት የማቆም ሥምምነት መሠረት ለግብረ ሰናይ ሠራተኞች እና ለድርጅቶች የደህንነት ዋስትና መስጠት እንዲሁም ለሰላማዊ ሰዎች ጥበቃ ማድረግን ያካተተ ነው። የአፍሪካ ኅብረት ያወጣው መግለጫ እንደሚያሳየው የትጥቅ አፈታት፣ አበታተን እና መልሶ ማዋሃድን የተመለከቱ ጉዳዮችን በዝርዝር የሚያብራራ የጋራ ኮሚቴ ለማቋቋም ተወስኗል። የኢትዮጵያ መንግሥት "በሰላም ሥምምነቱ በተያዘው የጊዜ ገደብ ትጥቅ የሚፈታበት እና መከላከያ ወደ መቐለ የሚገባበት ዕቅድ ላይ" ከሥምምነት መደረሱን ገልጿል። የአውሮፓ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ አኔተ ቬበር የትጥቅ አፈታትን በተመለከተ በሁለቱ ወገኖች መካከል የተደረሰው ሥምምነት "ወደ ፊት የሚወስድ አስፈላጊ እርምጃ" እንደሆነ ገልጸዋል።  ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
Show all...
ሸዋ ደራ ጉንዶ መስቀል  ከአድስ አበባ 220 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች! ከህዳር 03 ቀን ጀምሮ በኦነግ ሸኔ ከበባ ውስጥ ናት። አሸባሪ ሸኔ አምሰት የደራ ቦታ ላይ ሰፍሯል ▪️1. ባቡ ድሬ ▪️2. ሀርቡ ▪️3. ራቾ አሙማ ▪️4.ጁሩ ዳዳ ▪️5. ሰለልኩላ ዙሪያ ቡርቃ የሚባል አካባቢ በተለይ ጉንደ መስቀል ከተማ ውስጥ ገብተው ብዙ ሰው አግተዋል ሞተዋል። ከከበባ ለመውጣት እየተፋለመ ያለው ሚሊሻ ብቻ ነው ፤ እስካሁን በአካባቢው የመንግስት አካል የለም። ትኩረት ለደራ  ሽዋ! ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
Show all...
አሸባሪው ሸኔ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ጉንዶ መስቀል ከተማ መግባቱን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ። ነዋሪዎቹ መንግስት በአስቸኳይ እንዲደርስላቸውም ጠይቀዋል።የሽብር ቡድኑ ከትናንት ጀምሮ በተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ከተማዋ እየገባ መሆኑንና ከተማዋን ሙሉ በሙሉ እንዳይቆጣጠር ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናገረዋል። የከተማዋ ነዋሪዎች በቂ የጸጥታ ሀይል ባለመኖሩ ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ መግባታቸውን ገልጸው መንግስት በአፋጣኝ እንዲደርስላቸው ተማጽነዋል። [Ethio FM] ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
Show all...
የዛሬው ስምምነት የተፈረመበት ዶክመንት ተያይዟል። ዋና ነጥቦች: - በሚቀጥሉት 7 ቀናት ወታደራዊ ሀላፊዎቹ ለወታደሮቻቸው ኦረንቴሽን ይሰጣሉ - ከዛም የፌደራል ባለስልጣናት በትግራይ ሀላፊነታቸውን ይረከባሉ - የከባድ መሳርያዎች ትጥቅ አፈታት በትግራይ ክልል ያሉ የውጭ ሀይሎች እና ከመከላከያ ውጭ ያሉ ሀይሎች ከክልሉ መውጣት ጋር በአንድ ግዜ ይፈፀማል - የቀላል መሳርያዎች ትጥቅ አፈታትን ለማሳለጥ ከሁለቱም ወገን የተውጣጣ ኮሚቴ ይቋቋማል። Via:- ኤልያስ መሰረት ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
Show all...
በኬኒያ ናይሮቢ የተከናወነው የፊርማ ስነስርዓት ሙሉ ፕሮግራም። ስምምነቱን አስመልክቶ የተሰጠው መግለጫ፣ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና ጄ/ል ታደሰ ወረደ ያደረጉት ንግግር፣ ዋና አደራዳሪዎቹ ኦባሳንጆ እና ኡሁሩ ስለ ድርድሩ ሂደት እና ሁለቱ የጦር አዛዦች ምን አሉ። ለኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት ያስተላለፉት መልዕክት፣ እንዲሁም ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ምላሽ። #ሼር ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
Show all...
የሰላም ስምምነቱ በታቀደለት መንገድ እንዲፈጸም መንግሥት እየሠራ ነው- የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በደቡብ አፍሪካ የተፈረመው የሰላም ስምምነት በተታቀደለት መንገድ እንዲሄድ ለማድረግ የኢትዮጵያ መንግሥት እየሠራ ነው። በዚህም መሠረት በመከላከያ ሥር ወዳለው አብዛኛውየትግራይ አካባቢ ርዳታ እንዲደርስ እየተደረገ ነው። ወደተለቀቁት አካባቢዎች መሠረታዊ አገልግሎቶች ቀስ በቀስ እየተጀመሩ ነው። በሌሎች አካባቢዎች አገልግሎቶችን ለማስጀመር እንዲቻል በታጣቂዎች የወደሙመሠረተ ልማቶችን ለመጠገን ምቹ ሁኔታ እየተፈጠረ ነው። ከዚሁ ጎን ለጎን በሰላም ስምምነቱ መሠረት የሕወሐት ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበት ዝርዝር ዕቅድ ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አዛዥና የሕወሐት ታጣቂዎች አዛዥ በናይሮቢመክረዋል። በሰላም ስምምነቱ በተያዘው የጊዜ ገደብ ትጥቅ የሚፈታበትንና መከላከያ ወደ መቀሌ የሚገባበትን ዕቅድ ላይም ተስማምተዋል። ዕቅዱም በቀጣይ ተግባራዊ ይደረጋል። ለዕቅዱተግባራዊነት የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በስምምነቱ መሠረት የሚጠበቅባቸውን ሊወጡ እንደሚገባ መንግሥት ያሳስባል። Via FBC ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
Show all...
የኢትዮጵያ መንግሥት እና የሕወሃት ወታደራዊ አመራሮች በናይሮቢ ሲያካሂዱት የቆዩትን ውይይትን በስምምነት አጠናቀዋል። የውይይቱን መጠናቀቅ ተከትሎ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሄኑ ጁላ እና የሕወሃት ኃይሎች ዋና አዛዥ ጀኔራል ታደሠ ወረደ ሁለቱ ወገኖች የደረሱበትን የጋራ መግለጫ ስምምነት ዛሬ ማምሻውን ፈርመዋል። ሁለቱ ወገኖች የደረሱበትን ስምምነት በማስመልከትም አጭር የጋራ ፕሬስ መግለጫ በጽሀፍ ተነቧል። የጋራ መግለጫ ስምምነቱ አንኳር ጉዳዮች፣ ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ እና አጎራባች ክልሎች ያለ ገደብ እንዲገባና የረድዔት ሠራተኞች በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እና የሕወሃት ታጣቂዎች ትጥቅ በሚፈቱባት ሁኔታ ላይ በቀጣይ ለመነጋገር የሁለቱ ወገኖች ወታደራዊ አካላት የጋራ ኮሚቴ ለማቋቋም መስማማታቸው እንደሆኑ ተገልጧል። ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
Show all...
የኢፊዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅትን ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱ÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የተለያዩ ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡ ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
Show all...
ነገ በመዲናዋ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ!! የአዲስ አበባ ፖሊስ ነገ በአዲስ አበባ የሚካሄደው የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ አደረገ፡፡ በነገው ዕለት መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገ የሩጫ ውድድር በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ከዚህ ቀደም በርካታ ህዝብ በብዛት የተሳተፈባቸው ተመሳሳይ ሩጫዎች በሰላም መጠናቀቃቸው የሚታወስ ነው። በኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ አማካኝነት የተዘጋጀው የነገው የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በሰላም እንዲጠናቀቅ መላው የፀጥታ አካላት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል። የሩጫው ተሳታፊዎች ፀጥታው የጋራ ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበው ወደ መሮጫ ስፍራ ሲገቡ ለፍተሻ እንዲተባበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል። ውድድሩ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ፡- • ከቅዱስ ዑራኤል ቤተ-ክርስቲያን ወደ መስቀል አደባባይ • ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ • ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ • በወንጌላዊት ህንፃ ወደ ጎተራ • ከዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን ወደ ጎተራ • ከጎፋ ገብርኤል ወደ ጎፋ ማዞሪያ • ከሳር ቤት ወደ ጎፋ ማዞሪያ • ከአፍሪካ ህብረት ወደ ቡልጋሪያ • ከትንባሆ ሞኖፖል ወደ ገነት ሆቴል • ከጥይት ቤት ወደ ጠማማው ፎቅ • ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሃር • ከልደታ ቤተ ክርስቲያን ወደ ለገሃር • ከሰንጋ ተራ ወደ ለገሃር • ከብሔራዊ ቴአትር ወደ ለገሃር • ከሐራምቤ ሆቴል ወደ መስቀል • ከቤተመንግስት ወደ መስቀል • ከካዛኝቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11፡30 ጀምሮ ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ። ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
Show all...
" ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን " የሚኒስትሮች ምክር ቤት ፦ " በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ሲካሄዱ የቆዩት ግጭቶች #በሰላማዊ_መንገድ የመጨረሻ እልባት እንዲያገኙ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፣ በተደራጀ ኃይል ውስጥ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ኃይሎች ትጥቃቸውን ፈትተው ወደማህበረሰቡ በዘላቂነት እንዲቀላቀሉና ሰላማዊ ኑሮ መምራት እንዲችሉ ለማድረግ፣ በአገሪቱ የልማት፣ የሰላም እና የዲሞክራሲ ግንባታ ሂደት እንዲሳተፉ ለማስቻል ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን ማቋቋም አስፈላጊ በመሆኑ ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ለም/ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡ " ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
Show all...
አርሶ አደሩ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ የግብርና ሚኒስቴር አሳሰበ። የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ መለሰ መኮንን (ዶ/ር) በሀገሪቱ በቆላማ፣ ሞቃታማና መካከለኛ ቦታዎች ላይ ሰብል እየተሰበሰበ እንደሚገኝ ተናግረው በደጋማው አካባቢ ሰብል በመድረሰ ላይ እንዳለም አመላክተዋል። የብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስትቲዩት ትንበያ እንደሚያመለክተው በሚቀጥሉ ቀናት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ሊቀጥል እንደሚችል አስታውቋል። በደረሰ ምርት ላይ ዝናብ ጉዳት እንዳያደርስ አርሶ አደሩ፣ የግብርና ባለሙያው እና በየደረጃው የሚገኘው አመራር በልዩ ትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በተያዘው የመኸር ወቅት ስንዴ አሰባሰብ ላይም የህብረት ስራ ማህበራትን ጨምሮ ተማሪዎች፣ የግብርና ሙያተኞችና ልዩ ልዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳትፎ በማድረግ በዘመቻ የሰብልን ብክነት ቀድሞ መከላከል እንደሚገባ ጥሪ መቅረቡን ኢዜአ ዘግቧል።በ2014/2015 ዓ.ም የመኸር ምርት ዘመን ከተሸፈነ 13 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሄክታር መሬት 400 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ እየተሰራ እንደሚገኝም ተመላክቷል፡፡ ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
Show all...
ነገ በአዲስ አበባ የሚካሄደው የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች በነገው ዕለት መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገ የሩጫ ውድድር በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡ ከዚህ ቀደም በርካታ ህዝብ በብዛት የተሳተፈባቸው ተመሳሳይ ሩጫዎች በሰላም መጠናቀቃቸው የሚታወስ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ አማካኝነት የተዘጋጀው የነገው የጎዳና ላይ ሩጫም ውድድር በሰላም እንዲጠናቀቅ መላው የፀጥታ አካላት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡   የሩጫው ተሳታፊዎች ፀጥታው የጋራ ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበው ወደ መሮጫ ስፍራ ሲገቡ ለፍተሻ እንዲተባበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል፡፡ ውድድሩ ተጀምሮ እስኪሚጠናቀቅ ፡- • ከቅዱስ ዑራኤል ቤተ-ክርስቲያን  ወደ መስቀል አደባባይ • ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ • ከአጎና ሲኒማ  ወደ መስቀል አደባባይ • በወንጌላዊት ህንፃ ወደ ጎተራ • ከዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን ወደ ጎተራ • ከጎፋ ገብርኤል ወደ ጎፋ ማዞሪያ • ከሳር ቤት ወደ ጎፋ ማዞሪያ • ከአፍሪካ ህብረት ወደ ብልጋሪያ • ከትንባሆ ሞኖፖል ወደ ገነት ሆቴል • ከጥይት ቤት ወደ ጠማማው ፎቅ • ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሃር • ከልደታ ቤተ ክርስቲያን ወደ ለገሃር • ከሰንጋ ተራ ወደ ለገሃር • ከብሔራዊ ቴአትር ወደ ለገሃር • ከሐራምቤ ሆቴል  ወደ መስቀል • ከቤተመንግስት ወደ መስቀል • ከካዛኝቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11፡30 ጀምሮ ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡ በውድድር መስመር ግራና ቀኝ ለረጅም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ  አስታውቋል፡፡ ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
Show all...
"በወልቃይትና ራያ ጉዳይ ካለፈው የተለየ አቋም የለንም!" ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በወልቃይትና በራያ ጉዳይ የተደራደርንበት አግባብ የለም። ካለፈው የተለየ አቋም የለንም። ወደፊትም አይኖርም። የወልቃይትና ራያ ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው። ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
Show all...
#UPDATE ላለፉት ጥቂት ቀናት በናይሮቢ ሲካሄድ የነበረው ውይይትን ተከትሎ በነገው እለት 5 ሰአት ገደማ በዝርዝር ስምምነት ነጥቦቹ ላይ ፊርማ እንደሚያኖሩ የታወቀ ቢሆንም ከህወሓት መንደር ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ብዙዎች የተከድተናል ቅስቀሳው ከትላንት ጀምሮ እየተጎሰመ ይገኛል። ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
Show all...
ከወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ! “'የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ የስራ አመራሮች ጋር የነበረው የጋራ ውይይት ባለመግባባት ተበተነ' ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን!”- ኮሚቴው ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
Show all...
#UPDATE ላለፉት ጥቂት ቀናት በናይሮቢ ሲካሄድ የነበረው ውይይትን ተከትሎ በነገው እለት 5 ሰአት ገደማ በዝርዝር ስምምነት ነጥቦቹ ላይ ፊርማ እንደሚያኖሩ ከኬንያ ጋዜጠኞች ማምሻውን የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል ሲል ኤልያስ መሰረት አሳውቋል። 🤲ቸር ያሰማን 👐 ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
Show all...
ወደ ትግራይ ክልል የሚወስዱ ሁሉም ኮሪደሮች ለሰብዓዊ ደጋፍ አቅርቦት ክፍት መደረጋቸውን ተገለጸ! ወደ ትግራይ ክልል የሚወስዱ ሁሉም ኮሪደሮች ለሰብአዊ ደጋፍ አቅርቦት ክፍት መደረጋቸውን የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።የሰብአዊ ድጋፍ ተቋማት በአየርና በየብስ የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ እንደሚችሉ ገልጿል።የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር አምሳደር ሽፈራው ተክለማርያም ለተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢ ድርጅቶች የሰሜን ኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ሰብአዊ ድጋፍ ለሚያቀርቡ ተቋማት የየብስም ሆነ የአየር ትራንስፖርት ክፍት መደረጉን ገልጸዋል።በአፋር ክልል ከአብዓላ መቀሌ፣ በሁመራ በኩል ሽራሮ፣ ሽሬ አክሱም አድዋ፤ በጎንደር አዲ አርቃይ ማይጸምሪ ሽሬ እንዲሁም የወልዲያ አላማጣ መስመሮች ሁሉም ለሰብዓዊ እርዳታ ክፍት እንደሆኑ ተናግረዋል። በአፋር ክልል ከአብዓላ መቀሌ የሙከራ አገልግሎት የሰጠ ሲሆን በሁመራ በኩል ሽራሮ፣ ሽሬ አክሱም አድዋ በኩል ከገቡ 16 ከባድ መኪናዎች መካከል ሶስቱ የሕክምና ቁሳቁስ ይዘው መግባታቸውን አመልክተዋል።“ማንኛውም የሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢ ተቋም በአየርና በየብስ የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ ይችላል” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል። ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
Show all...
"ሎተሪ ደርሷችኋል፣ ሲስተም እያስተካከልን ነው፣ የሞባይሎትን አቅም ከ4G ወደ 5G እየቀየርን ነው" የሚሉ ማጭበርያዎች እንዳሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ! ስልክ እየደወሉ እና የተለያዩ የማጭበርበር ዘዴዎችን በመጠቀም ወንጀሎችን የሚፈፅሙ ግለሰቦች መኖራቸውን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ ፡፡ በከተማችን አ/አበባ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ስልኮች እየተደወለ እንኳን ደስ አላችሁ ሎተሪ ደርሷችኋል፣ ሲስተም እያስተካከልን ነው፣ የሞባይሎትን አቅም ከ4G ወደ 5G እየቀየርን ነው፣ ከሌሎች ባንኮች ጋር ኦንላይን ሲስተም እየጀመርን ነው በሚሉ እና በሌሎች ማደናገሪያዎች በመጠቀም የተለያዩ ግለሰቦች የማጭበርበር ወንጀል እየተፈፀመባቸው እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ ፖሊስ የምርመራ መዛግብቶችን ዋቢ አድርጎ እንደገለፀው አንዳንዶቹም የማጭበርበሪያ ስልቶች ግለሰቦች እንዲያምኑ በኤቲም ገንዘብ ያወጡበት ትክክለኛ ቀን ተነግሯቸው የወንጀሉ ሰለባ እየሆኑ የሚገኙ ሲሆን የግለሰቦች የባንክ ሚስጥር የሚወጣበትን ሁኔታ ለማረጋገጥ ምርመራው ተጠናክሮ ቀጥሏል። ወንጀሉ በልዩ ልዩ የአፈፃፀም ስልቶች እየተፈፀመ ከመሆኑም ባሻገር ስልክ በመንጠቅና ቴክኒካል የሆኑ ዘዴዎችን በመጠቀም የግለሰቦችን የባንክ አካውንት ወደ ቴሌ ብር በማስተላለፍ ወንጀሉ እየተፈፀመ ይገኛል፡፡ ፖሊስ አያይዞ እንደጠቀሰው ወንጀሉን ለመከላከል ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ በኢትዮ ቴሌኮም በኩል የተለያዩ የማስጠንቀቂያ መልዕክቶች ቢተላለፉም አሁንም ወንጀሉ እየተፈፀመ ሲሆን ግለሰቦች የማያውቋቸው የስልክ ጥሪዎች እና የጹሁፍ መልዕክቶች ሲደርሷቸው ተገቢውን ማጣራት ማድረግ እንደሚገባቸው እና ጥሪው እንደደረሳቸው ወደ ተግባር ከመግባታው በፊት አቅራቢያቸው ወደሚገኝ ባንክ በመሔድ እውነታውን ማረጋገጥ እንደሚገባ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል፡፡ ፖሊስ መሰል ወንጀሎችን ለመቆጣጠር ከሚሰራው ሥራ ባሻገር አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ መረጃውን ለፀጥታ አካላት በመስጠት ህብረተሰቡ ተባባሪ እንዲሆንም ጥሪውን አስተላልፏል። [አዲስ አበባ ፖሊስ] ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
Show all...
ሱዳን ወደ ሁለት ሀገር የመገንጠል ስጋት እንዳንዣበበባት የወታደራዊ ቡድን መሪ ተናገሩ ሱዳን ወደ ሁለት ሀገር የመገንጠል ስጋት እንዲኖርባት አደጋ የደቀነዉ ሀገሪቱን እየመራ ያለው ወታደራዊ መንግስት "ለሰላማዊ መፍትሄ ዝግጁ ባለመሆኑ " እና በስልጣን ላይ ለመቆየት ፍላጎት በማሳየቱ ነዉ ሲሉ የሱዳን ወታደራዊ ንቅናቄ መሪ ተናግረዋል::የሱዳን ህዝቦች ነፃ አውጪ ጦር መሪ አብዱላዚዝ አል ሂሉ በካርቱም ያለው መንግስት ካልተቀየረ ቡድናቸው ነፃነቱን እንደሚመርጥ ተናግሯል። የሱዳን ህዝቦች ነጻ አዉጪ በሀገሪቱ ደቡባዊ ክፍል ኑባ ተራሮችን እንዲሁም በደቡብ-ምስራቅ የብሉ ናይል ግዛትን ተቆጣጥሮ ይገኛል፡፡አል ሂሉ ቡድናቸው “አንድነትን ይመርጣል” ሆኖም ግን የካርቱም መንግስት የቀድሞዋን ሱዳን መርጦ ጭቆናን ማስቀጠል ከፈለገ “ነጻነትን እንመርጣለን” ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ኑባዎች ለበርካታ አሥርተ ዓመታት ተገልለው ቆይተዋል። ተገድለዋል፣ ተሰቃይተዋል፣ ከመሬታቸው እንዲፈናቀሉ መደረጋቸዉን ገልጸዋል፡፡የሱዳን ጦር የእርስ በርስ ጦርነትን ለመከላከልና የፖለቲካ ቡድኖች ሰላማዊ ዜጎችን በፀጥታ ሃይሎች ላይ እያነሳሱ ነዉ በሚል ከዓመት በፊት የመንግስት ግልበጣ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ የመፈንቅለ መንግስቱ መሪ ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ወደ ሲቪል አገዛዝ ለመሸጋገር ቁርጠኛ መሆናቸውን ከዚህ ቀደም ተናግረው ነበር። Via:- ዳጉ ጆርናል ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
Show all...
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ሳምንት የደንበኞቹን ቁጥር አንድ ሚልየን እንደሚገባ ገለፀ! ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በነሐሴ ወር ስራ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ከ900 ሺህ በላይ ደንበኞችን በኢትዮጵያ ማፍራት እንደቻለ አስታወቀ። የሳፋሪኮም ኩባንያ ዛሬ የግማሽ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት በናይሮቢ በቀረበበት መድረክ የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፒተር ንዴግዋ “በኬንያ እና በኢትዮጵያ እንደ የዋጋ ግሽበት፣ የምንዛሪ ዋጋ ማሽቆልቆል እና ፈጣን ያልሆነ የሀገር ውስጥ ምርት ዕድገት የመሳሰሉ ከማክሮ ኢኮኖሚ ጋር የተያያዙ ተግዳርቶች አጋጥመውናል” ብለዋል። የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚ አንዋር ሶሳ ከአዲስ ዘይቤ ለቀረበላቸው ጥያቄ በመድረኩ እንደተናገሩት ከነሐሴ 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ከ933 ሺህ ደንበኛ ማፍራት ተችሏል ብለዋል። “ቁጥሩ በየጊዜው የሚቀያየር ነው፤ እስካሁን ባለው ሁኔታ ከ900 ሺህ የተሻገርን ሲሆን በሚቀጥለው ሳምንት አንድ ሚልየን ደንበኞች እንደርሳለን” ሲሉ ዋና ስራ አስፈፃሚው አንዋር ሶሳ ተናግረዋል። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሀገሪቱ ያሉ ሁኔታዎችን ታሳቢ ያደረገ ስራ መስራቱን ይቀጥላል ያሉት አንዋር ሶሳ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ከጦርነቱ ነፃ የሆኑ አካባቢዎችን ለመድረስ እቅድ አለን ብለዋል። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም. በድሬደዋ ከተማ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ የሚታወስ ነው። [Addis Zeybe] ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
Show all...
Breaking : 70% የትግራይ ክልል በመከላክያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ሆኗል። በትግራይ ክልል አገልግሎቶች ዳግም እየጀመሩ ነው አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በትግራይ ክልል አገልግሎቶች ዳግም እየጀመሩ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ እና የሰላም አማራጭ ዐቢይ ኮሚቴ አባል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለጹ። በክልሉ 70 በመቶ በሚሆኑ አካባቢዎች ዕርዳታው ከመቼውም ጊዜ በላይ እየደረሰ መሆኑንም ጠቁመዋል። ዕርዳታውን በሌሎች ቀሪ አካባቢዎችም ለማዳረስ በ35 ተሽከርካሪዎች ምግብ እና በ3 ተሽከርካሪዎች መድኃኒት ተጭኖ ሽሬ ገብቷል ብለዋል። ወደ ክልሉ በረራ መፈቀዱን የገለጹት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ የሰብአዊ ዕርዳታን በተመለከተ ምንም ዓይነት መሰናክል አይፈጠርም ብለዋል። አንዳንድ አካላት የአፍሪካውያን ዕውቀት በፕሪቶሪያ ባመጣው ስኬት ደስተኛ እንዳልሆኑ ጠቁመው፣ ይህንን መልካም መንፈስ ለማወክ ሲጥሩ ይታያሉ ሲሉም ገልጸዋል። ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
Show all...