cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

SELAM

Worship Preach Poem & others "peace I LeaveWith You,My Peace I Give Unto You;Not AsTheWorldGives,Give I Unto You.Let Not Your Heart Be Troubled,Neither Let It Afraid" Jo 14/27 t.me/selamdiro

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
179Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የእግዚአብሔር መገለጥ የክርስትናችሁ ዋስትና ነው!!! እግዚአብሔር በመገለጥ ስታገኙት ህይወታችሁ በሀይልና በክብር ይሞላል።የተጠራ ሰው በእግዚአብሔር መንግስት ለመቀጠል የሚያስችለውን ጉልበት ለመታጠቅ የመለኮት መገለጥ ያስፈልገዋል። እግዚአብሔር የትናትና አምላክ አይደለም የዛሬ አምላክ ነው።ማለት የነ እትና አምላክ እያላችሁ የምትፀልዩበት አምላክ ሳይሆን የእኔ አምላክ የምትሉት አምላካችሁ ነው።እግዚአብሔር የነ እትና አምላክ ስትሉ የትናት ታደርጉታላችሁ የእኔ ስትሉ ደግሞ የዛሬ ታደርጉታላችሁ።እርሱ ትናት በአባቶቻችን የሰራ ዛሬ ደግሞ በእኛ የሚሰራ አምላክ ነውና።እግዚአብሔር ታሪክ ሆኖ አያውቅም በእኛም ዘመን ታሪክ ይሰራል እንጂ። 📜“ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው። — ዕብራውያን 13፥8 የሰው ልጅ በመጀመሪያ እግዚአብሔር የሚያውቀው በመፅሐፍ ሳይሆን በመገለጡ ነበር!!አዳም እግዚአብሔር ብሎ ጥቅስ አልነበረውም መገኘቱ ነበረው እንጂ።!!! 📜“እነርሱም ቀኑ በመሸ ጊዜ የእግዚአብሔርን የአምላክን ድምፅ ከገነት ውስጥ ሲመላለስ ሰሙ — ዘፍጥረት 3፥8A መሰዊያ የሚሰራው ለተገለጠ እግዚአብሔር እንጂ ገና ለሚገለጥ እግዚአብሔር አይደለም።መፅሐፍ ስለ አብርሃም ሲናገር እግዚአብሔር ለአብርሃም ተገለጠለት አብርሃምም ለተገለጠለት እግዚአብሔር መሰዊያ ሰራ ይላል።መናገር የምትችለው ስለተገለጠልህ እግዚአብሔር እንጂ ገና ስለሚገለጥልህ እግዚአብሔር አይደለም። 📜“እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፦ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ አለው። እርሱም ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ ስፍራ መሠውያን ሠራ።”ዘፍጥረት 12፥7 Emmanuel..."እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!!! ዘማሪ አዲስ በለጣ
Show all...
ከኖሩ አይቀርስ እንደ ሐዋርያው ዮሐንስ! ዮሐንስ (John/ Johanna/ Jehohanan) የሚለው ስም የይሆዋ ወይም የእግዚአብሔር ጸጋ ማለት ነው፡፡ የዘብዴዎስ ልጅ ነበር፡፡ እናቱ ሰሎሜ ስትሆን፣ ኢየሱስን በገንዘባቸው ካገለገሉት አንዷ ነበረች፡፡ የጌታ ኢየሱስ ተከታይ የሆነው በ30 ዓመቱ ነው፡፡ ለተከተለው አምላክ እጅግ የተለየ ፍቅር የነበረው ሲሆን፣ የቅርብ (inner circle) ሰውም ነበረ፡፡ በፍቅር ዙሪያ በመስበክ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው አገልጋዮችም አንዱ ነው፡፡ በመከራ ጊዜ ከተቸገረው ወገን አጠገብ መሆን ለታማኝ ወዳጅነት እጅግ ጥሩ ማረጋገጫ ነው፡፡ ወንድማችን ያንን በግሩም ሁኔታ አሳይቷል፡፡ እጅግ ደፋር የነበረ ደቀ መዝሙር ሲሆን፣ ጌታ ኢየሱስ በተሰቀለበት የመጨረሻ ሰዓት ከመስቀሉ ሥር የተገኘው እሱ ብቻ ነበረ፡፡ መንፈስ ቅዱስ በድንቅ የለወጠው ሥነ ጽሑፍ አዋቂም ነበረ፡፡ የጻፋቸው መልእክቶች ሲነበቡ አቤት መጣፈጣቸው! አለመሰልቸታቸውስ?! እንዳውም እያደር እየጨመረ ነው የሚሄደው ጥፍጥናቸው፡፡ ከአሣ አጥማጅነት ተነሥቶ እነዚያን ቢነበቡ እያደር የማይጠገቡ መልእክቶችን መጻፉ፣ የመንፈስ ቅዱስን የመለወጥ ጥበብና ኃይል ያሳየናል፡፡ “በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ” (ራእ.1፥10) የሚለው አገላለጹ፣ ግሩም የጸሎት ሕይወት እንደ ነበረው ያሳያል ብዬ አምናለሁ፡፡ በዚያም የሕይወት ጽናቱና ልዕልናው ራእይ ላይ ያለውን ከባድ የትውልዶች መልእክት ለማስተላለፍ ያሳጨው ይመስለኛል፡፡ በዚያ ከባድ የግዞት ሕይወቱ እጅግ ብርቱ ነበር፡፡ በዚያ በማይመች ሥፍራ ያንን ግሩምና ዛሬም ድረስ ለመተንተን እጅግ ከባድ የሆነ የራእይ መጽሐፍ የጻፈ ጀግና ሆኗል–የጨካኞች ዕቅድ የእግዚአብሔር ድንቅ ዓላማ ሲፈጽም ያየንበት፡፡ በሮማውያን ከፍተኛ ባለ ሥልጣናት ብዙ ከባድ መከራዎችን ተቀብሏል፣ በልቡ ውስጥ የነበረው የኢየሱስ ጥልቅ ፍቅር ጉልበት ሆኖት ነበርና፡፡ እጅግ ግሩም በሆነ የአተራረክ ስልቱ፣ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ አሳይቶናል፡፡ እኔ በግሌ ለማያምኑ ወይም በክርስትና ሕይወት ላይ ጥርጣሬና ብዥታ ላላቸው ሰው የምመክረው፣ ይህንን ወንጌል እንዲያነብቡት ነው፡፡ አንድ ሰው በትሕትናና ቅንነት በተሞላ ለውጥ ፈላጊ ልብ ሃያ አንዱን ምዕራፎች በዝግታ ቢያነብብ፣ ከዚያ በኋላ ሳያነብብ በፊት እንደ ነበረው እንደማይሆን አምናለሁ፡፡ ፈጣሪውን ያየዋላ! የእነ ጴጥሮስን፣ የያዕቆብንና የጳውሎስን መራራ የሞት ጽዋ ያየና የሰማ ቢሆንም፣ ምንም ሳይበገር እስከ መጨረሻው ጸንቷል፡፡ ለእኛም የጽናት ተምሳሌት ( አንዱ role model) ሆኖልናል፡፡ እግዚአብሔር ሆይ፣ ባለፈው ዘመን እንደ ነበሩ የእምነት አርበኞች ለጠራኸን ሕይወትና አገልግሎት አስጨክነን! በጊዜያዊና ምድራዊ ትርፍ ተልፈስፍሰን የከበረውን ተስፋችንን እንዳንጥል ማስተዋልን ስጠን! አሜን! Addis belete dibaba
Show all...
"ስትጸልዩ ኹል ጊዜ ትጉ" (ሉቃ. 21፥36) *** ፍሬዴሪክ ቢ. ሜየር፥ “የምሪት ምስጢር (The Secret of Guidance)” በምትባል ትንሽ መጽሐፉ “በሕይወት ውስጥ ታላቁ አሳዛኝ ተውኔት መልስ ያላገኘ ጸሎት ሳይኾን፥ ሳይጸለይ የቀረ ጸሎት ነው” ይላል። ጸሎትን ልክ እንደምንበላው እንጀራ ወይም እንደምንጠጣው ውሃ ወይም እንደምንተነፍሰው አየር ዘወትራዊ ተግባር ከማድረግ ይልቅ “በአደጋ ወይም በችግር ጊዜ ይጠቀሙበት” ተብሎ በሳሎናችን አንድ ጥግ እንደ ተሰቀለ የድንገተኛ አደጋ መርጃ ቍሳቍስ፥ መቍጠራችን ብዙ ሳይጐዳን የቀረ አይመስለኝም። . ብቅ ያልሁት፥ ስለ ጸሎት ለማስተንተን ፈለጌ አይደለም። ጸሎት ከትንታኔው ይልቅ ተግባሩ የበለጠ እንደሚሠራ ትገነዘባላችሁና። ነገር ግን፥ ጸሎትን የሚሰማና የሚመልስ አምላክ ያለን እኛ በብዙ ነገሮች መታወካችን ጥያቄ ይፈጥርብኛል፤ አንዳንዴ ይገርመኛል፤ በራሴ ድካምና ዝንጋኤ የማዝንበት ጊዜም አለ። ግን እኮ፥ ወደ እርሱ የምናደርገውን ልመና ሰምቶ እንደሚመልስ እግዚአብሔር በቃሉ ተስፋ ሰጥቶናል። . “ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እኾናለሁ፤ አድነዋለሁ አከብረውማለሁ” (መዝ. 91፥15) እስከ ማለት የደረሰ ጠንካራና ብሩህ ተስፋ አለን። ጌታ ኢየሱስም፥ “ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ኹሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል” (ማቴ. 7፥7-8) ብሏል። እነሆ፥ በከንቱ አንፈልግም፤ ላንቀበል አንለምንም፤ ላይከፈትልንም አናንኳኳም። . እንግዲያስ፥ ተወዳጆች ሆይ፥ ጸሎታችን እዚህ ግባ በማይባልና በተዘበራረቀ መንገድ ሊቀርብ ቢችልም፥ ቃሎቻችን ደካማ ቢኾኑም፥ ጸሎታችን ለውጥ ሊያመጣ የሚችለው የጸሎት ብርታቱ ያለው በሚጸልየው ሰው እጅ ሳይኾን ጸሎትን ሰምቶ በሚመልሰው በእግዚአብሔር እጅ ስለ ኾነ ነው። እኛ በጸሎት ስብራታችንን ስናቀርብ፥ እግዚአብሔር ይጠግነናል፤ ምሬቶቻችንን ስንዘረግፍ፥ እርሱ ሰላሙን ያፈስልናል፤ መዛላችንን በእርሱ ብርታት ይተካል። … . ተአምር ኾነም አልኾነ፥ ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት የማድረግ ተሞክሮ በመኾኑ ብቻ እንኳ ልናቋርጠው የማይገባን ነገር ነው። እግዚአብሔር በክርስቶስ ሥራ አባታችን እንዲኾነን ኹለተኛ ወልዶናል፤ ዳግመኛ የተወለዱ ኹሉ ከእርሱ ጋር ኅብረት ማድረግ ይችላሉ። ይህ ኅብረት የአባትና የልጅ ኅብረት ነው። በመኾኑም፥ “አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደ ገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁም” (ሮሜ. 8፥15)። . ጸሎት ጠናብኝ አይባልም። በጸሎት ያለፈ ጊዜ አልባከነም። እኛ በአምስት ሺህ አመታት ልናደርገው የማንችለውን እግዚአብሔር በአምስት ማይክሮ ሰከንዶች እንዲያደርግ የምንለምንበት ነው እንጂ። ጥያቄው አንዳንዴ ለጸሎት ያለን መነሣሣት ሲዳከም ምን እናድርግ? የሚል ነው። . በታሪክ ከታወቁ የጸሎት አርበኞች መካከል አንዱ የነበረው ጆርጅ ሙለር “ደስ ደስ የሚል ስሜት ባጣን ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብና መጸለይ እንድናቆም መፈተናችን የታወቀና የተለመደ የሰይጣን ደንቃራ ነው። በምናነብብ ጊዜ ደስ ደስ የሚል ስሜት ካልተሰማን፥ የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብ ዋጋ እንደሌለው እንድናስብ፥ የጸሎት መንፈስ ካልተሰማን ደግሞ መጸለይ ዋጋ እንደሌለው እንዲሰማን ያደርገናል። እውነቱ ግን፥ ቃሉ በደስታ እንዲያጥለቀልቀን ከፈለግን ማንበባችንን መቀጠል ነው። የጸሎት መንፈስ የምናገኝበትም መንገድ ጸሎትን ባለማቋረጥ መቀጠል ነው። ማንበብ ስናሳንስ ለማንበብ ያለን ፍላጎት እያነሰና እየኮሰመነ ይኼዳል። መጸለይን ስናሳንስም ለመጸለይ ያለን ፍላጎት እየደከመ ይኼዳል።” . ብዙ ጥያቄዎችና ውጥንቅጦች በሞሉበት ዓለም፥ አገር፥ ማኅበረ ሰብና ማኅበራነ ምእመናን ውስጥ እንኖራለን። እግዚአብሔር በከበቡን ማዕበሎቻችን ላይ ታላቅ ብርታቱን ማሳየት ይፈልጋል። ጸሎታችንንም ሰምቶ ይመልሳል። እንግዲያስ፥ በጸሎታችን እንትጋ። እርስ በርሳችንም፥ በጸሎት እንተሳሰብ። እግዚአብሔርም በመንፈሱ ኀይል ያበርታን። addis belete dibaba
Show all...
ሁልጊዜ በቃሉ ውስጥ ሐዋርያት 2 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁸ ደግሞም በዚያች ወራት በወንዶችና በሴቶች ባሪያዎቼ ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ ትንቢትም ይናገራሉ። ¹⁹ ድንቆችን በላይ በሰማይ፥ ምልክቶችንም በታች በምድር እሰጣለሁ፤ ደምም እሳትም የጢስ ጭጋግም ይሆናል፤ ²⁰ ታላቅ የሆነ የተሰማም የጌታ ቀን ሳይመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣሉ። ²¹ የጌታን ስም የሚጠራም ሁሉ ይድናል።
Show all...
ልጅ መሆን በክርስቶስ በማመናችን የእግዚአብሔር ልጆች ሆንን። ይህ በክርስቶስ ያግኘነው ደህንነት አንዱ ገጽታ ነው። አስቀድመን የስይጣን ባሪያዎች ነበረን አርሱ የስዎች ሁሉ ፈጣሪ ቢሆንም የሁሉም አባት አይደለም። እርሱ በኢየሱስ ለሚያምኑት ብቻ አባት ነው። የክርስቶስ ጽድቅ በእምነት ስንቀበል ብቻ የእርሱ ቤተሰብ አድርጎ ይቀበለናል። ማንኛውም በማደጎ ያለ ልጅ በአሳዳጊነት የወስደውን ሰው ሀብት መውረስ ይችላል በሥጋ ክእሳዳጊው የተወለደ ባይሆንም እንኳ በሕግ ልጅ ትደረጎ ስለሚቆጠር የልጅነት ሙሉ መብት ይቀበላል። ቀድሞ በፍጥረታችን ሃጢአትኞች የነበረን እኛም በክርስቶስ ኢየሱስ በመንፈስ የእግዚአብሔር ወንዶችና ሴቶች ልጆች ሆነናል። በስማይ ሙሉ ውርስ እንቀበላለን። ከመዳናችን አንድ ታላቅ በረከት የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችን ነው።ይህም የእግዚአብሔር ባሕርይ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ወደ እኛ ተዋሀደ ማለት ነው። ልጅ የሥጋ አባቱን እንደሚቀርብ እንዲሁ እኛም ክእግዚአብሔረ ጋር የቀረበ ግንኙነት ማድረግ እንችላለን እንዲሁም እንደ እግዚአብሔር ልጆች መኖር አለብን። የእግዚአብሔር ልጅ መሆን ታላቅ በረከትና ደስታ ነው። 🔥🔥@lewotatoch🔥🔥 🔥🔥@lewotatoch🔥🔥
Show all...
ሁልጊዜ በቃሉ ውስጥ ራእይ 5 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ² ብርቱም መልአክ፦ መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ማኅተሞቹንም ይፈታ ዘንድ የሚገባው ማን ነው? ብሎ በታላቅ ድምፅ ሲያውጅ አየሁ። ³ በሰማይም ቢሆን በምድርም ላይ ቢሆን ከምድርም በታች ቢሆን መጽሐፉን ሊዘረጋ ወይም ሊመለከተው ማንም አልተቻለውም። ⁴ መጽሐፉን ሊዘረጋ ወይም ሊመለከተው የሚገባው ማንም ስላልተገኘ እጅግ አለቀስሁ። ⁵ ከሽማግሌዎቹም አንዱ፦ አታልቅስ፤ እነሆ፥ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል አለኝ።
Show all...
መልካም ሰንበት በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ፤” — ኤፌሶን 6፥18 ግጥም ርዕስ: የእረፍት ቦታዬ ከመንፈሱ አለም የሌለበት ጫጫታ፣ የእረፍት ቦታዬ የነፍሴ ደስታ፣ አረንጓዴ ስፍራ ወይ መስክ አይደለም፣ በአበባ የደመቀ የእፅዋት አለም። የፀጥታዉ ድባብ ግርማ ሞገሱ፣ ንፁ አየር አግኝቶ በስርዓት መተንፈሱ፣ የተዋበ ስፍራ ሰዎች የሚሹት፣ ከሩቅ አይተው የሚጎመዡት፣ ያ አይደለም እረፍቴ! ያ አይደለም ሰላም ሀሴቴ፣ የልቤን ተናግሬ አድማጭ ባለበት፣ ደግሞ መልስ ጠብቄ ከቶ የማላጣበት፣ ምህረት ጠይቄ ነፃ የምወጣበት፣ ሸክሜን አምጥቼ የማራግፍበት፣ ጥያቄ ቢኖረኝ መሻት ወይ ምኞት፣ ለእርሱም ቅርቤ አምላክ ያለበት፣ ከመንፈሱ አለም ገብቼ በጥልቀት፣ በቅዱስ መንፈስ የምፅናናበት፣ በአምላክ ፊት በሞገስ የምቀርብበት፣ በልጅነት ስልጣን ጠላቴን ምረታበት፣ ፀሎት ነው ፀሎት ልብ የምታርፍበት!!!! ጌታ ዘመናቹን ይባርክ!! ሰላማዊት ዲሮ @selamdiro @selamdiro
Show all...
ሁልጊዜ በቃሉ ውስጥ ራእይ 1 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁰ በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፥ በኋላዬም የመለከትን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ሰማሁ፥ ¹¹ እንዲሁም፦ የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ኤፌሶንና ወደ ሰምርኔስ ወደ ጴርጋሞንም ወደ ትያጥሮንም ወደ ሰርዴስም ወደ ፊልድልፍያም ወደ ሎዶቅያም በእስያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ላክ አለኝ። ¹² የሚናገረኝንም ድምፅ ለማየት ዘወር አልሁ፤ ዘወርም ብዬ ሰባት የወርቅ መቅረዞች አየሁ፥ ¹³ በመቅረዞቹም መካከል የሰው ልጅ የሚመስለውን አየሁ፥ እርሱም እስከ እግሩ ድረስ ልብስ የለበሰው ደረቱንም በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ ነበር። ¹⁴ ራሱና የራሱ ጠጕርም እንደ ነጭ የበግ ጠጕር እንደ በረዶም ነጭ ነበሩ፥ ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ነበሩ፤ ¹⁵ እግሮቹም በእቶን የነጠረ የጋለ ናስ ይመስሉ ነበር፥ ድምፁም እንደ ብዙ ውኃዎች ድምፅ ነበረ። ¹⁶ በቀኝ እጁም ሰባት ከዋክብት ነበሩት፥ ከአፉም በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ወጣ፤ ፊቱም በኃይል እንደሚበራ እንደ ፀሐይ ነበረ። ¹⁷ ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ እንዲህም አለኝ፦ አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥ ¹⁸ ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።
Show all...
ሁልጊዜ በቃሉ ውስጥ ጌታ ኃጢአቱን የማይቆጥርበት ሰው ------ ነው።” ሀ, ፃዲቅ ለ, ብፁዕ ሐ, መልካም ሰው መ, ቅዱስ @selamdiro
Show all...
ሁል ጊዜ በቃሉ ውስጥ “አንተ ግን፥ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ከዚህ ሽሽ፤ ጽድቅንና እግዚአብሔርን መምሰል እምነትንም ፍቅርንም መጽናትንም የዋህነትንም ተከታተል።” — 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፥11
Show all...