cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ከ ብእር ጠብታ

እነሆ ለስነ ፅሁፍ አፍቃሪዎች የተከፈተ ምርጥ ቻናል; እዚህ ቻናል ውስጥ በእኛ እና በሌሎች ምርጥ ምርጥ ፀሐፍያን የተፃፉ ልዩ ልዩ ልብወለዶችን ፣ ግጥሞች፣የተለያዩ ሃሳቦችን እና አሪፍ የምንላቸውን የፅሁፍ አለማትንም እናጋራለን :: እነዚህ ሁላ በአንድ ላይ ማግኘት ይፈልጋሉ እንግዲያዉስ Join በማለት ለሌሎችም ያጋሩ:: በጋራ የጥበብ ባህርን በብዕር እንቅዘፍ ✊️✊️✊️

Show more
Advertising posts
239Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የጂኒየስነት ሚስጢር💡💡💡💡💡💡💡 ክፍል 4 💡 ዛሬ ምነግራችሁ Maths እና Physics እንዴት መነበብ እንዳለባቸው ነው፡፡ ተከተሉኝ ፦ 📚 በመጀመሪያ Maths ፣Physicsን ለማጥናት ራሳችንን በስነልቦና ማዘጋጀት አለብን ፣ማለትም ከባድ አለመሆናቸውን ራሳችንን ማሳመን አለብን ፡፤በመቀጠልም ትምህርቶቹን ስናጠና እነዚህን ማረግ አለብን ፦ ለPhysics ❓ 📚 concept መያዝ ያስፈልጋል ፡፡ እንዲሁም formula በመሸምደድ ፋንታ proof ማድረግ በጣም ጠቃሚ ናቸው ፡፡ እንዲሁም ዋና ዋና የሚታወቁ የ physics ህጎችን ለምሳሌ ፦ ፡-Newtons law of motion. ፦ Pascal principle ፦ Archemedian principle ወዘተ...ህጎችን መያዝ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ለMaths ❓ 📚 ስናጠና ደግሞ የtopicኡን ህግ እንዲሁም ጥያቄዎቹ የሚሠሩበትን መንገድ step by step በደንብ ለመረዳት መሞከር እንዲሁም ያልገባን ጥያቄ ካለ የተለያዩ አጋዥ መፅሀፍችን( ከላይብረሪ ብትጠቀሙ ብዬ እመክራለሁ ) እና ት/ቱን የሚያስተምረውን አስተማሪ መጠየቅ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ብዙዎች የሚሳሳቱት ነገር ❓ 📚 ደግሞ Maths ፣Physics ማጥናት ያለብን ፈተና ሲደርስ ብቻ አይደለም፡፡ሁልጊዜ ቢያንስ በዚያን ቀን የተማርነውን topic መከለስ አለብን እንዲሁም ቢያንስ በዚያን ቀን ከተማርነው topic 5 ጥያቄ ብንሠራ በጣም ይጠቅመናል ፤ ምክንያቱም እነዚህ ት/ቶች እንደሌሎች የሽምደዳ ት/ቶች ለፈተና concept እንዲሁም formula ሸምድደን በመግባት ብቻ የምንሰራቸው ከመሰለን በጣም ተሳስተናል፣ ይልቁንስ topicኡን በመረዳት እና የተለያዩ ጥያቄዎችን በመለማመድ የምንሠራቸው የት/ት አይነቶች ናቸው፡፡ አሁን ተግባባን አይደል ❓ 💬 ከእነዚህ ት/ቶች ደስ የሚለው ነገር ደግሞ topicኡን አንዴ በደንብ ከተረዳነው ከጭንቅላታችን አይጠፉም ስለዚህም ፈተና ሲደርስ በመጨናነቅ ፈንታ ራሳችንን በተለያዩ ጥያቄዎች challenge የማድረግ እድሉን እናገኛለን ማለት ነው፡፡ እንግዲህ ካለኝ ልምድ በመነሳት ይህንን ፃፍኩላችሁ ፡፡ በሉ ተነሱና ፍለጡት ❓ በተረፈ መልካም የፍሬሽነት ዘመን ይሁንላችሁ ፡፡ ስም :-ፀጋ ማቴዎስ ት/ቤት ፡- ሳውዝ ዌስት አካዳሚ የEntrance ውጤት:- 531 Join @Senior_exam_preparation
Show all...
Welcome To entrance exam preparation group (@Senior_exam_preparation ) On this group You Will Get : 👉Entrance exam related News 👉study tips 👉resources and materials including worksheets, hand outs and reference books 👉interviews with straight A students So join the group and increase your academic result ( @Senior_exam_preparation )
Show all...
የራሴንም የሌሎችንም ፅሁፋዊ ኪነ ጥበቦችን በማቅረብ አመታትን ቆይቻለሁ . ግን ከዚህ ቡሃላ ይሄንን channel manage ለማድረግ ጊዜ ስለማይበቃኝ ይሄንን channel ልሸጠው ወስኛለው . ማንኛውም ይሄን channel መግዛት ሚፈልግ ሰው @Lidsh19 በዚ account አናግሩኝ.
Show all...
ብዙዎቻችን የሆነ ነገር ልናደርግ እንል እና ወደ ሁላ የሚጎትተን, እንደ እውነት አምነን መቀበል ያቃተንማ ፍርሃት አለ . ምንድን ነው ምትፈሩት? አይጥ ,እንስሳትን , መብረቅን, መቃብር ቦታን , ውድቀትን , መክሰርን , ሕዝብ ፊት ቆሞ ማውራትን , ያለፈ ታሪካችሁን .... ምንድን ነው አስሮ የያዛችሁ ልክ ልትለወጡ ስትሉ አንተ እኮ አትችልም የሚላችሁ .የለም ብትሉኝ አላምናቹም ምክንያቱም አሁን ካላችሁበት እንዳትንቀሳቀሱ ያደረጋቹህ ፍርሃትማ አለ . ግን ዋናው ጥያቄዬ ፍርሃታቹን ለማሸነፍ ምን ያህል ዝግጁ ናችሁ ?አሁንም ደግሞ ይሰራችሁ ወይስ ትጋፈጡታላችሁ . እውነት ለመናገር እንደ'ኔ ፈሪ ሰው አልነበረም ምን ትፈርያለሽ እያላችሁ ነው መቼስ, public speech😂 ይገርማላ?ሰው ፊት ማውራት አሁን ምን ይከብዳል ትሉ ይሆናል ግን ለኔ ከባድ ነበር . Presentation ባለኝ ጊዜ ሁሉ even መምህር ክፍል ውስጥ ሲጠይቀኝ ማወራው ግራ ግብት ይለኛል እጆቼ በላብ ይዘፈቃሉ እንተባተባለው real pepresentation ያለኝ ጊዜማ panic attack ሁላ ያጋጥመኝ ነበር እንዴት ፍርሃትሽን አጠፋሽው ትሉ ይሆናል እውነት ለመናገር ፊት ለፊት ተጋፈጥኩት . እያንዳንዷ public speech ታለማምደኛለች ያልኩትን እድል ሁላ እጠቀም ጀመር ውስጤ አችይውም እያለኝ እንኩአን present ማድረግ ሚፈልግ ሲባል እጇን ምታወጣ ልጅ ሆንኩ . በአንዴ ሳይሆን ቀስ በ ቀስ ለመድኩት. ከ ጊዜ ቡሃላ እኔን የሚያስፈራውን ፍርሃቴን አስፈራው ጀመር ስሜ ሲጠራ እንኩአን በድንጋጤ ሮጦ የሚጠፋው ይመስለኛል ሁላ እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው ፍርሃታቹን ተጋፈጡት አለበለዚያ ዘላለም አስሮአቹ ይኖራል እናም በራሳችሁ መቼም ተስፋ አትቁረጡ . መልካም ምሽት ✍ሊዱ
Show all...
ይቅር አልልሽም """"""" """"''''''''''''''' ገፍተሽ ሄደሻል..........የፍቅርን ጉልበት ፣ ተረማምደሽዋል......የናፍቆትን ቁርበት ፣ ንቀሽ አልፈሽዋል .......የልመናዬን ቃል ፣ በይ........እስቲ ንገሪኝ ላኖርሽብኝ ሀዘን....ስንት እንባ ይበቃል ፣ ስንት ድንኳን ልጣል ስንት ቦይ ልገድብ ፣ ገለሽኛል ብዬ...........ተዝካሬን ልቀልብ ። ይቅር በለኝ ብለሽ.........እንዳትማፀኚ ፣ ይቅር አልልሽም..........ይህንን እመኚ ፣ ያንቺን በደል ጥፋት ስቆጥር አልገኝም ፣ ላንቺ የምሰጥሽ.........ይቅርታ የለኝም ። ተከፋሁኝ ብዬ ተበደልኩኝ ብዬ.....ቅንጣት ባንቺ አላዝን ፣ ደግሞም አውቃለሁኝ የፍቅር መስፈርቱ ፅድቅ እንደማይመዝን ፣ ልክ ነሽ እኮ.....አንቺም አንዳንዴም ቅመም ነው.....ለፍቅር ጥላቻ ፣ ሳይበዛ በስሱ............ፍቅርን ማጣፈጫ ። ግን የልብሽን በራፍ.............ጨክነሽ አትዝጊ ፣ ይቅር አይለኝም ወይ ? ብለሽ እንዳትሰጊ ፣ እንኳን ሰው እና ሰው  በመንገድ ይጋጫል........እግርም ከእግር ፣ ለሌለኝ ቅያሜ ላልቆጠርኩት በደል.......አልልሽም ይቅር ፣ ከጥፋት በላይ ነው ከስህተት በላይ ነው..ቂም አይዝም ፍቅር ። ግን......ይቅር አልልሽም ለምን አልተቀየምኩሽም #በረከት_ዘውዱ
Show all...
ሰው_መሆን !!! ረቂቅ ነው ቃሉ፣ ክቡድ እና ሙሉ፣ ገነትን ቀድሞ የረገጠ፣ መላዕክትን በፍርሃት ያንቀጠቀጠ፣ ሰውነት ክቡር ነው መለኮትን ያስቀመጠ። ሰው ማለት! ሰው ማለት ሰባተኛ፣ የጥበብ ልጅ ጥበበኛ፣ ክቡር ፍጡር እውነተኛ። ሰው ክቡድ ነው ታምረኛ። ሰው መሆን ሰውነት የታረዘን ማልበስ፣ ማዘን ማስተዛዘን ለራስ ለሰው ማልቀስ፣ የሰው እንባን ማበስ፣ ሰው መሆን ክቡር ነው! ምስለ መንፈስቅዱስ። ታዲያ.... ታዲያ የኛ ግብር ሰው ያስብላል፣? የሰውነት ትርጉም በኛ ተንፀባርቋል፣? እርኩሰት ወይንስ ቅድስና ክብር ወይንስ ውርደት፣ ማፍቀር ወይንስ መጥላት መግደል ወይንስ ማንሳት፣ ማልበስ ወይንስ መግፈፍ ማመፅ ወይንስ መርዳት፣ የትኛው ነው ሕይወታችን፣? የትኛው ነው ተግባራችን፣? ጉድ ነው ሰውነታችን ቆሽሿል ተበክሏል በድፍ፣ ሰው መሆን ተረስቷል ሰው አንሷል ከጉድፍ። ሰው መሆን ክቡር ነበር፣ ከራስ አልፎ መኖር፣ በሰውነት ሰውን ማክበር፣ ምስለ ማርያም ምስለ እግዚአብሔር። እዚያ ማዶ በምትታየው ዓለም፣ ከጥቂቶች በቀር ነብሴን ያለ የለም፣ ህዝቡ ያድራል ቅዠት ሲያልም፣ በስጋ ፍላጎት እንዲሁ ሲስለመለም። የተማረ ፤ የተመራመረ የሰውነት ክብርን ያወቀ፣ ደግሞም ከንቱ ነኝ ሚል እራሱን ያላመፃደቀ፣ ጥቂት ነው በዝች ዓለም ሰውነቱን የጠበቀ፣ ሰው ሆኖ የሚኖር ከፈጣሪው የታረቀ። ግድ የለህም የሰው ልጅ ሆይ፣ ሰውነትን መልበስ ያስከብርሀል በሰማይ፣ ደግሞም ከፍ ትላለህ ከፍጡራን በላይ፣ ሰውነት ወልድ ነው የአዳም ሲሳይ። ሰውነት ማለት የታረዘን ማልበስ የተራበን ማጠጣት፣ የታሰረን መጠየቅ የተጠማን ማጠጣት፣ እራስን ማሳነስ የወደቀን ማንሳት፣ ሰውነት ይሄ ነው ለሰው ክብር መስጠት። #ገጣሚ_ሄኖክ_ፀጋዬ #ብሶተኛው_ጢም_አልባው_ገጣሚ   
Show all...
ትጠብቀኛለህ? ከሚሰድቡኝ አስበለጥኸኝ ከሚሸነግሉኝ ሸሸግኸኝ ከቀኑብኝ አልቀኸኝ "እንዳልታበይ ትንሽ ትንሽ ጣልኸኝ።" ያንተን ጥበብ አላውቀውም። ግን ምርጥ ሐኪም ነህ። አንተን ያህል አምላክ አላውቅም። ጌታዬ የሚጠሉኝ በአቅም ይበልጡኝ ነበር እኮ ተሸነፍኩ ያልኩትን ትግል ሳሸንፍ አሳየኸኝ። እንደለመድኩት ልኮንንህ ቃል አበጅቼ ተነሳሁብህ አሁንም ተሳሳልኛለህ በሰውነቴ አመጽኩብህ እንደአባት ገላዬን ልታጥበኝ ትጠብቀኛለህ ስንቴ በስምህ እንደዋሸሁ አንተ ረስተሀል እኔ አውቃለሁ ጸሎቴ መሐል ቅጥ ያለው ቃል ሰምተህ አታውቅም ግን ታደርግልኛለህ የማይታመን አምኜ ፈራሁ አንተን ማመን እጅህ ላይ ራሴን መልቀቅ አሰጋኝ ዓለምና ውሸቷ ውሸቷና ትዕቢቷ በለጡብኝ። ደጅ ደጁን ታያለህ ይመጣል ብለህ ትጠብቀኛለህ? ኤልያስ ሽታኹን💜🔥
Show all...
በሕይወቴ እጅግ የማከብራቸው 2 ቀናት አሉ:: የመጀመሪያው የተወለድኩበት ቀን ሲሆን ሌላው ደግሞ ለምን እንደተወለድኩ የገባኝ ቀን ነው:: ዛሬ ወደዚች ዓለም ከመጣው 16 አመታትን ቆይቻለው :: እና ምን ተማርሽ ብትሉኝ ዘርዝሬ አልጨርስም; ካገኘውት ወይም ካጣውት, ከጠላኝ ወይም ከወደደኝ, ካስለቀሰኝ ወይም ካሳቀኝ,ከ ሕያዋን ወይም ከሙታን ውስጥ የሚመደብ በሕይወቴ ውስጥ ያለፈ እያንዳንዱ ሰው ትልቅ ትምሕርት አስተምሮኛል::ግን ከሁሉም በላይ የሌለንን ነገር እያሰቡ መብሰልሰል ምን ያህል እንደሚጎዳ እና ባለን ነገር ተደስተን ተመስገን ማለት እና ለፈጣሪ ምስጋና ማቅረብ ያለኝን ይበልጥ እንደሚያበዛልን እና እንደሚባርክልን በዚች ጥቂት አመታት ውስጥ ተረድቻለው:: ቀናቹን በምስጋና ጀምሩ እና ፍቅርን እስትንፋሳቹ አድርጉ እላለው የናንተው ሊዲያ ነኝ ሰናይ ቅዳሜ ይሁንላችሁ😉
Show all...
🔮🔦የ እናቴ ልጅ🔦🔮 💰🏮ክፍል ስድስት🏮💰 📣📣📣📣📣📣📣📣 ቤት ከገባው በጣም ቆየው አቤል ግን አልመጣም እናቴ በተደጋጋሚ ወጣ እያለች ትመለሳለች እንደጨነቃት ያስታውቃል ልጇ እንዲ ሲያመሽ የመጀመሪያው ነው ፡ እኔ ብሆን ባድርም ግድ የላት የኔ ነገር ድሮ ነው የበቃት እኔም ብሆን አዘኔታዋን አልፈልገውም ፡ምክንያቱም ለዚሁሉ መገፋት የኔም ድርሻ አለበት ፡ ፍቅሯን ፈልጌ አንዳንዴ ብወቅሳትም ፡ ስህተቱ የኔም መሆኑን ካመንኩ ቆይቻለው እና ዛሬ ላይ ዝቅ ብዬ እየሰራው እራሴን ለማስተካከል መወሰኔ ከዛ አንፃር ነው ,,,,,,,,, እናቴ በጣም ሲብስባት ወደ እኔ ዞረች "ስማ ከለሊቱ ስድስት ሰአት ሆኗል ወንድምህ አልገባም !አንተ ግን እዚ ተቀምጠሃል ትንሽ እንኳ አይጨንቅህም?!" ብላ አፈጠጠችብኝ "ምን ማድረግ እችላለው ከመጠበቅ ውጪ ፡እኔና እሱ እንደው ከተራራቅን ቆይተናል ፡ምን እንደሚያደርግ ምን እንደሚያስብ ከነማን ጋር ጓደኛ እንደሆነ አላውቅም ፡ ስለዚ አዲስ ያመጣው ባህሪም ካለ እንግዲ ከኔ ይበልጥ የሚቀርበው አንቺን ነው "ብያት ፊቴን ወደቲቪው መለስኩ "ምን ማለት ነው ?!"ብላ ቱግ አለች "እንዴ ካንቺ ጋር ቀን ላይ የተነጋገራችሁት ነገር ካለ አስታውሺ ፡ ወይም ጓደኛ ካለው ከነሱ ጋር የሚያከብረው ነገር ካለው ፡ አይታወቅም ትልቅ ልጅ ነው አንዳንዴ የሚያምረው ነገር ሊኖርም ይችላል"ብዬ ዝም ።እናቴ ልትመታኝ የፈለገች መሰለች ተጠግታኝ በቁጣ ስታየኝ ቆይታ "እሱ እንዳንተ አይደለም ከአጠገቤ ተለይቶ አያውቅም ደጁን አያውቀውም ከመሸ ልጄን አውቀዋለው ይሄኔ አንድ ቦታ ተጨንቆ ነው የሚሆነው ወይኔ ልጄን ተነስ አሁን አፍህን መክፈትህን ትተህ ፍለጋ እንውጣ ፡ "ብላ ጎተተችኝ ፡ወይ እናቴ ምንአለ ከዚሁሉ ፍቅር ትንሽ ቀንሳ በሰጠችኝ ብዬ ተመኘው ፡ ወደ በሩ ስትጣደፍ ስስ ነገር መልበሷን ልብ አልኩ ለማንኛውም ብዬ ወደክፍሌ ገብቼ ወፈር ያለውን ጃኬቴን ያዝኩላት እና ቀድማኝ የጊቢውን በር ከፍታ እየወጣች "ፍጠን" አለችኝ የቤቱን በር እየዘጋው ፡ መጣው ከማለቴ እናቴ ስትጮኽ ሰማዋት ፡በፈጣሪ ሰውነቴ ለሁለት የተተረከከ ነበር የመሰለኝ ፡ እናንተ ድንጋጤ ለካ ያስሮጣል ከመቼው ፡እናቴ አጠገብ እንደደረስኩ እኔነኝ የማውቀው ፡እናቴ ደግማ ግን አልጮኽችም ፡አካባቢውን በጥንቃቄ እየቃኘች ከቆየች በዋላ በትልቅዬ ዘንቢል የተቀመጠ ነገር አነሳችና ወደግቢ ገብታ በሩን ዘጋች እኔ እንኳ ከጊቢ ውጪ መሆኔን የዘነጋች ነው የምትመስለው ፡ "እናቴ ኧረ በሩን ክፈቺልኝ"አልኳት ፡ "ናግባ ይሄ ምን ጉድ ነው!"ብላ በሩን ከፍታ አስገባችኝ ወደ ዘንቢሉ እየተጠጋው "ምንድነው"አልኳት "ዕፃን ልጅ ነው አይታይኽም "አለችኝ "አአ አዎ አአ የውት"አልኩኝ በድንጋጤ ቃላቴን እየጎተትኩ ፡ ጉድ ፈላ አቤልን ዕፃን ልጅ ከታቀፈች ሴት ጋር አይቼው ነበር ይህን ለእናተሰ ብነግራት አታምነኝም ፡በቃ በታማኙ ልጇ የሚመጣባት ሰው አትፈልግም ፡ እናቴ ለአቤል ያላት ፍቅር ጥልቅ ነው ፡እንዲነው እንዲያነው ብሎ ለእናቴ መንገር ከበደኝ.. "ና ወደቤት ይዘነው እንግባ ማነው አምጥቶ የጣለብኝ ሆሆ ብለው ብለው የትም ሲልከሰከሱ ወልደው መጣያ ያድርጉኝ እኔ ከሰው አልቀርብ አልደርስባቸው ምን ፍለጋ ነው ሀብታም ናት ብለው ነው ፡እስኪ ከዚ ሁሉ ጊቢ የኔ በምን ታያቸው ፡ ልጄን ልፈልግ ወይስ የነሱን ዕፃን ላስተናግድ ምን አይነት ቀን ነው ዛሬ"እያለች እያጉረመረመች ከዘንቢል ውስጥ ድንገት ንቅት ብላ አይኗን የምታቁለጨልጭ ዕፃን አውጥታ ወደላይ በመያዝ "ውይ ጭካኔ ሴት ናት "ብላ ወደኔ ዞረች ፡እኔ አይምሮዬ ሁሉ አቤል ጋር ነው በቃ አቤል እሱ ቀርቶ ልጁን ልኮልናል ፡ የት ተደብቆ ይሆን ይህን ድራማ የፈጠረው ጉድ ነው አልኩ ፡ እናቴ ዕፃኗን ሶፋው ላይ አጋድማ ዘንቢል ውስጥ ጡጦ ይኖር እንደው ብላ ስትፈላልግ በዛውም አንድ ደብዳቤ አገኘች ደብዳቤውን ይዛ ወደኔ ስትዞር ፡የጊቢ በር ተንኳኳ ሁለታችንም ለአፍታ በድንጋጤ ተያየን ፡ከዛ እኔ እሮጥ ብዬ በር ከፈትኩ አቤል ነበር ምንም ነገር አልሆነም ለመጀመሪያ ጊዜ አከበረኝ ይቅርታ የጓደኛዬ ልደት ነበር አለ ዝም አልኩ ።እናቴ አቤል መምጣቱን ስታይ እፎይ አለች ፡እና ወደ ዕፃኗ እያሳየች "ጉድ ሆንን እኮ አቡ ተመልከት የጣሉብንን "ስትለው እንደ አዲስ ተገረመ እኔ የፊቱ ገፅታ አስገረመኝ ምንም አልመሰለውም ከጉዳዩ ለመሸሽ እራሱን አሳምኖ እንደመጣ ገባኝ ፡እናቴ የያዘችውን ደብዳቤ ለማንበብ ተዘጋጀች ,,,,,,,,,, ደራሲ unknown ይቀጥላል......    
Show all...