cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

TIKVAH-MAGAZINE

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። #ኢትዮጵያ ያግኙን +251913134524

Show more
Advertising posts
196 290Subscribers
+4924 hours
+7237 days
+2 42730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በደቡብ ኢትዮጵያ ኮሬ ዞን እየተባባሰ በመጣ ጠለፋ ነዋሪዎች ሴት ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ ተቸግረዋል ተባለ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ውስጥ «እየተባባሰ መጥቷል» ባሉት ጠለፋ የተነሳ ሴት ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ መቸገራቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ። በድርጊቱ ፈጻሚዎች ላይ አስተማሪ የሆነ ቅጣት እንደማይሰጥ ያመለከቱት ወገኖች በአሁኑ ጊዜ ሴት ልጆች ወጥተው ለመግባት ስጋት እንደሆነባቸው ዶይቼ ቬለ ዘግቧል። ስማቸው ያልተገለጸ አንድ አባት ከትምህርት ቤት የምትመለስ ልጃቸው ከሁለት ሳምት በፊት ከትምህርት ቤት እየተመለሰች ሳለ በስድስት ወንዶች ከመንገድ መወሰዷን ተናግረው ጉዳዩን በሕግ ለመፍታት ያደረጉት ጥረትም አለመሳካቱንም አመልክተዋል። በተጠቀሰው ዞን በያዝነው ግማሽ ዓመት ብቻ ተጠልፈዋል የተባሉ የ24 ልጃገረዶች ሥም ዝርዝር ይፋ መደረጉን ተከትሎ ወላጆችና የህዝብ ተመራጮች በዞኑ የሕግ አካላት ላይ ጫና እያደረጉ ስለመሆኑም ተገልጿል።
Show all...
😢 30😡 18 3
በሶማሊላንድ ወደ የመን ለመሻገር ሲሞክሩ የነበሩ 170 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መያዛቸው ተነገረ በራስ ገዟ ሶማሊላንድ ወደ የመን ለመሸጋገር ሲሞክሩ የነበሩ 170 ኢትዮጵያዊያን ህገወጥ ስደተኞች በሶማሊላንድ የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የራስ ገዟ ብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል። ስደተኞቹ መረጋጋት ወደ ሌለባት ሀገር የመን ለመጓዝ በ Snaag eion የባህር ዳርቻ በሚገኝ ትልቅ ጀልባ ላይ ተሳፍረው ሳሉ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ከነዚህ ስደተኞች መሃከል ሴቶችም ይገኙበታል ተብሏል። @TikvahethMagazine
Show all...
😢 15 1
በወር 15,000 ብር 💸💵💰💰 ማግኘት ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ 🚴‍♀️ ብስክሌት 🏍 ሞተር 🛵 E-bike ካልዎት ምን ይጠብቃሉ ከ ቢዩ ዴሊቨሪይ ጋር መስራት ይችላሉ። 💰ቢዩ ዴሊቨሪይ የምግብ አድራሽ ድርጅት ሲሆን ብስክሌት ፥ ሞተረ እና E-bike ካለው ግለሰብ ጋር አብሮ መስራት ይፈልጋል። የስራ አድራሻ ፥ አዲስ አበባ ለመመዝገብ:- ከታች ባለው ( Telegram Bot ) በመጠቀም የቀረባልችሁን ጥያቄ በመሙላት ✴️https://t.me/DriversRegistration_bot ወይም ☎️ 9533 ላይ በመደወል መመዝገብ ይችላሉ።
Show all...
6
ታላቅ ቅናሽ 📣📣📣📣📣 💵 ድርጅታችን ድሪም ቢዉልደርስ በካሬ 90,000 ሲሸጥ የነበረውን ውደ 79,900 ብር ቅናሽ  አድርጓል። 🕧በ10% ቅድመ ክፍያ፣ በ9 ዙር፣ በ2 አመት ከ6 ወር ከፍለዉ የሚጨርሱት። 📍 በ CMC የተሟላ የመኖርያ መንደር ከ ለሚ ኩራ ፓርክ ፊትለፊት ⛰️በ ተንጣለለ 23,000 ካሬ ላይ ያረፉ አፓርትመንቶች፣ ከተሟላ መገልገያዎች ጋር 🛏️ባለ 1 መኝታ  79.92ካሬ  91.56ካሬ  🛏️ባለ 2 መኝታ 125.4ካሬ   127.44ካሬ  🛏️ባለ 3 መኝታ  169.92ካሬ ☎️ ለበለጠ መረጃ ይደዉሉልን 0974388888
Show all...
የ17 አመቷን የግል ተበዳይ የግብረ-ስጋ ግንኙነት በመፈጸም አንገቷን አንቆ የገደለው ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ ከእኔ ጋር በፍቅር ጓደኝነት ለመቀጠል ፈቃደኛ አልሆነችም በሚል የ17 አመቷን የግል ተበዳይ አስገድዶ የግብረ-ስጋ ግንኙነት በመፈጸም ሕይወቷ እንዲያልፍ ያደረገ ግለሰብ በጽኑ እስራት ተቀጣ። አብዱ ኪያር ዩሱፍ የተባለው ተከሳሽ በጳጉሜን 01 ቀን 2015 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 6፡30 ሰዓት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ሰፈራ ቀርሳ ቢላ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የግት ተነዳይን አንገቷን አንቆ በመያዝ በአካባቢው ወደሚገኝ ካባ በሚወስዳት ጊዜ ላለመሄድ ስትታገለው ነበር። ግለሰቡ የግል ተበዳይ ጩኸት ስታሰማ በድጋሚ በልብስ ማሰሪያው ጨርቅ አንገቷን አጥብቆ በመያዝና እራስዋን እንዳትከላከል በማድረግ የግብረ-ስጋ ግንኙነት የፈጸመባት እና አንገቷን በእጅ እና በልብስ የወገብ ማሰሪያ ጨርቅ በማነቅ ሕይወቷ እንዲያልፍ አድርጓል። በዚህም ግለሱቡ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ተጣርቶበት በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 11ኛ ወንጀል ችሎት ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቶ በክርክሩ ሂደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ የመከላከያ ማስረጃ እንደሌለው በመግለጹ ፍርድ ቤቱ ለሰራው ወንጀል በ25 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡
Show all...
😡 203😢 56👏 25 8🤔 4😨 2
በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ በደረሰ የመኪና አደጋ የ6 ወጣቶች ህይወት አለፈ በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ በደረሰ የመኪና አደጋ በ10 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ሲደርስ የ6 ወጣቶች ህይወት ማለፉን የወረዳው ፖሊስ ፅ/ቤት አስታውቋል። አደጋው የደረሰው በእዣ ወረዳ ወርት ቀበሌ እንጨት ጭኖ ወደ ከተማ በመጓዝ ላይ የነበረ ሲኖ የጭነት ተሽከርካሪ በደረሰበት የመገልበጥ አደጋ ነው። ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸውም እንደሚገኝ ተገልጿል። @TikvahethMagazine
Show all...
😢 49 7
በ10 ከተሞች በሊዝ ጨረታ መሬት ለመውሰድ ካሸነፉት መካከል 71 በመቶ የሚሆኑት ስራ አለመጀመራቸውን ጥናት አመለከተ በኢትዮጵያ 10 ከተሞች በሊዝ ጨረታ መሬት ለመውሰድ አሸናፊ ከሆኑት 636 ተጫራቾች መካከል 71 በመቶ የሚሆኑት ስራ አለጀመራቸውን ጥናት አመለከተ። በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ድሬዳዋ፣ አሶሳ፣ ጋምቤላ፣ ባህርዳር፣ ሐረር፣ ሀዋሳ፣ ጂግጅጋ እና ሰመራ ከተሞች በሊዝ ጨረታ መሬት በወሰዱ ግለሰቦችና በመሬት ተቋማት ላይ ጥናቱ መካሄዱ ተነግሯል። በ2014 ዓ.ም ጥናቱ በተካሄደበት ወቅት መሬት ለመውሰድ ተጫርተው በሊዝ አሸናፊ የሆኑ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ደረጃ የያዙ 636 ተጫራጮች ሲካተቱ የግንባታ ግብዓት እጥረት፣ የፋይናንስ አቅርቦት ችግር፣ የመሰረተ ልማት አለመሟላት ምክንያት ወደ ስራ አለመግባታችውን መሬት የወሰዱ ግለሰቦችና ተቋማት አስረድተዋል። በሊዝ መሬት ወስደው ወደ ልማት ባልገቡ አካላት ላይ የሚመለከተው ተቋም በሚያከናውነው የክትትልና ቁጥጥር መላላት በ95 በመቶ በሚጠጉት ላይ እርምጃ #አለመወሰዱንም ጥናቱ አሳይቷል ሲል ኢዜእ ዘግቧል። @TikvahethMagazine
Show all...
😡 22🤔 9 7😢 4👏 2🕊 2😨 2
በወር 15,000 ብር 💸💵💰💰 ማግኘት ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ 🚴‍♀️ ብስክሌት 🏍 ሞተር 🛵 E-bike ካልዎት ምን ይጠብቃሉ ከ ቢዩ ዴሊቨሪይ ጋር መስራት ይችላሉ። 💰ቢዩ ዴሊቨሪይ የምግብ አድራሽ ድርጅት ሲሆን ብስክሌት ፥ ሞተረ እና E-bike ካለው ግለሰብ ጋር አብሮ መስራት ይፈልጋል። የስራ አድራሻ ፥ አዲስ አበባ ለመመዝገብ:- ከታች ባለው ( Telegram Bot ) በመጠቀም የቀረባልችሁን ጥያቄ በመሙላት ✴️https://t.me/DriversRegistration_bot ወይም ☎️ 9533 ላይ በመደወል መመዝገብ ይችላሉ።
Show all...
6😡 4👏 3😢 2
ዩናይትድ ኪንግደም የህጻናት ደፋሪዎችን የወላጅነት መብት የሚነጥቅ ህግ ልታወጣ ነው ዩናይትድ ኪንግደም በከባድ ወሲባዊ ጥቃቶች የተከሰሱ ህጻናት ደፋሪዎች በልጆቻቸው ላይ ያላቸውን መብት የሚነጥቅ ህግ ልታወጣ መሆኑ ተሰምቷል። አዲስ ለሆነው ለዚህ ህግ መነሻ የሆነው አንዲት እናት ህጻናትን ደፋሪ ነው የተባለው የቀድሞ ባለቤቷ ከልጃቸው ጋር እንዳይገናኝ ለማድረግ 30 ሺህ ፓውንድ ለህጋዊ ክፍያ ማውጣታቸውን ተከትሎ መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል። በዚህም በወሲባዊ ጥቃቶች ጥፋተኛ የሆኑ በህጻናት ላይ ወሲባዊ ዝንባሌ ያላቸው ግለሰቦች (ፒዶፋይልስ) የወላጅነት መብታቸውን ወዲያውኑ የሚገፈፍ ይሆናል ተብሏል። የፍ/ቤቶች፣ የማረሚያ ቤቶች፣ የአመክሮና የህገመንግሥታዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ኃላፊነት ያለው ሎርድ ቻንስለር በህጉ ላይ መስማማታቸውም ነው የተገለፀው። @TikvahethMagazine
Show all...
101👏 80🤔 6😨 6
የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል እድሳት 75 በመቶ መድረሱ ተገለፀ የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል እድሳት በ172 ሚሊየን ብር እየተከናወነ ሲሆን የጥገና ሥራው 75 በመቶ መድረሱ ተገለፀ። እድሳቱ በውሉ መሰረት መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም መጠናቀቅ ቢጋባውም በገቢ ማነስ እና ህንፃውን ለማጠናቀቅ የሚረዱ ግብአቶች ከውጭ ለማስገባት የውጭ ምንዛሬ እጥረት ችግር መሆኑ ተገልጿል። የካቴድራሉ እድሳት ለማጠናቀቅ 85 ሚሊየን ብር መሰብሰብ እንደሚጠይቅ የተገለፀ ሲሆን የካቴድራሉን እድሳት ከፍጻሜ ለማድረስ  አስተዋጽኦ እንዲደረግ ጥሪ ቀርቧል። @TikvahethMagazine
Show all...
👏 65😡 12 8🕊 5🤔 4😨 2