cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

•ተዋህዶ ሀይማኖቴ•

ኑ በእግዚያብሔር ደስ ይበለን ለታላቁ ክብር ለዚህ ላበቃን ከሞት ወደ ህይወት ላሸጋገረን

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
292Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#መልዕክት_ለወላጆች እናንት አባቶችና እናቶች! የምነግራችሁን አድምጡ! ሠዓሊያን ሥዕላቸውን በጥንቃቄ እንደሚሥሉ፣ ሐውልትን የሚቀርጹ ብልሐተኞችም ሐውልቱን ታላቅ በኾነ ማስተዋል እንደሚቀርጹ፥ እኛም እነዚህን ዕፁብ ድንቅ የኾኑ የእኛ ሐውልቶችን በጥንቃቄ መቅረጽ ይኖርብናል፡፡ ሠዓሊያን ሸራቸውን ወጥረው ሥዕል ሲሥሉ በአንድ ቀን አይጨርሱትም፡፡ በየዕለቱ እየመጡ የጎደለውን እየጨመሩ፣ የበዛውንም እየቀነሱ ይፈጽሙታል እንጂ፡፡ ቅርጻ ቅርጽን የሚሠሩ ጠቢባንም ከእብነ በረድ ይህን ሲያከናውኑ የሚከተሉት መንገድ ተመሳሳይ ነው፡፡ ወጣ ወጣ ያለውን ይቀንሱታል፤ የጎደለውንም ጨምረው ይሞሉታል፡፡ እናንተም እንዲህ ልታደርጉ ይገባችኋል፡፡ ልክ እንደ ሠዓሊያኑና እንደ ቅርጻ ቅርጽ ሠሪዎቹ ጠቢባን፥ እነዚህን የእግዚአብሔር ሕያዋን ሐውልቶች ለመቅረጽ አስፈላጊውን ጊዜ ልትሰጡት ይገባችኋል፡፡ ከእነዚህ ሐውልቶች አላስፈላጊውን ስታስወግዱ የጎደለውንም ስታሟሉም ዕለት ዕለት ተመልከቱአቸው፡፡ አሁንም ምን እንደ ጎደለና ምን መጨመር እንዳለባችሁ፣ ምን እንደ በዛና ምን መቀነስ እንዳለባችሁ ታውቁ ዘንድ ዕለት ዕለት ተመልከቱአቸው፡፡ ከኹሉም አስቀድማችሁም ጸያፍ ንግግርን ለማስወገድ ትጉ፡፡ ከምንም በላይ የሕፃናትን ነፍስ የሚጎዳው ይህን መውደድ ነውና፡፡ ስለዚህ አንተ ሰው! ልጅህ ጸያፍ ንግግርን ከመልመዱ በፊት ራሱን የሚገዛ፣ ንቁ፣ ጸሎት መጸለይ የሚችልና ትንሽ ትንሽ የሚተኛ፣ በእያንዳንዷ ቃሉና ድርጊቱም የሃይማኖት ማኅተም ያለበት እንዲኾን አድርገህ አስተምረው፡፡ "ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው" መጽሐፍ በገብረ እግዚአብሔር ኪደ ገፅ 87-88 @beteafework @beteafework @beteafework
Show all...
የልምድ ኃጢአት የጸጋ እንቅፋት! በቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም ሼር በማድረግ ለወዳጆ አዳርሱ ተወዳጆች ሆይ እኔን ጨምሮ አብዛኞቻችን በመንፈሳዊ ሕይወታችን የልምድ ኃጢአት አለብን፡፡ ለምደነው ኃጢአት አልመስል ብሎ የተዳበልነው፡፡ የልምድ ኃጢአት በመንፈሳዊ ሕይወታችን የነበሩን ጸሎት፣ስግደት፣ጾም፣ትምህርት ወዘተ እየቀነሰ ሲመጣ የልምድ ኃጢአት ይጀምረናል፡፡ የልምድ ኃጢአት ትልቁ ችግሩ ይህ ነው ብሎ በግልጽ መዘርዘር ይከብዳል፡፡ ምክንያቱም እንደ ጠባያችን እንደ ፍላጎታችን እንደ ልምዳችን የልምድ ኃጢአታችን ይለያያልና፡፡ ጫትን ለመጀመርያ ጊዜ ሲቅሙት ሊመር እና ሊያንገፈግፍ ይችላል፡፡ ግን እያዘወተሩት ሲመጡ ግን ሱስ ብቻ ሳይሆን ልክፍት ይሆናል፡፡ ቢራን ለመጀመርያ ጊዜ ሲጠጡት ምሬቱ ፊት ያኮሰትራል ምላስን ያመራል፡፡ ግን ሲለምዱት ለምሳስ ይጥማል ክፉ ሱስ ይሆናል፡፡ የልምድ ኃጢአትም የጀመርነው ቀን ኃጢአት ሆኖ ይታሰበናል ስንለምደው ጭራሽ ጽድቅ መስሎን ተዋህዶን ይኖራል፡፡ ወዳጆቼ ምስጥ ታውቃላችሁ? ምስጥ የጉንዳን ዝርያ ሆኖ ጉንዳንን ያህላል፡፡ ምስጦች በብዛታቸው ትልቁን ድንጋይ መሰል ጉይሳ ይሠራሉ፡፡ ኩይሳውንም ውስጥ ውስጡን ቦርቡረው ባዶ ያደርጉታል፡፡ ምስጦች በዚህ አያበቁም ትልቁን ተክል ሥሩን በልተው በቁሙ ያደርቁታል ይጥሉታልም፡፡ ስለዚህ የልምድ ኃጢአት በጊዜ ሂደት መንፈሳዊ ሕይወታችንን በመቦርቦር ባዶ ያደርገናል፡፡ የወደቅን ባይመስለንም በቁማችን ይጥለናል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹እንደ ቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ›› ያለው በልምድ ኃጢአት ለምንወድቀው ማስጠንቀቂያ ነው፡፡ ከመንፈሳዊ ሕይወት አደገኛው በመንፈሳዊ የሕይወት መሠረት ላይ የቆምን መስሎን በቁም መውደቅ ነው፡፡ /1ኛ ቆሮ 10÷12/ ወዳጆቼ ከኃጢአት ሁሉ ክፉ ኃጢአት የልምድ ኃጢአት ነው፡፡ የልምድ ኃጢአት በጊዜ ሄደት የምንለምደው ነው፡፡ የልምድ ኃጢአት ኃጢአት የማይመስለን እግዚአብሔር ዝም ስለሚለን ነው፡፡ የልምድ ኃጢአት የሚጠናወተን በድፍረት ኃጢአት ነው፡፡ መዝሙረኛው ዳዊት ‹‹የድፍረት ኃጢአት እንዳይገዛኝ ባሪያህን ጠብቅ፣ የዚያን ጊዜ ፍጹም እሆናለሁ፣ከታላቁም ኃጢአት እነጻለሁ›› ያለውን ልብ ካልን ብዙ አንድምታ አለው፡፡ /መዝ 19÷13/ የድፍረት ኃጢአት ሲገዛን ነው የልምድ ኃጢአት ባሪያ የምንሆነው፡፡ የድፍረት እና የልምድ ኃጢአት በመንፈሳዊ ሕይወታችን ካለ ወደ ፍጹምነት ጎዳና መሄድ አንችልም፡፡ ከድፍረት እና ከልምድ ኃጢአት እራሳችንን ካላራቅን ከታላቅ ኃጢአት መንጻት አንችልም፡፡ ለምሳሌ ግል ወሲብን መተግበር፣ የወሲብ ፊልምን ማየት እርግፍ አድርገን ትተን ግን ባገኘነው አጋጣሚ ያየነው በማሰብ ሰውነታችንን በፍትወት ማሞቅ እና አፍረታችንን መነካካት የልምድ ኃጢአት ሆኖ ይቀራል፡፡ ትልቁን ተላቀን ትንሹ ልምድ ይሆንብናል፡፡ የልምድ ኃጢአት በመንፈሳዊ ሕይወት ለምንኖረው አንዱና ትልቁ የጸጋ እንቅፋት ነው፡፡ ለምሳሌ ንስሐ ገብቶ የሰውን ሥጋ በሐሜት ዘወትር በልቶ ለሚኖር ሐሜት ኃጢአት አይመስለውም፡፡ ሐሜት የልምድ ኃጢአት ሆኖ ከነፍስ ከሥጋችን ሲዋሃድ ወዳጃችንን ስናማ ‹‹ይቅር ይበለኝና›› በማለት ነው፡፡ ቆራቢዎች ሆነን የልምድ ኃጢአት በሕወታችን ሲጠናወተን ቅዱስ ቁርባንን እንደ ሒሳብ ማወራራጃ እያደረግን እራሳችንን ከማረም በቆራቢነታችን እየተጽናናን ‹‹ እኔ ቆራቢ ነኝ›› እንላለን፡፡ ብዙዎቻችን ከንስሐ ባሻገር ላለው ለቅዱስ ቁርባን ሕይወት ያልታደልነው እግዚአብሔር ሳይፈቅድልን ቀርቶ ሳይሆን የልምድን ኃጢአት እንደ ዲሪቶ ለብሰነው ነው፡፡ ለመንፈሳዊ የጽድቅ ሕይወት በልምድ ኃጢአት የራሳችን እንቅፋት የሆንን ብዙ ነን፡፡ ለዓመታት መንፈሳዊ ሕይወትን ኖረን በጸጋ ያላደግነው፣ ለውጥ ያላመጣነው አንዱ የልምድ ኃጢአት ለጸጋ ሕይወት ትልቅ እንቅፋት ስለሚሆንብን ነው፡፡ ተወዳጆች ሆይ ጣናን ለውሃ ድርቀት የዳረገው፣የውሃውን ወዝ የሚያነጥፈው በሚያሳዝን ሁኔታ ለመቆጣጠር እስኪያቅተን የወረረው በሚሊዮን የሚቆጠረው እንቦጭ ከአንድ ጀምሮ ነው፡፡ ጣናን እያየነው በዓይናችን ስር የወረረው እንቦጭ ትላንት ተባብረን ብናርመው ዛሬ እዚህ አይደርስም ነበር፡፡ የልምድ ኃጢአትም እንቦጭ ነው፡፡ ዝም ባልነው እና ትኩረት በነፈግነው ጊዜ፣ ቆይ ዛሬ ነገ እያልነው ችላ ስንለው መንፈሳዊ ሕይወታችንን በመውረር ጸጋችንን አርቆ፣ እኛንም ደፍቆ በኃጢአት ይሸፍነናል፡፡ በጊዜ ያልታረመ አረም ተመልሶ እንደሚያቆጠቁጥ ሁሉ በጊዜ ያልታረመ ያልተተወ የልምድ ኃጢአት ተመልሶ በማገርሸት ለትልቅ ውድቀት ይዳርገናልና ከልምድ የኃጢአት ጎዳና እንራቅ፡፡ ምክንያቱም የልምድ ኃጢአት የትኛውንም ጸጋ ለማግኘት ትልቅ እንቅፋት ነውና፡፡ ‹‹እያንዳንዱ ግን በእርሱ ላይ እንዴት እንዲያንጽ ይጠንቀቅ›› /1ኛ ቆሮ 3÷10/ ግንቦት 29-9-12 ዓ.ም አዲስ አበባ
Show all...
አስደንጋጭ ዜና እኔ ተቀብዬ ነው አንብቡትና ተረዱ በሃገር ውስጥና ከሃገር ውጪ ላሉት አስተላልፉና ህይወት ይታደጉ የብዙዎች አላማ የህዝብ ቁጥር ለመቀነስ ነው መረጃ አይናቅም ማስረጃ እስከሚገኝ ነገሮችን እናስተውል ለራሳችን ስንል ጥንቃቄ እናርግ። ቫይረሱ አዲስ አበባ ላይ ብቻ እንዲህ በፍጥነት መሰራጨቱ የሆነ የተደበቀ ሚስጥር እንዳለው ያመላክታል። ይህ ፅሑፍ ሳነብ ያገኘሁት ነው። ከውጪ የገቡ የአፍ መሸፈኛ ማስክ ባትጠቀሙ እመክራለሁ ሚስጥሩ እስኪታወቅ ድረስ። ሎካል በሆነ ማቴርያል እራሳችሁ አሰፍታችሁ ተጠቀሙ። ማሰፋት ባትችሉ ወይም ለአፍ መሸፈኛ የሚሆን ጨርቅ ባታገኙ እንኳን በሀገራችን ውስጥ ተሰፍተው የሚሸጡትን ገዝታችሁ በፈላ ውሃ አጥባችሁ ተጠቀሙ። ይሄ የታናሽነት ምክሬ ነው። ፧ ፧ ፧ 🙆 🇪🇹የኮሮና ቫይረስ ሴራ በኢትዮጵያ🇪🇹 👉 ጃክማን ማመን ቀብሮ ነው! #ሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ #ሰዓት ከፍተኛ የተባለ የኮሮና ቁሳቁስ ድጋፍ እያገኝች ያለችው ከቻይናዊው ቢሊየነር ጃክ ማ #ነው። ጃክ ማ ላለፉት ወራት በኢትዮጵያ በኩል የርዳታ ቁሳቁሱን ለአፍሪካም በማዳረስ ላይ #ይገኛል። ጃክ ማ የኢሉሚናቲ አባል ከሆኑ #ነጋዴና ፖለቲከኞች ተርታ የሚመደብ ሲሆን በ2020 የፎርብስ መፅየት ላይ 40 ቢሊዮን $ ባለቤት መሆኑ ሰፍሩአል። ዋና #የቢዝነሱ መሰረቱ Alibaba የተባለው የኢንተርኔት መገበያያ(e-commerce) ነው። #ከወራት በፊት ከጃክማ በድጎማ እየመጡ ያሉ ማስኮች ከታች በምስሉ ላይ እንደሚታየው የ666 አርማ ያለባቸው እንደነበሩ #በየsocial mediaው ተሰራጭቶ ነበረ። ኢሉሚናቲዎች ሰይጣናዊ አጀንዳቸውን #በሚአስፈፅሙበት ነገሮች ላይ ይህንኑ አርማ በተደጋጋሚ ሲአሰፍሩ ይታያል። ታዲያ ከጃክማ #የሚለገሰው ቁሳቁስ ምን አይነት ተልኮ ቢአነግብ ይሆን ይህንኑ አርማ የተነቀሰው? #በቅርቡ የታንዛኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር በጃክ ማ የኮሮና መከላከያ የዕርዳታ ቁሳቁስ ላይ #ባደረጉት ምርመራ አስደንጋጭ ውጤት ማግኝታቸውን #አሳውቀዋል👇👇👇 #ከሁለት ሳምንታት በፊት ከቻይና ወደ ታንዛኒያ ለኮሮና ቫይረስ #መመርመሪያ የሚጠቅሙ የህክምና መሳሪያዎች ገብተው ነበር።በዚህ ጊዜ ፕሬዚዳንቱ #የገቡትን መሳሪያዎች "መጀመሪያ ከሰው ውጭ በሆነ #ፍጡር መሞከር አለበት" በማለት በእንስሳትና ዕፅዋት ላይ ሞክረው ነበር።የህክምና #መሳሪያዎቹ የተሞከሩት በበግ በፍየል እና ፓፓያ ላይ ሲሆን በሙከራው መሰረትም "በበግና #በፍየል ላይ የኮሮና ቫይረስ ታይቶባቸዋል" ተብሏል። #በመጨረሻም ፕሬዝዳንቱ "የሆነ ነገር እየተፈጠረ ነው፤ከዚህ በፊት እንዳልኩት የሚሰጡንን ሁሉ ለበጎ #ነው ብለን መቀበል የለብንም"ብለዋል። ያው ኢሉሚናቲዎች የሰው ልጅ #አሁን ካለበት 7ቢሊዮን ወደ 500 ሚሊዮን እንዲቀንሱ ሰይጣን አዙአቸዋል።( በድንጋይ ላይ 10ቱ #የሰይጣን ትዛዛት ተቀርፅው በአሜሪካ ጆርጂያ ቆሞ ይገኛል)። #ኢሉሚናቲዎችም ይህንን ትዕዛዝ ለመፈፅም የተለያዩ ስልቶች ነድፈው በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው። #ከነዚህ ስልቶች አንዱ ቫይረስ ነው። አሁን ላይ ኮሮናን በመጠቀም በርካታ ሰዎችን #እየጨረሱ ሲሆን በቀጣይ ዋና ታርጌታቸውም አፍሪካ ናት። እናም ጃክማ የተባለው የሰይጣን ተላላኪ #ቢሊየነር ወደ አፍሪካ እየላከ ያለው የህክምና ቁሳቁስ ለበጎ ነው ብቻ ብሎ መቀበል የዋህነት ነው #አስተውላቹ ከሆነ በሀገራችን መንግስት ማስክ የማረግ አስገዳጅ ህግ ካወጣ ጀምሮ #የኮሮና ቫይረስ በፍጥነት እየጨመረ ነው። አብዛኞቹ እየተያዙ ያሉት ደሞ ከውጭ #ከመጣ ሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው ናቸው። ታዲያ ከየት #እያመጡት ነው? የታንዛኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቀድመው #መልሱን ያወቁት ይመስላል። 👉 ከቻይና በዕርዳታ ስም #እየመጡ ያሉ የኮሮና ቁሳቁሶችን ባንጠቀም መልካም ነው። በሀገራችን ለሚሰሩ የአፍ #መሸፈኛዎች ቅድሚያ እንስጥ። #ይሄ ፅሁፍ ቢያንስ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያየው ይገባል ህዝቤ #ባለማወቅ ወደ ወጥመዳቸው #እየሰመጠ ነው! ያነበባችሁት እባካችሁ እያንዳንዳቹ ቢያንስ #ለ10 ሰው በማለክ የድርሻዎችን ይወጡ:: ....Josh studio B/H
Show all...
ሠላምለኪ ሠላምለኪ እንዘ ንሰግድንብለኪ ማርያም እምነ ናስተበቁዐኪ እም አርዌ ነአዊ ተማህፀነብኪ(፪x) በእንተ ሀና እምኪ ወኢያቄም አቡኪ ማህበረነዮም (፫x) ድንግል ባርኪ(፪x) @yetewahedowetatoch
Show all...
ሉ› እንዳለው የእግዚአብሔርን እናት ያዩ ዓይኖች ምንኛ ክቡራን ናቸው! እንደ አባ ይስሐቅ ‹አርእየኒ እምከ› ‹እናትህን አሳየኝ› ሳይሉ ፤ እንደ ዮሐንስና እንድርያስ ‹ማደሪያህ ወዴት ነው?› ብለው ሳይጠይቁ እመቤታችንን ያዩ ዓይኖች ምንኛ ዕድለኞች ናቸው፡፡ ሰዎች ጠፈርን አዩ ተብሎ ዝናቸው ይነገራል፡፡ ጠፈሩንም ምድሩንም በመሃል እጁ የያዘን ጌታ በእቅፍዋ የያዘችውን እመቤት ከማየት በላይ ምን ክብር አለ፡፡ ጌታ የተወለደበትን ሥፍራ ማየት ድንቅ ነው ፤ የወለደችውን ማየት ምንኛ ታላቅ ይሆን? የእናንተን አላውቅም ፤ እኔ ግን እንደ ቅዱስ ዳዊት የአምላክን ማደሪያ አይ ዘንድ እመኛለሁ፡፡ ‹መቅደሱንም እመለከት ዘንድ› (መዝ.27፡4) በሰው እጅ ከተሠራው መቅደስ ይልቅ ልዑል ራሱ የሠራትን ሕያዊት መቅደስ ድንግል ማርያምን ማየት ይበልጣል፡፡ ሰማይንና ምድርን ሙሉ ከማየት እርስዋን ማየት ይበልጣል ፤ ሰማይ ዙፋኑ ነው ፣ ምድርም የእግሩ መረገጫ ነው ፤ ድንግል ማርያም ግን እናቱ ናት፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ እንዳለው ሰማይ አላጠባውም አላቀፈውም አላሳደገውም እርስዋ ግን ይህንን ሁሉ አድርጋለች፡፡ አባ ጊዮርጊስ እንዲህ ይላል ‹‹የሽቱ ዕቃ ሽቱው ካለቀም በኋላ መዓዛው ከዕቃው አይለይም፡፡ እመቤታችን ጌታን ከወለደችም በኋላ የመለኮቱ መዓዛ አልተለያትም›› የጌታችንን የክብሩን መጠን የተረዳ ሰው ማደሪያው የሆነች እናቱን እመቤታችንን ይወድዳል፡፡ እንኳንስ የወለደችውን እናቱን ቀርቶ የለበሰውን ልብስ ሳይቀር አክብሮ ነክቶ ይፈወሳል ፣ ያደረገውን ጫማ እንኳን ልፈታ አይገባኝም ይላል፡፡ ይህን የእመቤታችንን ፍቅር ስንረዳ በሰማያት የጌታ ማደሪያ ወላዲተ አምላክ ወዳለችበት ፣ በደስታ ወደ ተሰበሰቡት አእላፍ መላእክት ማኅበር ገብተን ለማየት እንበቃለን። ከሁሉም በላይ ከተአምረ ኢየሱስ በፊት "ለላህይከ ንትሜነይ ከመ ንርአዮ" (ውበትህን ልናይ እንወዳለን) እያልን የምንለምነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለማየትም እንደርሳለን። መጽሐፉ "በጥቂቱ የታመነ በብዙ ይሾማል" ይላል። በታናሽዋ ብርሃን በድንግል ማርያም ያልታመነ ታላቁን ብርሃን ክርስቶስን እንዴት ሊያይ ይችላል? "ጥቂት ዘመን በብርሃኑ ደስ ባለን" በመጥምቁ ዮሐንስ ብርሃንነት ካልታመንን ወደ "ብርሃናት አባት" እንዴት እንደርሳለን? (ዮሐ 5:35 ፣ ያዕ 1:17) ዳዊትስ "በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን" ብሎ የለ? (መዝ 36:9) ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ Deacon Henok Haile @yetewahedowetatoch
Show all...
Go to Home ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ +++ ሙሴ ሆይ ተሸፈንልን! +++ ነቢዩ ሙሴ በብሉይ ኪዳን ለአርባ ቀንና ሌሊት ከጾሙ ሰዎች አንዱ ነው፡፡ ‹አርባ ቀን ሙሉ እህል በአፉ ሳይገባ እንዴት አልራበውም? እንዴትስ አስቻለው› የሚል ሰው ካለ ሙሴ ምን ሲያደርግ እንደሰነበተ ያላወቀ ሰው ነው፡፡ እነዚያን አርባ ቀናት ያሳለፈው በታላቁ የሲና ተራራ ላይ ነበር፡፡ በዚህ ቅዱስ ተራራ ራስ ላይ እንዲቆም የተነገረው ይህ ነቢይ በተራራው ጫፍ ላይ እንደደረሰ ድንገት ተራራው በደመና ተሸፈነ፡፡ ልዑል እግዚአብሔርም በደመናው ውስጥ ወረደ ፤ በዚያም ከእርሱ ጋር ቆመ፡፡ ‹‹እግዚአብሔር፥ እግዚአብሔር መሐሪ፥ ሞገስ ያለው፥ ታጋሽም፥ ባለ ብዙ ቸርነትና እውነት!›› የሚል ታላቅ ግርማ ያለው ድምጽም በተራራው ላይ ተሰማ፡፡ ሙሴ በፍርሃት እየተንቀጠቀጠ በእግዚአብሔር ፊት ወድቆ ሰገደ፡፡ በአምላካዊ ብርሃን ውስጥ ተከብቦ ፣ በእሳት መጋረጃዎች ውስጥ እያለፈ ፣ የሠራዊት ጌታ የልዑል እግዚአብሔርን ድምጽ እየሰማ ለአርባ መዓልትና ሌሊቶች ከፈጣሪው ጋር ሲነጋገር ቆየ፡፡ ልብ በሉ! በእንዲህ ዓይነት መንፈሳዊ ዓለም ውስጥ ተውጦ የከረመ ሰው መቼ ፋታ አግኝቶ ሊርበውና ሊጠማው ይችላል? በመጠየቃችንም ራሳችንን ሳንታዘበው አንቀርም! ከአርባ ቀናት በኋላ ሙሴ ከተራራው ሲወርድ በግራና በቀኝ ሁለቱን ጽላት ይዞ ነበር፡፡ ወደ ሕዝቡ ሲመጣ ግን ሕዝቡ ወደ ሙሴ እንዳይቀርቡ ያስፈራቸው አንድ ነገር ተፈጠረ፡፡ ከተራራው በወረደ ጊዜ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለ ተነጋገረ ፊቱ ያበራ ነበር፡፡ በቅዱሱ ተራራ በደመናት መካከል ቆሞ ከፈጣሪው ጋር ቃል በቃል የተነጋገረው ይህ ታላቅ ሰው አርባ ቀንና ሌሊት ሳይመገብ ቢቆይም በረሃብ ከመጠውለግ ይልቅ ከአምላካዊ ጸጋ የተነሣ የፊቱ ብርሃን አንጸባረቀ፡፡ ይህንን ተአምር ያዩት እስራኤልም በፍርሃት ተንቀጠቀጡ፡፡ ሙሴ ግን ‹ፊቱ እንዳንጸባረቀ አላወቀም ነበር።› የእግዚአብሔር ሰው ክብሩን ሌሎች ያዩለታል እንጂ ለራሱ አይታየውምና የፊቱ ክብር ለሙሴ አልታወቀውም፡፡ ይህ የሙሴ የፊቱ ማንጸባረቅ በብዙ ቅዱሳን ታሪክ ላይ የምናነበውና እግዚአብሔር ለሚወዳቸው የሚሠጠው አንዱ ክብር ነው፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሰማዕትነት ከመቀበሉ አስቀድሞ በሸንጎ ውስጥ እያለ ‹ፊቱ እንደ መልአክ ፊት ሆኖ› ሰዎች ተመልክተው የነበረው ሙሴ ላይ ያበራው የእግዚአብሔር ክብር በእርሱ ላይ ስላረፈ ነበር፡፡ (ሐዋ. ፮÷፲፮) በብዙ ቅዱሳን ገድላትም ላይ ፊታቸው ሲያበራ ሰዎች ያዩአቸው ቅዱሳን ታሪክ እናገኛለን፡፡ እንዲያውም አንድ ትሑት አባት የፊታቸው ብርሃን ለሌሎች ታይቶ ለከንቱ ውዳሴ ፈተና እንዳያጋልጣቸው ብለው ሰው እንዳያገኛቸው በጨለማ ይወጡ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ክብር አለመፈለጋቸውን አይቶ በጨለማ ፊታቸውን አብርቶ ሰው ሁሉ የነጋ መስሎት ከቤቱ እንዲወጣና ክብራቸውን እንዲያውቅ አድርጎባቸዋል፡፡ ይህ ክብር ለሁሉም ጻድቃን በሰማይ ይሠጣል፡፡ ‹‹በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ›› (ማቴ. 13፡42) ይህ ብርሃን እግዚአብሔር ለመንግሥቱ ቢያበቃን ለእኛም የተዘጋጀ ክብር ነው፡፡ ‹‹እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን።›› (2ቆሮ. 3፡18) ሊቀ ነቢያት ሙሴ ፊቱ ሲያበራ ታዲያ ለማየት እስኪሳናቸው ድረስ ስላበራባቸው አሮንና የእስራኤል ልጆች ሙሴን ‹ተሸፈንልን› (ተገልበብ ለነ) ሊሉት ተገደዱ፡፡ ለጊዜው ታይቶ የተሻረውን የሙሴን የፊቱን ክብር (ብርሃን) ማየት ስላልቻሉ በጽላቱ ላይ የተጻፉትን ዐሠርቱን ትዕዛዛት ለማንበብ ሲቆም ሙሴ ሕዝቡን እንዳይቸገሩ ብሎ ፊቱን በመጋረጃ ይሸፍን ነበር፡፡ ወደ ምስክሩ ድንኳን ሲገባ መሸፈኛውን ይገልጥና ወደ እነርሱ ሲመለስ ግን ይሸፍነው ነበር፡፡ (ሊቁ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ "ሙሴ ፊቱ ሲያበራ በልብሱ ሸፍኖት ነበር ፣ የሙሴ አምላክ ክርስቶስ ግን በታቦር ተራራ ፊቱ ሲያበራ በልብሱ እንዳይሸፍነው ልብሱም ያበራ ነበር" ብለው ተቀኝተዋል።) ቅዱስ ጳውሎስ ሙሴ ትእዛዛቱን ሲያነብ የተሸፈነበትን ያንን መጋረጃ የሙሴን ፊት ብቻ ሳይሆን ብሉይ ኪዳንም ሳይቀር ለእስራኤል የተሸፈነባቸው ለመሆናቸው ማሳያ አድርጎ አቅርቦታል፡፡ ‹‹ብሉይ ኪዳን ሲነበብ ያ መጋረጃ ሳይወሰድ እስከ ዛሬ ድረስ ይኖራልና፤ በክርስቶስ ብቻ የተሻረ ነውና። ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ የሙሴ መጻሕፍት በተነበቡ ጊዜ ሁሉ ያ መጋረጃ በልባቸው ይኖራል፤ ወደ ጌታ ግን ዘወር ባለ ጊዜ ሁሉ መጋረጃው ይወሰዳል።›› በማለት ኃጢአትን ቆጥራ ታስፈርድ በነበረችው በኩነኔ አገልግሎት (በኦሪት ፈንታ) የተተካችው አዲሲቱ የጽድቅ አገልግሎት (ወንጌል) ያልተከደነች እንደሆነችና የብሉይ ኪዳንን ምሥጢራት ሁሉ የምንረዳው ያለማወቅ መጋረጃን ወዳነሣልን ወደ ክርስቶስ ዘወር ብለን ስንመለከት መሆኑን አስረድቶናል፡፡ (2ቆሮ.3፡7-16) የሙሴ ፊቱ ያበራው ለምን ነበር? እስቲ ወደ ሙሴ እንመለስና እንጠይቅ! እስራኤል ለምን መሪያቸውን ትኩር ብለው መመልከት ተሳናቸው? ካህኑ አሮን እንዴት ወንድሙን መመልከት አስቸገረው? የሕዝቡ አለቆች እንደወትሮው ከሙሴ ላይ ማተኮር ለምን ተቸገሩ? ያለ ወትሮው የሙሴ ፊት ለምን አንጸባረቀ? ብለን ስንጠይቅ ሙሴ ያለማቋረጥ በደመና መካከል ከእግዚአብሔር ጋር ስለቆመና ቃል በቃል ለአርባ ቀንና ሌሊት ከአምላኩ ጋር ስለተነጋገረ ነበር፡፡ ስለተቀበለው የኦሪት ሕግ ክብር ሲባል የሙሴ ፊት በክብር አንጸባረቀ፡፡ የእግዚአብሔር ክብር በዙሪያው ስለነበር ፊቱ አንጸባረቀ ፤ ትኩር ብለው ማየት ቢሳናቸውም ዕድለኞች የነበሩት የዚያን ዘመን ሰዎች የሙሴን የሚያበራ ፊቱን ተመለከቱ፡፡ እስቲ ከፈጣሪው ጋር የተነጋገረውን የሙሴን ፊት በዓይነ ሕሊናችን ሲያንጸባርቅ እንመልከተው! በዘመኑ ባንኖርም ለአፍታ ያን ትሑት ሰው ሙሴን ዐሥርቱ ትእዛዛትን በጉያዎቹ ታቅፎ ከሲና ተራራ ሲወርድ ፣ ፊቱም ሲያበራ እንመልከተው......! ዕፁብ ድንቅ ነው! ውድ አንባቢያን! በሲና ተራራ በደመና ተሸፍኖ ፈጣሪውን ያነጋገረው ሙሴ ፊቱ እንዲህ ካበራ ‹እግዚአብሔር በብሩሕ ደመና ተጭኖ መጥቶ በማኅጸኗ ያደረ› የድንግል ማርያም ፊትዋስ እንዴት ያበራ ይሆን? ሙሴ በእሳት መጋረጃዎች መካከል አልፎ ዐሠርቱን ቃላት በመቀበሉ ፊቱ ካንጸባረቀ ሰባቱ የእሳት መጋረጃ በሆድዋ ውስጥ ተዘርግቶ ለእግዚአብሔር ቃል ማደሪያ የሆነች የእመብርሃን ፊትዋ እንደምን ያንጸባርቅ ይሆን? ለእኔስ ሁለቱን ጽላት ከታቀፈው ከሙሴ ፊት ይልቅ የእግዚአብሔርን ቃል የታቀፈችው የእመቤታችን ፊት እንደሚያበራ ይታየኛል፡፡ ሙሴ ለአንድ ወር ከዐሥር ቀን ያነጋገረውን ፈጣሪ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅጸንዋ ይዛ የወለደችው ድንግል የፊትዋ ብርሃንዋ መጠን ምን ያህል ይሆን? ሊቃውንቱ ዛሬ ሌሊት ‹ትበርህ እምኮከበ ጽባሕ ወታስተርኢ እም አርእስተ አድባር› ከጠዋት ኮከብ ይልቅ ታበራለች ከተራሮችም ራስ በላይ ትታያለች ይላሉ፡፡ አክለውም ‹ፈጽማ ያማረች ፣ የጸዳች እና የምታበራ ፣ እንደ ፀሐይ የምታበራ ናት› (አዳም ወሠናይት ጽዱት ወብርህት ከመ ፀሐይ ብርህት) ሲሉ ያድራሉ፡፡ እንደ ፀሐይ ብቻ ነው ወይ የምታበራው የሚል ካለ ደግሞ ‹‹ከፀሐይ ሰባት እጅ የምታበሪ ክብርሽ ከአድባራቱ ሁሉ ከፍ ከፍ ያለ›› እያልንም እናመሰግናታለን፡፡ የሙሴን ፊት ትኩር ብሎ ማየት ካስቸገረ እመቤታችንን ያዩ ሰዎች ምንኛ በብርሃን ተሞልተው ይሆን? ‹አሕዛብ ለፊትሽ ይማልላ
Show all...
ይ በሕዝቡ ሁሉ ፊት የገዛ ሚስቱን አሠቃይቶ ሰውነቷን ቆራርጦ ሰቅሎ አንገቷን በመሰየፍ ሰማዕትነት እንድትቀበል አደረጋት፡፡ ቅድስት እለእስክንድርያም ቅዱስ ጊዮርጊስን ‹‹ሳልጠመቅ አልሙት›› ስትለው እርሱም ‹‹ደምሽ ጥምቀት ሆኖልሻልና እነሆ የክብር አክሊል እየጠበቀሽ ስለሆነ አይዞሽ›› ብሎ አጽንቷታል፡፡ በመጨረሻም ቅዱስ ጊዮርጊስ ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ታላቅ ቃልኪዳን ከተቀበለ በኋላ በ27 ዓመቱ በሚያዝያ 23 ቀን ሰማዕትነቱን በድል ፈጽሞ የክብር አክሊልን ተቀዳጀ፡፡ አንገቱም ሲቆረጥ ውሃ፣ ደምና ወተት ወጥቷል፡፡ ከሥጋውም እጅግ ብዙ አስገራሚ ተአምራት ተፈጽመው ታይተዋል፡፡ የሊቀ ሰማዕታት የቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!!! (ምንጭ፡- ገድለ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ስንክሳር ዘወርሃ ሚያዝያ)
Show all...