cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Maranatha Digital Network

#Maranatha_digital_Network #youth center #spreading the gospel of the lord Jesus Christ #christian living Follow us on:- Instagram:https://www.instagram.com/maranatha_digital_network Youtube:https://www.youtube.com/@MDN146 Telegram group @Maranatha_MDN2

Show more
Advertising posts
1 973Subscribers
-124 hours
-37 days
-1730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

✨ፈተና✨ . . . . ♨️ፈተነና ሰዉ በምድር ላይ እስካለ ድረስ ከሚያጋጥሙት ነገሮች መሃከል አንዱ ነው። ህይወት ሁልጊዜ ደስታና ሳቅ ብቻ አይደለምችም መጨነቅና ማልቀስም አንዱ የህይወት ክፍል ነው። ክርስትያን ስለሆንን በዚህ መንገድ አናልፍም ማለት አይደለም። ምክንያቱም የምንኖረው በወደቀ ዓለም ዉስጥ ስለሆነ ነው። መጽሐፍ ሲናገርም በዚህ ዓለም ስንኖር መከራ እንዳለብን ነገር ግን የሚያግዘን ፀጋ እንደሚሰጠን ነው የሚያስረዳን። 🔆ሰው በዚህ ዓለም ሲኖር አማኝ ሆነም አልሆነም በመከራና ፈተና ማለፉ አይቀሬ ነው፡፡ እንደ ክርስትያን ደግሞ በእግዚአብሔር፣ በራሳችን ምኞትና በሰይጣን ግፊት እንፈተናለን። በዚህ ውስጥ ስናልፍ ግን የፈተናውን ምንጭለይቶ ማወቀ በጣም አስፈላጊ ነው።         ♦️እግዚያብሄር የሚፈትነው  ፈተና ምን አይነት ነው? ♨️እግዚአብሔር ማንንም በክፋ አይፈትንም ይሄ ማለት ከቅድስና እንድንጎድልና  ሀጢያት እንድንሰረራ የሚያደርግ  ፈተና አይፈትንም ማለት ነው። ያዕቆብ 1:13 ማንም ሲፈተን በእግዚአብሔር እፈተናለው አይበል እግዚአብሔር በክፉ አይፈትንምና 🔆በራስ ምኞትና በሰይጣን ግፊት ተፈትኖ በእግዚአብሔር ተፈተንን ማለት ተገቢ አይደለም። በስህተታችን/በወድቀት  ተማርን ማለት ከእግዚአብሔር የመጣ ነው ማለት አይደለም። መማር ከፈለግን ወድቀንም ሳንወድቅም ሊያስተምረን ዝግጁ ነዉ። ሌላኛው ደግሞ እኛ የማንችለውንና ከአቅማችን በላይ በሆነ ፈተና አይፈትነንም። 1ቆሮንቶስ 10:13 ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዝያብሔር የታመነ ነው።        ♦️እግዚአብሔር ለምንድ ነዉ የሚፈትነው? ♨️ፈተና/መከራ ያለንበትን ሀኔታ/ደረጃ መለኪያ መንገድ ነው። እግዚአብሔር የሚፈትነው እምነታችን እንዲጠነክርና ተፈትነን በዚያ መንገድ ስናልፍ የላወቅነውንና መማር ያለብንን ትምህር እንድንማር ነው።          ♦️ፈተናን ማባከን ምን ማለት ነው 🔆ከዚያ ፈተና መማር ያለብንን አለመማርና በፈተና ውስጥ ስናልፍ ማፍራት ያለብንን ፍሬ አለማፍራት ፈተናችንን ማባከን ነው። በፈተና ወስጥ የምናፈራው ፍሬ ትዕግሥት ነው መከራ/ፈተና ከሌለ ትዕግሥት አይኖረን። ትዕግሥት እንዲኖረን መፈተነን አለብን።ሮሜ5:3-4 ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ ትዕግስትም ፈተነናን ፈተናም ተስፋን እንዲያረግ እያወቅን በመከራችን ደግሞ አንመካለን።     ♦️ እኛላይ ብቻ የደረሰም ሆነ  የሚደርስ ምንም ነገር የለም። 1ቆሮ10:13 ለሰው ሀሉ ከሚሆን በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም።  ♨️ስለዚህ ለምን ተፈተንኩ ከማለት ይልቅ ፈተናውን ተፈትነን ማለፍ እንደንችል ካልሆነ ደግሞ ከስህተታችን መማር እንድንችል እግዚአብሔር እንዲረዳን መፀለይ የተሻለ ነዉ።
Show all...
❤‍🔥 5 4👍 2🔥 1🥰 1👏 1🙏 1🤝 1🆒 1
🍁#MDN_BIBLE_VERSE🍁
“ከላይ ሰደደ ወሰደኝም፥ ከብዙ ውኆችም አወጣኝ።” — መዝሙር 18፥16
〽️aranatha Digital Network ⛈@Maranatha_MDN⛈ .| @Maranatha_MDN2 |.
Show all...
❤‍🔥 3🆒 2 1👍 1🔥 1🥰 1
''አማኝ በምን ይሸለማል''
—በወንድም በእምነት ኤርምያስ ♨️ከዚህ ቀደም በማራናታ ዲጂታል ኔትዎርክ የተለቀቀ ተከታታይ ትምህርት በPDF መልኩ የቀረበ፡፡ ❄️የትምህርቱ አንጽሮት አማኝ ስለሽልማት(አክሊል) ያለውን መረዳት ማሳደግና ከድኅነት በምን እንደሚለይ ማስገንዘብ፡፡
Show all...
4👍 2💯 2 1 1🔥 1🥰 1
🍁#MDN_BIBLE_VERSE🍁
“በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት መሆን ይጠቅማል እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና።” — ገላትያ 6፥15
〽️aranatha Digital Network@Maranatha_MDN .| @Maranatha_MDN2 |.
Show all...
👍 3❤‍🔥 2 2🔥 2 1
ምጥ ይዞኛል😨 . . . . 📌#ምጥ_ይዞኛል ሲል ነበር ሐዋርያው ጳውሎስ ምን ያህል የክርስቶስ ምስል በእነርሱ ዳግም እንዲሳል እንደሚፈልግ ለገላትያ አማኞች በድብዳቤው ያስታወቃቸው፡፡✉️
“ልጆቼ ሆይ፥ ክርስቶስ በእናንተ እስኪሣል ድረስ ዳግመኛ ስለ እናንተ ምጥ ይዞኛል።” — ገላትያ 4፥19
✨ከእውነተኛው ወንጌል የተለየው ማለትም መዳን በተሰቀለው በኢየሱስ በኩል ብቻ መሆኑን የማያስተምረው ወንጌል በመልአክ እንኳን ቢሰበክ በእርሱ በሐዋርያው ጭምር ቢሰብክ የተረገመ እንዲሆን ይጽፍላቸዋል፡፡✍🏻
“ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን።” — ገላትያ 1፥8
⚡️ምን ያህል ፈጥነው ልዩ ወደሆነና እንግዳ ትምህርት የገላትያ አማኞች ፈቀቅ እንዳሉ የሚደነቀው ሐዋርያው ክርስቶስ እንደተሰቀለ ሆኖ በፊታቸው ተስሎ እንደነበር አሁን ግን አዚም ሆኖባቸው ለመዳን የገዛ ሥራቸውን የመስቀሉ ሥራ ማከላቸውን እያነሳ ይወቅሳቸዋል፡፡😔
“የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ፥ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር፤ ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው?” — ገላትያ 3፥1
✨ሐዋርያው ለመዳን መንገዱ የመስቀሉ ሥራ እንደሆን አጽንኦት እየሰጠ ከዚያ ውጪ ያለው ረበቢስ ከንቱ መሆኑን አበክሮ ያስታውቃል፡፡🤗
“ነገር ግን ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንዲጸድቅ እንጂ በሕግ ሥራ እንዳይሆን አውቀን፥ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በሕግ ሥራ ስለማይጸድቅ፥ እኛ ራሳችን በሕግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ እምነት እንጸድቅ ዘንድ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል።” — ገላትያ 2፥16
⚡️አማኞች ከክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት እንዳይኖራቸው በራሱ ትምክህቱ ምን እንደሆን እየተናገረ የሚዘልፈው ሐዋርያው ሌላ ትምክህትን በማስወገድ በመስቀሉ ብቻ ድኅነት ስለመሆኑ ይመኩ ዘንድ ገላትያውያንን ይገስጻቸዋል፡፡✍🏻
“ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።” — ገላትያ 6፥14
በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት መሆን ብቻ ነው የሚያዋጣው አድቡ ሲል ሐዋርያው ጳውሎስ ለገላትያውያኑ አማኞች መልዕክቱን ሰዷል፡፡📩
“በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት መሆን ይጠቅማል እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና።” — ገላትያ 6፥15
〽️aranatha Digital Network ❄️@Maranatha_MDN❄️ <.| @Maranatha_MDN2 |.>
Show all...
🥰 3👍 2❤‍🔥 2🔥 2 1🎉 1💯 1
🍁#MDN_BIBLE_VERSE🍁
“መዳንም በሌላ በማንም የለም”   — ሐዋርያት 4፥12
''#መዳን_በኢየሱስ_ብቻ_ነው'' 〽️aranatha Digital Network@Maranatha_MDN⛈ .| @Maranatha_MDN2 |.
Show all...
💯 4 2🕊 2❤‍🔥 1 1🔥 1🥰 1🎉 1
!!ጽፌላኋለሁ!! . . . . ♨️"#ጽፌላችኋለሁ" ሲል ነበር ሐዋርያው ዮሐንስ በቀዳሚ መልዕክቱ ለአማኞች ስለዘላለም ሕይወት እንዲሁም እንዳላቸውም ጭምር ያውቁ ዘንድ አስረግጦ የተናገረው።
“የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ።” — 1ኛ ዮሐንስ 5፥13
🔆የመዳን እውነቱ በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ማመን እንደሆን የሚናገረው ሐዋርያው "ልጁ #አላችሁ? እንግዲያውስ ሕይወት አላችሁ!" ሲል የመዳንን መንገድ እንዴት እንደሆን ያብራራል።
1ኛ ዮሐንስ 5 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹¹ እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው። ¹² ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።
♨️በእግዚአብሔር ልጅ ማመን እንዴት ያድናል? ብሎ የሚል ቢኖር ሐዋርያው በዚያው ደብዳቤ ምላሹን "የኃጢአት #ማስተስሪያ አድርጎ ስለላከው ነው" ሲል አስፍሯል።
“እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ...” — 1ኛ ዮሐንስ 4፥10
🔆እንቅጩን እወቁ የመዳን መንገድ ኢየሱስ ነው የሚለውን ሃሳብ በመልዕክቱ ያንፀባረቀው ሐዋርያው ዮሐንስ ለመዳናችን ዋስትና ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ጭምር በመልዕክቱ አስጨብጧል። ♨️ለእርቅ የሚሆን ስርየት በልጁ ከሆን ስርየት የሆነበትን ኢየሱስን ማመን ደግሞ ከእግዚኣብሔር ጋር እርቅን ፈጽሞ የዘላለም ሕይወት የሚሰጥ ከሆነ እንግዲያውስ "መዳን በሌላ በማንም የለም በልጁ ማመን ብቻውን ያድናል እንዲሁም ዋስትና ይሆናል"
“መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።” — ሐዋርያት 4፥12
✍🏼ተስፋሁን ታረቀኝ ምህረትና ጸጋ ይብዛልን!! 〽️aranatha Digital Network@Maranatha_MDN⛈ .| @Maranatha_MDN2 |
Show all...
🔥 3❤‍🔥 2🆒 2 1 1👏 1💯 1
🍁#MDN_BIBLE_VERSE🍁
«እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤» — 1ኛ ጴጥሮስ 2፥9
〽️aranatha Digital Network@Maranatha_MDN⛈ .| @Maranatha_MDN2 |.
Show all...
🥰 5❤‍🔥 2 2 1👏 1🕊 1💯 1
??አታውቁምን ?? . . . . 📌"#አታውቁምን?" ይህኑኑ ጥያቄ ነበር ሐዋርያው ጳውሎስ በቆሮንቶስ የሚገኙትን አማኞች የጠየቃቸው።
“የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?” — 1ኛ ቆሮንቶስ 3፥16
♨️ከሐዋርያው አጠያየቅ ተነስተን የቆሮንቶስ አማኞች የእግዚአብሔር መቅደስ መሆናቸውን የዘነጉ ስለመሆኑ እንገነዘባለን። ይህ ብቻ ሳይሆን ከመዘንጋት ባለፈም በሥጋ ምልልስ በተለያዩ የኃጢአት ልምምዶች ውስጥ መዘፈቃቸውን ሐዋርያው ከጻፈላቸው ደብዳቤ ማስተዋል ይቻላል፡፡ 🔆በመልዕክቱ የዘነጉትን ነገር የሚያስታውሳቸው ሐዋርያው ጳውሎስ በሌላ ሥፍራ ላይ ''ለራሳችሁ አይደላችሁም!'' ሲል በውድ ደሙ የራሱ አድርጎ የገዛቸው ጌታ የመንፈሱ ማደሪያ ስለማድረጉ እያስገነዘበ በሥጋ ከመመላለስ እንዲያድቡ ይነግራቸዋል፡፡
“ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።” — 1ኛ ቆሮንቶስ 6፥19-20
♨️በሥጋ መመላለስ በውስጥ ስላለው መንፈስ ቅዱስ በቅጡ ያለማወቅ ውጤት ነው፡፡ ሰውነትን ማደሪያው አድርጎ የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ በድካም ሊያግዝ፣ በውድቀት ጊዜ ሊያነሳ፣ ጸሎት ሊያስተምር፣ መንገድ ሊመራ ያለ ነው፡፡ ቆሮንቶሳውያኑ ይህንን አለመገንዘባቸው በሥጋ እንደሰው ልማድ እንዲመላለሱ ዳርጓቸዋል፡፡ 🔆ከቆርንቶሳውያኑ አይነት ውድቀት ለመውጣት ማለትም በሥጋ ከመመላስ ወይንም እንደሰው ልማድ ከመመላለስ የሚያስተወው ሐዋርያው በገላትያ ለሚገኙ አማኞች እንደገለጸው ''#በመንፈስ #በመመላለስ'' ነው፡፡
''ነገር ግን እላለሁ፟፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ፡፡'' —ገላትያ 5፥16
♨️በመንፈስ መመላለስ ማለት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል መታገዝ በርሱ መኖር እና በእርሱ አመራር ሀሳባችንን፣ ድርጊታችንን እንዲሁም ውሳኔአችንን ማስገዛት ነው፡፡ 🔆ወደ እውነት በሚመራው በቅዱሱ መንፈስ መመራት ሕይወትን ቀላል የሚያደርግ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ሕብረት የሚያሳልጥ #አይነተኛ #ብልሃት ነው፡፡ ✍🏽ተስፋሁን ታረቀኝ ምህረትና ጸጋ ይብዛልን 〽️aranatha Digital Network ⛈@Maranatha_MDN⛈ .| @Maranatha_MDN2 |.
Show all...
💯 4👍 2❤‍🔥 2 1🔥 1🥰 1🙏 1
በመከራ ስናልፍ በምን እንጽና?መከራ በዚች ምድር ስንኖር ሁላችንም በኑሯችን የምናስተናግደው ነገር ነው። አይነቱና መጠኑ ይለያይ እንጂ ሁሉም ሰው በብዙ መከራና ጭንቀት ውስጥ ያልፋል። በእርግጥ መከራ የሚወደድ ሳይሆን ከባድ እና በጣም አስቸጋሪ ነው። ይሁንና መከራው በራሱ ይዞ የሚመጣው ህመምና ስቃይ እንዳለ ሆኖ፥ እንዴት ያንን መከራ ማለፍ እንደምንችል አለማወቅና ከገጠመን ነገር ተነስተን የምንሰጠው ተገቢ ያልሆነ ምላሽ፥ አንዳንዴ እያለፍን ካለንበት መከራ እንኳን እጅጉኑ የከፋ ሊሆንና የራሳችንንም ሆነ የሌላውን ሕይወት አደጋ ላይ ሊጥል  ይችላል። ለዚህ ነው እውነት የሚቀዳበትን የእግዚአብሔርን ቃል ተመርኩዘን ምን ማድረግ እንደሚገባን መገንዘብ ያለብን። ☞በመጽሐፍ ቅዱሳችን ስለመከራ በብዙ መንገድ ተፅፎ እንመለከታለን። ይህ ቀጥሎ የቀረበው ጥቅስ ስለመከራ  ጠቃሚ መልዕክት ያዘለና በብዙ የሚያጽናና ነው:–                        1ኛ ቆሮንቶስ 10                       ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ ❛❛ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር #መውጫውን_ደግሞ_ያደርግላችኋል
☞ብዙ ጊዜ ሰዎች ከገጠማቸው መከራ ተንተርሰው፥ ያለመጠን ሲያማርሩና ተስፋ ቢስነት ያንዣበበትን የሕይወት ጎዳና ሲመሩ በውጤቱም በመኖር ተስፋ ቆርጠው ራሳቸው ላይ ክፉ ለማድረስ ሲጣጣሩ ይስተዋላል። ይህ ብቻ ሳይሆን፡ የእግዚአብሄርን በእነርሱ ላይ ያለውን ትኩረት፣ ፍቅር መሆን እና መሀሪነት ካሉበት የህይወት ሁናቴ ጋር አያይዘው ተገቢ ያይደለ ትርጉም ሲሰጡ እናያለን። ትልቁ ቁምነገር ግን እግዚአብሔር በክፉ አይፈትንም!! መውጫ በሌለው ዝግ መንገድ ስንከራተት ሊተወን ፈቃዱ አይደለም። ወፍ እንኳን ጫጩቶቿ ከጎጆው ወጥተው መብረር የሚችሉበት ወቅት ሲደርስ ጎጆዋን በእሾህ ትቀጥራለች። ይህን የምታደርገው የወለደቻቸውን ለመጉዳት ሳይሆን ውስጣቸው ያለውን ጥንካሬና አቅም ለማውጣጣት ነው። |•|እኛም በምድር የምናስተናግደው መከራ የምንፈተንበት እና የምንፀናበት አልፎም የእግዚአብሔርን ፍቅር ሀያልነት መገንዘቢያ፥ በክርስቶስ የተመሠረተውንም መልካሙን የአባትነቱን ግንኙነት ጥንካሬ ማያ ይሆነናል። እግዚአብሔር  መከራ እንደማይኖር ሳይሆን "ምንም ያህል መከራ ቢኖር ከእርሱ ጋር እሆናለሁ"ብሎ ለታመኑበት አብሮነቱን ያሳያል። •|ጳውሎስ በአንድ ስፍራ በመልዕክቱ:- ከሚመጣዉ እና ካለው መከራ ግዝፈት ይልቅ  የክርስቶስን ፍቅር አልቆ ሲያወራ እናያለን። መከራዉ ማነሱን ሳይሆን የተወደድንበት ፍቅር እና በፍቅሩ የተነሳ የተመሰረተው ህብረት እጅግ መብለጡን በማያወላውል ቋንቋ ይነግረናል። በጥበባችን አልያ በአቅማችን ሳይሆን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን። •|በየእለቱ ከሚገጥመን ፈተና እና ጥያቄ ይልቅ ኖረን ማንጨርሰው ሰላም ያገኘንበት ፍቅር ያይላል። እጅጉን ከባድ ያልነው ነገር ከተወደድንበት ፍቅር ጋር ፈጽሞ አይነፃፀርም። |•| ደግሞም እግዚአብሔር ለራሳችን ከምናስበው በላይ ያስብልናል፤ እያንዳንዱ ነገራችንም ግድ ይለዋል። ለፍጥረት ሁሉ  አስፈላጊውን አቅርቦት እንዲሁ የሚሰጥ የጸጋ አምላክ እንዴት ነው እርሱ በውድ ልጁ ደም ገዝቶን የክርስቶስ አካል ክፍል ለሆንን ለእኛ ማያስብልን?!! እንዴት ሆኖ ነው ለልጁ ታጭታ ለተሞሸረች እልፍ አማኞችን በውስጧ ላቀፈች ቤተክርስቲያን ማይጠነቀቅላት?! |•|ስለዚህ ጎደለ የምንለው ቢኖር ባይኖር፣ የፈለግነው ቢሳካ ባይሳካ፣ የከበበን ግራ አጋብቶ ማያልፍ ቢመስል፣ የተሻለ ነገ ርቆ ቢታይ... ትኩረታችንን በሰማይ ባለው፣ የልባችንን ሳናወራው በሚረዳን፣ ድምፁንም እስክንሰማ  ባስጠጋን አድራሻ መገኛችንን በክርስቶስ በቀየረው በአብ ላይ አድርገን ከፍቅሩ ማንም እንደማይለየን ተረድተን በፀጋው እንበርታ። እንደገዛ አካሉ በሚያስብልን፣ ከኃጢአት በቀር እንደ እኛ በነገር ሁሉ በተፈተነ፣ ሰው ሆኖ የሰውን ችግር በሚያውቅ፣ ሊራራልንና የሚረዳንን ጸጋ ሊሰጠን በሚችል ሊቀ-ካህናት ደስ ይበለን። አዎን በጌታ ደስ ይበለን። ሐዋርያቱ እጅ እግራቸውን ታስረው፥ የሞት ፍርሃት ከብቧቸው፣ ከሰው ንቀትና ግፊያ ጠግበው በተደሰቱበት ጌታ ሀሴት እናድርግ። ደግሞም በልባችን ለዘላለም ባደረ፣ ደከሙ ብሎ በማይተወን ይልቁኑ ድካማችንን በሚያግዝ፣ ሳይነቅፍ ጸጋ አብዝቶ የምንነቀፍበትን በሚያርቅልን በቅዱስ አጽናኝ መንፈስ ደስታን እንሞላ። ሁልጊዜም በነገር ሁሉ አመስጋኞች እንሁን።          ጸጋና ሰላም ይብዛልን!! 〽️aranatha Digital Network@Maranatha_MDN⛈ .| @Maranatha_MDN2 |.
Show all...
❤‍🔥 5👍 3 1 1💯 1