cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የስብዕና ልህቀት

በዚህ ቻናል ⚡ህይወትን የሚያንፁ የስነ-ልቦና ምክሮች ⚡መሳጭ የፍቅር ታሪኮች እና ወጎች ⚡ጥልቅ ማህበራዊ እና ፍልስፍናዊ እይታዎች ⚡ውብ የጥበብ ስራዎች በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio ይቀርባሉ። #ሼር በማድረግ ወዶጅዎን የዚህ የእውቀት እና የጥበብ ድግስ ታዳሚ እንዲሆኑ ይጋብዙ።

Show more
Advertising posts
89 186Subscribers
-4724 hours
-2857 days
-1 29330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

👍 41
ሰዓት ተሸካሚው ምንጭ ፦ የፍልስፍና ማዕድ በጥበበኛው ሰለሞን “አንድ ቀን በሕይወትህ ላይ እንዲጨመርልህ ምን ያህል ትከፍላለህ?” ሰዓት ተሸክሞ የሚዞር አንድ ሰው፣ በመንገድ ያገኘውን አንድ ህጻን ልጅ ጠየቀ ... ህጻኑም ያለማመንታት “አምስት ሳንቲምም አልከፍልም" አለ፡፡ ዳግም ሰዓት ተሸክሞ የሚዞረው ሰው ተመልሶ መጣና ትናንት ህጻን የነበረውን የዛሬውን ወጣት ጠየቀው “አንድ ቀን በሕይወትህ ላይ እንዲጨመርልህ ምን ያህል ትከፍላለህ?” “ቢበዛ አንድ ወይም ሁለት ብር” ወጣቱም መለሰ፣ ግድ በሌለው አኳሃን፡፡ ይህ ወጣት ሸምግሎ ለሞቱ አንድ ሐሙስ በሚጠባበቅበት ጊዜ ሰዓት ተሸካሚው ተመልሶ መጣ፡፡ “አንድ ቀን በሕይወትህ ላይ እንዲጨመርልህ  ‌ ምን ያህል ትከፍላለህ?” "በባህር ውስጥ ያሉ እንቁዎችን፣ በሰማይ ላይ ያሉ ከዋክብትን ሁሉ እከፍላለሁ” ሽማግሌው መለሰ፡፡ ከፍልስፍና እሳቤዎች መኻል ላይ ልናነሳው የወደድነው ጊዜ ነው፡፡ የሰው ልጅ ስለ ሁለንተና ባወቀ እና ይበልጥ በተራቀቀበት መጠን፣ መልስ አልባ ጥያቄዎችን ያነሳል። ከየት መጣን? ጊዜ መጀመሪያ አለው? ጊዜስ በራሱ ምንድን ነው? በጊዜ መስመር ውስጥስ እንዳሻን ወደ ፊት እና ወደ ኋላ መመላለስ ይቻለናል? እነዚህን መልስ አልባ እንቆቅልሾችን ፍልስፍናዊ መልስ እንስጣቸው ብንል፣ ጊዜ በራሱ እንቅፋት ይኾንብናልና ለአሁኑ በጊዜ ወደ ኋላ መመለስ ይቻላልን? ከተቻለስ ምን ይከሰታል እና ጊዜስ ምንድን ነው የሚሉትን ሃሳቦች ብቻ እናብላላለን፡፡ ጊዜ ሰዓታችን የሚለካው ነገር እንደሆነ እናስባለን፡፡ ምድር ላይ ያሉ ክስተቶችንም በቅደም ተከተል እናስቀምጥበታለን። እናም ጊዜ በእለት ተዕለት መንከላወሳችን ውስጥ ትልቅ ስፍራን ይይዛል፡፡ ጥድፊያችንንም ኾነ እርጋታችንን የሚወስነው ጊዜ ነው፡፡ ሆኖም እንደምናስበው ወይም ይህ ነው ብለን እንደጠራነው አይነት ጊዜን በቀላሉ ፍቺ ሰጥተን አውቀነዋል ማለት አንችልም። ለብዙ ዘመናት ሳይንሳዊያን እና ፍልስፍናውያን በጊዜ ጉዳይ ሲጨቃጨቁ ኖረዋል። ፈላስፎችን ብዙው ክርክራቸው የሚያተኩረው፣ አሁን፣ አላፊው ጊዜ እና የወደፊቱ ላይ ነው፡፡ የጊዜን የፍልስፍና እሳቤዎች በሶስት አጠቃለን መመልከት እንችላለን፡- የአሁናዊነት (Presentism) ፍልስፍና አራማጆች የእውኑ ዓለም አሁንን እና አሁንን ብቻ ይይዛል ይሉናል፤ ትናንት አልፏል እና የእውነት አይደለም፤ ነገም አልደረሰምና የእውነት አይደለም፤ የእውነት የሆነ ነገር ቢኖር አሁን ብቻ ነው፡፡ ያለፈው ትዝታችን፤ ያልደረሰው የወደፊቱም እንዲሁ ትንበያ ብቻ ነው። እውነት የአሁን ቅጽበት ላይ ብቻ ትገኛለች። በአንጻሩ የአላፊነት (growing-past) ፍልስፍና አቀንቃኞች እውነት አላፊው እና የአሁን ጊዜ ላይ ብቻ ትገኛለች ፤ ያልተከወነው የወደፊቱ ጊዜ የእውኑ ዓለምን አይወክልልንም ይላሉ፡፡ ዳይኖሰሮች የእውነት ናቸው፤ የአድዋ ጦርነት እውነት ነው ሆኖም ወደ ፊት መከሰቱ የማይቀረው የእኔ እና ያንተ ሞት ግን እውነት አይደለም። ሶስተኛው የጊዜ እሳቤ የዘላለማዊነት(eternalism) ይሰኛል። በአሁን፣ በአላፊ እና በወደፊት ጊዜ መካከል የእውነትነት ልዩነት የለም ይለናል። ለምሳሌ የአዶልፍ ሂትለር በጀርመን መነሳት የአላፊ ጊዜን አይጠቁምም፤ ላንተ ያለፈ ጊዜ ቢሆንም ለአርስቶትል ገና ያልተከሰተ የወደፊት ክስተት ነው። ሆኖም ጊዜ በራሱ ምንድን ነው? ጥንታውያን ኢትዮጵያውያን፤ ህንዶች፣ ግብጾች እና ግሪካውያን ጊዜን በተለያዩ መንገዶች ይገልጹት ነበር። ጥንታውያኑ ሰዎች ስለጊዜ አላቂነት ወይም ዘላለማዊነት፣ ስለ ጊዜ እንዲሁ ፈሳሽነት አልያም ዙሮ ገጠምነት (ለምሳሌ ቀን ይደጋገማል፤ አመትም እንደ አዲስ ይጀምራል) የተለያዩ መላምቶች ነበሯቸው፡፡ ሬኒ ዴካርቴ 'ጊዜ ምን ማለት ነው?' ለሚለው ጥያቄ እንዲህ ይለናል:- “ቁስ አካሎች፣ ለምሳሌ አንተ ዘላለማዊ አይደለህም። እንዲያውም ከቅጽበታት ያለፈ እድሜ የለህም፡፡ በአንጻሩ እግዚአብሔር አንተን ጨምሮ ዓለምን በሙሉ በየቅጽበታቱ ይፈጥራል። ከአምስት ደቂቃ በፊት ያለው ዓለም እና አሁን ያለንበት ዓለም ይለያያል። ከቅጽበት በኋላም የሚኖረው ዓለም፣ አሁን ላይ ካለው ዓለም ይለያል። እናም የአሁኑን ቅጽበት ከቀጣዩ ቅጽበተ ዓለም የሚያቆራኘው ነገር ምን ይባላል?... ጊዜ። እግዜርም በእያንዳንዱ ቅጽበት አንተን እና ዓለምን ደጋግሞ ከጥቂት ልዩነቶች ጋር ይፈጥርሃል።” ሁሉም እንስሳቶች ማለት ይቻላል አሁንን ነው የሚኖሩት፤ ሆኖም ሰው ትንኝ አይደለምና ትናንት ምን እንደነበር ያስታውሳል፤ ነገም እንደሚመጣ ያውቃል። ለጊዜም ያለን እይታም ከእንስሳት ለይቶናል፤ እናስባለን ... እናሰላስላለን እንወስናለን፡፡ ትናንት የረገጥነውን ፈንጂ ዛሬ ላይም መልሰን አንረግጠውም፡፡ ተፈጥሮ ጊዜን እንድናውቅ አድርጋናለች። ጊዜ የእውነት ያለ ነገር ነው? መስመሩስ እንዲሁ እንደ ወንዝ ወደፊት ብቻ የሚፈስ ነውን? መጀመሪያ እና መጨረሻስ አለውን? @Zephilosophy @Zephilosophy
Show all...
👍 40 5🔥 2
ከወሲብ ባሻገር ኦሾ፣ አንተ ወሲብ የማይረባ ነገር መሆኑን ስትናገር ሰምተን እንደገና ሞክረነው ነገር ግን አልገባንም የማይረባ የሆነው ምኑ ላይ ነው?” እየነገርኳችሁ የነበረው ስለ ሌላ ነገሮች ነው፡፡ እሺ እነሱን ሞከራችኋቸው፡፡ በየቀኑ ስለ መመሰጥ እነግራችኋለሁ ነገር ግን እያረዘማችሁ (ላለማድረግ እያዘገያችሁ) ወሲብን ግን ትሞክራላችሁ አያችሁ ይህ ነው እንግዲህ ቀሽምነታችሁን የሚያሳየው፡፡ ወሲብ የማይረባ አይደለም እናንተ ናችሁ የማትረቡት፡፡ ለዚህ ነው በእናንተ ምክንያት ተራ ወሲብ የማይረባ የማይሆነው፡፡ ማሳደግ ካልቻላችሁ፣ ንቁም ካልሆናችሁ ቀሽምነቱን ልትረዱት አትችሉም፡፡ በተመሳሳይ ደረጃ ሆናችሁ መገንዘብ አትችሉም፡፡ ወደ እብዶች ቤት ሂዱ አንድ እብድ ፈልጉና “እብድ ነህ" በሉት ነገር ግን ቅሉ ፍፁም ይናደድባችኋል፡፡ ማንም እብድ  መሆኑን አይቀበልም፡፡ "ምን እያወራችሁ ነው? ከእኔ በስተቀር አለም በሙሉ እብድ ነች" ይላችኋል፡፡ አንድ እብድ እብድነቱን አመነ ማለት በእርግጠኝነት ከእብድነት አለም እየወጣ መሆኑን ማወቅ ይኖርባችኋል፡፡ መመሰጥን ማግኘት ካልቻላችሁ የተሻለ መመልከት፣ ከተለየ አቅጣጫ መረዳት አትችሉምና የማይረባ መሆኑን ልትረዱት አትችሉም፡፡ አሁን እናንተ ምንም የምልከታ አቅጣጫ የላችሁም፡፡ ዝግ ናችሁ ዝግ፡፡ ወደ መስታውት ቅረቡ አፍንጫችሁ መስታወቱን እስኪነካ ድረስ፡፡ አስተውሉ በፍፁም ፊታችሁን ማየት አትችሉም፡፡ የመስታውቱ ችግር አይደለም፡፡ ከመስታወቱ ራቅ ስትሉና ቦታ ስትሰጡት አንፀባርቆ ፊታችሁን ያሳያችኋል ስለዚህ ከመስታውቱ ራቁ። ወሲብ ትልቁ ተወዳጅ ነገር ይመስላል፡፡ ወንድ በሴት ይማረካል ሴትም በወንድ ትማረካለች፡፡ አንዱ የሚያስፈልገው ነገር ሁሉ የወሲብ አጋሩ ያለው ይመስለዋል፡፡ ይህ ሁኔታ ሁለቱንም ለማኝ ያደርጋቸዋል፡፡ ፍላጐታቸውን ሁሉ ከወሲብ ጥላ ጀርባ የሚያገኙት ይመስላቸዋል፡፡ እንደዚህ አይነት ነገሮችን እንድትሰሩ የሚያደርጋችሁ ውስጣችው ያለው ሆርሞናችሁ ነው፡፡ ስነህይወታዊ ቀመር ነው፡፡ ምን እየሰራህ እንደሆነ፣ ለምን እየሰራኸው እንደሆነ ማየት ብትችል ለራስህ ይገርምሀል። ወሲብ በመፈፀምህ ያገኘኸው ነገር ምን ይሆን?፡፡ንቁ መንፈስ ውስጥ በምትገባበት ወቅት ምን እያወራሁ እንደሆነ ይገባሀል፡፡ ነገር ግን ንቁ መንፈስህ ጥልቅነት የሌለው በመሆኑ እያደገ ይገድልሀል እናም ወደ ነበርክበት የስህተት ጐዳና ትመለሳለህ። እንደገና ሞክረው ነገር ግን ስትሞክረው እያስተዋልክ እና እየተመሰጥክ ይሁን፡፡ ያን ጊዜ ወሲብን ፈፅመህ ላለማድረግ ትወስናለህ ወይም ተፈጥሯዊ አስገዳጅ ሀይል መሆኑን ትረዳለህ፡፡ እኔን ልትሸውዱኝ አትችሉም፡፡ እኔ ወሲብ የማይረባ ነው ስላልኳችሁ የፈፀማችሁት ይመስላችኋል?፡፡ ወሲብ በጣም ምርጥ ነው፣ ወሲብ በጣም የማይረባ ነገር ነው ብላችሁ አልያም ስለወሲብ አለመናገርን ብመርጥ እናንተ ከመፈፀም ወደኋላ አትሉም፡፡ ወደ አእምሯችሁ ተመልከቱ፡፡ እንዴት እራሳችሁን እያታለላችሁ እንደሆነ ለመረዳት ሞክሩ፡፡ አለበለዚያ እኔ ምን እያወራሁ እንደሆነ የንቃት ደረጃችሁ ካላደገ ፈፅሞ ልትገነዘቡኝ አትችሉም፡፡ የበለጠ ነገር ለማየት ከፈለጋችሁ ከዚህ የበለጠ ማሻሻል (ማደግ) አለባችሁ፡፡ ለምሳሌ እኔ አንድ መንገድ ዳር ላይ ያለ ዛፍ ጫፉ ላይ ሆኜ እናንተ በመንገዱ ላይ እየሄዳችሁ ጋሪ እየመጣ ነው" ብላችሁ "ምንም ጋሪ አይታየኝም ጋሪ የለም ትሉኛላችሁ፡፡ ነገር ግን እኔ ጋሪውን ማየት የምትችሉት ወደ እናንተ በቀረበ ጊዜ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ አልፏችሁ ሲሄድ እንደገና ከእይታችሁ ውጪ ይሆናል፡፡ አሁንም ወደ በለጠ ከፍታ በወጣችሁ ቁጥር የተሻለ ማየት ትችላላችሁ፡፡ የከፍታ ቁንጮ ላይ ስትሆኑ ሁሉንም ነገር ታያላችሁ፡፡ ከዚያ በኋላ ያለፈም ይሁን መጪ ጊዜ የለም ያለው አሁን ብቻ ነው፡፡ እውነታው ሲገባችሁ ወሲብ በጣም የማይረባ አና ለረጅም ጊዜ በባርነት የሚይዝ መሆኑን ትረዱታላችሁ፡፡ እያጣጣልኩት (እየነቀፍኩት) አይደለም ነገር ግን እውነታው ይህ ነው እኔም የተናገርኩት ያንኑ ነው፡፡ አያችሁ በውስጡ ዘልቃችሁ በመግባታችሁ በባርነት አስሮ ምን እየሰራችሁ እንደሆነ እንኳን ማየት እንዳትችሉ ወደ ንቃት እንዳትመጡም አድርጓችኋል። ወሲብ ከሚያሰክሩ (ስነህይወትህ) ውስጥ ነው፡፡ በደምስሮችህ ውስጥ የሚያሰራጨው ነገር በሱስ ተለክፈህ ምን እንደምትሰራ እንዳታውቅ እና ስሜቶችህን መቆጣጠር እንዲሳንህ ያደርጋል፡፡ በተደጋጋሚ እንድትፈፅመው የሚያስገድድህ ያልታወቀ ሀይል አለ እንደፈለጋችሁ ልትጠሩት ትችላላችሁ፡፡ በንቁ ጊዜያቶችህ ግን የማይረባ ነገር ስለምትረዳ "ምን እየሰራሁ ነበር? ለምን? ምን ነገርስ አገኘሁ?" በማለት ትጠይቃለህ፡፡ለዚህ ነው ብዙ ሴቶች ከወሲብ በኋላ የሚያለቅሱት እና የሚያዝኑት ምክንያቱም ሁሉም ነገር ትርጉም አልባ ሆኖ ያገኙታል፡፡ ለጊዜው ስሜትን የሚያነሳሳ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን በተመሳሳይ ሁኔታ ቢደጋገምም የትም አያደርስም፡፡ ወንዱ ከወሲብ በኋላ ወዲያውኑ ይተኛል ምክንያቱ ደግሞ በተረጋጋ መንፈስ ስላደረገው ነገር ማሰብ አለመፈለጉነው ጧት ሲነሳ ሁሉንም ነገር ይረሳል፡፡ በርግጥ ይገበኛል ጥሩ ነው ብለህ አምነህ የምትኖርበትን ልምድ ሲያንቋሽሹብህ አትወድም። ማንም ጅል ሲባል ደስ አይለውም፡፡ የምትረበሸው ስለ ወሲብ ባለህ ጥያቄ ሳይሆን በህይወትህ በራሱ ነው፡፡ ጅል ከሆነ እና ከኖርክባት አንተም ጅል እየሆንክ ነው። በርግጥ ያስቆጣል ነገር ግን በዚህ አጋጣሚ ከሱ የተሻሉ መልካም ነገሮች በህይወት ውስጥ መኖራቸው መናገር ይኖርብኛል፡፡ወሲብ ጅማሮ እንጂ ፍፃሜ አይደለም፡፡ እጥብቀህ እስካልያስከው ድረስ እንደ መጀመሪያ ያህል ከተጠቀምክበት ምንም ችግር የለውም፡፡ ፍቅር ከሰራህ በኋላ ቢያንስ ለአንድ ሰዓት ያህል በዜን እሳቤ ተቀመጥ ያን ጊዜ የምለው ይገባሀል፡፡ ወሲብ ጅል ነው የምለው ለምን እንደሆነ ይገባሀል፡፡ ከወሲብ በኋላ ለአንድ ሰዓት ያህል ስለተፈጠረው ነገር አስብ፡፡ አውቀህ ነው ወይስ ስሜትህ አስገድዶህ? አውቀህ ከሆነ ጅል አይደለህም፡፡ ተገዢ ከነበርክ ግን ጅል መሆንህን ተረዳው ምክንያቱም እየደጋገምክ በመፈፀም ራስህን ለበለጠ ባርነት እየሰጠህ ነው፡፡ በተመስጦ ብቻ ነው ምን እያወራሁ እንደነበረ ሊገባህ የሚችለው፡፡ በክርክር የሚወሰን ጥያቄ አይደለም፡፡ በራስህ ንቃት፣ በራስህ ግንዛቤ እና በራስህ ተመሰጦ የሚወሰን መሆኑን ተገንዘብ፡፡ ኦሾ የዜን መንገድ @Zephilosophy @Zephilosophy
Show all...
👍 47 3😢 2
👍 19
👍 12
👍 11
👍 15
#ዒድ_አልፈጥር ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ። ዒድ ሙባረክ ! በዓሉ #የሰላም፣ #የአንድነት፣ #የፍቅርና #የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን። መልካም በዓል !
Show all...
22👍 5
ክቡር ሰው - ካንት ምንጭ ፦ ፍልስፍና ከዘርዓያዕቆብ እስከ ሶቅራጠስ ፀሀፊ ፦ ፍሉይ አለም ከጓደኞችህ ጋር እራት እየበላህ፣ አንዱ ተስተናጋጅ ከመጠን በላይ እያጨበጨበ አስተናባሪውን ይጣራል “እዚህ ጋር አንድ ምግብ፡፡” አንዳንድ ሰውም በሰላም ላደረሰው ሾፌር “እንዴት ነህ፣ ቻው ወይም አመሰግናለሁ” ሳይል ከታክሲ ወርዶ ወደ ጉዳዩ ያቀናል፡፡ ወንጀለኞች ህጻናትን ሰርቀው እንደ እቃ ይሸጣሉ፡፡ መንግስትም አገሩን ከዳ ብሎ ያስበውን ግለሰብ ያስገድላል፡፡ እነዚህ ሁሉ ድርጊቶች በጋራ የያዙት ነገር ምን አለ? ኢማኑኤል ካንት አስተናጋጁን የሚያመናጭቀው ጓደኛህም፣ ለሾፌሩ ግድ የሌለው ተሳፋሪም፣ ልጆች የሚጠልፉ ወንጀለኞችም፣ አስገዳዩ መንግስትም... ሁሉም የሰውን ልጅ አግባብ ባልሆነ ሁኔታ አስተናግደዋል ይለናል። ካንት በምክንያታዊነት ላይ ባለው የጸና አቋም በእጅጉ ይታወቃል። ለእርሱ ምክንያታዊነት ከሁሉ የላቀ ንብረታችን እንደሆነ ነው የሚነግረን። ከዚህም በላይ ምክንያታዊነት ምን ልክ ምን ስህተት ምን ኃጢአት ምን ጽድቅ እንደሆነ ይለይልናል፡፡ ካንት የሞራል ህግጋት አይለወጤ እና የጸኑ ናቸው ብሎ ያስባል። የሚደረስባቸውም በምክንያት እና ምክንያታዊነት ብቻ ነው። ይህንንም ምክንያታዊ ግብረገብነትንም ለማስረዳት ካንት ባለ ብዙ ገፅ መጽሐፎችን አሳትሟል። ካንት ሁሉም ሰው ሊነካ የማይገባው ክብር አለው ይለናል። እናም የሁላችንም ድርጊቶች ይህን ክብር የጠበቁ ሊሆኑ ይገባል። በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ ብንሆንም የሰውን ክብር መንካት የለብንም፡፡ ሰዎች የምንገለገልባቸው ቁሳዊ መሳሪያዎች አይደሉም፡፡ ሁሉም የራሳቸው ዋጋ አላቸው። ለሁሉም ሰው ግድ ሊኖረን ይገባል። ሁላችንም እንደ ግለሰብ ዋጋ እንዳለን እናስባለን፡፡ ዓለም የግለሰቦች ጥርቅም ናትና ለራሳችን የምንሰጠውን ዋጋ ለሁሉም ሰው መስጠት የተገባ ነው፡፡ እኛ ምንም አይነት ጥያቄ እና ምክንያት ሳንደረድር፣ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለራሳችን ከፍ ያለ ዋጋን ከሰጠን፣ እንደ ማህበርም ለሌሎች ሰዎች ዋጋ ሊኖረን ይገባል። አዎ በማህበረሰብ ውስጥ አንደኛው ተገልጋይ፣ ሌላኛው አገልጋይ ሊሆን የተገባ ነው፤ ሆኖም በዚህ ሂደት ውስጥ ሰዎችን እንደ ሰውነታቸው ልናከብራቸው የተገባ ነው፡፡ አስተናጋጁም፣ የታክሲ ሹፌሩም ሆነ ሀገር ከዳተኛው ሰው ናቸው። ሁሉም ለራሳቸው ዋጋን ይሰጣሉ፡፡ ካንት ከእርሱ በኑሮ ደረጃ ዝቅ ያሉትን አገልጋዮቹን በታላቅ ክብር ይመለከታቸው ነበር፡፡ በቀጣይም ሰውን እንዴት ማዋራት እንዳለብህ ስታስብ ይህን “እንደ ሰው እያከበርኳቸው ነው ወይንስ እንደ መሳሪያ እየተጠቀምኩባቸው?” ይህም ቀላል እና ሊተገበር የሚገባው ግብረገባዊ ህግ ነው፡፡ @Zephilosophy @Zephilosophy
Show all...
👍 49 10😢 2
👍 148 38🙏 3🤔 2