Helina Dawit & Yeabsira Dawit
" ይቅርታዬ "
የክብር ልብሷን ለብሳ
እንደ ቆመች ንጉሱ ፊት
የወርቁንም ዘንግ እንደ ነካች
ጥያቄዋን እንደመለሰላት
እኔም እየሱስን ለብሼ
አብ ፊት ሞገስ አገኘው
አባ አባት ማለት ድፍረቴ
ተመለሰልኝ ወደ ህይወቴ
አባቴ የማለት እምነቴ
ተመለሰልኝ ወደ ቤቴ
የመማጸኛ ከተማዬ
ዘልዬ የማመልጥበት
ከአሳዳጅ ከአስጨናቂዎቼ
ተሸሽጌ ምገባበት
እየሱስ በተባለው ድንቅ ስም
ነፍሴ አርፋለች ከምንም
እርሱ የከፈለውን ዋጋ
አልፎ ማነው እኔን ሚነካ
በደም የከፈለውን ዋጋ
ደፍሮ ማነው እኔን ሚጠጋ
ከሳሾቼ ብዙ ናቸው
ተጨባጭ መረጃ አላቸው
በህጉ መሰረት ቢሄዱ
አሳማኝ ነው ምክኒያታቸው
በየትኛው ቅድስናዬ
ልጋፈጥ ልቁም ለራሴ
አንገት መድፋት መሸማቀቅ
ዝምታ ብቻ እንጂ መልሴ
የቤቴ ክፍተት ሳይገፋው
ገፍቶ ባይገባ ከደጄ
የልቤ ርቀት ሳይመልሰው
ባያቅፈኝ ባይሆን ወዳጄ
ሁሉን በራሱ ፈጽሞ
ባያደርገኝ ኖሮ ቀና
ጽድቄ ብዬ ማስቆጥረው
የማሳየው ምን አለና
ፍርድ አልተዛባም ልክ እኮ ነው
ተከድኖ ሳይሆን ተከፍሎ ነው
በከንቱ አይደለም ደስታዬ
ኢየሱስ ሆኖኝ ነው ይቅርታዬ
ፍርድ አልተዛባም ልክ እኮ ነው
ተከድኖ ሳይሆን ተከፍሎ ነው
በከንቱ አይደለም ደስታዬ
ስለሆነኝ ነው ይቅርታዬ
Show more ...