cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

✟ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮች እና ስዕሎች

ኣርቶዶክሳዊ መዝሙራትን እና HD መንፈሳዊ ስዕሎችን ለማግኘት ሲፈልጉ ቻናላችንን ይጎብኙ።

Show more
Advertising posts
348Subscribers
+124 hours
-37 days
-530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

+ በሐረገ ትንቢቷም :- "ኢይጻእ ዐቢይ ነገር እምአፉክሙ: እስመ እግዚአብሔር አምላክ ማዕምር ውዕቱ - እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ አምላክ ነውና ከአንደበታችሁ [ጽኑዕ] ነገርን አታውጡ" ስትል ተናግራለች:: [ሳሙ.፪፥፫] (2:3] አምላከ ቅዱሳን የእስጢፋኖስን ጸጋ: የፊልያስን ማስተዋልና የሐናን በጐነት ያሳድርብን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን:: [ † ጥቅምት ፲፯ [ 17 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት [ወቀዳሜ ሰማዕት] ፪. ቅዱስ ፊልያስ ሰማዕት ፫. ቅድስት ሐና ነቢይት ፬. ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘኑሲስ ፭. የደብረ ሊባኖስ ሰማዕታት [ካቶሊካውያን የገደሏቸው] ፮. ቅዱሳን ሔራን ሰማዕታት ፯. አባ ዲዮስቆሮስ ካልዕ [ † ወርኀዊ በዓላት ] ፩. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ [ወልደ ዘብዴዎስ] ፪. ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ ፫. አባ ገሪማ ዘመደራ ፬. አባ ዸላሞን ፈላሢ ፭. አባ ለትጹን የዋህ ፮. ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ [ዘደሴተ ቆዽሮስ] " እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር . . . አንዳንዶቹ ተነስተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር:: ይናገርበት የነበረውንም ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ አልቻሉም:: በዚያን ጊዜ በሙሴ ላይ: በእግዚአብሔርም ላይ የስድብን ነገር ሲናገር ሰምተነዋል የሚሉ ሰዎችን አስነሱ . . . በሸንጐም የተቀመጡት ሁሉ ትኩር ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት::" [ሐዋ.፮፥፰-፲፭] (6:8-15) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
Show all...
🕊 [ እንኩዋን ለቅዱስ "እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት": ለቅዱስ "ፊልያስ" እና ለቅድስት "ሐና ነቢይት" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ] † 🕊 ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት 🕊 † በሕገ ወንጌል [ክርስትና] የመጀመሪያው ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳሚው ሰማዕት ይህ ቅዱስ ነው:: ቅዱሱ በመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን አስገራሚ ማንነት ከነበራቸው እሥራኤላውያን አንዱ ነበር:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ :- + የቅዱስ እስጢፋኖስ ወላጆቹ ስምዖንና ማርያም ይባላሉ:: [ሌሎች ናቸው የሚሉም አሉ] ገና ከልጅነቱ ቁም ነገር ወዳድ የነበረው ቅዱስ በሥርዓተ ኦሪት አድጐ እድሜው ሲደርስ ወደ ት/ቤት ገባ:: የወቅቱ ታላቅ መምሕር ገማልያል ይባል ነበር:: ይህ ሰው በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ፭፥፴፫ [5:33] ላይ ተጠቅሷል:: + በትውፊት ትምሕርት ደግሞ ይህ ደግ [ትልቅ] ሰው በርካታ ቅዱሳንን [እስጢፋኖስን: ዻውሎስን: ናትናኤልን: ኒቆዲሞስን . . .] አስተምሯል:: በጌታችን መዋዕለ ስብከት ጊዜም ከፈጣሪያችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ እየቀረበ ይጨዋወት ነበር:: በፍጻሜውም አምኗል:: + ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ እስጢፋኖስ ከዚህ ምሑር ዘንድ ተምሮ: ኦሪቱን ነቢያቱን ጠንቅቆ ወጣ:: ወቅቱ አስቸጋሪና ለኃጢአት ሕይወት የተመቸ ቢሆንም ቅዱሱ ግን የመሲህን መምጣት በጸሎትና በተስፋ ይጠባበቅ ነበር:: + በወቅቱ ደግሞ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ የንስሃ ጥምቀትን እየሰበከ መምጣቱን የተመለከተ ቅዱስ እስጢፋኖስ ነገሩን መረመረ:: ከእግዚአብሔር ሆኖ ቢያገኘው የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ሆነ:: ለ፮ [6] ወራትም በትጋት ቅዱስ ዮሐንስን አገለገለ:: + ለ፮ [6] ወራት ከቅዱስ ዮሐንስ ዘንድ ከተማረ በሁዋላ ለስም አጠራሩ ስግደት ይድረሰውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠመቀ:: በወቅቱ የተደረገውን ታላቅ ተአምር ልብ ያለው ቅዱስ እስጢፋኖስ መምሕሩን ቅዱስ ዮሐንስን እንዲያስረዳው ጠየቀው:: + "ከእኔ ይልቅ ከፈጣሪው አንደበት ይስማው" በሚል ላከው:: ቅዱሱም ከጌታ ዘንድ ሔዶ: እጅ ነስቶ ተማረ:: [ሉቃ.፯፥፲፰] (7:18) በዚያውም የጌታ ደቀ መዝሙር ሆኖ ቀረ:: ጌታም ከ፸፪ [72]ቱ አርድእት አንዱ አድርጐት ለአገልግሎት ላከው:: አጋንንትም ተገዙለት:: [ሉቃ.፲፥፲፯] (10:17) + ቅዱስ እስጢፋኖስ ጌታችን መድኃኔ ዓለም ከዋለበት እየዋለ: ካደረበት እያደረ ወንጌልን ተማረ:: ምሥጢር አስተረጐመ:: ጌታ በፈቃዱ ስለ እኛ ሙቶ ከተነሳ በሁዋላ ሲያርግ ደቀ መዛሙርቱን በአንብሮ እድ ባርኩዋል:: + በዚህ ጊዜም ቅዱሱ እንደ ወንድሞቹ ሐዋርያት ቅስናን [ዽዽስናን] ተሹሟል:: በበዓለ ሃምሳም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከ፸፪ [72]ቱ አርድእት የእርሱን ያህል ልሳን የበዛለት: ምሥጢርም የተገለጠለት የለም:: በፍጹም ድፍረትም ወንጌልን ይሰብክ ገባ:: + በመጀመሪያይቱ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ከማዕድ ሥርዓት ጋር በተያያዘ ፈተና ሲመጣ በመንፈስ ቅዱስ ምርጫ ፯ [7] ዲያቆናት ሲመረጡ አንዱ እርሱ ነበር:: አልፎም የ፮ [6]ቱ ዲያቆናት አለቃ እና የ፰ [8]ሺው ማሕበር መሪ [አስተዳዳሪ] ሆኗል:: + ፰ [8] ሺ ሰውን ከአጋንንት ፈተና መጠበቅ ምን ያህል ከባድ እንደ ሆነ ለማወቅ አባቶቻችንን መጠየቅ ነው:: አንድን ሰው ተቆጣጥሮ ለድኅነት ማብቃት እንኩዋ እጅግ ፈተና ነው:: መጽሐፍ እንደሚል ግን "መንፈስ ቅዱስ የሞላበት: ማሕደረ እግዚአብሔር" ነውና ለእርሱ ተቻለው:: [ሐዋ.፮፥፭] (6:5) + አንዳንዶቻችን ቅዱስ እስጢፋኖስ "ሊቀ ዲያቆናት" ሲባል እንደ ዘመኑ ይመስለን ይሆናል:: እርሱ በመጀመሪያ ሐዋርያና ካህን ነው:: ዲቁናው ለእርሱ "በራት ላይ ዳረጐት" ነው እንጂ እንዲሁ ዲያቆን ብቻ አይደለም:: +ቅዱስ እስጢፋኖስ ከጌታ ዕርገት በሁዋላ ለ ፩ [1] ዓመት ያህል ፰ [8]ሺውን ማሕበር እየመራ: ወንጌልን እየሰበከ ቢጋደል ኦሪት "እጠፋ እጠፋ": ወንጌል ደግሞ "እሰፋ እሰፋ" አለች:: በዚህ ጊዜ "ክርስትናን ለማጥፋት መፍትሔው ቅዱስ እስጢፋኖስን መግደል ነው" ብለው አይሁድ በማመናቸው ሊገልድሉት አስበውም አልቀሩ ገደሉት:: + እርሱ ግን ፊቱ እንደ እግዚአብሔር መልአክ እያበራ ፈጣሪውን በብዙ ነገር መሰለው:: በመጨረሻውም ስለ እነሱ ምሕረትን እየለመነ በድንጋይ ወገሩት:: ደቀ መዛሙርቱም ታላቅ ለቅሶን እያለቀሱ ቀበሩት:: +ይህች ዕለት ለቅዱስ እስጢፋኖስ በዓለ ሲመቱ ናት:: ቅዱሱ መጽሐፍ እንደሚል "ምሉዓ ጸጋ ወሞገስ-ሞገስና ጸጋ የሞላለት" [ሐዋ.፮፥፭ [6:5], ቅዳሴ ማርያም] ነውና የ፮ [6]ቱ ዲያቆናት አለቃና የ8ሺው ማሕበር መሪ ሆኖ ተመርጦ እንደሚገባ አገልግሏል:: በሰማይ ባለችው መቅደስም የሚያገለግለው በዚሁ ማዕረጉ ነው:: † 🕊  ቅዱስ ፊልያስ ሰማዕት  🕊 † ሰማዕቱ የነበረበት ዘመን ፫ [3]ኛው መቶ ክ/ዘ [ዘመነ ሰማዕታት] ሲሆን ቀምስ ለምትባል የግብጽ አውራጃም ዻዻስ ነበር:: ቅዱሱ እጅግ ጻድቅ በዚያውም ላይ ክቡርና ተወዳጅ ሰው ነበር:: የመከራው ዘመን ሲመጣ በቃሉ ያስተማራቸውን እንደ በጐ እረኝነቱ በተግባር ይገልጠው ዘንድ ወደ መኮንኑ ሔደ:: + ሕዝቡ በአንድነት ተሰብስበው ሳለ መኮንኑ ቁልቁልያኖስ ቅዱስ ፊልያስን ፬ [4] ጥያቄዎችን ጠየቀው:: ምላሾቹ ለእኛ ሕይወትነት ያላቸው ናቸውና እንመልከታቸው:: ፩. "የእናንተ እግዚአብሔር ምን ዓይነት መስዋዕትን ይሻል?" ቢለው "ልበ ትሑተ: ወመንፈሰ የዋሃ: ወነገረ ሕልወ: ወኩነኔ ጽድቅ: ዘከመዝ መስዋዕት ያሠምሮ ለእግዚአብሔር-እግዚአብሔርን ትሑት ልቦና: የዋህ ሰብእና: የቀና ፍርድና ቁም ነገር ደስ ያሰኘዋል" ሲል መለሰለት:: ፪. "የምትወዳቸው ሚስትና ልጆች የሉህም?" ሲለው ደግሞ "እምኩሉ የአቢ ፍቅረ እግዚአብሔር - ከሁሉ የእግዚአብሔር ፍቅር ይበልጣል" አለው:: ፫. "ለነፍስህ ትጋደላለህ ወይስ ለሥጋህ?" ቢለው "ለ2ቱም እጋደላለሁ:: አምላክ በአንድነት ፈጥሯቸዋልና:: በትንሳኤ ዘጉባኤም ይዋሐዳሉና" ብሎታል:: ፬. "አምላካችሁ የሠራው ምን በጐ ነገር አለ?" ብሎትም ነበር:: ቅዱስ ፊልያስ መልሶ: "አስቀድሞ ፍጥረታትን በጥንተ ተፈጥሮ ፈጠረ:: በሁዋላም በሐዲስ ተፈጥሮ ያከብረን ዘንድ ወርዶ ሞተልን: ተነሣ: ዐረገ" ቢለው መኮንኑ "እንዴት አምላክ ሞተ ትላለህ!" ብሎ ተቆጣ:: ቅዱሱም "አዎ! በለበሰው ሥጋ ስለ እኛ ሙቷል" ብሎ እቅጩን ነገረው:: + ወዲያውም "እስከ አሁን የታገስኩህ በዘመድ የከበርክ ስለሆንክ ነው" ቢለው ቅዱሱ መልሶ "ክብሬ ክርስቶስ ነው:: መልካምን ካሰብክልኝ ቶሎ ግደለኝ" አለው:: በዚያን ጊዜ የሃገሩ ሰዎች "አትሙትብን! እባክህን ለመኮንኑ ታዘዘው?" ሲሉ ለመኑት:: + ቅዱስ ፊልያስ "እናንተ የነፍሴ ጠላቶች ዘወር በሉ ከፊቴ! እኔ ወደ ክርስቶስ ልሔድ እናፍቃለሁና" ብሎ ገሰጻቸው:: መኮንኑም ወስዶ ከብዙ ስቃይ ጋር ገድሎታል:: † 🕊   ቅድስት ሐና ነቢይት   🕊 † "ሐና" ማለት "የእግዚአብሔር ስጦታ" ማለት ነው:: እጅግ ከሚታወቁ ሴት ነቢያት አንዷ የሆነችው ቅድስት ሐና ከክርስቶስ ልደት ፲፻፩፻ [1,100] ዓመታት በፊት በዚህች ቀን እንደ ተወለደች ይታመናል:: ቅድስቲቱ ልጅ በማጣት ተቸግራ: ከጐረቤት እስከ ሊቀ ካህናቱ ኤሊ ድረስ ሽሙጥና ስድብን ታግሣ ታላቁን ነቢይ ቅዱስ ሳሙኤልን ወልዳለች::
Show all...
የስህተት ትምህርት ምን ምን ናቸው 1 የሥላሴን አንድነት እና ሶስትነት መካድ ዘፍ1፥26 ዮሃ 10፥30 2 መዳን በእምነት ብቻ ነው ብሎ ማሰብ ያዕ 2፥14 ያዕ 2፥17-20 3 በጥምቀት የስላሴን ልጅነት ማግኘት እንደምንችል መካድ ዮሐ 3፥1 ሐዋ 2፥38_39 ማቴ 28፥19_20 ሮሜ 6፥3 4 በቅዱሳን አማላጅነት አለማመን 1ቆሮ 9 ፥ 14 ራዕይ ዮሐ 6 ፥9 ሉቃ 16 ፥20 5 ንስሐን ለካህን መናዘዝ አስፈላጊ መሆኑን መካድ ኢያ 7፥ 1_19 ማር 1 ፥ 44 ሐዋ 5 ፥ 1 6 የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ፈራጅ እንጂ አማላጅ ኣለመሆኑን አለመረዳት ዮሐ 16፥26 ማቴ 25 -1_መጨረሻው መቼም ይሄን እያየ የሚሰናከል አይኖርም
Show all...
                          †                           🌼  [     የትሕርምት ሕይወት !     ]  🌼    ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን !                                🕊 [       ትእግስትን በተመለከተ  !    ] ------------------------------------------------ ምንም በመከራ ውስጥ ብንሆን ! " ጊዜውን አይተህ ተስፋ አትቁረጥ፡፡ ጠላት ለጊዜው መልካም መስሎ በሚታይ ነገር እንድትሳብ ይደክማልና፡፡ ስለዚህ ወንድሜ ሆይ ሥጋዊ ደስታን ከሚሰጡና ከትይንት ቤቶች ትርቅ ዘንድ ወደ እነርሱም ከመሳብ ራስህን ትጠብቅ ዘንድ እመክርሃለሁ። ወዳጄ ሆይ ! በእግዚአብሔር ደስ የሚልህ ሰው እንደ መሆንህ መጠን ሐዋርያው “አርነት ልትወጣ ቢቻልህ ግን አርነትን ተቀበል” ብሎአልና የሰው ባሪያ ከመሆን ወጥተህ ለክርስቶስ ባርያ ሁነህ ኑር፡፡ ለዚህም ሕይወት አርአያ ይሆኑ ዘንድ በብሉይ ኪዳን የነበሩ ቅዱሳን አሉ፡፡ እነርሱ በመከራ ውስጥ ቢያልፉም በሥራቸው ሁሉ ለእግዚአብሔር ታዘው የሚኖሩ ነበሩና ከአምላካቸው ቃል ኪዳንን ተቀበሉ፡፡ ከእግዚአብሔር አምላከ ዘንድ ቃል ኪዳንን የመቀበላቸው ምሥጢርም እርሱን በማምለክ መጽናታቸው ነው፡፡ ስለዚህ እኛም ከእነርሱ ጋር የመንግሥቱ ወራሾች የርስቱ ተሳታፊዎች እንድንሆን ምንም በመከራ ውስጥ ብንሆን እነርሱን አርአያ አድርገን ራሳችንን በቅድስና ሕይወት ልናመላልስ ይገባናል፡፡ " 🕊 [  ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ   ] †                       †                        † 🌼                    🍒                     🌼
Show all...
                           †                              [  🕊 ለእውነተኛ ፀሐይ መዝገቡ 🕊  ]   🌼▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🌼 " ለእውነተኛ ፀሐይ መዝገቡ የሆንሽ እመቤቴ ማርያም ሆይ በምድርም በሰማይም ዙርያ የክብሩ ደም ግባት ፣ ሙቀቱ ከአንቺ ተገኘ፡፡ የራሱንና የሕዝቡን ኃጢአት የሚያስተሰርይባት የሊቀ ካህናቱ መጋረጃ የሆንሽ የቅድስና ልብስ አንቺ ነሽ። በእርሷ የሚገለጥባት የቃል ድምፅም የሚሰማባት ኪሩቤልም ክንፋቸውን የሚያገናኙባት ፣ የእግዚአብሔር የጥበብ ማደሪያ ታቦት አንቺ ነሽ። በሃይማኖት ሰገነት የተኙ በሽተኞች የሚታጠቡባት ቀላይም አንቺ ነሽ። በዓለም ባሕር ስፋት አጥማጆች ነፍሳትን ለማጥመድ የጣሏት መረብ አንቺ ነሽ። " 🕊 [  እንዚራ ስብሐት   ] †                       †                      † 💖                    🕊                   💖
Show all...
                           †                            [ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ] ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [  በሁሉ በምልዐት የሚኖር ! ] -------------------------------------------------- " [ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ] ቀራጭ የነበረ ማቴዎስን ቢያምንበት ወንጌልን ፣ የሚጽፍ አደረገው፡፡ ዓሣ አሥጋሪ በነበረ በዮሐንስም በአደረ ጊዜ አንድነትን ሦስትነትን እንዲናገር አደረገው፡፡ ክርስቶስን ይሰድብ ፤ ክርስቲያንን ያሳድድ የነበረ ጳውሎስንም አምኖ ቢያገኘው ለአሕዛብ ሃይማኖትን የሚያስተምር ሐዋርያ አደረገው፡፡ ዳግመኛም ምርጥ ዕቃ አደረገው። [ ማቴ.፬፥፳–፳፫ ፣ ራእ.፲፱፥፲ ፣ ሐዋ.፩፥፩-፳፩ ፣ ገላ.፩፥፳፬–፳፬  ፣ ፩ጢሞ.፩፥፲፪–፲፯ ] እርሱ ስለ አደረባቸው ድኩማን ጽኑዓን ይሆናሉ ፤ አላዋቆች የነበሩትም ከጠቢባን ሁሉ ይልቅ አዋቆች ይሆናሉ ፤ ጳውሎስ ታማሚ ነበር ግን መንፈስ ቅዱስ ስለ አደረበት በለበሳቸው ልብሶች ለድውያን ድኅነትን የሚሰጥ ሆነ፡፡ ጴጥሮስም ሰውነቱን ታማሚ ነበር ነገር፡፡ ግን የመንፈስ ቅዱስ ፍጹም ሀብት ስለአደረበት በመንገድ ሲያልፍ ጥላው በአረፈባቸው ጊዜ ጥላው ድውያኑን አዳነ።  [ ሐዋ.፭፥፲፭-፲፯ ፣፲፱፥፲፩ ፤ ፪ቆሮ.፲፪፥፯-፲፫ ] ጴጥሮስና ዮሐንስ ድሆች ነበሩ፡፡ ወርቅና ብርም አልነበራቸውም ነገር ግን ሰውን ያከብሩ ነበር፡፡ ከወርቅ ከብር የሚበልጥ ጤናንም ያሰጡዋቸው ነበር። መፃጕዕ ብዙ ወርቅና ብርን ተመጸወተ ግን ጤና አላገኘም፡፡ ከጴጥሮስና ከዮሐንስ ሀብተ ፈውስን በአገኘ ጊዜ ምጽዋትን ከመቀበል ተከለከለ፡፡ ተነሥቶም እግዚአብሔርን እያመሰግ እንደ ዋልያ ፈጥኖ ሔደ። [ ሐዋ.፫፥፩-፲ ፣ ፱፥፴-፴፭ ] ዮሐንስ ከዚህ ዓለም ጥበብ ምንም ምን አያውቅም ነበር፡፡ ኅይለ መንፈስ ቅዱስ ስለ አደረበት ካዐዋቆች የሚበልጥ ብዙ ነገርን ተናገረ፡፡ [ዮሐ.፩፥፩-፲፰ ። ፫፥፱–፳፩ ፣ ራእ.፩፥፱ -፳ ] በሁሉ በምልዐት የሚኖር ይህ መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ በሚያምንበት በአንዱም በአንዱም ሁሉ ላይ እርሱ ኵለንተናው [ፍጹም አካሉ] አድሮ ይኖራል፣ እርሱ ሁለንታው በእግዚአብሔር አብ ፥ በእግዚአብሔር ወልድ ህልው ነው ፤ እስትንፋሳቸው ነውና። እንደ መልእክተኛ ታዝዞ ሀብትን የሚሰጥ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ነውና፡፡ ሀብትን ይሰጣል እንጂ እርሱ እንደ ወደደ ለሁሉ ክብሩን ያድላል ፤ በምልአት በሁሉ ያድራል ፤ በሥልጣኑም ጸንቶ ይኖራል። አሁንም በሰውነታችን እንዲያድርብን በዘመን ሁሉ ሀብቱን እንዳይከላክለን ተግተን እርሱን እንለምነው ፤ ለርሱ ፥ ለቸር አባቱ ፥ ለሚያድን ለመንፈስ ቅዱስ ለዘለዓለሙ ምስጋና በሚገባው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቸርነት አሜን። " [ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ ] ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን። †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
Show all...