cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

EPIGNOSIS TUBE🔔

#ሁሉን_በአንድ_ቦታ! የቻይናሉ አላማ፦ መንፈሳዊ፣ ማህበራዊ፣ ሳይኮሎጂካዊ ጉዳዮችን በጥልቀት መዳሰስ ነው። YouTube https://youtube.com/channel/UCSdC839xbH5IhEL_9H1O-VA Facebook page https://www.facebook.com/Epignosis-Tube-116304570206635/

Show more
Ethiopia10 088The language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
211Subscribers
No data24 hours
-17 days
-430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#ቤተልሄም_ተዘራ - ያነሳል - #Betty_Tezera - Yanesal - New mezmur Video - #ቤቲ_ተዘራ - #2023
Show all...
⚖ #ጠበቃ_ዳኛ_ ⚖ ================= [ #በሕግ_ባለሙያ_መብራቱ_በለጠ_ ] አንዲት ሴት በአንድ ወቅት አንድ ከባድ ወንጀል ፈጸመች፡፡ ይህም ወንጀል በፍርድ ፊት አቆማት፡፡ ወንጀሉ የዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት የሚያስፈርድ ነበር፡፡ በመሆኑም የፍርድ ሂደቱ በሚከናወንበት ወቅት ፊቷ በእንባ እየታጠበ ለይቅርታ ብትማጸንም ሰሚ ግን አላገኘችም፡፡ ፍርድ ችሎት ውስጥ የታደሙ ቤተሰቦቿ እና ወዳጅ ጓደኞቿ በእንባ ከመራስ ውጭ ምንም አማራጭ አልነበራቸውም፡፡ ነገር ግን በዚህ አስጨናቂ ወቅት እንድ ሰው ምስክሮች በሚቆሙበት ቦታ ላይ ቆሞ ፍርድ ቤቱን በመማጸን ውሳኔ ከመወሰኑ በፊት ስለዚህች ወጣት ሴት ዳኞቹን ይለምንና ይማልድ ጀመር፡፡ ጉዳዩ ከባድ ቢሆንም እርሱ ግን ያለ የሌለ ኃይሉን ተጠቅሞ በዚህች ሴት ምትክ ይሟገት ጀመር፡፡ ከብዙ ውጣውረድ እና ልፋት በኋላ ድካሙ ፍሬ አፍርቶ ልጅቱ በነጻ ተለቀቀች፡፡ ልጅቱም ጠበቃው ባደረገላት ነገር ተደንቃ በፊቱ ወደቀች፡፡ ከልቧም አመሰገነችሁ፡፡ ብዙም ሳይቆይ ይህቺ ወጣት ልጅ በሌላ ተመሳሳይ ወንጀል ውስጥ ተገኘች፡፡ ልክ የፍርድ ቤቱን በር አልፋ አይኖቿን ወደ ዳኞቹ ስታቀና ባለፈው እርሷን ከፍርድ ለማዳን ሲማጸን እና ሲማልድ የነበረው ሰው ዳኛ ሆኖ አገኘችው፡፡ ለካስ ያኔ ጠበቃ ሆኖ ሲሟገትላት የነበረው ሰው አሁን ዳኛ ሆኗል፡፡ ወጣቷ ይህ ሰው ዳኛ ሆኖ ስላገኘችው ደስ አላት፡፡ እንደገና መጣሁ በሚል መንፈስ ይመስላል፡፡ ሰውየው እጆቹን ወደላይ አነሳና ይህውልሽ ትናንት ጠበቃ ነበርኩ ለዚህ ነው አንቺን ለማዳን የተከራከርኩልሽ አሁን ግን ዳኛ ነኝ፡፡ እንደ ዳኛ ደግሞ ትክክለኛውን ፍርድ መፈጸም አለብኝ አላት፡፡ ልጅቱም አይኗ በእንባ እየራሰ ለመሆኑ አንተ ማን ነህ አለችው፡፡ እርሱም፡ የትናንቱ ጠበቃ የአሁኑ ዳኛ ነኝ አላት፡፡ ወዳጄ ዛሬ ኢየሱስ ጠበቃ ነው፡፡ ለጥፋትህ ሁሉ እየማለደ ወደ ሕይወት መንገድ ትገባ ዘንድ ስለአንተ ይማልዳል፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ ጠበቃ እንደሆነ አይቀጥልም ዳኛ ሆኖ የሚገለጥበት ወቅት ይመጣል፡፡ ቀኑም ቀርቧል። “እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ። ራዕይ 22:12 #Share to many Mebratu Belete Hegemony
Show all...
#የአምልኮ_ምሽት ተመለስ ወደ ቤት በማራናታ ኳይር ተጋባዥ አገልጋዮች : EXODUS SOUND ሕዳር 15/2016 ዓ.ም Join our social media: Telegram: t.me/BSKHC_HAWASSA Facebook: https://www.facebook.com/BethsidaKHCHawassa YouTube: https://youtube.com/@BSKHCTUBE
Show all...
ወርቁ ቢጠፋ፣ ሚዛኑ አይጥፋ! ዕቅበተ እምነት ክቡር አገልግሎት ነው፤ በተለይ የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ በተሳከረበት በዚህ ወቅት። ስክነትና ሚዛናዊነትን በሚጠይቀው በዚህ አገልግሎት ውስጥ የራሳቸውን ስሜት የእውነት ሚዛን አድርገው የሚያቀርቡና የሰዎችን ንግግር ከዐውድ ውጭ ጠምዝዘው እያቀረቡ የሚያወግዙ አንዳንድ የእቅበተ እምነት አገልጋዮች ግን ግራ ያጋቡኛል። አንዲህ ዐይነቶቹ ዐቃብያን፣ በተገኘው መንገድ ሁሉ ክርክሮችን የማሸነፍ፣ እንዲሁም የሌሎች አራሚ ከመሆን በቀር የመታረም ፍላጎት እንኳ አይታይባቸውም። የአገልግሎቱ ጠባይ ነው ሰዎቹን እንዲህ የሚያደርጋቸው? ወይስ ከመጀመሪያውም እንዲህ ዐይነት ሰዎች ስለሆኑ ነው አገልግሎቱን የመረጡት? ወይስ ዘመኑ ማኅበራዊ ሚዲያ የነገሠበት መሆኑ የሚፈጥረው ክፍተት ነው? ይህን የምለው በከንቱ አይደለም። በቅርቡ ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን፣ ከመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ጋር የተገናኘ ቃለ ምልልስ አካሂዶ ነበር። በዚያ ቃለ ምልልሱ ውስጥ “ወደ ኢየሱስ አይጸለይም” በማለት ተናግሯል። መጋቢ ዳዊት ፋሲል ደግሞ ስለ ሥላሴ ሲያስተምር፣ “በወልድ የሆነ እንጂ ከወልድ የሆነ ነገር የለም” የሚል ነገር ተናግሮ ነበር። በዕቅበተ እምነት ከሚያገለግሉ ወንድሞች መካከል አንዳንዶቹ እነዚህን ሁለት አገልጋዮች ለማውገዝና ለማስወገዝ የሄዱበት መንገድ ግን እጅግ አስደንጋጭና አሳሳቢ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። በመጀመሪያ ደረጃ፣ ሁለቱ አገልጋዮች ስሕተታቸውን በአግባቡ ቢነሣና ትምህርት ቢሰጥበት አግባብ ስለ መሆኑ ላሰምርበት እፈልጋለሁ። እዚህ ላይ ምንም ዐይነት ግርታ የለብኝም። ከዚያ ውጭ ግን፣ ያልተባለ ነገር ጎትቶ በማውጣት መናገር ግን ጭካኔ ነው። ለመሆኑ ወ/ዊ ያሬድ ወደ ኢየሱስ እንደማይጸለይ በመናገሩ፣ “ወልድ በራሱ ፍጹም እግዚአብሔር መሆኑን ይክዳል” ማለት ይቻላል? እንደው ስለ ያሬድ ምንስ ብናስብ፣ “የኢየሱስን ፍጹም አምላክነት ይክዳል” ለማለት ለማስባል የሚበቃ ነገር ተናግሯል? እውን ያሬድ ጥላሁን ለኢትዮጵያ ወንጌላውያን የማይታወቅ ሰው ሆኖ ነው? ከ30 ዓመታት ላላነሠ ጊዜ የምናውቀውንና ለብዙዎች ምሳሌ መሆን የሚችለውን ሰው በዚህ አንድ ዐረፍተ ነገር ብቻ አርዮሳዊ አድርጎ ማቅረብ ጭቦ አይሆንም? ለስንትና ስንት ዓመታት እውነተኛውን ወንጌል ተሸክመው የለፉ ሰዎችን ድመት ልጆቿ እንደምትበላ እየበላናቸው መጓዝ የሚያዋጣ አካሄድ ነው? ሌላው ደግሞ የመጋቢ ዳዊት ፋሲል ጉዳይ ነው። ዳዊት በቅርቡ በማኅበራዊ ሚዲያ የተሰራጨ አጭር ቪዲዮ ነበረው። የቪዲዮው ዋና ጭብጥ ምንድን ነው? ከተባለ፣ ሥላሴ ማለት ለየብቻቸው የሚንቀሳቀሱ ሦስት አምላኮች አለመሆናቸውን ማስረዳት ነበር። እናም አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላካዊ ባሕርይን የሚጋሩ ሦስት አካላት እንጂ ሦስት አማልክት አለመሆናቸውን ሲያስረዳ የተጠቀመውን ትንተና ስሕተት ሊሆን ይችላል። አስተምህሮውን ከዐውዱ ውጭ ወስዶ፣ “እያንዳንዱ የሥላሴ አካል በራሱ ፍጹም እግዚአብሔር መሆኑን ይክዳል” ማለት ግን ዕብደት ነው! እያስተማረ የነበረው እኮ ስለ ሥላሴ ነው። ወልድ አምላክ መሆኑን እያስተማረ ነበር! ታዲያ በምን ሒሳብ ነው ዳዊት አርዮሳዊ የሚሆነው? ለመሆኑ በዚህ ደረጃ ሰዎችን አላግባብ መኮነን እግዚአብሔርን ያስከብራል? እባካችሁ በዕቅበተ እምነት የምታገለግሉ ወገኖች ልብ ግዙ። ስለ እውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም አታድርጉ። አለዚያ በሥላሴ አስተምህሮ ላይ ያላቸውን ግልጽ አቋም በምናውቃቸው ሰዎች ላይ እንዲህ ዐይነት ግልጽ በደል እየፈጸማችሁ፣ ነገ በሌሎች ጉዳዮች ላይ እንዴት እናምናችኋለን? ሁላችንም እንሳሳታለን። ይህ የዕቅበተ እምነት አገልጋዮችንም ይጨምራል። ያኔ ስሕተታችሁ ተለጥጦ፣ ንግግራችሁ ከዐውዱ ውጭ ተጠምዝዞ፣ አላግባብ ብትወገዙ አግባብ  ይሆናል? ሚዛኑን እንዲህ ካበላሻችሁት ታዲያ ነገ  እንዴት ልትመዘኑ ነው? ወደዚህ አገልግሎት ለመምጣት የሚፈልጉ ወጣቶችስ ማንን በምሳሌነት ይመልከቱ? እባካችሁ ሚዛኑን እንኳ ለትውልድ እናስተላልፈው! ወርቁ ቢጠፋ፣ ሚዛኑ አይጥፋ! ©ምስባኮ ጳውሎስ- Paul's  pulpit ጳውሎስ ፍቃዱ
Show all...
Ayibekam /አይበቃም/Singer Muski Markos /#ethiopiangospelsong Song/#protestant_mezmur/2023
Show all...
አመልካለሁ ይህንን ታላቅ ጌታ| ሰባተኛው የማህሌት ፕሮግራም | New Gospel song 2023 | Mahlet Institute of Worship and Music
Show all...
BEREKET TESFAYE አቅጣጫ ቢስ AKITACHA BIS በረከት ተስፋዬ Cover MULUKEN MELESE አቅጣጫ ቢስ
Show all...
" ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፕላን እየበረረ የነበረው ሰውዬ የበረራ አስተናጋጇ በሰጠችው ጥቆማ መሰረት የአውሮፕላኑ መጸዳጃ ቤት ውስጥ መጠቀም ይጀምራል ታዲያ በመሐል አንዲት ቀይ ማብሪያና ማጥፊያ የምትመስል ነገር ያይና ነካ ያደርጋታል በዚህ ሰዓት አውሮፕላኑ በሐይል መንገጫገጭና ወደ ጎን ማጋደል ይጀመራል ሰውዬውም ደንግጦ ወይኔ ሳላውቅ የማይነካ ነገር ነክቼ ሕዝብ ጨረስኩኝ ብሎ በነካት ቀይ ነገር ይጸጸታል ከጥቂት ቆይታ በኃላ ግን መንገጫገጩ ይቆምና ከመጸዳጃ ቤቱ ይወጣል። ሁሉም ሰው አንተ የማትረባ ጨርሰኸን ነበር እኮ ብሎ ይጮህብኛል ብሎ ቢጠብቅም ዞር ብሎ ያየው ሰው እንኳን የለም።      መቀመጫው ላይ እንደደረሰም አጠገቡ የተቀመጠውን ሰው ቀስ እና ስቅቅ ብሎ ይቅርታ የማይነካ ነገር ነክቼ ጨርሻቹ ነበር አይደል? ይለዋል  ሰውዬውም አረ በፍጹም እንደዛ እንዳታስብ ይህን ያሕል ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮች እኮ መፀዳጃ ቤት ውስጥ አይደረጉም ካፒቴኑ ያለበት ክፍል ውስጥ ነው ያሉት። አጋጣሚ ነው ትንሽ የአየሩ ሁኔታ አስቸጋሪ ስለሆነ ነው አውሮፕላንኑ የተንገጫገጨው ይለዋል። "      ብዙ ጊዜ ሰዋች እንደዚ ያስባሉ የሆነች ነገር ነክተው ሕይወትህን የሚያንገጫግጩ እና መጨረሻህን የሚወስኑ ይመስላቸዋል የረሱት ነገር ቢኖር ይህን ያክል ጥንቃቄ የሚፈልገው ነገር እነሱ አጠገብ ሳይሆን የሕይወትህ ካፒቴን ጋር እንዳለ ነው። እንደዛማ ባይሆን ኖሮ ቀይዋን ነገር እየጠጠቀጠቁ ሕይወታችንን መንገጫገጭ ብቻ ያደርጉት ነበር። ምስጋና ለካፒቴኑ ይሁንና እንደዚሕ አይነት ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮችን በሱ እጅ ብቻ እንዲገኙ አድርጓቸዋል።   ዋና ነገሬ ያለው እግዚአብሔር ጋር ነው በማለት በእረፍት እንድንኖር እግዚአብሔር ይርዳን። ©Birukti Alemayehu
Show all...
Eneho Eyesus "እነሆ ኢየሱስ" by Dawit Getachew
Show all...
ፓስተር አገኘሁ ይደግ - ጠላት ስማ እፈር እፈር Pastor Agegnehu Yideg- Tlat Sima! Efer Efer
Show all...