cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የፍቅሩ ምርኮኞች

ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል መከራ ፥ወይስ ጭንቀት ፥ ወይስ ሰደት ፥ ወይስ ራብ ፥ወይስ ራቁትነት ፥ ወይሰ ፍርሃት ፥ ወይስ ሰይፍ ነዉን? ሮሜ 8፥35 እሱ መቼ በፈረስ አንገት በጦር አንደበት ሰዉ ይማርክና ሰይፍ ሳይመዝ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ደሙን አፍስሶ ዉድ ህይወቱን ከፍሎ የፍቅሩ ምርኮኞች አደረገን እንጂ ማርኮናል ምርኮኞቹ ነን

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
186Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
ወደ እግዚአብሄር መቅረብ🚶‍♂️ 1.ፈቃድ 📌ወደ እግዚአብሄር ለመቅረብ በሚደረግ ጉዞ የመጀመሪያው እርምጃ ፈቃድ ነው 📌እግዚአብሄር አምላክ ለሰው ልጆች ከሰጣቸው ድንቅ ስጦታዎች መካከል አንዱ የሆነው ፈቃድ የሰው ልጆች በክፉውም ይሁን በመልካም መንገድ እንዲጓዙ የራሳቸውን ውሳኔ የሚጠቀሙበት አቅም ነው 📌 እግዚአብሄር አምላክ እርሱ ሉአላዊና ሀያል አምላክ ቢሆንም የስው ልጆችን ፈቃድ ግን የማይጋፋ አምላክ ነው 📌እግዚአብሄር በሰዎች ህይወት ለመገለጥ የሚፈልገው የሰውን ፈቃድ ብቻ ነው ሰው ፈቃዱ ወደ እግዚአብሄር ከሆነ እግዚአብሄር ወደ እርሱ ይመጣል 📌ፈቃድን ለእግዚአብሄር መስጠት ወደ እግዚአብሄር በመቅረብ ውስጥ የመጀመሪያው መንፈሳዊ እርምጃ ሲሆን እግዚአብሄርን ወደ ሰው በማምጣት ቅርብ ያደርገዋል 👉ዛሬ በዚህ ሀሳብ የምናደርገው አንድ ነገር ነው በቅን ልብና በየዋህነት አብረን ይህን ፀሎት በመፀለይ ፈቃዳችንን ፈፅመን ለእግዚአብሄር እንዲሆን እንሰጠዋለን 🙏በሰማይ የምትኖር አባቴ ሆይ አመሰግንሃለው እኔ የአንተ ነኝ አንተ ራስህ ፈጥረኸኛል ቅዱስ እጆችህ ሰርተውኛል አንተ አምላኬ ነህ ይህን አምኛለሁ ዛሬ ደግሞ ፈፅሜ ፈቃዴን ልሰጥህ እወዳለሁ ፈቃዴን ስጋ አለምና ሰይጣን አይጠቀሙት ላንተ ብቻ እንዲሆን ፈቅጄ በእጆችህ አደራ አሳልፌ ሰጥቼሀለው አንተ ክበርበት ለዘላለም አሜን! ♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️ ♻️@yefkrumrkognoch ♻️ ♻️@yefkrumrkognoch ♻️ ♻️ ♻️ ♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️
Show all...
የሆነ ወንጀል ሰርተህ ብትከሰስና ከፍርድ ወንበር ፊት ቆመህ ከሕጉ አንፃር መከራከር ባትችል ስላንተ እንዲከራከርልህ ጠበቃ በገንዘብ ትቀጥራለህ። ☑️ጠበቃ ማለት አንተን ተክቶ የሚቆም "ምትክ" ማለት ነው። አንተ ዝም ትልና ጠበቃህ በዳኛው ፊት ቆሞ ያደረከውን "አላደረገም" እያለ or የሰራኀውን ስራ "ከሕጉ አንፃር ልክ ነው፤ መከሰስ የለበትም" እያለ ስላንተ ሽንቱን ገትሮ ይከራከርልሃል። 👉ይሄ ሁሉ ሆኖ ግን እንደ አጋጣሚ ጠበቃህ ቢሸነፍ "ወንጀለኛ" ተብሎ የሚቀጣው እሱ ሳይሆን በእርሱ ውስጥ የተደበቅከው አንተ ነህ። ጥብቅና በሰው አእምሮ ይሄን ያክል ብቻ ነው። 💓 💝 💓 💝 💓 💝 💓 💝 💓 "በድላችኋል ፡ አጥፍታችኋል" ተብለን በከሳሽ ዲያብሎስ ተከሰን ከፍርድ ወንበር ፊት ቆምን። አንዳንዶች ጠበቃ እንዲሆንላቸው የበግ፡ የዋኖስ፣ የፍየል፣ የኮርማ… ደም በገንዘባቸው አመጡ፤ ነገር ግን የነዚህ ደም ተከራክሮ ማሸነፍና እነርሱን ነፃ ማውጣት አልቻለም። 😔እኔ ግን ይህን ደም እንኳን ይዤ ለመግባት አልታደልኩም ነበር። 😇እና በዚህ ሁሉ መኃል አንድ ከነጭራሹ የማላውቀው እርሱ ግን ጨርሶ የሚያውቀኝ ከፍቅር የሆነ ጠበቃ "እኔ ልከራከርልህ" ብሎ ከፍርድ ወንበር ፊት ቆመ። ከሳሽ ሰይጣንም ክሱን ቀጠለ "አመንዝሯል፣ ተሳድቧል፣ ዘርፏል፣ ሰው ገሏል…" እያለ በእኔ ያየውን ሁሉ ለፍርድ ቤቱ አንድ በአንድ ተረከላቸው። ይናገር የነበረው ሁሉም እውነት ነበር። የኔ ጠበቃ ግን ዝም ብሎ ይሰማ ነበር፤ እንደውም ስለኔ በመከራከር ፈንታ "እውነት ነው፤ አጥፍቷል" እያለ የከሳሼን ቃል ያፀናው ነበር። የሚሆነው ነገር ግራ ቢያጋባኝም ለካ ደግመኛ እንዳልከሰስ ፈልጎ ነው። 📍እናም በመጨረሻ ፍርድ ቤቱ የሀጢአቴን ብዛት አይቶ የሞት ፍርድ ፈረደብኝ። ፍርዴን ለመቀበል እራሴን አሳምኜ ሳለሁ ጠበቃዬን "ልሞት ነው እኮ በቃ" ስለው "ጠበቃህ እኮ ነኝ" አለኝ። 💔ለካስ የእርሱ ጥብቅና ከፍርድ ወንበር ፊት ቆሞ እስከመከራከር ብቻ ሳይሆን፤ ሞት እኔን ፈልጎ ሲመጣም "ጠበቃው ነኝ" ብሎ እኔን ተክቶ እስከመጋፈጥ ድረስ ነው። ☑️በቆምኩ ሰዓት አቅፎ በወደቅኩ ጊዜ ከውስጡ ላያወጣኝ ☑️በወደቅኩ ሰዓት ይዞ በቆምኩ ጊዜ ላይተወኝ ምትኬ ሆነልኝ። ማንም አውጥቶ ላይቀጣኝ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ተደብቅያለው። ሞቱን ሳይሆን ሞቴን ሞተልኝ። ሕይወቴን ሳይሆን ሕይወቱን ሰጠኝ። በመጨረሻም "ይህን ሁሉ የምትሆንልኝ ለምንድ ነው?" ብዬ ጠየኩት። "ስለወደድኩህ ነው!" ብሎ መለሰልኝ። አሁንም መልሼ "ለምን ወደድከኝ" አልኩት። "ስለወደድኩህ" ብሎ አቀፈኝ። ጭራሽ የወደደኝ ሁላ ስለወደደኝ ነው። 🙏ፀጋ ይብዛላችሁ!!!!🙏 ⛓️ @yefkrumrkognoch⛓️ ⛓️ @yefkrumrkognoch ⛓️
Show all...
ይታወቅልኝ ዘማሪ በርከት ተስፋዬ Share♻️share @yefkrumrkognoch @yefkrumrkognoch
Show all...
ተቀሰቀሰ ዘማሪ በረከት ተስፋዬ New Protestant song 🕐5:42 💾5.3MB Share♻️share @yefkrumrkognoch @yefkrumrkognoch
Show all...
ጩኽ ✍ መፅሐፍ ቅዱስ በግልፅ ወደ እግዚአብሔር መጮኽ እንደለብን ይናገራል ነገር ግን እኛ ከመጮ ይልቅ ዝምታን መርጠን ተቀምጠናል ✍ ከእዚህም የተነሳ እግዚአብሔርም ዝም አዳለን ነዉ ምክንያቱም ወደ እሱ እንድንጮኽ ስለ ተናገረ እስካል ጮኸን ደረስ ዝምታዉ ይቀጥላል ✍እግዚአብሔር ኤርምያስ ገና በግዞት ቤት አደባባይ ታስሮ ሳለ እንዲ አለ ወደ እኔ ጩኽ እኔም እመልስልሃለሁ አንተም የማታዉቀዉን ታላቅና ሀይለኛ ነገርን አሳይሃለሁ (ኤር 33፥3) 🔴ስለዚህ ብትጮኽ ወይም ብትጣራ ሶስት ነገሮችን እንደሚያደርግልህ ቃል ገብቶልካል ▪️ይመልስልሀል፣ይናገርሀል ▪️አዲስን ራዕይ ይሰጥሀል አንተም ክብሩን ታያለህ ▪️አዲስን እዉቀት ይሰጥሃል የማታዉቀዉን አዲስ ነገር ያሳዉቅሀል 🔴 ዛሬ ላይ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር የምጮበት ብዙ ጉዳዮች አለን ስለዚህ የሀገሬ ልጆች እያሰማቹ ከሆነ ስለ ሀገራችን ጉዳይ እንጩ እየፈሰሰ ያለዉ የሰዉ ደም እንዲቆም እየጠፋ ያለዉ የንፁሃን ህይወት @yefkrumrkognoch @yefkrumrkognoch
Show all...
ስቀለው ስቀለው ይሉታል ሊሰቅሉት ለካ አልገባቸውም ገለው እንደሚያድኑት ጩኸታቸው ሁሉ የሞት ምኞት ሆነ ክፋት ግብራቸው ጠብን አሰፈነ አውርደው አውርደው እሚል ከቶ ጠፋ የሀጥያታቸው ጥግ ከበፊቱ ሰፋ ይህን የተረዳው ይህን ያስተዋለው መስቀል ላይ ሚወጋው አያውቁም እና ይቅር አይችሉም እና ፍቅር ብሎ እርቅን አሰፈነ ለኔ ተወዳጅቶ መሞትን ወሰነ ከፍታ ባለው ገደል ሰጠመ ለኔ ተሰቃይቶ አለ ተፈፀመ ነብሴን ጨፈለ‘ኳት ስጋዬ አስገድዶኝ ለኔ ብሎ ሲሞት ለእርሱ መኖር ከብዶኝ By #Nathan_Ermiyas 👉 @UniqueDY Share share share share share ⛓️ @berbantefeta ⛓️ ⛓️ @berbantefeta_bot ⛓️
Show all...
በአሁኑ ዘመን የወጣቶች እርድና መልኪያቸው በጣም የሚያስጠላ ነገር ነው አንድ ወጣት አራዳ ነው ከተባለ ጫት ስጋራ መጠጥ አደንዛዥ እፅ የተለያዩ ሴቶች ጋር ዝሙት መስራት ከቻለ አለም ይህን ወጣት አራዳ ትላለች።😭😭 ይገርማል ይች ዓለም የሰውን ማንነት ልክ እንደ ሰይጣን ትደብቃለች። አንድ ሰው ሀብትና ዝና ካገኘ በቃ አንተ አሁን ትክክለኛ ሰው ሆነሃልና በዚህ ቀጥልበት እያለች የሞትን ሰፈር ትጠቁማለች። ሀብት ዝና እውቀት ይህን ሁሉ ያገኘ ሰው ዓለም አጨብጭባ አሁን አንተ ሰው ሆነሃል ትላለች። አይደለም ዓለም ውሸቱዋን ነው ዋናውን ነገር ለሰው ልጅ እንዲሰወር አድርጋለች። ታዲያ ምንድነው ይህ ምስጢር?? ሰው መሆን ክርስቶስ ኢየሱስ ማወቅ ነው። ሰው መሆን የመዳንን መንገድ ማወቅ ነው። ሰው መሆን ክርስቶስን መቀበል ነው ። ሰው መሆን ከዚህ ጀምሮ ወደ ሌላ ነገር ደረጃ ይገባል እንጂ ከሀብት ከእውቀት ከዝና አይጀምርም ሰው መሆን። አንድ ክርስቲያን አራዳ ነው የሚባልበት ነገር ደግሞ ምን ይሁን🙄🙄??? ➡ለመንፈሳዊ ነገር ጊዜ መስጠት ➡ዘወትር በመንፈስ መፀለይ ➡ዘወትር በመንፈስ መዘመር ➡የክርስቶስን ፍቅር ማሰብ ማሰላሰል ➡ከዝሙት መሸሽ ➡ኢየሱስን ዘወትር መጠበቅ ብዙ ነገር ይቀጥላል .................... ሰው የመሆን አቅም አንድ ብቻ ነው ኢየሱስ ክርስቶስ እንደግል አዳኝ አርጎ መቀበል ከዛ ሰው ሆነህ መመላለስ ትጀምራለህ። ሰው የመሆን ምልክት ሆነ መለኪያ ሀብት❌ እውቀት❌ ዝና❌ አይደለም ክርስቶስ ኢየሱስን ማወቅ ነው የኢየሱስ መሆን ነው @yefkrumrkognoch @yefkrumrkognoch
Show all...
ያላንተ እንዴት ዘማሪ ኤፍሬም አለሙ 🕐3:45💾3.4mb Share ♻️share @yefkrumrkognoch
Show all...
ኢዮብ አሊ new mezmur 🕖6:27 💾5.0MB Share 🔄share @yefkrumrkognch
Show all...
(መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ምዕ. 3) ---------- 1፤ ሌሊት በምንጣፌ ላይነፍሴ የወደደችውን ፈለግሁት፤ፈለግሁት አላገኘሁትም። 2፤ እነሣለሁ በከተማይቱም እዞራለሁ፥ነፍሴ የወደደችውንበጎዳናና በአደባባይ እፈልጋለሁ፤ፈለግሁት አላገኘሁትም። 3፤ ከተማይቱን የሚዞሩት ጠባቂዎች አገኙኝ፤ነፍሴ የወደደችውን አያችሁትን? አልኋቸውም። 4፤ ከእነርሱም ጥቂት እልፍ ብዬነፍሴ የወደደችውን አገኘሁት፥ ያዝሁትምወደ እናቴም ቤት ወደ ወላጅ እናቴም እልፍኝእስካገባው ድረስ አልተውሁትም። ጥብቅ ማድረግ እንደማግኔት
Show all...
. ለምን ለማን ሞተ ገጣሚ ጌታያውቃል |የግጥም ጊዜ| ✟ @Markengeta ✟ ✟ @Markengeta ✟ ✟መልካም ፋሲካ✟
Show all...
አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ ━━━━━━━━━━━━ ➠ TITLE: "ኢየሱስ የእግዚአብሔር በግ" ➠ GENRE: New Teaching ➠ Quality: mp3 ➠ SIZE: 97.8 Mb ➠ TIME: 56:33 ➠ CHANNEL : @marsilchannel ━━━━━━━━━━ ➠share link:t.me//marsilchannel
Show all...
እንደ ሰማይ ሩቅ አድረገሽ የምታስቢው አምላክ እንደ እስትንፋስሽ ቅርብ ቢሆንስ? - ካንቺ ውጪ የምትፈልጊው አምላክ በአንቺ ውስጥ ሆኖ እየፈለገሽ ቢሆንስ? - ጨረቃ እና ጸሐይ የሚሰግዱለት እንዲሁም እልፍ አእላፍ መላዕክት የሚያመሰግኑት አምላክ ባንቺ ውስጥ ነው:: - እስከ ዛሬ የአምላክን ፍቅር ካልቀመስሽ ካንቺ ውጪ በማይገኝበት በመፈለግሽ ነው::እግዚአብሔር ባንቺ ልብ አዳራሽ ያለና የሚኖር አምላክ ነው::እንቺ በሱ ልብ እናዳለሽ እርሱም ባንቺ ልብ ይኖራል:: - በልብሽ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ ከጠፋ የክፋት: የቅናት: የፍርሃት: የጥላቻና የሐጢያት ሀሳብ ስለበዛ ነው::የአምላክን እውነተኛ ሐይል: ውበትና ፍቅር ለመቅመስ? ልብሽ በይቅርታ ሳሙና ይታጠብ:: - መፈሳዊነት ውስብስብ የህግ ጨዋታ አይደለም::መንፈሳዊነት የልብሽን መንፈስ ከአምላክ መንፈስ ጋር በፈቃድ የማገናኘት ጨዋታ ነው::መንፈሳዊነት ከዓለም ችግሮች ሁሉ መውጪያ ቀዳዳ ነው:: - በአለም ነገር ከአለም ችግር ያመለጠ አንድም ሰው በአለም ታሪክ የለም::በመንፈስ ግን ብዙ ተዓምራት እንደሚሆኑ ስምተናልም አይተናልም:: - ያለን አንድ ሐይል መንፈሳዊነት ነው::እርሱም የፈጠረን አምላክ ሐይል ነው::የሚገኘውም በእኛ ልብ ውስጥ ነው::ይህ የወደድነው በጎ ስኬት እንድንፈጥር የሚያስችል ሐይል ነው::በጎ ልብ መያዝ ይህንን ሐይል ለመጠቀም ቁልፍ ነው:: - መልካም እንሁን:: መልካሙ የአምላክ መንፈስ በልባንችን ይፍሰስ::ከራሳን አልፎ ለአለም ይተርፋል:: ©#manyazewaleshetu @marsilchannel ❇️
Show all...
ለሁሉም ችግርሽ አንድ መፍትሄ አለ::እግዚአብሔር ይባላል::ኦርጅናሉ አባትሽ እሱ ነው::ስምሽንም ፍቅር ብሎታል::ቤተሰቦችሽ ያወጡልሽ ጊዚያዊ ስም ነው::ከሁሉም አስቀድሞ የሚያውቅሽ እርሱ ነው::አንቺ እና እርሱ አንድ ናችሁ::ከእስትንፋስሽ በላይ ቅርብ ነው::የምድሩም የሰማዩም ህይወትሽ ጥራቱ የሚወሰነው ከእርሱ ጋር ባለሽ ግንኙነት ነው::ችግርሽን እርሺው::ስለአለም ህይወት አታስቢ::ቤተሰቦቼ: ትምህርቴ: ቢዝነሴ: ውበቴ: ዝናዬ...ወ.ዘ.ተ እያልሽ እትጨነቂ::እንቺ እሱን ብቻ አስቢ እርሱ ደሞ ስለአንቺ ብቻ ያስባል::ቤተስቦችሽን ይጠብቃል::ልጆሽን ይመግባል::ሀብትሽን ይባርካል::ጤንነትሽን ያበዛል::እርሱ የሚያስፈልሽን ሁሉ ያውቃል::የአናትሽን ፀጉር ቁጥር ሳይቀር ያውቃል::ያንቺ አንድ ሀላፊነት በሁሉም ሰዓት እና ቦታ እርሱን ማውቅ ነው::አሁን ባለበበት አለ::ካለእርሱ ምንም ነገር የለም::ፍጥረት ሁሉ የሚኖረው እርሱ ስላለ ነው::መገለጫው ደሞ ፍቅር ነው::ልብሽን ከህመም ያሳርፋል::እንባሽን ሁሉ ያብሳል::በመንገድሽ ሁሉ ጠባቂ መልዓክትን ይልካል::የቱንም ያህል ብታጠፊ አይተውሽም::በየትኛውም ሁኔታ አይለይሽም::እንቺም አትለይው::ከሁሉ አስቀድምሽ አስቢው::ሌላውን ሁሉ ይሰጥሻል::የፈጠርሽ አምላክ "ልጄ ሆይ ነይ!" ይልሻል::ለምን አትቀርቢውም? በሐጢያት መጨቅየት አይበቃሽም? በልብሽ ያለው ክፋት እና ይቅር አለማለት አላቃጠልሽም? እርሱ ሽክሙ ቀላል ነው::ለሚቀርቡት ሁሉ ቀለቡ ፍቅር ነው:: #manyazewaleshetu
Show all...
🔮 💐#ዋና_ያማራት_ጨው💐 *ከእለታት አንድ ቀን ጨው ዋና መዋኘት አምሯት ከምትጠቅምበት ማጀት(ማድቤት) ወደ ማትጠቅምበት አደባባይ ወጣች አሉ ወደ ወንዝም ወረዳ እንደ ድንጋይ በውሃ ወስጥ ልንከባለል አለች ከድንጋይ በምን አንሳለው ብላ ማነስ ጀመረች የምትበልጥ ሆና ሳለ ከእኩልነት ጀመረች "ጨው አኩል እሆናለሁ ብላ ወደ ድጋይነት ዝቅ አለች"። *ወደጆቼ የምትመኙትን ትበልጡታላችሁ "የሆናችሁትን የሚያክል የምትሆኑት ነግር የለም" ጨው ያልተረዳችው ትልቅ ቁም ነገር እንደ ድንጋይ ጠጣር እንጂ ድንጋይ አለመሆኑአን ነው። ፎክራም አልቀረችም ገባች "በአልጫ ውስጥ እንጂ በውሃ ውስጥ እንደማትጣፍ አልገባትም" የጨው ትልቁ ስተቷ በምትጣፍጥበት ቦታ አለመሟሟቷ ነው። *በጣም የገረመኝ የአካባቢው ሰዎች ጨው የሟሟችበትን ውሃ ሲቀምሱ ጨው ጨው ይላል እያሉ አቅረው ተፋዎት በአልጫ ውስጥ ስትጣፍጥ እያሉ እንዳላጣጣሙአት በውሃ ወስጥ ሲያገኟት ሲጎመዝዝ እያሉ አስወገዱአት ጨው ስለሆነች ብቻ የምትጣፍጥ መስሉአታል ጨው የሚጣፍጠው ጨው ስለሆነ ብቻ ሳይሆን አልጫ ውስጥም ሲገባ ጭምር ነው ። #ስለዚህ_ተወዳጆች *በምናጣፍጥበት ቦታ እንግባ፤ የሚያሸልመንንም እንስራ፤ እንደ ጥሪያችን እናገልግል፤ እንደ መክሊታችን እናትርፍ፤ ድርሻችንን እንለይ ። ይኸው ጆሮ ካላየሁ ብሎ የሚሰማ ጠፍቷል እግር ካልሰማሁ ብሎ መሄድ አቅቶናል። እግሮች እንሂድ፤ አይኖች እንይ፤ ጆሮዎች እንስማ። የዛኔ አልጫ ውስጥ እንደገባችው ጨው እንጣፍጣለን የምንጣል ሳይሆን የምንጥም እንሆናለን። ✍pheNi " እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም።" (የማቴዎስ ወንጌል 5:13) በምንመርበት ውሃ ውስጥ ሳይሆን በምናጣፍጥበት አልጫ ውስጥ እንግባ! 🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁 🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁 *SHARE* 💖💖💖💖💖💖 @yefkrumrkognoch
Show all...
‼️‼️‼️‼️‼️የመጀመርያ አመት እና የፍቅር ግንኙነት‼️‼️‼️‼️‼️‼️  እንዲህ አምናለሁ "ነፃነት እና ውሀ አንድ ናቸው እያሳሳቁ የመውሰድ ክህሎት አላቸው።" ከቤተሰቦቻቹ ጋር በነበራችሁ ቆይታ ቁጥጥር የበዛባችሁ እና የት ገባክ/ሽ የት ወጣክ/ሽ እየተባላችሁ አድጋችሁ ከሆነ እመኑኝ ወደ ጊቢ ገብታችሁ የሚያጋጥማችሁ ደስታ ሊያሳብዳችሁ ሁላ ይችላል። እንዴት ማለት ጥሩ... "ጓኛዬ ከቤተሰቦችሽ ጋር እያለሽ ስልክሽ በጠራ ቁጥር ደንብረሽ ወደ ጓዳ ሮጠሽ ገብተሽ ትመልሺ ነበር ብንል እመኚኝ ጊቢ ስትገቢ ቤት የለመድሽው ተግባርሽ ሆኖ ወደ ውጪ ሮጠሽ ካልወጣሽ በስተቀር እንደዛ አይነት ቁጥጥር የለም።" ፠ በዚህ ነፃነትሽ ሰክረሽ በሚመራሽ አቅጣጫ ፈሰስሽ ማለት..."ተበላሽ!" እመኚኝ የቴሌ operator የሆንሽ ያክል የጊቢው ጎረምሳ ሁሉ "ሀሎ ውዴ..." እያለሽ መፈናፈኛ ያሳጣሻል።ደሞዝ አልባ operator ሆነሽ ቀረሽ ማለት ነው። ፠ "መልክ ሳይኖረኝ የምን operator አመጣክብኝ!" ካልሽ እሱን ገብተሽ "አሀሀሀሀ ለካ ልክ ነበር።" ብለሽ ከስህተትሽ ከመማርሽ በፊት ላሳውቅሽ። እየነገርኩሽ ጎረምሶቹ ዶርማቸው ቁጭ ብለው "ስልኬን ታነሳዋለች አታነሳውም" ቁማር ሊጫወቱብሽ ሁላ ይችላሉ። "አንትስ ስልኬ ፓኬጅ ጨረሰ እያልክ እየተሳቀክ ኢንተርኔት ተጠቅመክ ይሆናል ጊቢ ስትገባ የመጀመርያው ናላክን የሚያዞረው የ wifi (ኢንተርኔት) ነፃነት ነው።" ፠ አሰብከው ያ የሌሊት የቀን ፓኬጅ እያስባለክ ብርክን ሲሞጨሙጭ የነበረው ኢንተርኔት እንደ ነፋስ በጊቢክ በነፃ ሲነፍስ..."ዶርም የራሱ ጉዳይ!!" ሊያስብልክ ሁላ ይችላል። እመነኝ ከዚህ የነፃነት ነፋስ ጋር ነፈስክ ማለት ከ4 ወር በኋላ ነፋሱ ሻንጣክን አስጠቅልሎ ከቤተሰቦችክ በር ጋር ነው የሚያላትምክ። አዎዎዎ ከጊቢ ሊያስጭርክ ሁላ ይችላል።(ለሰይጣንክ ነው ይህን የምመኘው።) ርእሴን ረስቼ አይደለም ዝምብዬ የምዘላብደው... ከፍቅር ግንኙነት ጋር በተያያዘ በሁለት ከፍዬ ዛሬ እተነፍስባችኋለሁ። ፠ እጮኝነት ላልጀመሩ ወዳጆቼ!! ፠ እጮኝነት ለጀመሩ ወዳጆቼ!! እጮኝነት_ላልጀመሩ እባካችሁን እናንተን አንድ ነገር እንድል ፍቀዱልኝ..."እድለኞች ናችሁ!!" የምሬን እኮ ነው። እስቲ ለእናንተ ስለ እጮኝነት የሆነ ነገር ልበላችሁ። ፠ እጮኝነት ብቸኛ ስለሆናችሁ የምትገቡበት ነገር አይደለም። - እመነኝ ብቸኝነት ተሰምቶክ እጮኝነት ከመጀመር ይልቅ ብቸኛ ሆነክ(ክርስቶስ እኮ አለክ ኣ?) የትምህርት ዘመንክን ብትጨርስ የተሻለ ነው። ፠ እጮኝነት ጊዜ የሚፈልግ ነገር ነው። - የጊቢ ነፃነት ጊዜ አለችሁ ሊል ይችላል። ግን በእኔ ይሁንባችሁ ከ1 ሴሚስተር በኋላ ነፃነት እና የጊዜ አጣቃቀም እንደሚለያዩ ከማስተዋላችሁ በፊት አሁን የምላችሁን እመኑኝ። ፠ እጮኝነት ሁለት ጥንዶች አንድ ወደሚሆኑበት ትዳር ከመግባታቸው በፊት የሚጠናኑበት ህብረት ነው እንጂ ፈታ ብለክ ዞር የምትልበት የመዝናኛ ክበብ አይደለም። - ግባችን ትዳር እስካልሆነ እጮኝነት ማሰቡ ትንሽ ሞኝነት አይመስልም?(መቼም አሁን ላይ አላማዬ ትዳር ነው አትለኝም። እንደሱ ካልክ የጋብቻ ትምህርት ቤት ነክ ማለት ነው።) ፠ ትምህርታችሁን አትዘንጉ ያለበለዚያ ነፃነት የተባለው ማእበል ከርስክ ጋር አጣልቶክ ህይወቴ እኮ ናት ካልካት እጮኛክ ጋር አጣልቶክ... "ሰራሁለት!" ይላል!! ማስታወሻ፦ ፠ በዩኒቨርሲቲ ቆይታ እጮኝነት ጀምረው ትዳር የመሰረቱ የሉም አልወጣኝም። ፠ ደግሞ ከ80% በላይ በተሳሳተ እጮኝነት ተሰብረው ከትምህርታቸውም ከአምላካቸው ሳይሆኑ የቀሩ እንዳሉም አስተውሉ። እጮኝነት_ለጀመሩ ፠ ምን ያህል በእጮኝነት ህይወት እንደቆያችሁ ባላውቅም ግን በነበራችሁ አጭርም ይሁን ረጅም ጊዜ የፍቅር ግንኙነት እንደሚነገርለት ቀላል እንዳልሆነ የተረዳችሁ ይመስለኛል። ካሰባችሁት በጣም ቀላል ሆኖ አግኝታችሁ ከሆነ ሁለት ነገር መገመት አያቅተኝም 1. ጌታ በጣም ረድቷችኋል ማለት ነው። 2. የጀመራችሁት ግንኙነት እውነተኛ ፍቅር መሆኑ ያጠራጥረኛል ግድ የላችሁም በዚህ እንስማማ ጌታ ካልረዳ እጮኝነት መጀመር በጊቢ ቆይታ ሌላ ዩኒቨርሲቲ መግባት ነው አ?(እንተማመና! እንደውም በጊቢ ቆይታው የእጮኝነት ህይወቱን ሳያበላሽ የወጣ ሁለት ዲግሪ እንደመስራት ነው።ለእኔ!!) ማስፈራሪያ በዛበት አ? እኔ እንዲህ አምናለሁ። " ትዳር የእግዜአብሔር ስጦታ ከሆነ እጮኝነትም ከእርሱ ዘንድ የተሰጠን ስጦታ ነው።" ስለዚህ ሰው ከሰው የተሰጠውን ስጦታ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ ከጠበቀ ከጌታ ለተሰጠው ስጦታ ደግሞ የፈለገ መስዋትነት ቢከፍል ሞኝ አያስብለውም። እጮኝነት ከጀመራችሁ እንዲህ ብታደርጉ መልካም ነው። ፠ ፀልዩ!!(አዎዎዎ የተለያየ ስፍራ ሆናችሁ ቢሆን እንካን አብዝታችሁ ፀልዩ።) ፠ የፍቅር አጋራችሁ ከጌታ የተሰጣችሁ ስጦታ ነውና ታማኝ ሁኑለት። ፠ አይናችሁ እጃችሁ ባለው ስጦታ ይሁን እንጂ በሌላ አትሸወዱ። ፠ በመካከላችሁ ክፍተት እንዳይፈጠር ነገሮችን በግልፅነት ተነጋገሩ። ፠ ከጊቢው ጋር ተያይዞ የሚሰማችሁን ስሜት በሌላ አትረዱ። ማስጠንቀቅያ፦ ፠ እጮኛሽ ወዳለሽበት ከተማ አንቺን ለመጠየቅ ሊመጣ ይችላል እና በዚህ ጊዜ እኔን ብሎ እኮ ነው የመጣው ብለሽ አብረሽው ቤርጎ ያዝሽ ማለት "ተበላሽ!!" እናንተ ከብረት የተሰራችሁ አይደላችሁም ውስጣችሁ የሚፈሰው ደም እንጂ ፈሳሽ ሜርኩሪ አይደለም። እመኑኝ ስሜታችሁን መቆጣጠር ተስኗችሁ ሌላ መዘዝ ውስጥ ትገባላችሁ።(ጌታ ከዚህ ይሰውራችሁ!!) 🧔🏾ወንድማችሁ ነኝ ! #ሼር ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ━━━━━━✦✗✦━━━━━━ ⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲ @yefkrumrkognoch
Show all...
ቆጠርከኝ New Amharic cover song By singer natniel kassa 🕐 6:28 💾4.5MB Share ♻️share @yefkrumrkognoch @yefkrumrkognoch
Show all...
😠ዘረኝነት😠 ማለት የራስን ጎሳ(ብሄር) ከሌሎች አስብልጦ ማየት ነው ይህ ደግሞ የሌሎችን ዝቅ አድርገን እንድናይ ያስገድዱናል ። በዘፍጥረት 1 ላይ የእግዚአብሔር አፈጣጠር በጣም የሚገርመኝ ሲፈጥር ሁለት ታላላቅ ነገሮች ግን የተለያዩ ነገሮች ነበሩ (ብርሀንና ጨለማ ፣ ሰማይና ምድር ፣ የብስና ውሀ ፣ ሰው እንስሳትና እፅዋት ፣ ፀሀይና ጨረቃ ፣ ወንድና ሴት ) ከዚህ የምንረዳው ልዩነት ውበት ነው አስባችሁታል ብርሀን ብቻውን ቢሆን የጨለማ ትርጉም አይገባንም የብስም ብቻውን ቢሆን ያለ ውሀ 🤔 የተለያዩ አርጎ ሲፈጥራቸው በምክንያት ነው ለምንድነው ይሄ ሁሉ ያልኩት 🙄 ዘረኝነት ደግሞ የራስን ብቻ የሚፋልግ የኔ ብቻ ከኔ ጎን ይሁን አውቀንም ሆነ ሳናውቀው ዘረኛ ሆነናል ልዩነታችን ነው ውበታችን እንዴት ሰው አስቦ ባልተወለደበት (እዚህ ብሄር) ነው የምፈልገው ብሎ ሳይወለድ በዘር ምክንያት ይገደላል 😥😥 ቢገባን ሁላችን አንድ አይነት ባህል ቢኖረን አለም በጣም ታስጠላለች ሌላው ቢቀር ሁሌ ደስተኛ መሆን እንኳን ያስጠላል የምሬብ ነው ምን ልላቹ ነው እርስ በእርስ መለያየታችን ውበታችን ነው ( ከምንጣላበት ይልቅ የምንዋደድበት ብዙ ምክንያት አሉን) ታዲያ እንዴት አንተ ከእኔ ትለያለህና በእኔ ወገን መቀላቀል የለብህም ተብሎ ሰው ይገለላል ቢገባን አንድ ስንሆን ነበር ሚያምርብን የምንዋደድበት ብዙ ምክንያቶች አሉን ። የተለያየ ሆነን መፈጣራችን እኔ እንትን ብሄር ሆኜ ስፈጠር ሌላው ደግሞ ሌላ ሆኖ የተፈጠረበት ምክኒያት አለ ለምን እኔን አልሆንክም ማለት ከእግዚአብሔር ጋር መጋፋት ይመስለኛል ተባረኩልኝ ውዶቼ @nazrawi_tube
Show all...
👍አንብበው ሲጨርሱ #ሼር 😍 🙏 ተመስገን እንበል 🙏 አንድ ሃብታም ሰውዬ በመስኮቱ በኩል ቆሞ አንድ ደሃ ከቆሻሻ ገንዳ ውስጥ ምግብ እየለቀመ ሲበላ ይመለከትና << ተመስገን አምላኬ እንኳንም ደሃ አላደረከኝ>> አለ። ደሃው ሰውዬም ምግብ እየለቀመ ካለበት ስፍራ ላይ እንዳለ አንድ የአይምሮ ህመምተኛ የሆነ ሰው እርቃኑን ሆኖ እዘለለ እየሮጠ ባጠገቡ ሲያልፍ አየና << ተመስገን አምላኬ እንኳንም እብድ አላደረከኝ>> አለ። እብዱ ሰውዬም መንገዱን እንደቀጠለ አንድ በጣም የደከመ ሰው የያዘ አንቡላንስ እየበረረ ባጠገቡ ሲያልፍ አየና <<ተመስገን አምላኬ እንኳንም በሽተኛ አላደረከኝ>> አለ። በሽተኛው ሰውዬም ሆስፒታል ደርሶ ወደ ድንገተኛ ክፍል እያስገቡት እያለ ሌሎች ሃኪሞች የሞተ ሰው እሬሳ ይዘው ሲወጡ አየና <<ተመስገን አምላኬ እንኳንም እሬሳ አላደረከኝ>> አለ። ልንማርበት ካሰብን ይሄ ታሪክ ብዙ ያስተምረናል እስኪ ይሄን አንብበን ከጨረስን በኃላ እነዚን ሁሉ ስላላደረገን ተመስገን እንበል🙏 Assignment ለሁሉም ምንጊዜም ማታ ወይም ጠዋት ለ 5⃣ ደቂቃ ፈጣሪያችንን ለሰጠን ነገር ተመስገን።የሰጠንን እያስታወስን ❕❕❕ እንዳይረሳ 🙏መልካም አዳር🙏 @yefkrumrkognch @yefkrumrkognoch
Show all...
#አስተማሪ_መልዕክት_እነሆ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 በአንድ መንደር ውስጥ የሚኖር አንድ ሰው ነበር። ይህ ሰው ውሀ ከወንዝ እየቀዳ ቤተ-መንግስት ዘወትር ያመላልስ ነበር። ውሀ የሚያመላልስባቸው ሁለት እንስራዎችም ነበሩት በነዚህ እንስራዎች ውሀ እየሞላ ወደ ቤተመንግስት ይውስድባቸው ነበር። ከሁለቱ እንስራዎች አንዱ ግን ቀዳዳ ነበረው፤ እና ምንም እንኳን ከወንዙ ሁለቱንም እኩል ውሀ ሞልቷቸው ቢሄድም ቤተመንግስት ሲደርስ ግን አንደኛው እንስራ #ሙሉ፤ ቀዳዳ ያለበት እንስራ ደግሞ #ጎዶሎ ይሆን ነበር። በዚህ ሁኔታ ሰውዬው በሁለቱ እንስራዎች አንድ ሙሉ እንስራ ውሀ፤ በሌላኛው ደግሞ ጎዶሎ ውሀ እያመላለሰ ለረጅም ጊዚያት ቆየ። ከእለታት አንድ ቀን ታዲያ ቀዳዳ ያለበት እና ዘወትር እያንጠባጠበ የሚሄደው እንስራ እንዲህ ሲል ለሰውዬው አቤቱታ አቀረበ፡፡ እንስራው፦ "እኔን እና ጓደኛዬን እየተሸከምክ ውሀ ማመላለስ ከጀመርክ እንሆ ቆየህ። #ሰባራ ሆኜም እንኳን ስታመላልስብኝ ሰነበትክ አሁን ግን ዘወትር ከጌታዬ ፊት ጎዶሎ ውሀ እየያዝኩኝ መቅረብ #አሳፈረኝ። ጓደኛዬ ዘወትር #ሙሉ_ውሀ ሲወስድ እኔ ግን #ሁሌ_ጎዶሎ ማቅረቡ አንገቴን አስደፈኝ። እናም በኔ ውሀ ማመላለሱ ቢበቃህ ይሻላል።" አለው። ይህን የእንስራውን አሳዛኝ ንግግር የሰማው ሰውዬ በማስተዋል ቀዳዳውን እንስራ እየተመለከተ፡- ሰውዬው፦ "ዛሬ ውሀ ቀድተን ስንመለስ አንድ ነገር አሳይሀልሁ" ሲል ነገረው። ውሀ ቀድተው ሲመለሱ ሰውዬው የሚያንጠባጥበውን እንስራ #ወደ_መሬት_እያስተዋለ እንዲሄድ ነገረው። እንስራውም እንደተባለው አደረገ። #በእሱ_በኩል_እጽዋቶችን ተመለከተ #ፍሬ_ያፈሩ አትክልቶችን አስተዋለ የሚያማምሩ አበባዎችን አየ። በዛኛው እንስራ በኩል ግን ምንም አልነበረም። ምንም እንኳን ዘወትር በተመሳሳይ መንገድ ቢሄዱም እንደዛሬው አስተውሎ አያውቅም ነበር። ሰውዬው፦ "አየህ ወደጄ አንተ #እንደምታንጠባጥብ_ሳውቅ_ባንተ_በኩል_ዘሮችን_ዘራሁ፤ ዘወትር ካንተ በሚንጠባጠበው ውሀ ጥማታቸውን አራሱ፣ ፍሬ አፈሩ፣ አበቡም። ይህ የምትመለከተው አትክልት ሁላ ባንተ በኩል ብቻ ነው ያለው ሌላኛውን እንስራ በምሸከምበት በኩል ምንም ነገር የለም እናም #ጥቅም_የለኝም_አትበል። ሌላው ቢቀር ደካማ ጎንህ እንኳን ለሌሎች ጥቅም አለው" ሲል አስረዳው። 📌 አንዳንዴ ልዩነታችንን አይተን፤ #በንጽጽር ብቻ ጥቅም የለኝም እርባና ቢስ ነኝ ብለን እናስብ ይሆናል። ሌላው ሰው የቻለውን እኛ ባለመቻላችን ብቻ ጎዶሎ እንደሆንን እናስባለን። 📌 የሌሎች ብርሀን እንጂ የኛ ስለማይታየን ከጨለማ መውጣት ያቅተናል። 📌 ሰባራው እንስራ ሌላኛው እንስራ ሙሉ ውሀ መውሰዱን ተመለከተ እንጂ በሱ ውሀ ስንት የእጽዋት ነፍስ እንደበቀለ አላስተዋለም። 📌 እኛም እንዲህ ነን #የየራሳችን_ብርሀን_አለን ነገር ግን #የሌላው_ሰው_ጭላንጭል_ያስቀናናል። 📌 ሌሎች ሙሉ ውሀ መሸከም ቢችሉ እንዳንተ ነፍስ መዝራት አይችሉም። አንተ እንደነሱ ሙሉ ውሀ መሸከም ቢያቅትህ ጉድለትህ ሌሎች እንዲያብቡ ያደርጋል። ━━━━━━✦✗✦━━━━━━ ⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲ አዘጋጅ፦ ⇨ @yefkrumrkognoch
Show all...
እቤታችን ያለው አምፑል የሚያበራው በውበቱ አይደለም። ሩቅ አገር ካለው የኀይል ምንጭ ጋር በመገናኘቱ ነዉ። ኀይሉ ከተቋረጠ ውበቱም ይጠፋል ብርሃኑም ይጨልማል። እንዲሁም የተስፋችን ብርሀን ከራሣችን የሚወጣ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ፍቅር ጋር የተያያዘ ነዉ። በራሳችን ሰውን መዉደድ ማፍቀር በራሳችን ተስፉ ማድረግ ሆነ መደሰት አይቻለንም። ከሀይላት ጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር መቆራኘት አለብን ። ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ። አሜን
Show all...
መጨነቅና መጨናነቅ ማንንም ሰው ከችግሩ ሲያድነው ታይቶና ተሰምቶ አይታወቅም፡፡ በመጨነቅና በመጨናነቅ ምክንያት ግን ሰዎች ቀስ በቀስ ወደሞት ሊያዘግሙ እንደሚችሉ መረጃዎችና ማስረጃዎች ሞልተዋል፡፡ እናንተ ማድረግ የምትችሉትን አድርጉ፡፡ እናንተ ማድረግ የማትችሉትን ደግሞ ሊያደርግላችሁ የሚችል ሰው ካለ አስደርጉ፡፡ ማንም ሊያደርግ የማይችለው ሁኔታ ውስጥ ካላችሁ ግን ጉዳዩን ለፈጣሪ አሳልፋችሁ ስጡና ኑሯችሁ ላይ አተኩሩ፡፡ መልካም ቀን ይሁንላችሁ!
Show all...
✴️የት ነህ?? * መገኛችን ማንነታችንን ይናገራል፡፡ 1.በሀሜት መንደር ነህን?-ምረትን ለምን ዘኁልቁ 12:13 *ሀሜት:- የውድቀት መጀመሪያ:የሽንፈት ምልክት፡ነፍሰገዳይነት ነው፡፡ ፊልጵስዮስ ሰወች 4-8 😂ለሀበሻ ቡና ያለሀሜት ደረቅ እንጀራ ያለወጥ በየሱስም ይሂን አባባል ገለበጥኩት🙏 2.እራስህን ከሌላው ጋር በማወዳደር ውስጥ ነህን?ሉቃ 18-9-14/ እራስህን ሁን፡፡ *እራስን ከሌላው ጋር ማወዳደር፡- የትእቢት ስ፡ የራስ ወዳድነነት ታላቅ ወንድም፡ የውርደት መጀመሪያ ነው፡፡ 3.በፍቅር ማጣት ውስጥ ነህን? -የአመፅ ልጂ ሁነሀል እና ንስሀ ግባ ፡፡ማቴ÷ 14-10-13 *ፍቅርን መኖር ስንጀምር እግ/ርን መምሰል እንጀምራለን፡፡b/c እግ/ር ፍቅር ስለሆነ፡፡ *ፍቅር የ ደቀመዝሙርነታችን መገለጫ ነው፡፡ ዩሀንስ ወጌል÷13-35 3.በውድቀት ውስጥ ነህን? -መውደቅህን ላይ ሳይሆን መነሳትህ ላይ አተኩር፡፡ -በሂወት እስካለን መውደቅ የሰውልጂ ባህሪ ነው ግን ለመነሳት ተስፋ አትቁረጥ፡፡ ✅ እግ/ር ባስቀመጠን ቦታ እንዲያገኘን ምን እናድርግ? 1.እንፅና(እስከ ሞት ድረስ) ሐዋርያት ሰራ÷7-55-69 2.በሁኔታወች አንናወጥ 3.የእግ/ርን ፈቃድ እንወቅ፡፡
Show all...
ቆራጥነት ይኑርህ! በአለማችን ውስጥ በርካታ አስገራሚ እውነተኛ ታሪኮች ይሰማሉ፡፡ አንዳንዶቹ አስቀውን፣ ሌሎቹ አሳዝነውንና አስለቅሰውን ያልፋሉ፡፡ አንዳንዶቹ ግን አዝናኝም፣ አሳዛኝም፣ አስተማሪም ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ አስተማሪ ገጽታ ያለው አንድ አጭር ታሪክ ላጋራችሁ፡፡ ሁለት ሕጻናት ከየራሳቸው ወላጆች በአንድ ሆስፒታል ተወለዱና የሆስፒታል ቆይታቸውን ሲጨርሱ ወላጆቻቸው ወደየቤታቸው ወሰዷቸው፡፡ ለካ አልፎ አልፎ የሚከሰተው ስህተት ተከስቷል፡፡ እነዚህ ወላጆች እቤታቸው ይዘው የሄዱት የራሳቸውን ልጅ ሳይሆን ሃኪሞቹ በሰሩት ስህተት ምክንያት ተቀያይረው ነው፡፡ ሁኔታው የታወቀው ግን ልጆቹ እደግ ብለው መልክ እየለዩ ሲሄዱ ነው፡፡ ልጆቻቸው እያደጉ ሲሄዱና መልካቸው እየለየ ሲመጣ ሁለቱም የማይተዋወቁ ወላጆች በየራሳቸው ጥያቄ ፈጠረባቸው፡፡ ከብዙ ማንገራገር በኋላና ልጆቹ አደግ ካሉ በኋላ አንደኛው ቤተሰብ ሁኔታው ስላሳሰበው ወደ ሆስፒታሉ በመሄድ የማጣራት ስራ እንዲሰራለት ይጠይቅና ሲጣራ መቀያየራቸው ተረጋገጠ፡፡ ይህ ወደመታወቅ የመጣው እውነት በብዙ ጭቅጭቅና የክስ ሂደት ውስጥ አለፈ፡፡ ጭቅጭቁና ክሱ ልጆቹ ይመለሱ አይመለሱ ነው፡፡ በመጨረሻ ዳኛው አንድ ፍርድ አስተላለፈ፡፡ “ሁለቱም ልጆች ይቅረቡና እውነቱ ተነግሯቸው ይጠየቁና የእነሱን ሃሳብ ሰምቼ እፈርዳለሁ” አለ፡፡ ልጆቹ ቀርበው ሲጠየቅ ሁለቱም አሁን ያሉበትን ቤትና ቤተሰብ እንደሚወዱና በፍጹም ወደ ትክክለኛ ቤተሰባቸው መመለስ እንደማይፈልጉ ተናገሩ፡፡ የአንዱ ቤተሰብ እጅግ ሃብታም የአንዱ ቤተሰብ ደግሞ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያላቸው ናቸው፡፡ ለልጆቹ ግን ይህ ሁኔታ ከቁጥርም አልገባም ነበር፡፡ የለመዱትን ስለወደዱት የእነሱ ከሆነው ነገር ውጪ ለመኖር ራሳቸውን አሳልፈው ሰጡ፡፡ የእነዚህ ልጆች ታሪክ እውነተኛ ቤተሰብ ማለት የለመድነው፣ የቀረብነውና ፍቅርና እንክብካቤ ያገኘንበት የመሆኑን አስገራሚ እውነት የመጠቆሙን ጉዳይ አልዘነጋሁትም፡፡ እንዲሁም አንድ ሰው የተቀበለውን ሰውም ሆነ ኑሮ ከሃብትና ከገንዘብ አስቀድሞ ደስተኛ ሆኖ ሊኖር የመቻሉን እውነታም አልሳትኩትም፡፡ ሆኖም ግን ታሪኩ ሌላ እውነታ ጨምሮ እንዲስተምረኝ ራሴን ክፍት ለማድረግ ፈለኩኝ፡፡ ይህ የሰውን ልጅ ሁል ጊዜ የማይለቀውን ትግል የሚጠቁም ታሪክ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በፍጹም “የእኛ” ያልሆነውን ነገር እና “እኛ” ያልሆንነውን ነገር ስለለመድነው ብቻ እንቀበለዋለን፡፡ የተወለድነው “ሌላ ቤት” የምንኖረው ግን “ሌላ ቤት”! . . . የተፈጠርነው ለሌላ ነገር፣ የምንኖረው ግን ሌላ ነገር! . . . የሚገባን ከፍ ያለ ነገር፣ እኛ ግን ወርደንና ተቀብለን የምንኖረው ሌላ ነገር! . . . የሚመጥነን ሰው ሌላ፣ መልቀቅ ያልፈለግነው ሰው ግን ሌላ ሰው! . . . የውስጣችን ጩኸት ሌላ፣ ስለለመድነው መልቀቅ ያቃተን ነገር ግን ሌላ! ልክ እነዚህ ልጆች በሕጻንነታቸው እንደሆኑት ምርጫው ባይኖረን ምንም ችግር አልነበረውም፡፡ ነገር ግን ልክ እንደነሱ አድገን የመምረጥ አቅሙም ሆነ መብቱ ኖሮን ከምናውቀው እውነታ ይልቅ የለመድነው ነገር ሲያይልብንስ !? እውነታውና ትክክለኛው ሲታይህ ስለለመድከው ብቻ የወደድከው፣ ለአንተ የማይመጥንንና የአንተ ያልሆነውን የሕይወት ዘይቤና አቅጣጫ ትተህ ለመሄድ ቆራጥነት ይኑርህ፡፡ @yefkrumrkognoch @yefkrumrkognoch
Show all...
የተሳኩልህና ያልተሳኩልህ ነገሮች ጉዳይ የማንነትህን ዋጋ በተሳኩልህና ባልተሳኩልህ ሁኔታዎች አንጻር ከፍና ዝቅ የማድረግ ምልከታ ካለህ ይህ ሁኔታ አደገኛ ነውና ውለህ ሳታድር አስብበት፡፡ ይህ ሁኔታ ለብዙ መዘዞች በርን የሚከፍተውን የአለመሳካት ፍርሃት ስሜትን ያስከትልብሃል፡፡ አለመሳካትን እጅጉን የሚፈራ ሰው ደግሞ የተለያዩ ስነ-ልቦናዊ ተጽእኖዎች ስር ወድቆ ራሱን ያገኘዋል፡፡ አንድን ነገር ሞክሮ ካልተሳካለት ሊገጥመው የሚለውን ሁኔታ በማሰላሰል ወዳልፈለገው አቅጣጫ ሲሄድ ራሱን ከማግኘቱም ባሻገር ከአንዳንድ ጠቃሚ እርምጃዎችም ራሱን ሊገታ ይችላል፡፡ የሚከተሉትን ነጥቦች እንደመንደርደሪያ ልትጠቀምባቸው ትችላለህ፡፡ ፍጹማዊነት የማንነቱን ዋጋ ከስኬታማነት ጋር ያስተሳሰረ ሰው ከሚታይበት አንድ አንድ ባህሪይ መካከል አንዳችም የጎደለው ነገር እንደሌለ ለማስመሰል መሯሯጥ ይገኝበታል፡፡ እንዲህ አይነቱ ሰው ብዙ የተሳኩለት ነገሮች ቢኖሩትም እንኳ ያልተሳካው አንዱ ላይ ስለሚያተኩር ያንን ለመሙላት ሲሮጥ ራሱን ያገኘዋል፡፡ እያንዳንዱ ያለመሳካት ሁኔታ ለማንነቱ ከሚሰጠው ዋጋ ጋር ስለሚገናኝበት የማንነቱን ዋጋ ላለማውረድ በሚያደርገው ጥረት ራሱን የማያልቅ ትግል ውስጥ ያገኘዋል፡፡ የዚህ ሰው ስሌት፣ “ስኬት = የማንነት ዋጋ” ነው፡፡ የስኬት ጉዳይ ደግሞ ተለዋዋጭና አንጻራዊ ስለሆነ፣ የማንነቱም ዋጋ እንዲሁ አንጻራዊና ተለዋዋጭ ይሆናል፡፡ ውጤቱ፣ በሁሉም ነገር ፍጹም ሆኖ ለመታየት መሞከር ነው፡፡ ተግባርን መሸሽ የአንድ ሰው የማንነቱ ዋጋ ከተሳካለትና ካልተሳካለት ሁኔታ አንጻር ተያይዞ ሲታይ ይህ ሰው ሙሉ ለሙሉ እንደሚሳካለት እርግጠኛ ያልሆነበትን ነገር ከመጀመር ይገታል፡፡ በእንደዚህ አይነቱ ሰው አእምሮ ውስጥ የሚጎላው የተለመደ ሃሳብ ይህንን ይመስላል፣ “አንድን ነገር ጀምሬ ሳይሳካልኝ ቀርቶ ከምዋረድ፣ ቀድሞውኑ ባልጀምረው ይሻላል፡፡” ይህ አይነቱ አመለካከት ደግሞ በሰውየው ሕይወት ላይ ገደብን ያስቀምጣል፡፡ ሰው አዳዲስ ነገሮችን ከመጀመርና ባልተሞከሩ ጎዳናዎች ላይ ከመራመድ ሌላ ወደ ተሻለ ነገር ለመዝለቅ የሚያስችለው መንገድ የለም፡፡ ስለዚህም፣ “ባይሳካስ” በሚል ቅድመ-ሃሳብ የተገታ ሰው ሳይጀምር የቆመ፣ ሳይራመድ የተሰናከለ፣ ሳይሞክር ደግሞ የከሸፈበት ሰው ነው፡፡ ፍርሃት “የማንነቴ ብቸኛ መለኪያ ስኬታማነት ነው” በማለት የደመደመ ሰው የሚፈራው ነገር ብዙ ነው፡፡ ከሁሉ በላይ ጎልቶ የሚታየው ፍርሃቱ ተቀባይነት የማጣት ፍርሃት ነው፡፡ በውስጡ፣ “ካልተሳካልኝ ሰዎች አይቀበሉኝም” የሚል ጽኑ አመለካከት ስላለው ስለ እሱ ማን ምን እያወራ ወይም እያሰበ እንደሆነ በማሰላሰል የቀን ሕልም ውስጥ ሲዋኝ ራሱን ያገኘዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የመውደቅ፣ ስኬት የማጣትና የመሳሰሉት ፍርሃቶች የሚያመጡበት ተጽእኖ ቀላል አይደለም፡፡ “ባይሳካ ምን እሆናለሁ?” በሚለው አሉታዊና ጉልበት አሳጪ ሃሳብ ስለሚጀምር የዚህ ፍርሃት ጫና ያለመሳካቱን እድል እጅግ ያሰፋበታል፡፡ የአይሳካም አሉታዊ አጀማመር ደክመን እንድንነሳ ከማድረጉም በላይ የተሳካውን ሳይሆን ያልተሳካውን የማየት ዝንባሌ ውስጥ ይጥለናል፡፡ ትእቢት የትእቢት መገለጫው ብዙ ነው፡፡ ትእቢት ብዙ ከእውነታው የገዘፉ ወሬዎችን በማውራትና ላይ ላዩን ብቻ ለታይታ በማጌጥ ሊገለጥ ይችላል፡፡ ትእቢት ሌላውን ሰው በመናቅና በመጨቆን ሊታይ ይችላል፡፡ እንዳንድ ሰዎች በውስጣቸው ያለው የትእቢት ዝንባሌ፣ የሌላቸውን እንዳላቸው አስመስለው እንዲኖሩ ግፊት ያደርግባቸዋል፡፡ ከሰዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት የበላይና አሸናፊ ማን እንደሆነ የማስመስከሪያ እድል እንደሆነ አድርገው ነው የሚቆጥሩት፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ፣ ትእቢት የተሸናፊነት እንጂ የአሸናፊነት ምልክት አይደለም፡፡ ትእቢተኛ ሰው ካየህ፣ በራሱ የማይተማመንና የዝቅተኝነት ስሜት የመታው ሰው እንዳየህ ቁጠረው፡፡ በአጭሩ፣ ስኬታማነት ከማንነት ዋጋ ጋር ሲምታታ ሰዎች ስኬትን ለማግኘትና የበላይነትን ለመጨበጥ ምንም ነገር ከማድረግ እንዳይመለሱ ይነዳቸዋል፡፡ የስኬቱን ጉዳይ ለጊዜው አዘግየውና በመጀመሪያ ራስህ ላይ እንድትሰራ ላነሳሳህ! @yefkrumrkognoch @yefkrumrkognoch
Show all...
ጊዜን ለራስህ ጨምር! እስቲ አንድ ነገር አብረን እናስብ፡፡ ይህንን ሃሳብ ከግል ልማዴ በመንሳት እንነጋገረው፡፡ ከጥቂት አመታት በፊት ማድረግ በምፈልገው ነገር ዙሪያ ትኩረትና ዲሲፕሊን (ስነ-ምግባር) የሞላው ጎዳና መጀመር አለብኝ ብዬ ወሰንኩ፡፡ ይህንን ጎዳና ለመጀመር በመጀመሪያ የትኩረት ጉልበቴን ማቃጠል የምፈልግበትን አስፈላጊ ነው የምለውን ነገር መምረጥ ነበረብኝ፡፡ ስለዚህም፣ ጠቃሚ ጽሑፎችን በመጻፍ ለሕብረተሰቤ ማበርከት መረጥኩ፡፡ ውሳኔዬ ይህንን ይመስል ነበር፤ በየቀኑ ቢያንስ ለአንድ ሰዓት ተኩል ያህል በአንድ ነገር ዙሪያ መጻፍ አለብኝ፡፡ ይህ ውሳኔ ቀላል ውሳኔ አልነበረም፤ ማድረግ የማይቻልም አይደለም፡፡ ስጀምረው ትንሽ ጫና የነበረብኝ ቢሆንም ከትኩረቴ ሳልወጣ ስለደጋገምኩት ማድረግ ችያለሁ፡፡ ይህንን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ ከየቀኑ አስፈላጊነቱ አናሳ ከነበረ ልማዴ ላይ አንድ ሰዓት ተኩል “መስረቅ” ነበረብኝ፡፡ ስለዚህ በመጀመሪያ ማድረግ የነበረብኝ፣ ለመጻፍ የሚያስችለኝ ንቁ ሰዓቴና በምንም ሁኔታና በማንም ሰው ትኩረቴ የማይሰረቅበት ጊዜና ሰዓት የትኛው እንደሆነ መለየት ነው፡፡ ንቁ ሰዓቴ ማለዳ ነው፣ በዚያን ሰዓት ደግሞ ከቤቴ የተለየ ምቹ ስፍራ የለም፡፡ ጉዞው የተጀመረው ያን ጊዜ ነው፡፡ ይህን ውሳኔ ከጀመርኩ ጀምሮ ከአቅም በላይ የሆኑ ጉዳዮች ካጋጠሙኝ ቀናት በስተቀር በየቀኑ ቢያንስ ለአንድ ሰዓት ተኩል እጽፋለሁ፡፡ በአመት ውስጥ የሰዓት ልማዴንና የእንቅልፍ ሁኔታዬን የሚያዛቡ የተለየ የጊዜ አቆጣጠር ያላቸው አገሮች በምጓዝበት ጊዜ እንኳ ይህንን ልማዴን በፍጹም ላለማቆም ጥረት አደርጋለሁ፡፡ ሂሳቡን እንስራው፡፡ በየቀኑ የአንድ ሰዓት ተኩል ጊዜን በመወሰንና በማመቻቸት ቀድሞ አደርግ ያልበረውን ነገር ማድረግ በመጀመሬ በአመት 547 ሰዓታትን በአንድ ነገር ላይ በማተኮር መስራት ጀምሬአለሁ ማለት ነው፡፡ እነዚህን 547 ሰዓታት በሳምንት 40 ሰዓት በሆነው የተለመደ የስራ ሰዓት ሳሰላቸው የሁለት ወራትን (68 ቀናት) የስራ ጊዜን ለራሴ ጨምሬአለሁ ማለት ነው፡፡ በሌላ አባባል በአመት ከሌሎች የስራ ሃላፊነቶቼ ውጪ የሆኑና ማንም የማይነካብኝ የሁለት ወራት የስራ ጊዜ ፈጥሬአለሁ፡፡ ምናልባት ይህንኑ ስሌት በመስራትና ተመሳሳይ ውሳኔን በመወሰን በአመት የተወሰኑ ነጻ የስራ ጊዜአት ለራስህ መጨመር ትችላለህ፡፡ ይህንን ለማድረግ የሚከተሉት ደረጃዎች ይጠቅሙሃል ብዬ አምናለሁ፡፡ 1. መገንባት የምትፈልገውን ነገር ለይ ከላይ የዘረዘርኩትን ሃሳብ የትኩረት እውነታ ተግባራዊ ለማድረግ ስታስብ ምናልባት በአንድ የሕይወትህ ሁኔታ ዙሪያ ትኩረት ሰጥተህ ለማዳበር የምትፈልገው ነገር ታይቶይ ይሆናል፡፡ ይህንን ጉዳይ በሚገባ አስበህበት አንድ ድምዳሜ ላይ በመድረስ ለመለወጥ፣ ለመገንባት ወይም ለማሻሻል የመረጥከውን ተግባር ለይተህ እወቅ፡፡ እኔ ከመረጥኳቸው ተግባሮች አንዱ የመጻፍን ነገር በማዳበር ለሕብረተሰቤና ለአገሬ ሕዝብ ጠቃሚና ተግባራዊ እውነታዎችን ማቀበል ነው፡፡ የአንተስ ምንድን ነው? 2. አመቺ ሰዓት ምረጥ አንድ ጊዜ ላተኩርበት የፈለኩትን ተግባር ከመረጥክ በኋላ ያንን ነገር ለመጀመርና ተግባራዊ ለማድረግ አመቺ ሰዓት መምረጥ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ ሰዓት ምርታማ ለመሆን ንቁ የሆንክበትና ከተለያዩ ሃሳብ ሰራቂ ሁኔታዎች ነጻ የምትሆንበት ሰዓት ሊሆን ይገባዋል፡፡ በእኔ ሁኔታ አመቺ የምለው ሰዓት የማለዳ ሰዓት ነው፡፡ ልጆቼ ከተነሱ በኋላ ጽሑፍ ላይ ማተኮር ስለማልችል ከማለዳው በ11 ሰዓት ነው የምጽፈው፡፡ አንተም ማዳበር ከምትፈልገው ጉዳይ አንጻር አመቺ ጊዜን መምረጥ ትችላለህ፡፡ 3. አመቺ ሁኔታንና ቦታን ምረጥ ለተግባር ስኬታማነት ስፍራ ወሳኝ ነው፡፡ ለምሳሌ፣ እኔ ለመስራት የመረጥኩትን የጽሑፍ ስራ ጫጫታ ያለበት ካፌ ሆኜ ልሰራው አልችልም፡፡ ስለዚህም የጸጥታውን ሁኔታ ልቆጣጠረው በምችልበት በቤቴ ሆኜ መጻፍ ይመረጣል፡፡ የጸጥታው ሁኔታ ብቻ ሳይሆን ለረጅም ሰዓት ተቀምጬ ለመጻፍ ምቹ የሆነ ስፍራ ላይ መቀመጥ አለብኝ፡፡ ከዚያም በተጨማሪ ራሴን ዘና ማድረግ ስፈልግና ከመጻፍ ተግባሬ እረፍት ስፈልግ ዘወር የምልባቸው ሁኔታዎች አመቻቻለሁ፡፡ አንተም ከዓላማህ አንጻር ይህንን ለማድረግ ሞክር፡፡ 4. እርምጃን ውሰድ ይህንን አስታውስ፣ አንድን ነገር እስክትጀምረው ድረስ አይጀመርም፡፡ ምንም እንኳን የመጻፍ ጽኑ ፍላጎት ቢኖረኝ፣ አንድ ቀን ተነስቼ ይህንን ተግባር መጀመር አለብኝ ብዬ እስክጀምረው ድረስ አልተጀመረም፡፡ በምኞት ብቻ የቆየሁባቸው ጊዜአት እንደነበሩ ማስታወስ አስፈላጊ ነው፡፡ ምኞትና የቀን ሕልም ግን የትም አያደርስም፡፡ አንድ ቀን ተነስቼ ከአንድ አረፍተ ነገር በመነሳት የጽሑፍን ስራ መጀመር ነበረብኝ፡፡ ሲጀመር ግር ይላል፣ ሲቀጥል ግን እየጠራ ይሄዳል፡፡ አንተም ከምኞት ውጣና ያሰብከውን ጀምር! ትችላለህ !!! ትችያለሽ !!! @yefkrumrkognoch @yefkrumrkognoch
Show all...
1ዮሐንስ 5:13-21ጥናት( ክፍል 16) 👉በክርስቶስ ኢየሱስ ስናምን ደግሞ ስንመሰክር የእግዚአብሔር ልጆች እንሆናል ታዲያ በክርስቶስ ላይ ባለን እምነታችን ደግሞ ድፍረትና እምነት ሆኖልናል ። 👉ታዲያ ምን አይነት ድፍረት አገኘን??? በመጀመሪያ በኤፌሶን 2:1 ጀምሮ ስለ እኛ ሲናገር ከፍጥረታችን በኃጢአታቸው ሙትን ነበርን ያም ብቻ አልነበረም ከኃጢአተኛ መንነታችን የተነሳ የእግዚአብሔር ክብር ጎሎን ነበር (ሮሜ 3:23) ስለዚህም ደግሞ በፍርድ እና በፍርሀት ውስጥ እንኖር ነበር ከዚህም የተነሳ ከእግዚአብሔር ህይወት ተቆርጠን በዚህ ዓለም ገዢ ለነበረው አለቃ መንፈስ እየተገዛን ለስጋችን እንንታዘዝ ነበር። 👉ነገር ግን በማመን ሞኝነት የእግዚአብሔር ልጆች እንሆንና እርሱ አባት ይሆነን ዘንድ አስገኘልን። #1ከቁጣ ልጅነት ---የእግዚአብሔር ልጅነት #2ከፍርድና ቁጣ---ወደ ጸጋው ዙፋን #3በኃጢአተኛነት---ወደ እግዚአብሔር ጽድቅ #4ከድቅድቅ ጨለማ🌑🌑🌑🌑--- ወደ ሚያስደንቅ ብርሃን 🌕🌕🌕🌕 👉" እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በመረቀልን በአዲስና በሕያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት ስላለን፥" (ወደ ዕብራውያን 10: 19-20) 👉ከእርሱ ጋር ህብረት ስላለን እንደ ፈቃዱ የምንለምነውን ሁሉ ይሰማናል። 👉እንደፈቃዱ የምንለምነው ምንድነው??? ከዚህ በታች ባለው ክፍል እንደተገለፀው እንደፈቃዱ የምንለምነው ብሎ ይስቀመጠው " ማንም ወንድሙን ሞት የማይገባውን ኃጢአት ሲያደርግ ቢያየው ይለምን፥ ሞትም የማይገባውን ኃጢአት ላደረጉት ሕይወት ይሰጥለታል። ሞት የሚገባው ኃጢአት አለ፤ ስለዚያ እንዲጠይቅ አልልም።" (1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5: 16) 👉ምህረት የሚያስገኝ ኃጢአት ይስተሰረይ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት የመለመንና ምልጃ የማድረግ ድፍረት ብሎ ያሰቅምጥልናል። ይህ ሃሳብ በዚህ እንደለ ከመልእክቱ እንደምንረዳው "ለሞት የሚያበቃ" እንዲሁም "ለሞት የሞያበቃ ኃጢአት" እንዳለ ያስገነዝበናል ።🙏🙏🙏🙏 👉ታዲያ ለሞት የሚያበቃ ኃጢአት የቱ ነው ብሎ ማሠብ አስፈላጊው ነገር ነው??? ✍️ ይህ ስንመለከት ስለ መንፈሳዊ ሞት ብቻ ሳይሆን ስጋዊ ሞትን ሊያስከትል እንደሚችል ይታሰባል ።ይሁንና ምን አይነት ኅጢአት ዘላለማዊ ሞትን ያስከትላል ብለን ስናስብ የማቴዎስ ወንጌል 12:32 እንዲህ ይላል " በሰው ልጅ ላይ ቃል የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ በዚህ ዓለም ቢሆን ወይም በሚመጣው አይሰረይለትም።" (የማቴዎስ ወንጌል 12: 32) ኃጢአት ሞትን እንድታመጣ ደግሞ በሮሜ 6:23 ላይ እንዲህ ይላል 👉" የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።" (ወደ ሮሜ ሰዎች 6: 23) 👉ሌላኛው ሞት ደግሞ ስጋዊ ሞት ሲሆን ይህ ደግሞ የጌታ የኢየሱስን ሥጋና ደም ሳይገባው ስለወሰዱ ሰዎች እንዲህ ተብሎ ተፅፎልናል (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11 ) ------------ 29 ሳይገባው የሚበላና የሚጠጣ የጌታን ሥጋ ስለማይለይ ለራሱ ፍርድ ይበላልና፥ ይጠጣልምና። 30 ስለዚህ በእናንተ ዘንድ የደከሙና የታመሙ ብዙዎች አሉ አያሌዎችም አንቀላፍተዋል። @yefkrumrkognoch
Show all...
አምስቱ ፍቅር-መሳይ ስሜት የሚሰጡን ሁኔታዎች የትክክለኛ ፍቅርን ስሜትና እውነታዎች በሚገባ ያልተገነዘቡ ሰዎች በውስጣቸው ካላቸው ፍቅርን የማግኘት ጥማት የተነሳ የመጀመሪያውን ፍቅር መሳይ ስሜት ጊዜ ወስደው ሳያጣሩ በመከተል የኋላ ኋላ የሚጸጸቱበት ግንኙነት ውስጥ ራሳቸውን ያገኙታል፡፡ ከዚህ አይነቱ ስህተት ለመጠበቅ የሚከተሉትን ነጥቦች እናስተውላቸው፡፡ 1. በብቸኝነት ጊዜ የምናገኘው ሰው ብቸኝነት በሚሰማን ጊዜና የብቸኝነቱ ስሜት ከርሞብንና ገዝግዞን ከዚህ ስሜት በቅርቡ የምንወጣበት ጭላንጭል አልታይ ሲለን የቀረበንና ትኩረት የሰጠን ሰው የሚሰጠን ስሜት ይህ ነው አይባልም፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆነን ለመጀመሪያ ጊዜ ትኩረት ስናገኝ የሚሰማን ስሜትና ከአንድ ሰው ጋር ፍቅር ሲይዘን የሚሰማንን ስሜት ሊመስል ይችላል፡፡ ይህ ከብቸኝነት ስሜት ያወጣን ግንኙነት የሰጠን ስሜት ከትክክለኛው የፍቅር ስሜት ጋር ከመመሳሰሉ የተነሳ እውነቱ የሚገባን ከብቸኝነት ስሜትና ስሜቱም አምጥቶብን ከነበረው ተጽእኖ ከወጣን በኋላ ነው፡፡ ከዙሪችን ሰው ጠፍቶ ምንም አይነት የጓደኝነት ምርጫ ባልነበረን ጊዜ የነበረን ስሜት አልፎ አሁን በሰዎች ስንከበብ ከዚህ በብቸኝነት ጊዜ ብቸኛ ትኩረት ከሰጠን ሰው ጋር የነበረን ስሜት እውነትም የፍቅር ይሁን አይሁን እየታየን ይመጣል፡፡ 2. ከአንድ ሰው ጋር የሚፈጠር የመላመድ ስሜት ቀደም ሲል እንደጠቀሰንው በአንዳንድ ሰዎች አመለካከት ትክክለኛ ፍቅር የሚመነጨው ከአንድ ሰው ጋር ብዙ ስናሳልፍና ስንላመድ ነው፡፡ ከአንድ ሰው ጋር ስንላመድ የምናገኘው ስሜት ትክክለኛ የፍቅር አጋር ስናገኝ ከሚሰማን ስሜት ጋር ሊመሳሰል ስለሚችል ሁኔታውን በሚገባ ማጤን አስፈላጊ ነው፡፡ እዚህ ላይ ከዚህ በፊት አንዳንድ ሰዎች ከመላመዳቸው የተነሳ ወደተዋጣለትና ወደዘለቀ የፍቅር ግንኙነት ውስጥ እንደገቡ ምንም ጥርጥር ባይኖረውም፣ ከአንድን ሰው ከመላመዳቸው የተነሳ የመጣውን ጊዜያዊ ስሜት ብቻ ተንተርሰው እስከወዲያኛው የሚዘልቅ ግኙነት ውስጥ ለመግባት የሞከሩና ምክንያቱ ግር እስኪላቸው ድረስ የተበላሸባቸው ሰዎች ቁጥር ከዚያ ይልቃል፡፡ 3. አንድን ሰው ስናደንቀው የሚመጣ ስሜት አንድ ሰው በእውቀቱ፣ በአርት ተሰጥኦው፣ በማሕበራዊ ተጽእኖው፣ በዝነኛነቱና በመሳሰሉት ሁኔታዎች ምክንያት ስናደንቀው ፍቅር መሳይ ስሜት ሊሰጠን እንደሚችል ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ በተዘረዘሩት መስኮች አካባቢ ዝነኛ ከሆኑ ሰዎች አካባቢ የሚያንዣብቡ ሰዎችን ስንመለከት ዚህ ስሜት ሰለባዎች እንደሆኑ ግልጽ ነው፡፡ አንድ ሰው በአንድ ሁኔታው ስላደነቅነው ብቻ የቀረውን ዘመናችንን ከእርሱ ጋር ለማሳለፍ ስንወስን በእርግጥም የወደድነው እርሱን ሳይሆን ለመደነቅ ያበቃውን ነገር እንደሆነ መገመት አያስቸግርም፡፡ 4. የአንድ ሰው መልክና ቁመና ሲስበን የሚመጣ ስሜት ስለመመጣጠን በምናወራበት ክፍላችን ውስጥ “አካላዊ መመጣጠን” በሚለው ሃሳብ ስር በሚገባ እንደምንመለከተው፣ የአንድን ሰው መልክና ቁመና ሳንቀበለውና በዚያ ሳንሳብ ወደግንኙነት መግባት አስቸጋሪ ነው፡፡ ነገር ግን በአንድ ሰው የውጭ አካል ሁኔታ፣ አንዲሁም መልክና ቁመና ስንሳብ ፍቅር የያዘን ሊመስለን ይችላል፡፡ ሆኖም፣ አንድ ሰው መልኩና ቁመናው ቀልብን የሚስብ ስለሆነ ፍቅር ሲይዘን ሊሰጠን የሚችለውን ስሜት ስለሰጠን ብቻ ወደዚያ መቸኮል በኋላ የምንጸጸትበትን ውሳኔ እንድንወስን አሳልፎ ሊሰጠን ይችላል፡፡ 5. ለአንድ ሰው ስንራራለት የሚመጣ ስሜት ለአንድ ሰው በጣም ስንራራለትና ካለልክ ስናዝንለት ፍቅር የያዘን የሚመስልን ስሜት ሊሰጠን ይችላል፡፡ ይህ ስህተት በብዙ ሰዎች የሚሰራ ስህተት ነው፡፡ የሚያዝኑለት ሰው በተለያዩ ችግሮች በሚያልፍበት ጊዜ ለዚያ ሁኔታ ምላሽ ሲሰጡና የስሜትና የቁሳቁስ ጉድለቱን ሲያሟሉለት የሚሰማቸውን ስሜት ከፍቅር ስሜት ጋር ይደባለቅባቸዋል፡፡ ይህ የሚንበት ዋነኛው ምክንያት አንዱ ለአንዱ የመራራትና የመደጋገፍ ሁኔታ ስሜት ትስስርንና መፈላለግን ስለመያነሳሳ ነው፡፡ ከአንድ ሰው ጋር መቀራረብ ስንጀምር ገና ለገና ከእነዚህ ሁኔታዎች አንዱ ሆኖብኝ ይሆናል በሚል ፍርሃት እንድንጨናነቅ ሳይሆን ማንኛውንም የተቃራኒ ጾታ መሳሳብ በሕይወታችን ሲከሰት በተረጋጋ መንፈስ ሆነን እንድናጤነው ለማድረግ ልንጠቀምባቸው ይገባል፡፡ (በቅርቡ ከታተመው “የፍቅር ሕይወት” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ መጽሐፍ የተወሰደ፡፡ መጽሐፉን በቅናሽ ዋጋ ለመግዛት ከፈለጉ 0911 47 51 96 ይደውሉ)፡፡ @yefkrumrkognoch @yefkrumrkognoch
Show all...
ዘመኑን እወቁ ወደ ሮሜ ሰዎች 13 11፤ ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና። 12፤ ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ። 13፤ በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥በክርክርናበቅናት አይሁን፤ 14፤ ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም እንዲፈጽም ለሥጋ አታስቡ ለአንድ ሰው ዘመንን /ጊዜን /ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው። ምክንያቱም እያንዳንዱ ነገር የሚከወነው በጊዜ /በዘመን/ ውስጥ ነው። አንድ ገበሬ የእርሻ ፣ የዘር ፣ የአረም ፣የአጨዳና የውቂያ ጊዜን እንደ ሚገባ አውቆ ለእየወቅቱ የሚገባውን ተግባር ካላደረገ ምርታማ ሊሆን አይችልም ። አንድ ተማሪም ነገ ውጤታማ ለመሆን ማጥናት በሚገባው ጊዜ ተግቶ ማጥናት ይጠበቅበታል ። የጥናት ጊዜ አለ የፈተና ጊዜ አለ ። በአጠቃላይ ለማናቸውም ነገ ዘመንን /ጊዜን /ማወቅ ለምርጫ የማይቀርብ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው ። በዚህ በሮሜ 13፦ 11_14 ባለው ክፍል ውስጥ ሐዋርያው ጳውሎስ አማኞችን ዘመኑን እንዲያውቁ አፅንኦት ሰጥቶ ይመክራቸዋል ። ለምንድነው ? ዘመኑን ማወቅ ያለብን ጊዜው ምንድነው ? ለሚለው ጥያቄ መልስ ሲሰጥ ካመንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቧል የሚል ነው ። ክርስቶስ ኢየሱስ አምነን ከተቀበልን ምንም ያህል ጊዜ ይሁነን ከትናንት ይልቅ ዛሬ ፍፁም የሆነው መዳናችን/በትንሳኤ አካል ከሞት ተነስተን በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ለዘላለም የምንኖርበት ጊዜ /ወደ እኛ እየቀረበ ነው ። 1ተሰ 4፦13_18 ዛሬ በአለማችን ላይ የምናያቸው ነገሮች ሁሉ ይህንን የሚጠቁሙ ናቸው ። ለዚህ የሚመጥን ሕይወት ከአማኞች ይጠበቃል ። ለዚህ ነው ጳውሎስ ትኩረት ሰጥቶ አማኞች ዘመኑን እንዲያውቁ የሚያሳስባቸው ። ጳውሎስ ዘመኑን የጨለማ/ የእንቅልፍ /እና የብርሃን /የመንቃት /በሚል በሁፍለዋል ። ዛሬም ቢሆን እኛ አማኞች ቆም ብለን ዘመኑን መለየት እለብን ። እማኞች ከእንቅልፍ ነቅተው መዳናቸውን የሚያስቡበት እንጅ የሚያንቀላፉበት ጊዜ አይደለም ። ዘመኑን ካወቁ አማኞች የሚጠበቁ ነገሮች 1 የጨለማን ሥራ አውጥቶ መጣል ሮሜ 13፦12 ኤፌ 5፦7_11 የጨለማ ሥራ ተብለው የተጠቀሱት ፥ ዘፈን፣ ስካር ፣ ዝሙት ፣ መዳራት /ለወሲብ የሚያነሳሱ ቅድመ ንክኪዎች/፣ ክርክርና ቅንአት ፣ ሌላውን መጥላት ፣ በሌላው ላይ ክፉ ማሰብና ማድረግ እነዚህ ሁሉ የጨለማ ሥራ ናቸው ። ኤፌ 5፦5_8 የአለም ብርሃን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አምኜ ድኛለሁ ብሎ የሚያምን ሁሉ እነዚህን የጨለማ ስራዎች ከሕይወቱ አውጥቶ መጣል አለበት ። ምክንያቱም ብርሃን ከጨለማ ጋር ሕብረት የለውም ። 2ቆሮ 6፦14_18 2 በቀን እንደምንሆን በአግባብ መመላለስ ሮሜ 13፦13 ፣ ኤፌ 5፦1_3 በቀን የሚመላለስ ሰው ከይሉኝታም ይሁን ከተጠያቂነት ለመዳን ራሱን ይጠበቃል ። በአለማችን ላይ የሚሠሩ ትልልቅ ወንጀሎች፣ ግድያዎች ፣ ሙስናዎች ፣ ዝርፊያዎች ቢኖሩም ጨለማን ወይም ደባቃ ስፍራን ተገን አድርገው እንጂ በግልፅ በብርሃን ሰው እያየ የሚፈፀሙ አይደሉም ። እኛ አማኞች የብርሃን ልጆች ነን ። ጨለማው አልፏል ። ጨለማን ተገን አድርገን የምንሰራው ወንጀል ሊኖር አይገባም ። ምክንያቱም የገባንበት መንግሥት ንጉሥ ፥ ጨለማ የማይጨልምበት ሁሉ በፊቱ የተራቆተና የተገለጠ አምላክ ነው ። ስለዚህ ለዚህ ብርሃን በሚመጥን ሕይወት በአግባቡ ልንመላለስ ይገባል ። አማኞች ነን እያልን በጨለማ ማለትም በዝሙት ፣ በመዳራት ፣ በዘፈን ፣ በስካር ፣ ሌላውን በመጥላትናክፉ በማድረግ የምንመላለስ ድቅድቅ ጨለማ በላያችን ላይ ወድቆብን በታላቅ እንቅልፍ ውስጥ እንዳለን ገብቶን ሰው ደንግጦ ከእንቅልፉ እንደሚነቃ እንንቃ ። ኤፌ 5፦11_14 ዘመኑ የእንቅልፍ ሳይሆን የመንቃት ነው ። ምክንያቱም ካመንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ወደ እኛ ዛሬ ቀርቧልና ። ይህንን ደህንነት የሚቀበሉት ደግሞ ከእንቅልፋቸው ነቅተው የጨለማንሥራ ከሕይወታቸው ያወጡና በቀን እንደሚሆን በአግባቡ የሚመላለሱ /ክርስቶስን /የለበሱ ናቸው ። ኤፌ 5፦5_6 ዘመኑን አውቀን የምንነቃበትን ፀጋ እግዚአብሔር ያብዛልን ። አሜን !!
Show all...
ምላስና ገንዘብ! ሁለት ካለማቋረጥ የሚናገሩ ነገሮች አሉ ይባላል፣ “ምላስና ገንዘብ”! ካለህበት ሆነህ አንድን መልካም ተጽእኖ ለማድረግ ወይም ደግሞ በተቃራኒ አንድን አጉል ዓላማ ለማስፈጸም የሚያስችሉ ሁለት ነገሮች አሉ፡- 1) አንደበትህና፣ እና 2) ገንዘብህ፡፡ እነዚህ ሁለት ወሳኝ ነገሮች አለምን የሚያሽከረክሩ ጉዳዮች ናቸው፡፡ ዛሬ የትኛውንም አይነት ማሕበራ ሚዲያ ብትከፍት የምትሰማው ወሬ ነው ወሬው ደግሞ በአብዛኛው የተገናኘው ከገንዘብ ጋር ነው፡፡ በእነዚህ በሁለት ነገሮች ሰዎች ካሉበት ስፍራ አንድ እርምጃ ሳይራመዱ በአስር ሺዎች ኪሎሜትር ርቀት ላይ ባሉ ግለሰቦች፣ ቤተሰቦች፣ ማሕበረሰቦችና ሃገሮች ላይ ወይም በመልካም ወይም ደግሞ በክፉ ጫና ማስከተል ይችላሉ፡፡ የትም ሳትሄድና እግርህ ሳታነሳ ባለህበት ሆነህ ስለሰዎች፣ ስለአንድ ተቋም፣ ስለአንድ ሕብረተሰብ፣ ስለሃገርና ስለሌሎችም ነገሮች በምትናገረው ነገር ብቻ አንድን ኃይል የማመንጨትና አንድን ነገር የመፍጠር አቅም አለህ፡፡ ይህ አንድ ነገር ግን መልካም ወይም መጥፎ ሊሆን ይችላል፡፡ እስቲ ዛሬ ለሰዎችና በሰዎች ላይ ከምትናገረው ጤና-ቢስ ንግግር ቆጠብ በማለትና በምትኩ መልካም ነገር በማውራት አዎንታዊ ኃይልን ለመፍጠር ሞክር! የትም ሳትሄድና እግርህ ሳታነሳ ባለህበት ሆነህ ለአንድ ሰው፣ ለአንድ ተቋም፣ ለአንድ ለተጎዳ ሕብረተሰብ፣ ለሃገርህ ወይም ለሌሎች ሁኔታዎች ገንዘብህን አውጥቶ በመስጠት ብቻ አንድን ኃይል የማመንጨትና አንድን ነገር የመፍጠር አቅም አለህ፡፡ ይህ አንድ ነገር ግን መልካም ወይም መጥፎ ሊሆን ይችላል፡፡ እስቲ ዛሬ ሌሎችን ሰዎችና የሕብረተሰቡን አካላት በሚጎዱ ጉዳዮ ላይ ገንዘብህን ከማውጣት ቆጠብ በማለትና በምትኩ መልካም ነገር ላይ ለተሰማሩ ሰዎች ልገሳህን በማድረግ አዎንታዊ ኃይልን ለመፍጠር ሞክር! የትም ሳትሄድ በአንደበትህ ብቻ ተአምር መስራት ትችላለህ! የትም ሳትሄድ በገንዘብህ ብቻ አስገራሚ ነገር ማድረግ ትችላለህ፡፡ በተቃራኒ፣ የትም ሳትሄድና ካለህበት ሆነህ በእነዚህ በሁለቱ ነገሮች ብዙ ጥፋቶችን ማጥፋት ትችላለህ፡፡ ምርጫው ያንተው ነው! @yefkrumrkognoch
Show all...
ሰዎች ሲሳሳቱ . . . በሕይወታችን በሚዛናዊነት ልንይዛቸው ከሚገቡን ወሳኝ ነገሮች መካከል በአካባቢያችን የሚገኙ ሰዎች፣ በተለይም የየእለት የኑሮ ስምሪታችን የሚያገናኘን ሰዎች ስህተት ሲሰሩ የምንሰጠው ምላሽ ቀንደኛው ነው፡፡ ከሰዎች ጋር የምናሳልፈው ጊዜ በበዛ ቁጥር ሰዎቹ ስህተት ሲሰሩ ማየታችን አይቀርም፡፡ የቤተሰብ አባሎቻችን፣ የትዳር አጋራች፣ የቅርብ ጓደኞቻችን፣ የስራ ባልደረቦቻችን፣ አለቆቻችን፣ የሃገር መሪዎቻችንና . . . ካለማቋረጥ ስህተትን ይሰራሉ፡፡ ለዚህ አይቀሬ ግላዊም ሆነ ማሕበራዊ ሂደት የምንሰጠው ምላሽ ሚዛናዊነት ለግልም ሆነ ለማሕበራዊ ስኬታችን እጅግ ወሳኝ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡ አብዛኛዎቻችን ከአስተዳደጋችን ለስህተታችን ምህረት ሳይደረግልን ከላይ ከላዩ ተጠብጥበን ስላደግን ሁኔታው አሁን ለሰዎች ስህተት ምህረት-የለሽ እንድንሆን ተጽእኖ አድርጎብናል፡፡ ስለዚህም፣ ለሁሉም ስህተት ጨከን ማለት ሚዛናችንን ስለሚያስተን መቼ ጠንከር፣ መቼ ደግሞ ለስለስ ማለት እንደሚገባን ማሰብ ታላቅ ሚዛናዊነትን ይሰጠናል፡፡ በቃ! የለመድነው መውቀስና መወቀስ፣ መምታትና መመታት፣ ማማትና መታማት፣ ስም ማጥፋትና ስም መጥፋት . . . ስለሆነ ስህተትን አይቶ በቀላሉ የማለፍን ጉዳይ ሆን ብለን ለራሳችን ካላስተማርነው በስተቀር ያስቸግረናል፡፡ ምንም ስህተትን በማያሳልፍና በተሳሳተን ሰው ላይ ልክ እንደወደቀ ዛፍ ሁሉም ሰው መጥረቢያውን በሚሰነዝርበት ሕብረተሰብ መካከል ስንኖር የምህረት፣ የይቅርታና አንዳንድ ጊዜ “ይሁን” ብለን አለፍ የምንል አይነት “አብሪ ኮከቦች” እንድነሆን የሚከተሉት ሃሳቦች ያግዙናል ብዬ አስባለሁ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ስህተት በሰሩ ሰዎች ላይ የመጨከን ዝንባሌችን የሚገናኘው ከማናውቃቸው ነገሮች የተነሳ ነው፡፡ ሶስቱን ዋና ዋና የማናውቃቸውን ነገሮች እንመልከት . . . 1. ይህ ሰው ይህንን ስህተት ላለመስራት ምን ያህል እንደታገለ አናውቅም፡፡ ሰዎች ስህተትን ሲሰሩ ያንን ስህተት ላለመስራት ምን ያህል እንደታገሉና እንደሞከሩ ብናውቅ ትንሽ ለስለስ እንልላቸው ነበር፡፡ እኛው ራሳችንም ብንሆን አንዳንድ ጊዜ አንድን ስህተት ላለመስራትና ላለመድገምም ጭምር ብዙ ታግለን ስላቃተን ብቻ ራሳችንን ስህተት ላይ እንደምናገኘው ማሰብ አለብን፡፡ 2. ይህ ሰው ይህንን ስህተት እንዲሰራ ጫና ያሳደረበትን ከአቅሙ በላይ የሆነን ሁኔታ አናውቅም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች አንድን ስህተት እንዲሰሩ የሚያስገድዳቸው የራሳቸው የሆኑ ሁኔታዎችና የሚያልፉበት ነገር ይኖር ይሆናል፡፡ የሰዎቹ ጾታ፣ የእድሜ ደረጃ፣ የገንዘብ አቅም፣ የእውቀት ብቃት፣ ያለፈ ልምምድና የመሳሰሉት ሁኔታዎች የራሱ ውህደት (Chemistry) ስላለው ማንም ሰው ያንኑ ችግር በእነሱ ሁኔታ ሊጋፈጠው አይችልም፡፡ ይህንን ማሰብ ትንሽ ሰፋ እንድንልና ሚዛናዊ እንድንሆን ያግዘናል፡፡ 3. ይህ ሰው በሚያልፍበት በተመሳሳይ ሁኔታ ብናልፍ እኛ ራሳችን ምን ያህል ስህተት ልንሰራ እንደምንችል አናውቅም፡፡ ሰዎች በመሪነት የውሳኔ ስህተት ሲፈጽሙ እኔ እንደ አንድ ዜጋ የፍርድ ቃል መናገር ሊቀለኝ ይችላል፤ መሪ ስላለሆንኩኝ፡፡ እኔ መሪ ብሆንና እሱ በሚያልፈበት ሁኔታ ባልፍ ግን ምን አይነት ስህተት እሰራ እሆን? በተመሳሳይ ሁኔታ ባልና ሚስቶች፣ ሴቶችና ወንዶች፣ መሪና ተመሪዎች፣ ነጋዴዎችና ገበያተኛዎች . . . ሊያስቡ የሚገባቸው እነሱ በዚያኛው ሰው ቦታ ቢሆኑ ሊሰሩ የሚገደዱት ስህተት ሊኖር የመቻሉን ጉዳይ ነው፡፡ በተቻለን መጠን ስህተትን ላለመስራት የመታገላችንን ጉዳይ ስናሰምርበት፣ ከዚያው ጋር በተቻለን መጠን ሰዎች ስሀተት ሲሰሩ የፍርድና የወቀሳ ሃሳብ ከመሰንዘራችን በፊት ግራና ቀኙን የማየት ሰፊነት የማዳበርንም ጉዳይ እንድናሰምርበት አሳስባለሁ፡፡ @yefkrumrkognoch @yefkrumrkognoch
Show all...
“በመሳሳም እርግዝና ሊከሰት ይችላል!” ሁለት ወንድ ወጣቶች ከፍቅረኞቻቸው ጋር አብረው የማሳለፍና የተለያዩ ለሕይወት ጠቃሚ ነገሮችን የመወያየት፣ አልፎ አልፎም የጋለ ክርክር ውስጥ የመግባት ልማድ አላቸው፡፡ አንድ ቀን የአንደኛው ፍቅረኛ አንድን ሃሳብ አቀረበችና የጦፈ ክርክር ተነሳ፡፡ ክርክር ያስነሳው ሃሳቧ፣ “አንድ ወንድና አንዲት ሴት ፍቅረኛሞች ከንፈር ለከንፈር ቢሳሳሙ በመሳሳማቸው ምክንያት ልጅ ሊጸነስ ይችላል” የሚል ነበር፡፡ በመጀመሪያ ይህንን ሃሳብ ያቀረበችበት ምክንያት የእሷና አብራት ያለችው የቅርብ ጓደኛዋ ወንድ ፍቅረኞቻቸው ካልተሳሳምን እያሉ ስላስቸገሯቸው ነው፡፡ የእሷ አቋም ከጋብቻ በፊት ከወሲብ መቆጠብ እንዳለባቸው ነው፡፡ ሆኖም ግን ከልጅነቷ ከሰማቸው ነገር የተነሳ “በመሳሳም እርግዝና ሊከሰት ይችላል” የሚለውን ሃሳብ ከልቧ ታምን ስለነበርም ነው፡፡ ይህንን ሃሳቧን ይዘው ብዙ ከተከራከሩ በኋላ ለሁለት በመከፈል ሊግባቡ ስላልቻሉ በመጨረሻ “በእድሜ ገፋ ያሉና ልምድ ያላቸው ሰው እንፈልግና እናማክራቸው” በሚለው ሃሳብ ከተስማሙ በኋላ፣ አራታችንም እሳቸው የሚሉትን በመስማማት እንቀበላለን ብለው ቃል ገቡና ተማማሉ፡፡ ለዚህ ጥያቄያቸው መልስ ለማግኘት በነበራቸው ጉዞ አንዲት በእድሜ ጠና ያሉ ብልህ ሴት እንዳሉና የብዙ ሰዎችን ጥያቄ በመፍታት የታወቁ እንደሆኑ ሰሙና ወደሳቸው ሄዱ፡፡ ክርስከራቸውን ለሴትየዋ ካቀረቡ በኋላ መልስን ሲጠብቁ የሰትየዋ መልስ አጭርና ያልጠበቁት ነበር፡- “አዎን፣ በመሳሳም እርግዝና ሊከሰት ይችላል” አሏቸው፡፡ ወጣቶቹም፣ እንዴት እንደዚያ ሊሆን እንደሚችል ሲጠይቋቸው፣ “ አይ፣ ልጆቼ ወጣቶች መሳሳም ከጀመሩ መች በዚያ ብቻ ያቆሙና! ከዚያ አንዴ ከተነሳሳ መመለሻ ከሌለው ጅማሬ በኋላ የሚከተለው ነገር እኮ ነው ጽንስን የሚያስከትለው” አሏቸው ይባላል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የምናደርገው ተግባርና የምንጀምረው ነገር ሳይሆን ከዚያ የሚከተለው ነገር ነው መዘዝ የሚያመጣብን፡፡ ያንን ስለማናስብ የጊዜውን ስሜት በመከተል ቀላል የመሰለንንና ችግር እንደሌለበት ያሰብነው ነገር ውስጥ ዘው ብለን እንገባለን፡፡ አንድ ከተባለ፣ ሁለት አለ! ሁለት ከተባለ ደግሞ ሶስት ቅርብ ነው! እያለ አንድን ነገር ከጀመርነው በኋላ፣ ይከናወናል ብለን በፍጹም ያላሰብነው ነገር ውስጥ ራሳችንን እናገኘዋለን፡፡ መግባት ቀላል፣ መውጣት ግን ከባድ የሚሆነው ለዚህ ነው፡፡ የመሳሳምን ጉዳይ ለምሳሌነት ተነሳንበት እንጂ በሕይወታችን የገባንባቸው አንዳንድ አስቸጋሪ ነገሮች በሙሉ ስንመለከታቸው ጅማሬው ምንም ችግር እንደሌለበት የምናስበው ነገር ነው፡፡ ሳናስበው ግን “የማይቀለበሰው ነጥብ” (Point of no return) ላይ ደርሰንና በሕይወታችን እንዲሆን ለማንፈልገው ክፉ ነገር ራሳችንን አጋልጠን እናገኘዋለን፡፡ ከላይ የጠቀስነውን ቀመርና የማይለወጥ የተፈጥሮ ሕግ በመጠቀም ብናሰላው . . . ለምሳሌነት የጠቀስነው የመሳሳምና መሰል ጅማሬዎች የሚወስዱንን ጥግ . . . ከጓደኞች ጋር መጠጥ ቤት እየሄዱ መዋል ወደሰካራምነት ደረጃ ከመሸጋገር ጋር ያለውን ግንኑነት . . . ከእጽ ሱሰኛ አቻዎቻችን ጋር ያለንን የቅርብ ግንኙነት በግድ-የለሽነት ማየት ወደሱሰኝነት ከመግባትጋር ያለውን ዝምድና . . . ማምታታትንና ሌብነት የሕይወት ዘይቤ ካደረጉ ወዳጆችን ጋር ያለን ቀረቤታ ወደምን ሊከተን እንደሚችል . . . ማሰብ አያዳግትም፡፡ “የማይቀለበሰው ነጥብ” (Point of no return) ላይ ከመድረሳችን በፊት ከጉዳዩ ጋር ያለንን ንክኪ እናስብበት፡፡ Share ♻️share♻️share @yefkrumrkognoch @yefkrumrkognoch
Show all...
ወይ ችግርህን ፍታው ወይ ውስጥህን ፍታው! በአንድ ከተማ ውስጥ ሰዎች ምክር ሲፈልጉ የሚሄዱበት አንድ ጠቢብ ሰው እንደነበረ ይነገራል፡፡ ሰዎች ወደዚህ ጠቢብ ሰው በመደጋገም እየመጡ ስለተመሳሳይ ችግር እየተነጫነጩ አሰለቹት፡፡ በሁኔታው የተበሳጨው ይህ ጠቢብ አንድ ጊዜ እነዚህ ሰዎች ሰበሰበና አንድ አስቂኝ ቀልድ ነገራቸው፡፡ ሰዎቹም ቀልዱን ሰምተው በጣም ሳቁ፡፡ ሁለት ደቂቃዎች ቆየና ያንኑ ቀልድ ደግሞ ሲነግራቸው የተወሰኑት ብቻ ሳቁለት፡፡ ጠቢቡ እንደገና ሁለት ደቂቃዎች ቆይቶ ያንን ቀልድ ለሶስተኛ ጊዜ ደግሞ ሲነግራቸው ማንም አልሳቀለትም፣ እንዲያውም አንዳነዶቹ እንደመበሳጨት አደረጋቸው፡፡ ከዚያም ጠቢቡ እንዲህ አላቸው፣ “ተመሳሳይ ቀልድ ደጋግሜ ስነግራችሁ መሳቅ እንዳቆማችሁ ሁሉ ስለተመሳሳይ ችግር በየጊዜው ደጋግሞ መነጫነጭም ማቆም አለባችሁ፡፡ በሉ ከዛሬ ጀምሮ ወይ ሁኔታውን ለወጡት፣ ሁኔታውን መለወጣ ካልቻላችሁ ደግሞ በሁኔታው ላይ ያላችሁን አመለካከታችሁንና ዝንባሌያችሁን ለውጡ”፡፡ ሁል ጊዜ ስለተመሳሳይ ችግር መነጫነጭ፣ ባለህበት እንድትረግጥ ያደርግሃል . . . ውስጥህን ያደክመዋል . . . ጤናህን ያዛባዋል . . . የፈጠራ ብቃትህን ይወስነዋል . . . የችግር አፈታት አቅምህ እንዳያድግ ያደርጋል . . . ሰዎች እንዲርቁህ ያደርግሃል . . . በል እንግዲህ! ከቻልክ ችግርህን ፍታው፣ ካልቻልክ ግን ውስጥህን ፍታው! @yefkrumrkognoch
Show all...
🎶 ያያል🎶 new cover song by singer By singer nati Share ♻️share @yefkrumrkognoch
Show all...
ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን: #የፖርኖግራፊ_ሱሰኝነት_ምልክቶች_እና_መዘዞቹ #ከፖርኖግራፊ_ሱስ_መውጣት_ይቻላል! #ክፍል_ሁለት የፖርኖግራፊ ሱሰኝነት ምልክቶች እና መዘዞቹ በቀደመው ክፍል ላይ ‘ፖርኖግራፊ’ ሰዎችን ሱሰኛ የማድረግ ከፍተኛ አቅም እንዳለው አይተናል። ለዛሬ ደግሞ የሱሰኝነቱን ምልክቶች /Symptoms/ እናያለን። 1. #ከፍተኛ_ፍላጎት አንድ ሰው ሱስ ደረጃ ላይ ከደረሰ ለፖርኖግራፊ ከፍተኛ ፍላጎት ይኖረዋል።በውስጡ የማያቋርጥ ፍላጎት ይቀጣጠላል። በማንኛውም ቦታ በማንኛውም ሁኔታ በማንኛውም ሰአት ፖርኖግራፊን መመልከት ይፈልጋል። ከዚህ በተጨማሪ የሚመለከትበትን ጊዜ እየጨመረ ይመጣል። በሳምንት ያይ የነበረ በቀን፤ በቀንም አንዴ ያይ የነበረው ሁለቴ ማየት ከጀመረ፣ በፖርኖግራፊም የሚያጠፋውም ጊዜ እያደገ ከመጣ፤ በሚመለከትበት ጊዜ የሚሰማው መነቃቃት እና ደስታ በሀፍረት፤ ጥፋተኝነት ስሜት እና ፀፀት ሲተካ ነገሩ ሱስ ደረጃ ላይ መድረሱን ይጠቁማል። #ነገም_ይቀጥላል....... #share #share #share ሀሳብ አስተያዬት ካላችሁ 👉 @yefkrumrkognoch @yefkrumrkognoch
Show all...
5. #ሱስ አንዳንድ ሰዎች ፖርኖግራፊን በተለያየ ምክንያት አንድ ጊዜ ወይም ከዚያ በላይ ከተመለከቱ በኋዋላ ሱሰኝነትን ያዳብራሉ። ሱስ ማለት ፈልገን የገባንበት ኋላ ግን እየጠላነውም ቢሆን የምናደርገው ነገር ነው። ማንኛውም ሱስ ሲጀመር በፍላጎት ሲሆን የሚቀጠለው ግን ያለ ፍላጎት ሊሆን ይቻላል። ፖርኖግራፊ ልክ እንደማንኛውም አደንዛዥ ዕጽ ሰዎችን ሱሰኛ የማድረግ ከፍተኛ አቅም አለው። በአንድ ወቅት ስለ ፖርኖግራፊ ሱስ ዶክተር ስዩም ያሉትን ልዋስ፤ “ብዙዎች ፖርኖግራፊ ሳያዩ መተኛት በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ሆነው ሱስ አይሆንም ብሎ የመናገር ድፍረት አላቸው:: ነገር ግን ፖርኖግራፊ ከሌሎች ሱሶች ባልተናነሰ እንዲያውም በበለጠ መልኩ ወደ ሱስነት ያድጋል። አንድ ሰው ፖርኖግራፊ ሲመለከት ደሙ ውስጥ የሚለቀቁ ቅመሞች (hormons) አሉ፤ እነዚህ ቅመሞች አንድ ሰው ኮኬንና ሄሮዊን የሚባሉትን አደዛዥ ዕፅ ሲጠቀም በደሙ ውስጥ የሚለቀቁ ቅመሞች ናቸው። እኚህን ዕጾች ስንወስድ ደማችን ውስጥ የሚለቀቁት ቅመሞች ፖርኖግራፊ በምናይበት ጊዜ ከተለቀቁ ፖርኖግራፊ ሱስ አይሆንም ማለት አንችልም። ሱስ ለመባል የግድ በአፍ በኩል ወደ ውስጣችን መግባት የለበትም። አሁን ባለን መረጃ ‘Pornography is not like a drug, it is a drug’ (ፖርኖግራፊ አንደ አደንዛዣ ዕፅ ሳይሆን እራሱ አደንዛዥ ዕፅ ነው) እንዲያውም መልከ ብዙ ዕፅ ነው። ሰው ፖርኖግራፊ ሲያይ ብዙ ዕፅ በአንድ ላይ እንደወሰደ ይቆጠራል። አንድ የኒዩሮ ሳይንቲስት (neuroscientist) ባለሙያ በፖርኖግራፊ ለመለከፍ የሚፈጅበትን ጊዜ ሲ ናገሩ አንድን ምስል ለግማሽ ሰከንድ ካየን በኋላ በሚቀጥሉት 5 ና 10 ደቂቃ ውስጥ አንጎላችን ውስጥ መሰረታዊ የሆነ የቅርጽ ለውጥ (nerve restriction) ይፈጠራል። ይሄ አይነት ለውጥ ልክ አንድ ሰው አደጋ ሲደርስበት የሚፈጠረውን የቅርጽ ለውጥ አይነት ነው። በፖርኖግራፊ ለመለከፍ የሰከንድ 1/3ኛ ይበቃል እንደማለት ነው:: አስተውላቹ ከሆነ ለሰከንድ ያየነው የፖርኖግራፊክ ምስል ለአመታት ከአይምሮአችን አይወጣም። ለምን ካላችሁ ‘epimerphine’ በተባለው ‘ሆርሞን’ ምክንያት እንዳይጠፋ ሆኖ ተቀርጿል:: ከዚህም የተነሳ ከአመታት በኋላ እንኳን አይረሳም። በዚህም ምክንያት ‘በቃ አይኔንም ስከድን ስተኛም በመንገድ ላይ ስሄድም የሚመጣብኝ እሱ ነው’ እያሉ በመንፈስ ጭንቀት የሚሰቃዪ ወጣቶች ገጥመውኛል።” ከዚህ የምንረዳው በቀላሉ የሚጀመር ነገር እንዴት ወደ ትልቅ ሱስ ሊያድግ እንደሚችል ነው። #ነገም_ይቀጥላል....... #share #share #share ሀሳብ አስተያዬት ካላችሁ 👉@yefkrumrkognoch @yefkrumrkognoch
Show all...
ስሙት በጌታ እኔን የለወጠኝ እናንተን የማይለውጥበት ምክንያት የለውም ተለወጡበት የሰዉ ሁለንተና ሰዉ ማነዉ? የስንት ነገሮች ስሪት ነዉ ነዉ? አሁን ይህን የምታነበዉ/ዊ ማን ነህ❓ ማን ነሽ❓ እራሰህን ታዉቃለህ❓ አንተ የስንት ነገር ዉጤት ነህ❓ እስካሁን ማንነትህንና ባንተ ዉስጥ ስንት ነገር እንዳለ ካላወቅ የህይወትን መዉጫና መግቢያ አላወክም። ድርጊት በፈቃድ ተወስኖ በስሜት ተብላልቶ ከሀሳብ(እዉቀት) ይጀምራል ሀሳብስ(እዉቀት) ከየት ይጀምራል ምንጭ አለዉ❓ ማንኛዉም ድርጊት ከሀሳብ(እዉቀት) ከጀመረ ሀሳቡን የሰጠን አካል(person) አለ። ማንኛዉም በኛ የተፈፀመ ድርጊት ሀሳቡ ከኛ ካልጀመረ ድርጊቱ ሀሳቡን(እዉቀት) በሰጠን አካል(person) ፈቃድ የተፈፀመ ነዉ። የትኛዉም ድርጊታችሁ ከእናንተ አልጀመረም። የመጀመሪያዋ ሰዉ ሄዋን ፍሬዉን የመብላት ድርጊት የፈፀመችዉ ከላይ በተመለከትናቸዉ process በማለፍ ነዉ። ዛሬ ላይም አንተ/ቺ የጥፋትን ድርጊት የምትፈፅመዉ ሄዋን ያለፈችበትን መንገድ(process) አልፈህ ነዉ። 👆ከላይ👆 ያለዉ ሀሳብ ከትምህርቱ በጥቂቱ የተወሰደ ፅሁፍ ነዉ። ብዙና ጠለቅ ያሉ ሀሳቦችን ለማግኘት በጥራትና በአነስተኛ ይዘት የተዘጋጀዉን የድምፅ ቅጂ በማዉረድ ይስሙት። ከሰሙት በኋላ በከንቱ የመነዳትን ህይወት ያቆማሉ። ተባረኩ
Show all...
3. #ብቸኝነት ብዙውን ጊዜ ብቸኝነትን የሚያዘወትሩ በተለያየ ምክንያት ከሰዎች ጋር ህብረት ማድረግ የማይችሉ ሰዎች በዚህ ሱስ ሊጠቁ እንደሚችሉ ጥናቶች ያሳያሉ። 4. #በጓደኛ_ግፊት በአብዛኛው ታዳጊዎች እና ወጣቶች ስለ ወሲብ ምንነት ለማወቅ ካላቸው ጉጉት የተነሳ ወደ ፖርኖግራፊ ሊሳቡ ይችላሉ። ብዙዎች ወደ ሚያደርጉት ነገር ወይም ከዚያም ባለፈ በደፈናው ‘አታርጉ!’ የሚባሉ ነገሮችን የመሞከር ዝንባሌ በወጣቶች ይስተዋላል ። ታዳጊዎችና ወጣቶችም በጓደኞቻቸው ግፊት ወደዚህ ህይወት በቀላሉ ሊሳቡ ይችላሉ። ለ10 አመት ያህል በፖርኖግራፊ ሱስ ውስጥ ያለች አንዲት እህት እንዴት ወደዚህ ሱስ እንደገባች እንዲህ ስትል አጫውታኛለች። “የዪኒቨርስቲ ተማሪ እያለሁ ዶርም ውስጥ ጓደኞቼ ተሰብስበው ፖርን ይመለከቱ ነበር። እኔ ግን ሁሌም እቃወማቸው ነበር። ከሆነ ጊዜ በዋላ ግን ሳላስበው እነሱን መቀላቀል ጀመርኩ። ከዚያ በኋላ ከነሱ የባስኩ ተመልካች ሆንኩኝ።” #ነገም_ይቀጥላል....... #share #share #share ሀሳብ አስተያዬት ካላችሁ 👉@yefkrumrkognoch @yefkrumrkognoch
Show all...
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!