cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

"ቃለ እግዚአብሔር "

"ጥበብን ማግኘት ምንኛ ከወርቅ ይሻላል! ማስተዋልንም ማግኘት ከብር ይልቅ የሚመረጥ ነው።" ምሳ 16 "ሥጋችን ምግብ ሲያጣ እንደሚደክም ሁሉ ነፍስም ምግቧን የእግዚአብሔርን ቃል ስታጣ ትደክማለች።" - ብጹዕ አቡነ ሽኖዳ በመንፈሳዊ ህይወት ዙሪያ ጥያቄ ካላችሁ ለመምህራችን በ @henokasrat3 መላክ ትችላላቹ።

Show more
Advertising posts
8 305Subscribers
+124 hours
+37 days
-2430 days
Posts Archive
#ሰው_እንደ_ዘር_ነው አባቶቻችን ሊቃውንት ሰው እንደ ዘር ነው ይላሉ። ሰው እንደ ዘር ነው ማለት ዘር ተዘርቶ የሚያድገው በሁለት መሠረታዊ ነገር ነው። በብርድ እና በጸሐይ። ዘር ዝናምና ጸሐይ ያስፈልገዋል። ዝናም ብቻ ከሆነ ሽባ ይሆናል ጸሐይ ብቻም ከሆነ ይደርቃል። ሰውም እንደ ዝናሙ የእግዚአብሔር ቸርነት ያስፈልገዋል፤ እንደ ጸሐዩም መከራ ያስፈልገዋል። ዘር በዝናሙ እየለዘበ፣ በጸሐዩ እየበሰለ እንደሚያድገው ሁሉ ሰውም በመከራ እየጠነከረ በተስፋና በእግዚአብሔር ቸርነት እየተጽናና ያድጋል። ሁልጊዜ የእግዚአብሔርን ቸርነት ብቻ ከሆነ የሚያስበው ሽባ ይሆናል። መከራ ባገኘው ጊዜ ወዲያው ተስፋ ይቆርጣል። ሃይማኖትን ሊክድ ይችላል። መከራ ብቻ ከሆነበት ደግሞ ወዲያው ደግሞ እንደዚሁ ተስፋ ቆርጦ ሊሠበር ይችላል። ስለዚህ ዘር ዝናምና ጸሐይ እንደሚያስፈልገው ሁሉ ሰውም መከራና የእግዚአብሔር ቸርነት ያስፈልገዋል። #አባ_ገብረ_ኪዳን (የብሉያት እና የሐዲሳት መምህር)
Show all...
👍 9
እንኳን ለኒቆዲሞስ ሳምንት አደረሳችሁ።
Show all...
"ወደ ጌታህ ደስታ ግባ" እጅግ ጥዑም ትርጓሜ፣ እጅግ ጥዑም ትምህርት።
Show all...
👍 3
👍 17
ነገ ሚያዝያ 6 2016 በቦሌ መድኃኒዓለም ልዩ ጉባኤ አለ እንዳትቀሩ ሁላችሁም። ጳጳሳት ይገኛሉ ታላላቅ መምህራንም አሉ እና እንዳትቀሩ 🙏
Show all...
👍 11
#ደብረ_ዘይት (የዐቢይ ጾም አምሥተኛ ሳምንት) የዐቢይ ጾም የአምስተኛው ሳምንት ደብረ ዘይት ይባላል፡፡ ጌታ በደብረ ዘይት የዳግም ምጽአቱን ነገር ማስተማሩ ይነገርበታል፡፡ ደብረዘይት የስሙ ትርጓሜ የዘይት ተራራ ማለት ነው ስያሜ የተሰጠው በቦታው ብዙ ወይራ ተክል ይበቅልበት ስለ ነበር ነው፡፡ እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ ደቀመዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው ንገረን ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድን ነው?›› አሉት (ማቴ. 24፥3፣  ዘካ. 14፥5 ፤ ሐዋ. 1፥11 ፤ 1ኛ ተሰ. 4፥16 ፤ ራዕ. 22፥7) #አመጣጡስ_እንዴት_ነው? ጌታ ይህንን ዓለም ለማሳለፍ ለሁሉም እንደ ሥራው ለመክፈል በግርማ መለኮቱ በክበብ ትስብዕቱ ይመጣል፡፡ ጊዜው ዘመነ ዮሐንስ ወርሃ መጋቢት ዕለት እሑድ መንፈቀ ሌሊት እንደሆነ ሊቃውንት ተናግረዋል፡፡ ምነው የሚያውቀው የለም ይባል የለምን? ቢሉ እውነት ነው የሚያውቀው የለም ብዙ የዮሐንስ ዘመን፤ ብዙ የመጋቢት ወር፤ ብዙ የእሑድ ዕለት አለና ለይቶ የሚያውቅ የለም፡፡ ሞት ለማን አይቀርምና ሁሉም ይሞታል፡፡ ዘፍ. 3፥19 በዕለተ ምጽአት ቅዱስ ገብርኤል ስምንቱን ነፋሳተ መዓት ከየመዛግብታቸው ያወጣቸዋል፡፡ ዛፏን ነቅለው ደንጊያውን ፈንቅለው ምድርን እንደ ብራና ይዳምጧታል፡፡ ቅዱስ ሚካኤል መለኸት ይነፋል፡፡ 1ኛ መቃ. 9፥8 ቅዱስ እግዚአብሔር ዘያነቅሖሙ ለሙታን ሲል በዱር በገደል በባሕር በየብስ በመቃብር ውስጥ ያሉት በአውሬ ሆድ ውስጥ ያሉ ሁሉ ይሰበሰባሉ፡፡ በሁለተኛው ነጋሪት ሲመታ አጥንትና ሥጋ አንድ ሆነው ፍጹም በድን ይሆናሉ፡፡ ሦስተኛው ነጋሪቱን መቶ (ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ህያው ዘኢይመውት) ንቃሕ መዋቲ ዘትነውም ባለ ጊዜ መቃብር ክፈቱልኝ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ደጉ ደጉነቱን ክፉውም ክፋቱን ይዞ ይነሳል፡፡     ወንዱ የ30 ዓመት ሴቲቱ የ15 ዓመት ሆነው ጻድቃን ብርሃን ለብሰው ብርሃን ተጎናጽፈው ከፀሐይ 7 እጅ አብርተው ማቴ.13፥43 ኃጥአን ጨለማ ለብሰው ፍጹም ዲያቢሎስን መስለው ይነሳሉ፡፡ ጻድቃን ስለሠሩት መልካም ሥራ ኑ የአባቴ ቡሩካን ብሎ መንግሥተ ሰማያትን ያወርሳቸዋል፡፡ ኃጥአንን ስለ ክፉ ሥራቸው (ከኔ ሂዱ) ገሃነም ይሰዳቸዋል፡፡ ጻድቃን ደስ ይላቸዋል ኃጥአን ግን ያዝናሉ፤ ዋይ ዋይ ይላሉ፤ ደረት ይደቃሉ እንባቸው ያፈሳሉ፡፡ የማይጠቅም ለቅሶ የማይጠቅም ሐዘን ሰቅለው የገደሉትም አይሁድ ክብሩን አይተው ላይጠቀሙ ይጸጸታሉ፡፡     #ምልክቱስ_ምንድን_ነው? ብለው ጌታን ሲጠይቁ ‹‹ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፡- ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፡፡ ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ፤ ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ አትደንግጡ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው፡፡ ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥት በመንግሥት ላይ ይነሳል፤ ረሃብም ቸነፈርም መናወጥም በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤ እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው፡፡ በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል ይገድሉአችሁማል፤ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ›› አላቸው፡፡ በዳግም ምጽአቱ ጊዜ ከቅዱሳኑና ከሰማዕታቱ ጋር ለመቆም ያብቃን፡፡ #የዕለተ_ሰንበት_መዝሙር_ከጾመ_ድጓ እንዘ ይነብር እግዚእነ ውስተ ደብረ ዘይት ወይቤሎሙ ለአርዳኢሁ ዑቁኬ ኢያስሕቱክሙ ወንበሩ ድልዋኒክሙ ብዙኃን ይመጽኡ በስምየ እንዘ ይብሉ አነ ውእቱ ክርስቶስ ወዘአዝለፈ ትዕግሥቶ ውእቱ ይድኅን ወአመ ምጽአቱሰ.... (ጌታችን በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ሳለ ለደቀ መዛሙርቱ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፤ ተዘጋጅታችሁም ኑሩ፤ ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ እስከ መጨረሻው የጸና እርሱ ይድናል፡፡....) #የዕለቱ_ምንባባት 1ኛ ተሰሎንቄ 4÷13-ፍጻ፡- ወንድሞቻችን ሆይ÷ ስለ ሞቱ ሰዎች÷ ተስፋ እንደሌላቸው ሰዎች እንዳታዝኑ ልታውቁ እንወዳለን፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞቶ እንደ ተነሣ ካመንን እንዲሁ እግዚአብሔር ሙታንን በኢየሱስ ያስነሣቸዋል ከእርሱም ጋር ያመጣቸዋል፡፡..... 2ኛ ጴጥ.3÷7-14፡- አሁንም ሰማይና ምድር በዚያ ቃል ለእሳት ተዘጋጅተዋል፤ ኃጥኣን ሰዎች እስከሚጠፉበት እስከ ፍርድ ቀንም ተጠብቀዋል፡፡ነገር ግን ወንድሞቻችን ሆይ÷ ይህን አትርሱ፤ በእግዚአብሔር ዘንድ አንዲት ቀን እንደ አንድ ሺህ ዓመት÷ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን ነውና፡፡..... ሐዋ. 24÷1-21፡- በአምስተኛውም ቀን ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ ከመምህራኑና ጠርጠሉስ ከሚባል አንድ ጠበቃ ጋር ወረደ፤ ጳውሎስንም በአገረ ገዢው ዘንድ ከሰሱት፡፡..... (ተጨማሪ ያንብቡ) #የዕለቱ_ምስባክ መዝ. 49÷2 እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ ወአምላክነሂ ኢያረምም እሳት ይነድድ ቅድሜሁ፡፡ ትርጉም፦ እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል፡፡ አምላካችንም ዝም እይልም፤ እሳት በፊቱ ይነድዳል በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ አለ፡፡ #የዕለቱ_ወንጌል ማቴ. 24÷1-25፡- ጌታችን ኢየሱስም ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ሄደ፤ ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው የቤተ መቅደሱን የሕንጻ አሠራር አሳዩት፡፡ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው÷ “ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፤ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም፡፡.....” (ተጨማሪ ያንብቡ) #የዕለቱ_ቅዳሴ፦ ቅዳሴ አትናቴዎስ ምንጭ፡- (የማቴዎስ ወንጌል 24፥1 ትርጓሜ፣ መዝገበ ታሪክ ቁጥር 2፣ ግጻዌ)
Show all...
👍 4
መጋቢት - 27 መድኃኔዓለም መጋቢት ሃያ ሰባት በዚችም ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለም ድኅነት በሥጋ ተሰቀለ። ፈጣሪዋ በእንጨት መስቀል ላይ ተዘርግቶ ተሰቅሎ በአየችው ጊዜ ፀሐይ ጨለመች እርሱም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የነሣትን ለባዊት ነባቢት የሆነች ነፍሱን ከሥጋው ለያት ሐዋርያ ጴጥሮስ በሥጋ ምውት ሲሆን በመለኮት ሕያው ነው እንዳለ ነፍሱ ከመለኮት ሳትለይ ከሥጋ ተለየች በዚያ ጊዜ ሥጋ ከመለኮት ሳትለይ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ነበር። እንዲሁም ነፍስ ከመለኮት ጋራ አንድ ሁና እሥረኞች ነፍሳትን ትፈታቸው ዘንድ ወደ ሲኦል ወረደች። መድኃኔዓለም ክርስቶስ ስለ ዓለም ሁሉ ድኅነት በሥጋ ተሰቅሏልና ሞቱን በአንክሮ እናዘክር ዘንድ የልቡናችን ዐይን ወደ ቀራንዮ እናንሳ! እነሆ ክፉዎች አይሁድ ሰይጣን ልባቸውን አስቶታልና እንደ ወረንጦና እንደ ወስፌ እንደመርፌም ያለ 300 እሾህ ያለው ስረወጽ አድርገው አክሊል ሠርተው ከፍላት አግብተው በጉጠት አንስተው ‹ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሥ ነህ ዘውድ ይገባሃል› ብለው በራሱ ላይ ደፉበት፡፡ ለአክሊለ ሦኩም 73 ስቁረት ነበረው፡፡ እራሳቸው እንደ መሮ፣ ወርዳቸው እንደ ሞረድ 4 ማዕዘን አሠርተው ቁመታቸውን ክንድ ከስንዝር፣ ስለታቸውን እንደ ወስፌ አድርገው 73 ችንካር ሠርተው በ73ቱ ስቁረት አግብተው በጌታችን በራሱ ላይ ቢመቱበት ሥጋ ለሥጋ ገብቶ መሐል ልቡን ወጋው፡፡ አክሊለ ሦኩን በራሱ ላይ አድርገው ሲያበቁ ከቤት ወደ አደባባይ እያመላለሱ ‹‹ንጉሥ ሆይ!...›› እያሉ ምራቃቸውን እየተፉበት ተዘባበቱበት፡፡ መስቀል አሸክመው ከሊቶስጥራ እስከ ቀራኒዮ ድረስ እያዳፉ ሲወስዱት 136 ጊዜ በምድር ላይ ጣሉት፡፡ ከኋላ ያሉት ‹‹ፍጠን›› እያሉ ገፍትረው ይጥሉታል፣ ከፊት ያሉት ደግሞ ‹‹ምን ያስቸኩልሃል?›› እያሉ መልሰው ገፍትረው ይጥሉታል፡፡ ከዚህ በኋላ ክፉዎች አይሁድ ቁመታቸውን ክንድ ከስንዝር ስለታቸው ደግሞ እንደ ወስፌ የሆኑ 5 ችንካሮችን ሠርተው ሳዶር በሚባለው ችንካር ቀኝ እጁን፣ በአላዶር ግራ እጁን፣ በዳናት ሁለት እግሮቹን፣ በአዴራ መሐል ልቡንና በሮዳስ ደረቱን ቸንክረው የአዳም ራስ ቅል ባለበት ቀራኒዮ አደባባይ ላይ ሰቅለውታል፡፡ ክፉዎች አይሁዶች መድኃኒታችንን በሁለት ግንዶች መካከል አድርገው 65 ጊዜ ከግንዱ ጋር አጋጩት፡፡ ቀያፋ በሚመረምረው ጊዜ ጌታችን ‹‹አምላክነቴን አንተው ራስህ ተናገርኽ›› ቢለው አይሁድ በእጃቸው ሲመቱት እጃቸውን ቢያማቸው ድንጋይ ጨብጠው 120 ጊዜ ፊቱን ጸፉት፡፡ አይሁድ ወደ ጲላጦስ ዘንድ ሲወስዱት ‹‹ምናልባት ጲላጦስ ባይፈርድበት እንኳ እንዳይቆጨን›› ብለው 305 ጊዜ በሽመል ደብድበውታል፡፡ በአምላክነቱ ቻለው እንጂ የአንዱ ምት ብቻ በገደለው ነበር፡፡ ሰይጣን ልባቸውን ለክፋት ያስጨከናቸው ክፉዎች አይሁድ በጲላጦስ አደባባይ የጌታችንን ፂሙን 80 ጊዜ ነጭተውታል፡፡ ጲላጦስ እንደ ሕጋቸው 41 ብቻ ገርፈው እንዲለቁት ቢያዝም ክፉዎች አይሁድ ግን ጌታችንን ሲገርፉት ‹‹አሠቃቂ ግርፋቱን አይተን ልባችን እንዳይራራ›› ብለው ሰንጠረዥ ገበጣ ሰርተው ሲጫወቱ አንዱ ተነስቶ እስከ 60 እና 70 ድረስ ይገርፍና ሲደክመው ‹‹ቆጠራችሁን?›› ብሎ ይጠይቃል፡፡ ‹‹አልቆጠርንም›› ሲሉት ከድካሙ የተነሣ ‹‹እኔው ልግረፍ እንደገና እኔው ልቁጠር›› ብሎ ትቶት ሲቀመጥ ሌላኛው ይነሣና እንደዛኛው ሁሉ በተራው 60 እና 70 ይገርፈዋል፡፡ ሁሉም እንዲህ እያሳሳቱ የራሳቸውን ሕግ እየተላለፉ አይሁድ ጌታችንን ሥጋው አልቆ አጥንቱ እንደበረዶ ነጭ ሆኖ እስኪታይ ድረስ 6666 ጊዜ ጽኑ ግርፋትን ገረፉት፡፡ በእነዚህ ሁሉ ግርፋቱ ወቅት 366 ጊዜ ሥጋው ተቆርሶ መሬት ላይ ወድቋል፡፡ የመድኃኔዓለም ወገኖች ሆይ! የጌታችን ሞቱ በፈቃዱ መሆኑንና የትዕግሥቱን ብዛት አይተን እናደንቅ ዘንድ ከመጻሕፍት ጠቅሰን እንነግራችኋለን፡፡ አይሁድ ጌታችን አብርሃም ሳይወለድ በፊት እርሱ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በአንድነት በሦስትነት የሚመሰገን አምላክ መሆኑን ቢነግራቸው ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፡፡ እሱ ግን ጊዜው ገና ነበርና ተሰውሮአቸው በመካከላቸው አልፎ ሲሄድ በፍጹም አላዩትም ነበር፡፡ በቅዱስ ወንጌል ላይ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፡- ‹‹አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ፥ አየም ደስም አለው። አይሁድም:- ገና ሃምሳ ዓመት ያልሆነህ አብርሃምን አይተሃልን? አሉት። ኢየሱስም:- እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው። ስለዚህ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወራቸው ከመቅደስም ወጥቶ በመካከላቸው አልፎ ሄደ ›› ዳግመኛም በዮሐንስ ወንጌል ላይ እንደተጻፈው አይሁድ መድኃኔዓለምን ሊይዙት የጦር መሣሪያቸውን ሰብስበው ወደ ጌቴሴማኒ በመጡ ጊዜ ‹‹ማንን ትፈለጋላችሁ?›› ቢላቸው ‹‹የናዝሬቱን ኢየሱስን እንፈልጋለን›› ሲሉት ‹‹እኔ ነኝ›› ቢላቸው ከአንደበቱ የወጣውን መለኮታዊ ቃል ብቻ መቋቋም አቅቷቸው መሬት ላይ ወድቀው ተዘርረዋል፡፡ (ዮሐ.18 ) እናም የጌታችን ሞቱ በፍጹም ፈቃዱ ባይሆን ኖሮ በጌቴሴማኒ ሊይዙት የመጡት ክፉዎች አይሁድን እንደመጀመሪያው ሁሉ በተሠወራቸው ነበር አሊያም ከአንደበቱ በሚወጣው አምላካዊ ቃሉ ብቻ ባጠፋቸው ነበር፡፡ በመጨረሻ ግን ጌታችን ወደዚህች ምድር የመጣበትን ዓላማ ይፈጽም ዘንድ እንዲገድሉት በፈቃዱ ራሱን አሳልፎ ቢሰጣቸው ያን ሁሉ እጅግ አሠቃቂ መከራ አደረሱበትና ለመስቀል ሞት አበቁት፡፡ ወዮ ለዚህ ለመድኃኒዓለም ፍጹም ትዕግስት አንክሮ ይገባል! ዓለምን በመዳፉ የያዘ አምላክ በአይሁድ እጅ እንደሌባ ተያዘ፡፡ ሠራዊተ መላእክት ለምሥጋና በፊቱ የሚቆሙለት መድኃኔዓለም እርሱ ሊፈረድበት በፍርድ አደባባይ ቆመ፡፡ በእስራት ያሉትን የሚፈታ እርሱ በብረት ችንካር ተቸነከረ፡፡ ሰማይን በከዋክብት ምድርም በአበባ ያስጌጠ እርሱ ግን የእሾህ አክሊል በራሱ ላይ ደፋ፡፡ ዓለሙን ሁሉ በቸርነቱ የሚመግብ እርሱ ተጠማሁ አለ፡፡ ወዮ የመድኃኔዓለም የማዳኑ ምሥጢር ምንኛ ድንቅ ነው!!! ለዚህ ባሕርይው አንክሮ ይገባል፡፡ በመድኃኔዓለም ክርስቶስ ሞት በአንድነት እናለቅስ ዘንድ ሁላችሁም ኑ መድኃኒታችን ሞቷልና ፍጥረታት ሁሉ አልቅሱ መከራን የተቀበለ ጌታችን ሞቷልና። የጌታችን ወዳጆቹ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ገንዘው በሐዲስ መቃብር ቀበሩት በሦስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ ተነስቷል። ዳግመኛም መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከዕርገቱ በኋላ ለቅዱሳን ሐዋርያት የሞቱን መታሰቢያ እንዲያደርጉ ነግሯቸዋልና፡፡ ሕማሙንና ሞቱንም እንዲዘክሩ አዟቸዋልና አሁንም ያንን ሁሉ የመድኃኔዓለምን ሞቱን ያላሰበና የሞቱን መታሰቢያ በዓል ያላከበረና እርሱንም የማይወደው ቢኖር ዕድል ፈንታው ጽዋ ተርታው ከአይሁድ ጋር ነው፡፡ የአምላካችንን የመድኃኔዓለምን ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ተባብረን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ከእርሱ ለመተባበር ያብቃን። አሜን @KaleEgziabeher
Show all...
👍 22
👍 4
ምናልባት ላልሰማችሁ እድሉ እንዳያመልጣችሁ 1 ቀን ይቀራል።
Show all...
👍 2
👍 14
ከምን ዓይነት ነገር መላቀቅ እንዳለብህ ታዉቃለህ ?? ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ምድራዊ ምኞት ምን ያህል አስከፊ እንደሆነና እንዴት ከዚህ ነገር ነፃ መውጣት እንዳለብን እንዲህ በማለት ይመክሩናል፦ "ወዳጄ ከምድራዊ ምኞትህ ተላቀቅ ከምን አይነት ነገር መራቅ እንዳለብህ ታውቃለህ? ከምድራዊ ፍላጎት ከመሳሰሉት ራቅ ፍፁም የመንፈስ ነፃነት እንዲኖርህ ከፈለክ ከምድራዊ ምኞቶችህ ተላቀቅ። በእርጋታና በግልጽነት ላውጋህ እጅግ አብዝተህ የምትጨነቅባቸው ልብህን የተቆጣጠሩት ታላላቅ ምድራዊ ተስፋዎች አሉህ። እነኚህም ሃሳብህን ሁሉ ይቆጣጠሩታል ብቻህን በምቶንበት ጊዜ በምናብ ይመጡብሃል በምትተኛ ጊዜ ህልምህ ሁሉ ይህ ይሆናል ልትክዳቸው የማትችለው ነገር ግን የምታውቃቸው ምድራዊ አላማዎች አሉህ። ተፈላጊነት እንዲኖርህ ትመኛለህ፣ ስልጣን እንዲኖርህና፣ ኃያል እንድትሆን፣ ዕውቅና እንዲኖርህና ስምህ ከጽንፍ እስከ አጽናፍ እንዲናኝ ትፈልጋለህ። በሀብት፣ በምድራዊ ስልጣን፣ በዕውቀት በማዕረግና በመልክ ዝነኛ የመሆን ተስፋ አለህ ፣ በመኖሪያ ቤት፣ በምግብ፣ በልብስና በሰውነት ደስታን በሚሰጡ ነገሮችም ተስፋ አለህ። ዓለም በአንተ እንጂ አንተ በዓለም እየኖርክ አይደለም። ስለዚህ አንተነትህ በዚህ ምድራዊ ተስፋ የታጠረ ነው። መንፈስህም ከስጋ ፍላጎቶች መራቅን ትመኛለች ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስ በሥጋ ላይ ይመኛልና። (ገላ.5፥17) እነዚህ ሥጋዊ ተስፋዎችና ፍላጎቶች ስኬታማ ስለማይሆኑ ግራ ትጋባለህ። ይህን በእርግጥ ቅሬታን ያመጣብሃል። እነዚህን ነገሮች ሁሉ ትናፍቃለህ ነገር ግን ናፍቆትህ አያስደስትህም። ስለዚህ ለምኞትህ ሁሉ ማስተካከያ ታበጅለት ይሆናል ምናልባትም ይጠቅሙኛል የምትላቸውን ሰዎች ማግኘት፣ በምኞትህ ዙሪያ የተጻፈ መዛግብት ማገላበጥ ትፈልግ ይሆናል በዚህም ላይ ታች ስትል ምኞትህን ለማሳካት ትታገላለህ እንዲሆን ሌላ ዘዴ ልትፈጥር ትችላለህ ይሁን እንጂ ሳይሳካልህ ቀርቶ በሃሳብና በጥረት ትታክታለህ ከዚያም ትበሳጫለህ። ከዚህ የከፋው ነገር በእነዚህ ምኞቶችና ተስፋዎች ስኬታማ አለመሆን ምክንያት ለከፋ ሕይወት መዳረግህ ነው። እንደምትሰለች አውቃለሁ አዘንኩልህ እስከመቼ ድርስ በምኞት ማዕበል ውስጥ ትኖራለህ? የምትመኘውን ባገኘህ ጊዜ ደስተኛ ትሆናለህ ይህ ደስታ ስለማያረካህ ሌላ አዲስ ደስታን እንድትመኝ ያደርግሃል። ልክ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ "ከዚህ ውሃ የሚጠጣ ሁሉ እንደገና ይጠማል" (ዮሐ.4፥13 ) እንዳለው እርካታ አይኖርህም። ስለዚህ ውድ ወንድሜ ነገሩን በእርጋታ ከአንተ ጋር ለመነጋገር እፈልጋለሁ። "አለሙም ምኞቱም ያልፋል" (1ኛ ዮሐ.2፥17) ታዲያ ይህን ቃል ካወክ ለምን አለማዊ ፍላጎቶችን ለማግኘት ትታክታለህ? አንተ ልክ እንደ እኔ ለመሬት እንግዳ ነህ። ዓለም የሚያልፍበት አንተም የምትጠፋበት ጊዜ ይመጣል ልክ ከእናትህ ማህጸን ራቁትህን እንደመጣህ እንደዚሁ ራቁትህን ትመለሳለህ።(ኢዮ. 1፥21) ዓለምን ከነክብሯ ከነሀብቷና ከነስሟ ለቀሃት እንድትሄድ በመገደድ እንደ ማንኛውም ሰው ወደ መሬት ትወርዳለህ። ከዚያም ከዓለም ያገኘኽውን ደስታ ታወቂነት ወይም ምንም ይሁን ምን ሥጋህን ከሞት ሊከላከልልህ አልያም ሥጋን ከሚበሉት ትል ሊከላከልልህ አይችልም። በፍርድ ቀን ከዓለም ሀብትና ንብረት ውጭ በእግዚአብሔር ፊት ትቆማለህ። መልካም ይሁን ክፉ የሰራኸው ሥራ እንጂ የዓለም ቁሳዊ ነገር አይከተልህም። ስለዚህ ውድ ወንድሜ ምኞትህንና ተስፋህን በዓለም ላይ በማድረግ መታወክህ ለአንተ ጥሩ አይደለም ይህችን ምድር እሾህንና አሜኬላን እንዳበቀለችልህ ትዘነጋለህን!!! ከእኛ በፊት የነበሩና ምድርን ሊረግጧት የማይገባት የቅዳሳን አባቶችና እናቶች አሠራርና ፈለግ ተከተል ቅድስናቸውን ያገኙት ይህችን ዓለም በመውደድ ሳይሆን በመናቅ ነበር ሁኔታዎች ሁሉ ተመቻችተውላቸው ሳለ በዓለም ስላሉ ነገሮች ለማንኛውም ጉጉት አልነበራቸውም ። ውድ ወንድሜ አሁንም ምኞት አሉህ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና (ማቴ.6፥21) የሥጋን ምኞቶችን ስለተቆራኘ መንፈሳዊ ነገሮች በአንተ አመለካከት ዋጋቸውን ያጣሉ ይህ የክብር ጌታ እንደተፈተነው ዓይነት ፈተና ነው። (ማቴ.4፥8-9) አሁን አስተውል እነዚህን ነገሮችን ብትይዝ በጥሩ ምኞት ያላሰርካት ነፍስህን ብታጣ ጥቅሙ ምንድን ነው? ነፍስህ ነጻነትን ትሻለች። ከስጋ ምኞት ተላቀን የመንፈስ ፍሬ የሆኑትን " የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣  እምነት፣ የውሃት፣ ራስን መግዛት ነው።"(ገላ.5፥22) እንዳለው ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ እነዚህን ገንዘብ አድርገን እንድንኖር እግዚአብሔር አምላክ ይርዳን!! (የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ "የመንፈስ ነጻነት "ከሚለውና በዲ/ን ደስታ ፍፁም ከተተረጎመው መጽሐፍ ላይ የተወሰደ። ምክር ወተግሳፅ እንዳቀረበው) @yehiwot_meaza @yehiwot_meaza @yehiwot_meaza
Show all...
👍 28
ጾም እጅግ ግሩም የሆነ ነገር ነው፡፡ ኃጢአታችንን እንደማይጠቅም አረም ከውስጣችን ይነቅለዋል፡፡ እውነተኛው የጽድቅ ተክልም በውስጣችን ልክ እንደ አበባ እንዲያብብ ይረዳዋል፡፡ (ቅዱስ ባስልዮስ) ከምግባራት ሁሉ ታላቁ ጸሎት ነው ነገር ግን የእርሱ መሠረቱ ጾም ነው፡፡ የምንጾምበት ምክንያት ርኩስ የሆነውን የሰይጣንን መንፈስ በነፍሳችን ውስጥ እንዳያድር ለመጠበቅ ነው፡፡ ሥጋችንን ለጾም ባስገዛነው ጊዜ ነፍሳችን ነፃነትን፤ ጥንካሬን ሰላምን፣ ንጽሕናን እንዲሁም እውቀትን ለመለየት እንድትበቃ ትሆናለች፡፡ (ጻድቁ ዮሐንስ ዘክሮስታንድ)
Show all...
👍 32
#New🔴በፆም ወቅት ልናደርጋቸው የሚገቡ?! || ድንቅ ትምህርት| ዲያቆን አቤል ካሳሁን | Kendil media @... https://youtube.com/watch?v=NREY2XOg-BQ&si=zd9EQBP485zQ0ZMT
Show all...
👍 5
ዘወረደ (የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት ) የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት ዘወረደ ይባላል፡፡ ‹‹ዘወረደ እምላዕሉ አይሁድ ሰቀሉ›› የሚልና ይህንን የመሳሰለ ጌታ እኛን ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን ከሰማያት መውረዱን ከድንግል ማርያም የእኛን ሥጋ መዋሐዱን የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ ሌላም ስም አለው #ጾመ_ሕርቃል ይባላል፡፡ ይህ ጾም የጾም መግቢያ የመጀመሪያ ሳምንት የምንጾመው ጾም ሲሆን #ሕርቃል የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ #ሕርቃል ማን ነው? ለምንስ በስሙ ተሰየመ? በ614 ዓ.ም ኪርዮስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ ውስጥ ሲገባ ንግሥቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው፡፡ ቢነካው አቃጠለው ዲያቆናቱን አሸክሞ ሌላውን ንዋየ ቅድሳት ዘርፎ 60ሺ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ 3ሺ የሚሆኑትን ማርኮ ከተማዋንም ቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡ በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ14 ዓመት በኋላ በ628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲየኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል ይነግሩታል። እርሱም ሐዋርያት ሰውን የገደለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርገው አላቸው እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማለን ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን በሚገባ ጾመውታል፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልና የተማረኩ ክርስቲያኖችን ለመመለስ ሕርቃል ጦር መዝዞ በኪርዮስ ላይ ተነሳበት ድል ለሕርቃል ሆነና መስቀሉን ያለበትን አጥቶ ሲቸገር መስቀሉን ሲቀብርና ዲያቆናቱን ሲያስገድል በመስኮት ሆና ያየችው ከኢየሩሳሌም የተማረከች አንዲት ብላቴና አሳይታው አውጥቶ በልብሰ መንግሥቱ ጠቅልሎ ወደ ቁስጥንጥንያ ተመለሰ፡፡ የተማረኩት በሙሉ ነጻ ወጡ ይህን ለማሰብ ለማስታወስ በተጨማሪ በኃጢአት ላይ ድል እንድናገኝ መንፈሳዊ ጦር በውስጣችን እንዲበዛልን መስቀልህ ከምርኮ እንደተመለሰ እኛንም ከኃጢአት ምርኮ መልሰን ለሕርቃል ድል መንሳትንና በጠላቶቹ ላይ ኃይልን እንደሰጠኸው ለእኛም በኃጢአት ላይ ድል መንሳት መንፈሳዊ ኃይልን ስጠን እያልን እንጾመዋለን፡፡ በጌታ ጾም ላይ እንዲጾም የሆነበት ምክንያት ጾሙ የጌታ ጾም በሚጾምበት ወቅት ላይ ስለተጾመ ቤተክርስቲያናችን አብራ ደንግጋዋለች፡፡ እዚህ ላይ በዚያን ጊዜ ለሕርቃል ሕዝቡ ሱባኤ ይዞለታል፡፡ ዛሬም እኛ ለቤተክርስቲያን ያደረግነውን በማሰብ እግዚአብሔር አምላክ ለሕርቃል የሰጠውን በጠላቶቹ ላይ ድል መንሳትን ለእኛም እንዲሰጠን የምንጠይቅበት ስለሆነ የመጀመሪያውን ሳምንት በሕርቃል ሰይመን ጾሙን እንጾማለን፡፡ የእኛ ጠላት የጨለማ ገዥ የሆነው ዲያቢሎስ ነውና እሱን ደግሞ በጾም እንደምናሸንፈው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል፡፡ «ዘወረደ» ማለትም በቀጥታ፣ ቃል በቃል ሲተረጐም «የወረደ» ማለት ነው፡፡ ይህም በምስጢሩ አምላክ ወልደ አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤዛ ዓለም በቅዱስ ፈቃዱ ሰው ሆኖ ከሰማየ ሰማያት፣ ከባሕርይ ልዕልናው በትሕትና ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመላክት፣ ይህም የሚታወስበት፣ የሚወሳበት የዐቢይ ጾም አንደኛው ሳምንት ነው፡፡ ዮሐ.3፥13፡፡ ሳምንቱ ሙሴኒ የተባለበትም ምክንያት በዚሁ ሳምንት መጀመሪያ የሰኞ ዕዝል «ከመዝ ይቤ ሙሴ ፀዓቱ እምትእይንት» «ሙሴ ከከተማ መውጣቱ እንደዚህ ነው አለ» ስለሚል እንደዚሁም የዚሁ ዕለት ማለት የሰኞ አቡን «ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት ምድር ሰናይት» እያለ የሙሴን ታሪክ ስለሚያጠቃቅስ ሳምንቱ ሙሴኒ ተባለ፡፡ነቢያትም አርባ አርባ ቀን ጾመው ከአለፉ በኋላ የሙሴ ሕግና ትንቢተ ነቢያት ፈጻሚ የሆነው ምላካችን እንደ እነሱ 40 ቀንና 40 ሌሊት መጾሙን የሚያስታውስ ነው፡፡ /ዘፀ.24፥18፤ 1ኛ.ነገ.19፥8፤ ማቴ. 4፥1-4/፡፡
Show all...
👍 20
👏👏👏👏👏👏👏ቅበላ👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏                ቅበላ   ቅበላ_ መቼም ቅበላ የሚለው ቃልን ስንሰማ ሁላችንም ጀሮ ላይ አንድ ነገር ያቃጭላል እሱም ፆም ከመግባቱ በፊት የምናደርገው ተግባር ነው። በመሰረቱ ቅበላ ማለት በእንግድነት ለሚመጣው እንግዳ ለእንግዳው የሚመጥነውን ያህል ክብር ለመስጠት አዘጋጅቶና ተዘጋጅቶ መቀበል ነው:: ስለዚህ ለአንድ ነገር ቅበላ ስናደርግ ያንን የምንቀበለውን ነገር በሚመጥን መልኩ መሆን አለበት። ለምሳሌ አንድ መንፈሳዊ መነኩሴ ወደ ቤታችን በእንግድነት ቢመጣ ለመነኩሴው ቅበላ የምናደርግለት እሱን ሊመጥን በሚችል መልኩ ነው የፀሎት ቤት አዘጋጅተን እግሩን አጥበን ጉልበት ስመን መኝታ ክፍሉ ውስጥ ቅዱሳት ስዕላትን ወይም መፅሐፍ ቅዱስ አስቀምጠን.  .  . የመሳሰሉትን ነገሮች እንደ እኛ አቅም አዘጋጅተን ልንቀበለው እንችላለን። አልያ ደግሞ አንድ ህፃን ልጅ ወደ ጎጆአችን በእንግድነት ቢመጣ መኝታ ክፍል አዘጋጅተን የተረት መፃሕፍቶችን አሰናድተን የህፃናት ፊልም ከፍተን የህፃናት መጫወቻ አወጋጅተን ቅበላ ልናደርግለት እንችላለን። ልክ እንደዚሁ ሁሉ ፆምንም ስንቀበል ከፆም ጋር የሚስማማ ነገር ማድረግ አለብን እንጅ ፍፁም ተቃራኒ የሆነ ተግባር ማድረግ ትልቅ ስህተት ነው። ፆም ሊገባ ነው ብለን ሆዳችን እስኪተረተር የምንበላ ጨንጓራችን እስኪላጥ የምንጠጣ ዝሙት የምንፈፅም በየ ጭፈራ ቤቱ የምንዞር ከሆነ ይህ የፆም ቅበላ ይባላልን? በጭራሽ አይባልም።እንደውም ይህ የሚያሳየው ፆሙን ሳንፈልግ እንደምንቀበለው ነው። "ነብይን በነብይ ስም የሚቀበል የነብይን ዋጋ ይወስዳል" ማቴ 10:41 እንዳለ ጌታችን ፆምን ስንቀበል በፆም ስም በፆም ተግባር መሆን አለበት። እንደውም አንዳንድ የበቁ አባቶች የአብይ ፆም ሊገባ ሲል ፆሙን በፆም ይቀበሉታል።በእርግጥ ይህ ለእኛ ሊከብደን ይችላል ቢሆንም ፆሙን በፆም መቀበል ቢያቅተን እንኳን ፆሙን ከፆም ጋር በሚስማሙ መልካም ተግባራት መቀበል እንችላለን። ፆም ከመግባቱ በፊት ንስሐ መግባት ፣ የበደሉንን ይቅር ማለት ፣ የበደልናቸውን ይቅርታ መጠየቅ ፣ የተጣላናቸውን መታረቅ ፣ መመፅወት ፣ ፆሙ የበረከት እንዲሆንልን መፀለይ ፣ መንፈሳዊ ምግባራትን መላበስ ፣ ከመጠን ያለፈ ደስታን ከራስ ማራቅና የመሳሰሉትን ከእኛ ጋር የሚስማሙትን መንፈሳዊ ተግባራት ከንስሐ አባታችን ጋር ተመካክረን ተግባራዊ በማድረግ ቅበላ ማድረግ ይኖርብናል። በዚህ መሰረት የሚፈፀም ቅበላ ፆሙ ከመግባቱ በፊት መንፈሳችን እንዲዘጋጅ ከማድረጉም ባለፈ እግዚአብሔር ከፆሙ በፊት አስቀድሞ እንዲባርከን ያደርጋል። ወዳጄ ሆይ የአንተ ቅበላ ከየትኛው ነው? መቼም በስካር በከርስ መሙላት በጭፈራና በዝሙት ቅዱሱን እንግዳ #ፆምን እንደማትቀበል ተስፋ አደርጋለሁ። አበው "ከምግብ ብቻ በመከልከል እንጾማለን አትበሉ .. ከክፉ ግብር መራቅ ጾማችንን ትክክል ታደርጋለች" ይላሉ:: በዚህም የአባቶቻችን ልጆች እንባላለን አባቶቻችን የወረሷትን መንግስት በእውነት እንወርሳለን:: . . . ኦ ጌታ ሆይ! ቸሩ አምላኬ ሆይ ሀጢያቴ እንደ ምድር አሸዋ እንደ ሰማይ ከዋክብት በዝቶ በደሌ ስፍር መለኪያ ጠፍቶለት ክፉዋ ምላሴ ፤ የተበረዘው ጭንቅላቴ ፤ የደነደነው ልቤ ሳያሰለችህ ሳያስቀይምህ ቀናትን በሳምንታት ሳምንታትን በወራት ወራትን በአመታት ተክተህ ለዚህች ቀን ስላደረስከኝ በደካማ አንደበቴ አመሰግንሀለሁ። እንደ እውነቱ ዘመኑ ዓመተ ምህረት ባይሆን ኑሮ እኔ ገና ድሮ ነበር የምቀሰፍ! ገና ድሮ ነበር የምጠፋ! ግን አምላኬ ሆይ አንተ እንደ ሰው ስላልሆንክ ለፍርድ አልቸኮልክም በፍቅር ታገስከኝ በስስት ዓይንም ተመለከትከኝ። ኦ አምላኬ ሆይ! እኔዋ ደካማይት ልጅህ ያለፈውን ፆም በቅጡ ሳልጠቀምበት ፍቃድህን ሳልፈፅም ደካሞችን ሳልረዳ የደከሙትን ሳልጎበኝ ያዘኑትን ሳላፅናና የሰጠህኝን ቅዱስ ቀናት እንዲሁ በከንቱ አሳለፍኩ። ጌታ ሆይ እኔ ደካማ እንደሆንኩ ታውቃለህ አንተ እኮ የልብና የኩላሊትን የምትመረምር ቅዱስ አምላክ ነህ። እናም ድካሜን ታውቃለህ ስንፍናዬን ታውቃለህ አምላኬ ሆይ ታዲያ እንደዚህ ደካማ ሰው ሁኜ ፆምህን እንዴት ልፆም እችላለሁ? እንዴት 40 የፆም ቀናት በፍቃድህ ላሳልፍ እችላለሁ? የድንግል ልጅ አማኑኤል ሆይ አንተ ካልረዳኸኝ አንተ ካልደገፍከኝ ታዲያ ይህን ነገር እንዴት ልወጣው እችላለሁ? አንተ እኮ መቅደላዊት ማርያምን ወደ ቅድስትነት ሙሴ ፀሊምን ከገዳይነት ወደ ባህታዊነት ሳኦልን ወደ ሰባኪነት ለውጠሀል። ጌታዬ ሆይ ታዲያ እኔን አንተ ካላገዝከኝ በእኔ አቅምማ እንዴት ይሆናል? የቅድስት ድንግል ማርያም ልጅ መድኃኒአለም ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በእናትህ በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት በቅዱሳን መላዕክት አማላጅነት በፃድቃን ሰማዕታት ፀሎትና ምልጃ እያመንኩና እየተማፀንኩ ከሰይጣን ፍላፃዎች ሁሉ እንድትታደገኝና ለደካማዋ ልጅህ ትደርስላት ዘንድ በሀጢያት በተዳደፌ አንደበቴ እለምንሀለሁ! ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ፆሙ የበረከትና የፍሬ እንዲሆንልን ከወዲሁ እመኛለሁ!
Show all...
👍 22
"አስታውስ" (አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ) † ደካማነትህን አስታውስ፣ ያንጊዜ በጣም ጠንቃቃ ትሆናለህ፣ ሊጎዱህ በሚችሉ በትምክህትና በውዳሴ ከንቱም አትሸነፍም፡፡ † የተሰጠህን በፍቅር የተሞላ የእግዚአብሔርን ቸርነት አስታውስ፣ ይህም በምስጋና የተሞላ ሕይወት እንድትመራ ያደርግሃል። በእግዚአብሔር ፍቅርና ሥራ ላይ ስትታመን ፍጹም የሆነ እምነት በልብህ እያደገ ይመጣል፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ያሳለፍከው ጊዜ ደግሞ በእምነት እንድትኖር ያበረታታሃል፡፡ † የሰዎችን ፍቅርና ካንተ ጋር ያሳለፉትን መልካም ጊዜ አስታውስ፡፡ የሰዎችን ቀናነት ትጠራጠር ዘንድ ወይም ያደረጉብህን ክፉ ነገር ታስብ ዘንድ ይገባሃልን? የቀደመ ፍቅራቸው ስለ እነርሱ ይማልዳል ያንተንም ቁጣ ያበርዳል፡፡ † ሞት እንዳለ አስታውስ፣ እንዲሁ በዓለም ያለ ፈተናም እንደሚያልፍ፡፡ "ሁሉ ከንቱ ነው፣ ነፋስንም እንደመከተል ነው፡፡" መክብብ 1፥14 ማለትን ትረዳለህ፡፡ † በእግዚአብሔርፊት መቆምህንና እርሱም እንደሚመለከትህ አስታውስ፣ ያኔ ኃጢአት አትሰራም እግዚአብሔርን ታየዋለህና፡፡ † ስለ አንተ የፈሰሰውን የክርስቶስን ክቡር ደም አስታውስ፡፡ በዚህም ሕይወትህ ያለውን ዋጋ በእርግጥ ታውቃለህ፤ በዓይኖችህ ፊት የከበረ ይሆናል፣ ስለዚህም በከንቱ በመኖር አታጠፋውም፣ "በዋጋ ተገዝታችኋልና" 1ኛ ቆሮ.6:20 እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ፡፡ † በወላጆችህ እምነት በተጠመቅህባት ቦታ ለእግዚአብሔር የገባኸውን ቃል አስታውስ፤ ዲያብሎስን፣ ሥራዎቹን ሁሉ፣ ሐሳቦቹንና ጥበቡን፣ ኃይሉንም ትክድ ዘንድ፡፡ † በዚህ ዓለም እንግዳመሆንህንና ወደ ሰማያዊው ቤትህ እንደምትመለስ ዘወትር አስታውስ፡፡ ያን ጊዜ በዚህ ዓለምና በደስታው ተስፋ ማድረግን ትተዋለህ፡፡ † በጠባቡ በር መጓዝ ወደ መንግስተ ሰማያት እንደሚያደርስህ አስታውስ፡፡ ሰፊው ደጅ ፊት ለፊትህ ተከፍቶ ብታየው፣ አልፈኸው ሂድ ከእሱም ራቅ፣ በእርሱ የሄዱ እንዳሉ አልቀዋልና፡፡ † ዘላለማዊውን ሕይወትህን አስታውስ፣ ሁልጊዜም ስለዚህ ትጋ፡፡ † የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህንና እርሱን መምሰል እንዳለብህ አስታውስ፡፡ እውነተኞች ከሆኑት ከእግዚአብሔር ልጆች ጋር አካሄድህን አስተካክል፡፡ † የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ መሆንህን አስታውስ፡፡ በውስጥህ ያለውንም ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አታሳዝን፡፡ ዘወትርም ቅዱስ የእግዚአብሔር ማደሪያ ሁን፡፡ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
Show all...
👍 33
ውድ ስጦታ ኹሌ ስጦታን የሚሰጥ አንድ ሰው ከሚሰጣቸው ስጦታዎች ኹሉ በአካል ሊለይ ሲል የሚሰጠው ስጦታ ልዩ ነው። መለየቱ እስከ መጨረሻው ከኾነና ስጦታውም በመለያው ሰዓት የሚሰጠው ስጦታ ከኾነ ደግሞ የስጦታውን እጅግ ክቡርነት የሚያሳይ ይኾናል። በተለይ ሰጪው በሞት አፋፍ ላይ ኾኖ ነባቢት ነፍሱ ከሥጋው ልትለይ ደርሳ በእንጥፍጣፊ ነቢብ ስጦታውን ለማን እንደሚሰጣት የሚናዘዛት ከኾነች የስጦታዋ ውድነት ከሕይወትም ይልቃል። 'ይህችን ሞቱ እስክትመጣ ድረስ ለሚወዳቸው ሰዎች እንኳን ያልሰጣት ምን ያህል ቢወዳትና ቢሰስታት ነው' ያሰኛል። ሊሞት ሲል የሚሰጣትም በጣም ለሚወደው ሰው መኾኑ አያጠራጥርም። እመቤታችን እንደዚህ ውድ የኾነች የሕይወት ስጦታ ነች። (ዮሐ.19:26-27)። (ከየመሰጠት ሕይወት መጽሐፍ ገጽ 71 የተቀነጨበ።) @KaleEgziabeher
Show all...
👍 36
👍 18
መንፈሳዊ ጉባኤ: ❖ ❖ ❖ ኪዳነ ምህረት (የካቲት 16) ❖ ❖ ❖                ❖ ❖ ❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖ ❖ ❖    ኪዳነ ምህረት ማለት የምህረት መሐላ ማለት ነው፡፡ ከ33ቱ በዓላተ እግዝእትነ ድንግል ማርያም አንዱ ነው፡፡ እመቤታችንም ከጌታችን መቃብር እየሄደች በምትለምንበት ጊዜ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉምና ምን ልታመጣብን ነው በማለት ሊጣሏት ሲመጡ ጌታችንም ከዓይናቸው ሰውሯታል አይሁድም ጠባቂ ቢያቆሙ እመቤታችን ዕለት ዕለት መሄዷን አላቋረጠችም እመቤታችንም እንዲህ ብላ ስትጸልይ ልጄ ወዳጄዘንድ ሆይ ከስጋዬ ስጋ ከነፍሴ ነፍስ ነስተህ ሰው በመሆንህ ዘጠኝ ወር ከ5 ቀን በቻለችህ ማሕጸኔ ከአንተ ጋር ሀገር ለሀገር ስለ መሰደዴ መትተህ ልምናዬን ትሰማኝ  እለምንሃለሁ አለች በዚህ ጊዜ ንውጽውጽውታ ሆነ መቃብራት ተሰነጣጠቀ ጌታችንም እልፍ ከእልፍ መላዕክቱ ጋር መጥቶ ሰላም ለኪ ማርያም ምን እንዳደርግልሽ ትለሚኚኛለሽ አላት፡፡ እርሷም መታሰቢያዬን ያደረገውን ስለ ስሜ ለችግረኛ የሚራራውን በስሜ ቤተ ክርስቲያን ያነጸውን መባዕ የሰጠውን ከሃይማኖት ከፍቅር ጽናት ልጁን በስሜ የጠራውን ሁሉ ማርልኝ ከሞተ ስጋ ከሞተ ነፍስ አድንልኝ አለችው፡፡ ጌታችንም ይህን ሁለ እንዳደርግልሽ መሐልኩ ለኪ በርእስየ ወበ አቡየ ሕያው ወበመንፈስ ቅዱስ ብሎ ቃል ገብቶላት አርጓል፡፡    ሌላው በላዔ ሰብ በአማርኛ ሰው በላ ማለት ነው፤ ትክክለኛ ስሙ ግን ስምዖን ይባላል ቅምር በሚባል አገር የሚኖር እጅግ ባለጸጋ ነበር፤ እንደ አብርሃም እንግዶችን እየተቀበለ ድሆችን እየመገበ የሚኖር ጻድቅ ነበር፤ ሰይጣን በዚህ ስራው ቀናበት ሊፈትነውም በሦስት አረጋዊ ሽማግሌዎች ሥላሴ ነን ብሎ ተገለጠለት ልክ እንደ አብርሃም፤ ሐዋርያው ጳውሎስ ሰይጣን የብርሃን መልአክ መስሎ ይመጣል እንዳለ፤ እርሱም ሥላሴ መስለውት ተቀበላቸው ተንከባከባቸውም፤ ምግብ አቀረበላቸው ምግብ አንበላም የምንጠይቅህን ግን ትፈጽምልን ዘንድ ቃል ግባልን አሉት ቃል ገባላቸው እንግዲያውስ የምትወደን ከሆነ አንድያ ልጅህን ሰዋልን አሉት፤ መጀመሪያ ደነገጠ ኃላ አብርሃም ልጁን ሊሰዋ አልነበረምን እኔንም ሊፈትኑኝ ይሆናል ብሎ ለማረድ ተዘጋጀ፤ ተው የሚለው ድምጽ አልሰማም፤ አረደው አወራረደው ይዞላቸው ቀረበ፤ መጀመሪያ ቅመስልን አሉት ቀመሰው ወዲያው እነዚያ ሰዎች ተሰወሩበት እርሱም አህምሮውን ሳተ ተቅበዘበዘ ከዚያ በኃላ ምግብ አላሰኘውም የሰው ስጋ እንጂ መጀመሪያ ቤተሰቦቹን በላ ከዚያም ጓደኞቹን ጦርና የውኃ መንቀል ይዞ ከቤቱ ወጣ ያገኘውን ሰው እየገደለ ይበላል የበላቸው ሰው ቁጥር 78 ደረሰ፤ በመንገድ ተቀምጦ የሚለምን በደዌ የተመታ አንድ ደሃ አገኘ ሊበላው ወደ እርሱ ተጠጋ ግን ቁስሉን አይቶ ተጸየፈው፤ ደሃውም “ስለ እግዚአብሔር ከያዝከው ውኃ አጠጣኝ” አለው “ዝም በል ደሃ” ብሎት አለፈ፤ “አረ በውኃ ጥም ልሞት ነው ስለ ጻድቃን ስለ ቅዱሳን” አለው አሁንም ዝም ብሎት ሄደ ለሦስተኛ ጊዜ “ስለ አዛኝቷ ስለ ድንግል ማርያም” አለው፤ ሰውነቱን አንዳች ነገር ወረረው “አሁን የጠራከውን ስም እስኪ ድገመው ስለ ማን አልከኝ” አለው፤ ስለ አዛኝቷ ስለ እመቤቴ ማርያም አለው፤ ይህቺስ ደግ እንደሆነች በምልጃዋም ከሲኦል እንደምታወጣ ህጻን እያለው እናትና አባቴ ይነግሩኝ ነበር፤ በል እንካ አለው እጁን ዘረጋለት ጥርኝ ውኃ ጠብ አደረገለት ወደ ጉሮሮው አልወረደም የተሰነጠቀ እጁ ውስጥ ገባ እንጂ፤ በለዔ ሰብ ከዚያች ደቂቃ በኃላ አዕምሮው ተመለሰለት እንዲህም አለ “በአንድ ዋሻ ውስጥ ገብቼ ስለ ኃጢያቴ አለቅሳለሁ ስጋዬ ከአጥንቴ እስኪጣበቅ እጾማለሁ ወዮሊኝ ወዮታም አለብኝ አለ፤ ወደ ዋሻ ገባ ምግብ ሳይበላ ውኃም ሳይጠጣ 21 ቀን ኖሮ በርሃብ ሞተ ይላል ተአምረ ማርያም። ጨለማ የለበሱ ሰይጣናት እያስፈራሩ እያስደነገጡ ነፍሱን ወደ ሲኦል ሊወስዷት መጡ፤ እመቤታችን ፈጥና በመካከላቸው ተገኘች፤ ልጄ ወዳጄ ይህችን ነፍስ ማርሊኝ አለችው እናቴ ሆይ 78 ነፍሳትን የበላ እንዴት ይማራል አላት፤ የካቲት 16 ቀን በጎልጎታ የገባህልኝ ቃል ኪዳን አስብ ስምሽን የጠራ መታሰቢያሽን ያደረገን እምርልሻለው ብለኸኝ የለምን አለችው፤ እርሱም እስኪ ይህቺን ነፍስ በሚዛን አስቀምጧት አለ ቢያስቀምጧት ጥርኝ ውኃው መዝኖ ተገኘ፤ ስላንቺ ስል ምሬታለው ሰባት ቀን ሲኦልን አስጎብኝታችሁ ወደ ገነት አግቧት አላቸው። ቦታሽ እዚህ ነበር እያሉ ሲኦልን አስጎብኝተው ወደ ገነት አገቧት። ልመናዋ ክብሯ የልጇም ቸርነት ከሁላችን ጋር ይሁን። ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ በዕለቱ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሚቀርበውን የምስጋና ቃል እንደሚከተለው አቅርበናል መልካም በዓል፡፡            ❖ ❖ ❖ ዋዜማ ❖ ❖ ❖ ሃሌ ሉያ (፬) ርግብየ ይቤላ በእንተ የዋሃታ፤ በሐኪ ማርያም ሐዳስዩ ጣዕዋ፤ እንዘ አመቱ እሞ ረሰያ ፤ ታዕካ ሰማይ ኮነ ማኅደራ፤ ዳዊት ይሴብሕ ወይዜምር ዕዝራ ፤           ❖ ❖ ❖ ምልጣን ❖ ❖ ❖ እንዘ ዓመቱ እሞ ረሰያ ፤ ታዕካ ሰማይ ኮነ ማኅደራ፤ ዳዊት ይሴብሕ ወይዜምር ዕዝራ ፤ ዳዊት ይሴብሕ ወይዜምር ዕዝራ ፤         እግዚአብሔር ነግሠ         እንተ ክርስቶስ በግዕት እንተ ታስተርኢ እምርኁቅ ብሔር፤         በቤተልሔም አስተብረከት ዕጓለ አንበሳ ግሩመ ወለደት፡፡            ❖ ❖ ❖ ይትባረክ ❖ ❖ ❖ እግዝእትየ እብለኪ ወእሙ ለእግዚእየ እብለኪ፤ ቃል ቅዱስ ኀደረ ላዕሌኪ፡፡            ❖ ❖ ❖ ሰላም ❖ ❖ ❖ ሃሌ ሉያ (3) ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር ወገበዋትሃኒ በሐመልማለ ወርቅ፤ የሐንፁ አሕዛብ አረፋተኪ በዕንቊ ክቡር፤ ወመሠረትኪ በወርቅ ንጹሕ ይሰግዱ ለኪ ውስተ ገጸ ምድር፤ በእንተ ዕበየ ክብርኪ አምላከ ፳ኤል ውእቱ ረዳኢኪ ዘአድኀነኪ እምእደ ጸላዕትኪ፤ ወረሰየ ሰላመ ለበሐውርትኪ፡፡          ❖ ❖ ❖ መልክአ ሥላሴ ❖ ❖ ❖ ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፡ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፡ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል ፡ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል           ❖ ❖ ❖ ዚቅ ❖ ❖ ❖ ወታስተሥርዪ ኃጢአተ ሕዝብኪ ተበውሐ ለኪ፤ እም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፤ ከመ ትኩኒ ተንከተመ ለዉሉደ ሰብእ ለሕይወት ዘለዓለም፤ ለኪ ይደሉ ከመ ትኩኒ መድኀኒቶሙ ለመሐይምናን ሕዝብኪ፤ ኦ መድኀኒተ ኵሉ ዓለም ፤ ወልድኪ ሣህሎ ይክፍለነ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡          ❖ ❖ ❖ መልክአ ኪዳነ ምህረት ❖ ❖ ❖ ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ ; ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኀኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪየኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ፡፡          ❖ ❖ ❖ ዚቅ ❖ ❖ ❖ ቅንዑ ለእንተ ተዓቢ ጸጋ መድኀኒት ለነፍስ ወሥጋ፤ እስመ ርቱዓት ፍናዊሃ ጻድቃን የሐውርዎን ፤ ወኃጥአን ይስዕንዎን፤ ዘእንበለ ትብጻሕ ግብተ አሠንዩ ፍኖተ፤ ይፈኑ ለክሙ እመቅደሱ ረድኤተ መድኀኒተ መቤዛዊተ እሞ ቅድስተ፡፡ ❖ ❖ ❖ መልክአ ኪዳነ ምህረት ❖ ❖ ❖ ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘአስተማልዎ በኮከብ፤ ሶበ ብርሃኖ ተከድኑ ጽልሙታነ ራእይ ሕዝብ፤ ኪዳነ አምላክ ማርያም ወተስፋ መድኀኒት ዘዐርብ፤ ተናዘዘ ብኪ አኮኑ ሕሊና ቀዳማይ አብ፤ አመ እምገነቱ ተሰደ በኃዘን ዕፁብ፡፡          ❖ ❖ ❖ ዚቅ ❖ ❖ ❖ አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም ፤ አመ ይሰደድ እምገነት፡፡           ❖ ❖ ❖ መልክአ ኪዳነ ምህረት በዓል ❖ ❖
Show all...
👍 15
ድንግል ማርያም ሕፃኑን እያባበለች በመደነቅ ቃል ነደደች እንዲህ ስትል "ድንግሊቱን  እጸንስ ዘንድ የሰጠኝ ማን ነው? ይህንን አንድ ሲሆን የበዛ ፣ ታናሽ ሲሆን ታላቅ የሆነ ፣ ከእኔ ጋር ሲሆን በሁሉ የሞላ ሕፃን የሠጠኝ ማን ነው? .... በእኔ [ማኅጸን] ውስጥ እያለህ ከእኔም ውጪ በሁሉ ቦታ ነበርህ ፣ በወለድሁህ ጊዜም ረቂቅ አምላክነትነህም ከእኔ ውስጥ አልወጣም።  በእኔ ውስጥ ነህ ፣ ከእኔም ውጪ ነህ! ይህ ነገር ለእኔ ለእናትህን ያስደነቀኛል። የሚታየው ሰውነህን በፊቴ ባየሁ ጊዜ የማይታየው አምላክነትህን በሕሊናዬ አየዋለሁ። ቅዱስ ሆይ በሚታየው ሰውነትህ ውስጥ አዳምን አየዋለሁ ፣ በማይታየው መለኮትህ ውስጥ ደግሞ በአንተ ሕልው ሆኖ የሚኖረውን እግዚአብሔር አብን አየዋለሁ። አንተ ምንጭ ሆይ ለአንተ ለማጠጣት የጡቶችን ምንጭ  እንዴት ልከፍታቸው ይቻለኛል? ሁሉን ከገበታህ የምትመግብ ሆይ እኔ አንተን ልመግብህ እንዴት ይቻለኛል? የክብርን ነጸብራቅ የተጎናፀፍከው ሆይ እንደምን በጨርቅ ልጠቀልልህ እችላለሁ? ምን ብሎ እንደሚጠራህ አንደበቴ አያውቅም። አእላፋት ስሞች ለአንተ አይበቁህም ፣ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ስትሆን የሰው ልጅ ነህና ፣ የዳዊት ልጅ ስትሆን የማርያም ልጅ ነህና! ልጄ ሆይ ከእኔ ጋር ሆነህ ሳለ ከሰው ልጆች ሁሉ ጋር በመሆንህ አልቀናም። ለሚያምንብህ አምላክ ነህ ፣ ለሚያገለግልህ ጌታ ነህ ፣ ለሚወድህም ሁሉን ያንተ ታደርገው ዘንድ ወንድም ነህ!" የአንደበቶች ሁሉ ጌታን አንደበት እንደሌለው ያደረገው ምን ይሆን? ልጄ ሆይ አንተን በድንግልና መፅነሴን ክፉ ሰዎች እየዘለፉ ነው። ቅዱስ ሆይ ለእናትህ አንደበት ሁነኝ  ፣ አንተን ከማን እንደፀነስሁህ  ይረዱ ዘንድ ተአምርህን አሳይ። ሁሉን የምትወድደው ሆይ ስለ አንተ ብዬ የተጠላሁ ሆንሁ ፣ ለሰው ልጆች መሸሸጊያ የሆንህ አንተን በመፅነሴ መከራን ተቀበልሁ። አቤቱ በዮናስ ላይ እንደተቆጣ ባሕር በእናትህ ላይ ተቆጥቷል። ሔሮድስ የተባለ ማዕበል የባሕርን ጌታ ሊይዝህ ፈልጓል። የእናትህ ፈጣሪዋ ሆይ ወዴት እንደምሸሽ ንገረኝ" (ቅዱስ ኤፍሬም)
Show all...
👍 30
ቤትህ ውስጥ ከፍተህ የረሳኸው ባንቧ ቢኖርና ድንገት ሌሊት ከእንቅልፍህ ስትነቃ መሬቱ እንዳለ በውኃ ተጥለቅልቆ ብታገኝ በቅድሚያ ምን ታደርጋለህ? የፈሰሰውን ውኃ ለመጥረግ ወይስ የሚፈሰውን ቧንቧ ለመዝጋት ነው የምትቸኩለው? ቧንቧውን ሳትዘጋ መሬት ላይ ያለውን ውኃ ለማፈስ ብትሞክር ትርፉ ድካም ነው። ቀኑን ሙሉ ስትዝቅ ብትውል ቤትህ የሞላውን ውኃ አታጎድልም። እናስ? ቧንቧውን ዝጋዋ! በኃጢአት በወደቅህ ጊዜ መፍትሔ በማታገኝበት ነገር ላይ ጊዜህን አታባክን። ለዚህ የሚዳርገኝ መነሻው ምክንያት ምንድን ነው? ብለህ ራስህን ጠይቅ። አእምሮህ ውስጥ የሞሉትን ክፋቶች ከመቁጠር በላይ እነዚያ ክፋቶች የገቡበትን አንድ ቀዳዳ ወይም ሽንቁር ለማወቅ ጣር። እርሱን ያወቅኸው ቀን ለችግርህ ትልቁን መፍትሔ አብረህ ታገኛለህ። ያን ቀዳዳ ከዘጋህ ወይም ምንጩን ካደረቅኸው የቀረው ቀስ እያለ ተኖ መጥፋቱ አይቀርም። ከመውደቅህ በላይ የውድቀትህ ምክንያት ያስጨንቅህ። ዲያቆን አቤል ካሳሁን [email protected]
Show all...
👍 45
ሰላም እንደምን ሰነበታችሁ። ተቀጥራችሁ መስራት የምትፈልጉ ሰዎች፣ በተለይ በሆቴል ቤት ዙርያ፣ ይህ ከታች የምትመለከቱት ክፍት የስራ ቦታ የምታገኙበት ግሩፕ ነው። መቅጠር የምትፈልጉ ሰዎችም እዛ ላይ በነፃ ፓስት እያደረጋችሁ ሰራተኛ ማግኘት ትችላላችሁ። ለስራ ፈላጊዎችም አደራ ሼር አድርጉ። ስራ ማግኘት በአሁን ሰዓት ከባድ ስለሆነ ይህ ብዙዎችን ይጠቅማል። 👇👇👇 https://t.me/hoteljobsinaddis
Show all...
👍 3
ጥር 28 በዚህች ቀን ጌታችን ተአምራትን በማድረግ ሰባት እንጀራና ጥቂት ዓሣ ቆራርሶ አበርክቶ ብዙ ሰዎችን ያጠገበበት መታሰቢያ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመዘገበው ይህ የጌታችን ተአምር በውስጡ ብዙ ምሥጢራትን የያዘ ነው እንጂ ስለ ሥጋዊ ምግብ ብቻ የተነገረ አይደለም፡፡ ማቴ 14፡13-23፡፡ የተመገቡትና የተቆጠሩት አምስት ሺህ ወንዶች ብቻ ናቸው እንጂ ሴቶችና ሕጻናት አልተቆጠሩም፡፡ ይህስ ለምን ነው ቢሉ ሴቶች በአደባባይ ሲበሉ በሃፍረት ዳር ዳር ስለሚሉ ነው፡፡ ሕጻናት ደግሞ ከሚበሉት የሚፈረፍሩት ይበዛልና ነው፡፡ ጌታችን ያንን ሁሉ ሕዝብ በመንደር አጠገብ ሊመግባቸው ሲችል ለምን አርቆ ወደ ምድረ በዳ ወሰዳቸው ከተባለ ስለ ሁለት ምክንያት ነው፡፡ አንድም ‹‹ጥንት አባቶቻችሁን ከመንደር (ከግብጽ) አውጥቼ አርባ ዘመን ሙሉ መና የመገብኳቸው እኔ ነኝ፤ አሁንም በሥልጣኔ በተአምራቴ መገብኳችሁ›› ሲላቸው ነው፡፡ አንድም ጌታችን ተአምራቱን ከመንደር አጠገብ አድርጎት ቢሆን ኖሮ ሁልጊዜ ክፋትንና ጠማማ ነገርን ማሰብ ለአይሁድ ልማዳቸው ነውና ‹‹ፈጣን ፈጣን ደቀ መዛሙርቱን በጎን ወደ መንደር እየላከ ያስመጣው ነው›› ይሉት ነበር፡፡ ስለሆነም ጌታችን ለጥርጥር ምክንያት እንዳይኖራቸው አድርጎ ነው ተአምራቱን የገለጠላቸው፡፡ ጊዜውም አመሻሽ ላይ ነበርና ምሽት ላይ ያደረገበትም ምክንያት ጠዋት ላይ ቢሆን ኖሮ ‹‹የበላነው ሳይጎድል ነው ያበላን›› ብለው ከማመን ይርቁ ነበር፡፡ በተጨማሪም በበረሃ ያውም በምሽት ሕዝቡን በውኃ አጠገብ በሣር ላይ አስቀምጧቸው መመገቡ ‹‹በፍጻሜው ዘመን በምቹ ስፍራ በመንግሥተ ሰማያት መንፈሳዊ ምግብ እመግባችኋለሁ፤ በውኃ (በጥምቀት) በሚገኝ ክብርም አከብራችኋለሁ›› ሲላቸው ነው፡፡ ተአምራቱን ከውኃ ዳር ማድረጉ ‹‹መታጠቢያ ብናጣ በደንብ ሳንበላ ቀረን›› እንዳይሉ ነው፡፡ ሳር የበዛበት ቦታ ላይ ማድረጉም ‹‹መቀመጫ ብናጣ በደንብ ሳንበላ ቀረን›› እንዳይሉ ነው፡፡ አምስቱ እንጀራ የአምስቱ አዕማደ ምሥጢር ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ሁለቱ ዓሣ ደግሞ የፍቅረ እግዚአብሔርና የፍቅረ ቢጽ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ፍቅረ እግዚአብሔር ማለት እግዚአብሔር አምላክን በፍጹም ነፍስና በፍጹም ሐሳብ መውደድ ነው፡፡ ፍቅረ ቢጽ ደግሞ ባልንጀራን እንደራስ አድርጎ መውደድ ነው፡፡ አንድም ደግሞ እንጀራውና ዓሣው የቅዱስ ሥጋውና የክቡር ደሙ ምሳሌ ነው፡፡ ቅዱስ አማኑኤል ሀገራችንና ቤተክርስቲያንን ይጠብቅልን አሜን። ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው። https://t.me/finotebirhan12
Show all...
👍 24
👍 13
#ወደእኔ_ነይ ደክሜ ባለሁ ጊዜ ከወደቅሁበትም መነሳት ሲከብደኝ ለነፍሳት ርኅሩኅ የሆንሽ ድንግል ሆይ ወደእኔ ነይ። ታማሚው ልጅሽ ከደጅሽ ቆሜ አለሁ፤ ሕመሜን ግን አንቺ ከእኔ በላይ ታውቂዋለሽ፥ ባለመድኅኒቱም ልጅሽ ነው። ድንግል ሆይ "ልትድን ትወዳለህን?" እባክሽ አትበይኝ። መታመሜን የማላውቅ ጎስቋላ በሽታዬን የምመርጥ ሞኝ ነኝና። በሲቃ ነፍሴ ወደአንቺ ትጣራለች፥ ወደልጇ ይዘሻት እንድትወጪ ዐይን ዐይንሽን ታይሻለች። ንጹሕ ለሆንሽ ለአንቺ የማቀርበው የሚመጥን እጅ መንሻ ከእኔ ዘንድ የለኝም፥ ለአዳም ዘር ስጦታ ሆነሽ በእግዚአብሔር ለተሰጠሽ ለአንቺ ከቶ ምን ማቅረብ እችላለሁ? ስለዚህም ድንግል ሆይ እንደምታስፈልጊኝ አውቀሽ ሕይወትን ለሚሞላ ልጅሽ "ብርታት አልቆበታልና ና ወደእርሱ ዘንድ እንሂድ" በይው፣ የቸሩ እረኛ ደግ እናት ሆይ ተኩላዎች ከልጅሽ በጎች እንዳይለዩኝ ወደእኔ ነይ፣ በመንገድ ወድቄ እንዳልቀር የደጉ ሳምራዊ እናት ሆይ ባለመድኅኒት ልጅሽን ይዘሽ ወደእኔ ነይ፣ ጉድፍ የሌለብሽ መሶበወርቅ ሆይ ተርቤያለሁና የሕይወት ሕብስት ልጅሽን ታቅፈሽ የነፍሴን ረሀብ ታስታግሺልኝ ዘንድ ነይ፣ የምግባር እንስራዬ ባዶ ነውና ከምንጭ ዳር እጠብቅሻለሁ ጥምን የሚያጠፋ የሕይወት ውሃ ልጅሽን ይዘሽ ነይ፣ መንገድ ጠፍቶኝ እጠብቅሻለሁ መንገድ እና ሕይወት እውነትም የሆነውን ልጅሽን ይዘሽ ወደእኔ ነይ፥ ብርታት አጥቻለሁና እኔ እስክመጣ አትጠብቂኝ ሰላማዊቷ ርግብ ሆይ አንቺ ቀድመሽ ወደእኔ ነይ። @ዲያቆን እስጢፋኖስ ግርማ
Show all...
👍 18
🌿❤️  ጥር 21  በዓለ  አስተርእዮ  ማለት🌿❤️ 《የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት እንኳን ለዚህች ታላቅ ክብረ በዓሏ አደረሳችሁ አደረሰን!!! 🌿❤️ ወላዲተ አምላክ ምንም እንኳን የአምላክ እናት ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፈንታ በመሆኑ በስድሳ አራት አመቷ ከሞት ወደ ሕይወት ከመከራ ወደ ደስታ የተሸጋገረችበት ዕለት ነው፡፡ 🌿❤️ ታላቁ የቤተክርስቲያን አባት ቅዱስ ያሬድም “ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ” ትርጉሙ ሞት ለማናኛቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል፡፡ በማለት አደነቀ፡፡ 🌿❤️ በመሆኑም በዓሉ የወላዲተ አምላክ በዓለ ዕረፍት ከመሆኑ የተነሳ ታላቅ በረከት የሚያስገኝ ስለሆነ በየዓመቱ ይከበራል፡፡ ... 🌿❤️ የእረፍቷስ ነገር እንደምን ነው ቢሉስድሳ አራት ዓመት በዚህ ዓለም ኖራ ጥር 21 እሁድ ቀን ጌታ እልፍ አዕላፋት መላዕክቱን አስከትሎ መጥቶ እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጣሁ አላት፡፡ 🌿❤️ ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህጸኔ ተሸክሜ በድንግልና ወልጄህ እሞታለሁミ አለችው፡፡ 🌿❤️ በሲዖል የሚሰቃዩ ነፍሳትን አሳይቶ እናቴ ሆይ ሞትሽ ለእነዚህ ቤዛ ይሆንላቸዋል አላት፡፡ እኚህን ከማርክልኝስ ይሁን አለችው፡፡ ቅድስት ሥጋዋን ከቅስስት ነፍሷ ለይቶ በቃለ አቅርንት በዝማሬ መላእክት አሳረጋት፡፡ 🌿❤️ ደቀመዛሙርቱንም ከያሉበት በደመና ጠቅሶ ካለችበት አድርሶ እመቤታችሁን ቅበሩ አላቸው፡፡ ባባ ይዘወት ወደ ጌሰማኒ ሲስደት አይተው ልጇን ተነሳ አረገ እያሉ ሲውኩን ይኖራሉ አሁን ደግሞ እሷን ተነሳች አረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለም ብሎ ኑ እናቃጥላት ተባባሉ፡፡ 🌿❤️ ከመካከላቸው አንዱ ታውፋንያ ዘሎ ያልጋውን ሸንኮር ያዘ፡፡ የታዘዘው መላእክት መጥቶ በሰይፍ ሁለት እጁን ቀጣው፡፡ በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማጸናት ድኖለታል፡፡ ከዚህ ቦሃላ ዮሐንስን ጨምሮ ከመካከላቸው ነጥቆ በእጸ ሕይወት ሥር አኑሯታል፡፡ 🌿❤️ አንድም በዓሉ-፡ እግዚአብሔር ወልድ በሰውነት ተወልዶና ማንነቱ በይፋ ታውቆ በተገለጠበት በዘመነ አስተርእዮ ውስጥ ስለሚከበር የ♥#አስተርእዮ__ማርያም♥ ተብሏል፡፡ 🌿❤️ አስቀድመው አሥራ ሁለቱም ሐዋርያት ለስብከተ ወንጌል ወደ ዓለም ሁሉ ተበትነው ነበርና በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ሁሉም ደመናን ጠቅሰው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፡፡ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ መርቶ አመጣቸው እንጂ ለምን እንደመጡ አያውቁም ነበር፡፡ እመቤታችንም ለምን እንደመጡ ጠየቀቻቸው፡፡ 🌿❤️ ቅዱስ ጴጥሮስም፡- “ጸጋን የተመላሽ ቅድስት ሆይ! የመምጣታችን ምሥጢርማ እኛ አንቺን እንጠይቅ እንጂ አንቺም እኛን ትጠይቃለሽን? ሁላችንም ለምን እንደመጣን አናውቅም፡፡ 💟ለምሳሌ እኔ አስቀድሜ በአንጾክያ ነበርኩኝ አሁን ግን እነሆ እዚህ ነኝ፡፡ ለምን እንደመጣሁኝ ግን አላውቅም” አላት፡፡ እርሷም ሁሉም በአጠገቧ በተሰበሰቡ ጊዜ የሚሆነውን ነገር አስቀድማ ከልጇ ከወዳጇ አውቃ ተዘጋጅታ ነበርና ለምን እንደመጡ 《ዕረፍተ ሥጋዋን ለማየት እንደሆነ》ነገረቻቸው፡፡ 💟ሌሊቱንም በሙሉ በጸሎትና በማኅሌት ደግሞም በዝማሬ ሲያመሰግኑ አደሩ፡፡ ከዚህ በኋላ የተወደደችው እናት በረከቷን አሳድራባቸው በሰላም አንቀላፋች፡፡ ነፍሷም በዐብይ ዕልልታና በታላቅ ምስጋና በመላእክት እጅ ወደ አምላኳ ሄደች፡፡ 🌿❤️ ኋላ ሐዋርያቱ ዮሐንስን ሲያገኙት፡- “እመቤታችን እንደምን ሆነች?” አሉት፡፡ እርሱም “በገነት በዕጸ ሕይወት ሥር ዐርፋለች” አላቸው፡፡ 🌿❤️ የቀሩት ሐዋርያት “ዮሐንስ ያን ድንቅ የእግዚአብሔርን ሥራ አይቶ እኛስ ሳናይ እንዴት እንቀራለን?! አቤቱ ለእኛም ቸርነትህን አድርግልን” ብለው በነሐሴ መባቻ በአንድነት ሆነው ወደ ፈጣሪያቸው የሚቀርብ የአንድ ሳምንት ጾምና ጸሎት ጀመሩ፡፡ 🌿❤️ በሁለተኛው ሱባዔ ማብቂያ ዕለት ነሐሴ 14 ቀን እሑድ የእመቤታችንን ትኩስ ሥጋ መልአኩ ከገነት አምጥቶ ለሐዋርያቱ ሰጣቸው፡፡ 💟እነርሱም ልመናቸው ስለ ተፈጸመላቸው ፈጣሪያቸውን በጸሎት አመስግነው በዚያችው ዕለተ እሑድ ቅዱስ ሥጋዋን ወስደው ቀብረውታል፡፡ እርሷም በሦስተኛው ቀን ነሐሴ 16 ቀን ማክሰኞ ተነሥታለች፡፡ 🌿❤️ ትንሣኤዋ “ከመ ትንሣኤ ወልዳ- እንደ ልጇ ትንሣኤ” ያሰኘው ይህ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይታ የመነሣቷ እውነታ ነው፡፡ 🌿❤️ የአዛኚቱ ድንግል አማለጅነትና በረከት አይለየን አሜን ። ❤️💜💚💛💙❤️💙💚💜❤️ ወስብሓት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክብር አሜን ❤️💜💚💛💙❤️
Show all...
👍 19
ከምን ዓይነት ነገር መላቀቅ እንዳለብህ ታዉቃለህ ?? ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ምድራዊ ምኞት ምን ያህል አስከፊ እንደሆነና እንዴት ከዚህ ነገር ነፃ መውጣት እንዳለብን እንዲህ በማለት ይመክሩናል፦ "ወዳጄ ከምድራዊ ምኞትህ ተላቀቅ ከምን አይነት ነገር መራቅ እንዳለብህ ታውቃለህ? ከምድራዊ ፍላጎት ከመሳሰሉት ራቅ ፍፁም የመንፈስ ነፃነት እንዲኖርህ ከፈለክ ከምድራዊ ምኞቶችህ ተላቀቅ። በእርጋታና በግልጽነት ላውጋህ እጅግ አብዝተህ የምትጨነቅባቸው ልብህን የተቆጣጠሩት ታላላቅ ምድራዊ ተስፋዎች አሉህ። እነኚህም ሃሳብህን ሁሉ ይቆጣጠሩታል ብቻህን በምቶንበት ጊዜ በምናብ ይመጡብሃል በምትተኛ ጊዜ ህልምህ ሁሉ ይህ ይሆናል ልትክዳቸው የማትችለው ነገር ግን የምታውቃቸው ምድራዊ አላማዎች አሉህ። ተፈላጊነት እንዲኖርህ ትመኛለህ፣ ስልጣን እንዲኖርህና፣ ኃያል እንድትሆን፣ ዕውቅና እንዲኖርህና ስምህ ከጽንፍ እስከ አጽናፍ እንዲናኝ ትፈልጋለህ። በሀብት፣ በምድራዊ ስልጣን፣ በዕውቀት በማዕረግና በመልክ ዝነኛ የመሆን ተስፋ አለህ ፣ በመኖሪያ ቤት፣ በምግብ፣ በልብስና በሰውነት ደስታን በሚሰጡ ነገሮችም ተስፋ አለህ። ዓለም በአንተ እንጂ አንተ በዓለም እየኖርክ አይደለም። ስለዚህ አንተነትህ በዚህ ምድራዊ ተስፋ የታጠረ ነው። መንፈስህም ከስጋ ፍላጎቶች መራቅን ትመኛለች ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስ በሥጋ ላይ ይመኛልና። (ገላ.5፥17) እነዚህ ሥጋዊ ተስፋዎችና ፍላጎቶች ስኬታማ ስለማይሆኑ ግራ ትጋባለህ። ይህን በእርግጥ ቅሬታን ያመጣብሃል። እነዚህን ነገሮች ሁሉ ትናፍቃለህ ነገር ግን ናፍቆትህ አያስደስትህም። ስለዚህ ለምኞትህ ሁሉ ማስተካከያ ታበጅለት ይሆናል ምናልባትም ይጠቅሙኛል የምትላቸውን ሰዎች ማግኘት፣ በምኞትህ ዙሪያ የተጻፈ መዛግብት ማገላበጥ ትፈልግ ይሆናል በዚህም ላይ ታች ስትል ምኞትህን ለማሳካት ትታገላለህ እንዲሆን ሌላ ዘዴ ልትፈጥር ትችላለህ ይሁን እንጂ ሳይሳካልህ ቀርቶ በሃሳብና በጥረት ትታክታለህ ከዚያም ትበሳጫለህ። ከዚህ የከፋው ነገር በእነዚህ ምኞቶችና ተስፋዎች ስኬታማ አለመሆን ምክንያት ለከፋ ሕይወት መዳረግህ ነው። እንደምትሰለች አውቃለሁ አዘንኩልህ እስከመቼ ድርስ በምኞት ማዕበል ውስጥ ትኖራለህ? የምትመኘውን ባገኘህ ጊዜ ደስተኛ ትሆናለህ ይህ ደስታ ስለማያረካህ ሌላ አዲስ ደስታን እንድትመኝ ያደርግሃል። ልክ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ "ከዚህ ውሃ የሚጠጣ ሁሉ እንደገና ይጠማል" (ዮሐ.4፥13 ) እንዳለው እርካታ አይኖርህም። ስለዚህ ውድ ወንድሜ ነገሩን በእርጋታ ከአንተ ጋር ለመነጋገር እፈልጋለሁ። "አለሙም ምኞቱም ያልፋል" (1ኛ ዮሐ.2፥17) ታዲያ ይህን ቃል ካወክ ለምን አለማዊ ፍላጎቶችን ለማግኘት ትታክታለህ? አንተ ልክ እንደ እኔ ለመሬት እንግዳ ነህ። ዓለም የሚያልፍበት አንተም የምትጠፋበት ጊዜ ይመጣል ልክ ከእናትህ ማህጸን ራቁትህን እንደመጣህ እንደዚሁ ራቁትህን ትመለሳለህ።(ኢዮ. 1፥21) ዓለምን ከነክብሯ ከነሀብቷና ከነስሟ ለቀሃት እንድትሄድ በመገደድ እንደ ማንኛውም ሰው ወደ መሬት ትወርዳለህ። ከዚያም ከዓለም ያገኘኽውን ደስታ ታወቂነት ወይም ምንም ይሁን ምን ሥጋህን ከሞት ሊከላከልልህ አልያም ሥጋን ከሚበሉት ትል ሊከላከልልህ አይችልም። በፍርድ ቀን ከዓለም ሀብትና ንብረት ውጭ በእግዚአብሔር ፊት ትቆማለህ። መልካም ይሁን ክፉ የሰራኸው ሥራ እንጂ የዓለም ቁሳዊ ነገር አይከተልህም። ስለዚህ ውድ ወንድሜ ምኞትህንና ተስፋህን በዓለም ላይ በማድረግ መታወክህ ለአንተ ጥሩ አይደለም ይህችን ምድር እሾህንና አሜኬላን እንዳበቀለችልህ ትዘነጋለህን!!! ከእኛ በፊት የነበሩና ምድርን ሊረግጧት የማይገባት የቅዳሳን አባቶችና እናቶች አሠራርና ፈለግ ተከተል ቅድስናቸውን ያገኙት ይህችን ዓለም በመውደድ ሳይሆን በመናቅ ነበር ሁኔታዎች ሁሉ ተመቻችተውላቸው ሳለ በዓለም ስላሉ ነገሮች ለማንኛውም ጉጉት አልነበራቸውም ። ውድ ወንድሜ አሁንም ምኞት አሉህ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና (ማቴ.6፥21) የሥጋን ምኞቶችን ስለተቆራኘ መንፈሳዊ ነገሮች በአንተ አመለካከት ዋጋቸውን ያጣሉ ይህ የክብር ጌታ እንደተፈተነው ዓይነት ፈተና ነው። (ማቴ.4፥8-9) አሁን አስተውል እነዚህን ነገሮችን ብትይዝ በጥሩ ምኞት ያላሰርካት ነፍስህን ብታጣ ጥቅሙ ምንድን ነው? ነፍስህ ነጻነትን ትሻለች። ከስጋ ምኞት ተላቀን የመንፈስ ፍሬ የሆኑትን " የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣  እምነት፣ የውሃት፣ ራስን መግዛት ነው።"(ገላ.5፥22) እንዳለው ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ እነዚህን ገንዘብ አድርገን እንድንኖር እግዚአብሔር አምላክ ይርዳን!! (የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ "የመንፈስ ነጻነት "ከሚለውና በዲ/ን ደስታ ፍፁም ከተተረጎመው መጽሐፍ ላይ የተወሰደ። ምክር ወተግሳፅ እንዳቀረበው) @yehiwot_meaza @yehiwot_meaza @yehiwot_meaza
Show all...
👍 22
👍 10