cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

"ቃለ እግዚአብሔር "

"ጥበብን ማግኘት ምንኛ ከወርቅ ይሻላል! ማስተዋልንም ማግኘት ከብር ይልቅ የሚመረጥ ነው።" ምሳ 16 "ሥጋችን ምግብ ሲያጣ እንደሚደክም ሁሉ ነፍስም ምግቧን የእግዚአብሔርን ቃል ስታጣ ትደክማለች።" - ብጹዕ አቡነ ሽኖዳ በመንፈሳዊ ህይወት ዙሪያ ጥያቄ ካላችሁ ለመምህራችን በ @henokasrat3 መላክ ትችላላቹ።

Show more
Advertising posts
8 322Subscribers
-224 hours
-77 days
-2630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ከምን ዓይነት ነገር መላቀቅ እንዳለብህ ታዉቃለህ ?? ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ምድራዊ ምኞት ምን ያህል አስከፊ እንደሆነና እንዴት ከዚህ ነገር ነፃ መውጣት እንዳለብን እንዲህ በማለት ይመክሩናል፦ "ወዳጄ ከምድራዊ ምኞትህ ተላቀቅ ከምን አይነት ነገር መራቅ እንዳለብህ ታውቃለህ? ከምድራዊ ፍላጎት ከመሳሰሉት ራቅ ፍፁም የመንፈስ ነፃነት እንዲኖርህ ከፈለክ ከምድራዊ ምኞቶችህ ተላቀቅ። በእርጋታና በግልጽነት ላውጋህ እጅግ አብዝተህ የምትጨነቅባቸው ልብህን የተቆጣጠሩት ታላላቅ ምድራዊ ተስፋዎች አሉህ። እነኚህም ሃሳብህን ሁሉ ይቆጣጠሩታል ብቻህን በምቶንበት ጊዜ በምናብ ይመጡብሃል በምትተኛ ጊዜ ህልምህ ሁሉ ይህ ይሆናል ልትክዳቸው የማትችለው ነገር ግን የምታውቃቸው ምድራዊ አላማዎች አሉህ። ተፈላጊነት እንዲኖርህ ትመኛለህ፣ ስልጣን እንዲኖርህና፣ ኃያል እንድትሆን፣ ዕውቅና እንዲኖርህና ስምህ ከጽንፍ እስከ አጽናፍ እንዲናኝ ትፈልጋለህ። በሀብት፣ በምድራዊ ስልጣን፣ በዕውቀት በማዕረግና በመልክ ዝነኛ የመሆን ተስፋ አለህ ፣ በመኖሪያ ቤት፣ በምግብ፣ በልብስና በሰውነት ደስታን በሚሰጡ ነገሮችም ተስፋ አለህ። ዓለም በአንተ እንጂ አንተ በዓለም እየኖርክ አይደለም። ስለዚህ አንተነትህ በዚህ ምድራዊ ተስፋ የታጠረ ነው። መንፈስህም ከስጋ ፍላጎቶች መራቅን ትመኛለች ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስ በሥጋ ላይ ይመኛልና። (ገላ.5፥17) እነዚህ ሥጋዊ ተስፋዎችና ፍላጎቶች ስኬታማ ስለማይሆኑ ግራ ትጋባለህ። ይህን በእርግጥ ቅሬታን ያመጣብሃል። እነዚህን ነገሮች ሁሉ ትናፍቃለህ ነገር ግን ናፍቆትህ አያስደስትህም። ስለዚህ ለምኞትህ ሁሉ ማስተካከያ ታበጅለት ይሆናል ምናልባትም ይጠቅሙኛል የምትላቸውን ሰዎች ማግኘት፣ በምኞትህ ዙሪያ የተጻፈ መዛግብት ማገላበጥ ትፈልግ ይሆናል በዚህም ላይ ታች ስትል ምኞትህን ለማሳካት ትታገላለህ እንዲሆን ሌላ ዘዴ ልትፈጥር ትችላለህ ይሁን እንጂ ሳይሳካልህ ቀርቶ በሃሳብና በጥረት ትታክታለህ ከዚያም ትበሳጫለህ። ከዚህ የከፋው ነገር በእነዚህ ምኞቶችና ተስፋዎች ስኬታማ አለመሆን ምክንያት ለከፋ ሕይወት መዳረግህ ነው። እንደምትሰለች አውቃለሁ አዘንኩልህ እስከመቼ ድርስ በምኞት ማዕበል ውስጥ ትኖራለህ? የምትመኘውን ባገኘህ ጊዜ ደስተኛ ትሆናለህ ይህ ደስታ ስለማያረካህ ሌላ አዲስ ደስታን እንድትመኝ ያደርግሃል። ልክ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ "ከዚህ ውሃ የሚጠጣ ሁሉ እንደገና ይጠማል" (ዮሐ.4፥13 ) እንዳለው እርካታ አይኖርህም። ስለዚህ ውድ ወንድሜ ነገሩን በእርጋታ ከአንተ ጋር ለመነጋገር እፈልጋለሁ። "አለሙም ምኞቱም ያልፋል" (1ኛ ዮሐ.2፥17) ታዲያ ይህን ቃል ካወክ ለምን አለማዊ ፍላጎቶችን ለማግኘት ትታክታለህ? አንተ ልክ እንደ እኔ ለመሬት እንግዳ ነህ። ዓለም የሚያልፍበት አንተም የምትጠፋበት ጊዜ ይመጣል ልክ ከእናትህ ማህጸን ራቁትህን እንደመጣህ እንደዚሁ ራቁትህን ትመለሳለህ።(ኢዮ. 1፥21) ዓለምን ከነክብሯ ከነሀብቷና ከነስሟ ለቀሃት እንድትሄድ በመገደድ እንደ ማንኛውም ሰው ወደ መሬት ትወርዳለህ። ከዚያም ከዓለም ያገኘኽውን ደስታ ታወቂነት ወይም ምንም ይሁን ምን ሥጋህን ከሞት ሊከላከልልህ አልያም ሥጋን ከሚበሉት ትል ሊከላከልልህ አይችልም። በፍርድ ቀን ከዓለም ሀብትና ንብረት ውጭ በእግዚአብሔር ፊት ትቆማለህ። መልካም ይሁን ክፉ የሰራኸው ሥራ እንጂ የዓለም ቁሳዊ ነገር አይከተልህም። ስለዚህ ውድ ወንድሜ ምኞትህንና ተስፋህን በዓለም ላይ በማድረግ መታወክህ ለአንተ ጥሩ አይደለም ይህችን ምድር እሾህንና አሜኬላን እንዳበቀለችልህ ትዘነጋለህን!!! ከእኛ በፊት የነበሩና ምድርን ሊረግጧት የማይገባት የቅዳሳን አባቶችና እናቶች አሠራርና ፈለግ ተከተል ቅድስናቸውን ያገኙት ይህችን ዓለም በመውደድ ሳይሆን በመናቅ ነበር ሁኔታዎች ሁሉ ተመቻችተውላቸው ሳለ በዓለም ስላሉ ነገሮች ለማንኛውም ጉጉት አልነበራቸውም ። ውድ ወንድሜ አሁንም ምኞት አሉህ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና (ማቴ.6፥21) የሥጋን ምኞቶችን ስለተቆራኘ መንፈሳዊ ነገሮች በአንተ አመለካከት ዋጋቸውን ያጣሉ ይህ የክብር ጌታ እንደተፈተነው ዓይነት ፈተና ነው። (ማቴ.4፥8-9) አሁን አስተውል እነዚህን ነገሮችን ብትይዝ በጥሩ ምኞት ያላሰርካት ነፍስህን ብታጣ ጥቅሙ ምንድን ነው? ነፍስህ ነጻነትን ትሻለች። ከስጋ ምኞት ተላቀን የመንፈስ ፍሬ የሆኑትን " የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣  እምነት፣ የውሃት፣ ራስን መግዛት ነው።"(ገላ.5፥22) እንዳለው ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ እነዚህን ገንዘብ አድርገን እንድንኖር እግዚአብሔር አምላክ ይርዳን!! (የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ "የመንፈስ ነጻነት "ከሚለውና በዲ/ን ደስታ ፍፁም ከተተረጎመው መጽሐፍ ላይ የተወሰደ። ምክር ወተግሳፅ እንዳቀረበው) @yehiwot_meaza @yehiwot_meaza @yehiwot_meaza
Show all...
👍 20
ጾም እጅግ ግሩም የሆነ ነገር ነው፡፡ ኃጢአታችንን እንደማይጠቅም አረም ከውስጣችን ይነቅለዋል፡፡ እውነተኛው የጽድቅ ተክልም በውስጣችን ልክ እንደ አበባ እንዲያብብ ይረዳዋል፡፡ (ቅዱስ ባስልዮስ) ከምግባራት ሁሉ ታላቁ ጸሎት ነው ነገር ግን የእርሱ መሠረቱ ጾም ነው፡፡ የምንጾምበት ምክንያት ርኩስ የሆነውን የሰይጣንን መንፈስ በነፍሳችን ውስጥ እንዳያድር ለመጠበቅ ነው፡፡ ሥጋችንን ለጾም ባስገዛነው ጊዜ ነፍሳችን ነፃነትን፤ ጥንካሬን ሰላምን፣ ንጽሕናን እንዲሁም እውቀትን ለመለየት እንድትበቃ ትሆናለች፡፡ (ጻድቁ ዮሐንስ ዘክሮስታንድ)
Show all...
👍 29
#New🔴በፆም ወቅት ልናደርጋቸው የሚገቡ?! || ድንቅ ትምህርት| ዲያቆን አቤል ካሳሁን | Kendil media @... https://youtube.com/watch?v=NREY2XOg-BQ&si=zd9EQBP485zQ0ZMT
Show all...

👍 5
ዘወረደ (የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት ) የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት ዘወረደ ይባላል፡፡ ‹‹ዘወረደ እምላዕሉ አይሁድ ሰቀሉ›› የሚልና ይህንን የመሳሰለ ጌታ እኛን ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን ከሰማያት መውረዱን ከድንግል ማርያም የእኛን ሥጋ መዋሐዱን የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ ሌላም ስም አለው #ጾመ_ሕርቃል ይባላል፡፡ ይህ ጾም የጾም መግቢያ የመጀመሪያ ሳምንት የምንጾመው ጾም ሲሆን #ሕርቃል የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ #ሕርቃል ማን ነው? ለምንስ በስሙ ተሰየመ? በ614 ዓ.ም ኪርዮስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ ውስጥ ሲገባ ንግሥቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው፡፡ ቢነካው አቃጠለው ዲያቆናቱን አሸክሞ ሌላውን ንዋየ ቅድሳት ዘርፎ 60ሺ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ 3ሺ የሚሆኑትን ማርኮ ከተማዋንም ቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡ በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ14 ዓመት በኋላ በ628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲየኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል ይነግሩታል። እርሱም ሐዋርያት ሰውን የገደለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርገው አላቸው እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማለን ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን በሚገባ ጾመውታል፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልና የተማረኩ ክርስቲያኖችን ለመመለስ ሕርቃል ጦር መዝዞ በኪርዮስ ላይ ተነሳበት ድል ለሕርቃል ሆነና መስቀሉን ያለበትን አጥቶ ሲቸገር መስቀሉን ሲቀብርና ዲያቆናቱን ሲያስገድል በመስኮት ሆና ያየችው ከኢየሩሳሌም የተማረከች አንዲት ብላቴና አሳይታው አውጥቶ በልብሰ መንግሥቱ ጠቅልሎ ወደ ቁስጥንጥንያ ተመለሰ፡፡ የተማረኩት በሙሉ ነጻ ወጡ ይህን ለማሰብ ለማስታወስ በተጨማሪ በኃጢአት ላይ ድል እንድናገኝ መንፈሳዊ ጦር በውስጣችን እንዲበዛልን መስቀልህ ከምርኮ እንደተመለሰ እኛንም ከኃጢአት ምርኮ መልሰን ለሕርቃል ድል መንሳትንና በጠላቶቹ ላይ ኃይልን እንደሰጠኸው ለእኛም በኃጢአት ላይ ድል መንሳት መንፈሳዊ ኃይልን ስጠን እያልን እንጾመዋለን፡፡ በጌታ ጾም ላይ እንዲጾም የሆነበት ምክንያት ጾሙ የጌታ ጾም በሚጾምበት ወቅት ላይ ስለተጾመ ቤተክርስቲያናችን አብራ ደንግጋዋለች፡፡ እዚህ ላይ በዚያን ጊዜ ለሕርቃል ሕዝቡ ሱባኤ ይዞለታል፡፡ ዛሬም እኛ ለቤተክርስቲያን ያደረግነውን በማሰብ እግዚአብሔር አምላክ ለሕርቃል የሰጠውን በጠላቶቹ ላይ ድል መንሳትን ለእኛም እንዲሰጠን የምንጠይቅበት ስለሆነ የመጀመሪያውን ሳምንት በሕርቃል ሰይመን ጾሙን እንጾማለን፡፡ የእኛ ጠላት የጨለማ ገዥ የሆነው ዲያቢሎስ ነውና እሱን ደግሞ በጾም እንደምናሸንፈው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል፡፡ «ዘወረደ» ማለትም በቀጥታ፣ ቃል በቃል ሲተረጐም «የወረደ» ማለት ነው፡፡ ይህም በምስጢሩ አምላክ ወልደ አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤዛ ዓለም በቅዱስ ፈቃዱ ሰው ሆኖ ከሰማየ ሰማያት፣ ከባሕርይ ልዕልናው በትሕትና ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመላክት፣ ይህም የሚታወስበት፣ የሚወሳበት የዐቢይ ጾም አንደኛው ሳምንት ነው፡፡ ዮሐ.3፥13፡፡ ሳምንቱ ሙሴኒ የተባለበትም ምክንያት በዚሁ ሳምንት መጀመሪያ የሰኞ ዕዝል «ከመዝ ይቤ ሙሴ ፀዓቱ እምትእይንት» «ሙሴ ከከተማ መውጣቱ እንደዚህ ነው አለ» ስለሚል እንደዚሁም የዚሁ ዕለት ማለት የሰኞ አቡን «ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት ምድር ሰናይት» እያለ የሙሴን ታሪክ ስለሚያጠቃቅስ ሳምንቱ ሙሴኒ ተባለ፡፡ነቢያትም አርባ አርባ ቀን ጾመው ከአለፉ በኋላ የሙሴ ሕግና ትንቢተ ነቢያት ፈጻሚ የሆነው ምላካችን እንደ እነሱ 40 ቀንና 40 ሌሊት መጾሙን የሚያስታውስ ነው፡፡ /ዘፀ.24፥18፤ 1ኛ.ነገ.19፥8፤ ማቴ. 4፥1-4/፡፡
Show all...
👍 20
👏👏👏👏👏👏👏ቅበላ👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏                ቅበላ   ቅበላ_ መቼም ቅበላ የሚለው ቃልን ስንሰማ ሁላችንም ጀሮ ላይ አንድ ነገር ያቃጭላል እሱም ፆም ከመግባቱ በፊት የምናደርገው ተግባር ነው። በመሰረቱ ቅበላ ማለት በእንግድነት ለሚመጣው እንግዳ ለእንግዳው የሚመጥነውን ያህል ክብር ለመስጠት አዘጋጅቶና ተዘጋጅቶ መቀበል ነው:: ስለዚህ ለአንድ ነገር ቅበላ ስናደርግ ያንን የምንቀበለውን ነገር በሚመጥን መልኩ መሆን አለበት። ለምሳሌ አንድ መንፈሳዊ መነኩሴ ወደ ቤታችን በእንግድነት ቢመጣ ለመነኩሴው ቅበላ የምናደርግለት እሱን ሊመጥን በሚችል መልኩ ነው የፀሎት ቤት አዘጋጅተን እግሩን አጥበን ጉልበት ስመን መኝታ ክፍሉ ውስጥ ቅዱሳት ስዕላትን ወይም መፅሐፍ ቅዱስ አስቀምጠን.  .  . የመሳሰሉትን ነገሮች እንደ እኛ አቅም አዘጋጅተን ልንቀበለው እንችላለን። አልያ ደግሞ አንድ ህፃን ልጅ ወደ ጎጆአችን በእንግድነት ቢመጣ መኝታ ክፍል አዘጋጅተን የተረት መፃሕፍቶችን አሰናድተን የህፃናት ፊልም ከፍተን የህፃናት መጫወቻ አወጋጅተን ቅበላ ልናደርግለት እንችላለን። ልክ እንደዚሁ ሁሉ ፆምንም ስንቀበል ከፆም ጋር የሚስማማ ነገር ማድረግ አለብን እንጅ ፍፁም ተቃራኒ የሆነ ተግባር ማድረግ ትልቅ ስህተት ነው። ፆም ሊገባ ነው ብለን ሆዳችን እስኪተረተር የምንበላ ጨንጓራችን እስኪላጥ የምንጠጣ ዝሙት የምንፈፅም በየ ጭፈራ ቤቱ የምንዞር ከሆነ ይህ የፆም ቅበላ ይባላልን? በጭራሽ አይባልም።እንደውም ይህ የሚያሳየው ፆሙን ሳንፈልግ እንደምንቀበለው ነው። "ነብይን በነብይ ስም የሚቀበል የነብይን ዋጋ ይወስዳል" ማቴ 10:41 እንዳለ ጌታችን ፆምን ስንቀበል በፆም ስም በፆም ተግባር መሆን አለበት። እንደውም አንዳንድ የበቁ አባቶች የአብይ ፆም ሊገባ ሲል ፆሙን በፆም ይቀበሉታል።በእርግጥ ይህ ለእኛ ሊከብደን ይችላል ቢሆንም ፆሙን በፆም መቀበል ቢያቅተን እንኳን ፆሙን ከፆም ጋር በሚስማሙ መልካም ተግባራት መቀበል እንችላለን። ፆም ከመግባቱ በፊት ንስሐ መግባት ፣ የበደሉንን ይቅር ማለት ፣ የበደልናቸውን ይቅርታ መጠየቅ ፣ የተጣላናቸውን መታረቅ ፣ መመፅወት ፣ ፆሙ የበረከት እንዲሆንልን መፀለይ ፣ መንፈሳዊ ምግባራትን መላበስ ፣ ከመጠን ያለፈ ደስታን ከራስ ማራቅና የመሳሰሉትን ከእኛ ጋር የሚስማሙትን መንፈሳዊ ተግባራት ከንስሐ አባታችን ጋር ተመካክረን ተግባራዊ በማድረግ ቅበላ ማድረግ ይኖርብናል። በዚህ መሰረት የሚፈፀም ቅበላ ፆሙ ከመግባቱ በፊት መንፈሳችን እንዲዘጋጅ ከማድረጉም ባለፈ እግዚአብሔር ከፆሙ በፊት አስቀድሞ እንዲባርከን ያደርጋል። ወዳጄ ሆይ የአንተ ቅበላ ከየትኛው ነው? መቼም በስካር በከርስ መሙላት በጭፈራና በዝሙት ቅዱሱን እንግዳ #ፆምን እንደማትቀበል ተስፋ አደርጋለሁ። አበው "ከምግብ ብቻ በመከልከል እንጾማለን አትበሉ .. ከክፉ ግብር መራቅ ጾማችንን ትክክል ታደርጋለች" ይላሉ:: በዚህም የአባቶቻችን ልጆች እንባላለን አባቶቻችን የወረሷትን መንግስት በእውነት እንወርሳለን:: . . . ኦ ጌታ ሆይ! ቸሩ አምላኬ ሆይ ሀጢያቴ እንደ ምድር አሸዋ እንደ ሰማይ ከዋክብት በዝቶ በደሌ ስፍር መለኪያ ጠፍቶለት ክፉዋ ምላሴ ፤ የተበረዘው ጭንቅላቴ ፤ የደነደነው ልቤ ሳያሰለችህ ሳያስቀይምህ ቀናትን በሳምንታት ሳምንታትን በወራት ወራትን በአመታት ተክተህ ለዚህች ቀን ስላደረስከኝ በደካማ አንደበቴ አመሰግንሀለሁ። እንደ እውነቱ ዘመኑ ዓመተ ምህረት ባይሆን ኑሮ እኔ ገና ድሮ ነበር የምቀሰፍ! ገና ድሮ ነበር የምጠፋ! ግን አምላኬ ሆይ አንተ እንደ ሰው ስላልሆንክ ለፍርድ አልቸኮልክም በፍቅር ታገስከኝ በስስት ዓይንም ተመለከትከኝ። ኦ አምላኬ ሆይ! እኔዋ ደካማይት ልጅህ ያለፈውን ፆም በቅጡ ሳልጠቀምበት ፍቃድህን ሳልፈፅም ደካሞችን ሳልረዳ የደከሙትን ሳልጎበኝ ያዘኑትን ሳላፅናና የሰጠህኝን ቅዱስ ቀናት እንዲሁ በከንቱ አሳለፍኩ። ጌታ ሆይ እኔ ደካማ እንደሆንኩ ታውቃለህ አንተ እኮ የልብና የኩላሊትን የምትመረምር ቅዱስ አምላክ ነህ። እናም ድካሜን ታውቃለህ ስንፍናዬን ታውቃለህ አምላኬ ሆይ ታዲያ እንደዚህ ደካማ ሰው ሁኜ ፆምህን እንዴት ልፆም እችላለሁ? እንዴት 40 የፆም ቀናት በፍቃድህ ላሳልፍ እችላለሁ? የድንግል ልጅ አማኑኤል ሆይ አንተ ካልረዳኸኝ አንተ ካልደገፍከኝ ታዲያ ይህን ነገር እንዴት ልወጣው እችላለሁ? አንተ እኮ መቅደላዊት ማርያምን ወደ ቅድስትነት ሙሴ ፀሊምን ከገዳይነት ወደ ባህታዊነት ሳኦልን ወደ ሰባኪነት ለውጠሀል። ጌታዬ ሆይ ታዲያ እኔን አንተ ካላገዝከኝ በእኔ አቅምማ እንዴት ይሆናል? የቅድስት ድንግል ማርያም ልጅ መድኃኒአለም ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በእናትህ በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት በቅዱሳን መላዕክት አማላጅነት በፃድቃን ሰማዕታት ፀሎትና ምልጃ እያመንኩና እየተማፀንኩ ከሰይጣን ፍላፃዎች ሁሉ እንድትታደገኝና ለደካማዋ ልጅህ ትደርስላት ዘንድ በሀጢያት በተዳደፌ አንደበቴ እለምንሀለሁ! ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ፆሙ የበረከትና የፍሬ እንዲሆንልን ከወዲሁ እመኛለሁ!
Show all...
👍 22
"አስታውስ" (አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ) † ደካማነትህን አስታውስ፣ ያንጊዜ በጣም ጠንቃቃ ትሆናለህ፣ ሊጎዱህ በሚችሉ በትምክህትና በውዳሴ ከንቱም አትሸነፍም፡፡ † የተሰጠህን በፍቅር የተሞላ የእግዚአብሔርን ቸርነት አስታውስ፣ ይህም በምስጋና የተሞላ ሕይወት እንድትመራ ያደርግሃል። በእግዚአብሔር ፍቅርና ሥራ ላይ ስትታመን ፍጹም የሆነ እምነት በልብህ እያደገ ይመጣል፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ያሳለፍከው ጊዜ ደግሞ በእምነት እንድትኖር ያበረታታሃል፡፡ † የሰዎችን ፍቅርና ካንተ ጋር ያሳለፉትን መልካም ጊዜ አስታውስ፡፡ የሰዎችን ቀናነት ትጠራጠር ዘንድ ወይም ያደረጉብህን ክፉ ነገር ታስብ ዘንድ ይገባሃልን? የቀደመ ፍቅራቸው ስለ እነርሱ ይማልዳል ያንተንም ቁጣ ያበርዳል፡፡ † ሞት እንዳለ አስታውስ፣ እንዲሁ በዓለም ያለ ፈተናም እንደሚያልፍ፡፡ "ሁሉ ከንቱ ነው፣ ነፋስንም እንደመከተል ነው፡፡" መክብብ 1፥14 ማለትን ትረዳለህ፡፡ † በእግዚአብሔርፊት መቆምህንና እርሱም እንደሚመለከትህ አስታውስ፣ ያኔ ኃጢአት አትሰራም እግዚአብሔርን ታየዋለህና፡፡ † ስለ አንተ የፈሰሰውን የክርስቶስን ክቡር ደም አስታውስ፡፡ በዚህም ሕይወትህ ያለውን ዋጋ በእርግጥ ታውቃለህ፤ በዓይኖችህ ፊት የከበረ ይሆናል፣ ስለዚህም በከንቱ በመኖር አታጠፋውም፣ "በዋጋ ተገዝታችኋልና" 1ኛ ቆሮ.6:20 እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ፡፡ † በወላጆችህ እምነት በተጠመቅህባት ቦታ ለእግዚአብሔር የገባኸውን ቃል አስታውስ፤ ዲያብሎስን፣ ሥራዎቹን ሁሉ፣ ሐሳቦቹንና ጥበቡን፣ ኃይሉንም ትክድ ዘንድ፡፡ † በዚህ ዓለም እንግዳመሆንህንና ወደ ሰማያዊው ቤትህ እንደምትመለስ ዘወትር አስታውስ፡፡ ያን ጊዜ በዚህ ዓለምና በደስታው ተስፋ ማድረግን ትተዋለህ፡፡ † በጠባቡ በር መጓዝ ወደ መንግስተ ሰማያት እንደሚያደርስህ አስታውስ፡፡ ሰፊው ደጅ ፊት ለፊትህ ተከፍቶ ብታየው፣ አልፈኸው ሂድ ከእሱም ራቅ፣ በእርሱ የሄዱ እንዳሉ አልቀዋልና፡፡ † ዘላለማዊውን ሕይወትህን አስታውስ፣ ሁልጊዜም ስለዚህ ትጋ፡፡ † የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህንና እርሱን መምሰል እንዳለብህ አስታውስ፡፡ እውነተኞች ከሆኑት ከእግዚአብሔር ልጆች ጋር አካሄድህን አስተካክል፡፡ † የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ መሆንህን አስታውስ፡፡ በውስጥህ ያለውንም ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አታሳዝን፡፡ ዘወትርም ቅዱስ የእግዚአብሔር ማደሪያ ሁን፡፡ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
Show all...
👍 33
ውድ ስጦታ ኹሌ ስጦታን የሚሰጥ አንድ ሰው ከሚሰጣቸው ስጦታዎች ኹሉ በአካል ሊለይ ሲል የሚሰጠው ስጦታ ልዩ ነው። መለየቱ እስከ መጨረሻው ከኾነና ስጦታውም በመለያው ሰዓት የሚሰጠው ስጦታ ከኾነ ደግሞ የስጦታውን እጅግ ክቡርነት የሚያሳይ ይኾናል። በተለይ ሰጪው በሞት አፋፍ ላይ ኾኖ ነባቢት ነፍሱ ከሥጋው ልትለይ ደርሳ በእንጥፍጣፊ ነቢብ ስጦታውን ለማን እንደሚሰጣት የሚናዘዛት ከኾነች የስጦታዋ ውድነት ከሕይወትም ይልቃል። 'ይህችን ሞቱ እስክትመጣ ድረስ ለሚወዳቸው ሰዎች እንኳን ያልሰጣት ምን ያህል ቢወዳትና ቢሰስታት ነው' ያሰኛል። ሊሞት ሲል የሚሰጣትም በጣም ለሚወደው ሰው መኾኑ አያጠራጥርም። እመቤታችን እንደዚህ ውድ የኾነች የሕይወት ስጦታ ነች። (ዮሐ.19:26-27)። (ከየመሰጠት ሕይወት መጽሐፍ ገጽ 71 የተቀነጨበ።) @KaleEgziabeher
Show all...

👍 36
👍 18
መንፈሳዊ ጉባኤ: ❖ ❖ ❖ ኪዳነ ምህረት (የካቲት 16) ❖ ❖ ❖                ❖ ❖ ❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖ ❖ ❖    ኪዳነ ምህረት ማለት የምህረት መሐላ ማለት ነው፡፡ ከ33ቱ በዓላተ እግዝእትነ ድንግል ማርያም አንዱ ነው፡፡ እመቤታችንም ከጌታችን መቃብር እየሄደች በምትለምንበት ጊዜ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉምና ምን ልታመጣብን ነው በማለት ሊጣሏት ሲመጡ ጌታችንም ከዓይናቸው ሰውሯታል አይሁድም ጠባቂ ቢያቆሙ እመቤታችን ዕለት ዕለት መሄዷን አላቋረጠችም እመቤታችንም እንዲህ ብላ ስትጸልይ ልጄ ወዳጄዘንድ ሆይ ከስጋዬ ስጋ ከነፍሴ ነፍስ ነስተህ ሰው በመሆንህ ዘጠኝ ወር ከ5 ቀን በቻለችህ ማሕጸኔ ከአንተ ጋር ሀገር ለሀገር ስለ መሰደዴ መትተህ ልምናዬን ትሰማኝ  እለምንሃለሁ አለች በዚህ ጊዜ ንውጽውጽውታ ሆነ መቃብራት ተሰነጣጠቀ ጌታችንም እልፍ ከእልፍ መላዕክቱ ጋር መጥቶ ሰላም ለኪ ማርያም ምን እንዳደርግልሽ ትለሚኚኛለሽ አላት፡፡ እርሷም መታሰቢያዬን ያደረገውን ስለ ስሜ ለችግረኛ የሚራራውን በስሜ ቤተ ክርስቲያን ያነጸውን መባዕ የሰጠውን ከሃይማኖት ከፍቅር ጽናት ልጁን በስሜ የጠራውን ሁሉ ማርልኝ ከሞተ ስጋ ከሞተ ነፍስ አድንልኝ አለችው፡፡ ጌታችንም ይህን ሁለ እንዳደርግልሽ መሐልኩ ለኪ በርእስየ ወበ አቡየ ሕያው ወበመንፈስ ቅዱስ ብሎ ቃል ገብቶላት አርጓል፡፡    ሌላው በላዔ ሰብ በአማርኛ ሰው በላ ማለት ነው፤ ትክክለኛ ስሙ ግን ስምዖን ይባላል ቅምር በሚባል አገር የሚኖር እጅግ ባለጸጋ ነበር፤ እንደ አብርሃም እንግዶችን እየተቀበለ ድሆችን እየመገበ የሚኖር ጻድቅ ነበር፤ ሰይጣን በዚህ ስራው ቀናበት ሊፈትነውም በሦስት አረጋዊ ሽማግሌዎች ሥላሴ ነን ብሎ ተገለጠለት ልክ እንደ አብርሃም፤ ሐዋርያው ጳውሎስ ሰይጣን የብርሃን መልአክ መስሎ ይመጣል እንዳለ፤ እርሱም ሥላሴ መስለውት ተቀበላቸው ተንከባከባቸውም፤ ምግብ አቀረበላቸው ምግብ አንበላም የምንጠይቅህን ግን ትፈጽምልን ዘንድ ቃል ግባልን አሉት ቃል ገባላቸው እንግዲያውስ የምትወደን ከሆነ አንድያ ልጅህን ሰዋልን አሉት፤ መጀመሪያ ደነገጠ ኃላ አብርሃም ልጁን ሊሰዋ አልነበረምን እኔንም ሊፈትኑኝ ይሆናል ብሎ ለማረድ ተዘጋጀ፤ ተው የሚለው ድምጽ አልሰማም፤ አረደው አወራረደው ይዞላቸው ቀረበ፤ መጀመሪያ ቅመስልን አሉት ቀመሰው ወዲያው እነዚያ ሰዎች ተሰወሩበት እርሱም አህምሮውን ሳተ ተቅበዘበዘ ከዚያ በኃላ ምግብ አላሰኘውም የሰው ስጋ እንጂ መጀመሪያ ቤተሰቦቹን በላ ከዚያም ጓደኞቹን ጦርና የውኃ መንቀል ይዞ ከቤቱ ወጣ ያገኘውን ሰው እየገደለ ይበላል የበላቸው ሰው ቁጥር 78 ደረሰ፤ በመንገድ ተቀምጦ የሚለምን በደዌ የተመታ አንድ ደሃ አገኘ ሊበላው ወደ እርሱ ተጠጋ ግን ቁስሉን አይቶ ተጸየፈው፤ ደሃውም “ስለ እግዚአብሔር ከያዝከው ውኃ አጠጣኝ” አለው “ዝም በል ደሃ” ብሎት አለፈ፤ “አረ በውኃ ጥም ልሞት ነው ስለ ጻድቃን ስለ ቅዱሳን” አለው አሁንም ዝም ብሎት ሄደ ለሦስተኛ ጊዜ “ስለ አዛኝቷ ስለ ድንግል ማርያም” አለው፤ ሰውነቱን አንዳች ነገር ወረረው “አሁን የጠራከውን ስም እስኪ ድገመው ስለ ማን አልከኝ” አለው፤ ስለ አዛኝቷ ስለ እመቤቴ ማርያም አለው፤ ይህቺስ ደግ እንደሆነች በምልጃዋም ከሲኦል እንደምታወጣ ህጻን እያለው እናትና አባቴ ይነግሩኝ ነበር፤ በል እንካ አለው እጁን ዘረጋለት ጥርኝ ውኃ ጠብ አደረገለት ወደ ጉሮሮው አልወረደም የተሰነጠቀ እጁ ውስጥ ገባ እንጂ፤ በለዔ ሰብ ከዚያች ደቂቃ በኃላ አዕምሮው ተመለሰለት እንዲህም አለ “በአንድ ዋሻ ውስጥ ገብቼ ስለ ኃጢያቴ አለቅሳለሁ ስጋዬ ከአጥንቴ እስኪጣበቅ እጾማለሁ ወዮሊኝ ወዮታም አለብኝ አለ፤ ወደ ዋሻ ገባ ምግብ ሳይበላ ውኃም ሳይጠጣ 21 ቀን ኖሮ በርሃብ ሞተ ይላል ተአምረ ማርያም። ጨለማ የለበሱ ሰይጣናት እያስፈራሩ እያስደነገጡ ነፍሱን ወደ ሲኦል ሊወስዷት መጡ፤ እመቤታችን ፈጥና በመካከላቸው ተገኘች፤ ልጄ ወዳጄ ይህችን ነፍስ ማርሊኝ አለችው እናቴ ሆይ 78 ነፍሳትን የበላ እንዴት ይማራል አላት፤ የካቲት 16 ቀን በጎልጎታ የገባህልኝ ቃል ኪዳን አስብ ስምሽን የጠራ መታሰቢያሽን ያደረገን እምርልሻለው ብለኸኝ የለምን አለችው፤ እርሱም እስኪ ይህቺን ነፍስ በሚዛን አስቀምጧት አለ ቢያስቀምጧት ጥርኝ ውኃው መዝኖ ተገኘ፤ ስላንቺ ስል ምሬታለው ሰባት ቀን ሲኦልን አስጎብኝታችሁ ወደ ገነት አግቧት አላቸው። ቦታሽ እዚህ ነበር እያሉ ሲኦልን አስጎብኝተው ወደ ገነት አገቧት። ልመናዋ ክብሯ የልጇም ቸርነት ከሁላችን ጋር ይሁን። ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ በዕለቱ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሚቀርበውን የምስጋና ቃል እንደሚከተለው አቅርበናል መልካም በዓል፡፡            ❖ ❖ ❖ ዋዜማ ❖ ❖ ❖ ሃሌ ሉያ (፬) ርግብየ ይቤላ በእንተ የዋሃታ፤ በሐኪ ማርያም ሐዳስዩ ጣዕዋ፤ እንዘ አመቱ እሞ ረሰያ ፤ ታዕካ ሰማይ ኮነ ማኅደራ፤ ዳዊት ይሴብሕ ወይዜምር ዕዝራ ፤           ❖ ❖ ❖ ምልጣን ❖ ❖ ❖ እንዘ ዓመቱ እሞ ረሰያ ፤ ታዕካ ሰማይ ኮነ ማኅደራ፤ ዳዊት ይሴብሕ ወይዜምር ዕዝራ ፤ ዳዊት ይሴብሕ ወይዜምር ዕዝራ ፤         እግዚአብሔር ነግሠ         እንተ ክርስቶስ በግዕት እንተ ታስተርኢ እምርኁቅ ብሔር፤         በቤተልሔም አስተብረከት ዕጓለ አንበሳ ግሩመ ወለደት፡፡            ❖ ❖ ❖ ይትባረክ ❖ ❖ ❖ እግዝእትየ እብለኪ ወእሙ ለእግዚእየ እብለኪ፤ ቃል ቅዱስ ኀደረ ላዕሌኪ፡፡            ❖ ❖ ❖ ሰላም ❖ ❖ ❖ ሃሌ ሉያ (3) ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር ወገበዋትሃኒ በሐመልማለ ወርቅ፤ የሐንፁ አሕዛብ አረፋተኪ በዕንቊ ክቡር፤ ወመሠረትኪ በወርቅ ንጹሕ ይሰግዱ ለኪ ውስተ ገጸ ምድር፤ በእንተ ዕበየ ክብርኪ አምላከ ፳ኤል ውእቱ ረዳኢኪ ዘአድኀነኪ እምእደ ጸላዕትኪ፤ ወረሰየ ሰላመ ለበሐውርትኪ፡፡          ❖ ❖ ❖ መልክአ ሥላሴ ❖ ❖ ❖ ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፡ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፡ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል ፡ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል           ❖ ❖ ❖ ዚቅ ❖ ❖ ❖ ወታስተሥርዪ ኃጢአተ ሕዝብኪ ተበውሐ ለኪ፤ እም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፤ ከመ ትኩኒ ተንከተመ ለዉሉደ ሰብእ ለሕይወት ዘለዓለም፤ ለኪ ይደሉ ከመ ትኩኒ መድኀኒቶሙ ለመሐይምናን ሕዝብኪ፤ ኦ መድኀኒተ ኵሉ ዓለም ፤ ወልድኪ ሣህሎ ይክፍለነ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡          ❖ ❖ ❖ መልክአ ኪዳነ ምህረት ❖ ❖ ❖ ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ ; ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኀኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪየኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ፡፡          ❖ ❖ ❖ ዚቅ ❖ ❖ ❖ ቅንዑ ለእንተ ተዓቢ ጸጋ መድኀኒት ለነፍስ ወሥጋ፤ እስመ ርቱዓት ፍናዊሃ ጻድቃን የሐውርዎን ፤ ወኃጥአን ይስዕንዎን፤ ዘእንበለ ትብጻሕ ግብተ አሠንዩ ፍኖተ፤ ይፈኑ ለክሙ እመቅደሱ ረድኤተ መድኀኒተ መቤዛዊተ እሞ ቅድስተ፡፡ ❖ ❖ ❖ መልክአ ኪዳነ ምህረት ❖ ❖ ❖ ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘአስተማልዎ በኮከብ፤ ሶበ ብርሃኖ ተከድኑ ጽልሙታነ ራእይ ሕዝብ፤ ኪዳነ አምላክ ማርያም ወተስፋ መድኀኒት ዘዐርብ፤ ተናዘዘ ብኪ አኮኑ ሕሊና ቀዳማይ አብ፤ አመ እምገነቱ ተሰደ በኃዘን ዕፁብ፡፡          ❖ ❖ ❖ ዚቅ ❖ ❖ ❖ አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም ፤ አመ ይሰደድ እምገነት፡፡           ❖ ❖ ❖ መልክአ ኪዳነ ምህረት በዓል ❖ ❖
Show all...
👍 15
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!