cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ዮቶጵ ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ በአምላክ የተወደደች፤ የጥንተ ስልጣኔ ምንጭ አኩሪ ባህል እና ታሪክ ያላት ሀገር ናት። የሀገር ፍቅር መገለጫው አንዱ ስለ ታሪኳ ጠንቅቆ ማወቅ ነውና ስለ ኢትዮጵያ ያልተነገሩ እና ድንቅ ታሪኮቿን ለማወቅ፤ ይቀላቀሉን። ለማንኛውም አስተያየት : @Dawit77

Show more
Advertising posts
351Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

🌿የሰው ሕይወት በምድር ላይ ብርቱ ሰልፍ ናት ! ሕይወት ብርቱ ሰልፍ ናት ፡፡ ብዙ ዔመታት የኖርክ ቢመስልህም ነገር ግን የምትጨርሰው ከጀመርክበት ነው ፡፡ ራቁትህን መጣህ ራቁትክን ትወለዳለህ ፤ በጥርስ አልባው ድድህ እየጋጥክ ትጀምራለህ ፤ የሕይወትን ትግል እየዳህ ትጀምራለህ ፤ አጎንብሰህ ትጨርሳለህ ፡፡ መጀመሪያህ መጨረሻህ ነው ፡፡ የጀመርክበትን አትርሳ መጨረሻህ ነውና ፡፡ የጀመርክበትን አትናቀው ትጨርስበታለህና ፡፡ ተራ ሰው ሆነህ ትጀምራለህ ምሁር ብትሆን ፤ ባለ ሐብት ብትሆን፤ ባለ ሥልጣን ብትሆን ፤ ክቡር ሆነህ የንግስና ዘውድ ብትጭን ፤ የምትጨርሠው ከአፈር ተፈጥረህ በአፈር ነው ፡፡ ባለማወቅ ትጀምራለህ በመርሳት ትጨርሳህ፡፡ምንም ይዘህ አለመጣህምና ምንም ይዘህ አትሔድም ። በለቅሶ ትጀምራለህ ፤ በጭንቅ ትጨርሳለህ፡፡ በሰው እቅፍ ትጀምራለህ ፤ በሠው ሸክም ትጨርሳለህ ፡፡ ልደትህ ከሞትህ በምን ይለያል ? ሞትህስ ከልደትህ በምን ይከፋል ? ሕይወት መጀመሪያዋና መጨረሻዋ አንድ ነው ፡፡በዚህ የተነሣ ጠቢቡ እንዳለው ሁሉም ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነው ፡፡ ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር የለም ፡፡ የዓለም ከንቱነት ግን ውበትዋ ነው ፡፡ ዓለም አዲስ ነገር ቢኖራት እኛን እንዴት በፀፀተን ፤ ሞት የእውነት መጨረሻ ቢሆን እንዴት በቆጨን። "ጨለማን መተቸት ብርሃን አያመጣም ክፋትን መኮነንም ደግነት አይሆንም ኋላቀርነትን ማጥላላት ሥልጣኔ አያመጣም ጦርነትን መፍራትም ሠላም አይሆንም እንዲሁም ረሃብን አለመፈለግ ጥጋብ አያመጣም ። ዕውቀትና በጎ አመለካክት ግን ማህበረሰብን መቀየር ይችላሉ ።" መልካም ሁን መልካምነት ራሱ ይከፍልሀል ይባል የለ ? ስለዚህ ዘላለማዊውን ክብር እንደ ይሁዳ በጊዜያዊ ደስታ አትቀይር። ለሰው ልጅ ዘላለማዊ ዋስትናን ሊሰጠው የሚችለው ከሰማይ የወረደው ኢየሱስ ክርስቶሰ ብቻ ነው።እርሱ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሞቶልሐል።የኃጢያት ዕዳህን ከፍሎልሐል ። ተቀበለው እመንበት ኑርበት አምልከው ዘለዓለማዊው የሰው ልጅ የሕይወት ዋስትና እርሱ ብቻ ነው ። ከ #ነገረጥበብ @zikiretibeb @Yotop77 @Yotop77 @Yotop77
Show all...
ጎልፃን ✍ በገጣሚ እና ባለቅኔ ኤፍሬም ስዩም "ጎልፃን የግሪክ ቃል አይደለም፣ ላቲንም አይደለም፡፡ እንዲሁም የግዕዝ የት-መጣ ያለው ቃልም አይደለም፡፡ “ጎልፃን” የፒያሳ ናዝራውያን (ጠቢባን) የፈጠሩት ሁለት የአማርኛ ውህድ ቃል ነው፡፡ ጎልማሳ እና ህፃን... በጉልምስናው እንደ ህፃን የሚያስብ በዕድሜው መግፋት ቁጥርን እንጂ የህይወት ልምድን ማካበት ያልቻለ ሰው “ጎልፃን” ይባላል። ለፒያሳ ናዝራውያን ባልተፃፈ መዝገበ ቃላታቸው ውስጥ፡፡ የጎልፃኖች ባህርይ አብዛኛውን ጊዜ ወደ “ተካ” ባህርይ ያደላል፡፡ “ተካ” ማን ነው ? ለምትሉ ... ተካ የስብሃቱ... ተካ የትኩሳቱ፡፡ ይሏችኋል ጎልፃኖች ድንገት የሆነ-ሥፍራ ላይ ሲያገኟችሁ ብዙ ድንገት አላስፈላጊ ጥያቄዎች ያነሱባችኋል ልክ እንደ “ተካ” የትኩሳቱ። ልክ እንደ ተካ የስብሃቱ “የት ነበርክ?...."የት እየሄድክ ነው?” ....ምን ልታደርግ ነው የምትሄደው?”.... “መቼ ትመለሳለህ?”... “ለምን እንዲህ አናደርግም?” ..... ይሄ ሁሉ የሚጠየቀው በአንድ ጊዜ ነው፡፡ ባገኟችሁ ቁጥር፡፡ የሚገርመው ጥያቄው እናንተንም እነሱንም የሚጠቅም አይደለም፡፡ በደረሱበት መመላለስ አለመቻል ባሉበት መርጋትን ካለማወቅ ይመነጫል። በጉልምስና ጡት መጥባት፣ ዘወትር እንደ ህፃናት ወተት ብቻ መጋት፣ አጥንት የሆኑ ሃሳቦችን መፍራት ከፍርሃታቸውም የተነሣ ጠንካራ አጥንታም ሃሳብ ሲነሣ ጮክ ብሎ በማውራት ፍርሃታቸውን ማስታመም የተካዎች ፀባይ ነው፡፡ ልክ አምባገነን መንግሥታት ቅልጥም የሆነ ሃሳብ የሚያነሡ ጋዜጠኞችና ፀሃፍት ሲነሱ በግርፋትና በእሥራት እንደሚያስፈራሩት ሁሉ ጎልፃኖችም እንደዚያው ናቸው። አንድ ቀን አንዱ የፒያሣ ናዝራዊን አንድ ጎልፃን ያገኘውና የተለመደ ጥያቄውን ያነሳበታል፡፡ “የት እየሄድክ ነው?” ጠየቀ ጎልፃኑ፡፡ “ካፌ” ናዝራዊው መልስ “ምን ልታደርግ?” “ወተት ልጠጣ” ናዝራዊው ዳግመኛ መለሠ፡፡ “ወተት መጠጣት ለምን ፈለክ?” የተለመደ ጎልፃናዊ ጥያቄውን ቀጠለ፡፡ “ትንሽ ጨጓራዬን አመም ስላደረገኝ” ጎልፃኑ ልክ እንደ ልክ እንደ መባነን ብሎ በፍፁም ወተት መጠጣት የለብህም፣ በፍፁም!” “ለምን!” አለው ናዝራዊው በተጨባጭ ምክንያት አማኝ ነውና። “ከስድስት ወር በፊት” አለ ጎልፃኑ .....” ከስድስት ወር በፊት ማናቸውም አይነት የወተት ምርቶች መጠቀም ህይወትን አደጋ ላይ መጣል ነው''። የሚል ነገር ፌስቡክ ላይ አንብቤአለሁ:: ስለዚህ ወተት የሚባል ነገር ባትጠጣ ጥሩ ነው፡፡ ይሄ መንግስት መምጫው አይታወቅም ....." ናዝራዊው ሳያስጨርሰው ጥሎት ሄደ..... ጎልፃኖች ሁሉን ነገር ፖለቲካ ማድረግ መለያቸው ነው፡፡ እናንተ አንድ ልታደርጉት ስለምታስቡት መልካም ሃሳብ ስታወሯቸው እነሱ ሃሳባቸሁ መሆን የማይችልበትን መቶ መንገዶች ይጠቁሟችኋል። የህይወታቸው ፍልስፍናም ከዚህ ተቃራኒ ልማዳቸው የተቀዳ ነው፡፡ ነገር በመጥለፍ እና የሚሆነው እንዳይሆን በማሠብ። በቅርቡ በተደረገ ጥናት ጎልፃኖች በርከት ብለው የሚገኙበት ሃገር “ኢትዮጵያ” እየሆነች መምጣቷን እስረጂ ፍንጮች ታይተዋል ይላሉ። ...ጥናቱን ያደረጉት የ”ሃዘንተኛ ልብ ባለቤት” የሚሰኙት ናዝራዊያን፡፡ ለጥናቱ ተጨባጭ ማስረጃ ብለው ያቀረቡት ደግሞ የሃገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር የአንድ ወቅት ቃለ መጠይቅ ነው። እርሱም “የእህል እጥረት ያጋጠመን እና ድርቅ ሊከሰት የቻለበት ዋና ምክንያት፡ ጤፍ የሚበላ ሠው ቁጥር መጨመሩ ነው፡፡ በፊት ጤፍ የማይበሉ ማህበረሰቦች አሁን ጤፍ፣ በሊታ መሆን ድርቁን (የእህል እጥረቱን) አስከትሏል” የሚለው የመሪው ቃል በኢትዮጵያ ውስጥ ጎልፃንነት የት-ድረሥ እንደተዛመተ ማሣያ ነው ብለዋል። ጥናቱን የሠሩት የ”ሃዘንተኛ ልብ ባለቤቶች” ዋና ሥራ እስኪያጅ የሆኑት ወይዘሪት ጥበብ ይሄይስ። በልጅነት ዕድሜው እኔ መሆን የምፈልገው ዶክተር፣ ፓይለት፣ ሠዓሊ፣ ደራሲ፣ ያላለ አንድም ህፃን የለም፡፡ ይህም ትክክለኛ የልጅነት ምኞት ነው፡፡ ይህ የልጅነት ተምኔት ውበቱንና ለዛውን የሚያጣው ግን በጉልምስናቸው “እኔ መሆን የምፈልገው ዶክተር መሆን ነበር፡፡ ፓይለት መሆን ነበር፡፡ ሠዓሊ መሆን ነበር፡፡ እንዲህ መሆን ነበረ፡፡ የሚለው አባባል የሚዘወተረው ጎልማሣም ልጅም መሆን በደባልቁ ጎልፃኖች ላይ ሲሰማ ነው፡፡ ብቻቸውን ሃገር ወዳድ ናቸው። ብቻቸውን ለሃገር አሳቢ ናቸው። ሁሉም ነገር የመንግስት ሥህተት ነው፡፡ የእነርሱ የመሆን ፍላጎት ፍላጎት ብቻ ሆኖ የቀረው በመንግስት ሥህተት ነው፡፡ በመንግስት አቅጣጫ የሚገኙ ጎልፃኖች ከሆነ ደግሞ በተቃራኒው ናቸው፡፡ እነዚህ መንግስት ሲሉ እነዚህ ደግሞ ህዝብ ይላሉ። በቀኝም ሆነ በግራ በኩል የተሰለፉ ጎልፃኖች አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር በግለሠብ አመለካከት የማያምኑ መሆናቸው ነው፡፡ ሁሉም ማለት ይቻላል መናጆዎች ናቸው።ከመንጋጋት በስተቀር ነጠል ብለው መቆም አይችሉም፡፡ በአንድነት እንጂ አንድ በመሆን አያምኑም፡፡ ጎልፃኖች በግለሠብ አመለካከት የማያምኑበት ትልቁ ምክንያት ብቻቸውን ሆነው ስለማያውቁ ነው። ለብቻ ቆም ብሎ ነጠል ብሎ ማሰብ ለጎልፃኖች ሞት ነው፡፡ ዕድሜያቸውን የሚገፋት በብቸኞች ሃሳብ ላይ በማሳደም ስለሆነ፡፡ ለብቻቸው ሊሆኑ የሚፈጠውን እውነት መሸከም ስለማይችሉ ግርርር ማለት እንጂ ነጠል ብሎ መገኘት እርማቸው ነው፡... ሁለት የተለያየ አቋም ያላቸው..... ሁለት የተለያየ የፖለቲካ ....የህይወትና የጥበብ አመለካከት ልዩነት ያላቸው ገልፃኖች እኩል የሚጣሉትና እንደጠላት የሚያስቡት ቢኖር ብቸኛንና ብቸኝነትን ነው። ለብቸኝነት ስፍራን የሚሰጡት “የሃዘንተኛ ልቦና ባለቤቶች” የሚል ስያሜ ከሕይወት ልምዳቸዉ የተሰጣቸው ናዝራዊያን ታሪክ በደቦ ተሠርቶ አያውቅም፣ ለውጥ የግለሰቦች አመለካከት ውጤት ናት፡፡” የሚል አመለካከት ስላላቸው በተቃራኒ መንገድ ላይ ያሉ ጎልፃኖች እኩል የሚጠሉት በሃሣባቸው ተቃራኒ የሆኑትን ናዝራዊያንን ነው። ናዝራውያን በሕብረት ሲሆኑ አንድ አይነት አስተሳሰብ ኖሯቸው ሳይሆን የተለያዩ ሃሳቦችን አክባሪ ስለሆኑ ጭምር ነው። ጎልፃኖች የዘር ሃረጋቸው የሚመዘዘው ከተረት እና ከጭፍን ስሜተኝነት ነው፡፡ ናዝራዊያን ዘወትር የሚያነሱት ምክንያተኝነት በጎልፃኖች ዘንድ የሚታየው እንደ አባታቸው ገዳይ ነው፡፡ ሁሉን እሺ ባይ ያልሆነ ሰው ከእነሱ ጋር መኖር አይችልም፡፡ እነሱም ሁሉን ከሚጠይቅ ሰው ጋር ሰላምታ የላቸውም:: ጎልፃኖች ሰውን ጠልፈው የሚጥሉበት አንድ መፈክር አላቸው፡፡ “ከእኛ ጋር ያልሆነ ከማንም አይሆንም"። ከራሱም ጭምር እንደማለት ነው እንግዲህ፡፡ “እንደኔ ካላሠብክ፡ .....ሃሳብህን ትተህ እኛን ምሰል.....” ከሚል የጅምላ አስተሳስብ ናዝራውያኑ የተለዩ ስለሆኑ ሁለት በደም የሚፈላለጉ ጎልፃኖች በአንድ ናዝራዊ ፊት “ከየት የመጣ ፍቅር ነው?” እስኪባሉ ድረስ ወዳጃሞች ይሆናሉ። “የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው “ እንዲል -ጎልፃኖች የተረት ኣባት..... በዚያች እለት ሄድሮስ እና ጲላጦስ ስምምነትና ፍቅር ሆኑ። አስቀድሞ በመሃላቸው ጠላትነት ነበርና .......... እንዲሉ ናዝራውያን፡፡ ምንጭ ፦ የአዋጁ ጊዜ ፀሀፊ ፦ ኤፍሬም ስዩም ከ #ኑእናንብብ @Zephilosophy @Yotop77 @Yotop77 @Yotop77
Show all...
ያንተ ጓደኛ ይሄ ነው?! ጦርነቱ ጋብ ካለ በኋላ አንድ ወታደር በውጊያ ሜዳ የወደቀውን ጓደኛውን ለመፈለግ አለቃውን ያስፈቅዳል፡፡ አለቃውም 'መሞቱ ለማያጠራጥር ሰው ብለህ ህይወትህን አደጋ ላይ እንድትጥል አልፈቅድልህም' በማለት ፍቃድ ይነፍገዋል፡፡ ወታደሩ ግን አሻፈረኝ ብሎ ፍለጋውን ይቀጥላል፡፡ ከፍለጋ በኋላ እሱም ሞት አፋፍ ላይ ባደረሰው ሁኔታ ቆስሎ የሞተ ጓደኛውን አስክሬን ተሸክሞ ይመጣል፤ አለቃውም 'ይሞታል ብዬህ አልነበረም? ለሚሞት ሠው ብለህ ይህን ሁሉ መስዋዕትነት መክፈል ነበረብህ፤' በማለት ይወቅሰዋል፡፡ ወታደሩ ግን በስራው ደስተኛ ነበር ፡፡ አለቃዬ ይህኮ ምንም ማለት አይደለም ጓደኛዬ በሞት አፋፍ ላይ ደርሸበት ያለኝን ብነግርህ ትረዳኝ ነበር ፣ አለቃውም 'ምን አለህ?' ሲለው ወታደሩም #እንደምትመጣ_እርግጠኛ_ነበርኩ'፡፡ ❖ እውነተኛ ጓደኛ ማለት ሁሉም ሠው ሲሸሽህ እሱ ግን የሚፈልግህ ነው! <3 <3 <3 ከ #ንባብለህይወት @yotop77 @Yotop77 @Yotop77
Show all...
🇪🇹በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ አበይት ክንውኖች 🇪🇹 ✏️ሚያዝያ 28/1875 አፄ ምንሊክ ከ እቴጌዪቱ ተጋቡ። ✏️ሚያዝያ 25/1881 ምንሊክ ከጣሊያን ጋር ውጫሌ ውል ተፈራረሙ። ✏️ ጥቅምት 2/1988 ለአድዋ ዘመቻ ምንሊክ ከአዲስአበባ ተነሱ። ✏️ሕዳር 28/1988 አምባላጌ ጦርነት ላይ ኢጣልያኖች ተሸንፈው ሸሹ። ✏️ ታህሳስ 28/1988 ራስ መኮንን የመቀሌን ምሽግ ከኢጣልያን አስለቀቁ። ✏️ የካቲት 23/1988 አድዋ ⚔ ✏️ጥቅምት 20/1902 የልጅ ኢያሱ ወራሽነት እንዲሁም የራስ ተሰማ ናደው ሞግዚትነት አፄ ምንሊክ አሳወጁ። ✏️መጋቢት 12/1902 እቴጌ ጣይቱ ከፖለቲካ ስልጣናቸው እንዲለቁ ተወሰነ። ✏️ታህሳስ 3/1906 አፄ ምንሊክ አረፉ በምትካቸውም ልጅ ኢያሱ ነገሡ። 🔎 የተጠቀሱት ዘመናት በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር መሆናቸውን ላሳስብ እወዳለሁ። ከ #ታሪካዊትኢትዮጵያ @ethioabesha @Yotop77 @Yotop77 @Yotop77 መልካም ቀን ይሁንላችሁ!!!
Show all...
የኖህ መልዕክተኛ _(የቁራ መልዕክተኛ) _ ያኔ በኖህ ዘመን መልካምን : ሊያመጣ : ጥፋትን : አዝንቦ በሞት : ህይወት : ውሀ : መርከቢቱን : ከቦ ቀኑም : ደረሰና : ዝናቡ :አባርቶ ቁራውን : ሰደደ : የዝምታን : ዜማ : በጆሮቹ : ሰምቶ የተከፋው : ቁራ : የኖህን : ቃል : ረስቶ ከሞላው : ውሀ : ላይ : ይፈልግ : ነበረ የፍቅሩን : ሬሳ : ደክሞ : እየበረረ **** ቁራ:በመልዕክቱ:ቃል:አባይ:ተደርጎ ሲያሙት : አሰማቸው : ይህን : እንጉርጉሮ * ስሜ : በኖህ: መዝገብ : በክፋት : ላይ ሰፋሯል ውሸታችሁ:ዘሎ:እውነቴ:አንክሷል አለመመለሴ : መልስ : እንዳይሆናችሁ ከሀዲ: አትበሉኝ : ታምኜ: እያያችሁ **** ኖህ: መርከብ: ሳይሰራ: ከፍቅር አጋሬ እየኖርኩኝ: ነበር: ጎጆዬ: ሰፍሬ እኔ: ተነጥዬ: ከውሃው: ባመልጥም የቀረችው: ፍቅሬ: መትረፏን አላውቅም ያንተን: መልዕክት: ይዤ: እንዲያ ምማስነው አንድ: መልዕክት: እንኳ: ትታልኝ ከሄደች: ብዬ: አስቤ: ነው **** የሆነውስ ሁኖ * ቁራው: ሳይመለስ: እርግቧ: ተልካ ከወይራው: ግንድ: ላይ: ቅጠልን አስታካ ይዛ: የሄደችው: ተራ: ቅጠል: ሳይሆን ቀርቦ: ላነበበው: በነብስ: ለገለጠው በጥፍቱ :ውሀ:የጠፉት:ትተውት:የሄዱት መፅሀፍ :ነው /******/ ✍ናታን ኤርሚያስ ከ #ግጥምብቻ @getem @Yotop77 @Yotop77 @Yotop77
Show all...
🔘የስዋስቲካ ምልክት አስደናቂ ምስጢር🔘 ቅዱስ ላሊበላ ባሳነፀው አስደናቂ ቤተ ክርስቲያን ላይ የምናየው አስደናቂ ምልክት በብዙዎች ዘንድ አነጋጋሪ እንደሆነ ይስተዋላል፤በርካቶችም የተለያዩ መላምልቶች ሲሰጡበት ይደመጣል።አንዳንዶች "የጀርመናዊው የናዚ አርማ ነው" ሲሉ አንዳንዶቹ ደግሞ "የግብፅ ነገስታት ያሰሩት ምልክት ነው" ይላሉ።ነገር ግን በቀደሙ ጥንታዊ የኢትዮጵያ መዛግብት እንደተገለጠው ይህ ምልክት ታላቅ ምሥጢር የያዘ ነው። በዚህ በአራት ማዕዘን ቅርፅ ውስጥ ተቀርፀው የምናገኛቸው አሀዞች|ቁጥሮች| ሁለት ሰባቶች ናቸው። በግዕዝ ቁጥር ሰባት "፯" ይህን መሰል ቅርፅ አላት።የአራት ማዕዘኑን ሠንጠረዥ ነክተው የተገኙት እነዚህ ሁለት ሰባቶች ቅዱስ ላሊበላ አንድ ታላቅ ምሥጢር የገለጠባቸው ምልክቶች ናቸው።በጥበብ የበለፀጉ በጥበብ ሁሉን ነገር ያዋቅራሉ። ፯×፯=፵፱ ሰፍረን ቆጥረን የማንጨርሰው የሚታዩትንና የማይታዩትን ፍጥረታት የፈጠረ የአብ ቀመር ነው። አብ የሚለውን ቃል በቀመር ስናየው አ=40 በ=9 በድምሩ 49 ይሆናል።በኦሪትም አምላክ"ሰባት ጊዜ ሰባት አድርገህ የዓመታትን ሰንበት ቁጠር" /ዘሌ 25፥8/ ያለውን የብርሀን ዕለት ነውና።ቅዱስ ላሊበላ በመንፈስ ቅኝት ውስጥ የነበረ ስለሆነ የሰማያዊቷን የብርሃን ዓለም ምሳሌ ለብርሀን ሰዎች የተዘጋጀላቸውን ያቺን ከተማ ነው በምድር የገነባው። #mezgeb_tebeb ከ #የኢትዮጵያታሪኮችናጥበቦች @Yotop77 @Yotop77 @Yotop77
Show all...
ከሀገሩ ውጪ ላሉ ጭቁኖች የተፋለመው ኢትዮጵያዊው አፄ ካሌብ 👉በ 5ኛው ክ/ዘመን ኢትዮጵያን ንጉሥ አፄ ካሌብ በሚአስተዳድሩበት ዘመን በዓረብ አገራት የሚኖሩትን የክርስትና እምነት ተከታዮች ላይ አይሁዳውያኑ በፋርስ ድጋፍ አማካኝነት በመጨፍጨፍ፣ በማሰቃየትና በመጨቆን አላኖር አሏቸው። በአሁን አጠራር የመን አካባቢ የሚኖሩ ህዝቦችን ንጉሥ ፊንሐስ ክፋኛ መከራቸውን አበዛው ፤ በአንድ ቀን ብቻ 20,000 ክርስቲያኖችን እንዳስፈጀ ብዙዎች ፅፈዋል። በዚህ ጊዜም ቶማስ የተባለ ጳጳስ ከየመን አምልጦ ወደ አክሱም በመምጣት ለአክሱም ንጉሥ ካሌብ የተፈፀመውን ግፍ ሁላ አብራራ። አፄ ካሌብም ሁኔታውን እንደሰማ ለዘመቻ ዝግጅት ጀመረ። ከዝግጅቱ በኋላም 72 ታላላቅ መርከቦችና 70,000 የሚሆኑ ሰራዊት ይዞ ጉዞ ጀመረ። በቦታው እንደደረሰም ውጊያው መርከብ ላይ እንዳሉ በጦር በቀስትና መርከቦቻቸው ተጠጋግተው በጨበጣ ለጥቂት ጊዜ ሲካሄድ ቆይቶ ፍልሚአው ወደየብስ ተቀይሮ በሁለቱም ወገን ብዙ ሰራዊት ካለቀ በኋላ ድሉ የአፄ ካሌብ ሆነና አይሁዳውያኑ ሲበታትኑ ንጉሥ ፊንሐስም ሸሸ። ከዚያም አፄ ካሌብ ወደ የመን ከተማ ወደ ዛፋር ሔዶ የከተማውን ጠባቂዎች አሸንፎ ከተማውን ያዘ። አፄ ካሌብና ንጉሥ ፊንሐስም ፊት ለፊት ተገናኝተው በጨበጣ ፈረሶቻቸው ላይ ሆነው ሲዋጉ ካሌብ ፊንሐስን ወግቶ ከፈረሱ ላይ በመጣል ወደ ባህር ገፍትሮ ወርውሮ በመገድል ድል አረገው። ከዚህ በኋላ የሸሹትና የተደበቁት ክርስቲያኖች ወደየመንደራቸው ተመለሱ። የፈረሱትንና ያረጁትን ቤተክርስቲያኖች ራሳቸው አፄ ካሌብ እየቆፈሩ በማሰራት ጥቂት ጊዜ በየመን ተቀመጡ። በየመን ህዝብ ፍላጎትም መሰረትም አርያት የተባለውን ሰው ንጉስ አርጎ ሾሞላቸው በየአመቱም ለአክሱም ቤተ መንግስት እንዲገብሩ ትዕዛዝ ሰጠ። በዚህም የየመን ህዝብ ከካሌብ ጀምሮ ለ100 ዓመታት በመገበር ቀጥለው የነበር ሲሆን ከዚያ በኋላ ግን ፋርሶች መጥተው የመንን በመቆጣጠር ቤተክርስቲያናትን አፍርሰው የጣኦት ቤተ መቅደሶችን ገነብተዋል። ረሱለላሂ ነብዩ መሐመድ መጥተው ፋርሶችን አሸንፈው የጣኦት ቤተ መቅደስ በማስፈረስ መስጊድ እስካአስገነቡበት 630 ዓ.ም ፋርሶቹ በየመን ቆይተዋል። እንግዲህ አፄ ካሌብ የአክሱምን ስልጣኔ ከማሳደጋቸው ባለፈ ከሀገራቸው ውጪ ላሉ ጭቁኖች በመፋለም ነፃነትን ያጎናፅፋ መሪ በመሆናቸው በአረቦችና በቆስጠንጢኒያ የገነኑ ንጉሥ ናቸው። ዛሬ ድረስ የሮም ቤተክርስቲያን ከሠማዕታቱ ጋር ቆጥራ በየዓመቱ የአፄ ካሌብን በዓል ኦክቶበር 27 ቀን ታከብራለች። ከ #ታሪካዊትኢትዮጵያ @ethioabesha @Yotop77 @Yotop77 @Yotop77
Show all...
Show all...
ዮቶጵ ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ በአምላክ የተወደደች፤ የጥንተ ስልጣኔ ምንጭ አኩሪ ባህል እና ታሪክ ያላት ሀገር ናት። የሀገር ፍቅር መገለጫው አንዱ ስለ ታሪኳ ጠንቅቆ ማወቅ ነውና ስለ ኢትዮጵያ ያልተነገሩ እና ድንቅ ታሪኮቿን ለማወቅ፤ ይቀላቀሉን። ለማንኛውም አስተያየት : @Dawit77

እውነት ሄድሽ በቃ? - ምትወጃት ጨረቃ ከሰማይ ሰሌዳ ሳትጠፋ ጠልቃ ነብሴም እንቺን ለምዳ፣ ልክ እንደ ህፃን ልጅ ሳይበቃት ፈንድቃ እውነት ሄድሽ በቃ? ለቅሶ ይሰማኛል፣ የሚያነቡ ሰዎች ከፊቴ አያለሁ አፈር ቡንን ይላል፣ መቃብር ሲቆፈር እመለከታለሁ ምን እያረጉ ነው? ምን እንደሚያደርጉ እኔ ምን አውቃለሁ ድንዝዝ ብያለሁ! መደንዝዝ ታውቂያለሽ፣ ሳይነቃነቁ ዝም ብሎ መገተር ምንም ስሜት አልባ፣ በጥፊ ቢመታ ወይም ቢገፈተር ደንዝዝ ብያለሁ አዎ ልክ እንደዛ እንዲሁ እንደ ወዛ! ፎቶሽን የያዙ፣ አሮጊት ሴትዮ ደረት ይመታሉ እንዳንዶች በዕንባ፣ እህህ እያሉ ይንከራተታሉ የማልቀስ የማንባት እነዚህ ስሜቶች እኔ ጋ የታሉ? ፍርጃ ፍዝዝ ብያለሁ ያላንዳች እርምጃ ድንዝዝ ብያለሁ የነካኝን እንጃ! በቆምኩበት ቦታ፣ እንደተገተርኩኝ ዕንባ ሳላወጣ የለቅሶ የዋይታ፣ አሰቃቂ ድምፀት እየተጠጋኝ መጣ! ድንገት ብንን አልኩኝ፣ ይደልቅ ጀመረ ልቤ በሀይል መምታት ለሁለት ተከፈልኩኝ አነቃኝ ማመንታት! በዚህ...፣ ዘላለማዊ ናት አትሞትም እሷ በዚያ...፣ እመን እመን እመን ከንግዲህ አትመጣም አፈር ሆኗል ልብሷ! በጥርጥር መሀል በማመንም መሀል ልቤ እየዋለለ ዕንባዬ ጠብ አለ! ጉም ዙሪያዬን ሞላው ጨለማ ከለለኝ መሄድ መሞትሽን አመንኩኝ መሰለኝ! ለራሴ አዘንኩኝ ባዘን ሆዴ ባባ አምርሬ አለቀስሁ ታጠብኩኝ በዕንባ! አይመስለኝም ነበር በግዜ ምትከፍቺው የማቃብርን በር! መውደድ ሳይዳብሰኝ ፍቅር ሳይነካካኝ አልቀርብሽም ነበር፣ መሆንሽን ባውቀው እዚህ ድረስ ጨካኝ:: ላትመጪ ነገር ላትመለሽ ነገር ወዴት ሄጄ ልበድ፣ የልቤን ትኩሳት ምን ብዬ ልናገር? ምትወጃት ጨረቃ ከሰማይ ሰሌዳ ሳትጠፋ ጠልቃ ነብሴም እንቺን ለምዳ፣ ልክ እንደ ህፃን ልጅ ሳይበቃት ፈንድቃ እውነት ሄድሽ በቃ? ✍ ዳናይት @getem @getem @getem
Show all...
በመዋጮ መስዋእትነት አለቅን!! #ባርቾ የሚለው የደራሲ ሕይወት እምሻው መጽሐፍ ላይ አንድ የሰፈረች ምሳሌ እንጋብዛችሁ... ፨፨፨ አቶ አሳማና እመት ዶሮ መንገድ ይገናኛሉ። ጥቂት ካወሩ በኋላ ዶሮዋ፣ "ስማ አንድ ግሩም ሃሳብ አለኝ። እኔና አንተ ለምን አንድ ምግብ ቤት በጋራ አንከፍትም?" ትለዋለች። አሳማም፣ "ምን የሚባል ምግብ ቤት?" ይላል። "የአሳማ ስጋና እንቁላል ምግብ ቤት ብንለውስ?" ዶሮ ትመልሳለች አሳማ ዝም ብሎ ሲያስብ፣ "ያው አንተም በስጋህ እኔም በእንቁላሌ ማለት ነው" ብላ ቀጠለች ዶሮ ። አሳማም ትንሽ አሰብ አድርጎ፣ "ግዴለም ይቅርብኝ። ይህንን ምግብ ቤት ማቅናት ላንቺ መዋጮ ነው። ለኔ ግን መስዋእትነት ይጠይቃል።" ብሎ መለሰላት አሉ። የኛም ማለቂያ አልባ መዋጮ፣ ምስኪኖቹን ከእመት ዶሮ ይልቅ አሳማውን እያስመሰለን አይመስላችሁም??? ምንጭ 📖 ባርቾ...ገጽ 124 ደራሲ ✍ ሕይወት እምሻው @Zephilosophy @Zephilosophy
Show all...