cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Tikvah-University

Show more
Advertising posts
211 362Subscribers
+5324 hours
+3807 days
+3 29830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፈው ወር ያጋጠመውን ችግር ተከትሎ ገንዘብ ያወጡ ወይም ያዘዋወሩና እስካሁን ገንዘቡን ያልመለሱ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እስከ ዛሬ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም ድረስ ገንዘቡን እንዲመልሱ ዩኒቨርሲቲው ለመጨረሻ ጊዜ አሳስቧል፡፡ የወሰዱትን ገንዘብ ተመላሽ ያላደረጉ 55 ተማሪዎችን ሙሉ ስም፣ የተማሪ መለያ ቁጥር እና የትምህርት ክፍል ይፋ ያደረገው ዩኒቨርሲቲው፤ ለመጨረሻ ጊዜ በተሰጣቸው ዕድል ገንዘቡን በማይመልሱ ተማሪዎች ላይ ዕርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው በጥብቅ አሳስቧል፡፡ @tikvahuniversity
Show all...
👎 130👍 53 3👏 1
#ጥቆማ “ኢትዮጵያ:- ከግብርናና ከምግብ ቀውስ ነጻ ስለ መውጣት” በሚል ርዕስ ለህትመት የበቃ መፅሐፍ ተመረቀ፡፡ “ኢትዮጵያ:- ከግብርናና ከምግብ ቀውስ ነጻ ስለ መውጣት” የተሰኘው የአቶ ጌታቸው ድሪባ የጥናት ውጤት የሆነው መፅሐፉ፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ ለህትመት መብቃቱ ታውቋል፡፡ በሀገሪቱ የግብርና ዘርፍ ልማት ላይ ጥልቅና ሳይንሳዊ ዕይታን ያቀረበው መፅሐፉ፤ በዘርፉ ለሚደረጉ ጥናትና ምርምሮች ማጣቀሻ ሆኖ ያገልግላል ተብሏል፡፡ መፅሐፉ ETHIOPIA: OVERCOMING AGRICULTURAL AND FOOD CRISES በሚል ርዕስ በእንግሊዘኛ መታተሙም ተገልጿል፡፡ @tikvahuniversity
Show all...
👍 19😢 3👎 2 2🥰 1
በሰኔ 2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ የርቀት እና ተከታታይ መርሐግብር ተመራቂ ተማሪዎች ትምህርት ሚኒስቴር በወሰነው መሰረት የአገልግሎት ክፍያ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) እስከ ሚያዚያ 15/2016 ዓ.ም ድረስ እንዲከፍሉ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አሳስቧል። ክፍያውን ያልፈፀመ ተማሪ የመውጫ ፈተና መውሰድ የማይችል መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። @tikvahuniversity
Show all...
👍 13👎 7
#የቻናል_ጥቆማ 🔔 ለኢንጂነሪንግ ተማሪዎች እና Construction ዘርፍ ላይ ለተሰማራችሁ በሙሉ‼️ የኮንስትራክሽን፣ ሲቪል ኢንጂነሪንግ፣ የአርክቴክቸር ተማሪ ነዎት? በጠቅላላ ኮንስትራክሽን የተሰማሩ ባለሙያ ነዎት? 📚 በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ የሌክቸር ትምህርቶች፣ መፃሕፍቶች፣ ቪዲዮዎች እና ጠቃሚ የኮንስትራክሽን ዕውቀቶች ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉን! 👉 ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያዎች፣ 👉 አዲስ የሚወጡ የግንባታ ጨረታዎች፣ 👉 እጅግ ጠቃሚ የኮንስትራክሽን መረጃዎች፣ 👉 በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ሌክቸር የምታገኙበት፡፡ Join Us :- ✅on Telegram 👇 https://t.me/ethioengineers1 https://t.me/ethioengineers1 ✅on TikTok tiktok.com/@ethiocons tiktok.com/@ethiocons
Show all...
👍 5
20ኛ ዙር የግራፊክስ ዲዛይን፣ ቪዲዮ ኤዲቲንግ፣ ሞሽን ግራፊክስ እና ዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን!! 🔔 አሁኑኑ ይመዝገቡ! 👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና 👉 ከ15 በላይ ፕሮጀክቶች ያሉት 👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት 👉 Advanced Graphics + Video Editing + Motion Graphics + Digital Marketing በአንድ ላይ ☎️ ለበለጠ መረጃ፦  0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ የበለጠ ይጠብቁ ...         ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት Facebook | Telegram | Instagram | LinkedIn
Show all...
👍 13 1
#ጥቆማ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ “የባህላዊ ቅርሶች ጥበቃ ተግዳሮቶችና መፍትሔዎች” በተሰኘ ጭብጥ ላይ የፓናል ውይይት መድረክ አዘጋጅቷል፡፡ ውይይቱ ዛሬ ሚያዝያ 10/2016 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ እሸቱ ጮሌ መታሰቢያ አዳራሽ ይካሔዳል፡፡ መርሐግብሩን የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በኢትዮጵያ ከሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ክፍል ጋር በመተባበር የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በባህላዊ ቅርሶች ጥበቃ ዘርፉ ታዋቂ የሆኑ ምሁራን በመድረኩ በአቅራቢነትና ተወያይነት ይሳተፋሉ፡፡ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል፡፡ @tikvahuniversity
Show all...
👍 55 11👎 5
#የሥራ_ቅጥር_ጥቆማ የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ከዚህ በታች በተገለፀው የትምህርት መስክ መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾችን አወዳድሮ በመምህርነት በቋሚ ኮንትራት ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡ ➤ የሥራ መደብ፦ መምህርነት ➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 16 ➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ በህክምና የመጀመሪያ ዲግሪ ➤ የሥራ ቦታ፦ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ➤ የመመዝገቢያ ጊዜ፦ ከሚያዝያ 8/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ብቻ ➤ የምዝገባ ቦታ፡- አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ የሰው ሃብት አስተዳደር 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 5 Note: አመልካቾች ለምዝገባ ስትሔዱ የ8ኛ እና 10ኛ/12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት፣ የመጀመሪያ ዲግሪ ማስረጃ ሰርቲፊኬት እንዲሁም የሙያ ፍቃድ ምዝገባ የታደሰ ዋናውና የማይመለስ አንድ ኮፒ መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡ አመልካቾች የመጀመሪያ ዲግሪ ውጤታችሁ 3.00 እና ከዚያ በላይ ሊሆን ይገባል፡፡ @tikvahuniversity
Show all...
👍 52 9😱 2
#ጥቆማ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በቀርከሃ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ያካሒዳል፡፡ "Climate-smart Bamboo Forest Economy for Sustainable Development” በተሰኘ ጭብጥ ላይ የሚመክረው ጉባኤው፤ ሚያዝያ 11 እና 12/2016 ዓ.ም ይካሔዳል፡፡ ቀርክሃ ከምግብነት እስከ ቤት ውስጥ መገልገያ እቃ፣ ለቢሮ እና ለመኖሪያ እንዲሁም ለቢዝነስ፣ ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለው አረንጓዴ ወርቅ ነው፡፡ ኢትዮጵያ አንድ ሚሊዮን ሄክታር የተፈጥሮ ቀርክሃ ሃብት እንዳላት የሚገመት ሲሆን በቢኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ የቀርክሃ ሃብት ይገኛል፡፡ ለሁለት ቀናት በሚካሔደው ጉባኤ፤ በርካታ የዘርፉ ተዋናዮች እና ተመራማሪዎች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡ @tikvahuniversity
Show all...
👍 34🙏 6 1
Are you a business owner with a gig matching model? Do you have a team committed to elevating your business to new heights? Is your business officially registered and backed by a six-month proof of concept? Does your business boast unique value propositions and a scalable model? If you answered yes to these questions, then unlock Mesirat’s business development, marketing, technology, and qualified financing support by applying to the Mesirat Entrepreneurship Program 5th Cohort applications. Application link: https://mesirat.org/apply/ #GigWork #MesiratEthiopia #GigEconomy
Show all...
👍 18 2
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መቼ ይሰጣል?2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና መቼ እንደሚሰጥ በርካቶች ጥያቄ አድርሰውናል። የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰኔ ወር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወቃል። በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ምዝገባ እንዳደረጉ መገለፁም ይታወሳል፡፡ ለሦስተኛ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተናው፤ ዘንድሮ ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ለማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ለእያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት አይነቶች እንዲሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑ አይዘነጋም፡፡ @tikvahuniversity
Show all...
👍 202👎 20 15🙏 12😱 8😢 8👏 3