cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

﷽ | Muslim | Theology | Comparative Religion | Philosophy | Student | Teacher |

Show more
Advertising posts
12 860Subscribers
+2524 hours
+1437 days
+40730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

"ከሰዎች መካከል አሉ፣ ይጾማሉ ግን ከጾማቸው ረሀብን እንጅ አያተርፉም" ሱነን ኢብን ማጃህ 1690
Show all...
😢 17👍 8
🥰 21 9👍 1
ቀልድ አይደለም..! እስልምናን የሚተች አንድ የቴሌግራም ቻናል ነው ብለው ወንድሞች ልከውልኝ ሳየው ያገኘሁት ነው። ቁርአን ከአማርኛ ቋንቋ የተዋሳቸው ቃላት አሉ በሚል ሲያቀርብ የተጠቀመው ነው። ሁለቱ ቃላት ማለትም "ፈርስና ፈረስን" በቅጡ መለየት አልቻለም። አፕልኬሽኑ እንኳን ቢያሳሳት ሰው ኮንቴክስት አይቶ እንዴት መረዳት ይሳነዋል? እስልምናን ሲተቹ የምትመለከቷቸው አብዛኛዎቹ ተሳዳቢዎች እውቀት ላይ እንዲህ መናኛ ናቸው። የአማርኛ ቋንቋ በመሠረቱ ለአረብኛ ቃላት ምንጭ መሆን የሚችል አይደለም። እድሜውም ለዚያ አያበቃውም። ባየ ይማም "የአማርኛ ሰዋሰው" በተሰኘ መጽሀፉ መቅድም ላይ አማርኛ ቋንቋ ከተለያዩ ቋንቋዎች ቃላትን በመዋስ የተፈጠረ ድብልቅ ቋንቋ እንደሆነ ይገልጻል። ፈረስ የሚለው ቃልም እንዲሁ የተውሶ ቃል መሆኑን እንዲህ ሲል ይገልጸዋል፦ "አማርኛ የተለያዩ ቋንቋዎችን ይናገር በነበረ ዘማችና አዝማች የተፈጠረ የሠራዊት ቋንቋ ነበር ለማለት ይቻላል፡፡ መሠረታዊ መድበለ ቃላቱ ባብዛኛው ሴማዊ ሲሆኑ፣ በመጠኑ ደግሞ ኩሻዊ ናቸው፡፡ ለዚህ እንደውሻ፣ ካራ፣ ውሃ፣ ሸኮና፣ አኮሌ፣ አሬራ፣ ኮርቻ፣ ቀብድ፣ #ፈረስ፣ ዱላ፣ ወዘተ. ያሉት ቃላት እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል" ባየ ይማም "የአማርኛ ሰዋሰው" መቅድም የአማርኛ ቋንቋ በመሠረቱ ልሳነንጉስ የሆነው በ1272 በአጼ ይኩኖ አምላክ ነበር። ከዚያ በፊት ይታወቅም ይነገር የነበረውም ቋንቋ ግዕዝ ሲሆን አማርኛም ድብልቅ ቋንቋ ሁኖ መነገር ሲጀምር ነገስታቱ ከዛግዌ ለተረከቡት ሰለሞናዊ ስርአት ይፋዊ መነጋገሪያ አደረጉት። እውነታው ይህ ነው፣ ትንሽም ቢሆን ማስተዋልና ማንበብ የታከለበት ሰው መሠል ስህተት ውስጥ አይወድቅም። ___ https://t.me/Yahyanuhe
Show all...
👍 30 4
ሸይጧን በረመዷን ታስሯል ካላችሁ ለምን ኃጥያት ላይ ትወድቃላችሁ?ሸይጧን ከታሰረ እንዴት ወንጀል አልጠፋም? ጥሩ ጥያቄ ነው፣ እስኪ በአጭሩ እንደሚከተለው እናብራራው፥ የሰውን ልጅ ወደ መጥፎ ተግባራት የሚመሩት ሁለት አካላት ናቸው። እነሱም፦ 1- የሰይጣን ጉትጎታ (شَرِّ الشَّيْطَانِ) 2- የነፍስ ጉትጎታ (شَرِّ نَفْسِي) ናቸው። የሰው ልጅ ከሸይጧን ጉትጎታ በተጨማሪ የነፍስያው ጉትጎታም ሀራም ተግባራት ላይ ይጥሉታል። ስለዚህም ሸይጧን መታሰሩ ብቻ የሰው ልጅ መጥፎ ከመስራት አያቅቡትም፣ ነፍሱንም ጭምር መግራት ካልቻለ በቀር..!በመሠረቱ የሸይጧን ጉትጎታም ደካማ ተብሎ በቁርአን ተጠቅሷል። ነፍስ በዚህ በኩል የምትፈጥረው ጉትጎታ ቀላል አይደለም። ለዚህ ምንድን ማስረጃው ከተባለ የሚከተሉት የቁርአን አንቀጾችና ሀዲሳት ይጠቀሳሉ፦ ◾️ ማስረጃዎች፡- 1- ቁርኣን እንዲህ ይላል፦ إِنَّ النَّفْسَ لَأَمَّارَةٌ بِالسُّوءِ إِلَّا مَا رَحِمَ رَبِّي "...ነፍስ ሁሉ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና፡፡.." (ቁርኣን 12፡53)። 2- ቁርኣንም ደግሞ እንዲህ ይላል፦ وَلَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنْسَانَ وَنَعْلَمُ مَا تُوَسْوِسُ بِهِ نَفْسُهُ وَنَحْنُ أَقْرَبُ إِلَّيْبِينَ "ሰውንም ነፍሱ (በሐሳቡ) የምታጫውተውን የምናውቅ ስንኾን በእርግጥ ፈጠርነው፤ እኛም ከደም ጋኑ ጅማት ይበልጥ ወደርሱ ቅርብ ነን፡፡" (ቁርኣን 50፡16)። 3- ነቢዩ "ﷺ" ይህንን ዱዓ አስተምረውናል፦ أَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ نَفْسِي وَمِنْ شَرِّ الشَّيْطَانِ "ከነፍሴ ክፋት ከሰይጣንም ክፋት በአንተ እጠበቃለሁ" ["አቡ ዳውድ"፣ 5067 - صحيح]። 4- ነቢዩ "ﷺ" እንዲህ ብለዋል፦ الْمُجَاهِدُ مَنْ جَاهَدَ نَفْسَهُ "ሙጃሂድ (ታጋይ ማለት) ነፍሱን የሚታገል ነው።" ["ቲርሚዚ", 1621 - صحيح]. 5- ቁርኣንም እንዲህ ይላል። وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَى فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَى "በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ፥ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፡፡ (ቁርአን 79፡40-41)። ወሏሁ አዕለም..! © አቡ ሐይሰም (Yahya) ___ https://t.me/Yahyanuhe
Show all...
👍 41 5👏 3
የኢዩ ጩፋ ስሁት ፍረጃ | ምላሽ -17 https://vm.tiktok.com/ZMMU8MN9b/
Show all...
👍 18
"ሳራ ነኝ ሰለምቴዋ" በሚል አካውንት የምናውቃት እህታችን በኦንላይን ሾፒንግ የሚከተሉትን አልባሳት የመሸጥ ስራ ጀምራለች። የወደዳችሁትን ልብስ በመግዛት አበረታታቷት፦ ስልክ ቁጥር፦ +96654 798 4638 📞
Show all...
👍 64 13🎉 1
ከጎኑ የሚሰግደውን ሰው የለቅሶ ሲቃ በመጠኑም ሰምቶ ነበርና ሲጨርሱ ወደሱ ዘወር ብሎ "ምን ያክል ትርጉሙ ቢገባህ ነው እንዲህ ያስለቀሰህ?" አለው ሰውየውም በትካዜ "የቁርአኑ ትርጉሙ አልገባኝም፤ ያስለቀሰኝም እሱ ነው" አለው። ለስንቱ የዱንያ ሀጃ በርካታ ስራዎችንና ሳይንሶችን ለብዙ አመታት ያጠናው ጭንቅላታችን የአሏህን ቃል ግን ትርጉሙን እንኳን አለማወቁን ማሰብ እንዴት ሀዘን ይፈጥራል?
Show all...
😢 119👍 19 8
ከፈትዋ ውጭ ላሉ የንጽጽራዊ ጥያቄዎች ብቻ፦ t.me/Yahyanuhe1
Show all...
Yahya Ibnu Nuhe

👍 39 2
ቲክቶክ እንደገባሁ ፕላትፎርሙ ለአጫጭር ቪዲዮዎች የተገነባ በመሆኑ ምን መስራት እንዳለብኝ ጊዜ ሰጥቸ ማሰብ ጀመርኩ። ከመጡልኝ ሀሳቦች መካከል "ስቲሮት - ከ100 በላይ የመጽሀፍ ቅዱስ ግጭቶች" የተሰኘውን መጽሀፌን ሙሉውን በአጫጭር ቪዲዮ በማቅረብ መጽሀፉን ላላነበቡ ሰዎች አሰልቺ ባልሆነ መንገድ ማቅረብ ነበር። ሀሳቡን ካመጣሁ በኃላ በምን መቅረብ እንዳለበትም የራሴን ምልከታ ይዠ ሁሌም ወደሚተባበረኝ ግራፊክስ ዲዛይነር ወንድሜ ሄድኩ። ከዚህ በፊት እንደነበረው ነጻ ትብብር እንዲያደርግ ሳይሆን ቋሚ ስራ ስለሚሆን የማክዮቶም ቢሆን የሆነ ነገር ለአንድ ቪዲዮ እያሰብኩለት እንዲሰራልኝ ነገርኩት፥ ብዙም አላሳሰበውም፣ ሁሉኑም የዳዕዋ ስራዎቼን ከመጽሀፎቼ ኢዲት ጀምሮ ስለሚሰራልኝ አጅሩ ላይ ብቻ ትኩረት እንደሚያደርግ አቃለሁና እምቢ እንደማይለኝ በመገመት ነበር የሄድኩት፣ ተስማምተን ስራውን ጀመረው፥ ቪዲዮዎቹ በተጀመሩ ሰሞን ጥቂት ሰዎች ቪዲዮዎቹ በተለያዩ አጋጣሚዎች ከወዳጅ ዘመድ እየተላከላቸው ማግኘታቸውን እየገለጹ ቴሌግራሜን አፋላልገው እስልምና ላይ ያሉ ጥያቄዎቻቸውን ይጠይቁኝ ጀመር። ብዙዎቹ ጋ ደስ የሚል ተግባቦት ፈጠርን። ከብዙ ቀናት በኃላ ሀገራችን ካፈራቻቸው ታላላቅ ዓሊሞች መካከል አንዱ የሆኑት ሸይኽ ትምህርቶቹን በብዙ ቦታዎች እንደሚያሰራጯቸውና እንደወደዷቸው ብዙ ፍሬም እንዳመጡ ነገሩኝ። ለካ ቪዲዮዎቹ ከተሰሩ የትም ቦታ መድረስ ይችላሉ በሚል ትልቅ ሞራል ነበርና ስራውን ማስፋት እንዳለብኝ አመንኩ። ወንድማችን ጋር በመነጋገር ግጭቶቹ 100ዎቹም በአሏህ ፍቃድ ለመዳሰስ ተስማማን። በተጨማሪም የመጽሀፍ ቅዱስ የንባብ ልዩነቶችን/Textual Variants/ አስመልክቶ "የመጽሀፍ ቅዱስ መበረዝ ማሳያዎች" በሚል የተጀመረው ፕሮግራምም ይደርሳል። - የመጽሀፍ ቅዱስ ግጭቶች 35 ክፍል የደረሱ ሲሆን በቲክቶክ፣ በፌስቡክ በቴሌግራምና በዩቲዩብ ይለቀቃል - የመጽሀፍ ቅዱስ መበረዝ ማሳያዎች እስካሁን 4 ክፍል የተለቀቀ ሲሆን ከረመዷን በኃላ በአሏህ ፍቃድ በሰፊው መድረስ ይጀምራል - መጽሀፍ ቅዱስና ጥያቄዎቼ እስካሁን 5 ክፍሎች የተለቀቀ ሲሆን እንደሁኔታው እሱም በአሏህ ፍቃድ ይቀጥላል። ትምህርቶቹን ባገኛችሁት አጋጣሚ በቀናነት ለወገኖቻችን ሼር ማድረግ አትርሱ፤ የትኛው ትምህርት ለሒዳያ ሰበብ እንደሚሆናቸው አናውቅም። የኛ ኃላፊነት በታዘዝነው መልኩ ማድረስ ብቻ ነው፥ በኒያችን ልክ እንመነዳለን። አሏህ ከፈቀደ ደግሞ በዚህች ትንሽ ስራ በርካታ ሰዎችን ወደ ሒዳያ ሊመራልንም ይችላል። አሏህ ይገዘን..! 📌 ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@yahyaibnunuhe?_t=8ktCFn5kjJt&_r=1 📌 ቴሌግራም https://t.me/Yahyanuhe 📌 ፌስቡክ https://www.facebook.com/share/LUWjmvQRLtVVzsSX/?mibextid=qi2Omg 📌 ዩቲዩብ https://youtube.com/@YahyaIbnuNuhe?si=-ffuMuU8R4Dp7w85
Show all...
የሕያ ኢብኑ ኑህ on TikTok

@yahyaibnunuhe 24.8k Followers, 241 Following, 144.7k Likes - Watch awesome short videos created by የሕያ ኢብኑ ኑህ

👍 34 6
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!