#A,
#B እና
#C የሚባሉ ሶስት ሰዎች ነበሩ።
#A በግሉ ስራ የሚተዳደር ሲሆን፣
#B እና # C ግን በአንድ ሆስፒታል የሚሰሩ የህክምና ሰራተኞች ነበሩ።
#A እና
#B ከነፍሳቸው ይዋደዱ ነበር፡ ከስራ ሰዓት ውጪ ያለውን አብዛኛውን ጊዜ አብረው ነው ሚያሳልፉት።
#C ግን በእነርሱ መዋደድ ደስተኛ የማይሆን የሚቀና ጠላታቸው ነበር።
የሆነ ቀን የ#A እናት በጣም ትታመምና
#Bና #C ወደ ሚሰሩበት ሆስፒታል ትሄዳለች። የያዛት በሽታ ቀለል ያለ ወይም በቀላሉ ልትፈወስ የምትችለው አይነት ነበር፡
ነገር ግን በሃኪም ስህተት ለእሷ የማይሆን መርፌ ተወግታ ህይወቷ አለፈ።
#A እናቱ እንደሞተች የሚያውቀው በሀኪም ስህተት ሳይሆን በሽታው ከባድ ሆኖ እንደነበር ነው።
#B እና
#C ግን ነገሩን በደንብ ያውቁ ነበረ፤ ምክንያቱም ለእናትየው የተሳሰተ መርፌ የሰጠው የ#A ወዳጅ
#B ነበር።
#ይሄን_ያደረገው_ግን_ሆን_ብሎ_ሳይሆን ታማሚዋ የ#A እናት መሆኗን ሲሰማ ለጓደኛው ካለው ፍቅር የተነሳ በችኮላ ማስታገሻ የሰጣት መስሎት ሌላ መርፌ ሰጥቷት ነበር። ነገሩን
#B ይህን ስህተት ሲፈፅም
#C ካጠገቡ ነበር።
የሆነ ቀን
#A እንዲ ብሎ
#Bን ይጠይቀዋል፦ "እውነት ግን እናቴ የሞተችው በሽታው ከባድ ሆኖ ነው… ወይስ ሌላ ነገር ተፈጥሮ ነበር?"
#B ግን ህሊነው እየኮረኮረውና ነፍሰ ገዳይነት እየተሰማው "ኧረ! እኔ ነገሩን በደንብ አላወቅኩም፤ ግን የያዛት በሽታ ከባድ እንደነበር ሰምችያለው" ብሎ የውሸት መልስ መለሰለት።
ከጥቂት ቀናት በኋላ ነገሩን ያውቅ የነበረው ጓደኛቸው
#C ለ#B ፦ "ከአሁን ሰዓት ጀምሮ እኔ የምልህን የማታደርግ ከሆነ የ#Aን እናት ሆን ብለህ የገደልከው አንተ እንደሆንክ ለ#A ነግሬ ከእርሱ ጋ እንድትጣሉና እርሱም በእናቱ ፈንታ አንተን አንዲገድልህ አደርገዋለው።" ብሎ አስፈራራው።
#Bም እውነቱ እንዳይወጣ ፈርቶ በሃሳቡ ተስማማ። ከዚያ ቀን ጀምሮ የ#B ህይወት መውጣት፣ መግባት፣ መተኛት፣ መነሳት… ሁሉ ነገሩ በራሱ ፍላጎት ሳይሆን
#C እንደሚፈልገው መሆን ግድ ሆነበት። እንግዲህ የተፈጠረው ስህተት እንዳለ ሆኖ
#B ውሸት በመናገሩ ምክንያት ለ#C ባሪያ ሆኖ መኖር ጀመረ፤ ነፃነቱም በ#C ተወሰደበት።
የሆነ ቀን ግን
#B ለ#C መገዛት እየከበደው ሲመጣ፡ "ለምን ያደረኩትን ሁሉ ግልፅ አድርጌ ለ#A ነግሬ አልገላገልም?
#C እንደፈለገ ከሚያደርገኝ
#A ቢገድለኝ ይሻላል፤
#A ጨክኖ ቢገድለኝም እሞታለው፤ እኔ አሁንም ቢሆን በስጋ እየኖርኩ ነው እንጂ ለራሴ ሞቼ ለ#C ነው እኖርኩ ያለሁት፤ ምክንያቱም በህይወቴ እየሆነ ያለው እኔ የፈለኩት ሳይሆን
#C የፈለገው ነው" ብሎ አሰበ።
ከዚያ ለ#A ያለውን እውነት ለመናገር ወሰነ።
………ለA "በእናትህ ሞት በሆነው ሁሉ እኔ ነኝ ጥፋተኛው፡ ከፈለክ ግደለኝ" ብሎ የተፈጠረውን ሁሉንም ነገር፣ ከዚያ በኋላ እየኖረ ያለውንም ህይወት ነገረው።
A ይሄን ሲሰማ በጣም ደነገጠ። ነገር ግን ነገሩ በጣም ብያስደነግጠውም Bን በጣም ይወደው ስለነበርና ነገሩ በስህተት የተፈጠረ እንደሆነ ሲገባው ብዙ ካሰበ በኋላ፡ እያለቀሰ " ያለፈው ሁሉ አልፏል፣ በቃ እኔ እድሜ ልኬን ላላስበው ይቅር ብዬሃለው፤ አሁን እናቴም የለችም ያለሀኝ አንተ ብቻ ነህ፤ የድሮው ፍቅራችን በጣም ነፍቆኛል፤ እንደድሯችን እንሁን" አለው።
#B የ#A መልስ ገረመውና ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ።
እውነትን ተናገረ ከ#C ባርነትም ነፃ ወጣ። አሁን
#C_Bን እንደፈለገ የማድረግ ስልጣን የለውም። ምክንያቱም
#A እውነትን አውቋል። እውነቱም
#Bን ከጠላቱ አገዛዝ ነፃ አውጥቶታል።
👋 ውሸት በተናገርን ቁጥር ሳናውቀው ለሆነ ነገር ባሪያ መሆን እንጀምራለን።
ከአንዱ ውሸት ለመውጣት ስንል ሌላ ውሸት እየፈጠርን( አንድ ውሸት ሌላ ውሸት እየወለደ ሌላውም ውሸት ሌላ ውሸት እየወለደ ) እኛ እራሳችን ውሸት በውሸት እንሆናለን፤ ይህ የውሸት ሰንሰለት ሊቆረጥ የሚችለው መሃል ላይ እውነት የሚባል መጋዝ ሲገባበት ብቻ ነው።
እውነት እንናገር!!!!! እላችኋለው
ተባረኩ🙏
🙏🙏
https://t.me/Ewunetinamiret
🙏🙏
🙏🙏
https://t.me/Ewunetinamiret🙏🙏Show more ...