cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ወንጌል ይለዉጣል📖

ወንጌል ይለዉጣል ትምህርቶች የእግዚአብሔር ቃል የዝማሬ ግብዣ እና ሌሎችም እራሳችንን እንድናይ የሚያደርጉ ፅሁፎች የሚቀርቡበት gospel channel contact us @kalu_hayal_new @enchanted_nuha

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
201Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
ፊል18 ላይ #አለቅሳለሁ ይለናል ይህን ጨካኝ ሰው ያስለቀሰው ነገር ለመስቀሉ ጠላት የሆነው ምልልሳቸው ነው ይህም ምልልስ ለሰው ፅድቅን ሚያመጣ ሳይሆን #ሞት የሆነ መጨረሻ ስላለው ነው።19 አንድ አባባል አለ "ለመኖር ስትል ብላ እንጂ ለመብላት ስትል አትኑር" ሚል ሆዳችን ጌታ ከሆነ ለሱ እንገዛለን በጣም ሚከብደው ቃል እዚህ ክፍል ላይ "ክብራቸው በነውራቸው ነው" ሚለው ነው ዛሬ ላይ እንደ ክብር የያዝነው ነገር ምንድነው እግዚአብሔር ነውር ያለው እኛ ግን ክብራችንን አውልቀን ክብር ያረግነው ነገር ምንድነው መፀሐፍ ሮሜ 8:33 ላይ"የሚያፀድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኮንንስ ማነው?"ይላል ስለዚህ እግዚአብሔር የኮነነውን ነገር ክብራችን ሊሆን ይገባልን እንደ እነዚህ ያሉትን ሰዎች "አሳባቸው ምድራዊ ነው" ይላቸዋል ከምድር ያላለፈ ሰው ደግሞ የሰማዩን ክብር አያይም እግዚአብሔር ያለው ይሁን ለማለት ለእርሱ ፈቃድ የተገዛን ሰዎች መሆን ይገባናል እግዚአብሔርን ለሚወዱ እንዳሳቡም ለተጠሩ ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ ይላል ፍቅራችን ሚታየው በአክብሮታችን ነው የዛኔ ታማኝ ከሆነው ጌታ የእምነታችንን ፍሬ እንቀበላለን ስለዚህ ለክርስቶስ ሕይወት እንጨክን!
Show all...
ገላ 5 ላይ "ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በስጋ ላይ ይመኛልና፥ እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ፣ ስለዚህም #የምትወዱትን.ልታደርጉ.አትችሉም።" ይላል መንፈስ እንዲበረታ ብረት አናነሳም 2ቆሮ 3"መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን" ይላል የክርስቶስን መልክ ለመምሰል መንፈስ በሆነው ጌታ መንፈሳችንን ልናበረታ ይገባል የዛኔ የምንወደውን የጌታን ሀሳብ እናደርጋለን የእግዚአብሔር ሀሳብ ደግሞ ፍፁምን ደስ የሚያሰኝ ነው ምክንያቱም ነገርን በጊዜው ውብ አርጎ ስለሚሰራ…
Show all...
በዘመንክ አንድ ነገር ፈፅሞ አጥብቀህ ያዝ እሱም ክርስቶስን። እሱ የሌለበት ስኬት ተድላ ፌሽታ ሁሉ ከንቱ ነው። ጳውሎስ በፊልጲ 3፥9 ላይ [[በእርሱ እገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጉድፍ እቆጥራለው፤]] ይላል ለምን ስንለው 10-11 [[ .እርሱንና .የትንሳኤውን.ኃይል እንዳውቅ #በመከራውም.እንድካፈል ፥ ወደ #ሙታንም.ትንሳኤ.ልደርስ ቢሆንልኝ #በሞቱ .እንድመስለዉ እመኛለሁ።]] ስለ እኛ ደግሞ አንድ ፍርሃቱን እያለቀሰ ይመክረናል 18[[ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶቹ ሆነው ይመላለሳሉና]] 19[[መጨረሻው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው።]] ይለናል ጳውሎስ ብዙ የሚመካበት ነበረው ብዙ ለኑሮዉ ለስጋው ሚመች ነገር ነበረው ስለ ድህነቱ ሲል ግን ሁሉን እንደ ረብ እንደ ከንቱ እንደ ቆሻሻ ቆጠረው ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶች ሆነው ይመላለሳሉ ይለናል ምክንያቱም መሰቀል አልፈለጉም በሞቱ አልመሰሉትም ስጋቸውን አልሰቀሉም ስለዛም ነው ከትንሳኤዉ ማይካፈሉት የሰው ሆዱ አምላኩ ሊሆን አይገባም ምክንያቱም ስጋ አይጠግብም ሁሌም አምጣ ሁሌም ለኔ ነው ሚለው …
Show all...
እንግዲህ ጳውሎስ በዚህ መፀሐፍ <<ፍለጋ የሌለውን የክርስቶስን ባለ ጠግነት>> ውረሱ እያለን ነው ኤፌ3፥8 ኤፌሶን 1፥3 [[[3 በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።]]] ስለዚህ ባለጠግነት ከማውራታችን በፊት ስለ በረከቱ ምንነት ማወቅ ያስፈልጋል 👇 ይህ ባለጠግነት እንደዘመኑ የብልፅግና ሰባኪያን ምድር ምድሩን የሚያስናፍቅ ገንዘብ ገንዘብ ሚሸት አይደለም ክብር ዝና ሀብት አያስናፍቅም አንዳንድ ሰዎች መንፈሳዊነት የሚመስል ምኞት አላቸው አትመኝ የሚለውን ቀይረውት <<ሀይልን በሚሰጠኝ>> በሚመስል ጥቅሳዊ ምኞት ውስጥ ተጠምደዋል ይሄ ኃጢአት ነው ምክንያቱም ጥረን ግረን እንድንበላ እና እንድናገኝ ታዘናል <<ሊሰራ የማይወድ አይብላ>> ነው ቃሉ 2 ተሰ 3፥8-10 እዚህ ጋር ዋናው መርሳት የሌለብን ነገር እግዚአብሔር የእጃችንን የጉልበታችንን ፍሬ እንደሚባርክ ነው የሰማዮ አባታችን በረከት አያልቅበትም ምክንያቱም እርሱ ባለጠጋ ነው እየሰጠ ይሞላለታል ስለዚህ በምድርም መቶ እጥር እናፈራለን ማለት ነው በበረከቱ ይባርከናል ነገር ግን ጳውሎስ በዚህ መልእክት ሊነግረን የፈለገው ስለዚህ በረከት ሳይሆን ስለ <<መንፈሳዊ በረከት>> ነው። በዚህ ውስጥ 1 በማን 2 የት 3 በምን ያህል 4 ማን የሚሉትን ሃሳብ እናያለን 5ምስጋና ((1)) በማን <<በክርስቶስ>> በማለቱ ይህ በረከት በክርስቶስ በኩል የሚገኝ መሆኑን ያስረዳል ፡ አማኝ በክርስቶስ ያመነ እለት የእግዚአብሔር መንግስት መራሽ ሆኗል በክርስቶስ ያመንን እለት አብ በልጁ አበልፅጎናል ((2)) የት <<በሰማያዊ ስፍራ>> ክርስቲያን ዜግነቱም ሀገሩም ተስፋውም አባቱም ልቡም በሰማይ ነው ለዛም ነው ሀብትን በሰማይ እንድናከማች መ.ቅ ሚነግረን ስለዚህ አምላካችንም በሰማያዊ በረከት በክርስቶስ አበልፅጎናል ((3)) <<በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ>> ሁሉ የሚለው ቃል የሚቀር ነገር እንደሌለ ያሳያል ይህ በረከት መንፈሳዊ ዓለም ውስጥ ያሉትን በረከቶች ሁሉ ይዟል እዚህ ላይ ገላ 5:22 ላይ ያሉትን የመንፈስ ፍሬዎች እና የፀጋ ስጦታዎች ማንሳት ተገቢ ነው ይነበብ👇 ዕብ 2፥4 ሮሜ 12፥6-8 1ጴጥ 4፥10-11 1ተሰ 5፥19-22 1ቆሮ 12፥4-11 : 28-31 ፤ 13፥1-3 ፤ 14፥16-40። ከምንም በላይ እግዚአብሔር በክርስቶስ ድነትን ሰቶናል በመዳናችን ደግሞ የመንፈስ ቅዱስን ማደሪያዎች ሆነናል በመሰረቱ ክርስቲያን የሁለት ዓለም ሰው ነው በምድር እያለ በሰማይም የሚኖር ነው <<ከክርስቶስ ጋር አስቀመጠን>> ስለሚል 🤔እስኪ ሰማይ ላይ ያለውን አለም 1min ጨፍነን እናስበው የበጉ ዙፋን፡ አምልኮት፡ አክሊል፡ መላዕክት፡ ቅዱሳን፡ በጉ ብርሃን የሆነበት ክርስቶስን ምናይበት የመንግስተ ሰማይ ዉበትና አኗኗር … እናስበው እስኪ ያልወረስነው ምናለ… ((4)) ማን የሚለውን ስናይ የበረከታችን ምንጭ ምን እንደሆነ ይነግረናል <<የጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት>> ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍፁም ሰው እና ፍፁም አምላክ ነው በዚህም በፍፁም ሰውነቱ እግዚአብሔር አምላኩ ነው ፡ በፍፁም አምላክነቱ ደግሞ እግዚአብሔር አባቱ ነው ። ስለዚህ የበረከታችን ምንጭ አባታችን ነው ልጅነትንም ያገኘነው በክርስቶስ ነው፡ አንድ አባት ለልጁ ማያወርሰው ነገር የለም ከሚጎዳው ነገር ውጪ ሁሉ ለልጁ ነው እንግዲህ አባታችን ያለውን እንይ ((5)) ምስጋና ሐዋርያው ይባረክ እያለ እግዚአብሔርን ሲያመሰግን እናያለን የማመስገናችንም ምክንያት <<በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ>> ስለመባረካችን ነው። አንድ ጠቅላይ ሚኒስተር ወንበሩ ላይ ተቀምጦ አይኖርም ስራውን ሁሉ ይሰራል ነገር ግን እሱ ከወንበሩ ላይ ስለተነሳ ስልጣኑን አያጣም የትም አገር ቢሄድ ያ ወንበር የሱ እንደሆነ እርግጥ ነው እኛም በምድር ላይ በተለያየ ሁኔታ ልንኖር እንችላለን አንድ ግን እርግጠኛ ምንሆንበት ነገር ከልጅነት ስልጣናችን ማንም እንደማይነቀንቀን ነው ምድር ላይ እያለን ሰማይ ላይ ስላለው ሕይወታችንና ቦታችን እርግጠኞች ነን ምክንያቱም ከአባታችን የበረከት ባለጠግነት ሁሉ ተካፋዩች ስለሆንን ስለዚህ ስለ መንፈሳዊ በረከቶች ስለ መንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ሁሉ አመስጋኞች መሆን አለብን አመስጋኝ ብቻ ሳይሆን እንደ ደሀ ሳይሆን እንደ ባለጠጋም አኖር አለብን እርሱን በይቀን ማንቀበለው አለቀብኝ ምንባለው ነገር የለም ምንድነው የነፍሳችን መሻት መዘመር ነው እሱን እንጠይቅ መስበክ ነው መፀለይ ነው ትንቢት ነው አጋንንት ማስወጣት ነው… በምድርስ ምንድነው ሰርተን ያልሆነልን የሁሉም ጥያቄ መልስ አንድ ነው አምላክና አባት የሆነውን እግዚአብሔርን በክርስቶስ መጠየቅ የዛኔ ከባለጠግነቱ ያጠግበናል 🙏God bless You 🙌 እንግዲህ እንደ ባለጠጋ እንኑር
Show all...
ኤፌሶን ምዕራፍ 1 [[1 በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፥ በኤፌሶን ላሉት ቅዱሳን በክርስቶስ ኢየሱስም ላሉት ምእመናን፤]] be ቁ 1lay ሐዋርያው በማን ፈቃድ የማን ሐዋርያ እንደሆነ ይናገራል ጳውሎስ እንደ ሌሎቹ ሐዋርያት ሹመቱን ከሌሎች እጅ አልተቀበለም ወንጌልንም ከሰዎች አልተሰበከም ሐዋ9 lay ክርስቶስ ተገልጦለት ነው ወደዚህ ጥሪ የገባው ይህም አስቦበት ሳይሆን የእግዚአብሔር እቅድና ፈቃድ ነበር ምክንያቱም እሱ የአሕዛብ ሐዋርያና ፀረ ክርስቲያን ወሪ የነበረ ሰው ነበር ነገር ግን የእ/ር ፈቃድ የክርስቶስ ሐዋርያነት ስለነበር ተቀይሯል ምንም ያህል አሳዳጅ ቢሆንም ከእ/ር እቅድ ማምለጥ አይቻልም ፥ <<የኢየሱስ ክርስቶስ>> በማለቱም የክርስቶስ ሰራተኛ መሆኑን ያሳያል ሌላው የሚፅፍላቸውን ሰዎች <<ቅዱሳን>> ይላቸዋል እኚ ሰዎች የመጀመሪያ ታሪካቸው ሲታይ አሕዛብ የነበሩና ጣኦት የሚያመልኩ ሰዎች ነበሩ በዛም ብዙ የዝሙት ስራ ይደረግ ነበር በከባድ ተፅእኖ ውስጥ የነበሩና ከዛም በስተጀርባ ክፉ ኃይላት እንደነበሩ መፀሐፍ ይናገራል (1፥19-20 ፤ 2፥1-2 ፤ 3፥10 & 6፥11-12) ታዲያ እነዚህ ሰዎች ቅዱሳን የሆኑት እንዴት ነው ስንል ቀደም ሲል የስጋቸውን እና የልቦናቸውን ፈቃድ የሚያደርጉ የነበሩ በበደላቸው የሞት ፍርድ የተገባቸው ነበሩ ነገር ግን በክርስቶስ በማመን የእግዚአብሔርን ምህረት የተቀበሉ ከስጋም ስራ ያመለጡ ሆነዋል ፤ በቀደመው ሥርዓት ቅዱስ የሚለው ስም ለሰዎች የሚሰጣቸው በሃይማኖት ተቋማት ሲሆን ቃሉም የሚፈታው <<ቅዱስ በሆነ ሕይወት ይፋዊ እውቅና ያገኘ>> በሚለው ሃሳብ ነበር ፡ የሞተ ሰውም እንደዛ ለመባል ያሰው በባህሪው እና በአኗኗሩ ነቀፋ የሌለበት ቢያንስ 2ተአምራትን ያደረገ መሆን ነበረበት ። ታዲያ እነዚህ ሰዎች ቅዱሳን የሆኑት እንዴት ነው ካልን በባሕሪም ይሁን በአኗኗር (ሐዋ 19) ፈፅሞ ተቃራኒዎች የነበሩ ቢሆንም ግን የቀደመው ህይወታቸዉ አሁን ላለው ህይወታቸዉ ምስክር ሊሆን አይችልም ምክንያቱም የተለያየ ዓለም ዉስጥ ነበሩ ያኛው አለም የኃጢኃት ዓለም ሲሆን ይሄኛዉ ደግሞ የፅድቅ ዓለም ነው <<ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው አሮጌው ሁሉ አልፏል>> ያረጀ እና የተናቀ ያለፈ ሕይወታቸው ነበር ያኛው ዛሬ ላይ በክርስቶስ ስራ በማመን ቅዱሳን ሆነዋል ላለፈው ሕይወት የሞቱና በአዲስ ሕይወት የተነሱ ሆነዋል ቅዱስ ለመባልም ነውር በሌለው የህይወት ኃይል ተነስተዋል ስለዚህ ኩነኔ የለባቸውም ፤ ሌላው <<በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት>> የሚለው ቃል እነዚህ ሰዎች አሁን ላይ በዓለም ስርዓት የሚኖሩ ሳይሆኑ በክርስቶስ የሕይወት ዓለም ውስጥ መሆናቸውን እና በክርስቶስ ማመናቸዉን ያስረዳል <<ቅዱስ>> <<የተለየ>>። <<ምእመናን>> ወይም ሌላ ትርጉሙ <<የታመኑ>> በክርስቶስ ኢየሱስ ያሉትን የሚያመለክት ነው ሰዎቹ የዳኑት ታማኞች ስለሆኑ ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ስላመኑ እና ስለዳኑ ነው። [[2 ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።]] ከአባታችን እ/ር ከጌታም ኢየሱስ <<ፀጋ>> የግሪክ ሰላምታ <<ሰላም>> የአይሁድ ሰላምታ ነው፤ በኤፌሶን መፀሐፍ ጳውሎስ 12 ጊዜ ፀጋ የሚል ቃል ጠቅሷል <<ፀጋ>> <<ለማይገባቸው ሰዎች እግዚአብሔር ያሳየውን ቸርነት>> ያሳያል <<ሰላም>> ከእ/ር የሚገኝ የመንፈስ እረፍትና መረጋጋት ነው። ቁ፫ <በረከት> ይቀጥላል
Show all...
አለመደሰት አልችልም። እውነተኛ ደስታ ከውስጥ ወደ ውጭ የሚፈስ ነው፡፡ ከመንፈሳችን ይነሳና ነፍሳችንን አጥለቅልቆ ወደ ውጭ ይወጣል( ፊታችን የፈካ እንዲሆን ያደርጋል):: የእውነተኛ ደስታ መነሻ ስፍራው አካባቢ አይደለም፡፡ ብዙ ሰዎች ይጠይቁኛል፤ "አስቸጋሪ ሁኔታዎችና ማይመች አካባቢ ውስጥ ሆነህ እንኳ ምትደሰትበት ሚስጥሩ ምንድነው?" ይሉኛል፡፡ መልሴ፡ "የደስታዬ ምንጭ( source) አካባቢዬና ሁኔታዎቼ አይደሉም" የሚል ነው፡፡ ጳውሎስ፡ የፊልጵስዩስ ክርስቲያኖችን "# ሁልጊዜ # በጌታ ደስ ይበላችሁ" ነው ያለው፡፡ የሚገርመው፡ ጳውሎስ ይሄን መልዕክት የተናገረው እስር ቤት ውስጥ ሆኖ ነው፡፡ ሰው፡ እስር ቤት ውስጥ ሆኖ እንዴት "#ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ" ሊል ይችላል? ...አዎን፡ ይቻላል! እውነተኛ ደስታ ከውስጥ-ወደውጭ( Inside-out) ነው የእኔ ደስታ የተመሰረተው ከውስጥ ወደ ውጭ እንጂ ከውጭ ወደ ውስጥ አይደለም። በአመት 365 ቀን 12 ወር 8760 ሰአት 525600 ደቅቃ 31536000 ሰከንድ 892160000 ማይክሮ ሰከንድ ደስተኛ ብቻ ነኝ አለመደሰት አልችልም ።
Show all...
በአፍጋኒስታን ነገ ከሰዓት በኋላ የሞት ፍርድ ለተፈረደባቸው 229 ክርስቲያን ሚስዮናውያን ጸልዩ ሊጎዱ ነው ብዙ ሰዎች መጸለይ እንዲችሉ እባክዎን ይህንን መልእክት በተቻለ ፍጥነት ያስተላልፉ። ይህ መልእክት የተላከው በጁዲት ካርሞና ሚስዮናዊው በአፍሪካ ከሚገኘው ከቺዋዋዋ ነው። መላው ፕላኔት በጸሎት አንድ ሆነ። እርስዎ ማስተላለፍ ከቻሉ እባክዎን በአፋጣኝ ጸሎት እኛን ይቀላቀሉ ፣ ምክንያቱም አክራሪ እስላማዊ ቡድኑ በኢራቅ ውስጥ ትልቁን የክርስቲያን ከተማ ኳራጎሽን ሰለተቆጣጠሩት አሁን በመቶዎች የሚቆጠሩ ክርስቲያን ወንዶች ፣ ሴቶች እና ልጆች ሊገደሉ ባሉበት ሰአት የጸሎት ሽፋን እየተጠየቀ ነው። እባክዎን አንድ ደቂቃ ወስደው ጸልዩላቸው። ለሚችሉት ሁሉ መልዕክቱን ያስተላልፉ። ኳራጎሽ ቀድሞውኑ ብዙ ጊዜ ተወስዷል። ፀሎት ጠይቀውናል እባክዎን ለሌሎች ያስተላልፉ።
Show all...
. ክርስቲያን ነኝ በረከት ተስፋዬ || Gospel Song sʜᴀʀᴇ◈📲JOIN📲◈sʜᴀʀᴇ 🔰ኢየሱስ እንደቃሉ ይመጣል sʜᴀʀᴇ◈📲JOIN📲◈sʜᴀʀᴇ 💡 𝑱𝑶𝑰𝑵 @jesusfollowing ⚠️ 🗣 መዝሙር ለመላክ ✉ @ushisha 😐
Show all...
. የመጨረሻ ቃልኪዳን ንጉሴ || New song ⏰9:26Min 📥26.6MB 🔰ወንጌል ክርስቶስ ነው🔰 Share 📲 Share 📲 Share 💡 𝑱𝑶𝑰𝑵 @jesusfollowing ⚠️ 🗣 መዝሙር ለመላክ ✉ @ushisha 😐
Show all...
. የመጨረሻ ቃልኪዳን ንጉሴ || New song ⏰-9:26Min📥-5.4MB
Show all...
Micah Tyler lyric >>different I don't wanna hear anymore, Teach me to listen I don't wanna see anymore, Give me a vision That you could move this heart To be set apart I don't need to recognize, The man and the mirror And I don't wanna trade your plan, For something familiar I can't waste a day I can't stay the same I wanna be different I wanna be changed 'Til all of me is gone And all that remains Is a fire so bright The whole world can see That there's something different So came and be different In me And I don't wanna spend my life, Stuck in a pattern And I don't wanna gain this world But lose what matters So I am giving up, Everything because... I wanna be different I wanna be changed 'Til all of me is gone And all that remains Is a fire so bright The whole world can see That there's something different So came and be different, Oh I know that I am far, from perfect Through you, the cross still says I'm worth it So take this beating in my heart and Come and finish what you started When they see me, let them see you 'Couse I just wanna be different,yeah I wanna be different I wanna be changed 'Til all of me is gone And all that remains Oh is fire so bright The whole world can see That there's something different So came and be different I just wanna be different So could you be different In Me join us🤳 👇👇👇👇👇 👉@kalu_hayal_new 👉@kalu_hayal_new
Show all...
💃💃💃💃💃💃💃💃💃 የማያሸልሙ 7 የሩጫ ዓይነቶች 💃💃💃💃💃💃💃💃💃 ከክፍል ሰባት የቀጠለ........ 🍎ስለ ፍቅር ሲነሳ ብዙ ነገሮችን መዳሰስ ይቻላል ነገር ግን ከዚህ ትምህርት አንፃር የመጨረሻውን ሀሳቤን እንካዋቹ ልበልና ሀሳቤን በመልካም ላሳርገው፦፦፦፦፦፦፦ 🍏 በክርስትናው አለም ውስጥ በትራኩ ላይ ስለሮጥን ብቻ ተሸላሚዎች እንሆናለን ማለት አይደለም።ሩጫው በፍቅር መሮጥን ይጠይቃል።ብዙዎቻችን መሮጣችን ላይ እንጂ በፍቅር መሮጣችን ላይ ብዙ ጊዜ ትኩረት ስናደርግ አንታይም። 🍊ፍቅር የህግ ሁሉ አራት ነጥብ እንደሆነ ቅዱስ ቃሉ በተለመደው ትህትናዊ ቃላቱ በተለያዩ ስፍራዎች ላይ አስፍሮልን ይገኛል።ለምሳሌ(ማቴ 22:36-40) 🍐ሐዋሪያው ጳውሎስ የፍቅርን ትርጉም በ1ጢሞ 1:5 ላይ የገለፀበት መንገድ በቀላሉ ለመረዳት የሚቀል ሆኖ አጊኝቼዋለው፦፦፦፦፦ ፍቅር በዋናነት ሶስት ነገሮችን በውስጡ እንዳቀፈ ክፍሉ ያሳብቀናል፦፦፦፦፦፦ 1)ንፁህ ልብ፦ይሄ ማለት 🍦ከክፋት ያልተዳቀለ ልብ 🍉በሌሎች ስኬት የማይቀና ልብ 🍒የክርስቶስን መስቀል የሚተነፍስ ልብ ወዘተ.. 2)በጎ ህሊና፦በጎ ህሊና ማለት በክፉ መረብ ያጠመደንን ሰው ከወጥመዱ ካመለጥን ማግስት መልሰን ገንዘባችን ለማድረግ የምንወስደው አዎንታዊ እርምጃ ማለት ነው። 3)ግብዝነት የሌለበት እምነት፦፦ ግብዝነት ማለት በማስመሰል ማንነት የተከፈነ ትወናዊ ህይወት ማለት ነው ግብዝነት የሌለበት እምነት ሲል ትወናዊ ያልሆነና በእውነተኛ ማንነት የተገለጠ እምነት ለማለት ፈልጎ ነው 🍍🍍🍍በአጠቃላይ ከዚህ ክፍል አንፃር ፍቅር ማለት ንፁህ ልብ በጎ ህሊናና ግብዝነት የሌለበት እምነት ማለት ነው። ተወዳጆቼ ሆይ ቀሪውን ዘመናችንን በፍቅር በመሮጥ ለታላቁ ሽልማት በክብር እንድረስ እላለው። እወዳችኋለው by biruk mohammed
Show all...
💃💃💃💃💃💃💃💃💃 የማያሸልሙ 7 የሩጫ ዓይነቶች 💃💃💃💃💃💃💃💃💃 የመጨረሻው ክፍል ሰባት 💃💃💃💃💃💃💃💃💃 እጅግ በጣም የምወዳችሁ የአባቴ ብሩካኖች በቅድሚያ ሰላምታዬ ይድረሳቹ እያልኩኝ በመቀጠል ደግሞ የመጨረሻውን ክፍል ወደ ማካፈሉ መንደር እዘልቃለው። ✍"በፍቅር አለመሮጥ አያሸልምም" ❤ስለ ፍቅር ጉዳይ ሲነሳ አለማችን ብዙ ዓይነት መረዳቶችን አንግታ እንደምትንቀሳቀስ ይታወቃል።ከሁሉም በላይ ግን መፅሀፍ ቅዱሳችን ፍቅርን በተመለከተ የሚሰጠን መረጃ በትልቁ ውሀ የሚያነሳ ነው። ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤ ፍቅርን ከመፅሀፍ ቅዱስ አንፃር ከማየታችን በፊት በግሪኩ በስንት እንደሚከፈል እንመልከት፦፦፦፦፦ ❤️ ፍቅር በግሪኩ በ8 ይከፈላል❤️ 1)ፊልያ፦የወንድማማች ፍቅር 2)ኢሮስ፦የእጮኝነት ፍቅር 3)ስቶርጅ፦የቤተሰብ ፍቅር 4)ሉዳስ፦ለአካለ መጠን ባልደረሱ ወንድና ሴት መሀል የሚፈጠር ፍቅር 5)ፕራግማ፦በባልና በሚስት መሀል ብቻ ያለ ፍቅር 6)ፊላሺያ፦ራስን መውደድ(አዎንታዊና አሉታዊ ገፅታ ያለው ነው 7)ፓትሮቲዝም፦የሀገር ፍቅር 8)አጋፔ፦የእግዚሀብሔር ፍቅር ✍✍✍ከእነዚህ የፍቅር አይነቶች መካከል እኛ አማኞች እንዲሁ የተካፈልነው የእግዚሀብሔርን ፍቅር ነው ✍✍✍የተካፈልነው የእግዚሀብሔር ፍቅር ቢያንስ ቢያንስ ሶስት ነገሮች ላይ የተመሰረተ ነው፦፦፦፦፦፦፦ A)በጥልቅ መስዕዋትነት ላይ B)እንካ በእንካ ባልሆነ መሠረት ላይ እና C)ከፍርድ ይልቅ ወደ ምህረት በኩል ባዘነበለ መሠረት ላይ የተመሰረተ ፍቅር ነው። ይቀጥላል............................. አደራ በትዕግስት ጠብቁኝ እወዳችኋለው by biruk mohammed
Show all...
💃💃💃💃💃💃💃💃💃 የማያሸልሙ 7 የሩጫ ዓይነቶች 💃💃💃💃💃💃💃💃 ክፍል ስድስት 💃 💃💃💃💃💃 ፨ወንድምን ጠልፎ መሮጥ አያሸልምም ✍ተወዳጆቼ ከዚህ በፊት አምስቱን የማያሸልሙ የሩጫ ዓይነቶች ለመዳሰስ ሞክረናል ለማስታወስ ያህልም፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦ 👉ግብን እያዩ አለመሮጥ አያሸልምም 👉የሩጫውን መርህ ሳያከብሩ መሮጥ አያሸልምም 👉ሩጫውን አቋርጦ መውጣት አያሸልምም 👉በበቂ ዝግጅት ያልታገዘ ሩጫ አያሸልምም 👉በልብ አለመሮጥ አያሸልምም ✍ዛሬ ደግሞ ስድስተኛውን የማያሸልም የሩጫ ዓይነት በጥቂቱ ለመዳሰስ እንሞክራለን """ወንድምን ጠልፎ መሮጥ አያሸልምም"" ፨የሚገርመው ወንድምን ጠልፎ በመጣል ቀዳሚ ሆኖ መገኘት አለብኝ የሚልን እኩይ ቢሂል አንግተው የሚንቀሳቀሱ ሰዎች በተለይ በዚህ ዘመን እንደ አሸዋ ለመቁጠር እስኪያዳግት ድረስ በዝተዋል። ✍እነዚህ ሰዎች 👉ከወንድማቸው መዘግየት ውስጥ ፍጥነታቸውን ለማምረት የሚፈልጉ፥ 👉ከወንድማቸው ሀዘን ውስጥ ደስታን ናፋቂዎች እና በተጨማሪም ደግሞ፦፦፦፦፦፦፦፦ 👉ከወንድማቸው ኪሳራ ውስጥ ትርፋቸውን ለመገብየት በማሰብ ዘምቢል ይዘው የሚንቀሳቀሱ ሰዎች ናቸው። ✍ተወዳጆቼ ሆይ እናስተውል ወንድማችንን ጠልፎ በመሮጥ የምናገኘው የትኛውም ሽልማት እንደ እግዚሀብሔር ቃል ከተመለከትነው ልክ እንደ መርዘኛው እንቦጭ ነው። ለዓይናችን ልምላሜ መስሎ እየታየን ቀስ በቀስ ግን ሁለንተናችንን እየገደለ የሚጓዝ በቀላሉ ተዛማች የሆነ ገዳይ መርዝ ነው። ✍(((((ፊል 2:3-4)))))) ✍✍✍✍✍✍በዚህ ክፍል ላይ ከባልንጀሮቻችን ጋር በትህትና አቆጣጠር መሮጥ እንደሚገባን ይነግረናል ፨ሶስት ነገሮችን በትህትና እየቆጠርን አብረናቸው እንሩጥ ይለናል 1)ባልንጀራዬ ከእኔ እንደሚሻል መቁጠር 2)ለባልንጀራዬ የሚጠቅመውን ነገር ሁሉ ልክ እንደ እኔ ማግኘት እንደሚገባው በአስተሳሰብ መቁጠርና 3)በከንቱ ውዳሴን ለማግኘት አስቦ አንዳች ነገር አለማድረግን በመቁጠር እንድንሮጥ ያበረታታናል።ከዚሁ ጋር አያይዘንም ትህትናን ከዚህ ክፍል ዐውድ አንፃር እንደዚህ መረዳት እንችላለን። 👉ተባብረን ተጋግዘን እንሩጥ 👉የመጨረሻውን ክፍል እባኮዎን በትዕግስት መስመር ላይ ይጠብቁኝ እወዳችዋለው by biruk mohammed
Show all...
💃💃💃💃💃💃💃💃💃 የማያሸልሙ 7 የሩጫ ዓይነቶች 💃💃💃💃💃💃💃💃💃 ከክፍል አምስት የቀጠለ..... ፨፨በሐጌ 1:5፤7)ላይ "ልባችሁን በመንገዳቹ ላይ አድርጉ"የሚል ቃል አለ ይሄ ቃል ላነሳውት የክፍል አምስት ርዕስ ከፍተኛውን የማብራራት ሚና የመጫወት አቅም አለው ✍ በሐጌ ዘመን የነበሩ ሰዎች የእግዚሀብሔርን ቤት መስራት ችላ ብለው የራሳቸውን ቤት በትጋት በመስራት ተጠምደው ነበር። ፨፨ጊዜው የእግዚሀብሔርን ሳይሆን የእኛን ስራ የምንሰራበት ነው በሚል እኩይ አስተሳሰብ ተቀንብረው ይነዋልሉ ነበር ከዚህ የተነሳ እግዚሀብሔር በነብዩ በሐጌ በኩል ህዝቤ ከመንገዱ ላይ ልቡን አንስቶ ትላንት በመልካም ያስጀመርኩትን ሠናይ ሩጫ እንደአጀማመሩ በልቡ መሮጥ ትቶ በእግሩ በመሮጥ ላይ ይገኛል እናም በዚሁ ከቀጠሉ መጨረሻቸው ስለማያምር አሁኑኑ ልባቸውን በመንገዳቸው ላይ እንዲያደርጉና በልባቸውም መሮጥ እንዲጀምሩ አሳስብልኝ በማለት አጣዳፊ መልዕክትን እንዲያስተላልፍ ይቀሰቅሰዋል ✍✍የሚገርመው እነዚህ ተደራሲያን በልባቸው ባለመሮጣቸው ምክንያት የሚሰሩት ሁሉ በኪሳራ ምች ተመቶባቸው ነበር 👉ይበላሉ አይጠግቡም 👉ይጠጣሉ አይረኩም 👉ይለብሳሉ አይሞቃቸውም 👉ደሞዛቸውን ይቀበላሉ በቀዳዳ ኪስ ይጨምራሉ 👉ይዘራሉ ምድር አትተባበራቸውም ነበር የዚህ ሁሉ ምክንያቱ ደግሞ በልባቸው ሳይሆን በእግራቸው በመሮጣቸው ነው ✍✍በልባችን በመሮጥ የእግዚሀብሔር ቤት እንስራ ፨፨ልባችንን በመንገዳችን ላይ እናድርግ ፨፨በእግራችን ሳይሆን በልባችን እንሩጥ እላለው ክፍል 6 ይቀጥላል እወዳችዋለው by biruk mohammed
Show all...
💃💃💃💃💃💃💃💃💃 የማያሸልሙ 7 የሩጫ ዓይነቶች 💃💃💃💃💃💃💃💃💃 ከክፍል አምስት የቀጠለ........ ፨ምክንያቱም ከሰማይ ለመጣላቸው ነፍሳችሁን አድኑ ወደ ኋላ እንዳትዞሩ ለሚለው ጥሪ(ድምፅ) የሰጠችው መንቻካ ምላሽ የነበራትን የወረደ መረዳት ያሳብቅባት ስለነበረ ነው። ✍✍በወቅቱ እግዚሀብሔር በሰዶምና ገሞራ ሰዎች የስርዓት አልበኝነት ኑሮ በእጅጉን በመበሳጨቱ ምክንያት በምድሪቱ ላይ የእሳትን ዲን ለማዝነብ በዝግጅት ላይ ነበረ ግን ደግሞ ከላይ በዘረዘርኳቸው ሶስት ነጥቦች ምክንያት እግዚሀብሔር ለሀጢያተኛው የመጣው ዱላ ፃድቁንም እንዳያገኘው በማሰብ በፍጥነት ከከተማዋ ሎጥና ቤተሰቡ እንዲያመልጡ በመልዕክተኞቹ በኩል እቤቱ ድረስ በመሄድ ሹክ ለማለት ግድ ሆነበት ✍✍ሎጥም ለመጣለት የራስህን አድን ጥሪ በፍጥነት አዎንታዊ ምላሽ መስጠት ጀመረ ፨ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዘው የሩጫው ትራክ ላይ በመገኘት ሩጫቸውን በመልካም ጀመሩ ✍✍የሚገርመው ደሞ ይሄኛው የሩጫ ዓይነት በእግር ሳይሆን በልብ የሚሮጥ ሩጫ ነበር የሎጥ ሚስት ግን የተወሰነ ርቀት ለዚህ መርህ ተገዢ ሆና መሮጥ ብትችልም ከተወሰነ ጉዞ በኋላ ግን ከሩጫው ለማፈንገጥ ስትንደረደር ተገኘች ፨፨እንዳሰበችውም ልቧን ለሰዶምና ገሞራ እግሯን ደሞ ለመጣላቸው ሰማያዊ ድምፅ ለማከራየት ሞከረች ሙከራዋም የአውልትነትን ዕጣ ፈንታ ወሰነላት ✍✍ሩጫውንም ሳትጨርስ ከሁለቱምም መሆን ሳትችል ምድረበዳ ላይ ቅጥር ያልተቀጠረለትና ጥበቃ የሌለው አውልት ሆና ቀረች ✍ሎጥና ልጆቹ ግን የተሰጣቸውን የራስህን አድን ጥሪ ይዘው ሩጫቸውን በእግራቸው ሳይሆን በልባቸው በመሮጥ በድል አጠናቀቁ ፨፨ውዶቼ በልብ የማይደረግ ሩጫ እንደማያሸልም ከሎጥ ሚስት እንማር ፨**የእግዚሀብሔርን ሩጫ በልባችን እንሩጥ እርሱም ኢየሱስ ነው** የዚህን ቀጣይ ክፍል ቀጥዬ አቀርባለው እባኮዎን መስመር ላይ ይጠብቁኝ ............ እወዳችዋለው by biruk mohammed
Show all...
💃💃💃💃💃💃💃💃💃 የማያሸልሙ 7 የሩጫ ዓይነቶች 💃💃💃💃💃💃💃💃💃 ክፍል አምስት 💃💃💃💃💃💃 ፨"በልብ አለመሮጥ አያሸልምም" ፨ለዚህ ሀሳቤ መነሻ የሚሆኑኝ የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍሎች ብዙ ቢሆኑም ነገር ግን ላነሳውት ሀሳብ ድጋፍ የሚሰጡልኝን ጥቂት ክፍሎች ብቻ ጠቆም ማድረግ እፈልጋለው ፨(ዘፍ 19)የሎጥ ሚስታ ታሪክ ፨(ከግብፅ የወጡ)እስራኤላውያን ፨ት/ሐጌ 1:5፤1:7) ✍✍በመፅሀፍ ቅዱሳችን ውስጥ ከተካተቱ አሳዛኝ ታሪኮች አንዱ የሎጥ ሚስት ታሪክ ነው ፨የሎጥ ቤተሰብ በሰዶምና ገሞራ ላይ ከመጣው መለኮታዊ ጥፋት እንዲያመልጡ እድሉን ያገኙት በሶስት ምክንያቶች ነው እነርሱም 1)በአብርሀም ምልጃ (((ዘፍ 18:23-33))) 2)በሎጥ የፅድቅ ህይወትና (((2ጴጥ 2:7-8))) 3)በእግዚሀብሔር የምህረት ልብ (((ሰቆ ኤር 3:22)))አማካኝነት ነው ይሄ ማለት ግን የአማኞች ምልጃና የፅድቅ ህይወት ከእግዚሀብሔር የምህረት ልብ ልክ ሰዎችን ከተለያዩ ጥፋቶች ውስጥ የመናጠቅና የመታደግ ሙሉ ብቃት አለው ለማለት ፈልጌ አይደለም ✍✍ለማለት የፈለኩት እግዚሀብሔር በመልካምነቱ ባህሪው በኩል ከመጣው የጥፋት ሰደድ ውስጥ ሰዎችን በአማኞች ምልጃና የፅድቅ ህይወት አማካኝነት እንደሚታደግ የገባውን የራሱን ቃል ተንተርሶ እንደሚሰራ ለማመላከት ነው ✍✍የሎጥ ሚስት ግን ይሄንን እውነታ የመረዳቷ ነገር አጠራጣሪ ይመስላል ምክንያቱም............................ እወዳችዋለው by biruk mohammed
Show all...
#ሠርቼ_ሳይሆን_ተቆጥሮልኝ...... ❇️ እኔ በራሴ ደካማ ነኝ! #አልችልም! በመልካም ማንነት በጥንቃቄ ብራመድም ለጥቂት ነው እንጂ ፤ ተመልሼ እወድቃለሁ ፤ እንዲሁም እነሳለሁ። እድሜዬን በሙሉ ጠንካራ ሁኜ ያለምንም ስህተት መኖር አልችልም! ህጉንም ሁሉ መጠበቅም አልችልም! ምክንያቱም ፍጹም አይደለሁም። ✝ በዚህ ሁኔታም ፤ ህግን በመጠበቅ እና በመልካም ሥራ የሚጸድቅ ማንነት የለኝም!.... #ብቁ_አይደለሁም ፤ እራሴን አላምንም! ምክንያቱም እጅግ ደካማ ነኝ [በመንፈስም ደሃ ነኝ]። #በሥራዬ_ብጸድቅ ፤ ነገ ደግሞ ስደክም ጽድቄን አጣዋለሁ። በእኔ ኃይል እና በሥራዬ ቢሆን ዛሬ ላይ ባልደረስኩ ነበር። #እንደ_ሥራዬ ቢሆንማ አጠቃላይ ውጤቴ የከፋ ነበር። በሥራዬ ቢሆን ፤ እንኳን በእግዚአብሔር ፊት #ልጸድቅ ይቅርና ፤ በሰዎች ፊት እንኳን ጻድቅ አልባልም ነበር። ✝ አሁን ግን #የምጸድቀው_በሥራዬ_አይደለም! 😁 የምጸድቅበት አዲስ ተስፋ መጥቷል ፤ እርሱም #እምነት ይባላል። ያገኘሁትም #ጽድቅ የራሴ አይደለም! #ተቆጥሮልኝ እንጂ። በራሴ በየትኛውም ሥራ #የእግዚአብሔርን_ጽድቅ ላገኘው ስለማልችል ፤ #እንዲሁ_ተቆጠረልኝ ፤ ያውም የራሱ #የእግዚአብሔር _ጽድቅ። እኔ መሥራት ስላልቻልኩ #ልጁ ሥራዬን ሠራልኝ እና ለእኔ ለደካማው #ተቆጠረልኝ። ልጁ በሠራው እኔ እንዲሁ በእምነት ገባሁ ፤ ልጁ ህጉን በሙሉ መፈጸሙ ለእኔ #ተቆጠረልኝ ፤ ያለ ኃጢአት መመላለሱ ለእኔ #ተቆጠረልኝ። ሮሜ 3÷28፤ [ #ሰው_ያለ_ሕግ_ሥራ_በእምነት_እንዲጸድቅ >>#እንቆጥራለንና<<። ] ሮሜ 4 (Romans) 5፤ [ #ነገር_ግን_ለማይሠራ_ኃጢአተኛውንም_በሚያደድቅ_ለሚያምን_ሰው_እምነቱ_ጽድቅ_ሆኖ >>#ይቆጠርለታል<<። 6፤ [ እንደዚህ ዳዊት ደግሞ እግዚአብሔር >>#ያለ_ሥራ<< ጽድቅን #ስለሚቆጥርለት ስለ ሰው ብፅዕና ይናገራል። ] 22፤ [ ስለዚህ ደግሞ ጽድቅ ሆኖ >>#ተቆጠረለት<<። 23፤ ነገር ግን፦ >>#ተቈጠረለት<< የሚለው ቃል #ስለ_እርሱ_ብቻ_የተጻፈ_አይደለም፥ >>#ስለ_እኛም<< ነው እንጂ፤ 24-25፤ ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለ ማጽደቅም የተነሣውን ጌታንችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው >>#ለምናምን_ለእኛ >>#ይቈጠርልን_ዘንድ<< አለው። ] ገላትያ 3 (Galatians) 8፤ [#መጽሐፍም እግዚአብሔር >>#አሕዛብን_በእምነት_እንዲያጸድቅ >>#አስቀድሞ_አይቶ፦ በአንተ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ ሰበከ። ] ✝ እግዚአብሔር #በልጁ_ስም በማመኔ ብቻ #የልጁን_ጽድቅ ለእኔ ለኃጢአተኛው እንዲሁ ከቆጠረልኝ ፤ ታዲያ ኃይማኖት የምን #ምቀኝነት ነው? ፤ ለምንድነው "#ለመጽደቅ_መሥራት_አለብህ" የምትለኝ? እህ!!!!!!...... ቆይ መቼም በሥራዬ ፈጽሞ መጽደቅ እንደማልችል ስለሚያውቅ መስሎኝ እግዚአብሔር እንዲሁ #በነጻ ፤ ማመኔን ጽድቅ አድርጎ #የቆጠረልኝ። ወይ ሃሳብህን አስተካክለው ፤ "#ስለጸደክ_መስራት_አለብህ" በለኝ። እንዲህ ስላልከኝም አይደለም ፣ መልካም መስራት የኔ አዲሱ ሰው ማንነት life system ነው። ሮሜ 8 ÷ 33፤ [ #እግዚአብሔር_የመረጣቸውን_ማን_ይከሳቸዋል? >>#የሚያጸድቅ_እግዚአብሔር_ነው፥ #የሚኰንንስ_ማን_ነው? ] ሮሜ 10 (Romans) 3፤ የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሳያውቁ የራሳቸውንም ጽድቅ ሊያቆሙ ሲፈልጉ፥ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም። ✝ እወድሃለሁ አንተ ወንድሜ! ይህ ጽድቅ ለእኔ ብቻ እኮ አይደለም #ላንተም ነው! እመን! #ይቆጠርልሃል! በሥራ ካልክ እውነቱን ልንገርህ መቼም አትጸድቅም! እግዚአብሔር የራሱን ጽድቅ ሊሰጥህ ይፈልጋል ፤ ታዲያ አንተ ለምን የእርሱን ትተህ #የራስህን_ጽድቅ ለማቆም ትጥራለህ? እርሱ እንዲሁ በነፃ ስለሰጠህ?...... የምትድነው እኮ #በራስህ_ጽድቅ ሳይሆን በራሱ #በእግዚአብሔር_ጽድቅ ነው። @marsilchannel @marsilchannel @marsilchannel
Show all...
ጌታዬ በአንተ ልጓም እየተገራው የቤትህን ኑሮ መርጬዋለው ስርአትን እንድማር ብታስጨንቀኝም ዓላማህ ፍቅር ነው ሀሳብህ መልካም
Show all...
ዝሙት ዝሙት፦ከጋብቻ ዉጭ የሚደረግ ማናቸዉም ዓይነት የወሲብ ግንኙነት ዝሙት ይባላል። ይህም የተከለከለ ነዉ፤ 1ቆሮ 6፥9 ወይስ አመፀኞች የእ/ርን መንግስት እንዳይወርሱ አታዉቁምን? አትሳቱ፤ #ሴሰኞች ቢሆኑ ወይም ጣኦትን የሚያመልኩ ወይም #አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም #ከወንድ_ጋር_ዝሙት የሚሰሩ... 13 ... ሥጋ ግን ለጌታ ነዉ እንጂ ለዝሙት አይደለም፤ጌታም ለስጋ ነዉ፤ 👉15 ስጋችሁ #የክርስቶስ #ብልቶች እንደ ሆነ አታዉቁምን? እንግዲህ #የክርስቶስን_ብልቶች ወስጄ #የጋለሞታ_ብልቶች ላድርጋቸዉን? አይገባም። 16 ወይስ ከጋለሞታ ጋር የሚተባበር አንድ ስጋ እንዲሆን አታዉቁምን? ሁለቱ አንድ ስጋ ይሆናሉ ተብሉአልና። 18 ከዝሙት ሽሹ፤ ሰዉ የሚያደርገዉ ኃጢያት ሁሉ ከስጋዉ ዉጪ ነዉ፤ ዝሙትን የሚሰራ ግን በገዛ ስጋዉ ላይ ኃጢያትን ይሰራል። ይላል ስለዚህ በዚህ ክፍል ዉስጥ አመንዝሮች የእ/ርን መንግስት እንደማይወርሱ ፤ ስጋችን የክርስቶስ ስጋ እንደሆነ እና ዝሙትን ብናደርግ የምናረክሰዉ የራሳችንን ስጋ ሳይሆን የክርስቶስን ስጋ እንደሆነ እና በራሳችን ላይ ፈቃድ እንደሌለን እንረዳለን። እንዲሁም ምሳሌ ምህራፍ 5፤6፤7 ስለ ግልሙትና ይናገራል ✴️ ም5፥3 ከጋለሞታ ሴት ከንፈር ማር ይንጠባጠባልና፤ አፍዋም ከቅቤ የለሰለሰ ነዉና፤ 4 ፍፃሜዋ ግን እንደ እሬት የመረረ ነዉ፥ ሁለት አፍ እንዳለዉ ሰይፍም የተሳለ ነዉ። 5 እግሮችዋ ወደ ሞት ይወርዳሉ፥ #አረማመድዋም ወደ #ሲኦል ነዉ፤ ይላል ✴️ ምዕ 6፥24 ከክፉ ሴት ትጠብቅህ ዘንድ፤ ከሌላይቱም ሴት ጥፍጥነት። 25 ዉበትዋን በልብህ አትመኘዉ፤ ሽፋሽፍትዋም #አያጥምድህ። 26 የጋለሞታ ዋጋ እስከ አንዲት እንጀራ ነዉ፤ አመንዝራም ሴት የሰዉን ሕይወት #ታጠምዳለች። 27 በጉያዉ እሳትን የሚታቀፍ፤ ልብሶቹስ የማይቃጠሉ ማን ነዉ? ይላል ✴️ ምዕ 7፥4 ጥበብን። አንቺ እህቴ ነሽ በላት፥ ማስተዋልንም። ወዳጄ ብለህ ጥራት፥ 5 ከጋለሞታ ሴት ትጠብቅህ ዘንድ ቃልዋንም ካለዘበች ከሌላይቱም ሴት። ይላል ስለዚህ ማናችንም ብንሆን ከግልሙትና እራሳችንን እንጠብቅ ወንድም ሆንን ሴት ያገባ ሆነ ያላገባች ስጋችንን በቅድስና እንይዘዉ ዘንድ እናም ቢቻል ደግሞ የደረስን ሰዎች ጋብቻ ቅዱስ ነዉና በቅድስና ማግባት ይመረጣል ስጋችንን እንቀድስ። Join & share 🤳 👉 @kalu_hayal_new 👉 @kalu_hayal_new
Show all...
ዝሙት & ግብረ-ሰዶም 👇👇👇👇👇👇 እ/ር አዳምን ሲፈጥር ሄዋን አጋር ትሆነዉ ዘንድ ፈጥሯታል። ወንድ እና ሴት በተቀደሰ ትዳር ቢጣመሩ የእ/ር ፈቃድ አለበት ዘፍ 2፥18-25 ፤ ክርስቶስም ጋብቻን በቃሉ አጵድቋል ማቴ 19።፥3-6። ነገር ግን በዚህ ዘመን እየተፈጠረ ያለዉ ነገር ከዚህ ተቃራኒ ነዉ ክርስቶስ ክብር ያለዉ ይሄ ታላቅ ቃልኪዳን እየተረሳ በዋል ፈሰስ ሆኗል ነገሩ ፤ ሐጢያት በራችንን እያንኳኳ ነዉ አንዳንዱ ግንኙነትን ለጊዜያዊ ስሜት ማርኪያ ያደርጉታል አንዳንዱ ትዳሩን ትቶ ሌላ ጋር ይሄዳል 👉 ይባሱን የከፋዉ ግን አሁን አሁን እየተለመደ የመጣዉ የ #ግብረ_ሰዶማዉያን ትልቅ ድፍረትና ብልግና ነዉ። በቅርብ በእስራኤል ከሆነዉ ነገር አንዱን ልንገራችሁ #እስራኤል እንደምናቀዉ የክርስትና እምነት መፍለቂያ ናት ብዙ ተዓምራቶች የተፈጠሩባት ሀገር ናት፤ አሁን ግን የተፈጠረዉ ይሄ አይደለም ከቅድስና መንገድ ወጥታ 😔በቅርብ ጊዜ የ ግብረ ሰዶም ቀን ተከብሯል በዝግጅቱም ከ #ግማሽ_ሚሊዩን በላይ ህዝብ ታድሟል ጌ & ሌዝቢያኖች እራቁታቸዉን ሆነዉ ነበር ሲያከብሩ የነበሩት እነዚሆ ሰዎች መዋለድ ስለማይችሉ ይባሱን ህፃናትን እየመለመሉ የዚህ ሐጢያት ተተኪ ለማድረግ በማሰልጠን ላይ ተሰማርተዋል። በራሳቸዉ እንደማፈር ባደባባይ ወተዉ የፍቃድና መብት ጥያቄ ሲያቀርቡ ይታያል።(በሚቀጥለዉ ጊዜ ስለ ግብረሰዶም በሰፊዉ እናቀርባለን) እ/ር የቀደሰዉን ትዳር እና ግንኙነት ትተዉ ወንድ ከወንድ እና ሴት ከሴት ግንኙነት ማድረግ ምን ያህል የዘቀጠና የወረደ ድርጊት እና ትልቅ ሐጢያት ላይ መድረሳቸዉን ማመን ይከብዳል። ክርስቶስ የተመኘ ሐጢያትን ያደርጋል ነበር ያለዉ የሰዉ ልጅ የዉድቀቱ ደረጃ ግን ከዛ አልፎ ለዚ በቅቷል ከእንሰሳትም አንሶ። 🤔ታዲያ የዘመን ፍፃሜ ላይ እንደ ደረስን ማየት የለብንም? ፊታችንን ወደ ፅድቅ እንመልስ ጌታ ይለመነን የዝሙት ጥግ ላይ ደርሰናል ጌታ ይመልሰን በሚቀጥለዉ ጊዚ የዚን 2ኛ ክፍል ይዘን እስከምንገናኝ አብሮነታችሁ አይለየን ተባረኩ🙌 Join us🤳👇 @kalu_hayal_new @kalu_hayal_new
Show all...
ግብረ-ሰዶም ✍ሰዶማዉያን፦ ግብረ-ሰዶም የሚፈፅሙ ማለት ወንድ ከወንድ፤ ሴት ከሴት ጋር ዝሙት የሚያደርጉ ማለት ነዉ። ይህ ኃጢያት በሰዶም ይበዛ ነበርና ግብረ ሰዶም ተባለ ዘፍ 19፥5(በሎጥ ዘመን ሰዎች ኃጢያታቸዉ በተለይም የዝሙት ሥራቸዉ እ/ርን አስቆጥተዉ ስለነበር ዘፍ 18፥20 እ/ር ሰዶምንና ገሞራን ሁለት መላእክት ልኮ ሎጥን ካወጣ በኋላ በእሳትና በዲን አጠፋ ሚስቱ ግን ወደ ኋላ ስላየች የጨዉ ሐዉልት ሆነች ዘፍ 19፥10-26 ፤እነዚህ ሀገሮች በዩርዳኖስ ሸለቆ የተቆረቆሩ ከተሞች ነበሩ አሁን በጨዉ ባህር እንደተሸፈኑ ይገመታል)። እንግዲህ ተመልከቱ ይህ ኃጢያት እ/ር የሁለት ሀገር ሰዎችን እስከማጥፋት ያስደረሰዉ ኃጢያት ነዉ እንስሳ እንኳን ማያደርገዉ እንደዉም በሙሴ ዘመን እንደዛ ያደረገ ሰዉ ያለ ምህረት ይገደል ነበር ዘሌ 20፥13 ፤ ዘዳ 23፥17። ታዲያ እንዴት በዚህ ክርስቶስ በመምጫዉ ዘመን እንደ መቀደስ ድሮ የቀረን ኃጢያት እንደ አዲስ ሰዎች ማድረግ ጀመሩ? በአሜሪካ ግብረ ሰዶም ተፈቅዷል እንደሁም በቤ/ክ እስከመጋባት ደርሰዋል በቅርብ ጊዜ አንድ የ3 ልጆች አባት የሆነ ቄስ እራሱን ግብረ ሰዶም እንደሆነና አነሱንም እንደሚያጋባ እና ትክክል እንደሆነም ሲያገር ነበር ቢሆንም ግን በቤ/ክ ተቀባይነት አላገኘም በአንፃሩ ደግሞ አንዳንድ የአፍሪካ አገራት ግ/ሰ ምን አጥብቀዉ እንደሚቃወሙና ሲያደርግም የተገኘ እንደሚታሰር አሳዉቀዋል እ/ውም የሚያስር አይል አቋቁመዋል እ/ር ከሚቆጣን ሰዉ ይቆጣን ብለዋል። #አንዳንድ ከዉጭ ሀገራት የሚመጡ ዲያስፎራዎች እና ፈረንጆችም ይህን ተግባር ሀገራችን ላይ በድብቅ ለማስፋፋት ጥረት እንደሚያደርጉም ሰምተናል። ብዙዎቹ የግብረ ሰዶም አባላትና ተጠቂዎች ወደዚህ የዘቀጠ ኃጢያትና ተግባር(የሰዉ ልጅ ማያስብል ተግባር) የሚገቡትም በመጠጥና አደንዛዥ ዕጶች በመደንዘዝና ብዙዎቹ ደግሞ በሚደርስባቸዉ አስገድዶ መደፈር ማለትም ወንድ ወንድን በልጅነታቸዉ ከነሱ በሚበልጡ ሰዎች አጎት፥ዘመድ፥እንግዳ፥አሳዳጊዎች እና በመሳሰሉ ሰዎች ነዉ፤ በዚህ ጊዜ እነዛ ልጆች/ሰዎች ትልቅ የአይምሮ መረበሽ ዉስጥ ይገባሉ እራሳቸዉን ማጥፋት ወይም በዛ ተግባር መቀጠልን ይመርጣሉ። ሰዎች እ/ርን ማምለክ ና መፍራት ሲተዉ እና ጣዖታትን ማምለክ ሲጀምሩ የዚህ አይነት መጥፎ መንፈስ ያድርባቸዋል፤ በአህዛብ መካከል ይህ ኃጢያት ይገኛል፤ ሮሜ 1፥22-27፤ 1ጢሞ 1፥9-11። ይህ አይነት መንፈስ ያደረባቸዉ ሰዎች ንስሀ ቢገቡና በወንጌል ኃይል ሊድኑ ይችላሉ፤ማር 6፥11 ፤ 1ቆሮ 6፥9-11።<<ቀላጭ>>ይመ መንቃት አለብን ጌታ መምጫዉ ጊዜ ደርሷል ጌታ ከእንደዚህ አይነት ዝቅጠት ይሰዉረን የገቡም ሰዎች መመለስ ይሁንላቸዉ🙏 Share & join @kalu_hayal_new @kalu_hayal_new @enchanted_nuha
Show all...
በተሰጠን ፀጋ ኪዳኗን ለአምላካችን ብናሳስብ ምንም ችግር የለውም ባይ ነኝ ከዚህ በተረፈ ግን ስለ ሰውም ሆነ ስለተለያዩ ኮልኮሌ ነገሮች እንድናዜም ምንም አይነት መመሪያ አልተሰጠንም። 👉እወዳችኋለው by biruk mohammed
Show all...
🎤🎤🎤🎤ዘፈን 🎤🎤🎤🎤🎤በመፅሀፍ ቅዱስ 🎤🎤 🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤 ሲመዘን🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤 1)ዘፈን ማለት በመፅሀፍ ቅዱሳችን ላይ የተለያየ ትርጉም ይሰጠዋል ትርጉሞቹንም እንደየአውዳቸው ነው የምንፈታቸው 🎧 ለምሳሌ በአንዳንድ ክፍሎች ላይ ዘፈን የሚለው ቃል በትርጉሙ መፅሀፍ ላይ ጭፈራ በሚለው ተተርጉሟል በተለይ በአዲስ ኪዳን ላይ(ሉቃ 15:25)ሮሜ 13:13)1ጴጥ 4:3)ማቴ 11:17) በእነዚህ ክፍሎች ላይ ዘፈን የሚለውን ሀሳብ በትርጉሙ መፅሀፍ ላይ ጭፈራ ብሎ ነው የሚተረጉመው 🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼በብሉይ ኪዳን የተለያዩ ክፍሎችም ላይ ዘፈን የሚለውን ሀሳብ በትርጉሙ መፅሀፍ ላይ የተለያየ ፍቺ ይሰጠዋል ለምሳሌ መዝ 149:3 እና መዝ 150:4 ላይ ዘፈን የሚለው ቃል በትርጉሙ መፅሀፍ ላይ ሽብሸባ ተብሎ ነው የተተረጎመው 🎷🎷🎷በት ዳን 3:5 እና 3:10 ላይ ዘፈን የሚለው ሀሳብ ከሙዚቃ መሳሪያዎች ተርታ ተመድቦ ነው የምናገኘው 🎸🎸🎸በት አሞፅ 6:7 ላይ ዘፈን የሚለው ሀሳብ በትርጉሙ መፅሀፍ ላይ በመዝናናት ወይም በፈንጠዝያ ነው የተመሰለው 🎺🎺🎺1ሳሙ 29:5 እና 1ሳሙ 21:11 ላይ ዘፈን የሚለውን ቃል በዘፈን የዘመሩለት በሚል ሀሳብ ተቀምጦ እናገኘዋለን 🎹🎹🎹🎹በአጠቃላይ የዘፈን ትክክለኛውንና ወጥ የሆነውን ትርጉም ከእነዚህ ክፍሎች አንፃር በቀላሉ ማወቅ ሊከብድን ይችላል ነገር ግን ከክፍሎቹ ዐውድ አንፃር እያንዳንዱን ቃላት መፍታት ይቻላል 🎬🎬🎬ለምሳሌ ዘፈን በጭፈራ ስያሜ በተተረጎመበት ስፍራ ላይ ማየት የሚቻለው ዘፈን አሉታዊ ነገርና እግዚሀብሔር የማይደሰትበት ነገር እንደሆነ ማየት ይቻላል ምክንያቱም ዘፈን ጭፈራ ከሆነ ጭፈራ ማለት ደሞ ራስን ከመቆጣጠር ያለፈ የተዛነፈ ስሜት ውስጥ መገኘት ማለት ነው የሰው ልጅ ደግሞ ራሱን መቆጣጠር እስከሚያቅተው ድረስ እንደ እንሰሳት በወረደ ማንነት ውስጥ ማንኛውንም ጨዋታ እንዲጫወት አይፈቀድለትም በዚህ ሁኔታ ውስጥ ከተገኘ ግን ለተለያዩ ጉዳቶች ራሱን በቀላሉ ያጋልጣል እናም ዘፈን ጭፈራ እንደሆነ በመተርጎሙ ምክንያት በእግዚሀብሔር ቃል ዕውቅና የተሰጠው ጉዳይ አይደለም ♟♟♟በሀገራችም ባህል እንኳን ጭፈራ የሚለውን ቃል ብዙ ጊዜ ለመልካም መጠሪያነት ሲውል አናገኘውም እናም ጭፈራ የሚለው ሀሳብ አሉታዊ ነገሩ ስለሚያመዝን እኛ ክርስቲያኖች ባንጠቀመው የተሻለ ነው 🎯🎯🎯በመዝሙረ ዳዊት ላይ ዘፈን በሽብሸባ መተርጎሙ አይሁዳውያን ዘፈን የሚለውን ቃል በወቅቱ ለተለያዩ ሀሳቦች ጥቅም ላይ ያውሉት ነበር ለምሳሌ አንዱ ሽብሸባ ለሚለው ቃል ዘፈን የሚለውን ቃል በተለዋጭነት ይጠቀሙበት ነበር በሌላ መልኩ ደሞ ዘፈን የሚለውን ቃል ለሙዚቃ መሳሪያዎች ልዋጭነት ይጠቀሙበት ነበር 🎨🎨🎨🎭🎭🎭🎭ሌላው በ1ሳሙ 29:5 እና 21:11 ላይ በዘፈን የዘመሩለት ሲል የምዕራፉን አጠቃላይ ዐውድ ስንመለከተው ዳዊት ጎሊያድን በማሸነፉ ምክንያት ህዝቡ ደስታውን የገለፀበት ክፍል ነው እናም ዳዊት እልፍ ሳኦል ሺህ ገደለ እያሉ ህዝቡ ለዳዊት ጀግንነት በተቻላቸው አቅም ሁሉ ያቀነቅኑለት ነበር ይሄ ማለት ለዳዊት ገድል በታላቅ ጩኸትና አድናቆት ስሜታቸውንና ዕውቅናቸውን ይሰጡት ነበር ማለት ነው ከዚህ ክፍል አንፃር በዘፈን የዘመሩለት ሲል ሁለት የተለያዩና እርስ በእርሳቸው የተለያዩ ሀሳቦችን መጠቀማቸውን አይደለም የሚያሳየው ይልቁኑም የተሰማቸውን ታላቅ የኩራት ስሜት መግለፃቸውን ነው የሚናገረው 🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼ከዚህ በተጨማሪ በብሉይ ኪዳን ዘመን እስራኤላውያን ዘፈንን ከላይ እንደተመለከትነው ለተለያየ አላማ በተለያየ መረዳት ይጠቀሙበት ነበር እናም ከዘፈን ጋር ተያይዞ በመፅሀፍ ቅዱሳችን ላይ ያሉትን ሀሳቦች በታላቅ ጥንቃቄ ነው ልንመረምራቸው የሚገባው ምክንያቱም በዚህ ጉዳይ ላይ የተፃፉትን ክፍሎች ቃሉን(ጥቅሱን) ብቻ እንደ ሰበዝ መዘን መጠቀም ሳይሆን አጠቃላይ የምዕራፉን ሀሳብ ማግኘት ነው ያለብን ያለበለዚያ ግን የተሳሳተ መረዳት ውስጥ ልንገባ እንችላለን 🎮🎮🎮🎮ዘፈን የሚለውን አሳብ ወደ እኛ ዘመን አምጥተን ከማየታችን በፊት በመፅሀፍ ቅዱስ ዘመን ✍ፀሀፊዎቸ ቃሉን ሊጠቀሙ የፈለጉበትን ምክንያት ✍ተደራሲያኑ ዘፈን ለሚለው ቃል ያላቸውን መረዳት ✍የሀሳቡ ዘመን ዘለል መልዕክቱ ምን እንደ ሆነ ጠንቅቆ ማወቅ ✍ዘፈን የሚለው ሀሳብ ከሁሉም የመፅሀፍ ቅዱሶች ክፍል አንፃር እንዴት ነው የሚፈታው የሚለውን ጉዳይ ✍በጉዳዩ ላይ የእግዚሀብሔር ሙሉ አስተምዕሮ ምን ይመስላል ✍ከጉዳዩ አንፃር ኢየሱስ ምን አስተማረ ሐዋሪያቶችሽ ምን አስተማሩ ✍በእኛስ ዘመን ወይም ባህል ሰዎች ዘፈን ለሚለው ሀሳብ ያላቸው አመለካከት ምን ይመስላል ወዘተ የሚለውን ጉዳይ በጥልቀት መመልከቱ ከተሳሳቱ ውሳኔዎችና ትክክለኛ ካልሆኑ መንገዶች ይጠብቁናል 🎷🎷🎤ለአገር ለሰው ለተለያዩ ነገሮች መዝፈን ምን ችግር አለው የሚሉ አንዳንድ ሰዎች አሉ በነገራችን ላይ በዚህ ጉዳይ ላይ የተለያዩ ምልከታዎች ናቸው ያሉት እንደ እኔ መረዳት ዘፈንም ዘፋኝነትም ሀጢያት ነው ምክንያቱም በገላ 5:21 ላይ ዘፋኞች የእግዚሀብሔርን መንግስት አይወርሱም ይላል እናም ከዚህ ክፍል አንፃር ዘፈንን መዝፈን ፍርድን እንደሚያስከትል ይነግረናል 🎤🎤🎺በተጨማሪም እንደ እኔ መረዳት ስለማንኛውም ነገር መዝፈን ስህተት ነው ብዬ አምናለው ምክንያቱም........ 1)ዘፈን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ አይደለም የእርሱ ስጦታ መዝሙር ነው 2)ክርስቲያን ዳግም በመወለዱ ምክንያት ክርስቶስን ለብሶታል በዚህ ምክንያት ሙሉ በሙሉ ክርስቶስን ነው በሙሉ አቅሙ መኖር ያለበት 3)ሰው በክርስቶስ አምኖ ከዳነ የአሮጌውን ሰው ማንነት ሙሉ ለሙሉ አውልቆ ጥሎታል ከተጣሉት ውስጥ ደሞ አንዱ ዘፈን ነው ምክንያቱም ዘፈን በአዳምና በሔዋን ሀጢያት ምክንያት ነው ወደ ምድር የገባው ከውድቀት በፊት ሰዎችም ከመፈጠራቸው በፊት የሚታወቀው በመላዕክቶችም ሆነ በአዳምና በሔዋን ዘንድ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሚል ዝማሬ ብቻ ነው ልክ ሀጢያት ሲገባ ነው እንደ ዘፈን ያሉ ሰዎችንና የተለያዩ አካላትን የሚያወዳድሱ ነገሮች መቀመር የጀመሩት 4)እኛ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያዎች ነን ስለዚህ ለቤዛ ቀን የታተምንበትን መንፈስ ከሚያሳዝኑ ነገሮች አንዱ ዘፈን ስለሆነ መዝፈን የለብንም ኤፌ 4:30 5)መንፈስ ቅዱስ እውነት ስለሆነው ስለ ኢየሱስ ብቻ ነው ሲነገርም ሆነ ሲዘመር ደስ የሚለው 6)ቆይ እኔ ምለው ስለ ኢየሱስ ውለታ ከመዘመር የትኛው ጊዜ ተርፎን ነው ሌላውን ነገር የምናስበው 7)እኛ የተፈጠርነው መልካሙን ስራ ለመስራት ብቻ ነው ኤፌ 2:10 8)የምንዘምርና የምንዘፍንም ከሆነ ቆይ ብርሀንና ጨውነታችን ለማነው ማቴ 5:13-14 9)የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ውስጥ ዘፈን ስላልተካተተ መዝፈን የለብንም ገላ 5:22 10)መዝሙር የመንፈስ ቅዱስ አንዱ ስጦታ ነው ዘፈን ግን በየትኛውም የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ስጦታ እንደሆነ አይናገርም 1ቆሮ 14:26 👉በአጠቃላይ ከሞላ ጎደል አሳቤ ይሄንን ይመስላል እኛ ዳግም የተፈጠርነው ስለ ኢየሱስ ብቻ ዘላለማችንን እንድናዜምለት ነው ይሄንን ስል ግን መንፈስ ቅዱስ ስለ ሀገራችን ሁኔታ ከመፅሀፍ ቅዱስ ኪዳኗ አንፃር መዘመርን ይከለክለናል እያልኩኝ አይደለም ስለ ሀገራችን ጉዳይ እንደ ተፃፈላት እንድትጎበኝ እንደምንፀልየው ሁሉ በመዝሙርም
Show all...
(((የይሁዳ ስላቃዊ ህይወት)))) ✍✍ኢየሱስ የአገልግሎትን መንበር ከቸራቸው ከአስራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርቶች መካከል የገንዘብ ሚኒስቴር ተደርጎ ሹምነትን በመጎንጨት ለታላቅ ተልዕኮ የተመረጠው የአስቆርቱ ይሁዳ ስላቃዊ ህይወቱ በእጅጉን የሚገርም ነበር ✍✍የክርስቶስን ትምህርት ለትውልድ እንዲደቃ ዕጣ ቢወድቅበትም እርሱ ግን የክርስቶስን ልብ በስላቅ ሲወቃ ነበር የከረመው ✍✍ይሁዳ ኢየሱስ በሚያስተምርበት ጉባዔ ላይ እንደ እኔ ግምት እስከ መባ ሰዓት ብቻ የሚታደም ይመስለኛል ምክንያቱም ከኢየሱስ ትምህርት ይልቅ ለገንዘብ የሚሰጠው ትኩረት ከፍተኛ ስለነበረ ነው ✍✍ብዙ ጊዜ ህይወቱ በስላቃዊነት የታጀበ ነበር ለምሳሌ ያህል አንዲት ሴት የከበረን ሽቶ በኢየሱስ እግር ላይ ስታፈስ አይቶ ስላቃዊ ማንነቱን ለድሆች ሰብዓዊ መብት ተሟጋች አስመስሎ ሲገልጠው እናገኘዋለን (((ዮሀ 12:4-5))) ✍✍ሌላም ጊዜ ኢየሱስን በ30 ብር መሸጡ ሳያንስ በሁለት ስላቃዊ ማንነት ውስጥ ራሱን ሲያጎላ እናየዋለን እነርሱም ሰይፍና ጎመድ የታጠቁትን ወታደሮች ይዞ ወደ እርሱ ሲመጣ የከወናቸው ናቸው ""ሰላም ላንተ ይሁን"" በማለት በአንደበቱ መሳለቁና ደላይ በሆኑ ከናፍርቶቹ በኩል ደሞ ጉንጮቹን መሳሙ ነበር(ማቴ 26:47-50) ✍✍ተወዳጆቼ ስላቃዊ ህይወት የቱንም ወንዝ ማሻገር አይችልም ✍✍ ይሁዳ ከስላቃዊ ህይወቱ የተከፈለው ክፍያ ራሱን አንቆ መግደልን ነው ✍✍ስለዚህ እኛም ብንሆን የእርሱን ፅዋ እንዳንጎነጭ ከፈለግን በእውነተኛ መንፈሳዊ ህይወት አብን አክብረነው ለማለፍ እንነሳ እላለው እወዳችኋለው by biruk mohammed
Show all...
💃💃💃💃💃💃💃💃💃 የማያሸልሙ 7 የሩጫ ዓይነቶች 💃💃💃💃💃💃💃💃💃 ክፍል አራት ፨በማቴ 25:1-13) ባለው ክፍል ላይ አራተኛውን የማያሸልም የሩጫ ዓይነት እናገኛለን ፨እርሱም ""በበቂ ዝግጅት ያልታገዘ ሩጫ ነው"" ፨ከላይ በጠቀስኩላቹ ክፍል ላይ ስለ አስርቱ ቆነጃጂት የሚዜነት ሩጫ ይዘይራል ፀሀፊው አስሩን ሯጮች ሁለት ቦታ በመክፈል የአሯሯጣቸውን ምንነት በጥልቀት ይተነትናል ፨ባለበርኖሱ አምስቱን ልባሞች ሲላቸው አምስቱን ደሞ ሰነፎች ይላቸዋል እንደው ምክንያቱ ምን ይሆን ሁለት አይነት ስያሜዎችን ለእነዚህ አስር ቆነጃጅቶች ለመሰየም የተገደደበት ካልን ደሞ ሁለቱም አካላት የሩጫው ሜዳ ላይ በእኩል ሰዓት ጠሪውን አክብረው ቢገኙም ነገር ግን በበቂ ዝግጅት ታግዘው የሩጫው ትራክ ላይ መገኘትና አለመገኘቱ ነው ልዩነቱን ያመጣው ፦፦፦፦፦ ፨ሰነፎቹ ቆነጃጂቶች ለሚዜነቱ ሩጫ የሰጡት ትኩረት እጅግ በጣም አናሳ ነው ፨ለውድድሩ ይዘውት የቀረቡት ዝግጅት የሩጫውን ሚኒማ የሚያሟላ አልነበረም እናም በዚህ ምክንያት ሽልማታቸው""ላም አለኝ በሰማይ አውሮፕራን ገጫት""ሆነ ፨የሚያሳዝነው ነገር ከብልኋቹ ሯጮች ለሚኒማው መሟላት ጥቂት እገዛ የሚያደርግላቸውን ግብዓት ቢለምኗቸውም እንኳን ሊሳካላቸው አልቻለም በዚህም በጣም አዝነው በጊዜ ያላሟሉትን ሚኒማ ሰዓቱ ከረፈደ በኋላ ለማሟላት አስበው ከትራካቸው ፈቀቅ አሉ በዚህ ሰዓት ድንገት ዋናው አዘጋጅ በስፍራው ተገኝቶ ፊሽካውን ነፋና ሩጫውን አስጀመረ አምስቱ ብልህ ቆነጃጂቶች ሩጫውን በብቃት ፈፀሙ ፨ሰነፎቹ ሯጮች ተመልሰው ሲመጡ ሩጫው አልቆ አገኙት በዚህ ብቻ ሳያበቃ እስከ ወዲያኛው ድረስ ከመልካሙ ሽልማት ውጪ ተደረጉ ፨ተወዳጆቼ የሚዜነቱ ሩጫችን በበቂ ዝግጅት ያልታገዘ ከሆነ የእኛም ዕጣ ፈንታ የሰነፎቹን ዓይነት መሆኑ አይቀሬ ነው ፨እናም የሩጫውን ሚኒማ ዘወትር አሟልተን በትራካችን ላይ ለመገኘት እንጋደል እላለው። እወዳችኋለው by biruk mohammed
Show all...
(ልትጠነቀቃቸው የሚገቡ ሰዎች) 2)ትላንትናቸውን በዛሬያቸው ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን ተጠንቀቃቸው፦ ሁለተኛው ልንጠነቀቃቸው የሚገቡን ሰዎች ትላንትናቸውን በዛሬያቸው ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን ነው።እነዚህ ሰዎች ብዙ መገለጫ ባህሪያቶች አሉአቸው ለምሳሌ፦1)ድሮ ድሮ ድሮ የሚል ቃል የአንደበት ወዳጃቸው ነው፦በመፅሀፍ ቅዱሳችን ላይ የእስራኤላውያንን ታሪክ ስናጠና ይሄንን ባህሪ እናገኛለን።(ዘፀ16)ድሮ በግብፅ እያለን የነበረን ውበት ድሮ የምንበላው ዱባ ድሮ የሚመራን መሪ ወዘተ እያሉ ድሮአቸውን አዝማች አድርገው እያዜሙት ይኖሩ ነበር። 👉እስራኤላውያን ከፊት እየጠበቃቸው ካለው ወተትና ማር ይልቅ ትተውት የመጡት ሽንኩርትና ዱባ ትዝታቸው ሆኖ ነበር።እነዚህ ሰዎች ልባቸውን ለትላንትና እግራቸውን ደግሞ ለዛሬና ለነጋቸው ሰጥተውት ነበር የሚጓዙት። ልናስተውል የሚገባን ነገር ቢኖር ልባችንን ከዛሬና ከነጋችን ጋር ፍቅር ካላሲያዝነው ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ልንወድቅ እንችላለን።የእስራኤላውያን መጨረሻ ያላማረው ልባቸውን ከትላንትናቸው ጋር የጠለቀ ፍቅር ስላሲያዙት ነበር።ከትላንቱ ጋር ልቡን ያጋባ ሰው ዛሬና ነገውን በዲቃላ መልክ ነው የሚመለከተው እናም ትላንትናቸውን በዛሬያቸው ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን በጣም ልንጠነቀቃቸው ያስፈልጋል። 👉እስራኤላውያን ለሙሴ ስልጣን እጅግ በጣም አስቸጋሪዎች ነበሩ እርሱ ስለነጋቸው ነፃነት ደጋግሞ ሲያወራቸው እነርሱ ግን ከትላንትናቸው ግዞት ጋር ከባድ ፍቅር እንደያዛቸው ይነግሩት ነበር።እርሱ ከፊት ስለሚጠብቃቸው ወተትና ማር ሲነግራቸው እነርሱ ግን ከኋላ ትተውት ስለመጡት ዱባና ሽንኩርት በበገና ያዜሙለት ነበር።ብቻ በዚህ ዙሪያ ላይ ብዙ ነገር ማለት ይቻላል እናንተ ግን እነዚህን ሰዎች ተጠንቀቋቸው ምክንያቱም የእነርሱን ዛሬና ነገ እስትንፋስ ከልክለውት ስለሚኖሩ የእናንተንም የዛሬና የነጋችሁን በህይወት መኖር አይፈልጉትም። እናም የዛሬና የነገ ነፍሰ ገዳዮች ስለሆኑ በከፍተኛ ሁኔታ ተጠንቀቋቸው። 👉እነዚህ ሰዎች ሌላው መገለጫ ባህሪያቸው የሞት ፍቅረኛ መሆናቸው ነው(ዘፀ16:6) የህይወታቸው ዋና ርዕስ ሞት የሚል ነው እነዚህን ቃላቶች ይደጋግሟቸዋል ✍ሞት እኮ ግልግል ነው ✍ራሴን ማጥፋት እንደናፈቀኝ ✍እንደዚህ ከምሆን ብሞት ይሻለኛል ✍እኔ ለምንም ስለማልጠቅም ሞቴን እመርጣለው ✍አቦ አብሮኝ የሚሞት አንድ ሰው ልጣ ✍ምድር የኔ ዕጣ አይደለችምና ክልትው ማለት ይሻለኛል ✍አምላክ እንኳን ጨክኖብኛል ታድያ ምን ተስፋ አለኝ ከሞት ውጪ ✍ቢያቅተኝ ቢያቅተኝ መሞት አያቅተኝም ✍እንኳን እኔ እንትናስ ሞቶ የለ እንዴ ✍ሞት ብርቅ ነው እንዴ ✍ከመኖር መሞት ይሻላል ✍አምላኬ ሆይ ግደለኝ አልኩክ እኮ ✍አምላኬ ሆይ በህይወት መኖርን ከባድ ብታደርገውም መሞትን ግን በጣም ቀላል ስላደረከው አመሰግንሀለው ✍ከሞት በኋላ ስላለው ህይወቴ ምናገባኝ ✍አሁን ከደረሰብኝ ስቃይ የሲዖል ስቃይ ይቀለኛል ✍አንቺስ እንደዚህ ከምትሆኚ ብትሞቺ አይሻልሽም ወዘተ የሚሉ ቃላትን ይደጋግማሉ።እነዚህን ሰዎች ተጠንቀቋቸው። 👉ትላንትናቸውን በዛሬያቸው ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ለእናንተ ወደ ፊት መጓዝ ግብዓት ሳይሆን እንቅፋት መሆን ነው የሚቀላቸው እናም ተጠንቀቋቸው። 👉ትላንትናቸውን በዛሬያቸው ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች የእናንተን ህልምና ራዕይ መረዳት ስለማይችሉ እንዲያጨነግፉባቹ ምንም ዕድል አትስጧቸው። 👉ትላንትናቸውን በዛሬያቸው ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች በእናንተ የነገ ግንባታ ላይ ምንም ጡብ እንዲያስቀምጡ አትፍቀዱላቸው።ቢያስቀምጡ እንኳን ጡቡ አገልግሎት መስጠት የሚችለው ለግንባታው መፍረስ እንጂ ለግንባታው መታነፅ አይደለም። 👉ተወዳጆቼ እነዚህን ሰዎች በጣም ተጠንቀቋቸው ቀጣዩን ክፍል ይዤላቹ እመለሳለው። እወዳችዋለው by biruk mohammed
Show all...
💃💃💃💃💃💃💃💃💃 የማያሸልሙ 7 የሩጫ ዓይነቶች ክፍል ሁለት 💃💃💃💃💃💃💃💃💃 2)የሩጫውን መርህ ሳያከብሩ መሮጥ አያሸልምም 💃💃💃💃💃💃💃💃💃 👍ተወዳጆቼ እያንዳንዱ የሩጫ ዓይነት የራሱ የሆነ መርህ እንዳለው ይታወቃል የሁሉም የሩጫ መርህም ሊለያይ ይችላል እያንዳንዱ ሯጭ በቅድሚያ የሚያደርገው ነገር የሚሮጥበትን የሩጫውን ዓይነት መለየት ሲሆን በመቀጠልም መርህውን ተከትሎ ለመሮጥ ራሱን ያዘጋጃል። 👍የሰው ልጅ በመለኮትዊ መልክና አምሳል ለመጀመሪያ ጊዜ ከምድር አፈር ተበጅቶ በመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ በኩል ወደ ህያውነት ምዕራፍ ሲሸጋገር በምድር ላይ እንደፈለገው እንዲኖር ታስቦ አይደለም።(ዘፍ 1:26)(ዘፍ 2:7) 👉ይልቁንም ፨የፍጥረታትን ስርዓት እንዲያሰፍን ፨ከፍጥረታት ጋር ሚዛናዊ ግንኙነት እንዲያደርግ ፨የእግዚሀብሔርን ብርሀን በፍጥረታት ላይ እንዲያበራ ፨በምድር ላይ የእግዚሀብሔር እንደራሴ እንዲሆን ፨ከእግዚሀብሔር መንፈስ ጋር ህብረት እንዲያደርግ ፨በመልካም ጋብቻ በኩል ምድርን እንዲሞላ ወዘተ ....... ነበር ✍እግዚሀብሔር በእነዚህ በረከቶች ዙሪያ እንዲሮጥ መርህን በመስጠት አዳምን ቢያስጠነቅቀውም እርሱ ግን አንድ ቀን በድንገት የማያሸልመውን ሩጫ ሲሮጥ ተገኘ 👉እግዚሀብሔር ተወከልተ ሰው በሆነው አዳም በኩል ለዚህ ሁሉ ክብር የሰው ልጅን አጭቶት ቢሆንም ነገር ግን አዳም የተሰጠውን መርህ ጠብቆ እስከ መጨረሻው ድረስ ባለመሮጡ ምክንያት ከሽልማቱ ስፍራ ላይ ሲባረርና እኛንም የሰለባው ተቃማሾች ሲያደርገን ይታያል። 👉እውነትም የሩጫውን መርህ ሳያከብሩ መሮጥ አያሸልምም።ግን ደሞ አንድ የምስራች አለኝ የመጀመሪያው አዳም መርሁን ጠብቆ መሮጥ ያቃተውን ሰማያዊ ሩጫ ሁለተኛ አዳም ሆኖ የተገለጠው ኢየሱስ ክርስቶስ እስከ መስቀል ሞት ድረስ በመታዘዝ የእግዚሀብሔርን የሩጫ መርህ ጠብቆ ሁሉን በድል አጠናቆ ሽልማቱን ከአባቱ ዘንድ በመቀበል ምሳሌውን ለእኛ እንደተወልን ቅዱሳት መፅሀፍት በሰፊው ያሳብቁልናል።ፊል 2:8)(ኤፌ 1:20-21)(ፊል 2:9-11) 👉ተወዳጆቼ የእግዚሀብሔርን ሰማያዊ መርህ ሳናከብር የምንሮጠው የትኛውም ምድራዊ ሩጫ ተሸላሚዎች አያደርገንም ስለዚህ ሰማያዊውን መርህ ተከትለን በመሮጥ ለመለኮታዊው ሽልማት እጩ ሆኖ ለመገኘት ዛሬውኑ ትራካችን ላይ እንገኝ እላለው።ይቀጥል እንዴ? እወዳችዋለው by biruk mohammed
Show all...
💃💃💃💃💃💃💃💃💃 የማያሸልሙ 7 የሩጫ ዓይነቶች 💃💃💃💃💃💃💃💃💃 ከክፍል ሶስት የቀጠለ......... ፨እነዚህን ከላይ ለአብነት ያህል አንስተን የዘረዘርናቸውን ነገሮችም ሆነ ሌሎች መሰሎቻቸውን ጨምሮ አለመጨረስ በሁለንተናዊ ህይወታችን ላይ ከፍተኛ ድክረትን እንደሚያስከትልብን ጠንቅቀን ማወቅ አለብን። ፨እስከዛሬ ድረስ ከአዳም ጀምሮ ምድራችን ከ100 ቢሊዮን በላይ ሰዎችን ማስተናገድ ብትችልም በጣም የሚገርመው ግን የጀመሩትን ነገር በብቃት የጨረሱ ሰዎች ብቻ ናቸው በታሪክ ማዕደር ላይ በጀግንነት ሰፍረው ከትውልድ ወደ ትውልድ በትምህርት መልክ እየተላለፉ የሚገኙት። ፨እኛስ ከየትኞቹ ወገን እንሆን? "ሁላችንም ራሳችንን ልንጠይቅ ይገባናል"""""""""""""""""""""""""""" ፨ተወዳጆቼ በተለይ በዚህ ዙሪያ እኛ አማኞች ነን የምንለው ላይ የሚታየው ትክተት በእጅጉን የጎላ ነው አብዛኛዎቻችን የጀመርነውን አንድ ነገር ስንጨርሰው ሳይሆን የቱጋር ጥለነው መሄድ እንዳለብን ስናውተረትረው ነው የምንታየው እናም ቆም ብለን ማሰብ ይኖርብናል ፨አሁን አሁንማ እየታማንበት ያለው ጉዳይ በእጅጉን ያስደነግጣል ምኑ አትሉኝም እኮ ልነግራቹ እኮ ነው ግን አጠገባቹ ማንም ከሌለ ነው የምነግራቹ እሺ መልሳቹ ማንም የለም ስለሆነ ልቀጥል ፨እግዚሀብሔር ከጀመራችሁት መጨረሳቹ የግድ ነው ፈፅሞ ሩጫውን በቃሌ ላይ ከተቀመጠው ምክንያት ውጪ(ማቴ19)ማቋረጥ አይቻልም ያለውን የጋብቻ ጉዳይ በሽሮ ቀጠነና ወፈረ ኢ-አመክኖአዊነት እንደፈለግን የፈለግንበት ቦታ ላይ የምናቋርጠው ነገርን ነው እኮ ልነግራቹ የፈለኩት ፨ዛሬ ላይ ይሄንን ሩጫ አቋራጩ በዝቷል እንደውም የፋሽን ያህልም ነው እየታየ ያለው ፨ከዚህ አጁዛ አስተሳሰብ ጌታ ይሰውረን ፨ይሄ ነፈዝ መንፈስ ከዙሪያችን ላይ በኢየሱስም የተመታ ይሁን ፨ውዶቼ በዚህ ሩጫ ውስጥ ካላቹ ሩጫውን በትዕግስት ቀጥሉ ገና ደሞ ለወደፊት ይሄንን ሩጫ ለመቀላቀል እያሟሟቅን ያለን ደግሞ ከመግባታችን በፊት በደንብ ስለ አሯሯጣችን ልናስብበት ይገባናል እላለው ፨እናስተውል አጀማመራችን ሳይሆን አጨራረሳችን ነው የሚያሸልመን ✍✍መልካም የመጨረስ ዘመን እወዳችኋለው by biruk mohammed
Show all...
🌜እየፈራህም ቢሆን ኢየሱስን🌛 🌗እየተመለከትክ ተጓዝ🌘 በማቴ 14:22-33 ባለው ክፍል ላይ ትዝ ካላቹ ጴጥሮስ በውሀው ላይ የተራመደበትን ታሪክ እናገኛለን ✍ጴጥሮስ ኢየሱስን ካስፈቀደ በኋላ በውሀው ላይ ወደ ኢየሱስ መራመድ ጀመረ ኢየሱስን እያየ ድንገት ግን የንፋሱንና የሞገዱን ሀይል ሲሰማ ውስጡ በፍርሀት ተዋጠ ✍በዚህ ጊዜ ከጴጥሮስ የሚጠበቁ ሁለት ነገሮች ነበሩ 1)ወደ ኢየሱስ ብቻ መጓዝ፦ይህ ማለት ጴጥሮስ ምንም እንኳን በባህሩ ላይ የመራመድ ስልጣን ተሰቶት መራመድ ቢጀምርም ነገር ግን በወቅቱ መራመድ የሚጠበቅበት ወደ ባህሩ ፈጣሪና ወደ ጠራው ወደ ኢየሱስ ጋር ብቻ ነው ✍በተሰጠኝ ስልጣን በባህሩ የተለያዩ ክፍሎች ዙሪያ እንደፈለኩት መረማመድ እችላለው ብሎ ቢያስብና ወደ ጠራው አምላክና የባህሩ ፈጣሪ ወደሆነው ኢየሱስ ጋር እርምጃውን ባይጀምር ኖሮ "ወደ እኔ ና" ከሚለው መለኮታዊ ጥሪ ጋር ስለሚፋለስ ለማዕበሉና ወጀቡ ረሀብ በምግብ መልክ እስከ ወዲያኛው ድረስ ታልፎ መሰጠቱ የማይቀር ጉዳይ ነበር ✍ጴጥሮስ ግን ጥሪውን ወዳመጣለት ወደ ኢየሱስ ጋር ብቻ ሲጓዝ እናገኘዋለን 2)ሁለተኛው ከጴጥሮስ የሚጠበቀው ነገር፦፦፦፦ኢየሱስን ብቻ እየተመለከተ መጓዝ ነው የሚገርመው ጴጥሮስ በመጀመሪያው መመሪያ መሠረት ውጤታማ ቢሆንም ነገር ግን በዚህ በሁለተኛው መመሪያ መሠረት ከጉዞው ሲደናቀፍ እናየዋለን ✍በወቅቱ ብዙ ድምፆች በዙሪያው ሲያንዣብቡ ድንገት ከኢየሱስ ላይ ዓይኑን አነሳ በዚህ ጊዜ መስጠም ጀመረ ✍✍""ተወዳጆቼ በዙሪያችን የከበቡን ነገሮች ሁሉ የሚያስፈሩ ቢሆኑና እኛም ምናልባት መፍራት ብንጀምር እንኳን አደራ የምላቹ ነገር እየፈራንም ቢሆን ዓይናችንን ከኢየሱስ ላይ ሳናነሳ እርምጃችንን ወደ ፊት እንቀጥል"""""""""""""""""""""""""""""" እመኑኝ እርምጃችንን በድል ከጨረስን ያኔ ከጠራን አምላክ ጋር ፊት ለፊት በክብር እንገናኛለን። ✍ከዚህ ክፍል የምንማረው ቁምነገር ከሰማይ ለመጣልን ጥሪ ወደ ኢየሱስ ብቻ መጓዝንና ኢየሱስን ብቻ እየተመለከቱ እስከ ፍፃሜው ድረስ መራመድን ነው ✍✍በዙሪያችን የሚያስፈራን ነገር ቢበዛም እንኳን ዓይናችንን ከኢየሱስ ላይ ለሰከንድም ሳናነሳ የምድሩን እርምጃ እስከ መጨረሻው ድረስ እንራመድ አንድ ቀን በአብ ቀኝ ቆሞ ከሚጠብቀን ጌታ ጋር በክብር ፊት ለፊት መገናኘታችን የማይቀር ይሆናል። እወዳችዋለው by biruk mohammed
Show all...
💃💃💃💃💃💃💃💃💃 የማያሸልሙ 7 የሩጫ ዓይነቶች ክፍል ሶስት 💃💃💃💃💃💃💃💃💃 3)ሩጫውን አቋርጦ መውጣት አያሸልምም 💃💃💃💃💃💃💃💃💃 ብዙ ሰዎች አንድን ነገር መጀመር ላይ ጀግኖች ናቸው ነገር ግን ያንን የጀመሩትን ነገር የተወሰነ ከገፉበት በኋላ ሁኔታው እንደ ጠበቁት ሆኖ ካላገኙት እንደገና ሌላ አዲስ ነገርን ለመጀመር ይከጅላሉ ✍✍ለሰው ልጅ ትልቁ ኪሳራ ደሞ አንድን ነገር ጀምሮ አለመጨረስ ነው ለምሳሌ፦ ፨አንድን መፅሀፍ ማንበብ ጀምሮ አለመጨረስ(1ጢሞ 4:13) ፨ትምህርት መማር ጀምሮ አለመጨረስ(ሆሴ 4:6) ፨ስራ መስራት ጀምሮ አለመጨረስ(1ሳሙ 15) ፨አንድን ዕቅድ አቅዶ በታቀደው መስመር ተጉዞ አለመጨረስ (2ጢሞ 4:7) ፨አገልግሎትን ጀምሮ አለመጨረስ (2ጢሞ 4:5) ፨ትዳርን ጀምሮ አለመጨረስ (ማቴ 19) ፨ቅድስናን ጀምሮ አለመጨረስ (ኢያ 3:5) ፨አስራት መክፈልን ጀምሮ አለመጨረስ(ዘፍ 14:20) ፨ፀሎትን ጀምሮ አለመጨረስ (ማቴ 26:41) ፨የቃል ጥናትን ጀምሮ አለመጨረስ(ቆላ 3:16) ፨መባ መስጠትን ጀምሮ አለመጨረስ(ማቴ 8:4) ፨በቸርች ህብረት ማድረግን ጀምሮ አለመጨረስ(መዝ 133) ፨መንፈሳዊ ረሀብተኝነትን ጀምሮ አለመጨረስ(ኤፌ 5:17-18) ፨የክርስትናን ጎዳና ጀምሮ አለመጨረስ(2ጢሞ 4:10) ፨ክርስቶስን መምሰል ጀምሮ አለመጨረስ(1ጢሞ 4:8) ፨ማህበራዊ ድህረ ገፆችን ለክርስቶስ ክብር መቀደስ ጀምሮ አለመጨረስ(ቆላ 3:17) ፨በጌታ ብቻ መደሰት ጀምሮ አለመጨረስ(ፊል 4:4) ፨በወንድሞቻችን ስኬታማነት ሀሴት ማድረግ ጀምሮ አለመጨረስ(ፊል 4:3) ፨በሌላው ላይ አለመፍረድን ጀምሮ አለመጨረስ(ማቴ 7:1) ✍✍......................................................................... ....................... ....................... ....................... .......................
Show all...
(ልትጠነቀቃቸው የሚገቡ ሰዎች) 1)ሁሉን አውቃለው ባይ ሰዎችን ተጠንቀቃቸው በ3ዮሀ 9 ላይ ዲዮጥራጢስ የሚባል ሰው ነበር እናም ይሄ ሰው ራሱን እንደ አዋቂ ስለሚቆጥር ሐዋሪያው ዮሀንስን አይቀበለውም ነበር።የሁሉን አውቃለው ባይ ሰዎች አንዱ መገለጫ ባህሪያቸው የሌላውን አቅም መቀበል አለመቻላቸው ነው።ነገሮችን እነርሱ በሚያስቡት አንፃር ብቻ እንዲከወን ይፈልጋሉ ለዚህም የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። 👉እነዚህ ሰዎች ለሁሉም ሰው ያላቸው አመለካከት በጣም ዝቅተኛ ነው።ማጉረስን እንጂ መጉረስን መለማመድ አይፈልጉም።ሙሉ እንደሆኑ ስለሚያስቡ የሌላውን አቅም ያክፋፋሉ።ዲዮጥራጢስ የተባለው ሰው ለዮሀንስ አገልግሎት የራስ ምታቱ ነበር።የሚገርመው እኮ ይሄ ሰው ረጅም አመታትን ያሳለፈው በቤተክርስቲያን ውስጥ መሆኑ ነው። 👉ሁሉን አውቃለው ባይ ሰዎች አንዱ መኖሪያ ቄያቸው በቤተክርስቲያን ውስጥ ነው።ራሳቸውን በመንፈሳዊ ካባ ውስጥ አጥልቀው የሚንቀሳቀሱ ስለሆነ እነርሱን ለመለየት ረጅም ጊዜን ሊፈጅ ይችላል።የሚገርመው ደሞ ዓመፃቸውን የሚንከባከቡበትን በርካታ ጥቅሶች ከመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ አሰበጣጥረው በማዕደራቸው ላይ ማስፈራቸው ነው።ያሰፈሩትንም ጥቅስ እንደ አሸንክታብ በአንገታቸው ላይ አንጠልጥለው በመዞር የጤነኛውን ሰው አስተሳሰብ ካለሳለምን በማለት ሌተ ቀን ይዳድራቸዋል። 👉እነዚህ ሰዎች ሌላውን ሰው ሆን ብሎ መቃወም ዘውትራዊ ማዕዳቸው ነው።ምናልባትም የሚቃረናቸው ሰው ካጋጠማቸው እንኳ ስለሚወስዱበት ማንኛውም እርምጃ ደጋፊ ጥቅሳቸውን ተጠያቂ ማድረግ የለመዱ ናቸው። 👉ሁሌም እነርሱ ትክክል እንደሆኑ ስለሚያስቡ የሌላውን ትክክል ለማፅደቅ ይተናነቃቸዋል።ራሳቸውን የመጨረሻው የዕውቀት ማማ ላይ ስለሚያስቀምጡ እንደ ውሀ ከታች ወደ ላይ የሚወጣ አንድም አዲስ ነገር የለም ብለው ስለሚያስቡ የሌላውን መልካም ነገር ዘወትር ይገፋሉ። 👉የሁሉን አውቃለው ባይ ሰዎች የንቀታቸው ግንፍልታ ከልክ ያለፈ ነው።ማንንም ከቁብ አይቆጥሩም።ከሁሉ በላይ እንደሆኑ ስለሚያስቡ ማህበራዊ መስተጋብሮችንም ሆነ መንፈሳዊ ህብረቶችን የሚሳተፉት በይስሙላና በግብዝነት መንፈስ ተነቅዘው ነው። 👉እነርሱ ባሉበት ቦታ መማር መስራት ማገልገልም ሆነ መጎራበት ትርፉ ህይወትን ማድከም ነው።መታረም ስለማይፈልጉ የህይወታችን አረም ሆነው መገኘታቸው አይቀርም።ዲይጥራጢስ የተባለው ሁሉን አውቃለው ባይ ሰው ለዮሀንስ አገልግሎት ትልቅ ረብሻ ነበር። 👉በአጠቃላይ ሁሉን አውቃለው ባይ ሰዎች ከሚገለጡባቸው ባህሪያቶች መካከል በጣም ጥቂቶቹን ነው ለማካፈል የሞከርኩት የእነርሱ ጉድ ምንም ቢወራ ማለቂያ የለውም።ከባህሪያቸው መካከል ለማስታወስ ያህል 1)የሌላውን አቅም ከመቀበል ይልቅ ኪሊማንጃሮ ተራራን በአንድ ሰከንድ መውጣት ይቀላቸዋል 2)የንቀታቸው ጡንቻ ፍርጣሞነቱ ተጋጣሚ አይገኝለትም።3)የህይወት ታላቅ ረብሻ ናቸው።4)ሌላውን መቃወም የህይወት ቀለባቸው ነው። ተወዳጆቼ እኛስ ምን አይነት ሰዎች ነን?የሌላውን አቅም በደስታ እንቀበላለን?ለሌላው ያለን አክብሮትስ ምን ይመስላል?ለሰዎች ህይወት ረብሻ ሆነናል?ህይወታችንስ በተቃውሞ ብቻ የተሞላ ነው?ሁላችንም በዚህ ቃል ራሳችንን መፈተሽ አለብን ብዬ አስባለው።ቀጣይ ልንጠነቀቃቸው የሚገቡ ሰዎችን ይዤላችሁ እመጣለው እስከዛው እባኮዎን መስመር ላይ ይጠብቁኝ።በተጨማሪም ደሞ ታዲያ ከእነዚህ ሰዎች ጋር እንዴት ነው መኖር የሚቻለው የሚለውንም ሀሳብ በደንብ አጢኑበት። እወዳችዋለው by biruk mohammed
Show all...
(((መንፈስ ቅዱስ እና ምሪት))) ውዶቼ ሁሉ ሻሎም እንደሚሆን ቅንጣትም ታህል አልጠራጠርም ጌታ በመርከባቹ ላይ ስላለ እስቲ ደሞ ዛሬ ስለመንፈስ ቅዱስና ምሪት አንዳንድ ነገሮችን ላካፍላችው እወዳለው በቅድሚያ መንፈስ ቅዱስ መለኮት የሆነና ከአብና ወልድ ጋር እኩል መከበርን የተላበሰ ልዕለ ተፈጥሮን ከያንያን ነው።መንፈስ ቅዱስ የስላሴ ሶስተኛ አካል እንጂ አንዳንዶች እንደሚሉት ወልደ-ፍጡር አይደለም።ሌላው 👉መንፈስ ቅዱስ የእግዚሀብሔር ሙሉ ምሪት ነው።በዚህ ዘመን የሰው ልጆች ትክክለኛውን የህይወት መንገድ ለማግኘት ሲሉ የሚጠቀሟቸው የአቅጣጫ ብዛቶች አዕላፋት ናቸው ነገር ግን ከትክክለኛው ወደ ህይወት አቅጣጫ ጠቋሚው ጋር ሳይገናኙ ዘመናቸው ወና ሆኖ ያልቅባቸዋል። 👉መንፈስ ቅዱስ የእግዚሀብሔር ሙሉ ምሪት ስለሆነ ወደ ትክክለኛው የህይወት መስመር የሚያመለክተንን ከእርሱ ውጪ አንዳችም አካል አናገኝም።እስቲ እነዚህ ጥያቄዎች ልጠይቃችሁ፦፦ 1)ምሪት ማለት ምን ማለት ነው? 2)ምሪት ለክርስቲያኖች ምን ያህል ይጠቅማል? 3)የምሪት አይነቶች ምን ምን ናቸው? 4)ስለመንፈስ ቅዱስ ምሪት ምን ማለት ትችላለክ? 5)በብሉይና በአዲስ ኪዳን የመንፈስ ቅዱስ ምሪት ልዩነቱ ምን ላይ ነበር? ውዶቼ እነዚህን ጥያቄዎች እስቲ እንማማርባቸው ሀሳባችሁን በጌታ ፍቅር አካፍሉኝ አደራ እወዳችኋለው by biruk mohammed
Show all...
👉ከአባባሎቼ መካከል ጥቂቶቹን እነሆኝ እላለው 👎"ለእግዚሀብሔር የሚገባውን እየሰጠነው ካልሆነ የማይገባውን እንዲቀበለን እያስገደድነው እንደሆነ መዘንጋት የለብንም።" 👎የእግዚሀብሔርን ሀሳብ ለማሻሻል መሞከርና በፈቃዱም ላይ የእርምትን አስተያየት ለመስጠት መዳከር ሰይጣን የወደቀበትን ትዕቢት ጥራቱንና ደረጃውን አሻሽለን መቅረባችንን እየገለፅን ለመሆኑ ምልክት ነው።" 👎የምንሄድበትን መንገድ የማናውቅ ከሆነ መንገዱ በራሱ መዳረሻችንን ይወስንልናል።" 👎ወደ ፊት መሄድ ከፈለግን ከትላንትናችን ትክክል ይልቅ የዛሬያችን ስህተት ለመንገዳችን የተሻለ ስንቅ እንደሆነ አንዘንጋ።" 👎የአንዳንድ ሰዎችን ባህሪይ መቀየር እንደማንችል ከገባን የራሳችንን ባህሪይ እንዳይዘርፉን ማድረግ እንደምንችል ይግባን።" 👎 ለሳቀልን ሁሉ ሻማ ካበራንና አምርሮ ለጠላን ሁሉ ሰይፍን ከመዘዝን የምስኪኖች ሁሉ አምበል ነን።" 👎ከወደቁ ሰዎች አንድ ነገር ብቻ እንማር መውደቅ የህይወት አንዱ ክፍል እንደሆነ ያኔ በሚመታን እንቅፋት ሁሉ ትምህርት የመስራት አቅማችን ከፍ ይላል።" 👎እግዚሀብሔርን ለማመስገን አዲስ ምክንያትን መፈለግ የመስቀሉ ስራ እንዲሻግት የመፍቀድን ያህል ይቆጠራል።" 👎የተረጋጋ ማንነት ከሌለን የረጋ ራዕይን መፀነስ አንችልም። 👎ክርስትና የክርስቶስን ህይወት ስለመካፈል እንጂ ሰውን ከሰው በዘርና ብሔር ስለመከፋፈል አያስተምርም" 👎ሰው መሆን ያቃተው ሰው አውሬ አለመሆን አይችልም" by biruk mohammed
Show all...