cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

RealLoveinGod

በእውነተኛ ፍቅር TUBE 👉 መዝሙር ለማደመጥ🎧➠ @Akichombe_Bot አስተያየት ለመላክ📩➡ @Akichombe Our YouTube Channel 👇👇 https://www.youtube.com/@RealLoveinGod

Show more
Ethiopia7 223The language is not specifiedReligion & Spirituality50 723
Advertising posts
896Subscribers
No data24 hours
-47 days
-2730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

💽 Album: Echo The Angels 👤 Artist: Elevation Worship 📅 Date: 2023-10-27
Show all...
አማኝ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታውን እንዴት ማወቅ ይችላል? bdu_fellowshipNovember 26, 2023  #blog #Monday #eyuel ብዙዎቻችን “የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዬን እንዴት ማወቅ እችላለሁ? እግዚአብሔር ምን ዓይነት ስጦታዎችን እንደ ሰጠኝ እንዴት ለይቼ ማወቅ እችላለሁ? ስጦታዬን ለማወቅ የምከተለው ቅደም ተከተል የያዘ መመሪያ አለ ወይ?" ብለን መጠየቃችን አይቀርም። አንድ ነገር እርግጠኞች እንሁን። ያም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ምንጊዜም ቢሆን የድብብቆሽ ጨዋታ የማይጫወት መሆኑን ነው ።  ስጦታችንን ደብቆ " ፈልጋችሁ አግኙት "አይለንም። ስጦታችንን እርሱ እንደሚያየው እኛም በግልጽ እንድናየው ይፈልጋል። መንፈስ ቅዱስ የሰጠንን “የጸጋ ስጦታ ለይተን ለማወቅ ምን ማድረግ አለብን? ፩ መፀለይ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታችንን ለማወቅ መውሰድ ያለብን እርምጃ፥ አንደኛው መጸለይ ነው። እግዚአብሔር የማናውቀ ውን እንድናውቅ የምንችልበትን መንገድ ከፍቶልናል። ያም ጸሎት ነው። ያዕቆብ “…ስለማትጸልዩ የምትፈልጉትን ነገር አታገኙም" ይለናል (ያዕ. 4፥2)። እግዚአብሔር ስጦታችንን እንዲያሳየን ጸልየን፥ ስጦታችንን ማውቅ ካልቻልን፥ ያዕቆብ 04:3 "የለመናችሁትን ነገር በሥጋዊ ደስታ ላይ ለማዋል በክፉ አሳብ ስለምትጸልዩ ነው” እንዳለው፥ እኛም ምናልባት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታችንን ለማወቅ የፈለግነው ለሥጋዊ ፍላጎታችን ማርኪያ እንዲሆንልን በመፈለጋችን ይሆናል። በአካባቢያችን የምናውቃቸው አማኞች በመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ምክንያት ያገኙትን ዝናና ክብር ስንመለከት፥ እኛም እንደነርሱ ለመሆን በመመኘት “ጌታ ሆይ! ለእኔስ የሰጠኸኝ ስጦታ ምንድነው?” ብለን እንጠይቅ ይሆናል። በሐዋርያት ዘመን “ሐዋርያት እጆ ቻቸውን ሲጭኑባቸው መንፈስ ቅዱስ ለሰዎቹ መሰጠቱን ሲሞን ባየ ጊዜ ገንዘብ አመጣላቸውና እኔም እጄን የምጭንበት ሰው መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበል ይህን ሥልጣን ስጡኝ አለ። ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለው፥ የእግዚአብሔርን ስጦታ በገንዘብ ለማግኘት በመፈለግህ ገንዘብህ ካንተ ጋር ይጥፋ! ልብህ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ስላልሆነ አንተ ከዚህ ነገር ክፍል ወይም ዕጣ የለህም" እንዳለው እናስታውሳለን (የሐዋ. 8+ 18-21)። በአሁንም ዘመን እንደ ሲሞን “የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን" ለራሳቸው ክብር ሲሉ የሚመኙ አሉ። ምን ዓይነት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እንደተሰጠን ማወቅ የምንፈልገው ለምን ይሆን? በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ራሳችንን ከፍ ከፍ ልናደርግበት፥ ወይንም ራሳችንን ልናሳይበት ይሆን? ስጦታችንን አውቀን ሌሎችን እንድናገለግልበት ከሆነ፥ “ጌታ ሆይ! ቤተ ክርስቲያንን እንደሚገባኝ ማገልግል እንድችል ስጦታዬ ምን እንደሆነ አሳውቀኝ" ብለን ብንጸልይ፥ እግዚአብሔር ለጥያቄያችን መልስ ይሰጠናል። መንፈስ ቅዱስ ዓይናችንን ከፍቶ የሰጠን ስጦታ ምን እንደሆነ ያሳየናል። ማሳየት ብቻ ሳይሆን የምናገለግልበትንም በር ይከፍትልናል። ፪ የሚሰማንን ስሜት መመርመር የመንፈስ ቅዱስ ስጦታችንን ለማወቅ ሌላው ማድረግ ያለብን ነገር ቢኖር ስሜታችንን መመርመር ነው። “አማኝ በአገልግሎቱ ደስ የሚለው ከሆነ፥ አንድ ልክ ያልሆነ ነገር በሕይወቱ መኖር አለበት" ብለው የሚያምኑና የሚያስቡ አንዳንድ አስተማሪዎች እንዳሉ እናውቃለን። ይህ ከእውነት የራቀ አስተያየት ነው። እግዚአብሔርን ማገልገል ደስታ ያለበት እንጂ የሚጨፈግግ አይደለም። ደስ ብሎን እንጂ፥ በግድ ወይንም ደስ ሳይለን እንድናገለግው አይፈልግም። እግዚአብሔር የሥነ-ልቦና ይዞታችንን፣ የሚሰማንን ስሜት ሁሉ ያውቃል። ስንሠራው ደስ የሚለንን ሥራ ስንሠራ የበለጠ ፍሬያማ እንደ ምንሆን ያውቃል። ስለዚህ እግዚአብሔር የሚሰጠን መንፈሳዊ ስጦታ ደስ ብሎን የምንሠራው እንጂ እየጨፈገገን፥ ደስታ ሸሽቶን የምናገለግልበት የአገልግሎት ስጦታ አይደለም። መንፈሳዊ አገልግሎት በፈቃደኝነት ደስ ብሎን የምናገለግለው እንጂ፥ በግድ አይደለም። በምናገለግለው አገልግሎት ደስ ካለን “ከእግዚአብሔር ነው" ወይም ስንሠራው ደስ ካላለን ደግሞ “ከእግዚእብሔር አይደለም” ብሎ በአጠቃላይ መገመት ግን ስህተት ላይ ስለሚጥለን መጠንቀቅ አለብን። መስበክ ደስ የሚላቸው ክርስቲያኖች አሉ፤ ሊሰብኩ ደስ ስላላቸው ስጦታው አላቸው ማለት አይደለም። ደስ ያላቸው ምክንያት የክርስቶስን እውነት ለሰዎች መግለጻቸው ሳይሆን፥ በሰው ዘንድ እንዲታወቁ ስላደረጋቸው ይሆናልና፥ የደስታቸውን እውነተኛ ምክንያት መመርመር ይገባቸዋል። ፫ የአገልግሎታችንን ፍሬ መመዘን ስናገለግል በአገልግሎታችን ፍሬ እናያለን? የምናስተምር ከሆነ ስናስተምር ሰዎች ይባረካሉ? ይማሩበታል? በወን ጌል ስብከታችንስ ሰዎች ወደ ጌታ ይመጣሉ? ስጦታችን የበለጠ ግልጽ እየሆነልን የሚመጣው፥ በተግባር ላይ ስናውለውና በአገልግሎታችን ፍሬ የማየት ዕድል ሲኖረን ነው። ፬ የሰዎችን ምስክርነት መስማት ሌሎች ሰዎች በአገልግሎታችን እንድንቀጥል ያደፋፍሩናል? ሁሉም ባይሆኑ፥ ዕድገታችንን የሚናፍቁ አንዳንድ ሰዎችን እግዚአብሔር በዙሪያችን እንዳስቀመጠ እናውቃለን። ክርስቲያን ጓደኞቻችን፣ መጋቢዎቻችን፥ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ስለምንሰጠው አገልግሎት ምን ይላሉ? አንዳንድ ጊዜ እኛ ራሳችንን ከምናውቀው የበለጠ ሌሎች ሰዎች ያውቁናል።ያለ ቦታችን ሆነን የምናገለግል ከሆነ፥ “የምታገለግለው ያለቦታህ ነው" ይሉናል? ወይንስ “ለዚህ አገልግሎት እግዚአብሔር ስጦታውን እንደሰጠህ እናምናለን! በርታ! ቀጥል" ብለው ስለ አገልግሎታችን መልካም ምስከርነት ይሰጣሉ? ፭ መንፈስ ቅዱስ ለልባችን የሚሰጠንን ምስክርነት ማዳመጥ መንፈስ ቅዱስ መዳናችንን ብቻ ሳይሆን ስጦታችንም ምን እንደሆነ በልባችን ይመሰክርልናል። ክርስቲያን የፈለገውን ዓይነት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እየመረጠ አይቀበልም። መንፈስ ቅዱስ ለቤተ ክርስቲያን የሚያስፈልገውን ስጦታ ስለሚያውቅ የሚያከፋፍለው እርሱ ራሱ ነው። “...መንፈስ ቅዱስ እንደ ፍላጎቱ ለእያንዳንዱ ሰው የተለየ ስጦታ ይሰጠዋል” ይላል (1 ቆሮ. 2፥11)። የትኛውም የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ቢሆን ከእግዚአብሔር ጋር የተቀራረበ ሕይወት መኖራችንን ወይንም በመንፈሳዊ ሕይወታችን ከሌሎች የተሻልን ወይንም የበለጥን ክርስቲያኖች መሆናችንን አያሳይም። እግዚአብሔርን ማገልገል መታደል ነው።
Show all...
“እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም፥ ሥጋ በሆነ በልብ ጽላት እንጂ በድንጋይ ጽላት ያልተጻፈ፥ በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ መልእክት እንደ ሆናችሁ የተገለጠ ነው።” — 2ኛ ቆሮ 3፥3 “እናንተ በቀለም ሳይሆን በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ፣ በድንጋይ ጽላት ላይ ሳይሆን በሰው ልብ ጽላት ላይ የተጻፋችሁና በእኛ የተገለገላችሁ የክርስቶስ ግልጽ ደብዳቤ ናችሁ።” — 2ኛ ቆሮንቶስ 3፥3 (አዲሱ መ.ት)
Show all...
ሮሜ 12 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው። ² የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።
Show all...
1
ዘማሪ ይድነቃቸው ተካ|Yidnekachew Teka .     ✨ ብቸኝነት አይሰማኝም  ✨ Volume 2 | Track 1  https://t.me/YidnekachewTekaofficial
Show all...
“እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም።” — ሮሜ 8፥1 በክርስቶስ ከሆንን ፍርድ/ኩነኔ አይኖረንም።በክርስቶስ ስንሆን ሓጢአታችን ይወገዳል/ይቅር ይባልልናል። በጭራሽ የሚቀር ነገር አኖረንም። #በክርስቶስ #መሆን ማለት ክርስቶስ ኢየሱስን #ጌታ እንደሆነ #ማመን እና እርሱ #አዳኝ እንደሆነ አድርጎ መቀበል ነው። ደግሞም በህይወታችን #የገዝነትን ስፊራ ለእርሱ ስንሰጥ የዛኔ በክርስቶስ እንሆናለን። @RealLoveinGod
Show all...