cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

ሀበሻ 🇪🇹

🇪🇹 ኢትዮጽያዊነታችንን የምናሳይበት 🤝 አንድነታችንን የምናጠነክርበት 🥰 ፍቅርን የምንማርበት ቻናል ነው ። ☞☞ @Ferhanhabesha

Show more
Advertising posts
8 513Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-6030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

[እኔ አለሁ እንዳለሁ እንዴት ነሽ እመ?] ከጦርነት ቀጠና ወጥቼ አዲስ አበባ እንደገባሁ የመጀመሪያው ስራየ ስራቦታ ጎራ ማለትና ቤት መፈለግ ነበር። እውነት ለመናገር ከሆነ አዲስ በብዙ ግልምጫዎችና በሰቃዥ የኑሮ ውድነት የታጀበች እጅግ ባይተዋር ከተማ ሆና ነው የጠበቀችኝ። አዲስ አበባ ቁመት ሙሉ እንባ ስጋ ሙሉ ኧረወይለሊቴ ሆናለች ወገን። “ጃክሮስ ቆንጆ ቤት አግኝቼልሀለሁ” ደላላው ነበር ሄድኩ ቤቷ ሁለት በሶስት ናት። ጭራሽ መሀከሉ ላይ እንደሰፊው ህዝብ መድረሻ ያጣ የሚመስል ኮለን ተገትሯል። “ኧኸ እንዴት ነው ወደድሻት? 3500 ናት” ምን ነካህ ደላላ!? ይሄኮ እንኳን አልጋ ሊያዘረጋ ጠረንጴዛና ወንበር ሊይዝ ፍራሽ እንኳን ካላጠፍኩት አያስነጥፈኝም። 😳 የውሻውን ቤት ነው እንዴ ልታከራዮኝ ያሰባችሁት🤔 “ውሻውማ የተሻለ አግኝቶ ስለወጣ ነው እምናከራይህ” አከራዩዋ እንባየ ደርሶ ግጥም አለ🥴 ደግሞ ሌላ ቤት መስቀል ፍላወር “ድርድር የለውም። 6 ክፈል” ሸምገል ያሉ ናቸው አከራዮ ቆንጀት ያለ ቤት ነው እሺ እከፍላለሁ “ታመሻለህ?” አዎ አንዳንዴ ሚቲንግ ሲኖረኝ እስከ 4 ምናምን ላመሽ እችላለሁ “አይሆንም አይሆንም እስከ 2 ልፍቀድልህ” እንዴ ልጅዎ አደረጉኝ እንዴ! “ምን አልክ? ይሄንም እኔ ሆኜ ነው” እንዴ ትራንስፖርቱ ራሱ ያስመሻል እኮ። ቁልፍ ካለ ይስጡኝ ላስቀርጸው። “ቁልፍ? ለምንድን ነው ቁልፍ እምሰጥህ? አምሽተህ እየገባህ ልታዘርፈኝ!” እ😳 “ተወው ለሌላ አከራየዋለሁ። በዚያ በኩል ውጣ” እንባየ ደርሶ ግጥም አለ🥴 ከሰአቱን ድክም ሲለኝ ልረፍ ምሳም ልብላ ብየ የሆነ ሆቴል ገባሁ ቅቅል ተፈርሾ አምጪልኝ። By the way ቅቅል ኢዝ ማይ ተወዳጅ ምግብ በድንች፣ በካሮት እና በሆኑ ቅጠላቅጠሎች የታጀቡ 3 ግድንግድየ ቅልጥሞች መረቅ ደፍቀው መጡ ተጠራጠራጠርኩ ሂሳብ ስንት ነው እናት? “550” እ😳 እንስቷ እንባዋ ደርሶ ግጥም አለ🥴 ከጎጃም በእግርና በባጃጅ ያስወጣኸኝ አንድየ አንተ ታውቃለህ ብየ በላሁት ሂሳብ ከፍየ ስወጣ ከጀርባየ የሆነ ድምፅ ሰምቼ ዞር ስል አስተጋጇ እጇን እያውለበለበች “ዌል ካም ቱ አዲስ የዝቅተኛው ማህበረሰብ አባል” ስትለኝ ደረስኩ እስኪ ሆዴ ቻለው ቻለው ቻለው እያልኩ ወደስራ ቦታየ ወክ አደርግ ጀመር አለም ሲኒማን እልፍ ስትሉ ባስ መጠበቂያው አለአይደል፣ አንድ በግምት 60 ዎቹ አካባቢ የሆነ ሰውየ እግሩን አጥፎ ወንበሩ ላይ ተቀምጦ አይኑን ጨፍኖ “ኦም…ኦ….ም…. ኦ….ም” ይላል ሆዴ ቦጭ ቦጭ አለ ዝርዝር የአምስት ብር ሳንቲሞች መፀወትኩት ሰውየው ግን አንድ አይኑን ገልጦ “ወንድም ዮጋ እየሰራሁ እንጂ እየለመንኩ አይደለም። አዲስ አበባ መቆየት ከቻልክ ይጠቅምሀል ገንዘብህን ያዝ” አለኝ አደነጋገጤ😳 ህዝቤ እንዳለ ለቆ ነው🤔 ቢሮ ልደርስ አካባቢ የሆነ ሙዚቃ ሰመቼ ዞር ስል የሬሳ ሳጥን የሚሸጥበት ሱቅ ላይ ሁለት ወጣቶች እየቃሙ በትንሽየ ስፒከር “ጉርምርሜ ና ጉርምርሜ ያሆ መሌ ያሆ መሌ ና ጉርምርምርሜ” የሚል ሙዚቃ ያዳምጣሉ ጆሮየ ፕራንክ ነው በለኝ😳 እውነት ለመናገር የሬሳ ሳጥን መሸጫ ውስጥ ሙዚቃ ስሰማ ይህ የመጀመሪያየ ነው “የኔ ልጅ ተውው አሽሙር ነው። መንገድህን ቀጥል” አሉኝ በአጠገቤ ሲያልፉ የነበሩ እናት ወይ አዲስ አበባ እንዲህ ሁሉን ነገር ድብልቅልቅ አደርጋ ትጠብቀኝ። ታክሲዎች ትንሽ መንገድ አምቦራችተውህ 10 ብር አምጣ ይሉሀል። ከመሸብህ ይሄ ብር ሁለት እጥፍ ሁሉ ሊሆን ይችላል። ራይድ ልያዝ ካልክ happy textile road bruh በሶስት ቀን ሆድህ ፈርደሀል ማለት ነው! ደግሞ ሰው ምንድን ነው እንዲህ የተፈራራው🤔ለንደን ያለህ ይመስል ማንም ሰላም ሊልህ አይፈልግም። ሰላምታ ብታቀርብም አበጀህ የሚልህ የለም። ወንድም ሰአት ስንት ነ..? “እግዜር ይስጥልኝ እኔ ራሱ የታክሲ ብቻ ነው የቀረኝ። እህል ከቀመስኩ ዛሬ ሁለት ወሬን ደፈንኩ” እ😳 “ተወኝ በቃ እኔ የትኛውንም ፖለቲካ ፓርቲ አልደግፍም። የሁሉም ባንክ አካውንት አለኝ” ዋ ኧረ ምንጉድ ነው ብየ ወደ ጎዳናየ ተመለስኩ ወገን እንግዲህ አዲስ ጥይት አልተተኮሰባትም እንጂ ጦርነት ላይ ናት የሚባለው ነገር እውነት ነው መሰል… ቢጨንቀኝ እመ ጋ ደወልኩና “እመ ለካንስ ይሆን መስሎኝ እንዲያው ሳላውቀው ከሞት ሸሽቼ ወደ ሞት ነው የመጣሁት” አልኳት እመ ግን ሳግ በሚተናነቀው ድምፅ ምን አለችኝ? “ልጅ ታምሩ ምን የሚያጓጓ ህይወት ኖሮህ ነው ሞት የሚያስፈራህ!” እንባየ ደርሶ ግጥም አለ🥴 @wegoch @wegoch @paappii By Tamiru Temesgen
Show all...
Repost from Jafer Books 📚
የአድዋው ጀግና ራስ መኰንን የታፈነው ዜና መዋዕል በአማርኛ ተተርጉሞ ለንባብ በቃ! በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ከሚይዙት ታላላቅ የጦር ሰዎች ውስጥ ቀዳሚው ራስ መኰንን ናቸው፡፡ እኒህ ታላቅ የጦር መሪ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ አባት፤ የምኒልክ ዙፋን ታማኝ፤ የሣህለ ሥላሴ የሥጋም የመንፈስም ውርስ ያላቸው ታላቅ የጦር ሰው ናቸው ፡፡   ይህ ዜና መዋዕል መነሻውን ከዘመነ አክሱም በማድረግ የንግሥና ሐረጎችን እያጣቀሰ፣ ዋናውን የታሪክ መቼቱን ዐፄ ምኒልክ አንኮበር ላይ ከተወለዱበት ከ1836 ዓ.ም. ያደርጋል፡፡ ከዚህ ዘመን ጀምሮ ፍሰቱ እስከ 1910 ዓ.ም. ዋዜማ ይቀጥላል፡፡ በእነዚህ ዘመናት በኢትዮጵያ ቤተ መንግሥት የተከናወኑ ታላላቅ ተግባራት በዚህ ዜና መዋዕል ተመዝግበዋል፡፡ የመጽሐፉ ርእስና ዋና ተተራኪ ራስ መኰንን ይሁኑ እንጅ በሐረር የተሾሙ ደጃዝማቾች የአስተዳደር ሁኔታ፣ ሐረርና ጅጅጋ ሲያዙ የተካሄዱ ጦርነቶች፣ በምሥራቅ ኢትዮጵያ የተተከሉ ቀዳምያን አድባራት ዝርዝርና የአተካከል ታሪክ፣ በማዕከላዊ መንግሥት የነበሩ የሥልጣን ሽኩቻዎች፣ የአድዋ ጦርነትና ሌሎችም አካባቢያውያን ዘመቻዎች ተካተዋል፡፡ ስለሆነም ይህ ዜና መዋዕል በዘመኑ ስለነበረችው ታሪካዊቷ ኢትዮጵያ አስተዳደር አንደኛ ሁነኛ ምንጭ ሆኖ ሊጠቀስ የሚችል ድንቅ ትርጉም ነው፡፡ ዜና መዋዕሉን አንብቦ ምስክርነቱን የሰጠው ደብተራና የሕግ ባለሙያው በአማን ነጸረ የዜና መዋዕሉ ጸሐፊ ግራጌታ ኃይለጊዮርጊስ የአጻጻፍ ክህሎታቸውን እንዲህ ሲል አወድሶታል፡- ‹‹… ጸሐፊው ፍሬ ነገር አያዛቡም፡፡ ታሪክ አያንዛዙም፡፡ የድርጊት ጊዜን፣ ቦታንና ሁኔታን አይስቱም፡፡ ከቀደምት ጸሐፍት በተለየ ዓመተ ምሕረትን በጥንቃቄ ይመዘግባሉ፡፡ ከውጋዴን እስከ አድዋ ዐቢይ ድርጊት የተፈጸመባቸው የቦታ ስሞችን ፊደል ሳያዛንፉ ጠንቅቀው ይጽፋሉ…››
Show all...
👍 1
Repost from Jafer Books 📚
"ዛሬ ቅዳሜ አይደለም" በተሰኘው መጽሐፍ ዙሪያ የተሰጠ ዳሰሳ። በዮሴፍ ተመስገን (የቋንቋ እና ሥነ ፅሁፍ መምህር) ክፍል አንድ በአዳም ረታ የምናውቀው የህጽናዊነት አጻጻፍ በ “ዛሬ ቅዳሜ አይደለም” መጽሐፍ ውስጥ ረብቦበታል የሚል ሀሳብ ውስጤ ተፈጥሮ ነበር፡፡ (ለመጀመሪያ ጊዜ ሳነበው፡፡) ነገር ግን ከደራሲው ማረጋገጫ ካላገኘሁ በስተቀር ይህንን ሀሳብ እንድቀይር የሚገፋፋ ስሜት ከውስጤ ተፈጥሯል፡፡ (ለሁለተኛ ጊዜ ሳነበው፡፡) መጽሐፉን ሁለት ጊዜ አንብቤው የተፈጠረብኝ ስሜት ሁለት አይነት ነውና የማስቀምጠው አልሆነም፡፡ እሰልሠው ግድ ነው፡፡ የመጽሐፉ ደራሲ ናትናኤል ቀረዓለም “ዛሬ ቅዳሜ አይደለም” የመጀመሪያ የታተመ መጽሐፉ እንጂ የመጀመሪያ መጽሐፉ ላለመሆኑ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ቁጭ ብለን እናጠናቸው ዘንድ ሊያስገድዱን የሚቃጣቸው ቴክኒኮችን በመጽሐፉ ውስጥ አካቷል፡፡ (ዶክተር እንዳለጌታ ከበደ ለዚህም ይመስለኛል መጽሐፉን “ቋንቋው ፣ ቴክኒኩ እና የሀሳቡ ፍሰት አጃኢብ ነው፡፡) ሲል የገለጸው፡፡ መጽሐፍ አንብቤ የመጽሐፍ ዘውግ ፣ ቴክኒክ እና የአጻጻፍ ስልት መለየት እስኪሳነኝ ድረስ ስደነቅ ይህ የመጀመሪያዬ ነው ብል ብዙም ያጋነንኩ አይመስለኝም፡፡ “ምን አይነት መጽሐፍ ነው?” ብዬ ከማንበቤ በፊት ለጠየቅኩት ጥያቄ ያገኘሁት መልስ “በአጫጭር ታሪኮች እንዲሁም በዘፈቀደ ሀሳቦች የተዋቀረ” የሚል መልስ ነበር ያገኘሁት፡፡ ያገኘሁት መልስ እውነት ያልነበረ ስለመሆኑ እመሰክራለሁ፡፡  የመጽሐፉ የመጀመሪያ ገጽ ላይ… “…እውነት የሚባል ነገር የለም! ሊል ፈልጎ…” “…እውነት የሚባል ነገር የለም! ማለቱ እውነት አይሆንምና ተወው…” (ገጽ 1) የሚል ሀሳብ ስታገኙ አንዴ አንብበን ወደ ቀጣዩ ገጽ እንሻገር ዘንድ መጽሐፉ እንዴት ይፈቅድልናል? ሮማን ተወልደ መጽሐፉን ስትገልጸው “አጫጭርም ወጥም ፣ ወጥም አጫጭርም ፣ ፍልስፍናዊ ልብ ወለድ” ብላዋለች፡፡ እውነት አላት፡፡ ያለማቋረጥ የሚዥጎደጎዱ ጥያቄዎቹ እና የተሰመረበት ምላሽ ሳይሰጥ አንባቢውን አስተክዞ ፣ ማለቂያ ወደሌለው የሀሳብ ዓለም አሻግሮ መጽሐፉ ወደ ቀጣዩ ገጽ ይሻገራል፡፡ “…ልጄ ማታ በጊዜ ነው የምትመጣው?” እናቱ ጠየቁት፡፡ “እርግጠኛ አይደለሁም እማዬ!” መለሰ፡፡ እየወጣ ማብሰልሰል ጀመረ፡፡ “እርግጠኛ አይደለሁም!” ስል ምን ማለቴ ነው? በምንም አይነት ነገር ላይ በእርግጠኝነት እርግጠኛ መሆን ይቻል ይሆን? በጊዜ ስለመምጣቴ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ጭራሽ ስለመመለሴስ እርግጠኛ መሆን እችላለሁ? አይመስለኝም፡፡ ሰው እኮ እርግጠኛ ስለመሆኑ ራሱ በእርግጠኝነት መናገር አይችልም፡፡ እኔም… ሰው እርግጠኛ ስለመሆኑ በእርግጠኝነት መናገር አይችልም ብዬ በእርግጠኝነት መናገር አልችልም፡፡” ማብሰልሰሉን ቀጠለ፡፡… (ገጽ 44) ማብሰልሰሉን የሚቀጥለው ገጸ ባህሪው ብቻ ሳይሆን ተደራሲው መሆኑንም ማስተዋል ልብ ይሏል፡፡ ይህ በየመሀሉ ከእናቱ እና እህቱ ጋር የሚጨዋወት ገጸ ባህሪይ ካፌው ውስጥ የሚመሰጠው እንዲሁም ከመምህራኑ ጋር የሚከራከረው መምህር ይሆንን ብዬ እጠረጥራለሁ፡፡ (ገጸ ባህርያቱ ስም አልተሰጣቸውምና እርግጠኛ ለመሆን ቢከብደኝም እርግጠኛ የሆንኩ ይመስለኛል፡፡ ያው መጽሐፉ “ሰው ስለ አንድ ነገር በእርግጠኝነት እርግጠኛ መሆን አይችልም…” ብሎ እንዳይሞግተኝ እየሰጋሁ፡፡  መጽሐፉ በዚህ ገጸ ባህርይ ላይ ያጠነጥናል የሚል ድምዳሜ መስጠት ግን ስህተት መፍጠርም ይሆናል፡፡ በአጫጭር እና ራሳቸውን የቻሉ በሚመስሉን (ራሳቸውን የቻሉ ሊሆኑም ከሌሎች ጋር ሊደጋገፉ ቢችሉም) ታሪኮች ውስጥ አላገኘነውም ይሆን የሚል ጥያቄን ማስከተሉ አልቀረም፡፡ …በብቸኝነት አላደገም፡፡ በብቸኝነት አድጓልም፡፡ ከሰው አልተለየምና በብቸኝነት አላደገም፡፡ ሰው መሀል ሆኖ ተነጥሏልና ብቸኝነት አጥቅቶታል፡፡ ፀሐይ በብቸኝነት የምታንጸባርቀውን ጨረር ተመልክቶ ብቸኝነቱ ኃይል ስለመሆኑ አያስብም፡፡ ውብ ቅላጼ ያለው ሕብረ ዝማሬ አድምጦ ብቸኝነቱ ድክመት ስለመሆኑ አያስብም፡፡ እሱ እሱ ነው፡፡ ብቸኛ የሆነ፡፡ ብቸኛም ያልሆነ፡፡  (ገጽ 10) የገጸ ባህርያቱ ስም አልባ መሆን ገጸ ባህርያቱን እንዳንወዳቸው ወይም እንዳንጠላቸው አላገደንምና (እሷ ፣ እሱ እንዲሁም እነሱ) ያጎደሉብን የለም፡፡ እንዲያው አንዳንዴ ጥቂት እንድንመራመር እና የመጽሐፉን ገጽ እንድንገለብጥ ማመንታት ውስጥ ቢከቱንም፡፡ ይቀጥላል
Show all...
Repost from Jafer Books 📚
"ዛሬ ቅዳሜ አይደለም" በተሰኘው መጽሐፍ ዙሪያ የተሰጠ ዳሰሳ። በዮሴፍ ተመስገን (የቋንቋ እና ሥነ ፅሁፍ መምህር) ክፍል ሁለት በግዕዝ ፊደላትና እና ቁጥሮች በተከፋፈሉ ምዕራፎቹ ውስጥ “ዛሬ ቅዳሜ አይደለም” በአስደናቂ mythological እና fantasy ታሪኮቹ እንደመም እና ከሀሳቦቹ ፋታ እንወስድ ዘንድም ያድለናል፡፡ “ለረጅም ጊዜ እንደመዘጋቱ መጠን ቤቱ በሸረሪት ድርና አዋራ ተወርሶ ልታገኘው እንደምትችል ጠርጥራ ነበር፡፡ ጥርጣሬዋ ከንቱ የነበረ ቢሆንም፡፡ የቤታቸውን ጽዳት በአግባቡ በሚከታተሉ ሰዎች ቤት ውስጥ የገባች እስኪመስላት ድረስ ቤቱ ፍጹም ጽዱ ነበር፡፡ ከአንዱ ክፍል ወደ ሌላው እየተዘዋወረች ትመለከት ጀመር፡፡ ቤቱ ውስጥ ሰው ካለመኖሩ በስተቀር የተለየ ነገር አልነበረውም፡፡ ከጭንቀት ይቆጠር የነበራት ሀሳብ ቤቱ ባለቤት አልባ አይመስልምና የሰዎች ቢመጡብኝስ ስጋት ነበር፡፡ ወደ መኝታ ቤት ዘለቀች፡፡ በሥነ ሥርዓት የተነጠፈ አልጋ ከአንዱ ጥግ ሲገኝ ከፊት ለፊቱ የመጻፊያ ጠረጴዛ እና ጥቂት መጽሐፍት ይገኛሉ፡፡ የመኝታ ክፍሉ መስኮት አልነበረውምና ውስጡን ትመለከት ዘንድ የረዳት ከጠረጴዛው ጥግ ላይ በርቶ የነበረ ሻማ ነበር፡፡ “ሰው የማይኖርበት ቤት ከሆነ ይህን ሻማ ማን ለኮሰው?” የእሷም ጥያቄ ነው፡፡ ወደ ውስጥ ስትዘልቅ የመኝታ ክፍሉ በር ድምጽ ሳያሰማ ከኋላዋ ሲዘጋ ዞራ አልተመለከተችም፡፡ የመጻፊያ ጠረጴዛው አጠገብ የሚገኘው ወንበር ላይ በዝግታ ተቀመጠች፡፡ ወደ ቤቱ ውስጥ ስትገባ በውስጧ ያልነበረው ፍርሃት ደብዛው ርቋል፡፡ ከጥራዝ መጽሐፍቶቹ ውስጥ አንዱን አንስታ ተመለከተችው፡፡ ታነብ ጀመር፡፡ ቀና ትል አልፈቀደችም፡፡ የያዘችውን መጽሐፍ ሳታስቀምጥ ጨልሞ እየነጋ መሆኑን ታስተውል አልሆነችም፡፡ ያን ያህል መጽሐፍ የማንበብ ፍቅሩም ሆነ ልምዱ አልነበራትም፡፡ ያገኘቻቸውን መጽሐፍት አታነብ ዘንድ ምክንያት ባይሆናትም፡፡ አንዱን መጽሐፍ ስታገባድድ ሌላውን እያነሳች ለረጅም ጊዜ ቆየች፡፡ ስለ ሌላ ታስብ ዘነጋች፡፡ ስለ ሌላ ታስብ ስለመዘንጋቷ ታስብ ዘነጋች፡፡ የመጻፊያ ጠረጴዛው ላይ የነበሩ መጽሐፍትን አንብባ ስትጨርስ ቀና አለች፡፡ ለረጅም ጊዜ ስለመቆየቷ ሳይታወቃት ቀና አለች፡፡ ለመውጣት በማሰብ ወደ መኝታ ቤቱ በር በማምራት ልትከፍት እጇን ከመስደዷ በፊት ደንገጥ አለች፡፡ ወደ ጠረጴዛው ዞራ ተመለከተች፡፡ ንባቧን ስትጀምር በመብራት ላይ የነበረው ሻማ ምንም አይነት የመጠን መቀነስ አላሳየም፡፡ ለረጅም ጊዜ ስለመቆየቷ ባይገለጥላትም ያነበበቻቸውን መጽሐፍት ስትመለከት ፍርሃት ቢጤ ተሰማት፡፡…” (ገጽ 141-142) ሸኚ ቤት አያደርስምና ያላነበበችሁ አንብቡ፡፡ ያነበባችሁ ድገሙ፡፡ የደገማችሁ ሰልሡ፡፡ (እንደ እኔ) ከታሪኮቹ መለስ ስንል አዕምሯችንን “ጂም” የሚያሰሩ የፍልስፍና ፣ የማኅበራዊ ፣ የሥነ መለኮት (ተፈጥሮ እና ፈጣሪ) ጥያቄዎች እና ሀሳቦችን እንጋፈጥ ዘንድ የ”ዛሬ ቅዳሜ አይደለም” ግብዣ ይሆናል፡፡ ሀሳብን በሀሳብነቱ መሞገት ፣ መውቀስ እና መታገል የአባት ነውና ግብዣውን ተቀብለን ወደ የአዕምሮ “ጂም” መዝለቅ ነው፡፡ “ሰው ምንድነው?” “ሰው ምን ማለት ነው?” ከተጠየቀ ቆይቷል፡፡ መመለስ ባለመቻሉ ቅር አልተሰኘም፡፡ ዛሬም ያብሰለስል ዘንድ እድል ሰጥቶታል፡፡ “ሰው ምንድነው?” “ሰው ምን ማለት ነው?” በፈጣሪ አምሳል ከአፈር ተፈጥሮ እስትንፋስ እፍ የተባለበት ፍጡር ነው? ከዝንጀሮ መሳይ እንስሳ በዝግመተ ለውጥ አሁን የያዘውን ቅርጽ የያዘ ማኅበራዊ እንስሳ ነው? ወይስ… “ሰው ምንድነው?” “ሰው ምን ማለት ነው?” ብሎ መጠየቅ የቻለ ነው?  (ገጽ 18) ተሻገርን… “በመጀመሪያ እግዚአብሄር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ፡፡” የሰማይ እና የምድር መፈጠር መጀመሪያ ነበር? የፈጣሪያቸው መፈጠር ምን ይባል ይሆን? ፈጣሪ አይፈጠርም፡፡ ካልተፈጠረና ሰማይና ምድርን ከመፍጠሩ በፊት ከነበረ ከዚያ በፊት ምንም አልነበረም? ላይኖር ይችል ይሆናል፡፡ ሰማይንና ምድርን ከመፍጠሩ በፊት ሰማይንና ምድርን ለመፍጠር ማሰቡ መጀመሪያ አይሆን ይሆን? (ገጽ 72) አንድ እንጨምር… እንፈራው ዘንድ አይፈልግ ይሆን ይሆናል፡፡ አንፈራው ዘንድ ቢሳነንም፡፡ ከቁጣው እንርቅ ዘንድ ብንጠነቀቅም፡፡ ወድደን ነው? ትላቸው ወደማይሞትበት እሳቱም ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነም ወደማይጠፋ እሳት ስለመሄድ ሳይሆን ስለመሄድ ማሰብ ከሥጋችን ልትለይ ገና የሆነችን ነፍስ ያለጊዜዋ ሊነጥል በሚጥር ፍርሃት ውስጥ አያሳድራትም? የሚንቦገቦግ እሳት ባይከበን ፣ የማይሞት ትል ባይታየን ፣ በሰፈረ ጽሁፍ የምናውቀውን ገሃነም እየኖርንበት አይሆን ይሆን? ብቻችንን ቀርተን ይሆን አይሆን? አምላካችን… “በአምሳላችን ሰው እንፍጠር!” ብሎ ሲያበቃ ፣ ፈቃደኝነታችንን ሳይጠይቅ በምድር ላይ አኑሮን ሲያበቃ ፣ ለእኩይ እና ሰናይ አጋፍጦን ሲያበቃ ፣ ቀድመው ለነቁ ሰጥቶን ሲያበቃ ፣ ወዴት ሸሸ?   (ገጽ 168) ከሚዥጎደጎዱ ጥያቄዎች እና ከሚብሰለሰሉት ሀሳቦች እኩል ነፍስን ሰቅዞ የሚይዝ የፍቅር ታሪክ ያድለን የሆነ መጽሐፍ እንደሆነ ለአፍታ ዘንግቼውም ነበር፡፡ በማንበብ ማትረፍ ግልጽ እንደሆነ የሚታወቅ ቢሆንም፡፡ “ዛሬ ቅዳሜ አይደለም”ን በማንበብ ፍትሐዊ ያልሆነ ሀብትን እናካብት ዘንድ እመክራለሁ፡፡ ሀሳብ በራሱ ቅርጽ እና ቁመና ታቅፎ ፣ ሥጋ እና ደም ተላብሶ እንዲሁም ነፍስ እና እስትንፋስ ታድሎ በመሀላችን ይንሸራሸር ዘንድ ያደረገልንን ደራሲ እና መጽሐፍ አለማመስገን ንፉግነት ነው፡፡ “ዛሬ ቅዳሜ አይደለም”ን ያበረከትክልን ናትናኤል ቀረዓለም ሆይ… ከፍ ብለህ ጀምረሃልና ከፍፍፍ… ብለህ ቀጥል፡፡ ብዕርህ አይንጠፍ፡፡ ዶክተር እንዳለጌታ ከበደ እንዳለው እኔም ቀጣዩን ስራህን ከአሁኑ መናፈቅ ጀምሬያለሁ፡፡ ላላነበባችሁ መልካም ንባብ! ላነበባችሁም መልካም ንባብ!
Show all...
ማስታወሻ - ዘነበ ወላ በስብሐት ገብረእግዚአብሔር (1928 እስከ 2004ዓ.ም) የሕይወት ታሪክና ኪነጥበባዊ ክህሎት ዙሪያ በዘነበ ወላ በተጻፈው "ማስታወሻ" መጽሐፍ ላይ የኢትዮጵያ ቡክ ፎረም አሰናኞችና ተሳታፊዎች ውይይት ያደርጋሉ። የውይይቱ ሊንክ: https://www.clubhouse.com/invite/DwdI13znJQ0b03yXn5ad0Aq8Wp5dcBo9N0:jx_iw6QCLbPwS2D4t4CwauP7Is16VSledfGjvY_K2G8
Show all...
‘ጊዜ ድሮ ቀረ’ (ጋዜጠኛና የኪነጥበብ ባለሙያ ተፈሪ ዓለሙ) ድሮ ጊዜ ነበር!!! ጠላትን ለማጥመድ ወዳጅ ለመሰብሰብ፣ ፍቅር ለመጠንሰስ ሴራ ለመሸረብ። የፍንጥር ለማለት ለመጣል ደንቃራ፣ ለወሬ ክርክር ለምክር ለሴራ። ለስድብ ሰላምታም፣ ለውዳሴ ሃሜታም። አድፍጦ ለማድባት ለመደበቅ ሸሽቶ፣ ግብዣ ለመታደም ለመጋበዝ ጠርቶ። ለጠብ ቀን ለመቁረጥ ለፍልሚያ ቀጠሮ፣ ሰዓት … ዕለት … ዓመት … ጊዜ ነበር ድሮ! ዘንድሮ ጊዜ የለም!!! ከሚፈቅዱት ወዳጅ ከሚወድዱት ጋርም፣ ቆይታ ለመያዝ ወግ ለመደርደርም። አላደርስ እያለ ለእግዚአብሔር ሰላምታ፣ ዛሬ ምን ጊዜ አለ ለፍቅር ጨዋታ፧ ለምን ሰው ዘንድሮም ጠብ ጠብ ያሰኘዋል፧ ምን ያኳርፈዋል፧ ያቀያይመዋል፧ እንኳን ተቀያይሞ በጥል ተራርቆ፣ ጠኗል መተያየት ከአንጀት ተነፋፍቆ። መቼ ጊዜ አለና፧፧፧ የሃሳብ መለያየት በአንድ አለመግጠሙ፣ ያለ ነው ይኖራል አለመጣጣሙ። በጋራ ሚከፈል ብዙ እቁብ እያለን፣ ሃሳባችን ቢለይ እኛን ምን ለያየን፧ ጎበዝ! መኖር እንደዚህ ነው!!! ከልዩነት በላይ ከቅራኔ ልቆ፣ አልፎ ሂያጅ ትኩሳት ግጭቶችን ንቆ። አርቆ አስተውሎ የጋራን አላማ፣ በፈገግታ አንግቶ የኩርፊያን ጨለማ። ጠብ መምጫውን መንገድ ባቋራጭ አሳብሮ፣ ጠብ መንጃውን መሪ አፈሙዝ አዙሮ። አይተው እንዳላዩ እንዳልሰሙ ሰምተው፣ ቸለል ቀለል አርገው በማለፍ በመተው፡ ችሎ ተችሎ ነው ሰው አብሮ ሚኖረው! በመቻቻል እንጂ እየተላለፉ፣ በትንሽ ትልቁ ከተኮራረፉ፧ መቼ ቀን ሊገፉ! ይሞቷታል እንጂ ቂም እንደቋጠሩ፣ በንዴት፣ በጸጸት፣ ቁ…ጭት እያረሩ፡ መቼ ሰላም ሊያድሩ፧ ለመወቃቀስም ቆሞ ባደባባይ፣ ለመግለጥ ደመና በይቅርታ ፀሃይ። የለ አቃቤ ሰዓት፣ ለምልጃ ደጅ ጥናት። መቼ ጊዜ ተርፎ መቼ ጊዜ አለና፧ ድሮ እንጂ ዘንድሮ ቀርቷል ሽምግልና። ተጣልቶ መታረቅ ላማላጅ ቀጠሮ፣ ለይቅርታ ካሣ ጊዜ የለም ዘንድሮ፡ ጊዜ ቀረ ድሮ። @kederasiyan
Show all...
Repost from Zeraf Books
"አውሮራ" "ታላቁ ተቃርኖ" "የቄሳር እንባ" "አስኳላ" "ሕንፍሽፍሽ" "የሱፍ አበባ" "አንፋሮ" የተሰኙትን መጻሕፍት የደረሰው ሀብታሙ አለባቸው።
Show all...
Repost from Jafer Books 📚
ለትምህርት ለንግድ ለግል ንባብ ልምዳችሁ ይጠቅማቹሃልና የምትፈልጉት በዚህ ሊንክ    @abumame በኩል ስለዋጋው አውሩን ::
Show all...
Repost from Zeraf Books
"ወዲያውኑ ቅድመ ዝግጅቴን ጀመርኩ። እናቴ ስሙኒ ሰጥታኝ ጸጉሬን 'ተማሪ ቁርጥ' ተስተካከልኩ፣ ቁንጮዬንም ተሰናበትኳት። በወቅቱ የአራተኛ ክፍል ተማሪ የነበረው ከበደ ደብተሬ ላይ አንድ ማሳሰቢያ ጻፈልኝ: ‘ይህ ደብተር የተማሪ ተስፋዬ ዜራሞ ደብተር ነው፣ ማንም እንዳይነካ። የነካ አርባ ጅራፍ ይገረፋል።’ ቆጥሬ አንብቤው ተገቢው ማስታወቂያ በተገቢው ቦታ ላይ በመስፈሩ ተደሰትኩኝ። በዚህ አኳኋን የቄስ ትምህርቴን 'ዊዝድሮው' አድርጌ ዳዊት ሳልደግም ከሳቴ ብርሃን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዜሮ ክፍል ገባሁ።” (ዘነበ ወላ ~ ልጅነት) ፨፨፨፨፨፨ Inbox @Zerafb or Call us on 0985333153 To Order. Shipping Worldwide 🇺🇸🇮🇸🇨🇦🇩🇪🇰🇷🇿🇦~🌎 & Delivering Locally.
Show all...
Repost from Jafer Books 📚
የምድራዊው ሕይወታችን ስንሞት ይገታና በሰማይ ቤት አምላካችን ዘንድ በመቅረብ ፍርዳችንን እንቀበላለን፡፡ ጥሩ የከወነ ወደ ገነት ሲገባ ትዕዛዝ ያላከበረ እና በኃጢአት የተዘፈቀ ደግሞ ወደ ሲኦል ይጣላል፡፡ የገነት እና የሲኦል ገጽታ ምን ይመስል ይሆን? ሰው ከሞተ በኋላ “በምድር ሳለህ ጥሩ ከውነሀልና ገነት ትገባለህ!” ሲባል እንዴት ያለ ቦታ ይሆን የሚገባው? በተቃራኒው “ስትበድል ኖረሃልና መዳረሻህ ሲኦል ነው!” ሲባልስ እንዴት ያለ ቦታ ይሆን የሚጣለው? ገነት ማለት በልምላሜ ያማረ ፣ ምንም ነገር ተፈልጎ የማይታጣበት ፣ መሻት ሁሉ የሚፈጸምበት ቦታ ይሆን? ሲኦል ማለትስ የማይበርድ ፍም ያለበት ፣ የሚንቀለቀል እሳት የሞላበት ቦታ ይሆን? ቢሆን ብንል… ሲኦል በስቃይ የተሞላች ፣ ገነት ደግሞ ስልቹነት የሚያጠቃው ቦታ ይሆን ይሆን? እሳት ውስጥ መጣል ለስቃይ እንደሚዳርግ የሚያጠያይቅ እንዳልሆነው ሁሉ ገነት ውስጥ መኖርም እንደሚሰለች ግልጽ አይሆን ይሆን? ምኞት ሲሰምር ፣ መሻት ይፈጸም ዘንድ ልፋት አልጠይቅ ሲል ፣ ሁሉ በእጅ ሁሉ በደጅ ሲሆን ስልቹነት መከተሉ ይቀር ይሆን? ስልቹነት ያጠቃው ሕይወት ገነት ሲኦል አይሆንበት ይሆን? "ዛሬ ቅዳሜ አይደለም"
Show all...
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!