cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ethio zodiac/ ዞዳይክ

ኮኮብዎን መዋቅ ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ ይሄን ቻናል ይቀላቀሉን ይወዱታል አይቆጩበትም ♥️♣️♦️ … … … … ማንኛውንም አስታየት ሆነ ጥያቄ በ @zoskales_13 መጠየቅ ትችላላቹ

Show more
Ethiopia406Amharic361The category is not specified
Advertising posts
46 904Subscribers
+324 hours
-437 days
-19230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የዞዳያኮች ደስታ ቪርጎ (ከነሀሴ 17 እስከ መስከረም 12) - ቪርጎዎች ጣፋጭና ዝምታኛ ናቸዉ፣ ግን እያንዳንዷ ትናንሽ ነገር አታመልጣቸዉም፣ በዉል ይከታታሏታል። ጎበዝ አድማጭና ተንታኝም ስለሆኑ፣ ቁም ነገር ያለዉ ምክር መስጠት ላይ የተካኑ ናቸዉ። በአብዛኛዉ ደስተኞች፣ ነገር ግን በቅርባቸዉ ካለዉ ሰዉ ጋ ከተቀያየሙ፣ ደስታ ይርቃቸዋል፣ ይከፋሉ። - ማንንም ለማስደሰት መጣር የለባቹም፣ ራሳቹ ላይ ትኩረት አድርጉ። ብቁና ምክንያታዊ በራስ መተማማን እንዲኖራቹ ያደርጋቹዋል። እንዲሁም ሚሰማቹንም በግልጽነት መናገር፣ ከለአላስፈላጊ ጭንቀትና ደስታ ማጣት ይከላከላቹዋል። ዘና ማለትና መዝናናትን አካላቹ በደንብ እንዲፍታታ፣ ዐእምሯቹ በደንብ እንዲያስብና የፈጠራ ክህሎቱንም እንዲያሳድግ ያግዘዋል። አንድ አንዴ ፍልስፍናቹንና ስለውደፊት ማሰብ ትታቹ አሁንን ብቻ አስቡ። ምግብ መስራት፣የጓሮ አትክልት መንከባከብ፣ ሲኒማ ማየት፣ ለየት ያሉ ምግቦችን መሞከርና በፊት የረሳቹትን አርት ለመስራት ሞክሩ። - ሁሉንም ጥፋታቹን ወደ ራሳቹ በመዉሰድ ራሳቹን እንደ ጥፋተኛ አትዩ፣ ምክንያታዊነት ለናንተም ሆነ ለአጋራቹ ጠቀሜታ አለው፣ ሚሰማቹን ያለምንም መወዛገብ ጨዋ በሆነ መንገድ ግለጹ። ቪርጎዎች መስራት ሚትፈልጉትንና የተሰሩ ስራዎችን ሊስት ማየት ደስ ይላቸዋል፣ ብዙ ግዜም ቼክ ያደርጋሉ፣ ይሄም ስለሚሰሩት ስራ ጥንቅቅ ያለ ግንዛቤ እንዲኖራቸዉ ይረዳቸዋል። - ቪርጎዎች መጀመሪያ ላይ ሲታዩ ምንም ከሰዉ ሚግባቡ አይመስሉም፣ ትንሽ ግዜ ብቻ ስጧቸው፣ በደንብ ይግባባሉ፣ ሀሳባቸዉንም በነጻነት ይገልጻሉም ያወያያሉም። አእምሯቸዉን በደንብ ማለማመድና ማስሞከርን ይወዳሉ፣ ጫዎታዎችና ካልኩሌሽኖች ሊሆኑም ይችላል። ቪርጎዎች በራሳቸው ዛቢያ ፈታ ማለትን ይወዳሉ፣ ደስታ ከራቃቸዉ ግን ማንም አጠገባቸዉ ድርሽ እንዲል አይፈልጉም፣ ድንበራቸዉ ጠንከር፣ ፊታቸዉም ፈካ አይልም፣ ሰዉንም ለማስከፋት ቅርብ ይሆናሉ። ለራሳቸው ያላቸዉ ግምትም ይወርዳል። . . . . . . . . . ማንኛውንም አስታየት ሆነ ጥያቄ በ @zoskales_13 ማድረስ ትችላላቹ  ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ 👉🏼@zodiac_channels
Show all...
👍 156 77 21❤‍🔥 15🍓 13😡 9🆒 7🌚 6🍾 6👏 4🤝 2
የዞዳያኮች ደስታ ሊዮ (ከሀምሌ 16 እስከ ነሀሴ 16) - ሊዮዎች ሁሌም ቢሆን ፖዛቲቭ አከባቢን አንዲፈጠር ሚተጉ ሰዎች ናቸው፣ ምንም አይነት ሁኔታ ዉስጥ ቢሆኑ፣ የተሻለ ከባቢ እንዲፈጠር ይተጋሉ፣ በዚህም ደስታን ስለሚፈልጓት፣ ደስታን ያገኗታል። ከናንት በላይ ላሉ ስራዎች ትኩረት ስጡ፣ ባትደርሱበት እንኳን መሞከራቹ ደስታን ይሰጣቹዋል። በጎ አድራጎት ላይ መሳተፍ፣ ምንም ያልተሞከሩ ማንኛዉም ሙከራዎችን መሞከር፣ ዳንስና ትይንቶች ላይ መሳተፍ ሀሴትን ትጎናጸፉበታላቹ። - ሁሌም ቢሁን የፈጠራ ክህሎታቹንና ራሳቹን መግለጽ ምትችሉበት ቦታ ላይ ስትሆኑ የበለጠ ደስተኛ ትሆናላቹ። አርቲስቲክ የሆኑ ሩመሮችም ሆነ ቦታዎች ላይ ስትሆኑ ሙዳቹ ቡስት ይሆናል፣ በቂ ጸሀይ ማግኘትም እንደዛዉ። ሊዮዎች ተነሳሽና ብቃት ያላቸዉ ስዎች ሲሆኑ፣ በዛዉም ልክ ግን በእቅድ ሚመሩና ነገሮችን መዛኝ ናቸዉ። የሰሩት ስራ ተቀባይነት እንደማግኘትና በብዙዋን ሰዎች እዉቅና እንደመሰጠት ደስታ ሚሰጣቸዉ ነገር የለም። - አነስ ያለች ድራማ ይወዳሉ፣ ሲበዛ ግን ይሰላቻሉ። በሚወዱት ማንኛዉም ፊልምም ሆና መጻፍ ዉስጥ ሁሌም ከኣአምሯቸዉ ማይጠፋ ገጽ ወይም ሲን አለ። በሚገርም ሁኔታ ከሚጨበጡ ሆነ ከሚዳስስ ነገሮች፣ ሌሎች ለነሱ ሚያሳዩት ታማኝነት የበለጠ ይማርካቸዋል፣ ይገዛቸዋል። - ሊዮዎች ከጓደኞቻቸዉ ጋ በመሆን ስለ አዲስ ጀብድ እቅድ ማዉጣትና መሄድን ይወዳሉ። ትልቅ ሀዘን ዉስጥ ቢሆኑ እንኳን እንዴት ከዛ መዉጣት እንዳለባቸዉ ያዉቃሉ፣ ይወጣሉም። ይሄም ደስተኛ ያደርጋቸዋል። አሪፍ ሁኔታ ላይ ካልሆኑ፣ በስራ ቢዚ ይሆናሉ፣ ስራ ባይኖርባቸዉ እንኳን ቢዚ ሚያደርጋቸዉን ነገር ይፈልጋሉ፣ በዚህም ስለ ወቅታዊ ሁኔታቸዉ እንዳያስቡ ያደርጋቸዋል፣ ቀስ በቀስም ደስታቸዉ እየተመለሰ ይመጣል። . . . . . . . . . ማንኛውንም አስታየት ሆነ ጥያቄ በ @zoskales_13 ማድረስ ትችላላቹ  ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ 👉🏼@zodiac_channels
Show all...
👍 60 27🌚 4🆒 3🌭 2❤‍🔥 1
የዞዳያኮች ደስታ ካንሰር (ከሰኔ 14 እስከ ሀምሌ 15) - ካንሰሮች ከሌሎች በተለየ መልኩ፣ ብዙ ዑደትን ያሳልፋሉ። ታማኝ፣ ሚተማመኑባቸዉና አዛኝ ናቸው። ስሜታዊነታቸዉ በቶሎም ደስታና ሀዘን እንዲፈራረቅባቸዉ ያደርጋቸዋል። ነገር ግን ሁሌም ቢሆን ቀና፣ ብሩህና ተስፍ ሚያደርጉ ሰዎች ጋ ለማሳለፍ ቢሞክሩ፣ በጥሩም በመጥፎም ግዜ አብሯቸው ሚሆኑት ሰው ጋ ቢሆኑ፣ የዛኔ ዘና ይላሉ። ፖዘቲቭ አስተሳሰብ፣ ፖዘቲቭ ህይወትን ያመጣል። - ካንሰሮች ጤናማ የሆነ ምግብ ወዳጅ ናቸው፣ ከምግብነቱ ባለፈ ደስታን ጭምር ይሰጣቸዋል፣ ሲመገቡ ብዙ ማይስማማቸዉ ምግብ እንደመኖሩ መምረጥ ያስፈልጋቸዋል። ምግብ ላይ ጥሩ ከሆኑ፣ ስሜታቸዉም፣ ኣዕምሯቸውም፣ አካላቸዉም የተረጋጋና ደስተኛ ይሆናል። - ካንሰሮች በግዚያዊ ሚፈጠሩ ሁኔታዎች ደስተኞች አይደሉም። ሁኔታዎች ባይሳኩም ግብና ቀጣይ ስራዎች ትልቅ እንደሆኑ ማሰብ ይኖርባቸዋል፣ መደናገጥ አያስፈልግም። ያለፉበትን ትዝታዎች ማሰብ ያስደስታቸዋል፣ በተለይ ስለሚዎዱትና ስለሚያስገርማቸዉ ማንኛዉም ጥቃቅን ትዝታዎች አንደ ትላንት ያስታዎሱታል። ስዎች ስላለፉበትም የጉዞ ትዝታ፣ የሙዚዬም ትዝታ፣ የፍቅር ትዝታም ሆነ ገጠመኞችን መስማትን ይወዳሉ። - በማንኛዉም ሁኔታ ዉስጥ ብትሆኑ አስቀድሞ ማንኳኳቱና እነሱን ቼክ ማድረጉ ጠቀሜታ አለው፣ ለናንትም ለነሱም። ከቅርብ ጓደኞቻቸዉና ቤተሰቦቻቻዉ ጋ ጥብቅ ሚባል ቁርኝት አላቸው፣ ደስታ በማይሰማቸው ብዙዉን ግዜ ከነሱ ጋ ቢያሳልፉ ይመርጣሉ፣ ዘና ያደርጋቸዋል። ካንሰሮችን በጣም ጥቃቅን ሚባሉ ነገሮች ይረብሻቸዋል፣ ረፍትም ይነሳቸዋል። . . . . . . . . . ማንኛውንም አስታየት ሆነ ጥያቄ በ @zoskales_13 ማድረስ ትችላላቹ  ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ 👉🏼@zodiac_channels
Show all...
👍 59❤‍🔥 17 15👏 7🆒 6🥰 1
የዞዳያኮች ደስታ ጄሚናይ (ከግንቦት 14 እስከ ሰኔ 13) •  ጄሚኒዎች ሁሌም ቢዚ ናቸዉ፣ በጣም ንቁ ሁሌም ቢያንስ ሁለት እርስ በእርሱ ሚጋጭ ሀሳቦች በዉስጣቸዉ አለ፣ በዚህም ራሳቸዉን ካለዉ ሁኔታ ጋ ለማስማማት በሚያደርጉት ጥረት ጭንቀት ዉስጥ ይገባሉ፣ ደስታም ይርቃቸዋል። ቢሆንም ግን በደስተና በሀዘን መሀል፣ በመምረጥና በለመምረጥ፣ በመሄድና ባለመሄድ ማሃል ባለችው ትንሽ እፎይታ ዉስጥ ሚያገኙት ደስት ወደር አይኖረውም። •  አጭርና ያልተሰማ ቀልድና ትምህርታዊ ቁም ነገር ያለው ንግግር ያስደስታቸዋል፣ በዛዉም የጄሚኒንም ትኩረት ለማግኘት ያቀላል። ጄሞች ጥልቅና ረዘም ያሉ ንግግሮችን ከቅርቦቻቸዉ ጋ ቢያደርጉ አሪፍ ነዉ፣ ዉስጣዊ ሰላምም ደስታም ያገኙበታል፣ ትክክለኛዉንም ያዉቁበታል። አላስፈላጊ ዉስብስብ ነገሮች ዉስጥ መግባት አያስፈልጋቸዉም። በአከባቢያቹ ሰላማዊ ተሟጋች ሰዎች ሲኖሩ፣ አዳዲስ ነገሮችን ለመሞከር ዘግጁ የሆኑ ሰዎች ሲኖሩ፣ ስለማንኛውም ነገር ለማውራት ፍቃደኛ የሆኑ ስዎች ሲኖሩና ብዙ የሀሳብ ልዩነት ያለበት አከባቢ ሲሆኑ ጄሞዎች ደስተኛና የበለጠ ንቁ ይሆናሉ። •  ጄሞዎች መከፋትን አይፈልጉም፣ ሲከፉ ለማንኛዉም ደስታ ሚሰጣቸው ትይንት ራሳቸውን ክፍት ያደርጋሉ፣ በተቻላቸዉ መጠን ካስካፋቸው ሀሳብ መውጣትን ይፈልጋሉ። ህይወት ለነሱ ምርጫ ናት፣ ሚፈልጉትን ህይወት መምረጥ እንደሚችሉ ያስባሉ። እንቆቅልሾችን መፍታት፣ ስላልተሰሙ ሚስጥሮች መስማትና ማዉራት፣ የችግሮችን አፈታትና ሂደት ላይ ሀሳብ መስጠትና ማውራት ያስደስታቸዋል። እዉቀቱም አላቸዉ። ትልቁ ጠላታቸው ድብርትና ድብርት ነዉ። ሚሰጡት አስታየትና ምክር በቁም ነገር ሲታይና መሬት ላይ ሲወርድ ደስ ይላቸዋል፣ እንደዛ እንዲሰማቸዉ ካደረጋቹ፣ አንድ ደስተኛ ጄሚኒ በእጃቹ ላይ አለ ማለት ነዉ። ጄሞዎች ተስፋ መቁረጥን ሳታስቡ፣ በደንብ ደስተኛ ለመሆን አንገታቹን በጉም ዉስጥ እግራቹን ግን መሬትን በደንብ መርገጥ አለበት። የዞዳይኩ ተግባቢዎች ሲሆኑ፣ ከሰዎች ጋ መግባባትም ሆነ መተዋዎቅ ያስደስታቸዋል፣ ግን አሪፍ ሁኔታ ላይ ካልሆኑ ድካምና መሰልቸት ይታይባቸዋል። ጄሞዎች በደስታ ዉስጥ ሲሆኑ የፈጠራም ሆነ የመግባባት ክህሎታቸዉ ይጨምራል። . . . . . . . . . ማንኛውንም አስታየት ሆነ ጥያቄ በ @zoskales_13 ማድረስ ትችላላቹ  ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ 👉🏼@zodiac_channels
Show all...
👍 122 56❤‍🔥 21 18🆒 7🍓 4🌭 3🍾 3🌚 2🤩 1
የዞዳያኮች ደስታ ቶረስ (ከሚያዝያ 13 እስከ ግንቦት 13) •  ቶርሶች የሮማንስ፣ የምግብና ማንኛዉም ሚያምርና ቅንጡ ነገር ወዳጅ ናቸዉ። ዙሪያቸዉም በምኞት የተሞላ እንዲሆን ይፈልጋሉ። ድርቅናቸውና በሚጠብቁት ልክ ምላሽ አለማግኘታቸው ግን ድብርት ውስጥ እንዲገቡ ያደርጋቸዋል። ደስተኛ ለመሆን የግድ እርግጥ የሆነ ፍቅር ግንኙነት ዉስጥ መግባት አያስፈልጋቹም፣ ዋናው ግንኙነት በናንተ፣ በአዕምሯቹና፣ በውስጣቹ ያለውን ግንኙነት አንድ ማድረግ ነዉ። በዚ ግዜ በጣም ተነሳሽ፣ ተወዳጅና ጅብድ የሞላበት ህይወት ይኖራቸዋል። •  በቻላቹት መጠን ቤታቹን ማስዋብና በምትፈልጉት መንገድ ለማስተካከል ሞክሩ፣ እንዲሁም አበባ መትከልም ሆነ ምትወዱትን እንስሳ ማሳደግ ተፈጧራዊ ደስታን ይሰጣቹዋል። ችግሮችን እንዳለ ወደ ራሳቹ አትዉሰዱ፣ ራሳቹንም አትዉቀሱ፣ ይሄንን ደጋግማቹ ታደርጋላቹ። ከቤታቸዉ ብዙም ሩቅ ያልሆን መዝናናትን ይወዳሉ፣ ሩቅ ቦታ መሄድ አይፈልጉም፣ ገጠርና የተለየ ቦታ ካልሆነ በቀር፣ እሱንም በምርጫ ነዉ። ቁስ ይስባቸዋል፣ ንጹ ደግነትም ልባቸዉን ለማሸነፍ ቅርብ ነዉ፣ ጠንክረዉ ለሚሰሩት ስራም ሲበረታቱ ደስ ይላቸዋል። •  የተረጋጉ፣ ወግ አጥባቂና እዉነተኞቹ ቶረሶች እነሱ ሚፈልጉት መንገድ ላይ ለመድረስ ቃላል መንገድ አይጓዙም። ጥሩ ገንዘብ ማግኘት ይፈልጋሉ፣ ለሱም  ሁሌም ተነሳሽ፣ ሁሌም ዝግጁ ናቸዉ። ከዛም ምግብ፣ መዛነጥና ጥሩና አስተማማኝ ህይወት መኖር ይፈልጋሉ። ሚፈልጉትን እቃ መሸመት እንዲነቃቁና ወደ ጥሩ ሙድ እንዲመጡ ያደርጋቸዋል። ቶረሶች ሚወዱት ሆነ ትንሽ ሞልቀቅ ሚያደርጋቸዉ ሰዉ ጋ ሲሆኑ ደስተኛ ናቸዉ። . . . . . . . . . ማንኛውንም አስታየት ሆነ ጥያቄ በ @zoskales_13 ማድረስ ትችላላቹ  ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ 👉🏼@zodiac_channels
Show all...
👍 89 33❤‍🔥 22🍓 2🆒 2🤩 1
የዞዳያኮች ደስታ ከመጋቢት 12 እስከ ሚያዚያ 12 ለተወለዱ (ኤሪስ) •  ኤሪስ ዞዳይክ ያላቸዉ ሰዎች፣ሕይወት ላይ ፈታ ያሉ ለመዝናናትም ቅርብና መጨናነቅ ማይወዱ ሰዎች ሲሆኑ፣ በማንኛውም ግዜና አጋጣሚ ቀልድን ሚፈጥሩና ሚፈልጉ ናቸው። በዚህም ምክያት አከባቢያቸው ቀልድ አይጠፋም። ለዚህም ይመስላል ደስታ ሲጠፋ በቶሎ ድብርት ውስጥ ሚገቡትና ለማዘንም ቅርብ ሚሆኑት፣ ደስታ እነሱ ጋ ትልቅ ቦታ አለው። •  ማንም ሰዉ ፍጹም አይደለም እናንተም ብትሆኑ አይደላቹም እሱን ማዎቅ አለባቹ። ሁልግዜም በማንኛውም ነገር፣ በማንኛዉም ሁኔታ ዉስጥ ሆናቹ አንደኝነትንና ፉክክርን በማሰብ ብቻ ዉስጣቹን አታስጨንቁ። ራሳቹን ማስጨነቅ ስታቆሙና ሁሉንም ፉክክር ማድረግ ማቆም ስትጀምሩ፣ አካሄዳቹን ማስተካከል ትጀምራላቹ፣ አካሄዳቹ ሲስተካከል፣ ደስተኛ መሆን ትጀምራላቹ። •  መሮጥ ከወደዳቹ ተነሱና ሩጡ፣ ዋና ምትወዱም ከሆነ ለመዋኘት ሞክሩ፣ ሳይክልም ምትነዱ ከሆነ ተነሱና ለመንዳት ሞክሩ ግን አትቀመጡ። ኤሪሶች ለድርጊት፣ ለአካል እንቅስቃሴና ዉድድር የተፈጠሩ ናቸዉ፣ ዘና ያደርጋቸዋል፣ ካልሆነ ብኩንነት ይሰማቸዋል። ቀጥሎ ለማይታዎቅ፣ አጓጊና ዉድድር ላለበት ማንኛዉም ነገር ዝግጁና ጉጉ ናቸው፣ ደስታን ያገኙበታል። •  በተፈጥሯቸው ዘና ያሉና ለደስታ ቅርብ፣ በቀልድ ዉስጥ ሌላ ቀልድ፣ በቀልድ ዉስጥ ሌላ ስላቅ መፍጠር ይችላሉ። ነገር ግን በአከባቢያቸዉ ባሉ ሰዎችና ቦታ ደስተኛ ናቸው ማለት አይደለም። ስልጣናቸውንም ሆነ ብቃታቸውን በደንብ ማሳየት ሚችሉበት ማንኛውም ቦታ ለነሱ ደስታን ይፈጥራል። ደስታቸዉም ጥንካሪያቸዉን በእጥፍ፣ ቅልጥፍናቸዉን በብዙ፣ ፍጥነታቸዉንም ደብል ያደርገዋል። ድካምም ስለማይሰማቸው፣ በአንዴ ብዙ ስራ እንዲሰሩ ያደርጋቸዋል፣ ይሄን ሀይል ከየት እንደሚያመጡት ማስገረሙም ማይቀር ነዉ። . . . . . . . . . ማንኛውንም አስታየት ሆነ ጥያቄ በ @zoskales_13 ማድረስ ትችላላቹ  ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ 👉🏼@zodiac_channels
Show all...
👍 116 24❤‍🔥 14🆒 10💯 6 3🔥 2🎉 2🍾 2🤝 2👏 1
ሰላም ሰላም? ዞዳይኮች እንዴት እንደሚደሰቱና ምን የበለጠ ያስደስታቸዋል ሚል ፕሮግራም ከነገ ጀምሮ ፖስት ማድረግ እንጀምራለን፣ እስከዛ ብዙ ሰዉ ጋ እንዲደርስ የናንተ ድጋፍ ያስፈልገናልና ለወዳጆቻቹ ሼር እያደረጋቹ። ሌላ አንዲቀርበላቹ ምትፈልጉት ርዕስ ካለም @zoskales_13 ይንገሩን፣ እናቀርባለን። @zodiac_channels
Show all...
👍 180 15🆒 12 11
እስቲ ስለ ዞዳይክ 2 ፓይሰሶች የከረረና ሲሪየስ የሆነ ክርክር ሲገጥማቸው እንባ እንባ ይላቸዋል፣ አኳሪየሶች ሳይፈልጉ ቤታቸውን ትተው ከሰው ጋ እንዲጫወቱ ከሚያደርጓቸው ቢሞቱ ይቀላቸዋል፣ ካፕሪኮርኖች ሳያስቡት ስለ ራሳቸው ብዙ ኢንፎርሜሽን ከተናገሩ ሙሉ ቀን ቅር ቅር ሲላቸው ይውላል፣ አንድ አንዴ ሳጆች ከድብርት ለመላቀቅ ኦን ላይን ላገኙት ሰው እንደለ ቴክስት ሊልኩ ይችላሉ፣ ስኮዎች አንድ ሰው ረብ የለሽ ወሬ ደገግሞ ሲያወራቸው ይመራቸዋል፣ ሊብራዎች በጀመሩት ርዕስ ሰዎች ሲከራከሩ ማየት ደስ ያሰኛቸዋል፣ ቪርጎዎቸ የሆነ ሰው ከልቡ እነሱን ለማወቅ ከሞከረ ላብ ላብ ይላቸዋል፣ አብዛኛውን ግዜ ሊዮዎች ከተበሳጩ ከነገሩ በላይ ተናግሬ ይውጣልኝ ወይስ ባልሰማ ዝም ልበል ሚለው ረጅም ግዜ ይወስድባቸዋል፣ ካንሰሮች ሲከፉ እናታቸው ጋ ደውለው ያለቃቅሳሉ፣ ባያለቃቅሱ እንኳን ቢያንስ ይደውላሉ፣ ጄሚኒዎች ግሩፕ ቻት ላይ እያወሩ፣ ዝም ካሏቸው ቅር ይሰኛሉ፣ ቶረሶች አዲስ የስራ ቦታ ላይ እንዴት ማሽቃበጥ እንዳለባቸው አያቁም፣ ባልተጠየቁት ነገር ላይ ማንም ሰው ስለነሱ አስታየት እንዲሰጣቸው ኤሪሶች አይፈልጉም። . . . . . . . . . ማንኛውንም አስታየት ሆነ ጥያቄ በ @zoskales_13 ማድረስ ትችላላቹ  ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ 👉🏼@zodiac_channels
Show all...
👍 111 25🆒 8👏 7🎉 6 3
🔚
Show all...
11👍 7
(የዞዳይክ ሁለት ገዝጣዎች) ፓይሰስ አንደኛው ጎን •  ፓይሰሶች እንደ ካንሰሮች ስሜታዊ፣ ስስ፣ አዛኝና በፈጠራ የተካኑ ናቸው። ማንኛዉንም ምርጥ ጓደኛ ሆነ ተጣማሪን መሳብ ይችላሉ። አዛኝና ከነሱ ጋር ርጅም መንገድ መጓዝ ለሚችሉ ሰዎች ላይ ይመሰጣሉ። የሰዉን ችግር አይቶ መረዳት ይችላሉ፣ ከላይ የተሰጣቸው ነው። ለሚወዱት ሰው ታማኝና እስከ መጨረሻ ድረስ አይለዯቸውም። •  ሥስነታቸዉ የሰዎች ችግር ሆነ ፈተና በቶሎ እንዲገባቸዉና ደራሽ ያደርጋቸዋል። የነሱ መኖርም በአከባቢያቸው ያሉትን ሰዎች ማረጋጋት እንዲችሉ አስተዋጾ አለዉ። ሌላኛዉ ጎን •  አለም ሁሉ ከሚያዉቀው እዉነታ ጋር ሲጋፈጡ ማየት የተለመደ ነው፣ አምኖ ለመቀበል ሲቸገሩ ይታያሉ። ብቻቸዉን ለመሆን ከሚወስዱት ረዘም ያለ ግዜ በመነሳት፣ ብቸኝነት ያጠቃቸዋል። ከምናብ አለማቸውም ወደ አለማዊዉ አለም ለመመለስ ይከብዳቸዋል። •  ሌሎች ለናንተ ክፍት ሆነዉ እንደሚያወሩት፣ እናንተም ስሜታቹን ግልጽ አድርጋቹ ማዉራት መቻል አለባቹ፣ ማንም ሰው እናንተን አይቶ ስሜታቹን አያነብም። . . . . . . . . . ማንኛውንም አስታየት ሆነ ጥያቄ በ @zoskales_13 ማድረስ ትችላላቹ  ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ 👉🏼@zodiac_channels
Show all...
👍 44 25😱 2💋 1