cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Meleket Tube

መንፈሳዊ መረጃዎችን እንዲሁም ዝማሬዎችና የወንጌል ትምህርቶች በየእለቱ ከዚህ ገፅ ያገኛሉ። ኢየሱስ በክብር ይመጣል! Find us on more- https://linktr.ee/meleket_tube Contact us - @LiveMeleket_Bot

Show more
Ethiopia1 569The language is not specifiedReligion & Spirituality6 686
Advertising posts
12 470Subscribers
-1124 hours
-487 days
-15430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

https://t.me/notcoin_bot?start=r_577266_33236117 🎁 +2.5k Notcoin as a first-time gift 🎁🎁🎁 +50k Notcoin if you have Telegram Premium @PremiumBot
Show all...
Notcoin

Probably nothing @notcoin

#ካውንስሉ_አስቸኳይ_መግለጫ_ሰጠ በወንጌላዊያን አማኞች እና አብያተክርስቲናት ላይ እየደረሰ ስላለዉ ጥቃት ህዳር 27 ቀን 2016ዓ/ም መግለጫ_ሰጠ። 1-ባለፋት ዘመናት በተለይ በደርግ ዘመን የተወረሱ የቤተክርስቲያን ይዞታዎች በኢሕአዴግ ዘመን በከፊል ቢመለሱም እስካሁን ያልተመለሱ የኦሎምፒያ መሰረተክርስቶስ፣ የአዲስ ከተማ ገነት፣ የኢትዮጵያ ወንንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ብረት የሆነው የጉድ ሼፐርድ ማዕከል ፣ቄራ አካባቢ ያለው የብርሃነ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አዳራሽ፣እና ሌሎች እስካሁን ያልተመለሱ ይዞታዎች ሲሆኑ እነዚህ ይዞታዎች የቤተክርስቲያን ንብረት በመሆናቸዉ እንዲመለሱ ተጠይቋል። 2-የድሬዳዋ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ ይዞታዋን ለቃ እንድትነሳ የከተማዉ አስተዳደር የወሰንኑ ቢሆንም የከተማዉ አስተዳደር እና የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች እንዲሁም የካውንስሉ አመራሮች ሰፊ ዉይይት አድርገዉ የከተማዉ አስተዳደር ጉዳዩን እየመከረበት ይገኛል።የከተማዉ አስተዳደር የደረሰበትን ደረጃ በአጭር ጊዜ ግልፅ እንዲያደርግ ተጠይቋል። 3-የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ይዞታ ነጥቆ የራሱ ጽህፈት ቤት አድርጎት ይገኛል።እንዲሁም የቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን ይዞታ የሆነዉን የኩሪፍቱ የጸሎት ማዕከል በተመለከተም በማእከሉ ምንም አይነት የልማት ስራ ቤተ ክርስቲያን እንዳታከናወን በማገድ የቤተክርስቲያኑን ይዞታ ለመንጠቅ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝኝ ተገልጾ የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ከዚህ ህገወጥ ድርጊቱ እንዲቆጠብ እና የወሰደዉን የቤተክርስቲያን ንብረት እንዲመልስ ተጠይቋል። 4-በአዲስ አበባ ዙሪያ ባለችው የሸገር ከተማም የፈረሱ የወንጌላዊያን የእምነት ተቋማት ይዞታቸዉ እንዲመለስ እንዲሁም በከተማዋ ለ23 አብያተክርስቲያናት ከካቢኔ ቦታ ተወስኖላቸዉ ቦታቸዉን መረከብ ላልቻሉ በአፋጣኝ ካቢኔ የወሰነዉ ዉሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን ተጠይቋል። 5-የመቃብር ስፍራን ጥሶ በመግባት እየተደረገ የሚገኘዉ አግባብ ያልሆነ ተግባር በአስቸኳይ እንዲቆም 6-በምዕራብ ኢትዮጵያ በቄለም ወለጋ ዞን በጊዳሜ ወረዳ ዘጠኝ ምእመናንን የአምልኮ ስነስርአት እየፈፀሙ ካሉበት ሌሊት ላይ ተወስደዉ መረሸናችው እጅግ አሳዛኝ እንደሆነና ለነዚህ ንፁሃን ፍትህ እንዲሰጥ ተጠይቋል። በአጠቃላይ ፍትህ ያስፈልጋል ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት ሊከበሩ ይገባል ይህ ሁሉ እየሆነ ያለዉ የታችኛዉ የመንግስት አካል የመንግስትን ስልጣን በመጠቀም ጥቂት ግለሰቦች የግል አጀንዳ ይዘዉ የሚፈፅሙት ተግባር ነዉ። የፌደራል መንግስት ጣልቃ በመግባት ፍትህ ሊያሰፍን ይገባል ሲል የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል በመግለጫዉ አስታዉቋል።
Show all...
👍 14
ኢየሱስ ይፋዊ አገልግሎቱ እስኪደርስ ድረስ በየት ከተማ ውስጥ ነበር ሲጠብቅ የቆየው?Anonymous voting
  • ቤተሳይዳ
  • ገሊላ
  • ቅፍርናሆም
  • ናዝሬት
0 votes
16
አስደሳች ዜና! እንደ "ዴስፓሲቶ" እና "ጋሶሊና" በመሳሰሉት በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂው ሙዚቃዎቹ የሚታወቀው የአለማዊ ዘፈን አቀንቃኝ የነበረው የፖርቶ ሪኮ ራፐር ዳዲ ያንኪ ህይወቱን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለመስጠት እንደወሰነ እና ከአለማዊው ሙዚቃ እራሱን እንዳገለለ አሳውቋል። "እንደ ሙዚቃ፣ ማህበራዊ ሚዲያ፣ መድረኮች፣ ማይክራፎን ኢየሱስ የሰጠኝ በእጄ ውስጥ ያሉኝ መሳሪያዎች ሁሉ አሁን ለመንግስቱ ነው ሲል ተናግሯል።" Join➴ @MELEKET_TUBE
Show all...
👏 18 8👍 5🙏 3😢 1
Godina Qellem Wallagaa, Aanaa Gidaamiitti ajjeechaa Amantoota irratti raawwate ilaalchise Ibsa WKWW Mekane Yesus Itiyoophiyaatiin kenname. Sadaasa 24-2016 ህዳር 25 ቀን 2016 የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በቄለም ወለጋ ዞን በተለይም በጊዳሚ አውራጃ በአባላቶቹ ላይ የተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል።
Show all...
👍 6😢 3 1
ራሴን ስመለከት እንዴት ልድን እንደምችል አይታየኝም ክርስቶስን ስመለከት እንዴት ልጠፋ እንደምችል አይታየኝም፡፡
ማርቲን ሉተር
Show all...
11
♦#የልሳን_(#የቋንቋ)#ስጦታ♦ =========================== 📌 1 ቆሮ 14:40 #ነገር ግን ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን። 👉#ልሳን ማለት ምን ማለት ነው? -------------------------- ✍️አዲስ ኪዳን በተጻፈበት በግሪክ ቋንቋ ግሎሳ (γλῶσσα) የሚል ቃል ሲሆን “ልሳን" የሚል ፍቺ ይዟል። ይህም ምላስንና ቋንቋን የሚያመለክት ነው። ✍️ከዚህ የተነሳ ልሳን ማለት ቋንቋ ማለት ሲሆን መንፈስ ቅዱስ ለክርስቶስ አካል(ለቤተክ) ጥቅም እንደወደደ እያካፈለ ለቅዱሳን ከሚሰጣቸው ከብዙ የፀጋ ሥጦታወች መካከል አንዱ ነው። 1ቆሮ 12:7 ✍️ በልሳን(በቋንቋ) መናገር መንፈስ ቅዱስ ከሚሰጣቸው ብዙ ስጦታወች መካከል አንዱ ሲሆን የሰው ልጆች በሚሰሙት እና በሚናገሩት ቋንቋ ያለ ሰዋዊ ጥበብ (ልምምድ ) በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት መናገር እና ቅዱሳንን ማነጽ ነው። ✍️ የፀጋ ስጦታ ነው ማለት ተቀባዮ በየትኛውም ሰዋዊ ጥበብ እና ልምምድ ሊያገኘው የማይችለው ከእግዚአብሔር የሆነ ነፃ ሥጦታ ነው። ✍️ የትኛውም የፀጋ(ነፃ) ስጦታ ለአካል (ለቤተክ) ጥቅም የሚሰጥ እንጂ ለግል ጥቅምና ለማፍረስ የሚሰጥ እንዳልሆነ ልብ ልንል ይገባል ። ❤#ስለ_ልሳን_መጽሐፍ_ቅዱስ_ምን_ይላል፦ =================== የልሳን የጸጋ ስጦታ በብሉይም ዘመን ትንቢት የተነገረለት የጸጋ ስጦታ ነው። 📌ኢሳይያስ 28 11፤ በባዕድ አፍ በልዩም ልሳን ለዚህ ሕዝብ ይናገራል፤ 12፤ እርሱም፡— ዕረፍት ይህች ናት፥ የደከመውን አሳርፉ፤ ይህችም ማረፊያ ናት፡ አላቸው፤ እነርሱ ግን መስማትን እንቢ አሉ።(ዘዳ 58:49-50) ✍️በአዲስ ኪዳን ስለ ጸጋ ስጦታዎች አስቀድሞ ያስተማረው ኢየሱስ ነው። በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ የተለያዩ ምልክቶች(የጸጋ ስጦታወች) እንደሚከተሉአቸው ኢየሱስ ይናገራል፦ 📌 ማርቆስ 16:17 ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ #በአዲስ #ቋንቋ ይናገራሉ፤ እባቦችን ይይዛሉ፥ 🤔 ምልክቶች(የጸጋ ስጦታዎች) ቅዱሳንን የሚከተሉ እንጂ የሚቀድሙ እንዳልሆኑ አንባቢው ልብ ሊል ይገባል። 📌 ሐዋ. ሥራ 2:4- በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ #መንፈስም #ይናገሩ #ዘንድ #እንደ #ሰጣቸው #በሌላ #ልሳኖች(ቋንቋዎች) #ይናገሩ ጀመር፦ ይህም ድምፅ በሆነ ጊዜ ሕዝብ ሁሉ ተሰበሰቡ፥ እያንዳንዱም በገዛ ቋንቋው ሲናገሩ ይሰማ ስለ ነበር የሚሉትን አጡ። ተገርመውም ተደንቀውም እንዲህ አሉ፡— እነሆ፥ እነዚህ የሚናገሩት ሁሉ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን? እኛም እያንዳንዳችን የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋችንን እንዴት እንሰማለን? 🔥 ከተለያዩ ሀገሮች የመጡ አይሁዶች እና ወደ አይሁድ እምነት የተቀየሩ ሰዎች በዓለ 50ን ለማክበር በተሰበሰቡበት በተወለዱበት እና በሚኖሩበት ሀገር ከ 16 ባላነሱ በተለያዩ ልሳኖች(ቋንቋዎች) 120 የሚሆኑ አማኞች በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው የእግዚአብሔርን ታላቅ ስራ ተናግረዋል ብዙዎችም ወደ እውነት ተመልሰዋል። 📌 መንፈስ ቅዱስ እንደወደደ_እያካፈለ የጸጋ ስጦታን እንዴት እደሚሰጥ እና #ጌታ ኢየሱስ በጉባኤ ውስጥ ስርዓት ያለው አምልኮ ምን መምሰል እንዳለበት በሐዋርያው ጳውሎስ በኩል ለአብያተክርስቲያናት ሁሉ መመሪያ እና ድንጋጌ ይሰጣል፦ =========================== 📌 1 ቆሮንቶስ 12:10- 1 ለአንዱም ትንቢትን መናገር፥ ለአንዱም መናፍስትን መለየት፥ ለአንዱም በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፥ ለአንዱም በልሳኖች የተነገረውን መተርጎም ይሰጠዋል፤ ይህን ሁሉ ግን ያ አንዱ መንፈስ እንደሚፈቅድ ለእያንዳንዱ ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል። ✍️ ለአንዱም ይላል እንጅ ለሁሉም እንዳላለ ልብ እንበል። ስለዚህ ሁላችንም ልንናገር አንችልም። 📌 1 ቆሮንቶስ 14:27 ፤ በልሳን የሚናገር ቢኖር ሁለት ወይም ቢበዛ ሦስት ሆነው በተራቸው ይናገሩ አንዱም ይተርጉም፤ የሚተረጉም ባይኖር ግን በማኅበር መካከል ዝም ይበልና ለራሱና ለእግዚአብሔር ይናገር። ✍️ ይህ የጌታ ድንጋጌ መሆኑን ልብ እንበል በጉባኤ መካከል ሁለት ቢበዛ ሶስት ደግሞ በየተራ እና ተርጓሚ ከሌለ አይቻልም። ታድያ አሁን በየቤተክርስቲያኑ እየሆነ ያለው ነገር ምንድነው ሁላችንም እንጮሀለን የሚለውን ከየት አመጡት። 📌 1 ቆሮንቶስ 14:13 ስለዚህ በልሳን የሚናገር እንዲተረጉም ይጸልይ። 📌 1 ቆሮንቶስ 14 11 እንግዲህ የቋንቋውን ፍች ባላውቅ ለሚናገረው እንግዳ እሆናለሁ፥ የሚናገረውም ለእኔ እንግዳ ይሆናል። 📌 1 ቆሮንቶስ 14 :16 እንዲያማ ካልሆነ፥ አንተ በመንፈስ ብትባርክ ባልተማሩት ስፍራ የተቀመጠው የምትለውን ካላወቀ እንዴት አድርጎ ለምስጋናህ አሜን ይላል? 📌 1 ቆሮንቶስ 14:26 እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ምንድር ነው? በምትሰበሰቡበት ጊዜ ለእያንዳንዱ መዝሙር አለው፥ ትምህርት አለው፥ መግለጥ አለው፥ በልሳን መናገር አለው፥ መተርጐም አለው፤ #ሁሉ #ለማነጽ #ይሁን። ✍️ የትኛውም የጸጋ ስጦታ ዋና አላማው ቅዱሳንን ማነጽ እንጂ መዝረፍና መጉዳት አይደለም 📌 1 ቆሮንቶስ 14:39 ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ትንቢት ለመናገር በብርቱ ፈልጉ፥ በልሳኖች ከመናገርም አትከልክሉ፤ ነገር ግን #ሁሉ #በአገባብና #በሥርዓት #ይሁን። 📌 1 ቆሮንቶስ 14 33፤ እግዚአብሔርስ የሰላም አምላክ ነው እንጂ የሁከት አምላክ አይደለምና፤ በቅዱሳንም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንዲህ ነው። ❤ #ቅዱሳን_ሊጠነቀቁ_የሚገባቸው፦ ========================= ✍️ 1 #ቆሮንቶስ 3:18 #ማንም_ራሱን_አያታልል ..... 📌(1) ልሳን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እንጂ መንፈስ ቅዱስ አይደለም። 📌2) ልሳንን ሰዎች (አገልጋዮች) የሚሰጡት አይደለም ። 📌3) ልሳን ካልተናገርክ ምኑን ዳንከው በማለት የመድረክ አገልግሎት ለቅዱሳን መከልከል ተገቢ አይደለም። 📌4) ልሳን በልምምድም የሚገኝ አይደለም። 📌5) ልሳን ለሁሉም ሰው(አማኝ) የሚሰጥ አይደለም። 📌6) የኔ የመላእክት ልሳን ነው በማለት ራስንም ቅዱሳንን ማታለል ተገቢ አይደለም። 📌7) ሁላችንም ለ 10 ደቂቃ በልሳኖቻችን እናወራለን እያሉ የእግዚአብሔርን ጉባኤ መረበሽ መንፈሳዊነት አይደለ። 📌8)የኔ የማይተረጎም ልሳን(ቋንቋ) ነው በማለት እና ቋንቋ ያልሆነ ተደጋጋሚ ቃል በመደጋገም ቅዱሳንን ማወክ መንፈሳዊነትም መጽሐፍ ቅዱሳዊም አይደለም። 📌 1 ቆሮንቶስ 14 33፤ እግዚአብሔርስ የሰላም አምላክ ነው እንጂ የሁከት አምላክ አይደለምና፤ በቅዱሳንም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንዲህ ነው። 📌 1 ቆሮንቶስ 14 37፤ ማንም ነቢይ ወይም መንፈሳዊ የሆነ ቢመስለው ይህች የጻፍሁላችሁ የጌታ ትእዛዝ እንደ ሆነች ይወቅ፤ ፀጋ እና ሰላም ለሁላችን ይብዛ።
Show all...
👍 10 3
ትቤላ ኤልሳቤጥ ለማርያም ሶበሰማይኩ ቃለኪ አንፈራፀ እጓል በውስተ ከርስየ ወብፅይት አንቲ። እንተ ተአምኒ ዘነከሩኪ እፎኑ ይከውነኒ ከመትምፅኢ እሙ ለእግዚእየ። ሉቃስ ወንጌል 1:41-43
Show all...
2
#ይድረስ_ለወንጌል_አማኞች_በሙሉ.... (እባክዎ መልዕክቱን ሼር ያድርጉ) በቢሾፍቱ ከተማ የሚገኘው ኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ኩሪፍቱ ማዕከል የቃለህይወት ቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን የሁሉም ወንጌላውያን አማኞች ንብረት የሆነ፣ ብዙዎቻችን በግል እና በቡድን እየሄድን ለቀናት የፀለይንበት ስፍራ ነው። በዚህ ስፍራ ሄዶ ያልተገለገለ፣ ያልፀለዬ አማኝ ይኖራል ማለት ዘበትነው። በአዲሳባ ያሉ ሁሉም ቸርቾች ወጣ ብለው የሪትሪት፣ የፆምፀሎት ፣ የህብረት ጊዜ ማሳለፍ ሲፈልጉ የመጀመሪያም የመጨረሻም ተመራጩ ቦታ ይህ የኩሪፍቱ ቃለህይወት ነው። ይህ ስፍራ በከተማ አስተዳደሩ ከቸርች ተነጥቆ ለግለሰቦች ሊሰጥ መሆኑን በትናንትናው ዕለት ቸርቿ ይፋ አድርጋለች። ይህ የሁሉም አማኝ ቅርስ ከቤተክርስቲያን በግፍ ከመነጠቁ በፊት ሁላችሁም የወንጌል አማኞች ድምፃችሁን እንድታሰሙ ጥሪ እናቀርባለን። እባኮ መልዕክቱን ሼር ያድርጉ...
Show all...
👍 23👏 2
#ቤቱ_ራሱ_ይናገራል፤ ለጸሎት ቤት እንጂ ለሌላ አልተፈጠርኩም ይላል። በአዲስአበባ ከተማ ከ1954 ዓም አንስቶ የመጀመሪያው የመሠረተ ክርስቶስ ጸሎት ቤት በደርግ ያለሕግ ወርሶ ግቢውን ትምህርት ቤት "#የአብዮት_እርምጃ" ብሎ ሰየሙት ጸሎት ቤቱን ግን የስፖርት መሥሪያ አደረጉት። #ቤቱ_የጸሎት_ቤት_ይሁን!! #MKCchurch @meleket_tube
Show all...
👍 16
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!