cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

EthioipaNews

⚠️ Увага: надійшло багато скарг, що цей акаунт видає себе за відому особу чи організацію.

Show more
Advertising posts
30 324Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የጀማ ድልድይ ባልታወቀ ምክንያት መደርመሱ ተሰማ!! በሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ እንሳሮ እና መራሐቤቴን የሚያገናኘው አገር አቋራጭ የጀማ ድልድይ በቀን 27/7/2015 ዓ.ም ሁለት ሲኖ ትራክ ተከታትለው ሲሆዱ አንዱ ሲኖ ትራክ የውሃ መያዣ ቦቴ የጫነ ሲሆን አደኛ በዶውን ሲጓዝ ባልታወቀ ምክንያት ድልድዩ ሊደረመስ ችሏል። በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም። እንሳሮ ወረዳ የመንግስት ጉዳዮች ፅ/ቤት @EthioipaNews
Show all...
👍 103😢 24 22👎 17🥰 8😁 4👏 1
የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተወያዩ! የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡በውይይታቸውም÷ በሀገራቱ የድንበር አዋሳኝና ከቀጠናው የሰላምና ፀጥታ ሁኔታ አንፃር አብረው መስራት በሚገባቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ መክረው መግባባት ላይ መድረሳቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡የኤርትራ የጦር ጀነራሎችና ከፍተኛ መኮንኖች ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት እያደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡ @EthioipaNews
Show all...
👍 34👎 8 2🔥 1🍾 1
የአድማስ ሎተሪ እጣ መደብ ቁጥር 009 አሸናፊ እጣ ቁጥሮች ይፋ ሆነዋል!! 9ኛው ዙር የአድማስ ሎተሪ የሽልማት መጠን ወደ 3 ሚሊየን ከፍ ብሎ በትናንትናው እለት እጣው ወጥቷል። 1ኛ እጣ ሶስት ሚሊየን ብር የሚያስገኘው እጣ ቁጥር 0091844739 2ኛ እጣ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የሚያስገኘው እጣ ቁጥር 0090540530 3ኛ እጣ 8 መቶ ሺሕ ብር አሸናፊ እጣ ቁጥር 0092021699 4ኛ እጣ 4 መቶ ሺሕ ብር አሸናፊ እጣ ቁጥር 0090412316 5ኛ እጣ 2 መቶ 50 ሺሕ ብር አሸናፊ ቁጥር 0092260801 6ኛ እጣ 1 መቶ 50 ሺሕ ብር አሸናፊ እጣ ቁጥር 0090567816 7ኛ እጣ 1 መቶ ሺሕ ብር አሸናፊ እጣ ቁጥር 0091588711 8ኛ እጣ 50 ሺሕ ብር አሸናፊ እጣ ቁጥር 0090361764 9ኛ እጣ 30 ሺሕ ብር አሸናፊ እጣ ቁጥር 0090947970 10ኛ እጣ 25 ሺሕ ብር አሸናፊ ቁጥር 0090876951 በመሆን ወጥቷል፡፡ @EthioipaNews
Show all...
👍 36👏 4 3🤯 2🤮 1
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2015 ድረስ ባለበት ይቀጥላል‼️ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በመጋቢት ወር ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ እንዲቀጥል ተወሰነ። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለኢቢሲ በላከው መግለጫ፣ እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ የመሸጫ ዋጋ በመጋቢት ወር ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ እንዲቀጥል ተወስኗል። @EthioipaNews
Show all...
👍 9 4🙏 2
ነዳጅ ላኪ ሀገራት አቅርቦት ለመቀነስ መወሰናቸውን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ጨምሯል! የዓለማችን ግዙፍ ነዳጅ ላኪ ሀገራት ያልተጠበቀ የምርት ቅነሳን ይፋ ካደረጉ በኋላ የነዳጅ ዋጋ ጨምሯል። ያልተጣራ ድፍድፍ ነዳጅ በበርሚል ከ5 ዶላር ወይም ከ7 በመቶ በላይ ጭማሪ አሳይቷል። ይህንኑ ተከትሎ ያልተጣራ ድፍድፍ ነዳጅ በበርሜል ከ80 ዶላር ወደ 85 ዶላር ከፍ ብሏል። ጭማሪው የተከሰተው ሳዑዲ አረቢያ፣ ኢራቅ እና በርካታ የባህረ ሰላጤው ሀገራት በቀን ከአንድ ሚሊዮን በርሜል በላይ ከምርታቸው ላይ እየቀነሱ መሆናቸውን ተከትሎ ነው። ሩሲያ ዩክሬንን በወረረችበት ወቅት የነዳጅ ዋጋ ጨምሮ የነበሩ ቢሆንም አሁን ላይ ግን ግጭቱ ከመቀስቀሱ በፊት ወደነበረበት ተመልሷል። ይሁን እንጂ አሜሪካ የነዳጅ ዋጋን ዝቅ ለማድረግ አምራቾች ምርታቸውን እንዲጨምሩ ስትጠይቅ ቆይታለች። ባለፈው አመት ከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መደረጉ በመሰረታዊ ምርቶች ላይ ግሽበት እንዲፈጠር ማድረጉ ይታወሳል።የዩናይትድ ስቴትስ ብሄራዊ የጸጥታ ምክር ቤት ቃል አቀባይ ስለ ቅርብ ጊዜ የምርት ቅነሳ በሰጡት መግለጫ ቅነሳው በአሁኑ ጊዜ ጠቃሚ ነው ብለን አናምንም ይህንንም ግልፅ አድርገናል ብለዋል። የምርት ቅነሳው በኦፔክ የነዳጅ ዘይት አምራቾች አባላት ሀገራት እየተደረገ ይገኛል። የኦፔክ አባል ሀገራት ከዓለም ድፍድፍ ዘይት ምርት 40 በመቶውን ድርሻ ይይዛሉ። ሳዑዲ አረቢያ በቀን 500,000 ፣ ኢራቅ 211,000 በርሜል ያልተጣራ ድፍድፍ ነዳጅ ምርትን እየቀነሱ ይገኛል። የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ፣ ኩዌት፣ አልጄሪያ እና ኦማን ቅነሳ በማድረግ ላይ ናቸው። የሳውዲ ኢነርጂ ሚኒስቴር ባለስልጣን እርምጃው የነዳጅ ገበያውን መረጋጋት ለመደገፍ የታለመ የጥንቃቄ እርምጃ ማለቱን የሳውዲ ፕሬስ ኤጀንሲ ዘግበል። [ዳጉ ጆርናል] @EthioipaNews
Show all...
👍 20 1🔥 1🤯 1
ጀርመኖች በዓለም የመጀመሪያውን ፈጣን ቢራ ሠሩ። በቀላሉ ሁለት የሾርባ ማንኪያ የቢራ ዱቄት በብርጭቆ ውስጥ በማድረግና ከውሃ ጋር ቀላቅሎ በማማሰል ቢራውን ሰርተውታል። ቀማሾች ምርቱ የሚጣፍጥ እና ልክ እንደ መደበኛ ቢራ ነው ይላሉ። @EthioipaNews
Show all...
👍 10 3👏 2👎 1😁 1
አቡበከር ናስር ከጉዳት በተመለሰበት ጨዋታ ጎል አስቆጥሯል! ከሁለት ወራት በላይ በጉዳት ከሜዳ ርቆ የነበረው ኢትዮጵያዊው የማሜሎዲ ሰንዳውንስ አጥቂ አቡበከር ናስር ቡድኑ በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ኮተን ስፖርትን 2ለ1 በረታበት ጨዋታ በ62ኛው ደቂቃ ተቀይሮ በመግባት በ86ኛው ደቂቃ ሁለተኛው ጎል በስሙ አስመዝግቧል። @EthioipaNews
Show all...
33👍 10🔥 1
የዓለማቀፉ ወንጀል ፍርድ ቤት መመስረቻ ስምምነት ፈራሚዋ ደቡብ አፍሪካ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቱን ለ"ብሪክስ" አገራት የመሪዎች ጉባኤ ሲሄዱ እንደምታስተናግዳቸው ዛሬ በውጭ ጉዳይ ሚንስትሯ ናለዲ ፓንዶር በኩል አስታውቃለች። የዓለማቀፉ ወንጀል ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ፑቲን በዩክሬን "የጦር ወንጀል ፈጽመዋል" በማለት የእስር ማዘዣ ማውጣቱን ተከትሎ፣ በቀጣዩ ነሐሴ የ"ብሪክስ" አገራት የመሪዎች ጉባኤ አዘጋጇ ደቡብ አፍሪካ አቋሟ ምን እንደሚኾን በጉጉት ሲጠበቅ ነበር። ደቡብ አፍሪካና ሩሲያ በሌሎች አገራት ግፊት በድንገት ጠላት ሊኾኑ አይችሉም ያሉት ፓንዶር፣ ፑቲንን በጉባኤው እንዲገኙ እንደተጋበዙ ተናግረዋል። በዓለማቀፉ ፍርድ ቤት ስምምነት መሠረት፣ ደቡብ አፍሪካ ፑቲን ግዛቷን ከተረገጡ አስራ ለፍርድ ቤቱ የማስረከብ ግዴታ አለባት። "ብሪክስ" በፍጥነት በማደግ ላይ ያሉት ኃያላኑ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሩሲያ፣ ቻይና፣ ሕንድና ብራዚል የመሠረቱተ ቡድን ነው። @EthioipaNews
Show all...
👍 44👏 7🔥 2 1😱 1
ሰበር ዜና‼️ የክልል ልዮ ሀይል የተባለው ወታደራዊ አደረጃጀት መሉ በሙሉ እንዲፈርስ ትዕዛዝ ተላልፏል። ልዮ ሀይሉ ሲፈርስ ወደ መደበኛ መከላከያ ስራዊት የሚቀላቀሉ ሲሆን የቀረው መደበኛ ፖሊስ ሆኖ ይቀጥላል። ልዮ ሀይሉ የያዛቸውን የስራ ድርሻ ፌደራል ፖሊስና መከላከያ ስራዊት ይረከባቸዋል። አንድ ፖሊስ ( በፌደራል ፖሊስ ዕዝ የሚመራ) አንድ የኢትዮዽያ መከላከያ ስራዊት ብቻ ሆነው ይቀጥላሉ። @EthioipaNews
Show all...
👍 130👎 22 6👏 4🤔 4🤡 1🤣 1
ከዕስር ተፈቱ‼️ ኬሪያ ኢብራሂም፣ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ እና ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማ ከእስር ተፈቱ! በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል እና በጄነራል ታደሰ ወረደ መዝገብ ተከስሰው በእስር ላይ የነበሩ የህወሓት ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 21፤ 2015 አመሻሽ ላይ ከእስር መፈታታቸውን የተከሳሾቹ ጠበቆች አስተባባሪ የሆኑት አቶ አቶ ሃፍቶም ከሰተ ተናገሩ። በዛሬው ዕለት ከእስር ተለቅቀው ወደ ቤታቸው መግባታቸው ከተረጋገጡ ተከሳሾች ውስጥ፤ የህወሓት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ እና ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማ እንደሚገኙበት ጠበቃው አስታውቀዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር) @EthioipaNewss
Show all...
👍 35👎 12 3🔥 1