cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

blood of JESUS

ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንት ዛሬም እስከ ለዘላለምም ያው ። ዕብ 13፡8 በዚህ ሊንክ ያገኙናል @jacobbbbb

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
169Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

" የአባቴ ብልጠት" አንድ ቀን ወደ ትምህርት ቤት እየሄድኩኝ መንገድ ላይ አስገራሚና አስተማሪ ነበረ(የድሬ ዝናብ) መሬቱ አሸዋማ ቢሆንም አልፎ አልፎ ከጭቃ ጋር እየታገልኩ ስሄድ ሁለት ጎልማሳ ሰዎች ከፊት ለፊቴ ይሄዱ ነበር ። አንደኛው ሁለት ትንንሽ ልጆች ይዛል ልጆቹም ከፊት እየሮጡ አስቸገሩ አባታቸው "ተው ትወድቃላችሁ እኔ ልያዛችሁ" ቢላቸውም አሻፈረኝ አሉ ከዚያ አባትየው ትንሽ አሰላስሎ ለጋደኛው "አሁን እንዴት እደምይዛቸው ተመልከት" አለው ከዚያ አባትየው እየተንገዳገደ "ልወድቅ ነው ልጆቼ ያዙኝ" ብሎ ጭኸ ልጆቹም በፍጥነት አንዱ የግራ እጁን ሌላኛው የቀኝ እጁን ያዙት እርሱም ጠበቅ አርጎ ያዛቸውና ልጆቼ እንዳልወድቅ እጄን አትልቀቁኝ አላቸው እነርሱም እሺ አባዬ አሉት ይሄኔ አባትየው ዞር ብሎ ለጓደኛው አየህ እንዴት እንደያዝኩቸው ትወድቃላችሁ ልያዛችሁ ብላቸው አንወድቅም ብለው ይወድቃሉ ያዙኝ ብላቸው ግን እንይዘዋለን ብለው ይያዛሉ አለው ልያዛችሁ ብዬ ከማልይዛቸው ያዙን ብዬ ብይዛቸው ይሻልል አለው። በጣም ገረመኝ የአባትየው ብልጠት የሰማዩ አባቴን አስታወሰኝ የልጆቹ መረዳት አባታቸውን መያዛቸው ነው እውነቱ ግን እነሱ በአባታቸው መያዛቸው ነው። አገልግሉኝ ያለን ለካ ሊያገለግለን ፈልጎ ነው! ዘምሩልኝ ያለን ለካ ሊባርከን ፈለጎ ነው! ስጡኝ ያለን ለካ ሊሰጠን ፈልጎ ነው! እንጂማ የትኛውን ጉድለቱን ልንሟላ የትኛውን ደካሙን ለናግዝ " እርሱም ሕይወትንና እስትንፋስን ሁሉንም ለሁሉ ይሰጣልና አንዳች እንደሚጎድለው በሰው እጅ አይገለገልም።" (የሐዋርያት ሥራ 17:25) ለካ የሳምራዊቷን ሴት ውሃ አጠጪን ያላት እንደተጠማች አውቆ የህይወትን ውሀ ሊያጠጣት ነው ለካ "ውሀ አጠጪን ብሎ ውሃ የሚጠጣ የአባት ብልጠት" " ኢየሱስ መልሶ።... ውኃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ፥ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ የሕይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር አላት።" (የዮሐንስ ወንጌል 4:10) እሷማ ምንታርግ ምድራዊ ውሃ የሚለምን ሰማያዊ ውሃ ያጠጣኛል ብላ እንዴት ትጠርጥር የአባቷ ብልጠት አልገባትም "ሊያጠጣ ሲፈልጎ አጠጡኝ እንደሚል " እግዚአብሔር አምላክ ሕዝቡን ከባርነት ቤት ሲያወጣ ያለውን ተመልከቱ " እግዚአብሔርም ሙሴን ተናገረው። ወደ ፈርዖን ግባ እንዲህም በለው። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ያገለግለኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።"(ኦሪት ዘጸአት 8:1) የእውነት ግን እስራኤል ነው እግዚአብሔርን ያገለገለው ወይስ እግዚአብሔር ነው የእስራኤልን ያገለገለው? ማነው መና ከሰማይ ያወረደው? ማነው ደመና ጋርዶ የእሳት አምድ ዘርግቶ ያገለገለው? ማነው በምድረ በዳ ከነክፉ አመላቸው እንደ ንስር በክንፍ የተሸከማቸው? እግዚአብሔር ነው። እነሱማ አስመረሩት እንኩዋን ሊያገለግሉት። ታገለግሉኛላችሁ ብሎ አውጥጦ እራሱ አገለገላቸው ። የአባቴ ብልጠት አገልግሉኝ እያለ ማገልገሉ፤ አክብሩኝ ያለ ማክበሩ፤ ስጡኝ እያለ መስጠቱ ነው። እኔ በአባቴ ብልጠት ተገርሚያለሁ እናንተስ? @jesusis ❤️
Show all...
👍 3
❤️ 4
Blood of JESUS
Show all...
፩ሰው ።።።። አንድ ሰው ነበረ ዘመኑን በሙሉ አብት፣ዝና፣ክብር፣ስልጣን ሚባሉትን ሲያሳድድ የኖረ ለፈጠረው አምላክ ጊዜውን ያልሰጠ በዚህ ዓለም ሃሳብ ውስጡ የናጠጠ አንድ ሰው ነበረ... በወሲብ፣በስፖርት፣በፊልም የታሰረ እራሱን "ሊያዝናና" በእጅጉ የጣረ በጤዛ ተዝናኖት ራሱን የወተፈ በሚያዝናናው ነገር ስቃይ ያተረፈ አንድ ሰው ነበረ... ሊቅና አዋቂ እንዲሁም ፈላስፋ "ምሁር ነው" ለመባል በእጅጉ የለፋ አንድ ሰው ነበረ... በአይማኖተኞች ዘንድ እጅግ የከበረ በመባ፣ባስራት፣"በፍቅር ስጦታ" ቅልብ የወፈረ አንድ ሰው ነበረ... ዘመኑን ያልዋጀ ባመፃ ተወልዶ ባመፃ ያረጀ እድሜውን በሙሉ በከንቱ የፈጀ አንድ ሰው ነበረ... ተፈትቻለው ሚል ውስጡ የታሰረ በኑሮው ጣዕም ያጣ ቅርር የቀረረ አንድ ሰው ነበረ... ይህቺን ጠፊ ዓለም በጣም ያፈቀረ የእምነት ጉዞውን በጅምር ያስቀረ አንድ ሰው ነበረ... ደስታ አለበት ብሎ ያሰበውን ሁሉ ለማግኘት የለፋ ግና ሲደርስበት ጉም ዝግን ሆኖበት እጅግ የተከፋ አንድ ሰው ነበረ... በነበረ ዙረት እጥር የታጠረ ከእውነት የተጣላ ፀቡም የከረረ አንድ ሰው ነበረ... ግ...ና ሁሉ እንዲሆን መና ሞት አይቀርምና ሰጋም ወዳፈር.. ነብስም ከፍርድ ወንበር "ነበረ" ለመባል ሽቅብ ተነጠቀች ፍርድን ለመቀበል ካምላኳ ፊት ቆመች የምድር ቆይታ ጊዜዋን አሰበች ነፍስ ፍርሃት ገባት እጅግ ተጨነቀች ምክንያቱም "ቢዚ ነኝ" እያለች ቢዝነስ ነው እያለች ቤተሰብ እያለች ስጋዬን እያለች ካምላኳ ርቃለች በባለጠግነት ምኞት ተቃጥላለች ለስልጣን ለዝና ዘመኗን ሰጥታለች ከእውነት እርቃ በኃጢያት ተደብቃ በጨለማው ስራ እስራቶች ታስራ ለስጋዋ ተድላ ሁሉ እንዲሞላ ብቻ ታትራለች ፀጋውን ትታለች ፍቅሩን ንቃለች ራሷን ስታታልል በጣም ስታስመስል በትርፍ ጊዜዋ መንፈሳዊ መስላ ልትታይ ጥራለች በአይማኖት ውስጥ ሆና የኃጢያቷን ችግር ሳትፈታ ኖራለች በመርገም ተወልዳ በመርገም ሞታለች ስለዚህም ያንድን ሰው ዋጋ ትከፍላለች ያልተዋጀውን ኑሮ በዘላለም ፍዳ ታወራርዳለች ስለዚህ አንድ ሰው ዛሬ ላይ ያለኸው ብልህና አዋቂ "ከነበር" ነው ሚያውቀው እራሱን ሚያርመው የነእንትናን "ነበር" አንተም እንዳትደግመው በጣም ሳይረፍድብህ ዘመንህን ዋጀው።
Show all...
❤ 4
👏 7
😡
Har'a galgala Iji hojjii (firiin) keessaani maqaa yesuus, isa du'a moo'ee ka'een #dachaa 30,60,100 isiniif haa argatu!! የስራችሁ ፍሬ ዛሬ ማታ ሞቶ ከሞት በተነሳው በናዝሬቱ በኢየሱስ ስም 30; 60;100 እጥፍ ፍሬ ያፍራላችሁ ❤️❤️❤️ጌታ ይወደናል❤️❤️ Jaalalli gooftan nuuf qabu herreegan oli lakkoofsi namtochee isa hin ibsu
Show all...
የክርስትናው ኢየሱስ Vs የኢስላሙ ዒሳ (10 መሰረታዊ ልዩነቶች) 1⃣. ስማቸው አንድ አይደለም! በዕብራይስጥ - የሆሹዋ (Yehoshua' ወይም Yeshua') በአረአይክ - የሹዋ (Yeshua) በግሪክ - የሱስ (Iyesus) በላቲን/እንሊዘኛ- ጂሰስ (Jesus) ዓረብኛ - የሱዋ (Yasu') �ቁርዓን - ዒሳ( Eesa) ዓረብኛውና ዕብራይስጡ አንድ መሆናቸውን የቁርዓኑ ግን ልዩ መሆኑን ለማወቅ የተሰሩባቸውን ፊደላት ይመልከቱ Yeshua'= yod + Shin + Waw + 'Ain Yasu' = ya + sin + Waw + 'Ain Eesa(ዒሳ) = Ayin + sin 2⃣ የተፈጠረው ማን? ፈጣሪ የሆነውና በፈቃዱ ሰው የሆነው ማን? 👉ዒሳ በፈጣሪ የተፈጠረና ከጊዜ ብኋላ የመጣ ነው =>3:59:-አላህ ዘንድ የዒሳ ምሳሌ እንደ አዳም ብጤ ነው! ከአፈር ፈጠረው ለርሱም ሁን አለው ሆነም! 👉ኢየሱስ ግን ዓለም ሳይፈጠር የነበረ ፈጣሪና በፈቃዱ ሰው የሆነ ነው! =>ሚክ5:2:- አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፤ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል =>ዮሐ1:1:- በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ!ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን! =>ዮሐ8:56:-አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ፥ አየም ደስም አለው! አይሁድም፦ ገና አምሳ ዓመት ያልሆነህ አብርሃምን አይተሃልን? አሉት ኢየሱስም፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው =>ዮሐ17:5:- አሁንም፥ አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ 3⃣የትና እንዴት ነው የተወለዱት? 👉በበረሃ ከዘንባባ ስር ተወለደ =>ሱራ19:23:- ወዲያውኑም አረገዘች! በርሱም (በሆድዋ ይዛው) ወደ ሩቅ ስፍራ ገለል አለች:: ምጡም ወደ ዘንባባይቱ አስጠጋት! "ዋ ምኞቴ ምነው ከዚህ በፊት በሞትኩ ተረስቼ የቀረሁ በሆንኩ" አለች! ከበታችዋም እንዲህ ሲል ጠራት:: "አትዘኝ ጌታሽ ከበታችሽ ትንሽን ወንዝ በእርግጥ አድርጓል! የዘንባባይቱም ግንድ ወዳንቺ ወዝውዣት ባንቺ ላይ የበለስን የተምር እሸት ታረግፍልሻለች" 👉በቤተልሔም ከተማ በግርግም ተወለደ =>ሉቃ2:4-7:- ዮሴፍም ደግሞ ከዳዊት ቤትና ወገን ስለ ነበረ ከገሊላ ከናዝሬት ከተማ ተነሥቶ ቤተ ልሔም ወደምትባል ወደ ዳዊት ከተማ ወደ ይሁዳ፥ ፀንሳ ከነበረች ከእጮኛው ከማርያም ጋር ይጻፍ ዘንድ ወጣ!በዚያም ሳሉ የመውለጃዋ ወራት ደረሰ፥ በኵር ልጅዋንም ወለደች፥ በመጠቅለያም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው 4⃣. የእግዚአብሔር ልጅ ማን ነው? 👉ዒሳ የአላህ ልጅ አይደለም(አላህ ለመውለድ ሚስት ስለምታስፈልገው) =>9:30:-አይሁድ ዑዘይር የአላህ ልጅ ነው አላች:: ክርስቲያኖችም አልመሲሕ የላህ ልጅ ነው አሉ! ይህ በአፎቻቸው የሚናገሩት ቃላቸው ነው! የነዚያን ከነርሱ በፊት የካዱትን ሰዎች ቃል ያመስላሉ:: አላህ ያጥፋቸው! ከውነት እንዴት ይመለሳሉ! =>6:101:- እርሱ ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው! ለርሱ ሚስት የሌለችው ሲሆን እንዴት ለርሱ ልጅ ይኖረዋል? ነገርን ሁሉ ፈጠረ እርሱም ነገሩን ሁሉ አዋቂ ነው =>72:3:- እነሆም የጌታችን ክብር ላቀ! ሚስትንም ልጅንም አልያዘም! =>19:88:-አልረሕማን ልጅን ያዘ (ወለደ) አሉ:: ከባድ መጥፎን ነገር በእርግጥ አመጣችሁ! 👉ኢየሱስ ግን የእግዚአብሔር ልጅነቱ በራሱ አንደበት ይናገራል! =>ማር14:67:- እርሱ ግን ዝም አለ አንዳችም አልመለሰም። ደግሞ ሊቀ ካህናቱ ጠየቀውና፦ የቡሩክ ልጅ ክርስቶስ አንተ ነህን? አለው ኢየሱስም፦ እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለ:: ሊቀ ካህናቱም ልብሱን ቀደደና፦ ከእንግዲህ ወዲህ ምስክሮችን ምን ያስፈልገናል? ስድቡን ሰማችሁ፤ ምን ይመስላችኋል? አለ። እነርሱም ሁሉ፦ ሞት ይገባዋል ብለው ፈረዱበት:: =>ዮሐ10:36:- የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ስላልሁ እናንተ አብ የቀደሰውን ወደ ዓለምም የላከውን፦ ትሳደባለህ ትሉታላችሁን =>ራእይ2:18:- በትያጥሮንም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ እንደ እሳት ነበልባል የሆኑ ዓይኖች ያሉት በእቶንም የነጠረ የጋለ ናስ የሚመስሉ እግሮች ያሉት የእግዚአብሔር ልጅ እንዲህ ይላል። =>ዮሐ3:16:-በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና =>ዮሐ5:25:- እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ሙታን የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል እርሱም አሁን ነው፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ 👉እግዚአብሔር አብ መስክሮለታል =>ማቴ3:16:-ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤ እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ። =>ማቴ17:5:- እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ። =>ማር9:7:- ደመናም መጥቶ ጋረዳቸው፥ ከደመናውም፦ የምወደው ልጄ ይህ ነው፥ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ =>ሉቃ9:34:-ይህንም ሲናገር ደመና መጣና ጋረዳቸው፤ ወደ ደመናውም ሲገቡ ሳሉ ፈሩ! ከደመናውም፦ የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው፥ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ። 👉መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል መስክሮለታል =>ሉቃ1:35:-መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል 👉ነቢዩ ዮሐንስ መስክሮለታል =>ዮሐ1:34:- እኔም አይቻለሁ እርሱም የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ መስክሬአለሁ 👉ደቀመዛሙርቱ መስክረውለታል =>ማቴ16:16:- ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፦ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ። =>1ዮሐ3:9:- ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በሚታመን ሁሉ እግዚአብሔር በእርሱ ይኖራል እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል =>1ዮሐ5:5:- ኢየሱስም የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ከሚያምን በቀር ዓለምን የሚያሸንፍ ማን ነው? =>1ዮሐ5:12:- ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም። =>ዮሐ6:68:- ጴጥሮስ፦ ጌታ ሆይ፥ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ!እኛስ አንተ ክርስቶስ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ አምነናል አውቀናልም ብሎ መለሰለት =>ማር1:1:- የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ =>2ዮሐ1:3:- ከእግዚአብሔር አብና ከአብ ልጅ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም በእውነትና በፍቅር ከእኛ ጋር ይሆናሉ 👉አጋንንት በፍርሐት መስክረውለታል =>ማቴ8:29:-እነሆም፦ ኢየሱስ ሆይ፥ የእግዚአብሔር ልጅ፥ ከአንተ ጋር ምን አለን? ጊዜው ሳይደርስ ልትሣቅየን ወደዚህ መጣህን? እያሉ ጮኹ =>ማር3:11:-ርኵሳን መናፍስትም ባዩት ጊዜ በፊቱ ተደፍተው፦ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ እያሉ ጮኹ =>
Show all...
🙏 2
👏 2