cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ፍኖተ - ጥበብ ቤተ - መጻህፍት..ኑ.!! እናንብብ...

# ትውልዱ በንባብ እራሱን እና ሀገሩን እንዲለውጥ ሁሉም ዜጋ የድርሻውን መወጣት ይጠበቅበታል!!!

Show more
Advertising posts
266Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የመውደድ ጥግ፣ የፍቅር ተምሳሌት! ፨፨፨፨፨፨፨፨/////////////፨፨፨፨፨፨፨ የአምላክ በቀራንዮ መዋል፣ በአደባባይ መሰቀል የፍቅሩ ጥግ ነው፤ የመውደዱ ማሳያ ነው። ፍቅር በተግባር ሲገለፅ አለም አየ፤ ምድር ፈጣሪዋን በስቅላት ስትቀጣ አለም ተመለከተ። ከእርሱ በፊትም ሆነ ቦሃላ የመጣ የሰው ልጅ ያደርገው ዘንድ ያልተቻለውን እርሱ ጌታ መድሃኒአለም ያንን ማለቂያ የሌለውን ፍቅሩን በቀራኒዮ ተሰቅሎ፣ በደም ታጥቦ አሳየን። የፍቅር ጥግ በመስቀል ተገለጠ፤ በትግባርም ታየ። ከዚህ የሚበልጥ የመውደድ ጥግ ከወዴት አለ? ማንስ አሳይቶናል? ከዚህ የሚበልጥ የፍቅር ተምሳሌት ከወዴት ይገኛል? ማንስ አስተምሮናል? አምላክ በሞቱ ፍቅሩን ገለፀ፤ ከዘላለም ሞቱ የሰውን ልጅ ነፃ አወጣ። ለነፃነታችን የማያልቅ ፍቅሩን ሰጠን። አዎ! የሰው ልጅ የፍቅርን ሃያልነት መማር ቢፈልግ የጌታውና የፈጣሪው ለእርሱ መሰዋትን የሚበልጥ መማሪያ ከወዴት ያመጣል? አዎ! ጀግናዬ..! ፍቅርን እንኑር፤ የተሰቀለውን ቅዱስ ጌታ እናስብ። እርሱ ፍቅርን መስሎ አላሳየንም ሆኖ እንጂ፣ እርሱን የፍቅርን ሃያልነት በቃላት አለገለፀልንም በተግባር እንጂ፣ እርሱ ፍቅሩን ለመግለፅ ማንንም አልላከም እራሱ ዋጋ ከፍለ፣ ከፍቅር የተሻለ፣ ከመዋደድ፣ ከመደጋጋፍ፣ ከመረዳዳት የተሻለ የነፍስ መድሃኒት፣ የመንፈስ ማረፊያ፣ የስሜት እርካታ አይገኝም። ፍቅርን የሚኖር በጌታው ይመረጣል፤ በረከቱን፣ ፀጋውን ይታደላል፤ መንግስቱንም ይወርሳል። አዎ! የዚህ ዘመን ፍቅር መሱዓትነት አይጠይቅም ይሆናል፤ ስቅላትን አይፈልግም ይሆናል። ወንድም ወንድሙን እንደራሱ ሲወድ ፍቅርን ይኖራል፣ ማንም ቢሆን ባልንጀራውን ከእራሱ በላይ ቢወድ፣ ቢያከብር፣ ቢያግዝ እርሱ የፍቅር ሰው ይሆናል፤ ማንም እርሱ ጠላቱን የሚወድ፣ በፍቅር የሚያሸንፍ፣ በደልን በይቅርታ የሚሽር ቢኖር እርሱ ብርቱ የፍቅር ሰው ነው። ፍቅርን ከሞተልን፣ እራሱን በቀራንዮ አደባባይ አሳልፎ ከሰጠን የዘላለም አምላክ የፍቅር ጌታ እንማር፣ በእርሱ ልክ ባይጠበቅብንም በአቅማችን እንኑረው፣ ከጎናችን ላሉት እንግለፅ፤ በፍቅሩ እንታነፅ። ብሩክ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ https://t.me/bookmyfavour https://t.me/bookmyfavour
Show all...
ፍኖተ - ጥበብ ቤተ - መጻህፍት..ኑ.!! እናንብብ...

# ትውልዱ በንባብ እራሱን እና ሀገሩን እንዲለውጥ ሁሉም ዜጋ የድርሻውን መወጣት ይጠበቅበታል!!!

#3ቱ_የፍቅር_ሕይወቶች 💎 የፍቅር ህይወትህ የደስታህ መሰረት ነው። ፍቅር የተለያዩ ሰዎች የሚተሳሰቡበት የስሜት ትስስር አለው። ፍቅር በግፊት ሊሆን አይችልም። ብዙዎች ለዚህ ሰዋዊ ስሜት ትኩረት አይሰጡም ይህ ከባድ አደጋ አለው። የፍቅር ህይወትህ የተሻለና የምትወደው እንዲሆን እኒህን ሶስት መሰረታዊ ነገሮች ተለማመድ። #1_ጠባቂ_አለመሆንን። 👉 በሰጠኸው ልክ ለመቀበል አትጓጓ። ያ ውስጥህን የሚያከስም ሊሆን ይችላል። ማድረግ ያለብህን በፍቅር ስታደርግ ምላሽ ለማግኘት አይሁን። ደስታህ ከመስጠትህ ላይ ብቻ ይሁን። #2_ሙጥኝ_አለማለትን። 👉 ይህን እውነት ተቀበል። የወደድከው ሁሉ ሊወድህ... ያከበርከው ሁሉ ሊያከብርህ... የፈለከው ሁሉ ሊፈልግህ ግዴታው አይደለም። አንተ ያለህን ያህል ሁሉም ሰው የራሱ ፍላጎትና ምርጫ አለው። ሰዎች ምርጫቸው ካላደረጉህ ያ ያንተ ችግር ሊሆን አይገባም። አቅጣጫህን ቀይር እንጂ ሙጥኝ በማለት ራስህን የሌሎች ፈተና አታድርግ። #3_ራስህን_መውደድ። 👉 ራስህን መውደድ አለብህ። ይህ ሀጢአት አይደለም። ራስህን ስትወድ ለሌሎች የምትሰጠው ቦታ ልክ ይኖረዋል። ሰዎችም ሊወዱህ ይገደዳሉ ምክንያቱም በልካቸው ስለምትወዳቸው። ራስህን መውደድ ስትጀምር ሌሎች ባይወዱህ ብቸኝነት አይሰማህም ምክንያቱም መቼም የማይጠላህ ትክክለኛ ወዳጅ እንዳለህ አውቀሃልና። ☑️ ያ ወዳጅህ ደሞ ራስህን መውደድህ ብቻ ነው። #የሕይወት_ኬሚስትሪ መጽሐፍ #2ተኛው ዕትም በገበያ ላይ በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል። ©ምንጭ ተክሉ ጥላሁን https://t.me/bookmyfavour https://t.me/bookmyfavour
Show all...
በዋጋ እዚህ አለህ! ፨፨፨፨//////፨፨፨፨ በመስቀሉ አዳነን፤ በሞቱ ህይወትን ዘራብን፤ የፍቅርን ሃያልነት፣ የመውደድን ጥግ እራሱን ሰውቶ፣ እራሱን ሰጥቶ ገለፀልን። ገደብ አልባው ፍቅሩ፣ ማለቂያ የሌለው መውደዱ ከዙፋኑ ሳበው፤ ወደ ምድር አወረደው፤ በወደዳቸው፣ በመረጣቸው፣ ባፈቀራቸው ልጆቹ እጅም እንዲሰቀል አበቃው። ሰቃዮቹም ሰዎች የሚድኑትም ሰዎች፣ የሚሰቀለውም አምላክ የሚያድነው፣ የሚፈውሰውም እራሱ የተሰቀለው፣ ህይወቱን የሰጠው ድንቅ መካር ኀያል ቅዱስ ጌታ። የፍቅሩ ግዝፈት እየሰቀልነው ማዳኑ፣ የመውደዱ ጫፍ እያወቀ ለመሞት መዘጋጀቱ። በእርግጥ ፍቅር የለም ቢባል እንዴት ይሆናል እራሱ ፍቅር፣ እራሱ መውደድ፣ እራሱ ትርጉሙ ለሰው ልጅ ሲል መስቀል ላይ ተቸንክሮ እየታየ። ገዳዮቹን ሊያድን የሚመጣ፣ አጥፊዎቹን ከእስራታቸው ሊፈታ፣ በደለኞችን በገባው ቃል ነፃ ሊያወጣ የሚችል ከአንድ አምላክ በቀር እርሱ ማን ሊሆን ይችላል? አዎ! ጀግናዬ..! በዋጋ እዚህ አለህ፤ በደሙ ህይወትን አገኘህ፤ በፍቅሩ ሃያልነት ከዘላለም ሞት አመለጥክ፤ በርህራሔው ጥግ በሰውነትህ ከበርክ። የአምላክ መውደድ በተግባር እስከሞት ነው፤ የእኛስ ፍቅር እስከምን ይሆን? እርሱ ውደዱኝ ባይል እንኳን ባልንጀራችንን ብንወድ፣ ብናከብር እርሱን እንደወደድን እንደሚቆጠር አስተምሮናል። የምታየውን፣ የምታውቀውን፣ ከጎንህ ያለውን ወዳጅህን ሳትወድ እኔን ያላየሀኝን፣ ያላወከኝን፣ ያልዳሰስከኝን እወድሃለሁ ብትል እንዴት ይሆናል? ይላል አምላክ። ቃላት ቢደረደሩ፣ ዜማ ቢረቅ፣ ጥበብ ብትኖር የአምላክን የማዳን ጥበብ አይገልፁትም። ለዚህም ነው እግዚአብሔር አለምን ከፈጠረበት አለምን ያዳነበት ጥበቡ ይበልጣል መባሉ። አዎ! ፍቅርን ከክርስቶስ እንማር፤ መሰዋትን፣ እራስን መስጠትን፣ ሳይሳሱ ለቃል መታመንን ከቸር አምላካችን እንማር። ሰላም እርሱ ነው፤ መውደድ እርሱ ነው፤ ፍቅር እርሱ ነው። በእርሱ ልኬት መሰዋት፣ በእርሱ መጠን እራስን መስጠት ባይጠበቅብን እንኳን እርስ በእርስ ብንዋደድ፣ ብንደጋገፍ፣ ብንማከር፣ ህይወት ላይ ብንተባበር ዳግም በረከቱን እንቋደሳለን። ስሙን መጥራት፣ ለምስጋና መትጋት፣ ለውዳሴ መንቃት ትንሹ ክፍያችን ነው። ስራውን መመስከር፣ ማዳኑን መናገር፣ ለአምላክነቱ ለክብሩ መስገድ ጥቂቱ ስራችን ነው። ሀጢያት ቢበዛብን፣ በደል ቢደራረብብን፣ ጥፋታችን እልፍ ቢሆን ይቅር ለማለት ህይወቱን የሰጠ አምላክ አለና እራሳችን እንስጠው፣ ውስጣችንን እናሳየው፣ ማዳኑንም በእያንዳንዳችን ህይወት እንመልከት። ውብ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅 https://t.me/bookmyfavour https://t.me/bookmyfavour
Show all...
ፍኖተ - ጥበብ ቤተ - መጻህፍት..ኑ.!! እናንብብ...

# ትውልዱ በንባብ እራሱን እና ሀገሩን እንዲለውጥ ሁሉም ዜጋ የድርሻውን መወጣት ይጠበቅበታል!!!

ማህበራዊ ስኬት! ፨፨፨፨//////፨፨፨፨ ሲታዩ ደስተኛ መምሰል፣ ለይስሙላ ለባብሶ ደምቆ መውጣት፣ ሰው ፊት እንዲወራልን መጠበቅ፣ ሁሌም ተከብረን፣ ተሞግሰን፣ ተደንቀን መኖርን መመኘትን የማህበራዊ ስኬት ጥማት እንለዋለን። እያንዳንዱ ጉዟችን ለእኛ ሳይሆን ለስማችን ነው፤ ለሚሰጠን ክብርና ዝና ነው፤ በሰው ዘንድ ለምናገኘው ቦታ ነው። ለእራሰህ ያልሆነህ፣ አንተን ያላስደሰትህ፣ ላንተ ያልጠቀመህ ስኬትም ይሁን ከፍታ በሰው ፊት ቢያስከብርህ፣ ከፍ ቢያስደርግህ ለከፋው ውድቀት ከማመቻቸት ውጪ ምንም ጥቅም የለውም። የምትችለው ነገር ብዙ ሆኖ ሳለ ለሰዎች ጭብጨባና አድናቆት ብቻ መልፋትህን አቁም። ዛሬ ብትነሳ ነገ ላለመውደቅህ ምንም ዋስትና እንደሌለህ ተረዳ። ትናንት ያነሳህ፣ ያሞገሰህ፣ የደገፈህ ሰው ዛሬ በተራው ሊጥልህ እንደሚችል አስብ። አዎ! ጀግናዬ..! የማህበራዊ ስኬት ጥማትህን ገታ አድርገው፤ በሰው ለመወደድ፣ ይሁንታን ለማግኘት፣ ዝናን ለማትረፍ ከመሯሯጥ መለስ በል። እራስህን ማስደሰት ሳትችል ደስተኛ ሆኖ መታየት ሸክም እንጂ ምንም ትርፍ አያመጣልህም። የሆንከውን ብትሆን ሰው ቢቀበልህ ባይቀበልህ፣ ቢያጨበጭብልህ ባያጨበጭብልህ፣ ቢደግፍህ ባይደግፍህ ዋናው ቁብ ነገር አንተ የእራስህ ደጋፊ መሆንህ ነው። ለእራሱ የሚወግንን ሰው ማንም ሊያስቆመው አይችልም። ምክንያቱም አብሮት ያለው ሁሉን ማድረግ የሚችለው አምላክ ነውና። ዛሬ አንተ ደክመህ፣ ለፍተህ፣ እራስህን አተህ፣ ተጋግጠህ ያመጣሀውን ዝና ነገ በሌላ ነገር የሚቀይረው በወረት የሚመራ የሰው ልጅ ውስጥ እንዳለህ አስታውስ። ትናንት ሲመረቁ የነበሩ ሰዎች ዛሬ ሲረገሙ ማየት አዲስ አይደለም። ቦታህን ይዘህ የምትቀጥለው በሰዎች ስሜት ስለተነዳህ ሳይሆን እራስህን ስለሆንክና እራስህን ከማስደሰት ስለተነሳህ ነው። አዎ! ለመታየት፣ ለመደነቅ፣ ለመሞገስ ሳይሆን ዋጋህን ለመጨመር፣ ጥራትህን ለማሳደግ፣ ማንነትህን ለማሳየት ትጋ። ከምንም በላይ እራሱን ማውጣትና ከፍ አድርጎ ተፅዕኖ መፍጠር የሚችለው እራሱ ሰውዬው ነው። አለም በቅፅበታት ትቀያየራለች፣ የሚቀይራትም የሰው ልጅ ቅፅበታዊ ስሜት ነው። በምክንያት ቢወድህ በምክንያት ሊጠላህ ከሚችል ሰው ጋር እየኖርክ ለእርሱ ደስታና እርካታ፣ ከእርሱ ቅቡልነትን ለማግኘት ብትሰቃይ ዋጋህን ከማሳነስ በቀር የምታተርፈው ነገር አይኖርም። ሁላችንም የተለያየ አቅም አለን። ያ አቅም ሰዎችን Impress ለማድረግ ሳይሆን እራሳችንን በጠለቀ የመሞላት ስሜት ለማነፅ ብንጠቀመው ስሜቱ በእራሱ ውጫዊውን ድባብ ሲቀይረው ለመመልከት ጊዜ አይፈጅብንም። ለመታየት ሳይሆን ብቁ ለመሆን ስራ፤ ለተቀባይነት ሳይሆን ለውስጥ መሻትህ ትጋ፤ ለስምና ዝና ሳይሆን ለእውነተኛው መጠራትህ እራስህን ስጥ። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ https://t.me/bookmyfavour https://t.me/bookmyfavour
Show all...
ፍኖተ - ጥበብ ቤተ - መጻህፍት..ኑ.!! እናንብብ...

# ትውልዱ በንባብ እራሱን እና ሀገሩን እንዲለውጥ ሁሉም ዜጋ የድርሻውን መወጣት ይጠበቅበታል!!!

ምርጥ አሥር (10) የአማርኛ ልቦለዶች 1.ፍቅር እስከ መቃብር፤ ክቡር ዶክተር ሀዲስ ዓለማየሁ፡፡‹‹አባይን ያላየ ››አለ ያገሬ ሰው፡፡ ዓለም ፍቅር እስከ መቃብርን አንብቦ ቢሆን ሮምዮና ጂሊየት የልጆች ጨዋታ ይሆን ነበር፡፡ 2. 5ቱ የዴርቶጋዳ ክፍሎች (ዴርቶጋዳ :ራሕማቶሃራ: ዣንቶዣን: ዩራቶራድ: ዮቶድ) በ ደራሲ ይስማዕከ ወርቁ :: 3. የደራሲ አለማየሁ ዋሴ እሸቴ ድንቅ ሶስት+1 ተከታታይ መፅሐፍቶች:: እመጎ:ዝጎራ እና መርበብት +ሜተራልዮን :: አገር በቀል እውቀትን መሰረት ያደረጉ መፅሐቶች ናቸው:' 4. የታንጉት ምስጢር፤ ብርሃኑ ዘርይሁን ፡፡ታሪከዊ ልቦለድመፃፍ ካማረህ ብልሃቱን የታንጉት ምስጢር ውስጠ ታገኘዋለህ፡፡ 5. ኦሮማይ፤ በዓሉ ግርማ፡፡የኖርክበትንና የምትኖርበትን ሕይወት ትንሽ ቅመም ጣል አድርገህ በከባድ መስዋዕትነት ለመጻፍ ወኔው ካለህ አዲዮስ-ኦሮማይ! 5. አልወለድም፤ አቤ ጉበኛ፤ ማሕበራዊ ኢፍታሀዊነትን የምትዋጋ ከሆነ ‹‹አልወለድም!›› በል፡፡ 6. ጉንጉን፤ ሀይለመለኮት መዋዕል፤ ለኔ ከሀይለመለኮት ድርሰቶች ከወዲያነሽ ይልቅ ጉንጉን ይበልጣል፡፡ በተለይ የቋንቋው ዘይቤው፡፡ 8. ሰመመን ፤ሲሳይ ንጉሱ፡፡ የማይረሱ ገጸ-ባሕሪያት እንዴት እንደሚሳሉ ማወቅ ከፈለግህ በሰመመን ተጓዝ፡፡ 9. ሀሽማል : ከርታታ ኮከቦች....በ ቅኔ ቤቶች መሰረታቸውን የጣሉት ሁለቱ ተያያዥነት ያላቸው መፅሐፍቶች ሲሆኑ በተደራሲያንም ተወዳጅነትን አትርፈዋል:: የደራሲና ባለቅኔ ማዕበል ፈጠነ ስራዎች ተጠቃሽ ናቸው 10. ሜሎሪና :ቴሎስ...... ከወጣት ደራሲዎች መካከል አንዱ የሆነው ናሁሰናይ ፀዳሉ:: 📌እጅግ ብዙ ተወዳጅና ማራኪ መፅሐፍቶች ቢቀሩም ሚፈለጉት ግን 10 ብቻ ናቸው🙏 https://t.me/bookmyfavour https://t.me/bookmyfavour
Show all...
ፍኖተ - ጥበብ ቤተ - መጻህፍት..ኑ.!! እናንብብ...

# ትውልዱ በንባብ እራሱን እና ሀገሩን እንዲለውጥ ሁሉም ዜጋ የድርሻውን መወጣት ይጠበቅበታል!!!

📚ርዕስ:- አላቲኖስ 📝ድርሰት:-ቃልኪዳን ኃይሉ ገብሬ 📜ይዘት:- .. 📆የመጀመሪያ ዕትም:- 2010 📖የገፅ ብዛት:- 305 📌አዘጋጅ:- ብሄረ መፃሕፍት ዘ-ኢትዮጵያ ማጋራት አይዘንጋ! @ETHIO_PDF_BOOKS @ETHIO_PDF_BOOKS @ETHIO_PDF_BOOKS
Show all...
ሳይላክ የቀረ ደብዳቤ እና ሌሎችም ✍በተለያዩ ዕውቅ የሩሲያ ደራሲያን ትርጉም:- ካሳ ገብረህይወት ═════════════ @Amharic_books_in_pdf
Show all...
ፈልገህ ቅረባቸው! ፨፨፨፨//////፨፨፨፨ ብርቱ እጆች ይደጋገፉ ዘንድ፣ ህልመኛ ነፍሳት ይተሳሰሩ ዘንድ፣ ንቁ አዕምሮዎች ይግባቡ ዘንድ፣ ጠንካራ ልቦች አብረው ይጓዙ ዘንድ፣ አዋቂዎች እውቀትን ይመጋገቡ ዘንድ የግድ ነው። የሚመስልህን ለማግኘት ግዴታ በአዋጅ ማስነገር፣ ማስታወቂያ ማሰራት አይጠበቅብህም፤ ስሜትህ በእራሱ ይጠራዋል፤ ማንነትህ በእራሱ ያቀርበዋል። ነገር ግን ይህ ስሜት የማይዋዥቅ፣ ማንነትህም የማይዛባ መሆን ይኖርበታል። አንዴ ሰው አንዴ አፈር እየሆንክ የሚጠጋህን ሰው አታገኝም። ጓደኞችህን ተመልከት፣ በቅርበት የምትግባባቸውን ሰዎች አጢናቸው፣ ቀለል የሚሉህን ሰዎች አስተውላቸው ቅርበታቸው፣ ጓደኝነታቸው፣ ቅለታቸው ያለምክንያት ይመስልሃል? በፍፁም! የሚያመሳስላቹና የሚያቀራርባችሁ ብዙ ነገር ይኖራል። አብረውህ ያሉ ሰዎች አብረውህ የሆኑት፣ የቀረቡህ፣ የተወዳጁህ በምክንያት እንደሆነ አስተውል፤ ከዚህም በላይ ሌሎች ተጨማሪ ሰዎች እንደሚያስፈልጉህ እወቅ። አዎ! ጀግናዬ...! ፈልገህ ቅረባቸው! እነዛን ያስፈልጉኛል፣ ይረዱኛል፣ ሃሳቤ ይገባቸዋል፣ ራዕይዬን ይጋሩኛል የምትላቸውን ሰዎች ፈልገህ አግኛቸው። እነዛን የእኔ ያልካቸውን፣ ይደግፉኛል ያልካቸውን፣ አገናኝ የጋራ ሃሳብ፣ ህልም፣ ራዕይ አለን ብለህ የምታስባቸውን ሰዎች ፈልገህ ቅረባቸው፣ ተወዳጃቸው፣ አብረሃቸው ሁን፣ አብረሃቸው ስራ፣ ደግፋቸው፣ ይደግፉህ። ብቻህን ጊዜ የፈጀብህ ነገር በህብረት፣ በትብብር፣ በአንድነት ወዲያው ይጠናቀቃል፣ ለተሻለው አፈፃፀምና ግብ ያዘጋጅሃል፣ ለላቀው ከፍታ ያቀርብሃል፤ ወኔና ብርታት ይሆንሃል። ሃሳብ እንኳን ሸክም ነው፤ ጭንቀት በእራሱ ህመም ነው፤ ለውጥን እየፈለጉ ሳያደርጉ መቅረትም የምኞት ስቃይ ነው። አዎ! ደክሞሃል? ድካምህን የሚጋራ ብርቱ ደጋፊ ተወዳጅ፤ ሃሳብ በዝቶብሃል? ለሃሳብህ እውንነት ከጎንህ የሚቆመውን ሰው ቅረብ። ስራህ ሰልችቶሃል? በተለያየ ዘርፍ የተሰማሩ ሰዎችን ተዋወቅ። ብቻህን ከምትሮጥ አሯሯጭ ፈልገህ አብረሀው ሩጥ፣ ብቻህን ከምትጀግን አንተን መሳይ ሌላ ጀግና ፈልገህ አብረሀው ጀግን፣ ብቻህን ከምታልም ህልመኛ ፈልገህ አብረሀው በትልቁ አልም። የተደጋገፉ እጆች ግንብ ይነቀንቃሉ፣ የተባበረ ክንድ ጠላትን ይረታል፤ አንድነት የእድገት መሰረት ነው። ብቸኝነትህ ሃይልህ ነው፤ ነገር ግን ሲደክምህ ድጋፍ ያስፈልግሃልና ከመደገፍ ወደኋላ እንዳትል፤ ያልገባህን ጠይቅ፤ ያልተረዳሀውን ተረዳ፤ ያላወከውን ከማንም እንዴትም እወቅ። ለከበደህ ነገር እጅ ከመስጠትህ በፊት ድጋፍ በመፈለግ ለማሸነፍ ሞክር። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ https://t.me/bookmyfavour https://t.me/bookmyfavour
Show all...
ፍኖተ - ጥበብ ቤተ - መጻህፍት..ኑ.!! እናንብብ...

# ትውልዱ በንባብ እራሱን እና ሀገሩን እንዲለውጥ ሁሉም ዜጋ የድርሻውን መወጣት ይጠበቅበታል!!!

ስም ይጥልሃል! ፨፨፨///////፨፨፨ ስምህን ለማሳመር፣ በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት፣ ከላይ ከላይ ጎልቶ ለመታየት፣ ለመወደድ፣ ለመደነቅና ለመሞገስ የምታደርገው የትኛውም ጥረት ጥፋትን ሊያስከትልብህ እንደሚችል እወቅ። ሰዎች ተቀብለውህ አንተ እራስህን ባትቀበል ምን ይጠቅምሃል? ሰዎች በሚያዩት ነገር ቢያጨበጭቡልህና አንተ በምታውቀው ነገር ብታዝን ምን ታተርፋለህ? አንድ ቀን የሚፈርስ ጥሩ ስም ከመገንባት ይልቅ ሁሌም አብሮ የሚቆይ ፅኑ ማንነትን መገንባት ይሻልሃል። አንተነትህን ስትገነባ፣ ብቁ ለመሆን ስትተጋ፣ እራስህ ላይ ስትሰራ ተቀባይነት ማግኘት፣ መወደድ፣ መደነቅ፣ መሞገስ ዋናው መስፈርትህ አይደለም። ትልቁና ዋነኛው ምክንያትህ ለውጥና እድገትህ ነው፤ ስኬትና ተፅዕኖ ፈጣሪነትህ ነው። ማንም ነገ የሚለቅ የተቀባባ፣ የተሽሞነሞነና ለጊዜው የሰዎችን ትኩረት ብቻ ሊስብ የተዘጋጀን ነገር የመጀመሪያ ምርጫው ሊያደርግ አይችልም። ወርቅ ቅብ ነሐስ እውነተኛው ነሃስነቱ ሲታወቅ ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት አይከብድም። አዎ! ጀግናዬ..! ስም ይጥልሃል! ስምህን ለመገንባትና ክብርን ለማግኘት ያልሆንከውን ነኝ፣ ያሌለህን አለኝ፣ ያልሰራሀውን ሰርቼያለው፣ ያንተ ያልሆነውን የእኔ ነው ብትል ለጊዜው የምትገነባው ጥሩ ስም ሊኖርህ ይችላል በሒደት ግን የሚፈርስ ማንነት ይኖርሃል። ማንም ሰው ውሸትን አይወድም፤ መታለልን አይፈልግም፤ በሌለ ማንነት መተዋወቅም አይመቸውም። በምላስ የተሽሞነሞነና በማንነት የሚታወቅ ሁለት ገፅታ የውድቀት ሁሉ መሰረት ነው። እራስህን የጠቀምክ እየመሰለህ ሰዎችን ለማስደመም ብቻ ወጪህን ብታበዛ፣ ለታይታ ደስተኛ ብትመስል፣ ለይስሙላ እንደ ሃብታም ብትንቀሳቀስ ውጫዊ ገፅታህን እያስዋብክ እራስህን ትጥላለህ። ያንተ ለብሶ መታየት፣ ደምቆ መገኘት፣ እንዳለው ለማሳየት ደረቱን ነፍቶ መሔድ የሚያሳስበው ሰው ያለ ይመስልሃል? በፍፁም። አዎ! ማንነትህን በስምህ ለመገንባት አትሞክር፤ እራስህን በምታገኘው ተቀባይነት አተለካ፤ ሰውነትህን በውጫዊ ሙገሳና አድናቆት አትመዝነው። ሊቀይርህና ሊታወቅ የሚገባው ከላይ በወሬና በጌጣጌጥ የደመቀው ገፅህ ሳይሆን በውስጥ የተደበቀው እውነተኛ አንተነትህ ነው። የምታገኛቸው ሰዎች ነገ አብረውህ አይኖሩም፤ የሚያውቁህ ሰዎች ዘወትር አብረውህ አይኖሩም። ሰዎችን ለማታለል ትጥራለህ እንጂ የምታታልለው የገዛ እራስህን ነው፤ ሰጣ ገባ ውስጥ የምትገባው፣ ሃሳብህን የምታጋጨው አንተው ነህ። ገፅህን አይተው፣ ዝናህን ሰምተው፣ ለእራስህ በሰጠሀው ሃሰተኛ ስም ተታለው የሚመጡ ሰዎችም ሆኑ ሌሎች ጥቅማጥቅሞች በእርግጥም ሊቀይሩህና ሊያሳድጉህ ሳይሆን ሊጥሉህና ማንነትህን ሊያጎድፉ ነው። ከስምህ ማንነትህን አስቀድም፤ ከገፅህ ስብዕናህን አሳውቅ፤ ከውጫዊው ከበሬታ ውስጣዊውን የእራስህን ክብር ጠብቅ፣ አስጠብቅ። https://t.me/bookmyfavour https://t.me/bookmyfavour
Show all...
ፍኖተ - ጥበብ ቤተ - መጻህፍት..ኑ.!! እናንብብ...

# ትውልዱ በንባብ እራሱን እና ሀገሩን እንዲለውጥ ሁሉም ዜጋ የድርሻውን መወጣት ይጠበቅበታል!!!

ህልምህ ይፈልግሃል! ፨፨፨፨//////////፨፨፨፨ ህልመኛ ስትሆን እብድ መባልህ አያሳስብህ፤ በትልቁ ስታስብ ነካ ያደርገዋል መባልህ አያስጨንቅህ፤ ትልቁን ራዕይ ስትሰንቅ ዘላባጅ መባልህ አያስፈራህ። ለህልምህ ስትል መባል ከሚገባህ በላይ መሆን ያለብህን ትሆናለህ፣ ራዕይን ስትሰንቅ መገፋት እስካለብህ ሳይሆን መውደቅ ያለብህ ስፍራ ትወድቃለህ፤ መጣል ያለብህ ቦታ ትጣላለህ። ውስጥህ የሚታይህ ስዕል ካንተ በቀር ለማንም አይታይም። ለህልምህ እንደምታስፈልገው ለማንም አታስፈልግም። መኖር ከውስጥህ፣ መሳቅም ከአንጀትህ ከሆነ የአለም ጫጫታና ንትርክ ምንህም አይደለም። ከማሰብ በላይ እንድተኖረው፤ ከጭንቀት ባሻገር አሁን ላይ እንድትገኝ የሚያደርግህ ድፍረትና ቆራጥነት ያስፈልግሃል። ህልመኛ መሆን፣ በእራስ መንገድ መጓዝ፣ የእራስ ህይወት ፈጣሪ መሆን ቀላል ነገር አይደለም። ብዙዎች የማያደርጉትም ቀላል ስላልሆነ ነው። አዎ! ጀግናዬ..! ህልምህ ይፈልግሃል፤ ራዕይህ አንተን ይሻል። ከጎኑ እንድትቆም፣ እንድትታገልለት፣ እንድትለፋለት፣ እንድትተጋለት፣ ዋጋ እንድትከፍልለት ይፈልጋል። ያለምክንያት ወዳንተ የሚመጣ የተለየ ሃሳብ አይኖርም፤ ከምንም ተነስቶ የሚታይህ የተለየ ስዕል የለም። ህልመኛ የምትሆነው ህልምህን የመኖር አቅም ስላለህ ነው፤ ባለ ራዕይ የሆንከው ራዕይህን የመፈፀም ብርቱ ጉልበት፣ ፅኑ ሃይል ስላለህ ነው። ለሀሳብህ እድል ስጠው፤ ይሆን፣ ይከናወን፣ ወደ ምድርም ይወርድ ዘንድ ፍቀድለት። ያንተ ነገር ያንተ ነው፤ ላንተ የታየህ ትርጉም የሚሰጠው ላንተ ብቻ ነው። ባመንክበት መንገድ ብትጓዝ ምርጫው ያንተ ነው። አማኝ፣ ደጋፊ፣ አበርታች፣ አይዞህ ባይ ፍለጋ መኳተን ትርፉ ድካም ብቻ እንደሆነ እወቅ። አዎ! ውስጥህ ያለውን ስዕል፣ በምናብህ የታየህን ሁነት ያመንከው በገሃድ ዳሰሀው፣ ጨብጠሀው አይደለም። ላንተ የሚታው ትልቁ የጥበብ ሰው ለማንም አይታይም፤ ላንተ የተገለፀው ባለራዕይው ስራ ፈጣሪ (entrepreneur) ለማንም አልተገለፀም፤ አንተ ያመንክበትን ውስጥህ ያለው ጀማሪ ህልመኛ ማንም አላመነበትም። በሚገርም ሁኔታ አንተ የፈለከውን እንደፈለክ ማድረግ የምትችለው፣ የተመኘሀውን ታላቅነት መገንባት የምትችለው አንተ ብቻ ነህ። ሁሉ በምክንያት ነውና በትልቁ ህልምህ ምክንያት ለሚደርስብህ መገለል፣ በራዕይህ ምክንያት ለሚወርድብህ ስድብና ትቺት በፍፁም አታማር። ለታላቅነት የመረጠህ አምላክ ለትናንሽ ጩሀቶች አሳልፎ አይሰጥህም፤ ለመፍትሔ የጋበዘህ ህልምህ ችግር መሃል አይጥልህም። የመጣው ቢመጣ፣ የደረሰብህ ቢደርስብህ፣ የተባልከውን ብትባል ህልምህን ከመኖር፣ ራዕይህን ከማሳካት፣ ግብህን ከመምታት ወደኋላ እንዳትል። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ https://t.me/bookmyfavour https://t.me/bookmyfavour
Show all...
ፍኖተ - ጥበብ ቤተ - መጻህፍት..ኑ.!! እናንብብ...

# ትውልዱ በንባብ እራሱን እና ሀገሩን እንዲለውጥ ሁሉም ዜጋ የድርሻውን መወጣት ይጠበቅበታል!!!