cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot

Show more
Advertising posts
29 501Subscribers
+3824 hours
+2417 days
+78930 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViewsSharesViews dynamics
01
በገድለ አቡነ ሀብተ ማርያም ላይ ተጽፎ የሚገኝ አንድ መንፈሳዊ ታሪክ አለ፡፡ ከዕለታት በአንድ ቀን የእመቤታችን የድንግል ማርያም በዓል በሚከበርበት ዕለት ቅዳሴ ለመቀደስ የተዘጋጁ አንድ ካህን ነበሩ፡፡ እኚኽ አባት ማታ ተኝተው ሳለ አንድ ጋኔን በሴት አምሳል አብሯቸው በማደር ሕልመ ሌሊት እንዲያገኛቸው አደረገ፡፡ ከመኝታ ሲነቁም ቅዳሴ መግባት የማያስችል እንቅፋት እንደገጠማቸው ስላወቁ በእርሳቸው ቦታ ጻድቁ አቡነ ሀብተ ማርያም ተተክተው ቅዳሴውን አከናውነዋል፡፡ የገድላቸው መጽሐፍም የእመቤታችን ፈቃድ ቅዳሴውን አቡነ ሀብተ ማርያም እንዲቀድሱት ነበረ በማለት በግልጽ ይተርካል፡፡ ይህ ሁኔታ የተፈጸመው ስለ አቡነ ሀብተ ማርያምም ክብር ሲባል ነው። አቡነ ሀብተማርያም በእመቤታችን በድንግል ማርያም ዘንድ ምን ያህል ተወዳጅ እንደሆኑ ያሳያል:: ከዚህ አልፎ ግን “ያኚኽ ካህን ምን በደል ቢገኝባቸው ነው» ማለት አይቻልም፡፡ እንዲህ ማለት በሰው መፍረድ ነውና፡፡ መጽሐፈ ገድሉም ካህኑ እንደዚህ ያለ በደል ነበረባቸው ብሎ የሚጠቅሰው ምንም ነገር የለም፡፡ ያልተጻፈውንና የማናውቀውን መናገር በእግዚአብሔር ሥራ ገብቶ እንደ መተቸት ይቆጠራል፡፡ ይህ ታሪክ በሕልመ ሌሊት በሚፈተኑ ሰዎች ላይ እንዳንፈርድ ይልቁኑም በሌላ አቅጣጫ ማየት የሚገባን ነገር እንዳለ ያስረዳል፡፡ በቀጣይ «ዝንየት»ና መንፈሳዊ ሥርዓቱ ይቀጥላል.... @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
3 33213Loading...
02
በዐፍላ ጉርምስና ወቅት ፈጣን ዕድገት ከሚያሳዩና ከሚለጠጡ የሰውነት ክፍሎች መካከል የድምፅ ጅማቶች ስለሚገኙበት አንዳንድ ጊዜ ሳይታሰብ «ቀጭን» ድምፅ ማውጣትና የድምፅ መጎርነን እንደ ጉርምስና ምልክት ይታያሉ፡፡ የአዳም ፍሬ በመባል የሚታወቀው ‹‹ማንቁርትም» ማደግና መታየት የሚጀምረውም በዚሁ ጊዜ ነው፡፡ ከዚህም ሌላ ብዙ ወንዶች ብጉር የሚያበጉሩ ሲሆን፣ በብብት፣ በደረትና በብሽሽት (በአባለ ዘርዕ) አካባቢ ፀጉር ማብቀል ይጀምራሉ፡፡ እንደዚሁም ከራስ እስከ ጽሕም በግራና በቀኝ የሚወርድ ለጊዜው ለስለስ ያለና ስስ ጠጉር ወይም ሪዝ ማቆጥቆጥ ይጀምራል፡፡ ይህንን ጽሕም (ሪዝ) መከርከምና መቀነስ እንጂ ሴት እስኪመስሉ ድረስ ሙሉ በሙሉ ልጭት አድርጐ ማንሣት የሚገባ አይደለም፡፡ ይህን በተመለከተ ፍትሐ ነገሥት መንፈሳዊና ዲድስቅልያ የተሰኙ መጻሕፍት እንዲህ ብለዋል፡፡ «ወባሕቱ ኢመፍትው ለነ ንላጺ ጽሕመነ ወኢንወልጥ ፍጥረተ ብእሲ ውስተ ካልዕ ግዕዝ - ነገር ግን ጽሕማችንን ልንላጭ የወንድነት መልካችንን ወደ ሌላ ማለትም ሴት ወደ መምሰል እንለውጥ ዘንድ አይገባንም::›› ማለት ነው:: ዲድ.አን.1፤ ፍት.መን.አን .11 የጉልምስና ምልክት የሆነው የዚህ ጠጉር ብዛት ከሰው ሰው ይለያያል:: ሆኖም ምን ያህል <<ወንድ>> መሆንን አመልካች አይደለም:: ሌለቹ የዐፍላ ጉርምስና ምልክቶች ደግሞ የሰውነት ጠረን መለወጥ፣ የዘር ፍሰት ወይም ሕልመ ሌሊት ማየት መጀመር ናቸው፡፡ «ሕልመ ሌሊት» ምንድር ነው? በዐፍላ የጉልምስና ወቅት አባለ ዘርዕ ወደ ሙሉ የዕድገት ደረጃ መድረስ ብቻ ሳይሆን መሥራትም ይጀምራል:: በዚህ ጊዜ ከንዑስ መሌሊት (ኀፍረተ አካል) ዘርዓ ብእሲ የሚባል የአፍንጫ ዛሕል (ንፍጥ) የሚመስል ፈሳሽ ነገር ይወጣል፡፡ ወንድና ሴት ግንኙነት በሚያደርጉበት ጊዜ ወደ ሴቲቱ ማኅፀን በመግባት ፅንስ እንዲፈጠር የሚያደርገው ይህ ፈሳሽ ንጥረ ነገር ነው፡፡ የወንድ ወጣቶች ሰውነት ይነስም ይብዛ በየጊዜው ከላይ ‹‹ዘርዓ ብእሲ›› ወይም «የወንድ ዘር» ተብሎ የተጠቀሰውን ፈሳሽ ንጥረ ነገር ያስወጣል፡፡ ለዘር የበቁ ወጣቶች ዘር የሚከፍሉት ወይም የሚወጣቸው በልዩ ልዩ መንገድ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ግን ተኝተው ሳለ በጠለቀ እንቅልፍ ሆነው ሕልም በሚያልሙበት ወቅት ነው፡፡ ይህ ሲሆን እንደ ጤናማ የተፈጥሮ ሂደት ይቆጠራል። የዚህ ዓይነቱን ሕልም መጽሐፈ መነኮሳት በአንድ ስፍራ «ሕልመ ጽምረት» በሌላ ቦታ ደግሞ «መስቆርርት ሕልም» ሲለው ይገኛል:: ሕልሙን ያየው ሰው ደግሞ «ዝንየት መታኝ» ወይም «ሕልመ ሌሊት» አገኘኝ ይላል፡፡ ይህ በቤተ ክርስቲያን ልጆች ዘንድ የተለመደና በቀላሉ የሚያግባባ የቃል አጠቃቀም ነው:: ወደ አቅመ አዳም እየደረሱ ባሉ ልጆች ላይ ይህ «የዘር ፍሰት» ባልጠበቁት ጊዜ ሲከስት በጣም ሊረብሻቸው ይችላል፡፡ ይልቁኑም ልጆቹ ከዚህ አስቀድሞ ስለ ጉዳዩ በተለያየ መንገድ በቂ ግንዛቤ ያላገኙ ከሆኑ መረበሻቸው በእጅጉ ይጨምራል፡፡ እነዚህ ታዳጊዎች እንዳይረበሹና ስለ ጉዳዮ የተሳሳተ ሐሳብ ይዘው እንዳያድጉ ለነገሩ በቂ ግንዛቤ እንዲያገኙ ከማድረግ ጋራ እንደ አስደሳች ተግባር በመውሰድ እያወቁ ዘራቸውን በራሳቸው እጅ ማፍሰስ እንዳይጀምሩ የነአውናንን በዚህ ተግባራቸው መቀሠፍ እየጠቀሱ ኃጢአትነቱን ኣጥብቆ ማስረዳት ያስፈልጋል:: መጽሐፍ ቅዱስ ስለ <<ዘር መውጣት>> እና በአጠቃላይ <<ፈሳሽ ነገር>> ስላለበት ሰው በዝርዝር ይናገራል፡፡ ዘሌ.15፥16፡ 15፥1-33  ይህንን ጨምሮ የወንድ ዘርን የሚመለከት ሐሳብ የያዙ መንፈሳዊ መጻሕፍቶችን ማንበብ ለወጣቶች የተሻለ ግንዛቤ ይሰጣቸዋል፡፡ ይህን በመሳሰሉ ፆታዊ ጉዳዮች ላይ ወጣቶች ጥያቄ ሲኖራቸው ከማን ጋር መወያየት የተሻለ እንደሚሆን ሊለዩ ይገባል፡፡ ልጆች የሚጓዙበት ተፈጥሮአዊ የሕይወት ጐዳና በሙሉ ጤናማ ወላጆች የተጓዙበት ስለሆነና ሌሎችም ብዙ ተሞክሮዎች ስላሏቸው ለልጆች ፆታዊ ችግር ጉዳት የሌለበት የመፍትሔ ሐሳብ ማቅረብ ይችላሉ፡፡ ካህናትና መምህራነ ቤተ ክርስቲያንንም ማማከር ለወጣቶች መንፈሳዊውን ሥርዓት እንዲያውቁ ይረዳቸዋል፡፡ እኩዮችንና ሌሎች ወጣቶችን ወይም የእግዚአብሔርን ቅዱስ ቃል መሠረት ያላደረጉ ጽሑፎችን መስማትና ማንበብ ጥቂት እውነትና ብዙ የፈጠራ ወሬ ያለበትን የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ወጣቶችን ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ ሊመሯቸው ይችላሉና ሊጠነቀቁባቸው ይገባል፡፡ «ሕልመ ሌሊት» ኃጢአት ነውን? በጠለቀ እንቅልፍ ላይ ሳሉ የሚከሠት ሕልመ ሌሊትን እንደ ኀጢአት እንዲቆጠርና እንዳይቆጠር የሚያደርጉ የተለያዩጨሁኔታዎች አሉ:: ስለዚህ ሕልመ ሌሊትን በጥቅሉ ኀጢአት ነው ወይም አይደለም ማለት አይቻልም፡፡ ነገር ግን እንደ ኀጢአት እንዲቆጠር የሚያደርጉ ሁኔታዎችን በመጠኑ መዘርዘር ይቻላል፡፡ ሀ. አጋንንት የሰው ልጆችን በልዩ ልዩ መንገድ ክፉኛ ይዋጓቸዋል፡፡ የሰው ልጆች ሲያንቀላፉ አጋንንት ግን ለቅጽበት እንኳን እያሸልቡም፡፡ ያንቀላፋውን ሰው እስኪነቃ ድረስ እንኳን አይጠብቁትም: አጋንንት የሰውን ልጅ በተኛበት ክፉ ክፉ ሕልም በማሳየት ይፈትኑታል፡፡ አንድ ጊዜ የተራቆተ የሴት ገላ፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ እንደ ወንድና ሴት አለሌና ባዝራ እየሆኑ ሲጨዋወቱና ሲደራረጉ በምትሐት ያሳዩታል፡፡ በዚህ ጊዜ እርሱም በዝሙት ሐሳብ ይሳብና በሕልሙ ዝሙት ሲፈጽም ያድራል፡፡ በዚህ መልኩ የተከሠተ ሕልመ ሌሊት «ጸዋግ» ወይም «ኅሡም» ሕልም ይባላል፡፡ ክፉ ወይም ጥፉ ሕልም ማለት ነው:: በዚህ መልኩ አጋንንት ሰውን እንደሚዋጉት በመጽሐፈ መነኮሳት እንዲህ ተጽፏል፡፡ «ይትቃተልዎ ሰይጣናት በመዓልት በሕሊናት እኩያት ወበሌሊት በአሕላማት ኅሡማት» በአማርኛ «ሰይጣናት የሰውን ልጅ ቀን ቀን ክፉ ሐሳብ በማሳሰብና በማሠራት በሌሊት ደግሞ ዝሙት የሞላበት አስጸያፊ ሕልም በማሳየት ይዋጉታል» ማለት ነው፡፡ በዚህ መልኩ ሰይጣናት ያቀረቡለትን ረቂቅ ፈተና ከመቃወም ይልቅ ደስ እያለው የሚያጣጥም ማለትም ከመጸጸትና ከመቆጨት ይልቅ በደስታ ስለ ዝሙት የሚያሰላስል፣ የሚዳራ፣ የሚዛለል፣ ወደ ዝሙት ከሚያመሩ ማናቸውም ነገሮች የማይሸሽ ሰው እነዚህ ነቅቶ ሳለ ያልተቃወማቸውን ተግባራት በሕልሙ በሚፈጽማቸው ጊዜ በተግባር እንደፈጸማቸው ያህል ኃጢአት ሆነው ይቆጠሩበታል:: ይህን የሚያስረዳ እንዲህ የሚል የመጻሕፍት ቃል ይገኛል:: «ዘይትቄበል በመዓልት ስሕተታተ ፍትወት ውስተ ልቡ ወኢይከሥታ ወለዝንቱ ሕሊናቲሁ ወአሕላማቲሁ ወፍትወታቲሁ ርኩሰት ትትሐሰብ ሎቱ ኃጢአተ» ይህም ‹‹በቀን ነቅቶ ሳለ ኃጢአትን ወዶ የሚቀበልና ገልጾ የማይናዘባት ለዚያ ሰው የረከሰች ሐሳቡ፣ ሕልሙ ኃጢአት ሆና ትቆጠርበታለች፡፡» ማለት ነው፡፡ በተጨማሪም <<ወኢይጻሙ ውስተ ንስሐ ወኢየኀሥሥ እም እግዚአብሔር ሥርየተ አበሳቲሁ በቀዳሚ ወለዝንቱ አሕላማቲሁ መስቆርርት ትትሐሰብ ሎቱ ኃጢአተ::›› ወደ አማርኛ ሲመለስ <<በንሥሐ ሥራ የማይደክም (ንስሐ የማይገባ)፣ በቀደመው ኃጢአቱ እግዚአብሐርን ይቅር በለኝ የማይለው ለዚያ ሰው የሚያጸይፉ ሕልሞቹ ዕዳ በደል ሆነው ይቆጠሩበታል::» ማለት ሲሆን ይህ የሆነበት ምክንያት ሰውዬው የነዚህ ሥራዎች ተቃዋሚ ባለመሆኑ ነው፡፡ ይህም ንስሐ ባለመግባቱ ይታወቃል:: እነዚህን ኃጢአቶች የማይቃወም ሰው ደጋፊ ስለሆነ በነዚህ ኃጢአቶች ለምን እጠየቃው ለማለት አይችልም፡፡
2 23411Loading...
03
ከሥራ ብዛት ሕልም እንደሚታይ ጠቢቡ ሰሎሞን «ሕልም በሥራ ብዛት ይታያል» በማለት የተናገረው ቃል ያስረዳል፡፡ መክ5፥3 እንደዚሁም ሁሉ ከምኞት ብዛትም ሕልም ሊከሠት ይችላል:: ክፉ ምኞት በሕልምም ቢሆን ማርከሱ አይቀርም፡፡ ሐዋርያው ይሁዳ «እያለሙ ሥጋቸውን ያረክሳሉ» በማለት የጻፈው መልእክት እዚህ ቦታ ላይ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ ይሁዳ 1፥ (ቁ8) እንደሚታወቀው ነፍስ እንደ ሥጋ አትተኛም እንቅልፍም በእርሷ ዘንድ የለም:: ስለዚህ ነፍስ በእንቅልፍ ልቤ ነው በማለት ማመካኘት አትችልም፡፡ ነፍስ በረከሠ ሕልም ምክንያት ከተጠያቂነት ነፃ መሆን የምትችለው ሥጋ ከእንቅልፍ ውጭ በሚሆንበት ጊዜ ተግባረ ዝሙትን በመቃወምና በመጥላት ከእግዚአብሔር ጋር መሆኗን ስታስመሰክር ብቻ ነው፡፡ ሌላው ሕልመ ሌሊትን እንደ ኃጢአት የሚያስቆጥረው ሁኔታ አብዝቶ መመገብ ነው:: ጾም ለጽድቅ ሥራ ሁሉ መሠረት እንደሆነ እንደዚሁ አብዝቶ መመገብም የኃጢአት ሁሉ መሠረት ነው:: <<እኅልም ጉልበትን ያጠነክራል>> ተብሏልና፡፡ ሰው ሁሉ ለቁመተ ሥጋ ያህል መመገብ ያሻዋል፡፡ መዝ103፥15 ሆኖም ለልዩ ልዩ የምግብ ዓይነቶች መጐምጀትና ከዚያም አልፎ አብዝቶ መመገብ ነፍስን ለሥጋ ማስገዛት ነው:: ይህ ደግሞ ገዥዋን ተገዥ ማድረግ በመሆኑ ግፍ ነው፡፡ ሊቀ ጳጳስ ለዐቃቢት እንደመገዛት ያህል ነውና፡፡    ለሥጋ መገዛት የሚያሻውንም ሁሉ ጥሮ ግሮ ማቅረብ የገዛ ሰውነትን ማምለክ ነው፡፡ ሐዋርያው «ሆዳቸው አምላካቸው ነው፡፡» በማለት የተናገረው «እንብላ እንጠጣ ነገ እንሞታለን» በማለት ከሞት በኋላ ተከትሎ የሚመጣባቸውን ወቀሳና ፍርድ ችላ ላሉ ሰዎች ነው፡፡ በአዳምና በሔዋን ሊነገር የማይችል ውርደትና ጉስቁልና ያመጣባቸው ለሆዳቸው መገዛታቸው ወይም ለመብል መሳሳታቸው መሆኑ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ ፊልጽ3፥19፣ 1ቆሮ 15፥32፡ ዘፍ3፥ 1-24 ወጣቶች ይልቁኑም በዝሙት ሥራና ሐሳብ በእጅጉ የሚፈተኑ ስዎች በሚገባ መጾም አለባቸው:: በሰውነት ላይ የዝሙት ፆር ጸንቶ ሳለ አብዝቶ መመገብ የሚቃጠል ክርን ሰም እንደ መመገብ (መቀባት) ነው:: ሰም ክሩን የበለጠ እንደሚያቀጣጥለው አብዝቶ መመገብም የዝሙት ፍላጐትን የበለጠ እንዲበረታ ያደርገዋል፡፡ መጽሐፈ መነኮሳትም ይህን ሲገልጽ <<መብዝኀ መባልዕትኒ ምስለ ኃይለ ውርዝውና ያስተዳልው ምጽአተ ሕማማት በኃይል፣ አብዝቶ መመገብ ከወጣትነት ጋር የኃጢአት ሐሳብን በግድ እንዲመጣ ያደርጋሉ» ይላል፡፡ (ማር ይስ አን.20 ምዕ.1) አብዝቶ መመገብና ለመብል መሳሳት የኃጢአት ምንጭ ከመሆናቸው ባሻገር በራሳቸው ኃጢአት ሆነው ይቆጠራሉ፡፡ የሰዶም ኃጢአት አብዝቶ መመገብና ጠግቦ መብላት እንደ ነበር መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር፦ «እነሆ የእኅትሽ የሰዶም ኃጢአት ይህ ነበረ፡ ትዕቢት፣ እንጀራን መጥገብ፣ መዝለልና ሥራ መፍታት በእርስዋና በሴቶች ልጆቿ ነበረ>> ይላል:: «እንጀራን መጥገብ›› ኃጢአት መባሉን ተመለከትክን? ሕዝ16:49 ስለዚህ በልክ ተመገብ እንጂ ለስስት አትሽነፍ፡፡     ሳይጠነቀቅ ቀርቶ አብዝቶ ከመመገቡ የተነሣ ሕልመ ሌሊት ያገኘው ሰው እንደ ኃጢአት ይታሰብበታል፡፡ ምክንያቱም አብዝቶ መመገብ ኃጢአትን እንደሚወልድ እያወቀ ችላ ብለሎ በመመገቡ ነው፡፡ መጽሐፈ መነኮሳት አብዝቶ ከመመገብ የተነሣ ሕልመ ሌሊት ስለሚከሠትበት ሰው እንዲህ በማለት ይተርካል፡፡ «ወመንጸፈ ኅርትምናሁስ ወልብሱ ወትፍግዕተ ሥጋሁ ኩለንታሁ ርሱሕ፡፡ በእንተ ብዝኀ ውኂዝ ርኵስ ዘይውኅዝ እም ሥጋሁ ከመ ዐይነ ማይ አኮ በሌሊት ባሕቲቱ ዘይመጽእ ዝንቱ እስመ ሥጋ ያውኀዝ ወትረ ወያረኩሶ ለሕሊና›› ወደ አማርኛ ሲመለስ «ከሰውነቱ እንደ ምንጭ የሚነቃ ርኩስ ዘር በዝቶ ስለ ፈሰሰ ጎስቋላ ምንጣፉ፣ልብሱ፣በዝሙት ደስ የተሰኘ ሥጋው ሁለንተናው የረክሰ ነው:: ሥጋ ሁልጊዜ ያነቃዋልና ዘሩ የሚፈሰው በሌሊት ብቻ አይደለም፡፡ ሕሊናውንም ያረክሰዋል›› ማለት ነው፡፡ ይህም ለምግብ ከመሳሳትና አብዝቶ ከመመገብ የተነሣ የሚመጣ ሕልመ ሌሊት እንዴት ሰውን እንደሚያረክስና ኃጢአት ሆኖ እንደሚቆጠርበት ያስረዳል:: ማር.ይስ. አን.20 ምዕ.2 አንድ ሰው በንቁ ልቡና ሳለ ወደ ኃጢአት የሚየመሩትን ነገሮች ተግቶ እየተቃወመ ነገር ግን በተኛና ባንቀላፋ ጊዜ ዝንየት ቢያገኘው በተራክቦ፣ ዘር በማፍሰስ ያያት ሕልሙ ዕዳ ሆና አትቆጠርበትም፡፡ መሐሪ የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውዬው ተቃወማት እንጂ ወዶ ወደ እርሷ እንዳልተሳበ ያውቃልና፡፡ አንቀላፍቶ ላለ ዘሩ ቢወርድ ፈልጎ አለመጣውምና ዕዳ አይሆንበትም፡፡ ነገር ግን ተቃውሞ ለማራቅ አልተቻለውም:: ይህ ከዚህ በላይ የሰፈረው ሐሳብ በግዕዙ እንዲህ ይነበባል። <<ወዘሰ ይትጋደል ሕሊናተ እንተ የሀውክዋ ሰይጣናት ውስተ ልቡ በመዓልት ወዝኒ አሕላማቲሁ መስቆርርት ዘበሐሊመ ስዕበት ኢትትሐሰብ ሎቱ ኃጢያተ፡፡ እስመ እግዚአብሔር ጻድቅ ወመሐሪ የአምር እስመ ውእቱ በጊዜ ፈቂዶቱ ኢተሰፍጠ በፍትወት አላ ተቃተላ ወሰደዳ፡፡ ወለእመኒ ወረደት ላዕሌሁ በጊዜ ንዋሙ ኢየሐስባ ላዕሌሁ ኃጢያተ እስመ ውእቱ ኢተቀበላ በፈቃዱ ወኢኮነ ክሀሌ ለተጋድለሎታ ወሰዲዶታ ወአርኅቆታ::>> ኃጢአትን ከልቡ በሚቃወምና በሚጠላ ሰው ላይ ሕልመ ሌሊት እንደ ኃጢአት እትቆጠርበትም፡፡ ይህን ለማስረዳት አረጋዊ በፊልክስዮስ መጽሐፍ እንዲህ የሚል ሐተታ አስፍሯል፡፡ ሰይጣን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን:- የኔን ወገኖች አጋንንትን ባንተ ወገኖች ላይ አሰለጥናቸዋለው፣ ነገር ግን ወገኖቼ የአንተን ወገኖች አይችሏቸውምና ድል ይሆናሉ:: እነርሱ ምንም ባይችሏቸው እኔ ግን «በሕልመ ሌሊት አስሕቶሙ» «በሕልመ ሌሊት አስታቸዋለሁ።» አለው:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ለሰይጣን እንዲህ ሲል መለሰለት <<ለእመስ ድቀት ይወርስ አባሁ ዛቲኒ ትትሐሰብ ኀጢአተ ላዕለ እሊአየ።» ትርጓሜውም <<ጭንጋፍ አባቱን ለመውረስ ከቻለ ሕልመ ሌሊትም በወገኖቼ ላይ ዕዳ ሆና ትቆጠርባቸዋለች» ይህም ማለት ተስዕለተ መልክዕ ያልተፈጸመለት ጭንጋፍ አባቱን መስሎና አህሎ ባለመገኘቱ የአባቱ የሆነውን ነገር መውረስ እንደማይቻለው እንደዚሁም በተግባር ያልተፈጸመች ሕልመ ሌሊትም እንደ ተግባር ኃጢአት ተቆጥራ አታስኮንንም ማለት ነው፡፡ : አረጋዊ እንዲህ ማለቱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስና ሰይጣን ከሕልመ ሌሊት አንጻር ያላቸውን ፈቃድ ለማስረዳት ፈልጐ ነው እንጂ ሰይጣን ደፍሮ ኢየሱስ ክርስቶስን ተናግሮት ኢየሱስ ክርስቶስም እንዲህ ተዋርዶ ለዲያብሎስ መልስ ሰጥቶት አይደለም:: ይህ ቃለ ምልልስ በመጽሐፈ ኢዮብ ምዕራፍ አንድ ላይ እና በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ አራት ላይ ከሰፈረው የሰይጣንና የእግዚአብሔር ንግግር ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡ በሕልመ ሌሊት በተደጋጋሚ የሚፈተን ሰው በቅርብ እናውቅ ይሆናል:: እንዲህ ባሉ ሰዎች ላይ መፍረድ ተገቢ አይደለም፡፡ ለምን ቢባል ጥፋት ሳይገኝባቸው በዚህ መልኩ የሚፈተኑ ብዙ ሰዎች ስለሚገኙ ነው:: እኛም ብንሆን በዚህ ፈተና እንዳንወድቅ መጠንቀቅና መጸለይ ይገባናል፡፡ በሰው መፍረድ ራስን ወደ ወጥመድ ማስገባት ነውና፤ በሰው ከመፍረድ ለሚፈተን ለዚያ ሰው መጸለይ በእጅጉ ይበልጣል፡፡ ሰው ራሱ በራሱ ላይ ይህን የመሰለ ፈተና ማምጣቱን እየመረመረ ኃጢያተኛ ነኝ ቢል ተገቢ ነገር ነው:: ሌሎች ግን በእርሱ ላይ ቢፈርዱበት ኃጢአት ሠሩ ማለት ነው:: ፈጣሪ በሌላው እንድንፈርድ አይፈልግምና፡፡
2 8319Loading...
04
.                      ምዕራፍ ሦስት              የዐፍላ ጉልምስና ምልክቶች     ዐፍላ የጉርምስና ወቅት የጉልምስናን የመጀመሪያ ወቅት ይሸፍናል፡፡ ጉልምስናና ጉርምስና የሚሉት ቃላት አንድ ናቸው። የዘይቤ እንጂ የምስጢር ልዩነት የላቸውም፡፡ ይህ ወቅት በፆታ የመብሰል ምልክቶች የሚታዩበት ዕድሜ ነው፡፡ ከላይ እንደተጠቀሰው ጉልምስና የሚጀምርበት ዕድሜ እንደየሰዉ ሁኔታ ከፍና ዝቅ ሊል ስለሚችል የኔ ፈጥኗል የኔ ደግሞ ዘግይቷል በማለት ሊጨነቁበት የሚገባ አይደለም፡፡ የሆነው ሆኖ አንድ ሰው በጉልምስና ወቅት ሊከሠቱ ከሚችሉ የአካል ለውጦች ጋር ተያይዘው የሚከሠቱ ሌሎች ለውጦችንበሚገባ ሊያውቃቸውና ሊጠብቃቸው ይገባዋል:: እነዚህም ለውጦች በአጭሩ ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፡፡   በጉልምስና ወቅት ከሚከሠቱ የአጥንቶች ዕድገትና የጡንቻዎች መለጠጥ የተነሣ በወጣቶች ላይ የመፍዘዝና የቅንብር ጉድለቶች ይስተዋላሉ:: በዚህ ምክንያት ለአደጋ መጋለጥ እንዳይኖር ተጨማሪ ጥንቃቄ ቢያስፈልግም ይህ ዓይነቱ የመቅዘዝና ቅስስ የማለት ሁኔታ ጊዜውን ጠብቆ ያልፋልና የሚያሳስብ ጉዳይ አይደለም:: ወጣቶች በብዙኀኑ ዘንድ የሚታወቁበት ገጽታ ንቁነትና ቀልጣፋነት ቢሆንም በአፍላ የጉልምስና ወቅጥ መፍዘዝና ቅስስ የማለት ሁኔታ መከሠቱን ማወቅ ለሚያሳዩት ባሕርይና ያልተለመደ እንቅስቃሴ ሌላ ትርጓሜ ከመስጠት እንድንቆጠብ ይረዳል፡፡
2 3356Loading...
05
Do you enjoy reading this channel? Perhaps you have thought about placing ads on it? To do this, follow three simple steps: 1) Sign up: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox 2) Top up the balance in a convenient way 3) Create an advertising post If the topic of your post fits our channel, we will publish it with pleasure.
1 8423Loading...
06
ምኩራብ የዐብይ ጾም ሦስተኛ እሑድ(ሳምንት) ሦስተኛው ሰንበት ምኩራብ ተብሎ የተሰየመበት ምክንያት በዚሁ ዕለት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ከዋዜማው ጀምሮ እስከ ሰላሙ ድረስ በዕለተ ሰንበት «ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ» «ምኩራብ» ማለትም ቀጥተኛ ፍችው ኮረብታ፣ ተራራ የሚያኸል ታላቅ ሕንጻ ማለት ነው፡፡ ከዚህም የተነሣ የአይሁድ ቤተ ጸሎት ወይም ቤተመቅደስ ማለት ይሆናል፡፡ ዐቢይ ፍሬ ቃሉ ግን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያነ ሥጋን በትምህርቱ፣ ድውያነ ነፍስን በታምራቱ ሲፈውስ በምኩራብ እየተገኘ የፈጸመውን የማዳን ሥራ በኀሊና እያሳሰበ የሚያስተምር ሦስተኛ ሳምንት ነው፡፡ ዮሐ. 2:12 «ኢየሱስ በሰንበት ቀን ወደ አይሁድ ምኩራብ ገባ» እያለ ኢየሱስ በአይሁድ ምኩራብ ማስተማሩን እየጠቃቀሰና እያነሣሣ ስለሚዘምር ይህን ሰንበት ለዚህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምኩራብ እየገባ ለማስተማሩና በምኩራብ የሚሸጡ የሚለውጡ ነጋዴዎችን ለማስወጣቱ ቤተ መቅደሱን ለማስከበሩ መታሰቢያ ሳምንት ነው። የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ) ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ ወመሐረ ቃለ ሃይማኖት ወይቤሎሙ ምጽዋተ አበድር እመሥዋዕት አነ ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት እግዚኣ ውእቱ ለሰንበት ወልደ እጓለ እመሕያው ኢትግበሩ ቤተ አቡየ ቤተ ምስያጥ ቤትየሰ ቤተ ጸሎት ይሰመይ ቦአ ምኩራቦሙ ወገሠፆሙ ያርምሙ አንከሩ ምህሮቶ ሞገስ ቃሉ ወጣዕመ ነገሩ ወሣዕሣዓ አፉሁ፡፡ ትርጉም:- ጌታችን ኢየሱስ ወደ አይሁድ ምኩራብ ገባ፤ የሃይማኖት ቃልን አስተማረ፤ ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወዳለሁ፤የሰንበት ጌታዋ የምሕረት አባቷም እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም የሰንበት ጌታዋ ነው ፡፡ያባቴን ቤት የንግድ ቦታ አታድርጉት፤ቤቴስ የጸሎት ቤት ይባላል (እያለ የሃይማኖትን ቃል አስተማራቸው፡)፡ ወደ ምኩራባቸውም ገብቶ ዝም ይሉ ዘንድ ገሠፃቸው፤ እነርሱም ትምህርቱን፣ የቃሉን ግርማ፣ የአነጋገሩን ጣዕምና፣ የአንደበቱን ቅልጥፍና አደነቁ። ምስባኩም፦ መዝ ፷፰፥፱ "እስመ ቅንዐት ቤትከ በልዐኒ ትዕይርቶሙ ለእለይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ" "የቤትህ ቅናት በልቶኛል የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆብኛልና ነፍሴን በጾም አስመረርኳት" በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ ጥቅሶች፦ -ቆላ ፪፥፲፮ እስከ ፍጻሜ -ያዕ ፪፥፲፬ እስከ ፍጻሜ -የሐዋ ሥራ ፲፥፩-፱ ወንጌሉም፦ ዮሐ ፪፥፲፪ እስከ ፍጻሜ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
4 23742Loading...
07
@Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
3 91111Loading...
08
"ምኩራብ" በዲያቆን ዘማሪ ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
3 93331Loading...
09
"በእጸ መስቀሉ የተከፈለልኝ" ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
6 99055Loading...
10
@Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
5 5219Loading...
11
መጋቢት ፲ በዓለ ቅዱስ መስቀል መጋቢት አስር በዚህች እለት የክብር ባለቤት ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል የተገለጠበትና የተገኘበት ነው። የዚህም የከበረ ዕፀ መስቀል መገለጡና መገኘቱ ሁለት ጊዜ ሆኗል። መጀመሪያ የፃድቁ ንጉስ የቆስጠንጢኖስ እናት በሆነች በንግስት እሌኒ እጅ ነው። እርሷ ለእግዚአብሄር ተስላ ነበርና ልጇ ቆስጠንጢኖስ ወደ ክርስቲያን ሀይማኖት ቢገባ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዳ መስቀሉን እስከ አገኘችው ድረስ ልትፈልግው በኢየሩሳሌም ያሉ ቅዱሳት መካናትንና አብያተ ክርስቲያናትን ልታንፃቸው ነው። ከዚህ በኋላ ልጇ አምኖ የክርስትና ጥምቀትን በተጠመቀ ጊዜ እሌኒ ቅድስት ወደ ኢየሩሳሌም ሄደች ከእርሷ ጋርም ብዙ ሰራዊት ነበር ደርሳም ስለ ከበረ መስቀል መረመረች የሚያስረዳት አላገኘችም የአይሁድ ወገን የሆነ አንድ ሽማግሌ ሰው አስራ በርሀብና በጥማት አስጨነቀችው። በተጨነቀም ጊዜ ለንግስት እሌኒ "የጉልጎታን ኮረብታ አስጠርጊ" ብሎ ነገራት እርሷም ይጠርጉ ዘንድ አይሁድን አዘዘቻቸው። ቤቱን የሚጠርግ ሰው ሁሉ ጥራጊውን በውስጡ የከበረ መስቀል በአለበት በጌታችን መቃብር ላይ እንዲጥል አይሁድ አስቀድመው አዝዘው ነበርና ንግስት እሌኒ እስከደረሰችበት ጊዜ ከሁለት መቶ አመት በላይ ጥራጊያቸውን ሲጥሉበት ኖሩ ኮረብታም ሆነ። አይሁድም በጠረጉ ጊዜ ሶስት መስቀሎች ተገለጡ የክብር ባለቤት ክርስቶስ የተሰቀለበት የትኛው እንደሆነ አላወቁም። የሞተ ሰውም አግኝተው አመጡ። አንዱንም መስቀል አምጥተው በሞተው ሰው ላይ አኖሩት አልተነሳም ደግሞ ሌላውን መስቀል አምጥተው በሙቱ ላይ አኖሩ አሁንም አልተነሳም ከዚህም በኋላ ሶስተኛውን መስቀል አምጥተው በሙቱ ላይ አደረጉት ያንጊዜ የሞተው ሰው ተነሳ እሌኒም የክርስቶስ መስቀል እንደሆነ አውቃ ሰገደችለት የክርስቲያንም ወገኖች ሁሉ ሰገዱለት። ለልጇ የላከችው ይህ መስቀል ነው የሚል በሌላ መፅሀፍ ይገኛል የቀረው ግን ግንዱ በውስጡ ተተክሎበት የነበረው ከእርሱም እኩሌታውን ከቅንዋቱ ጋራ ወደ ልጅዋ የላከችው ነው። ከዚህም በኋላ ስርዓታቸውና የህንፃቸው ነገር በመስከረም ወር በአስራ ሰባት ተፅፎ የሚገኝ አብያተ ክርስቲያናትንና የከበሩ ቦታዎችን አነፀች። ሁለተኛው በሮሙ ንጉስ በህርቃል ዘመን የሆነው ሲሆን የፋርስ ሰዎች በግብፅ አገር ሳሉ ወደ አገራቸው ሊመለሱ ወደዱ። ከሹማምንቶቻቸው አንዱ የጦር መኰንን ተነጥሎ ወደ ኢየሩሳሌም አልፎ ደረሰ ወደ ከበረ መስቀል ቤተ ክርስቲያንም ገባ። መስቀሉም በላዩ በተተከለበት ግንድ ፊት ታላቅ ብርሀን ሲበራ አይቶ ሊያነሳው እጁን ዘረጋ። እሳትም ወጥታ እጁን አቃጠለችው። ከክርስቲያን በቀር ማንም ሊነካው እንደማይችል የመስቀልን የክብሩን ነገር ሰዎች ነገሩት። ሁለት ዲያቆናትንም ይዞ የከበረ መስቀልን እንዲሸከሙ አዘዛቸው ከኢየሩሳሌምም ብዙ ሰዎችን ማርኮ ወደ አገሩ ተመለሰ። የፋርስ ሰዎች ኢየሩሳሌምን እንዳጠፏት ብዙዎች ሰዎችንም እንደማረኩና የከበረ የክርስቶስንም መስቀሉን እንደወሰዱ የሮም ንጉስ ህርቃል በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ። ስለርሱም እንዲፆሙ ምእመናንን አዝዞ ወደፋርስ ዘምቶ ወጋቸው ብዙዎችንም ገደላቸው የከበረ እፀ መስቀልንም እየፈለገ በሀገራቸው ሁሉ ዞረ ግን አላገኘውም። ያ ዲያቆናቱና መስቀሉን የወሰደ መኰንን ከቦታዎች በቤቱ አንፃር ባለ በአንድ ቦታ ላይ ወስዷቸው ጥልቅ ጉድጓድ እንዲቆፍሩ አዝዞ በዚያ የከበረ መስቀልን አስቀበረ እነዚያንም ዲያቆናት ገደላቸው። ነገር ግን ያ መኰንን የማረካት የካህናት ወገን የሆነች በእርሱ ቤት የምትኖር አንዲት ብላቴና ነበረች። እርሷም የከበረ መስቀልን ሲያስቀብርና ሁለቱን ዲያቆናት ሲገድላቸው በቤቱ ውስጥ ሁና በመስኮት ትመለከት ነበር ወደ ንጉስ ህርቃልም ሂዳ መኰንኑ ያደረገውን ሁሉ ነገረችው። ይህም ንጉስ ሰምቶ እጅግ ደስ አለው ያቺ ብላቴናም መራችው ከእርሱም ጋራ ብዙ ሰራዊት ሆኖ ኤጲስቆጶሳትና ካህናትም ነበሩ ።ወደ ቦታውም እስከምታደርሳቸው ያቺን ልጅ ተከተሏት ቆፍረውም የከበረ እፀ መስቀልን አገኙት ከአዘቅቱም አወጡት ንጉሱና ሰራዊቱም ሰገዱለት። በልብሰ መንግስቱም አጎናፀፈው ታላቅ ክብርንም አከበረው ከሰራዊቱም ጋር እጅግ ደስ አለው። የዚህም መስቀል ሁለተኛ የተገለጠበትና የተገኘበት በዚች ቀን በመጋቢት አስር ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ንጉሱ የከበረ እፀ መስቀልን ተሸክሞ ወደ ቁስጥንጥንያ ከተማ ወሰደው፡፡ የመድኃኒታችን የመስቀሉ በረከት ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን። ©ስንክሳር @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
5 48825Loading...
12
             የወጣቶች ምኞት   የሰው ልጆች ከልጅነት ወደ ወጣትነት በሚሸጋገሩባቸው ወራትና ዓመታት አካላቸው እንደሚደረጅና አእምሮቸው እንደሚዳብር ሁሉ ምኞታቸውም በዓይነትና በመጠን እየሰፋና እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ይህ የወጣቶች ምኞት በአመዛኙ ከመንፈሳዊነት ጋር የሚቃረንና ሥጋዊ በመሆኑ «እኩይ ፍትወት» ይባላል፡፡   ከዚህም በተጨማሪ በጎልማሶችና በኮረዶች ላይ የሚከሠተውን ምኞት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ <<አንተ ግን ከክፉ የጎልማስነት ምኞት ሽሽ>> በማለት የክርስትና ልጁን ጢሞቴዎስን በመከረበት ጊዜ ይህንን የወጣትነት ምኞት «ክፉ የወጣትነት ምኞት>> ብሎ ሲጠራው እናነባለን፡፡   በእርግጥ በወጣትነት ዘመን የሚገኝ ምኞት እጅግ ክፉ ነው:: ወጣትነት የሚሠራበት ዘመን እንጂ የሚመኙበት ዘመን አይደለምና። በተጨማሪም በዚህ ዘመን የሚከሠት ምኞት በወጣቶች አእምሮ ክፉነቱ ሊደረሰበት የማይችልና አታላይ ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ «ሰው ራሱ በገዛ ምኞቱ ሲሳብና ሲታለል ይፈታናል::>> በማለት እንደተናገረው በወጣትነት ዘመን የሚገኝ ምኞት ከመጠን በላይ ወደ ጥፋት የሚስብ፥ የሚጐትትና <<የሚያታልል>> ነው፡፡   በተለይም <<በገዛ ምኞቱ ሲሳብ>> የሚለው ቃል ምኞት ከፍተኛ ጉልበት እንዳለው ይጠቁማል፡፡ በወጣትነት ዘመን ምንም አእምሮ የበሰለ ቢሆን ከዚያ የሚበረታው ግን ምኞት ነው፡፡በወጣቶች ላይ ከዕውቀታቸው ይልቅ ምኞታቸው መበርታቱን ለማስረዳት ወጣትነት <<በዘመነ ኦሪት>> ይመሰላል፡፡   ኦሪት ከመሠራቷ በፊት ያለው ዘመን የሕገ ልቡና ዘመን ይባላል:: በዘመኑ ምንም ሕግና ሥርዓት ባለመኖሩ ሰው በልቡናው እንደ መሰለው ይኖር ነበር። እንዲሁም ሁለ ሕፃናት በልቡናቸው እንዳሰቡት ስለሚኖሩ በሕገ ልቡና የሚኖሩ ሰዎችን ይመስላሉ:: በዘመነ ኦሪት ደግሞ በመስፍኑ ሙሴ አማካኝነት ለእስራኤላዊያን ሕግ ተሰጠ:: ዘመኑም ዘመነ ኦሪት ተባለ፡፡ ሕገ ኦሪት በዘመኗ ክፉና ደግን ለመለየት አስችላለች:: እንደዚሁም ሁሉ ወጣትነት ከሕፃንነት ዘመን ይልቅ ክፉና ደግን ለመለየት የሚቻልበት ዕድሜ በመሆኑ በዘመነ ኦሪት ይመሰላል፡፡ ሆኖም ምንም ዕውቀት ቢገኝ በዘመነ ኦሪት የሰው ባሕርይ በኃጢአት የጐሰቆለ ስለ ነበር ሕጉን ፈጽሞ ለመጽደቅ አልተቻለም ነበር። በተመሳሳይ መልኩ ወጣቶች ዕውቀታቸው እየጨመረ ቢመጣም ምኞታቸውም የዛኑ ያህል ስለሚበረታና ስለሚስባቸው ዕውቀታቸውን ተጠቅመው የሚያጸድቃቸውን ጐዳና ለመከተል ይቸግራሉ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ <<በብልቶቼ ውስጥ ያለው ይህ የኀጢአት ሕግ (ምኞት) ወደ እርሱ ማረከኝ ተበረታታብኝ።>> ሮሜ7፥23 በማለት የተናገረው በወጣቶች ዘንድ ምኞት ምን ያህል ወጥመድ እንደሆነ ሲገልጽ ነው፡፡   ቅዱስ አባ ሕርያቆስም ስለ እመቤታችን ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም አስተዳደግ በተናገረበት የቅዳሴ መጽሐፍ እንዲህ ብሏል “አኮ ድንግል ወራዙት ስፉጣን ዘናዘዙኪ አላ መላእክተ ሰማይ ሓወጹኪ፤ ድንግል ሆይ የሚያታልሉ ጕልማሶች ያረጋጉሽ አይደለሽም:: የሰማይ መላእክት ጎበኙሽ እንጂ>> ይህ አገላለጽ ወጣቶች በወጣትነት ምኞት እንደሚታለሉ ከመግለጹም ባሻገር እነርሱ በምኞታቸው ተሸንግለው ሌላውን ለማታለል እንደሚያባብሉ ይናገራል፡፡ እመቤታችን ግን በሰማይ መላእክት ተጎበኘች እንጂ በሚያታልሉ ጐልማሶች አልተጽናናችም፡፡    <<ምኞት>> በውስጣችን እንዲኖርና እንዲያድግልን የምንንከባከበው ነገር መሆን የለበትም:: ምኞት ተስፋ አይደለምና፡፡ ኃጢአተኛ ሰው ምኞት ያበዛል። <<ኃጥእ ቀኑን ሙሉ ይመኛል።>>በማለት ጠቢቡ ሰሎሞን የተናገረው ለዚህ ነው፡፡ ምኞት ተጭኖን እንዳንሞት ምኞታችንን መወሰን ጥረትን ግን ማብዛት መልካም ነው።    «ምኞት። አስደሳችና ጣፋጭ ነገር ትመስል ይሆናል እውነቱ ግን እንዲህ አይደለም፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ምኞት እንዲህ ይላል፡- <<እስመ ፍትወት አኮ ጣዕም ይእቲ አላ ስሕተት ወዳኅፅ>> ይህም <<ምኞት ስሕተትና ውድቀት ናት እንጂ ጣፋጭ አይደለችም::>> ማለት ነው፡፡ ምኞትን ማብዛት ልፋትን ወይም ተስፋ መቁረጥን ማብዛት ነው። ምክንያቱም ምኞትን ለማሳካት ብዙ መድከም ከማስፈለጉም በላይ ብዙ ምኞት ካልተሳካ የሚያስከትለው ተስፋ መቁረጥም እንደዚሁ ብዙ ይሆናል።   ብዙ ወጣቶች የሚመኙት ጉዳት የሚያስከትልባቸውንና ከጥቂት ጊዜ በኋላም በብርቱ የሚያስቀጣቸውን ነገር ነው፡፡ ከሁሉ የሚደንቀው ደግሞ ጓጉተው ይፈልጉት እንጂ ሲያገኙት ወዲያው የሚሰለቹት ወይም የሚጸጸቱበት መሆኑ ነው:: አሁን ሀብታም ከመሆን በላይ ምንም የምፈልገው ነገር የለም ትላለህ:: ሀብታም ስትሆን ግን ይህ ከንቱ እንደሆነና ሌላ የሚቀርህ ብዙ ነገር እንዳለ ይሰማሃል። ይህ የሚሆነው ሁሉንም ነገር የተሟላና ፍጹም የሚያደርገው የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በመሆኑ ነው። ፈጣሪን ሳይጠጉ ምንም ነገር በቂና አርኪ መሆን አይችልም:: ስለዚህ መመኘትና ለማግኘት መጣር ብቻ ሳይሆን አስቀድመህ ፈጣሪህን መጠጋት ይኖርብሀል።   በወጣትነት የሚከሠት ምኞት አንድ ብቻ አይደለም:: ወጣቶች ሁሉም ያምራቸዋል። ከዚህ የተነሣ በአንድ ነገር ላይ መርጋትና መጽናት አይሆንላቸውም:: ተምሮ በማዕርግ መሠረቅ፣ አጭቶ ማግባት፣ ሀብታም ነጋዴ መሆን፣ ትልቅ ባለሥልጣን መሆን ጊዜ ሰጥተን በተራ ብንኖርባቸው ጊዜ ጠብቀው ይሳካሉ፡፡ እነዚህን ነገሮች በአንድ ጊዜ ለማሳካት ብንጥር ይሳካሉን? አበው <<ሁለት የወደደ አንዱን ሳያገኝ ሄደ።>> እንደሚለት ይሆንና አንዱም ላይሳካልን ይችላል:: ስለዚህ ወጣቶች አንድን ነገር መጀመር ሳይሆን በእርጋታ ሆኖ እስከ መጨረሻ መፈጸም እንደሚኖርባቸው ማወቅ አለባቸው::   ከዚህም ሌላ ወጣቶች ምኞቶቻቸው ብዙ ከመሆናቸው የተነሣ ሁለት የማይጣጣሙ ነገሮችን በአንድ ላይ የሚመኙበት ጊዜ አለ፡፡ ሙሽራ ሲያዩ ማግባትንና መውለድን ይመኙና በዚያው ጊዜ ደግሞ ልቡናቸው በመንፈሳዊ ነገር ተነክቶ መመንኮስና መመነንን የሚመኙበት ጊዜ አለ። ታዲያ እነዚህን ሁለት የሚጻረሩ ፍላጐቶች በአንድ ሰው ሕይወት ውስጥ እንዴት ማስኬድ ይቻላል:: ይህ መታወክ ነው።  እንዲህ ያለ ነገር ሲከሰት ወጣት ከመሆናችን የተነሣ እሳታዊና ነፋሳዊ ባሕሪያችን እየተሟገቱ ፈተና ላይ መውደቃችንን ተረድተን ብንታገሥ እንዲህ ያለ ፈተና ከጊዜ ብዛት ራሱ ይርቃል።   በማቴዎስ ወንጌል <<ዝናብም ወረደ ጐርፍም መጣ ነፋስም ነፈስ ያንንም ቤት ገፋው በዓለት ላይም ስለ ተመሠረተ አልወደቀም>> ማቴ 7፥25 ተብሎ የተጻፈው ኃይለ ቃል ሲተረጐም <<ቤት>> የተባለው የወጣት ሕይወት ነው፡፡ <<ነፋስ ነፈሰ>> ማለት የአጋንንት ፈተና በወጣቱ ላይ ተነሣበትና ከሴት ርቆ ንጽሕናውን ጠብቆ እንደ እንጦንስና እንደ መቃርስ ለመኖር እንዲመኝ አደረገው ማለት ነው ይለናል፡፡ <<ዝናብም ወረደ>> ማለት ደግሞ ያንኑ ወጣት እንደ እንጦንስና እንደ መቃርስ መኖር አይቻለኝም ባይሆን እንደ ኢዮብና እንደ አብርሃም አግብቼ ልጆች ወልጄ በሕግ ጸንቼ ልኑር አሰኘው ማለት ሲሆን <<ጎርፍም ጎረፈ>> ማለት ደግሞ በመጨረሻ ተስፋ በመቁረጥ ሁሉንም አልችልም እስኪል ድረስ አደረሰው ማለት ነው፡፡ ለመመነንም ሆነ ለማግባት መመኘት መልካም ነገር ሆኖ ሳለ በማይሆን ጊዜና በስሜታዊነት የሚወሰን ግን አይደለም:: ወጣቶችን እንዲህ ያለ መንፈሳዊ የሚመስል የሰይጣን ፈተና ሊያውካቸው ስለሚችል በግብታዊነት ከመወሰን ይልቅ በምክረ ካህን በፈቃደ ካህን መኖር ይኖርባቸዋል፡፡ ያ ቤት ነፋስ ነፍሶበት ጐርፍ ጐርፎበትና ዝናብ ዘንቦበት አልወደቀም፡፡ ምክንያቱም <<በዓለት ላይ>> ስለ ተመሠረተ ነው። ዝናብ፣
3 93521Loading...
13
ጐርፍና ነፋስ ምን ዓይነት ትርጓሜ እንዳላቸው ከላይ ተብራርቷል። <<ዓለት>> የተባለ ግን የእግዚአብሔር ቃል ነው። ስለዚህ ወጣቶች በቤት የተመሰለ ሕይወታቸው እንዳይናጋና እንዳይፈርስ ኑሮአቸውን መመሥርት ያለባቸው በምክረ ካህን በፈቃድ ካህን ላይ ነው:: ካህናት ወጣቶችን የሚመክሩበት የእግዚአብሔር ቃል እውነተኛ የ<<መሠረት ድንጋይ>> ነውና፡፡   ወጣቶች ከፈቀዱ በእግዚአብሔር ቃል ላይ መመሥረት ብቻ ሳይሆን ቃሉ ከውስጣቸው እንዳይጠፋ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ምክንያቱም ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ <<የእግዚአብሔር ቃል በእናንተ ስለሚኖር>> በማለት የተናገረው ከአረጋውያንና ከባልቴቶች ይልቅ የእግዚአብሔርን ቃል በልቡና መያዝ ለወጣቶች የሚቻል ነገር ስለሆነ ነው፡፡ 1ዮሐ2፥14         ወጣቶችና ፆሮቻቸው(ፈተናዎቻቸው)   በቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አስተምህሮ መሠረት ምዕመናን በአምስት መደብ ይመደባሉ። ይህም መደብ <<ፆታ ምእመናን>> ይባላል፡፡ አምስቱ ፆታ ምእመናን የሚባሉት ካህናት፤ መነኮሳት፣ አዕሩግ(አረጋውያን)፣ ወራዙት(ወንድ ወጣቶች)፣ እና አንስት(ሴት ወጣቶች) ናቸው።   አምስቱም ፆታ ምእመናን በየራሳቸው የሚቸገሩበት ዓቢይ ፈተና አለ፡፡ <<ፆር>> በመባል የሚታወቀው ይህ ዓቢይ ፈተና ነው:: የካህናት ፆራቸው ትዝኅርት (ትዕቢት) ነው:: የመነኮሳት ፆር ስስት ሲሆን የአረጋውያን ደግሞ ፆራቸው ፍቅረ ንዋይ ነው። ቀሪዎቹ ወጣት ወንዶች ሲሆኑ ዐቢይ ፆራቸውም ዝሙት ነው:: የወጣት ሴቶች ዓቢይ ፆር ደግሞ ትውዝፍት(የምንዝር ጌጥን መውደድ) ነው።(ዮሐ 5፥4 ትርጓሜ)   ይህ ማለት ግን ዋና ዋና ፈተናቸውን አንጓሎ ለመናገር ነው እንጂ እያንዳንዱ ፆታ ምእመን የሚፈተነው በአንድ ነገር ብቻ ነው ማለት አይደለም። <<ሰውነቱ በደዌ የተጠቃን ሰው ጉንፋን እንኳን እንደሚያልበት>> እንዲሁ በዋና ፈተናው ድል የተደረገ ምእመን ሌሎች ጥቃትን ፈተናዎች ይረባረቡበታል። ነገር ግን ዋናውን ፆሩን ድል ካደረገ የሚመጡበትን ሌሎች ፈተናዎች በቀላሉ ድል ለማድረግ ይቻለዋል።   ወጣቶች ልዩ ልዩ ፆር(ፈተና) እንዳለባቸው ነገር ግን ዕድሜያቸው እየገፋ በመጣ ቁጥር ወጣትነታቸው ሲያልፍ የወጣትነት ፈተናቸውም አብሮ እንደሚያልፍ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ሲህ ተናግሯል:: <<ወከመ ሥጋ ሶበ ይረክቦ ሕማመ ፈጸንት ወካልዕ ደዌያት ይደክም። ወለእመኒ ጥቀ ጽኑዕ ውእቱ ወእመሰ ድኅነ እምደዌሁ ይገብእ ኅቤሁ ኃይሉ ወከማሁ ነፍስኒ ትደዊ በዘመነ ውርዛዌ እስመ ባቲ ፍቅረ ትዕቢት ወተድላ ወተዋስቦ። ወዘይመስሎ ለዝንቱ ጣዕመ ፍትወታት ወእመሰ መጽኣ ጊዜ ርስአን ይሴስል ሕማም እምኩለንታሁ።>> ይህ ንባብ ወደ አማርኛ ሲመለስ <<ሥጋን ንዳድ ሌላም ልዩ ልዩ ደዌ በያዘው ጊዜ ምንም ብርቱ ቢሆን እንደሚደክምና ከበሽታው በዳነ ጊዜ ግን ኃይሉ እንደሚመለስለት እንደዚሁ ነፍስም በወጣትነት ወራት በደዌ ኃጢአት ትያዛለች። ትዕቢተኛነት፣ ሥጋዬ ይድላው ማለት፣ በጾታ መፈላለግና ይህን የመሳሰሉ ብዙ የምኞት ጣዕም ያድርበታል። የእርጅና ወራት በደረሰ ጊዜ ግን ፈቃደ ሥጋ ፈጽሞ ከሰውነቱይርቃል።>> ማለት ነው:: ዮሐ.አፈ.ተግ.7 ምዕራፍ ሦስት ይቀጥላል... @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
5 41319Loading...
14
.                   ምዕራፍ ሁለት                      የልጅ ዐዋቂ   ወጣቶች በመልካም አኗኗር ከኖሩ የልጅ ዐዋቂ ይባላሉ፡፡ ወጣቶች ከፈቀዱ አረጋዊ መሆንና አረጋዊ ከደረሰበት ጸጋና ክብር መድረስ ይችላሉ:: ወጣት የሽማግሌ ሥራ መሥራት ይቻለዋልን? የሚል ቢኖር ከሽማግሌዎች ወገን የወጣቶችን ሥራ በመሥራት ጸንተው የሚኖሩ ብዙ እንዳሉ ሁሉ <<ከማሁ ይትከሀሎ ለወሬዛ የሀሉ በከዊነ አዕሩግ>>፣ <<እንዲሁ ወጣትም የሽማግሌዎችን ሥራ በመሥራት መኖር ይቻለዋል>> የሚል መልስ ተጽፎ ይገኛል፡፡ ተግሣጽ ዘዮሐ አፈ 7   ነጭ ጉተና (ፀጉር) ከመኮነን እንደማያድን ሁሉ <<ከማሁኪ ጸሊም ድምድማ ኢይከልዕ ረኪበ ጸጋ : እንደዚሁም ጥቁር ፀጉርም ጸጋ ከማግኘት አያስከለክልም::>> በክርስትና መልካም ሥራን እንጂ ነጭና ጥቁር ፀጉርን ማበላለጥ የለም። አረጋዊም ሆነ ወጣት በቅተው ከተገኙ ለማንኛውም ክብር ይበቃሉ፡፡
4 56818Loading...
15
  አረጋዊ ዮሴፍ ሽማግሌ ሲሆን በብዙ ጎዳና መልካምነቱ ተመስክሮለት አማናዊት ታቦት ድንግል ማርያምን ለማገልገል ተመርጧል:: እመቤታችንን በአደራ እንዲጠብቃት ለአረጋዊ ዮሴፍ ተሰጠች። እንደዚሁም ሁሉ ወንጌላዊ ዮሐንስ ምንም ወጣት ቢሆን በቅቶ ስለተገኘ ለአረጋዊ ዮሴፍ የተሰጠችው ድንግል ማርያምን ለማገልገል እንደ ዮሴፍ ሁሉ እርሱም ከመስቀሉ ሥር በመገኘት በአደራ ተቀዘላት፡፡ ይህ ጸጋን ለመቀበል በቅቶ መገኘት እንጂ ዕድሜ ወሳኝ አለመሆኑን ያስረዳል። ዮሐ19፥26-27 ማቴ 1፥18-25   ወንጌላዊ ዮሐንስ ለኛ ለወጣቶች መመኪያችን ነው:: በወጣትነት ድንግል ማርያምን አስተናግዷልና። በክርስትና እምነት ከድንግል ማርያም ጋር የሚመሳሰልና የሚተካከል ሀብትም ጸጋም የለም፡፡ ታዲያ ድንግል ማርያምን ለመቀበል የበቃ ሌሎች ነገሮችን ከመቀበል ምን ያግደዋል፡፡ ይህን ሲባል ግን በቅቶ ከተገኘ እንጂ ካልበቃ ሊሆን አይችልም:: በአረጋዊ ዮሴፍ ዘመን ብዙ አረጋዊያን ነበሩ ነገር ግን በትሮቻቸው ተሰብስቦ ቢጸለይበት የቅዱስ ዮሴፍ በትር እንደ አሮን በትር ለምልማ በመገኘቷና በላይዋም «ኦ! ዮሴፍ ዕቀባ ለማርያም : ዮሴፍ ሆይ ማርያምን ጠብቃት» የሚል ጽሑፍ ተገኝቶ ድንግል ማርያምን ወደ ቤቱ ወስዷታል፡፡ (የሕዝቅኤል ትርጓሜ) በዮሐንስ ወንጌላዊም ዘመን ብዙ ወጣቶች ነበሩ ነገር ግን እመቤችንን እንደ ዮሐንስ በአደራ ለመቀበል አልታደሉም። እንዲሁም በዘመናችን ብዙ ወጣቶች አሉ ሁሉም ለቁርባን፣ ለተክሊልና ለክህነት አይበቁ ይሆናል:: ነገር ግን ለዚህ ሁሉ ግን የሚበቁ ወጣቶች መኖራቸው መዘንጋት የለበትም፡፡   ጸጋ እግዚአብሔር በዕድሜ የሚሰጥ ቢሆን ኖሮ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም «ከሴቶች መካከል ተለይታ የተባረከች» ለመሆን እንዴት ትችል ነበር? ነገር ግን ጸጋ እግዚአብሔር በዕድሜ ባለመሆኑ ምልዕተ ጸጋ ለመሆን በቃች። ምንም እንኳን በዕድሜ ትንሽ ብላቴና ብትሆን መጽሐፈ መነኮሳት <<ለብፅዕትኒ ማርያም ኢከልዓ ደቂቅናሃ ከመ ትኩን ቡሩክተ እም አንስት>> እንዳለ «ብፅዕት ማርያምን በዕድሜ ትንሽ መሆኗ ከሴቶች መካከል ተለይታ ቡርክት ለመሆን አልከለከላትም» ፊል ክፍል4 ተስ47 በዚህም ምክንያት ድንግል ማርያም «ምክሐ ደናግል» ብቻ ሳይሆን «ኃይለ ወራዙት»ም ትባላለች፡፡ ድንግል ማርያም «ኃይለ ወራዙት» ናት ማለት ለወጣቶችም ሆነ ለአረጋዊያን የወጣትነታቸው ኃይል እርሷ ናት ማለት ነው:: (መልክዐ ቁርባን)   እንዲሁም ወጣቶች በሚገባ ከኖሩ ከአረጋዊያን ተሽለው ሊገኙ ይችላሉ:: ይህም «ወራዙትኒ እመኒ ሕፃናት እሙንቱ ወተጸምዱ ለሥርዓተ ንጽሕ ይኄይሱ ፈድፋደ እም አዕሩግ፤ ወጣቶች ምንም ታዳጊዎች ቢሆኑ ንጽሕናን ጠብቀው ከኖሩ ፈጽመው ከአረጋዊያን ይበልጣሉ» በማለት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በተናገረው ቃል ይታወቃል፡፡ ትንሽ ዘመን ኖሮ በብዙ ዘመን የሚገኝ ዕውቀትን ገንዘብ ያደረገ ብልህ ወጣት ብዙ ዘመን ኖሮ ዕውቀት በማጣት እንደ ሕፃን ከሚኖር ሽማግሌ እንደ ምን አይበልጥ?   ቅዱሳት መጻሕፍትም በዚህ ሐሳብ ተስማምተዋል። ጠቢቡ ሰሎሞን «ክብረ ርእስ አኮ በብዝኃ መዋዕል ፤ መከበር በዘመን ብዛት አይደለም» በማለት ሲናገር ፤ ሲራክ ደግሞ <<ሲበቱ ለብእሲ አእምሮቱ ይእቲ፣ የሰው ሽበቱ ዕውቀቱ ናት» ብሏል፡፡ ጻድቁ ኢዮብም «አኮ ዘአብዝኃ ክራማተ ዘየአምራ ለጥበብ ፤ ጥበብን የሚያውቃት ዕድሜ የጠገበ አይደለም» በማለት ተናግሯል:: እነዚህ ጥቅሶች ሁሉ መብለጥ በሥራ እንጂ በዕድሜ አለመሆኑን የሚያስረዱ ናቸው።   አንዳንድ ወጣቶች በቤታቸው በዕድሜ ታላቅ ስለሆኑ ብቻ ታናናሾቻቸው እንዲንቀጠቀጡላቸው ይሻሉ፡፡ ይህ እጅግ የሚያስገርም ነው:: መልካም ሽምግልና የሌለው ሰው ስለሸበተ ብቻ ማን ያከብረዋል? ሽበት የክብር ምልክት ብቻ ነው እንጂ በራሱ ማስከበር አይችልም:: ዘውድ መድፋት፣ ዝናር መታጠቅ፣ ቅብዓ መንግሥት መቀባት ብቻ ንጉሥን አያስከብሩትም:: አንተም ብትሆን እንዲህ የተሸለመን ንጉሥ የገዛ ባሪያዎቹ ዘውዱን እንደደፋ ሲያቃልሉትና ሲንቁት፤ እያሸሟጠጡ ሲጎትቱት ብታይ ታዝንለት ይሆናል እንጂ አታከብረውም፡፡ ምክንያቱም መከበር በክብር ምልክት ብቻ አይደለምና፡፡ ታዲያ አንተ የታላቅነትን ምልክት ይዘህ ብትጣላ፣ ብትሳደብ፣ ብትሰክር፣ ብታመነዝር፤ ዲቃላ ብትወልድ፣ ገንዘብ አያያዝና ቤት አስተዳደር ባታውቅ ከዚህም በላይ ሰው ማክበርን ጨምሮ ምንም ዓይነት ፍቅርና ሃይማኖት ሳይኖርህ ክብርን መሻትህ እጅግ ያስገርማል፡፡   ጥሩ ወጣትና ጥሩ ታላቅ መሆን ካልቻልክ የምታጣው ክብርን ብቻ አይደለም:: ማንኛውም ኃላፊነትም አይሰጥህም:: አንተ እንደ ዔሳው ስትሆን እንደ ያዕቆብ ያለ ታናሽ ወንድምህ ብኩርናህን ይወስድና አንተ የሱን እጅ ስታይ ትኖራለህ፡፡ ታናናሾችህን የመቆጣትና የመገሠጽ መብት አይኖርህም። ሴሰኛ ሽማግሌ ወጣቶችን መገሠጽ እንደማያምርበት አንተ ሕገ ወጥ ወጣት ሆነህ ታናናሾቼን ልቅጣ ብትል ማን ይሰማሃል። እንዳንተ ያለውን ሰው መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ሲል ይገሥጻል፦ <<እንተ ግብዝ አስቀድመህ ከዓይንህ ምሰሶውን አውጣ፤ከዚያም በኋላ ከወንድምህ ዓይን ጉድፉን ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ። ማቴ 7፥5   አላረጀሁም ለማለት ነጭ ጉተናቸውን ቀለም እየቀቡ የሚያጠቁሩ አልያም <<ሽበት የሆነብኝ ማር ነክቶኝ ነው፣ ስብ ነክቶኝ ነው፣ በዘር ነው፣ ኑሮ አጎሳቊሎኝ ነው!>> የሚሉ ተራ ምክንያቶችን በማቅረብ ልጅ ነኝ እንደሚሉ ሽማግሌዎች አንተም ምንም እንኳን የወጣት ቁመና ይዘህ ጎልማሳ ብትሆንም ነገረ ሥራህ ሁሉ የሕፃን ከሆነ «ገርጅፎ ነው እንጂ ገና ሕፃን ነው፣ አልበሰለም>> መባልህ አይቀርምና እንደ አካልህ ሁሉ በሥራህና በዕውቀትህም ማደግ ይኖርብሃል። ከዚህ ወጥተህ ወጣትነትህን አታስንቀው::   አንድ ሽማግሌ ዕድሜ እያገዘውና ሥጋው ደክሞለት ሳለ ገና እንደ ወጣት ዘልዬ አልጠገብኩም ቢል ከቅጣት አያመልጥም:: ስለ ስሕተቱም ምክንያት የለውም ማለትም ባለመብሰሌ ነው ወይም ሰውነቴ እንደ እሳት እየፈጀኝ ንጽሕናን ጠብቆ መኖር አልቻልኩም ለማለት አይችልም።   እንደዚሁም ሁሉ ወጣቶችም ሕግ ሲያፈርሱ የሚነቀፉበት ብዙ ነገር አለ፡፡ ሽማግሌ በፍቅረ ንዋይ ቢጠቃና ስስታም ቢሆን እርጅናው ስላመጣበት ድካም የሚረዳው ይሻልና ገንዘብ ካለኝ በገንዘቤ እጦራለሁ ብሎ ነው ይባላል:: ወጣቶች የሚስገበገቡት ለምን ይሆን? እነርሱ ወጥተው ወርደው ራሳቸውን መርዳት ስለሚችሉ ወጣቶች በፍቅረ ንዋይ ቢያዙ ይነቀፋሉ። በዚህም ብቻ ሳይሆን ንጽሕናቸውን ባለመጠበቃቸው፤ በሰካራምነታችው፣ በስንፍናቸውና በመሳሰሉት መጥፎ ሥራቸው ሁሉ ተጠያቂዎች ናቸው:: ንጽሕናን ጠብቀን ለመኖር አንችልም እንዳይሉ ንጽሕናን ለመጠበቅ ያላቸውን አጋዥ ኃይል መመልከት በተገባቸው ነበር:: ወጣቶች አረጋውያን የሌላቸው ኃይለ ሥጋ ስላላቸው ፍትወትን ለማሸነፍ ሲሉ መጾም፣ መጸለይ፣ መስገድና መጽሐፍ መመልከት ይችላሉ፡፡ ይህ ከፍትወት የሚጠበቁበት መሣሪያ የተሰጠው ለመነኮሳት ብቻ አይደለም:: ፍትወት ወዲህና ወዲያ ለሚያፍገመግማቸው ለወጣቶችም ጭምር ነው:: ስለዚህ ወጣቶች የመጸለይ፣ የመጾም፤ የመስገድና የመሳሰሉትን ክርስቲያናዊ ግዴታዎች የመፈጸም ኃላፊነት አለባቸው::
3 29420Loading...
16
"ቅድስት" በዲያቆን ዘማሪ ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ በኩር ናት የበዓላት ኑ ከፍ ከፍ እናድርጋት በእርሷ ደስ ይበለን በሰንበተ ክርስቲያን አዝ... በዝማሬ እንበርታ በገናውን እንያዝና መልካም ስራ ሚሠራባት ሰንበት ቅድስት ናትና ከጨለማ ብርሀን ከመገዛት ነጻነት እግዚአብሔር ይህን ሰጠን ደስ ይበለን በሰንበት አዝ... ለአብርሃም ተገልጣለች ለሙሴም በደብረ ሲና በነቢያት የታወቀች ሰንበት ደሀራዊት ናትና በሳምንቱ ሠለጠነች ተሰበከች በሀዋሪያት ሀሌሉያ እለተ ሰንበት ተሰጠችን ልናርፍባት አዝ... በእልልታ እንሞላ እንደነቢዩ አሳፍ በከበረች የሰንበት ቀን ኑ ለቅኔ እንሰለፍ በመቅደሱ ናቸውና ቅዱስነት እና ግርማ ቅዳሴአችን ይሰማልን ከምድር እስከ ኢዮር ራማ አዝ... እግዚአብሔር አብ የባረካት እግዚአብሔር ወልድ የቀደሳት ከእለታት ሁሉ መርጦ መንፈስ ቅዱስ ከፍ ያረጋት በእርሧ ሀሴት እናድርግ እናክብራት እንድንከብር ከደጀ ሰላሙ ታዛ ከመቅደሱ እንሰብሰብ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
4 99043Loading...
17
@Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
4 52011Loading...
18
፣በዕዳ የሚጠየቅም ሆነ የሚጠይቅ ሁለቱም በአንድነት ቅዱስ ቃሉን ሲሰሙ ዋሽቶ የሰው ዕዳ ያልከፈለውም ተጸጽቶ ይክሳል ወራት ብሶበት ቀን ጥሎት መክፈል ላልቻለውም ምህረት ይቅርታ እንዲያገኝ ቅዱስ ቃሉ ጸሎቱ ምክንያት ይሆነዋል ። በዚህም የተነሳ ሁለቱም ወገኖች በክፉ ከመፈላለግ ይልቅ የይቅርታ የምህረት ሰዎች ይሆናሉ። በዚህች በኵረ በዓላት በምትሆን በቅድስት በዕለተ ሰንበት የምእመናን መንፈሳዊ ሕይወት ይባረካል ይቀደሳል በዚህ ታሳቢነት ዕለቱም ዕለተ ቅድስና መሆኑን ለማጠየቅ ቅድስት ተብሏል ። ቅድስና የተፈቀደልን ብቻ ሳይሆን የታዘዝነውም ጭምር ነው “እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ” (ዘሌ.፲፱፥፪) በዚህ ኃይለ ቃል ውስጥ ቅድስና እንደ ፈቃድም እንደ ትእዛዝም ሆኖ ተሰጥቶናል፤ እግዚአብሔር ያልፈቀደውን ነገር አድርጉ ሁኑ ብሎ አያዝም።የቅድስና ሕይወት መሰረቱ የእግዚአብሔር ፈቃድና ትእዛዝ ሆኖ ሳለ ለመቀደስ የእኛ መሻት መፈለግ ዝንባሌም ወሳኝ ነው። ለዚህም ነው ሐዋርያው እንዲህ ሲል የጻፈልን “ትቀደሱም ዘንድ ፈልጉ፥” (ዕብ. ፲፪፥፲፬) ምንም አንኳን ቅድስና የተፈቀደና የታዘዘ ቢሆንም የውዴታ እና የነጻ ፈቃድ ውጤት እንጂ የምንገደድበት አይደለም፡፡እግዚአብሔር ፍቅሩ ገብቶን ወደን እና ፈቅደን በፈቃዱ እና በትእዛዙ ስንመራ ያስደስተዋል እንጂ ተገደን ፈርተን ተንቀጥቅጠን እንድንገዛለት አይወድም፡፡ ወደ ቀደመ ነገራችን ስንመለስ ዕለተ ሰንበትም ቅድስት መባሏ ከላይ ያብራራነውን መሰረታዊ ሃሳብ በተከተለ መልኩ ነው። ዕለቲቱ ቅድስት መባሏ ዋና ዓላማ በሰዎች እና በእግዚአብሔር መካከል ለቅድስና ሕይወት ምልክት ማስታወሻ እንድትሆን ነው። በባህሪው ቅዱስ የሆነ አምላክ ዓለምን የማዳን ስራውን የጀመረበትን ጽንሰቱን እንዲሁም የማዳን ስራውም አጠናቆ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ዘላለማዊ ሕይወትን ያበሰረበትን ትንሳኤውን የምናስብበት በመሆኑ የዕለቱ ቅድስና የፈጣሪን ቅዱስ ተግባር የምናደንቅበት ከማንኛውም የሥጋ ሥራ ተለይተን የዋለልን ውለታ ከፍ ከፍ እያድረግን እርሱን የምናመሰግንበት ዕለት ነው። ይህም እኛን ወደ በለጠ የቅድስና ሕይወት የሚያሸጋግረን ከመሆኑም በላይ የእግዚአብሔርን ጥልቅ ፍቅር በየጊዜው እንድናስብና በፍቅሩም እንድንኖር ያግዘናል፡፡ ©ተሚማ ምስባኩ፦ መዝ ፺፭፥፭ "እግዚአብሔርሰ ሰማያተ ገብረ አሚን ወሠናይት ቅድሜሁ ቅድሳት ወዕበየ ስብሐት ውስተ መቅደሱ" "እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ ምስጋና ውበት በፊቱ ቅዱስነትና ግርማ በመቅደሱ ውስጥ ናቸው" በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ መልእክታት፦ -፩ኛ ተሰ ፬፥፩-፲፫ -፩ኛ ጴጥ ፩፥፲፫ እስከ ፍጻሜ -የሐዋ ሥራ ፲፥፲፯-፴ ወንጌሉም፦ ማቴ ፮፥፲፮-፳፭ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
4 54629Loading...
19
ቅድስት የዐብይ ጾም ሁለተኛ እሑድ(ሳምንት) ቅድስት የሚለው ቃል ግሱ “ቀደሰ” ሲሆን "ለየ፣ አከበረ፣ መረጠ" የሚል ትርጉም ይይዛል። ቅድስት ማለት የተለየች፣ የተመረጠች፣ የከበረች ማለት ነው። ቅዱስ የሚለው ቃል እንደየአገባቡ ለፈጣሪም ለፍጡርም ያገለግላል። ለፈጣሪ ሲነገር እንደ ፈጣሪነቱ ትርጉሙ ይሰፋል ይጠልቃል ለፍጡር ሲነገር ደግሞ እንደ ፍጡርነቱ እና እንደ ቅድስናው ደረጃ ትርጉሙ ሊወሰን ይችላል። እግዚአብሔርን ቅዱስ ስንል የባህሪይው የሆነ፣ ኃጢአት የማይስማማው ፣ ለቅድስናው ተወዳዳሪ ተፎካካሪ የሌለው፣ ወደር የማይወጣለት፣ ዘለዓለማዊ የሆነ ማለታችን ሲሆን ፍጡራንን ግን ቅዱሳን ስንል ቅድስናቸው የጸጋ የሆነ፤ ከእግዚአብሔር ያገኙት፤ እንደነጭ ልብስ ጽድቁም ኃጢአቱም እንደ ዝንባሌአቸው የሚስማማቸው፤ ለቅድስናቸው ማዕረግ ደረጃ የሚወጣለት እንደ ገድል ትሩፋታቸው መጠን ሊጨምርም ሊጎድልም የሚችል ማለታችን ነው። ከፍጡራን መካከል ለእግዚአብሔር የተለዩ ሁሉ በጸጋ የቅድስናው ተሳታፊ ሊሆኑ ይችላሉ። መላእክት፣ ሰዎች፣ መካናት፣ ዕለታት፣ አልባሳት፣ ንዋያት ሁሉ ለእግዚአብሔር እስከተለዩ ድረስ ከቅድስናው በረከት ይሳተፋ እንደየደረጃቸው ቅዱሳን ተብለው ይጠራሉ። በዚህ ዕለት ስለ ቅድስና እንዲሁም ዘወትር በዕለተ ሰንበት ከሌሎች ቀናት በተለየ ሁኔታ ለጽድቅ ስራ እንድንበረታ፣ ለቅድስና እራሳችንን እንድንለይ ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ይሰበካል ይነገራል። የሚዘመረውም መዝሙር “ግነዩ ለእግዚአብሔር ወጸውዑ ስሞ ወንግርዎሙለአሕዛብ ምግባሮ ሀቡ ስብሐተ ለስሙ አክብሩ ሰንበተ ተገበሩ ጽድቀ ዝግቡ ለክሙ መዝገበ ዘበሰማያት ኀበ ፃፄ ኢያማስኖ ወኢይረክቦ ሰራቂ ድልዋኒክሙ ንበሩ ዘበላዕሉ ጸልዩ ኀበ ሀሎ ክርስቶስ፤ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ስሙንም ጥሩ፤ ሥራውንም ለአሕዛብ ንገሯቸው፤ ለስሙም ምስጋናን አቅርቡ፤ ሰንበትን አክብሩ፤ እውነትንም አድርጉ፤ ብል የማያበላሸው ሌባም የማያገኘው በሰማያት ያለ መዝገብን ለእናንተ ሰብስቡ፤ ተዘጋጅታችሁም ተቀመጡ፤ ክርስቶስ ወዳለበት ወደላይ አስቡ፡፡” በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ እንደ ዘመረልን በተለይ ሰንበት ነገረ እግዚአብሔር በተለየ ሁኔታ የሚዘከርባት፤ ኅሊናችን ከምድራዊው ሃሳብ ወጥቶ ወደ ሰማይያዊው የሚነጠቅባት፤ ለቅድስና የተለየች ቅድስት ዕለት መሆኗን ይጠቁማል። በቅዱስ መጽሐፍም “የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ” (ዘፀ. ፳፥፰) ተብሏል፡፡ የሰንበትን ቀን አስቀድሞ የቀደሰ የባረከ እራሱ እግዚአብሔር ነው "እግዚአብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፎአልና"(ዘፍ.፪፥፫) እንግዲህ “የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ” የተባለው እግዚአብሔር አስቀድሞ የባረከውን የቀደሰውን እኛ ድጋሚ የምንቀድስ የምንባርክ ሆነን ሳይሆን በዕለተ ሰንበት እራሳችንን በተለየ ሁኔታ ለቅዱስ ተግባር እንድንለይ ለሥጋችን ከምንፈጽማቸው ተግባራት ይልቅ ለተግባረ ነፍስ እንድናደላ ያስረዳናል። ምንም እንኳን ለስጋችን ስንባክን ጊዜ ቢያጥረን በዕለተ ሰንበት ግን ቅዳሴ ከማስቀድስ ቅዱስ ቃሉን ከመስማት ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ከመቀበል እንዳናስታጉል በሥርዓት ቤተ ክርስቲያን ታዝዘናል፡፡ ሊቃውንቱ በፍትሐ ነገሥት "ተጋብኡ ኩሎ ዕለት ኀበ ቤተ ክርስቲያን ወፈድፋደሰ በዕለተ ሰንበት ወበበዓላት ወበዕለተ ትንሣኤ ዘውእቱ ዕለተ እሑድ፤ ሁልጊዜ በቤተ ክርስቲያን ተሰብሰቡ፤ ይልቁንም በዕለተ እሑድ፣ በዕለተ ቀዳሚት፣ በጌታ በዓላት ወደ ቤተ ክርስቲያን ተሰብሰቡ፡፡” (ፍትሐ ነገሥት ገጽ ፪፻፶፬) ብለው ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ከሌሎች ቀናት በተለየ ሁኔታ ትኩረት የምንሰጥበት የምንቀደስበት ዕለት ቅድስት ሰንበት እንደሆነች ተናግረዋል። ሐዋርያዊው ቅዱስ አትናቴዎስም በቅዳሴው ላይ ሰንበት የተቀደስች እና ሕይወታችን እንዲቀደስባት የተለየች ቀን መሆኗን ሲያስረዳ እንዲህ ይላል፡፡ “ወንበል ዛቲ ዕለት እንተ ገብረ እግዚአብሔር ንትፈሣሕ ወንትሐሰይ ባቲ፤ ይህች ዕለት እግዚአብሔር የሠራት ያከበራት ዕለት ናትና በእርሷ ፈጽሞ ደስ ይበለን” ሰንበት ለክርስትያኖች ለመንፈሳዊ ደስታ የተለየች ቀን ናት። የመንፈሳዊ ደስታ ምንጩ በነፍስ የሚገኝ መንፈሳዊ በረከት ነው። ሰው የኃጢአትን ሸክም በንስሃ ሲያራግፍ፤ ነፍሱ በጸጋ እግዚአብሔር ስትቃኝ የሚሰማውን ደስታ በሌላ በምንም መንገድ ሊያገኘው አይችልም። ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ሰንበት ቅድስትና ለቅድስና የተለየች ቀን መሆኗን ያስተማረን አስቀድሞ በነብያት ትንቢት ያናግር የነበረ መንፈስ ቅዱስ አነሳስቶት ነው። ስለ ሰንበት መለየትና መቀደስ እንዲሁም የመንፈሳዊ ሐሴት ቀን ለመሆኗ ነቢዩ ቅዱስ ዳዊት መዝሙሩ እንዲህ ብሎ ነበር “እግዚአብሔር የሠራትቀን ይህች ናት፤ ሐሤትን እናድርግ፥ በእርስዋም ደስ ይበለን።” (መዝ. ፻፲፯፥፳፬) ቅዱስ ዮሐንስም ራእዩ ሰንበት የጌታ ቀን ስለመሆኗ እንዲህ ይላል “በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ” (ራእ. ፩፥፲) ሰንበት የእኛ ቀን ሳትሆን ለጌታችን የምንሰራባት የምንለይባት ፣ የምንቀደስባት፣ ነገረ እግዚአብሔርን የምንዘከርባት የጌታ ቀን ናት። ለቅድስና የተለየች ቅድስት ቀን ናት ። በተለይ የክርስቲያን ሰንበት እሑድ “በኵረ በዓላት” ትባላለች በኵር ታላቅ እና መጀመርያ ማለት ነው፤ የመዳናችን መሰረት የተወጠነባት የጌታ የጽንሰቱ ቀን ዕለተ ሰንበት ናት፤ የመዳናችን ማረጋገጫ፣ የእምነታችን መሰረት ፣ የበዓላት ሁሉ ዓቢይ ትንሳኤው የተፈጸመው በዕለተ ሰንበት ነው። እንግዲህ በዚች ቅድስት ዕለት፥ ለቅድስና በተለየች ዕለትስ ሥጋውንም ነፍሱንም በሚያርያረክስ ተግባር የተሰማራስ ለነፍሱ ምን ዋስትና ይኖረዋል? ቅድስት በተባለች በሰንበት እሑድ ማንም በምንም ምክንያት ወደ ቤተ እግዚአብሔር ከመሄድ እንዳያስታጉል በስርአተ ቤተክርስትያን ተቀምጦልናል። ሌላው ቀርቶ በዕዳ በብድር በቀረጥ በግብር በአስራት በበኩራት ይሉኝታ ፈርቶ ማንም ቅድስት በምትባል በእሑድ ሰንበት ቅዳሴ እንዳያስታጉል ማንም ማንንም በዚህች ቅድስት ዕለት ምንም አይነት እዳ እንዳይጠይቅ ታዟል። “ወኢይኅሥሥ መኑሂ በይእቲ ዕለት ንዋዮ እምካልኡ ወኢይጽሐቅ አሐዱሂ እምእመናን በእንተ ኃሥሠ ዕዳ ። አው ተጻልኦ አው በዘይመስሎ ለዝንቱ። ወይሑሩ ቦቱ ኩሉሙ ሰብእ ኀበ ቤተ ክርስቲያን ወይምጽኡ ኲሉ ለለ ፩ ፩ እምእመናን ኅቤሃ በንጽሕ ወበትህትና ዘእንበለ ፍርሃት እምነ መኮንን ወእም በዓለ ዕዳ አው እምፈታሒ አው ዘይመስሎ። ወእመሰ ተሀበለ ፩ሂ ክርስቲያን ምክዕቢተ ይፍዲ፤ ከምእመናን ወገን አንድስ እንኳ በእሑድ ቀን ለገንዘብ መትጋት፤ገንዘቤን አምጣ ብሎ መጣላት፣ ዋስ መያዝ አይገባውም ። ሁሉም ምእመናን ወደ ቤተክርስቲያን በንጽሕና በትሕትና ሆነው ይምጡ እንጂ ። ዳኛ ግብሬን፣ አበዳሪ ብድሬን ፣ኤጲስቆጶስ ዐሥራት በኵራት ፣ ነጋ ድራስ ቀረጥ አምጡ ይሉናል ብለው ሳይፈሩ ይምጡ። ከነጋድራሶች አንዱ እንኳ ወደ ቤተክርስትያን ከሚሄዱ ሰዎች ቀረጥ ይቀበል ዘንድ የድፍረት ሥራ የሠራ ቢሆን እጽፍ አድርጎ ይክፈል።” (ፍትሐ ነገሥት ገጽ ፪፻፶፰-፪፻፶፱) ቅድስት ቤተክርስቲያን ይህን ያህል ጥንቃቄ የምታደርገው ሰዎች በተለያየ ምክንያት ከቤተ እግዚአብሔር እንዳይርቁ ከዛም አልፎ ተበዳይም ሆነ በዳይ
4 39037Loading...
20
@Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
6 08316Loading...
21
ይትበሃሉንና ቃሉን አነበብነው: ሐተታውንና ምሥጢሩን ተማርነው: በቅዱሳን ህይወት ወንጌሉን አየነው።[፪] @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
6 12316Loading...
22
መጋቢት ፭ እረፍቱ ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ መጋቢት አምስት በዚህች ቀን ተአምራቱና ትሩፋቱ እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነ ቅዱስ አባት ተጋዳይ አባ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የእረፍቱ ቀን መታሰቢያ ሆነ፡፡ ይህም ቅዱስ አባት በተወለደባት ቀን ድንቅ የሆነ ስራን ሰራ ተነስቶ ከእናቱ እቅፍ ወርዶ ከጨለማ ወደ ብርሀን ላወጣኸኝ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን እያለ ለስላሴ ሰግዷልና ምስጋናም አቅርቧልና። ህፃኑም ሶስት አመት በሆነው ጊዜ የእግዚአብሔር መልክተኛ ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ህፃኑን ከእናቱ እቅፍ አንስቶ ብዙ ባህታውያን ወዳሉበት ገዳም ወስዶ በደጅ አኖረው ወደ አበምኔቱ ወደ አባ ዘመደ ብርሀንም ገብቶ ስለ ህፃኑ እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ነገረው። በዚያን ጊዜም ነገሩ እውነት እንደሆነ ይረዳ ዘንድ አባ ዘመደ ብርሀን ተነስቶ ወደ ደጅ ወጣ። መልአኩም እንደ ነገረው ህፃኑ ከበር ተቀምጦ ፈገግታን ተሞልቶ አገኘው። እጅግም ደስ ብሎት ለእግዚአብሄር ሰገደ ህፃኑንም አንስቶ ሳመው ታቅፎም ወደ በአቱ አስገባው። በፍቅር በስነስርአት አሳደገው። የዳዊትን መዝሙርና ቤተ ክርስቲያን የምትቀበላቸውን መፃህፍት ሁሉ ብሉይንና ሀዲስን አስተማረው። ከዚያም በኃላም ክህነት ይሰጠው ዘንድ ስሙ አብርሀም ወደሚባል ጳጳስ ወሰደው ጳጳሱም በአየው ጊዜ ደስ አለው።የዲቁና ማእረግንም ሾመው እንደ ቀዳሜ ሰማእት እስጢፋኖስም ፀጋንና ሞገስን የተመላ ሆነ። ከጥቂት ቀኖች በኃላም በጌታችን ትእዛዝ ቅስና ተቀበለ። በፆም በፀሎት በስግደት በብዙ ትጋትም እየተጋደለ በበረሀ ውስጥ ብቻውን ኖረ። በበረሀም ብዙ ዘመናትን ሲኖር ነፍሱን "ነፍሴ ሆይ እወቂ በእግዚአብሔር ፊት ራቁትሽን ትቆሚ ዘንድ እንዳለሽ እንግዲህስ ፅኚ በርቺ ታገሺ!" ይለት ነበር። ቆዳው ከዐጥንቱ እስቲጣበቅ ያለ መብልና ያለ መጠጥ በእንዲህ ያለ ግብር በገድል ተጠምዶ ኖረ።ከእፅዋት ፍሬዎች ወይም ከእንጨት ስሮች አልተመገበምና ለስጋውም የሚጠቅም ምንም ምን ምክንያት አልፈለገም። ለገብረ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር እንዲህ አለው ከእንግዲህ በአለም ካሉ ሰዎች ከካህናት ከመነኮሳት ወይም ከምእመናን ህዝባውያን እንዳያውቁህ አደርግልሀለሁ። እንዳንተ ካሉ በቀር አንተ ራስህ ብትፈቅድ እንጂ መላእክትም ይጎበኙሀል። የብርሀን ሰረገላም ይሁንልህ መድረስ ወደምትሻበት ሁሉ ብረር እኔንም ማየትና በፈለግህ ጊዜ ከአባቴና ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ በሶስትነቴ ታየኛለህ። አሁንም ወደ ኢትዮጵያ ምድር ሂድ በዚያም ከደይን የምታወጥቸው ነፍሳት አሉህ አለው። ከዚህም በኃላ ስልሳ አንበሶች ስልሳ ነብሮች በፊት በኃላ አጅበውት ወደ ኢትዮጵያ ምድር ተጓዙ። የእግዚአብሔር መልእክተኛ ቅዱስ ገብርኤልም ከአንበሶችና ከነብሮች ጋር በነፋስ ሰረገላ አሳፍሮ ይመራው ነበር። ወደ ምደረ ከብድም አደረሰው ከዚያም ወደ ልዩ ተራራ ወደ ደብረ ዝቋላ ወሰደው። አባታችንም በባህሩ ቁሞ ምስራቁን ምዕራቡን ሰሜኑን ደቡቡን አራቱን ማእዘን ተመለከተ።የኢትዮጵያ ሰዎች የሚሰሩትን ኃጢአታቸውን በአይኖቹ ፊት የተገለጠ ሆኖ አየ። በራሱም ተዘቅዝቆ ተወርውሮ ወደ ባህሩ ውስጥ ገባ እሊህን የእጅህ ፍጥረቶች የሆኑትን ካልማርካቸው ከእዚህ ባህር እንዳልወጣ በእግሮቼም እንዳልቆም በህያው ስምህ እምላለሁ እያለ ማለ እንዲሁም ሆኖ አርባ ቀን አርባ ሌሊት ኖረ። ስምህን የጠራውን መታሰቢያህን ያደረገውን እምርልሀለሁ የሚል ቃል በመልአክ አማካይነት ወደ አባታችን መጣ። አባታችንም መልአኩን መላውን የኢትዮጵያን ሰው ካልማረልኝ ከዚህ ባህር አልወጣም አለው መልአኩም ከአጠገቡ ሄደ። አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስም በዚያ ባህር ውስጥ መቶ ዓመት ኖረ ስጋው ሁሉ አለቀ ደሙም በባህሩ ውስጥ ፈሰሰ አጥንቶቹም እንደበረዶ ነጭ ሆነው ታዩ። አጋንንትም ከአራቱ ማእዘን በየቀኑ ሰባት መቶ ሽህ ሶስት መቶ ሽህ እየሆኑ በመምጣት በቀስታቸው ይነድፉታል እስከ መቶ አመትም አጥንቶቹን በሻፎ ድንጋይ ይፍቁታል ይህን ሁሉ መከራ በትእግስት ሲቀበል ኖረ። ከዚህም በኃላ ጌታችን ወደርሱ መጥቶ ከባህሩ ዳር ቆመ። አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስንም መላውን የኢትዮጵያ ሰው ምሬልሀለሁና ተነስተህ ውጣ አለው ያንጊዜም ወጣ አጥንቶቹም እንደ ወንፊት ቀዳደሰ የተበሳሱ ሆነው ተገኙ ጌታም ዳሰሰውና ጤነኛ አደረገው ወደ ምድር ከብድም ሰደደው። ከዚያም ወደ ላይ ወጥቶ ከፀሀ ከሰማይ በታች እስከ ሰባት አመት ኖረ። ዳግመኛም ወደ ምድረ ከብድ ተልኮ እንደ አምድም የተተከለ ሆኖ ሰባተረ አመት ቆሞ ኖረ። ወደ ሰማይም ሲመለከት ቅንድቦቹን አልከደነም ራሱንም ወደ መሬት ዝቅ አላደረገም ነበር እጆቹም ወደ ሰማይ ተዘርግተዋል። እነሆ ሰይጣንም በቁራ ተመስሎ መጣ አይኖቹንም ወደ ሰማይ ያንጋጠጡ ሁለቱን አይኖቹን አንቁሮ አሳወረው። እርሱ ግን ምንም ሳያጓድል እስከ ሁለት ሳምንት ድረስ እንደ ቀድሞው በመትጋት ሲፀልይ ኖረ። ከዚህም በኃላ ሚካኤልና ገብርኤል መጥተው በፊቱ ቆሙ በሁለቱ አይኖቹ ላይም እፍ አሉበት ብርሀንም ተሰጥቷቸው እንደ ቀድሞው አዩ። ከሰማይ ታላቅ ኃይል ተሰጥቶሀልና ጠላቶችህን ትበቀላቸው ዘንድ ወደ ዝቋላ ሂድ አሉት ከዚያም መላእክት ከአጠገቡ ሄዱ። እርሱም ተነስቶ ወደ ዝቋላ ተጓዘ በጎዳናም ሲጓዝ ሶስት ሽማግሌዎች ከእንጨት ጥላ በታች ተቀምጠው አየ አባታችንም በአያቸው ጊዜ ልሰውራቸው ብሎ በልቡ አሰበ። እንርሱም ፈጥነው በእግዚአብሔር ዙፋን ተማጥነናልና ሶስታችንንም በጀርባህ እያዘልክ አንዳንድ ምእራፍ ሸኘን እንጂ አትተውን ብለው ተጣሩ። በመጣም ጊዜ ሁለመናቸውን ሽበት የከበባቸው የደከሙ ሽማግሎች ሁነው አገኛቸው አንደኛውንም አንስቶ በጀርባው አዘለው ወደ አንድ ምእራፍም አደረሰው ሽማግሌውም ከዚህ አሳርፈኝ አንተ ደክመሀል የማትበላ የማትጠጣ ስለሆንክ አለው አባታችንም ሽማግሌ ሆይ በምን አወቅከኝ አለ። ሽማግሌውም ሂደህ ባልንጀሮቼን አምጣልኝ አለው ተመልሶ ሁለቱ ወደአሉበትም ደርሶ ሁለተኛውን ሽማግሌ በጀርባው አዝሎ ወደ ቀደመው ሽማግሌ አድርሶ አብሮ አስቀመጠው ሶስተኛም ተመልሶ ሶስተኛውን ሽማግሌ አዝሎ ሁለቱ ወዳሉበት አድርሶ በአንድነት አኖረው፡፡ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስም እነዚያን አረጋውያን እናነተ ከወዴትናችሁ መአዛችሁ ልብ ይመስጣል እጅግም ደስ ያሰኛል አላቸው።እነርሱ ግን ተነስተው ቆሙ አንድ ሲሆኑ ሶስት ሶስት ሲሆኑ አንድ መሆናቸውን ገለጡለት የአባቶች አለቃ አብርሀም እንደ አየ። ያንጊዜም የእግዚአብሔርን የጌትነቱን ክብር አየ የእሊያ አረጋውያንም ፊታቸው ተንቦገቦገ ከፀሀይና ከመብረቅ ብልጭታም ሰባት እጅ በራ አባታችንም በምስጢራት ጎርፍ የተዋጠ ሆኖ ፈራ ተንቀጠቀጠ በምድር ላይም ወደቀ። ህልምን የሚአልምም መሰለው ከዚያም ጌታችን አባታችንን አነቃውና መቶ አመት ያህል ስጋህን ሲነዱፉህ አጥንቶችህን ሲፍቁህ የኖሩ አጋንንትን ታጠፋቸው ዘንድ ወደ ዝቋላ ተራራ ውጣ አለው። እኔ እንደ ወሰድኩህ ባለማወቃቸው በባህር ውስጥ አለ በማለት በትእቢት ላይ ናቸው ሰባቱ ሊቃነ መላእክትም ይረዱሀል መባርቅትም በፊት በኃላ ሆነው ይከተሉሀል አለው። ያን ጊዜ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ በመብረቅ ላይ ተጭኖ በረረ እነዚያ አጋንንት ወደአሉበትም ወረደ። ደመናትም ከበቡአቸው
5 98231Loading...
23
መላእክትም በእሳት ሰይፍ መተሩአቸው በመብረቅም አጨዱ አቸው አመድም ሆነው በነፋስ በተኑአቸው። የእነዚያም አጋንንት ቁጥራቸው ሰባት መቶ ሺህ እልፍ ከአንዱ ሺህ ነበር። ከዚህም በኃላ ጌታ ክርስቶስን የካዱ ወዳሉበት ወደ ምእራብ ሀገር ወሰደው። ነገስታቱና መሳፍንቱ መኳንንቱም በሚወ ጡበትና በሚገቡበት ጉዳና ላይ አቆመው ጌታችንም በዚች ጉዳና ብዙ መከራ ያገኝሀል ግን በርታ ታገስ ብሎት በዚያ ተወው። በዚያን ጊዜም የአርብ ንጉስ ጣዖታቱን አስይዞ መኳንንቱን ሰራዊቱን አስከትሎ በዚያች ጎዳና መጣ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስን በጎዳና ውስጥ በተገናኙት ጊዜ ጣኦታቱ ወድቀው ተሰባበሩ። ንጉሱም አባታችንን በአየው ጊዜ አንተ ጠጉር ለባሽ ምንድነህ ሰው ነህን አለው።አባታችንም አዎን ክብር ያለው የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያው የሆንኩ ሰው ነኝ ብሎ ለከሀዲው ንጉስ መለሰለት። ንጉሱም ዳግመኛ አባታችንን በዚያ አይሁድ በሰቀሉት ታምናለህን አለው አባታችንም በሰው ፊት አምንበታለሁ።ስለ እኔ በተሰቀለው አላፍርበትም ስለ እኔ ብቻ የተሰቀለ አይደለም ስለ አንተና ከአንተ ጋራ ስለ አሉትም ነው እንጂ ንጉስ ሆይ የዘላለም ህይወትን ታገኛላችሁ እመኑበት አለው። ንጉሱም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ተቆጣ ሰራዊቱንም ጠርቶ በፍጥረት እሳትን አንድዱ ለተሰቀለው ለናዝሬቱ ሰው ባሪያው ነኝ የሚለውን ጠጉር ለባሽ ወስዳችሁ ጨምሩት አላቸው። የእሳቱም ነበልባል በረጅም ዛፍ መጠን ከፍ ከፍ እስከሚል አነደዱ። አባታችን ግን ንጉሱና ሰራዊቱ ሁሉ እያዩት አልፎ በፈቃዱ ወደ እሳቱ ገባ። እሳቱም እንደወንዝ ውኃ ሆነ ሰረዊቱም እጅግ አደነቁ እኩሌቶቹም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ። ንጉሱም ሲያደንቁ በአየ ጊዜ ፈፅሞ ተቆጣ ከሰባ ሰባት አርበኞቹ ጋራ በቁጣ ተነስቶ ያደነቁትንና ያመኑትን አንገታቸውን ቆረጠ ። በዚያችም ቀን የተቆረጡ አርባ መቶ ሺህ ሆነው ተቆጠሩ።ንጉሱም የአባታችንን አንገት ሊቆርጥ ሰይፉን መዞ ተወርውሮ ሄደ። ያን ጊዜም ከመብረቅና ከነጎድጓድ ጋራ ታላቅ ንውፅውፅታ ሆነ ንጉሱንም ከሰራዊቱ ጋራ አጠፋው ከከሀዲው ንጉስ ጋራ የሞቱት ቁጥራቸው አራት ሺህ እልፍ ሆነ። ጌታችንም አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስን ጠላቶችህንና የኔንም ጠላቶች አጠፋሁልህ አለው።አባተችን ግን በመብረቅ የሞቱትን ሬሳቸውን ነፍሳቸውንም መላእክተ ፅልመት ወደ ስቃይ ሲወስዱአቸው በአየ ጊዜ መድኃኒታችንን እሊህን ስሁታን ማርልኝ ሰው ስሁትና ከዳተኛ ነውና አቤቱ አንተ ግን መሀሪ ይቅር ባይ ታጋሽም ነህ አለው።አባታችንም ይህን ሲናገር ጌታችን ተሰወረ። አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስም ከዚያ ሄደ ታላቅ ገደልም አገኘ እግሮቹንም በገመድ አስሮ በገደሉ ውስጥ ተዘቅዝቆ ተሰቀለ።ሰይጣንም መጥቶ ያቺን ገመድ ቆረጣት ወደ ታችም ተወርውሮ ወረደ።ቅዱስ ሚካኤልም ቀድሞ አባታችንን ያዘው በእግርህ ላቁምህ ወይም በራስህ አለው በራሴ እቆም ዘንድ ተወኝ አለው ትቶት ሄደ። በዚያም በራሱ ቁሞ በጥርሶቹም ደንጊያ ነክሶ እስከ ሰላሳ አመት ኖረ አንጀቱና ናላው ሁሉ እየፈሰሰ አልቆ መላ አካሉ እንደእንጨት ቅርፊት ሆነ። ከሰላሳ አመትም በኃላ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባታችንን ገብረ መንፈስ ቅዱስ እያለ ሶስት ጊዜ ጠራው። እርሱም እነሆኝ ጌታዬ አለ ጌታችንም እነዚያን ከሀዱዎች ምሬልሀለሁ ከዚህ ተነሳ አለው።ያን ጊዜ የነከሰውን ደንጊያ ትቶ ተነሳ።ጥርሱም ተነቅሎ በድንጊያ ተተክሎ ቀረ። ክንፎችም ተሰጥተውት እየበረረ ከእግዚአብሔር ፊት ደረሰ ጌታውንም ከማርክልኝ ከስጋቸው ጋራ ተነስተው በመጠመቅ ክርስቲያኖች ይሁኑ ብሎ ለመነው። መድኃኒታችንም በሽተኞችን ልትፈውስ ሙታንን ልታስነሳ ስልጣን ሰጥቼሀለሁ አሁንም ወደተገደሉት ሄደህ በመስቀል ምልክት በላያቸው አማትብ ህይወት መድኃኒት በሆነ ስሜም አስነሳቸው አለው።ያን ጊዜም በድኖቻቸው ወዳሉበት ሂዶ አስነሳቸው አጥምቆም ክርስቲያኖች አደረጋቸው ከእርሳቸውም ሄደ። ከዚህ ዓለም የሚለይበት በቀረበ ጊዜ እነሆ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እነሆ ተገለጠለት። ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያውን ለሚያደርግ እስከ አስራ አምስት ትውልድ የምህረት ቃል ኪዳን ሰጠው።የእድሜውም ዘመናት አምስት መቶ ስልሳ ሁለት ሲሆን በሰላም በፍቅር አረፈ። ጌታችንም ነፍሱን ተቀበለ አቅፎም ሳማት በመላእክትና በቅዱሳን ሁሉ ምስጋና አሳረጋት። በጸሎቱ ያስምረን:ሀገራችንን ኢትዮጵያን ከገባችበት ፈተና በጸሎቱና በተሰጠው ቃልኪዳን ያድናት: አሜን! @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
5 55627Loading...
24
«ጾም እስከ ስንት ሰዓት ነው?» የቅድስቲቱ ቤተክርስቲያን ሥርዓቱ በልኬት እና በምክንያት የታጀበ ነው። ጾምን ስንመለከት አብዛኞቻችን በተለምዶ ሰዓት ሳንጠብቅ (እስከ 3፣ 6፣ 7፣ 9፣ 11 ሰዓታት እያልን) እንጾማለን እንጂ የአዋጅ አጽዋማት የተወሰነ የተገደበ ሰዓት አላቸው። ፍትሐ ነገሥታችን “ሕማማት እስከ 12 ሰዓት ይጹሟቸው፥ ሌሎቹን አጽዋማት በዓለ ልደት እና ጥምቀት ረቡዕ እና ዐርብ የሚውሉባቸው ካልሆኑ በቀር እስከ 9 ሰዓት ይጹሙ” (ፍት.ነገ አን 15፥565-566) ብሏል። የአጽዋማትን ዝርዝር ካስቀመጠ በኋላም በዚሁ አንቀጽ ቁጥር 572 ላይ ደግሞ “በእነዚህ በታዘዙት ጾሞች ከቀኑ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ይጹሙ፣ ... ከዚህ አብልጦ የጾመ ግን ዋጋው ይበዛለታል፣ ከጥሉላት ምግቦች መታቀብ ካልሆነ በቀር እሑድና ቅዳሜ ግን አይጹሙ” ብሎ ወስኗል። ዐቢይ ጾም/ጾመ ሁዳዴ/ጾመ ዐርብዓ ግን ይለያል። “በዐቢይ ጾም መጀመሪያ ሱባኤ(ዘወረደ) ፀሐይ እስኪገባ ይጹሙ፣ ሌሎቹን ሳምንታት(ከቅድስት እስከ ሆሣዕና) እስከ 11 ሰዓት ይጹሙ፥ በሰሙነ ሕማማት ግን ኮከብ እስኪወጣ ይጹሙ” ብለዋል። (ፍት.ነገ.አን 15፥595) ፍትሐ ነገሥት ቁጥር 578 ላይ ደግሞ “(የሰሙነ ሕማማትን) ዓርብንና ቅዳሜን(አክፍሎት) ግን ሁለቱንም በአንድነት ይጹሟቸው፣ የሚችል እስከ ሌሊት ዶሮ ጩኸት ድረስ ምንም ምን አይቅመስባቸው፣ ሁለቱን በአንድነት መጾም የማይቻለው ግን ቅዳሜን ይጹም” ተብሎ ህግ ተሠርቷል። የበረከት ጾም ያድርግልን! @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
9 554157Loading...
25
ዘወረደ የዐብይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት የመጀመሪያ የዐብይ ጾም መግቢያ እሁድ ዘወረደ ይባላል። በዚህ ቀን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማይ ወደ ምድር መውረድ ይሰበካል ይዘመራል። ሰውም በታላቅ ፍርሃት ወደ አምላክ መቅረብ እንዳለበት ይነገርበታል። ደግሞም ጾመ ሕርቃል ይባላል። ስያሜውም በ614 ዓ.ም ኪርዮስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተ መቅደስ ውስጥ ሲገባ ንግሥቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው ቢነካው አቃጠለው ዲያቆናቱንም አሸክሞ ሌላውን ንዋየ ቅዱሳን ዘረፈ: 60 ሺ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ 3 ሺ የሚሆኑትን ማርኮ ከተማውንም አቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል። በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተስብሰበው ከ14 ዓመት በኃላ በ628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲያኑ የሮም ንጉስ ሕርቃል ይነግሩታል። እርሱም "ሐዋሪያት ሰው የገደለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርገው?" አላቸው "እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማን" ብለን አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን በሚገባ ጾመውታል። ምስባኩም:- መዝ ፪፥፲፩ "ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ወተሐሰዩ ሎቱ በረዓድ አፅንእዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመዐፅ" "ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ በርአድም ደስ ይበላችሁ ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቆጡ" በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡት ጥቅሶች: -ዕብ ፲፫፥፯-፲፯ -ያዕቆብ ፬፥፮ እስከ ፍጻሜ -የሐዋ ሥራ ፳፭፥፲፫ እስከ ፍጻሜ ወንጌሉም:- ዮሐ ፫፥፲-፳፭ "¹⁰ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ አንተ የእስራኤል መምህር ስትሆን ይህን አታውቅምን? ¹¹ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን፥ ምስክራችንንም አትቀበሉትም። ¹² ስለ ምድራዊ ነገር በነገርኋችሁ ጊዜ ካላመናችሁ፥ ስለ ሰማያዊ ነገር ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ? ¹³ ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው። ¹⁴-¹⁵ ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል። ¹⁶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ¹⁷ ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና። ¹⁸ በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል። ¹⁹ ብርሃንም ወደ ዓለም ስለ መጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለ ወደዱ ፍርዱ ይህ ነው። ²⁰ ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፥ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤ ²¹ እውነትን የሚያደርግ ግን ሥራው በእግዚአብሔር ተደርጎ እንደ ሆነ ይገለጥ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል። ²² ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ይሁዳ አገር መጣ፥ በዚያም ከእነርሱ ጋር ተቀምጦ ያጠምቅ ነበር። ²³ ዮሐንስም ደግሞ በሳሌም አቅራቢያ በሄኖን በዚያ ብዙ ውኃ ነበርና ያጠምቅ ነበር፥ ²⁴ እየመጡም ይጠመቁ ነበር ዮሐንስ ገና ወደ ወኅኒ አልተጨመረም ነበርና። ²⁵ ስለዚህም በዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና በአይሁድ መካከል ስለ ማንጻት ክርክር ሆነ።" @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
6 86266Loading...
26
@Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
7 03210Loading...
27
"ዘወረደ" በዲያቆን ዘማሪ ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ በእርሱ ፍቃድ በአባቱ ፍቃድ በመንፈስ ቅዱስ ፍቃድ ከሰማያት ወረደ ከድንግል ማርያም ተወለደ። ዓለሙን እንዲሁ ወደደና ከሰማያት በላይ ወረደና በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወሰነ አምላከ አማልክት   ከሰማያት የወረደው ፍቅር ስቦት የመጣዉ   ወልደ አብ ወልደ ማርያም ኢየሱስ ፈራጅ ነዉ          አዝ።።።።።።።።።።። ቅድመ አለም ተወልዶ ያለ እናት ድህረ አለምም ያለ አባት የእግዚአብሔር ልጅ በእርግጥም ሰው ሆነ ሁሉ በእርሱ ይኸው ተከናወነ   ከሰማያት የወረደው ፍቅር ስቦት የመጣዉ  ወልደ አብ ወልደ ማርያም ክርስቶስ አምላክ ነዉ          አዝ።።።።።።።።።።። የማይታይ ታየ በምድር ረቂቁ ገዘፈ ስለፍቅር ሥጋን ተዋሕዶ ሆነልን ፈውሥ አማኑኤል የነገስታት ንጉሥ  ከሰማያት የወረደው ፍቅር ስቦት የመጣዉ    ወልደ አብ ወልደ ማርያም እግዚአብሔር እርሱ ነዉ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
7 48372Loading...
28
@Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
4 6055Loading...
29
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ዐብይ ጾም ------------------------------- @Ethiopian_Orthodox ------------------------------- ጾም ማለት "ተወ"፣ "ታቀበ" ፣"ታረመ" ካለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ነው። ፍቺውም ምግብ መተው ፤መከልከል፤ መጠበቅ ማለት ነው። ጾም ማለት ሰውነት ከሚያስፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ መከልከል፤ መወ'ሰን ማለት ነው። ወይም ሰውነት የሚያምረውን የሚያስጎመጀውን ነገር መተው ማለት ነው። ጾም ከሃይማኖት ጋር ዝምድና ስላለው ሃይማኖት ባለበት ሁሉ ጾም አለ። ✳️ ጾም በብሉይ ኪዳን ከፍተኛ ቦታ አለው። ነብያት ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት ወራት እህል ውሃ በአፋቸው አይገባም ነበር። (ዘፀ 30÷34-28) ✳️ በኃጢአት ብዛት የታዘዘውን የእግዚአብሔርን መዓት የሚመልሰው ሕዝቡ በጾም ሲለምኑት ሲማልዱት ነበር። (ዮሐ 2÷7-10) ✳️ በሐዲስ ኪዳንም ጾም ሰው ሰራሽ ህግ ሳይሆን እራሱ መድኃኒታችን በመዋዕለ ሥጋዌው የሥራ መጀመሪያ አድርጎ የሰራው ህግ ነው። ✳️ ይህ ብቻ ሳይሆን በቁራኝነት አብሮ የሚኖር መንፈስ እርኩስ ሰይጣን እንኳን በጾም የሚወገድ መሆኑን መድኃኒታችን ተናግራል።(ማቴ 17÷21) ✳️ ቤተክርስቲያንን እንዲያገለግሉ የታዘዙት ሐዋርያትም ከመንፈስ ቅዱስ በየጊዜው ትዕዛዝ የሚቀበሉበት በጾም እና በጸሎት ላይ እንዳሉ ነበር።(ሐዋ 13÷2) ✳️ ለስብከተ ወንጌል የሚያገለግሉ ዲያቆናት ቀሳውስት የሚሾሙት በጾምና በጸሎት ነበር። (ሐዋ 13÷3) ጾምስ በታወቀው እለት በታወቀው ሰዓት ሰው ከምግብ መከልከል ነው። ጾም ማለት ጥሉላት ማባልዕት ፈፅሞ መተው ሰውነትንም ከመብልና ከመጠጥ ከሌላውም ክፉ ነገር ሁሉ መጠበቅ፣ መግዛት፣ መቆጣጠር፣ በንስሐ ታጥቦ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ "ይቅር በለኝ" በማለት ቅድመ እግዚአብሔር በመንበረከክ ምሕረት ለአምላክ ለመቀበል መዘጋጀት ነው። ፆም ነፍስን ቁስልን የምትፈውስ፣ ሀይለ ፍትወትን የምታደክም የበጎ ምግባር ሁሉ መጀመሪያ ከእግዚአብሔር ጸጋን የምታሰጥ የወንጌል ስራ መጀመሪያ ፣ የፅሙዳን ክብራቸው፣ የደናግል የንፅህና ጌጣቸው ፤የንፅህና መገለጫ ፣ የጸሎት ምክንያት እናት፤ የእንባ መናኛ መፍለቂያ አርምሞን የምታስተምር፣ ለበጎ ስራ ሁሉ የምታነቃቃ፣ ሰውነትን በእግዚአብሔር ፊት በማዋረድ ትህትናን ገንዘብ ለማድረግ የምትረዳ መድኃኒተ ነፍስ ናት። ከህገ ልቦና ከነበሩ አበው አንስቶ በዘመነ ኦሪት እስከ ክርስቶስ መምጣት ድረስ በተለያዩ ጊዜያት የነበሩ ቀደምት አበው ነቢያት፣ ነገሥታት፣ ካህናት በፆምና በጸሎት ፅመድ ሆነው እግዚአብሔር አምላካቸው ከክፉ ነገር እንዲሰውራቸው በይቅርታ እንዲጎበኛቸው ሀይልም እንዲጎናፅፋቸው ተማፅነው ሀሳባቸውን ፈፅሞላቸዋል። በሀዲስ ኪዳን ጾም ስለ ፅድቅ ተብሎ መከናወን ያለበት አብይ ተግባር ነው።// ማቴ 5÷6// ስጋዊ ጥቅምን ለማግኘት ተድላ ሰጋን በመሻት ሳይሆን ዘላለማዊ መንግስት ለመውረስ ስለ ፅድቅ ተብሎ የሚፈፀም ነው። ጾም እንደምን ነው ቢሉ የስጋ ምግባር ነው። ምፅዋት የገንዘብ ግብር እንደሆነች አንድም ምፅዋት ስጋን መገበር ነው። ምፅዋት ገንዘብ መገበር እንደሆነች ~~~ ስለዚህም የሚፆም ሰው በፈቃደ ስጋው ላይ ድልን ይቀዳጃል። በእምነት ሆኖ የለመነውን እግዚአብሔር ይሰጠዋል። ሰማያዊ የሆነውን ምስጢር ለማየት ከዓለማዊነት ነገሮች ተለይቶ ይነጠቃል። በዓለም እየኖረ ከዓለሙ ይለያል። ከዓለም አይደለምና //ዮሐ 15÷19// 🔰ዐብይ ጾምም ቤተክርስቲያናችን እንድንጾም ካወጀችልን ጾም አንዱ ነው። አብይ ጾም የተለያዩ ስሞች አሉት: ፩. ዐብይ ጾም: ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ የጾመው የአርባ ቀን ጾም በመሆኑ እንዲሁም ዐብይ እግዚአብሔር ወዓቢይ ኀይሉ ዓቢይ እግዚአብሔር ወብዙኃ አኰቴቱ የተባለ ጌታ የጾመው ስለሆነ፣ //መዝ 47÷1 መዝ 146÷5// ዐብይ ጾም መባሉ ትልቅና ታላቅ ጾም መሆን ለማሳወቅ ነው። ይህ ጾም ታላቅ መባሉም ለ55 ቀናት ያህል መጾሙና ከሌሎች አፅዋማት ጋር ሲነጻጸር በቁጥር መብለጡ ብቻ ሳይሆን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ ቆሮንጦስ መጾም ሳይገባው ለእኛ አርአያና ትልቅ ምሳሌ ለመሆን የጾመው ጾምም በመሆኑ ነው። ፪. ሁዳዴ ጾም: ይህም የመንግሥት እርሻ ወይም ማንኛውም የሕዝብ ብዛት ያለበት ሥራ ሁዳድ ስለሚባል ሲሆን ከአጽዋማት ሁሉ ብዙ ቀናት ስለሚጾምና ኃያሉ አምላካችን ስለጾመው ነው።፣ /አሞ 7÷1 // ፫. በዓተ ጾም : ፆም መግቢያ፣ መባቻ ወይም ጾሙ የሚሰፍርበት በዓል ማለት ነው ፬. ጾመ አርቦ: ጌታችነ ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመዉ 40// አርባ ቀን ስለሆነ ነው //ማቴ 4÷1 ፭. ጾመ ኢየሱስ : ጾሞ ፣ ጹሙ ብሎ ስላዘዘን፣ ፮. ጾመ ሙሴ : ቅዱስ ያሬድ በዘወረደ ሰኞ "ዕዝል ከመዝ ይቤ ሙሴ እስመ ለዓለም ፣ ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት" እያለ በጾመ ድጓ ስለ ዘመረ ነው። 🌿ዐብይ ጾም ጌታ ከተጠመቀ በኋላ የጾመው የአርባ ቀን ጾም ነው። //ማቴ 4÷1 ምእመናንም ጌታቸው ያደረገውን ምሳሌ ተከትለው ይጾሙታል። 🌿ዐብይ ጾም ስምንት ሳምንታት //55 ቀኖች // አሉት። 7//ሰባት ቅዳሜ 8//ስምንት እሁድ ይገኛሉ። አስራ አምስት ቀን 55//ማለት ነው። ከጥሉላት እንጂ ከእህል ወኃ ስለማይጾሙ የጾሙ ወራት አርባ ቀን ብቻ ይሆናል። የዐብይ ጾም ሶስት ክፍሎች ፩. ዘወረደ ( ጾመ ሕርቃል)፦ ይህም ጾሙ ከሚገባበት ሰኞ ጀምሮ እስከ እሁድ ያረሰ ያለው 7 ቀን ነው። ፪. የጌታ ጾም፦ ይህም ከቅድስት ሰኞ እስከ ሆሣዕና ዋዜማ ዓርብ ድረስ ያለው አርባ ቀን ነው። ፫. ሕማማት፦ ይህ ጌታችን በአልዓዛር ቤት ለማዕድ ከተቀመጡበት የሆሳዕና ቅዳሜ ጀምሮ እስከ ሥዑር ቅዳሜ ያለው መከራን የተቀበለበት 8 ቀን ሕማማት ነው። ይህም ፯+፵+፰=፶፭(7+40+8=55)ቀን ይሆናል። የዐብይ ጾም ሳምንታት 8 ሲሆኑ: ፩. ዘወረደ ፪. ቅድስት ፫. ምኲራብ ፬. መጻጉዕ ፭. ደብረ ዘይት ፮. ገብርሔር ፯. ኒቆዲሞስ እና ፰. ሆሣዕና ናቸው። ጾሙን ጾመን ድኅነት የምናገኝበት የበረከት እንዲሁም ቤተክርሰቲያናችንን ከመዓት የምንታደግበት ያድርግልን! አሜን! @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
6 03069Loading...
30
.                       መግቢያ መግቢያ የአንድን መጽሐፍ ጠቅላላ ይዘት ለማወቅ የሚያስችል መግቢያ በር፣ መሪ ምርኩዝ ነው፡፡ ከዚህ ሐሳብ በመነሣት በመግቢያችን የመጽሐፉን ጠቅላላ ይዘት ስንመለከት በዐሥራ አንድ ምዕራፎች የተከፋፈለ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ እያንዳንዱም ምዕራፍ በውስጡ በርካታ ዓበይትና ንዑሳት አርእስትን አካቶ ይዟል፡፡   ምዕራፍ አንድን ስንመለከት የሰውን የሕይወት መነሻና አጀማመር፣ ቀጥሎም «ሙሉ ሰው› እስከሚሆን ድረስ ያለውን የእድገት ሂድት በየጥቂቱ ያስቃኛል፡፡ አያይዞም እግዚአብሔር «አምላክ ፅንስ›› እንደ ሆነና ለፅንስ ሊደረግ የሚገባውን አክብሮት ካስረዳ በኋላ ወጣት የሚያሰኘው ዘመን ከየት አስከ የት ያለው እንደ ሆነ ትንተና በመስጠት ምዕራፉን ይቋጫል::   ምዕራፍ ሁለት ደግሞ ወጣቶች ካሰቡበት «የልጅ ዐዋቂ» የሚያስብል እምቅ ችሎታ እንዳላቸው ጠቁሞ በተለይ በወጣትነት ዘመን በሚከሠት «ክፉ የጎልማስነት ምኞት» ተስበው ወጣቶች ከመልካም አኗኗር እንዳይወጡ ያሳስባል፡፡ በምዕራፉ ማጠቃለያ ላይም በወጣቶች ላይ ጎልተው የሚታዩና «ፆር» በመባል ስለሚታወቁ ዋና ዋና ፈተናዎች ያብራራል፡፡   በምዕራፍ ሦስት ላይ የዐፍላ ጉልምስና ምልክቶችን ከዘረዘረ በኋላ ምዕራፉ እስኪፈጸም ድረስ «ሕልመ ሌሊት» ምን እንደ ሆነ፣ ኃጢአት ስለሚሆንበትና ስለማይሆንበት መንገድ በአጠቃላይ ከ«ሕልመ ሌሊት» ጋር ተያይዘው ስለ ተሠሩ ሥርዓቶች ያብራራል:: በመጨረሻም ከ«ሕልመ ሌሊት›› ለመዳን የሚያስችሉ የመፍትሔ ሐሳቦችን በመጠቆም ምዕራፉን ይደመድማል፡፡   ምዕራፍ አራት «ግብረ አውናን» ምን እንደ ሆነና ተያያዥነት ያላቸውን ነጥቦች በሙሉ በሰፊ ገጸ ንባብ አስረድቶ የመፍትሔ ሐሳብ ይሰነዝርና ምዕራፉን ይፈጽማል፡፡
4 7209Loading...
31
አበው ከአፋፍ ላይ ነፋስ ከአፍ ላይ አስትንፋስ፡፡ እንዲሉ የሰው ልጅ በዘመኑ ሁሉ ሲተነፍስ ይኖራል፡፡ ይህም በተፈጥሮው ባሕርየ ነፋስ ለመኖሩ ምልክት ነው:: በጤናማ ሕይወት የሚታየው ቋሚ የሰውነት ሙቀቱ፤ በተለያዩ እንቅስቃሴዎችና በጤና መታወክ ጊዜ የሚያስመዘግዘበው ከፍና ዝቅ ያለ የሰውነት ሙቀት በሰውነቱ ባሕርየ እሳት ለመኖሩ በቂ ማስረጃ ነው፡፡ ምክንያቱም ዋዕይ ባሕርየ እሳት ነውና። ከሰው ሰውነት ብዙው እጅ ውኃ መሆኑ ደግሞ ከውኃ መገንባቱን ያሳያል፡፡ በተጨማሪም የሰው ልጅ በሚሞትበት ጊዜ አፈር ይሆናል፡፡ «አፈር ነህና ወደ አፈርም ትመለሳለህ>> ተብሏልና፡፡ ዘፍ. 3፥19 በሌላ አቅጣጫም ብንመለከት ሰው ሁሉ ግዙፍ ነገር ተመግቦ ግዙፍ ነገር ማስወገዱ የአፈርነት ባሕርይ አለው ያሰኛል:: ምክንያቱም የምንመገበው ማንኛውም ነገር ምንጩ አፈር ፍጻሜውም አፈር ነውና። የማቴዎስ ወንጌል ትርጓሜ <<በዪውም አፈር ተብዪውም አፈር ነውና።>> በማለት ምግቡ ብቻ ሳይሆን ተመጋቢው የሰው ልጅም አፈር መሆኑን ይገልጻል:: ማቴ. 15፥20   ቅዱስ ዳዊት << የዘመኖቻችንም ዕድሜ ሰባ ዓመት ቢበረታም ሰማንያ ዓመት ነው።>> ይላል፡፡ መዝ 89፥10 ይህን የሰው ልጃ ዕድሜ አራቱ ባሕርያተ ሥጋ በእኩል ይካፈሉታል፡፡ ይህም ማለት ምንም እንኳን አራቱም በሰው ልጅ የሕይወት ዘመን ሙሉ በአንድነት ቢዘልቁም በተለየ መልኩ ጐልተው የሚታዩበት ሃያ ሃያ ዘመን አላቸው ማለት ነው።   ከአንድ አመት እስከ ሃያ ዓመት ያለው ዕድሜ የነፋስ ባሕርይ ጉልቶ የሚታይበት በመሆኑ ይህ ዘመን <<ዘመነ ነፋስ>> ወይም «ምግበ ነፋስ» ይባላል፡፡ በዚህ ወቅት ነፋስ ወደ ወደደው ይነፍሳል» እንደተባለው ሕፃናት እንደመሰላቸው ሽው ሽው ይላሉ፡፡ ዮሐ 3፥8 ነገር ግን ነፋስ ምንም እንደማያሳይ ሁሉ በምግበ ነፋስ ያሉ ሕፃናትም ብዙ የሚያስተውሉት ነገር የለም፡   ሕፃናት በዘመነ ነፋስ ስለሚገኙ ዐላዋቂነት ያጠቃቸዋል፡፡ የያዙትን ውድ ነገር ዋጋ ለሌለው ብልጭልጭ ነገር ለመለወጥ በቀላሉ ይታለላሉ፡፡ ይህን በማነጻጸር እኛም በምግበ ነፋስ እንደሚገኝ ብላቴና ሆነን ሰማያዊውን ዓለም በኃላፊውና በብልጭልጩ ዓለም እንዳንለውጥ፤ ከሃይማኖትም ወደ ጥርጥርና ወደ ክህደት እንዳንመለስና በአእምሮ ሕፃናት መሆን እንደማይገባን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ሲል ይመክረናል፡፡ <<እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን ሕፃናት መሆን ወደፊት አይገባንም::>> ኤፌ 4፥14   ከሃያ እስከ አርባ ያለው ዕድሜ ደግሞ የእሳት ባሕርይ ጎልቶ የሚታይበት ነውና <<ዘመነ እሳት>> ወይም <<ምግበ እሳት>> ይባላል፡፡ ይህ ሰውን ወጣት የሚያሰኘው ዘመን ነው:: ከዚህም ምስጢራዊና ምሳሌያዊ ትምህርት በመነሣት ወጣትነትን «የእሳት ዘመን>> ወይም <<ፋየር ኤጅ>> ማለት ከቤተክርስቲያን የተገኘ እንጂ ከፈረንጅ (ከአውሮፖና ከአሜሪካ) የተወረሰ አለመሆኑን ልብ ይሏል፡፡ እሳት ብሩህ እንደሆነ ወጣቶችም ክፉና ደግን የሚያስለይ የዕውቀት ብርሃን አላቸው፡፡ ሆኖም እሳት ያገኘውን ልብላ (ላቃጥል) እንደሚል ሁሉ እንደዚሁም ወጣቶች ሁሉ የሚያምራቸውና ትምክህተኞች ናቸው። ከአርባ እስከ ስድሳ ያለው ዘመን <<ዘመነ ማይ>> ወይም <<ምግበ ማይ>> ሲባል ከስድሳ እስከ ሰማንያ ያለው ደግሞ <<ዘመነ መሬት>> ወይም <<ምግበ መሬት (አፈር)>> ይባላል::   ከሃያ እስከ አርባ ዘመን ያለው ዕድሜ ምግበ እሳት ቢባልም አንድ ወጣት ልክ ሃያኛ ዓመቱን ሲይዝ እሳታዊ ባሕርይ መጋቢነቱን ክነፋሳዊ ባሕርይ ይቀበላል ማለት አይደለም፡፡ ከአሥራዎቹ ዓመታት ጀምሮ እሳታዊ ባሕርይ መጋቢነቱን በእጁ ለማድረግ ሲጥር ነፋሳዊ ባሕርይም በበኩሉ ይዞታውን ለማስከበር እየታገለ እስከ ሃያዎቹ አጋማሽ ሊዘልቅ ይችላል:: በዚህ ትግል ምክንያት እሳታዊ ባሕርይ የበረታ እንደሆነ የወጣትነት መገለጫ ምልክቶች በአሥራ ሁለትና ከዚያም በታች በሆነ ዕድሜ ይከሠታሉ፡፡ ምግበ ነፋስ ከበረታ ደግሞ በሃያዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ወጣቶች ከጎረምሳነት ይልቅ ልጅነት ማሳየት የሚጀምሩት ዘግየት ብለው ይሆናል፡፡ ወጣትነትን በዘመን ሰፍሮ በዚህ ጊዜ ይከሠታል በዚህ ጊዜ ደግሞ ያክትማል» ብሎ የተወሰነ እኃዛዊ መረጃ ለመስጠት አስቸጋሪ ያደረገው ይህ መዋዠቅ ነው።   የእሳትነት ዘመን (ጕልማስነት) ከሃያ ዓመት በታች ሊጀምር እንደሚችል መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ዖዝያን <<የዐሥራ ስድስት ዓመት ጎልማሳ የነበረውን>> በማለት የሰጠው ገለጻ ያስረዳል፡፡ ዖዝያንን በዐሥራ ስድስት ዓመቱ ጎልማሳ ብሎታልና፡፡ 2ዜና 26፥1   ጎልማስነት ያለጥርጥር እስከ አርባና እስከ ሠላሳዎቹ መገባደጃ ድረስ ወይም ከዚያም በላይ ሊቆይ እንደሚችል ደግሞ «ኢዮሣፍጥም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሠላሳ አምስት ዓመት ጎልማሳ ነበር።>> ከሚለው የእግዚአብሔር ቃል መረዳት ይቻላል:: 2ዜና 20፥ 31 ምዕራፍ ሁለት ይቀጥላል...... @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
6 94223Loading...
32
ምዕራፍ አምስት ደግሞ በአጠቃላይ ስለ «ምትረተ እስኪት» በሰፊው ያብራራል፡፡ ምዕራፍ ስድስት ለዐቅመ ሔዋን የመድረስ ምልክቶችን በመዘርዘር ብቻ ያበቃል፡፡   ምዕራፍ ሰባት ደግሞ ስለ የ«ወር አበባ» ከስያሜዎቹ አንሥቶ አጠቃላይ ገጽታውን ካሳየ በኋላ ¡ዚሁ ጋራ ተያያዥ የሆኑ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ያስቀምጣል፡፡   ምዕራፍ ስምንት ስለ «ድንግልና» ምንነት፤ ስያሜዎች፣ ዓይነትና በድንግልና ዙሪያ በምእመናን ለሚጠየቁ የተለያዩ ጥያቄዎች ዝርዝር ማብራሪያ ይሰጣል፡፡ በአጠቃላይ ድንግልናን አስመልክቶ ሊባሉ የሚችሉትን ዙሪያ ገብ ነጥቦች የሚያስቃኝ ምዕራፍ ነው፡፡   ምዕራፍ ዘጠኝ የሴት ወጣቶች ዓይነተኛ ፈተና ስለሆነው የአለባበስ ሁኔታ ያትታል፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ስለ ፀጉር አያያዝና ስለ ተፈጥሮአዊ መልክ ሊኖር ስለሚገባ ትክክለኛ አመለካከት ሳይጠቁም አያልፍም፡፡   ምዕራፍ ዐሥር ወጣትነት ምቹ የትምህርት ጊዜ መሆኑን ይጠቁምና «በሚገባ መማር» እንደሚያስፈልግ ይገልጻል፡፡ ስለትምህርት ዓይነቶች! የመማርን ጥቅምና መማር በመንፈሳዊነት ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ በመግለጽ አስተያየቱን ያጠቃልላል፡፡   ምዕራፍ ዐሥራ አንድ ደግሞ የመጨረሻው ምዕራፍ እንደ መሆኑ መጠን ከላይ ከተጠቀሱት ሐሳቦች ሁሉ ጋር ወጣቶች «እግዚአብሔርን በመፍራትና ሰውን በማፈር» ለመኖር በሚያደርጉት ጥረት መጠን «ስኬታማ›› የመሆን ዕድል እንደሚኖራቸው ያስረዳል፡፡ በመጨረሻም «በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪን ማሰብ›› ለደስተኛና ስኬታማ ኑሮ ወሳኝ ነገር መሆኑን ጠቁሞ ሐሳቡን ይደመድማል፡፡  መልካም ንባብ!           ዲያቆን ኅብረት የሺጥላ(አሁን ቀሲስ) @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
3 5378Loading...
33
.                    ምዕራፍ አንድ                የሕይወት አጀማመር   የፍጥረት ሁሉ ባለቤት እግዚአብሔር ዓለም ሳይፈጠር እንደዛሬው ሁሉ ጥንትም አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይለያየው በአንድነት በሦስትነት ሲመስገን ይኖር ነበር። ዓለም ሳይፈጠር ማን ያመሰግነው ነበር? ቢባል በገዛ ባሕርዩ ይመሰገን ነበር ይሏል፡፡ «እምቅድመ ይፍጥር መላእክተ ለቅዳሴ አኮ ዘተጸርዓ ስብሐተ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ›› ፤ «መላእክትን ለምስጋና ሳይፈጥር የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ምስጋና አልተጓደለም» የሚል ቃል ተጽፎ ይገኛል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም «እንተ አባ ሰብሐኒ በስብሐትየ ዘሀሎ ምስሌክ እምቅድመ ይትፈጠር ዓለም «አባት ሆይ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር እንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ» ብሏል፡፡ ይህም የሥላሴ ምስጋናና ክብር ከዓለም በፊት እንደነበረ ሲያሳይ፡- ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ይህንን ይዞ በቅዳሴው ስብሐቲሁ ዘእምኀቤሁ ወውዳሴሁ እምዚአሁ» በማለት የሚመሰገነው ምስጋና ከሱ የተገኘ የባሕርይ ገንዘቡ መሆኑን ገልጿል፡፡ ዮሐ17፥5 ፣ ቅዳ. ዮሐ.አፈ.ም 1፥13
3 46025Loading...
34
እግዚአ ዓለም ሥላሴ ዓርብ ዕለት በነግህ «ንግበር ሰብኣ በእርእያነ ወበአምላሊነ>> ማለትም «ሰውን በመልካችን እንደምሳሌያችን እንፍጠር» ብለው አራቱን ባሕርያተ ሥጋና አምስተኛ ባሕርየ ነፍስን አዋሕደው አዳምን የሠላሳ ዓመት ጎልማሳ አድርገው በምድር ማዕከል በቀራንዮ ፈጠሩት፡፡    ፈጣሬ ፍጥረታት አምጻኤ ዓለማት ልዑል እግዚአብሔር «አዳም ብቻውን ይኖር ዘንድ አይገባም ረዳትን እንፍጠርለት» በማለት በአዳም ላይ እንቅልፍ አመጣበት፡፡ ከዚህ በኋላ አዳም ፈጽሞ ሳይተኛ ፈጽሞም ሳይነቃ ማዕከል ነቂሕ ወነዊም ሆኖ ሳለ ከጎኑ እንድ አጥንትን ወስዶ ያችንም ሥጋ አልብሶ የዐሥራ አምስት ዓመት ቆንጆ አድርጎ ሔዋንን ፈጠረ።   «ዘበጸጋሁ ተፈጥረ ኩሎ» ፤ «ሁሉ በቸርነቱ ተፈጠረ» እንደተባለው አዳምና ሔዋን ከእግዚአብሔር የባሕርይ ደግነት የተነሣ እርሱን ለማመስገን ክብሩን ለመውረስ ተፈጠሩ፡፡ (ቅዳ.ሠለ.ምዕት 1፥7) አዳምና ሔዋን በቀጥታ በእግዚአብሔር እጅ ተፈጠሩ እንጂ መፀነስና መወለድ አላስፈለጋቸውም፡፡ ከእነርሱም ሌላ ፅንስ ምክንያት ሳይሆነው በቀጥታ በእግዚአብሔር እጅ የተፈጠረ የሰው ወገን የለም፡፡ ሰው ሁሉ ለመገኘት መወሰድ ለመወለድ ደግሞ መፀነስ ይኖርበታል:: የሰው ሁሉ ሕይወት የመጀመሪያ መንገድ ይህ ነውና፡፡ ስለሆነም የአዳም ዘር ሁሉ የተገኘው ወንድና ሴት (ባልና ሚስት) በፈጸሙት ሩካቤ አማካኝነት ተፀንሶ ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የአዳም ዘር ሆኖ ሳለ በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንበለ ዘርና እንበለ ሩካቤ በኅቱም ድንግልና ተወልዷል:: እግዚአብሔር የሰው ልጆች ዘር በመውለድና በመዋለድ እንዲበዛ በአዳምና በሔዋን የጋብቻ መሠረትን ጣለ። በሩካቤም አማካኝነት መብዛት የእርሱ ፈቃድ መሆኑን ለመግለጽ «ብዙ ተባዙ» በማለት ባረካቸው ተባዙ የሚለው ቃል ለመብዛት ሲሉ ሰዎች እርስ በእርሳቸው የሚያከናውኑት ተግባር እንዳለ ያስረዳል፡፡ እርሱም ሩካቤ ሥጋ ነው፡፡ የሰው ልጆች የሚፈጽሙትን ሕጋዊ ሩካቤ እግዚአብሔር የማይቀበለው ሆኖ እርሱ የሚፈልገው መብዛታቸውን ብቻ ቢሆን ኖሮ « ብዙ» የሚለው ቃል ብቻውን በቂ በሆነ ነበር ምክንያቱም እግዚአብሔር <<ብዙ>> ካለ እሳቱም፤ እንጨቱም! ድንጋዩም ስለሚበዛ ነው፡፡ (ትዳርና ተላጽቆ)          «ሙሉ ሰው ወደ መሆን» ማደግ   ቀደም ሲል እንደተገለጸው ‹ብዙ ተባዙ» በሚለው እመላካዊ ቃል መሠረት ባልና ሚስት (ወንድና ሴት) ሩካቤ በፈጸሙ ጊዜ ከሴት ደም ከወንድ ደግሞ ዘር ይከፈልና በሴቲቱ ማኅፀን ውሕደት ያደርጋሉ፡፡ በዚህ ጊዜ አዲስ ሕይወት ይጀምራል፡፡ ፅንስ ይፈጠራል፡፡    ይህ ፅንስ ነፍስ ያለችው ነው እንጂ የዘርና የደም ውሕደት ብቻ አይደለም:: በቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አስተምህሮ መሠረት ሰው ሲፈጠር ሥጋውም ነፍሱም በአንድ ጊዜ ይገኛሉ እንጂ አይቀዳደሙም:: በፅንስ ጊዜ ዘርና ደም ከአባትና ከእናት ሲከፈሉ ነፍስ ሳትቀደም እርሷም ሳትቀድም አብራ ትከፈላለች:: የነፍስም የሥጋም መገኛዎች ወላጆች ናቸውና።    እንጨትን ሲሰብቁት ድንጋይን ሲያጋጩት ከእንጨት ከድንጋይ የተለየ ባሕርይ ያለው እሳት እንደሚገኝ ባልና ሚስትም ሩካቤ ባደረጉ ጊዜ ዘርና ደም ተዋሕደው ፅንስ ሲፈጠር በዚያው ጊዜ እንደ እሳቱ ምሳሌ በባሕርይዋ ከዘርና ከደም ልዩ የሆነች ነፍስ ትገኛለች፡፡   ቅቤ አስቀድሞ በወተት ውስጥ በመኖሩ ወተት ለመርጋት ይችላል:: ቅቤ ባይኖረው ኖሮ ግን ለመርጋት ባልቻለም ነበር። እንደዚሁም ፅንስ በሚፈጠርበት ጊዜ በዘርና በደም አማካይነት ነፍስ ከእናትና ከአባት ተከፍላ ከፅንሱ ጋር ተዋሕዳ ባትኖር ኖሮ ፅንሱ በገበታ እንደተቀበሎት ደም ከመርጋት አልፎ እየደረቀ በሄደ ነበር እንጂ ሕያው ፍጡር ወደ መሆን መራመድ ባልቻለም ነበር፡፡   የትዕግሥት አባት ኢዮብ የወተት መርጋት ለፅንስ አጀማመር በምሳሌ መጠቀስ እንደሚችል «ከመ ሐሊብ ሀለብከኒ ወከመ ግብነት አርጋዕከኒ» ማለትም« እንደ ወተት አለብከኝ እንደ እርጎም አረጋኸኝ ቁርበትና ሥጋ አለበስኸኝ በአጥንትና በጅማትም አጠነከርኸኝ። ሕይወትና ቸርነት አደረግህልኝ በማለት ተናግሯል::>> ኢዮ10፥10-12   በዚህ መሠረት የዕለት ፅንስ በመሆን የተገኘው ሕያው ፍጡር ቀስ በቀስ ሥጋ፣ አጥንት፣ ጅማት፣ ጠጉር፣ ጥፍር …ወዘተ ወደመሆን ሲራመድ ነፍስም በበኩሏ ሥጋዊ አካል ወይም ገላ መሆን የጀመረውን ፅንስ በማንቀሳቀስ የሕይወትነት ሥራዋን ትጀምራለች::ይህ የሕይወት ጉዞ የሚከናወነው በፅንሱ ኃይል ወይም በወላጆቹ ሐሳብና ፈቃድ አይደለም፡፡ ነቢዩ ዳዊት «ውእቱ ፈጠረነ ወአኮ ንሕነ - እርሱ ሠራን እኛም አይደለንም፣>> ብሎ እንደተናገረው ፅንስ የሚፈጠረው በእግዚአብሔር ፈቃድና ኃይል ነው፡፡   ወላጆች ልጆቻቸውን ምን ዓይነት ሰው መምሰል እንዳለባቸው የሚወስን ንድፍ እውጥተው እይወልዷቸውም። ሆኖም ለአዲስ ሕይወት መጀመር ምክንያት መሆናቸው አይካድም አሁንም ስለዚህ ጉዳይ ቅዱስ ዳዊት እናትና አባቴ ትተውኛልና እግዚአብሔር ግን ተቀበለኝ>> በማለት ተናግሯል፡፡ የዚህ ዐረፍተ ነገር ምሥጢር «አባትና እናቱ የፈቃዳቸውን ያህል ተገናኝተው በማኅፀን ጥለውኛልና እግዚአብሔር ግን በሕይወት ተቀበለኝ : ማለትም ሕያው እንድሆን አደረገኝ::» ማለት እንደሆነ የዳዊት አንድምታ ያስረዳል:: ከዚህም ትርጓሚ ጠላጆች ለፅንስ መገኘት ምክንያት ሊሆኑ እግዚአብሔር ግን የፅንስ ባለቤትና ተጠሪ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡ መዝ 26 ፥10   ፅንስ አምላክ አለው፡፡ አምላኩም ተስፋውም እግዚአብሔር ነው፡፡ ብዙዎች ግን ይህን የተገነዘቡ አይመስልም፡፡ ከእነርሱ በላይ ለፅንስ ተጠሪ ያለ አይመስላቸውም፡፡ ለዚህም ምስክሩ ፅንስን አንደ ቆሻሻ ውኃ የትም (በየቦታው) ማፍሰሳቸውና ውርጃን ያለ ሐሳብ ከመፈጸማቸውም በላይ በሀገራችን በኢትዮጵያ ሕግ ጸድቆ በአዋጅ እንዲፈቀድ ለማድረግ ሲሯሯጡ መመልከታችን ነው፡፡ ቅዱስ ዳዊት ነቢይ ነውና ያለፈውንም የሚመጣውንም የሚያውቅበት ጸጋ እግዚአብሔር ለግሶታል፡፡ በዚህም ጸጋው እሱ ራሱ ፅንስ በነበረበትና ምንም በማያውቅበት ዘመን ስለነበረው የእግዚአብሔር ጥበቃ ሲናገር እንዲህ ብሏል:- «ከማኅፀን ጀምሮ በአንተ ላይ ተጣልሁ፤ ከእናቴ ሆድ ጀምረህ አንተ አምላኬ ነህ» መዝ 21፥10 ከዚህ ጥቅስ እግዚአብሔር አምላከ ፅንስ እንደሆነና ሂደቱንም በሙሉ ከወላጆችና ከሕክምና ባለሙያዎች በላይ እንደሚከታተል መረዳት ይቻላል። ከላይ የተጠቀሰውን የሕይወት እጀማመር ጨምሮ ከፅንስት አስከ ውልደትና ርሥአን (እርጅና) ድረስ ያለው የሰው ልጅ የሕይወት ጉዞ በእግዚአብሔር ጠባቂነትና ኃይል እንደሚከናወን ለማስረዳት ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንዱ የሆነው ቅዱስ አትናቴዎስ የሚከተለውን ጽፏል፡፡ «ኦ! ዘታወፅእ ለሕፃን እምሐቌ ብእሲ ወትፌንዎ ውስተ ከርሠ ብእሲት - ሕፃንን ከወንድ ወገብ (አብራክ) ክፍለህ ወደ ሴት ማኅፀን የምትልከው ሆይ!>> ብሏል:: በዚህ ጽሑፍ ሊቁ <<ሕፃን>> ያለው ዘርዓ ብእሲን (የወንድ ዘርን) ነው፡፡ ምክንያቱም ሕፃን ለመሆን የሚበቃው የወንድ ዘር ስለሆነ በወደፊት ማንነቱ ሕፃን በማለት ጠራው:: ከዚህም ገጸ ንባብ የፅንስ መፈጠር የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑንና ወንድና ሴት ሩካቤ ቢያደርጉም ያለ እግዚአብሔር አጋዥነት ፅንስ የመፍጠር ችሎታ እንደሌላቸው እንረዳለን፡፡ ሕግ ወጥ ሰዎች እንኳን በዝሙት ቢፀንሱ እነርሱ ስለዝሙታቸው ይጠየቃሉ እንጂ ፅንሱ የተገኘው በእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑ መጠርጠር የለበትም፡፡
4 42721Loading...
35
አትናቴዎስ ስለፅንስ በመቀጠል <<በሰፋድል የምትጠቀልለው፣ ውኃ ሲሆኑ በባሕርይ ጥበብህ የምታረጋው አንተነህ፣ የሕይወት መንፈስንም እፍ ትልበታለህ » በማለት ከተናገረ በኋላ በተጨማሪ <<በሆነ ሆኖ በ፵/40 ቀን ታድለዋለህ:: ባለጸጋ ለመሆን ለመደኽየትም ቢሆን ለመጽደቅም ለመኮነንም ቢሆን» ይላል:: ይህን ማለቱ ግን እግዚአብሔር በ፵ኛው/40ኛው ቀን አንተ ባለጸጋ ሁን እንተ ደግሞ ደሀ ሁን፤ እንተ ጽደቅ አንተ ደግሞ ተኰነን የሚል ሆኖ አይደለም፡፡ የዚህ ሐተታው እንደሚከተለው ነው፡፡ ፅንስ እንደ ውኃ ሆኖ ሳይታወቅ ለቀናት ይሰነብታል:: በኋላም ጭራ ከምትመስል እይታ በመነሣት እየዳበረ ይመጣና በ፵ኛው ቀን ተሥዕሎተ መልክዕ (ሕዋሳት) ይሟሉለታል፡፡ በእነዚህ ሕዋሳት ቢጥርባቸው ባለጸጋ የሚሆንባቸው ቢታከይ (ቢታክት) ደሀ የሚሆንባቸውና በጎ ቢሠራ የሚጸድቅባቸው ክፉ ቢሠራራ ደግሞ የሚኰነንባቸው በመሆናቸው እንዲህ በማለት ተናገረ፡፡   ፅንስ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ብቻ አስገራሚና የተወላሰበ አደረጃጀት ያለው ሙሉ በሙሉ የዳበረና በቂ አካል (አካል ዘየእክል) ያለው ሕፃን ይሆናል፡፡ ከዚህ በኋላ ከውስጥ የሚገፋ ከውጭ የሚስብ ሳይኖር በእግዚአብሔር ጥበብ ከጨለማ ወደ ብርሃን ከጠባብ ወደ ሰፊው ዓለም ይመጣል:: በዚህ ጊዜ ሕፃን ተወለደ ይባላል፡፡  ዮሐ 16፥21   ሕፃን እንዲወለድ የሚያደርገው እግዚአብሔር ነው፡፡ ቅዱስ ዳዊት <<አንተ ግን ከሆድ አውጥተኸኛልና>> በማለት ተናግሯል፡፡ መዝ21፥9 ይህን ይዞ ቅዱስ አትናቴዎስም <<ዳግመኛም ከማኅፀን ታወጣዋለህ>> ብሏል:: በተጨማሪም <<ዓይኑን ትግልጥለታለህ ጉሮሮውን ከፍተህ ታስጮኸዋለህ እጁንና እግሩን ታንቀሳቅሰዋለህ የእናቱን ጡት ያውቅ ዘንድ>> የዚህን አንቀጽ ሐተታ የቅዳሴ አትናቴዎስ ትርጓሜ ሕፃን በተወለደ ጊዜ ዓይኑ ይገለጣል፤ ጉሮሮው ይከፈታል፡፡ የእግዚአብሔርም መልአክ የሚቀበርበትን መቃብር ከፍቶ በሕሊና ያሳየዋል፡፡ እንዲሁም ከሚቀበርበት ምድር አፈር አምጥቶ ያቀምሰዋል፡፡ የዚህን ጊዜ ምርር ብሎ ያለቅሳል፡፡ ሲያለቅስ ዕንባ የለውም ዕንባው የሚፈሰው በሚሞትበት ጊዜ ነው» በማለት አስቀምጦታል፡፡   የሰው ልጅ ስለ አፈጣጠሩ በመረመረ ጊዜ የእግዚአብሔርን ውለታ ይረዳል፡፡ በኑሮውም ማማረርን ትቶ ወደ ማመስገን ይመለላል፡፡ ቅዱስ ዳዊት «ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፣ ሥራህ ድንቅ ነው ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች፡፡ እኔ በሥውር በተሠራሁ ጊዜ እካሌም በምድር ታች በተሠራ ጊዜ አጥንቶቼ ከእንተ አልተሠወሩም፡፡ ያልተሠራ አካሌን ዓይኖችህ አዩኝ! የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ>> በማለት የተናገረው አፈጣጠሩን በመንፈስ ቅዱስ መነጽርነት መመርመር ስለቻለ ነበር፡፡ መዝ 138፥14-16   ካለ መወለድ መወለድ ይሻላል፡፡ ምክንያቱም መወለድ በሚወደድ ፈጣሪ ልቡና በፍጡርነት አንድ ተብሎ መቆጠር ከመሆኑም ባሻገር ለዘለዓለም ሕይወት መታጨት ነውና፡፡ነገር ግን ተወልዶ በክፉ ሥራ ምክንያት ከመኮነን ጥንቱንም አለመፈጠር ይሻላል፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለይሁዳ ሲናገር «ያ ሰው ባልተወለደ ይሻለው ነበር» ያለው ስለዚህ ነው:: ማቴ 26፥ 24፤ ትዳርና ተላጽቆ 2ኛ እትም ገጽ 43   የፅንስ ዕድገት ፈጣን ነው:: ነገር ግን ከተወለደ በኋላ አስተዳደጉ እንደ ፅንስነቱ ወራት ፈጣን አይሆንም፡፡ ሆኖም ከመጀመሪያዎቹ አሥራዎች ጀምሮ ሌላ የተፋጠነ የዕድገት እመርታ ይከሠታል:: በዚህ ጊዜ ከልጅነት ወደ ወጣትነት የመለወጥ ሂደት ይጀምራል፡፡   <<በበሕቅ ልህቀ» እንደተባው በየጥቂቱ ይሁን እንጂ ሰው ሁሉ እያደገ ሄዶ ሙሉ ሰው» የሚባለው በአዳም ልክ ሲሆን ነው፡፡ ዓቅመ አዳም እንደሚባለው ማለት ነው:: ይኸውም ሠላሳ ዘመን ነው፡፡ አዳም በተፈጠረ ጊዜ የሠላሳ ዓመት ጎልማሳ ነበርና። ዓመት የሞላው ጠቦት ወርድ እንጂ ቁመት እንደማይጨምር ሠላሳ ዓመት የሞላው ጎልማሳም እንዲሁ ቢወፍር ቢከሣ እንጂ ቁመት አይጨምርም፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንደ ጎልማሳ እንጂ በአእምሮ እንደ ሕፃናት እንዳንሆን ይመክርና ማደግ እንደሚያስፈልገን ይናገራል፡፡ ዕድገታችንም እስከ የት እንደሆነ ልኩን ሲናገር «ሙሉ ሰውም እስከ መሆን>> ይለናል፡፡ የሙሉነትም መለኪያው እስከ አዳም ወይም እስከ ሁለተኛው አዳም «ብጹሐ አምጣን በአቅመ ፍጻሜሁ ለክርስቶስ›› (ለአካለ መጠን እስከ ደረሰ እስከ ክርስቶስ) በዕድሜ መድረስ መሆኑን በዚህ መልኩ ገልጾልናል:-<< ሙሉ ሰውም ወደ መሆን የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ እንደግ» ኤፌ.4፥13-15   ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በቅዳሴው የሰው ልክ ወይም ወጣትነት የሚባለው በክርስቶስ ዕድሜ ልክ መሆኑን ሲገልጽ «ወልህቀ በበሕቅ እስከ ወርዘዉ በእምጣነ ብእሲ - በሰው መጠን እስኪጎለምስ ድረስ በየጥቂቱ አደገ» ብሏል። ቅዳ.ኤጲፋ.ቁ.54   <<ሙሉ ሰው>> የሚባለው ወጣት ነው፡፡ ወጣት ማለት ደግሞ ሎጋ፣ሽበላ፣ልጅ እግር፣ መዘዞ፣ ቀንበጥ ማለት ሲሆን በተጨማሪም ጉልማሳ፣ ጎብዝ፣ ሪዛም፤ ለዘር የበቃ፣ ዐፍላ ማለት እንደሆነም የሚያትት መዝገበ ቃላት ይገኛል፡፡ (ዘርጋው የአማርኛ መዝገበ ቃላት፣ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት) የግእዝ ቋንቋ ደግሞ ወጣት ለማለት <<ወሬዛ>> በብዙ ቁጥር ወጣቶች ለማለት ደግሞ «ወራዙት ይላል፡፡   አስቀድሞ እንደ ተገለጸው <<ሙሉ ሰው>> የሚባለው ንዋያት የተሟሉለት ማለትም ሕዋሳት ተደራጅተውለት እንደ ልቡ ማሰብ፤ መንቀሳቀስና መናገር የሚችል ሰው ነው:: <<ሙሉ ሰው>> ኃላፊነት መውሰድ ይችላል:: <<ሙሉ ሰው>> ስለ ራሱ መግለጽ ይቻለዋል፡፡ መልስ ለመስጠት ብቁ በመሆኑም እርሱን በሚመለከት ጉዳይ ሁሉ ይጠየቃል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ዓይኑ በፈጣሪ ተአምር ስለዳነለትና ለአቅመ አዳም ስለደረሰ ልጃቸው ወላጆቹ ማብራሪያ ሲሰጡ <<እርሱ ሙሉ ሰው ነው እርሱ ስለ ራሱ ይናገራልና ራሱን ጠይቁት>> ብለዋል፡፡ ዮሐ9፥21-23 ከዚህ ወጣት ወላጆች ንግግር <<ሙሉ ሰው>> የሚባለው ስለ ራሱ መናገር የሚችል፤ አስቦ የሚሠራና ሲጠየቅ የሚመልስ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡ በአጠቃላይ <<ሙሉ ሰው>> የሚባሉት ለአቅመ ሔዋንና ለአቅመ አዳም የደረሱ ወንዶችና ሴቶች ናቸው።                 ዘመነ ውርዛዌ   ዘመነ ውርዛዌን (የወጣትነት ዘመንን) በቁጥር ሰፍሮ ከዚህ እስከዚህ ያለው ነው ብሎ ለመናገር አስቸጋሪ ነው፡፡ ሆኖም አንዳንድ መጻሕፍት ከዚህ እስከዚህ ያለው ዘመን ወጣት ያሰኛል በማለት አዛዊ መረጃ ይሰጣሉ። በቅድስት ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊና ምሳሌያዊ አስተምህሮ ደግሞ ወጣትነት የሚባለው ከሃያ እስከ አርባ ዓመት ያለው ዕድሜ እንደሆነ ከዚህ በታች የተሰጠው ሐተታ ያስረዳል፡፡ እንደሚታወቀው ሁሉ የሰው ተፈጥሮ ከነፋስ፣ ከእሳት፣ ከውኃ፤ ከአፈርና አምስተኛ ደግሞ ነፍስን ጨምሮ ነው:: አራቱ ባሕርያተ ሥጋ የሚባሉት ነፋስ፣ እሳት፣ ውኃና አፈር ሲሆነ እነዚህ በሙሉ በአንድ ሰው የሕይወት ዘመን ሲንጸባረቁ ይኖራሉ፡፡ በሚሞትበትም ጊዜ አራቱም ወደ ነበሩበት ጥንተ ህላዌ ይመለሳሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ሥጋ ይበሰብሳል ይፈርሳል:: በትንሣኤ ዘጉባኤ ደግሞ አራቱም ባሕርያት ከነፍስ ጋራ እንደገና ተዋሕደው ይነሣሉ፡፡
5 67613Loading...
36
@Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
6 5664Loading...
37
ነዋ ጊዮርጊስ ነዋ ጊዮርጊስ አሐዱ እም ቅዱሳን ሰማዕት መጽአ ይርድአኒ ይቤ ምኒልክ ንጉሥ። ትርጉም ንጉሥ ምኒልክ አለ እነሆ ከቅዱሳን ሰማዕት አንድ የሆነ ጊዮርጊስ ሊረዳኝ መጣ። @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
7 85122Loading...
38
የካቲት ፳፫ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት በዓድዋ የካቲት ሀያ ሦስት በዚህች ቀን ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት አባቶቻችንን ዓድዋ ላይ የረዳበት ነው፡፡ በዚያን ወራት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ከአንድ ሺህ ስምንት መቶ ሃምሳ አራት ዓመት በኋላ የኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አጤ ምኒልክ በነገሡ በሃያ ስድስት ዓመት የምኒልክ የጦር አለቃ ገበየሁ ድል ከአደረጋቸው በኋላ እንደገና ምኒልክን ወግተው ኢትዮጵያን በቅኝ አገዛዝ ሊገዙ የሮም ሰዎች መጡ። ከዚህም በኋላ የኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት፡ ዳግማዊ አጤ (ዓፄ) ምኒልክ መስከረም ፯ ቀን ፲፰፻፹፰ (1888 ዓ.ም) ላይ "እግዚአብሔር በቸርነቱ፡ እስከ አሁን ጠላት አጥፍቶ አገር አስፍቶ አኖረኝ፡፡ እኔም እስከ አሁን በእግዚአብሔር ቸርነት ገዛሁ፡፡ እንግዲህ ብሞትም ሞት የሁሉ ነውና ስለ እኔ ሞት አላዝንም፡፡ ደግሞ እግዚአብሔር አሳፍሮኝ አያውቅም፡፡ እንግዲህም ያሳፍረኛል ብዬ አልጠራጠርም፡፡ አሁንም አገር የሚያጠፋ፤ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት፤ እግዚአብሔር የወሰነልንን የባህር በር አልፎ መጥቷልና እኔም የአገሬን ከብት ማለቅ፤ የሰውን መድከም አይቼ እስከ አሁን ዝም ብለው ደግሞ እያለፈ እንደ ፍልፈል መሬት ይቆፍር ጀመር፡፡ አሁን ግን በእግዚአብሔር ረዳትነት አገሬን አሳልፌ አልሰጠውም፡፡ የአገሬ ሰው፤ ከአሁን ቀደም የበደልሁህ አይመስለኝም አንተም እስከ አሁን አላስቀየምኸኝም፡፡ ስለዚህ ስንቅህን በአህያ አመልህን በጉያህ ይዘህ ጉልበት ያለህ በጉልበትህ እርዳኝ፡፡ ጉልበት የሌለህ ለልጅህ፤ለሚስትህ፤ ለሃይማኖትህ ስትል በኀዘን እርዳኝ፡፡ ወስልተህ የቀረህ ግን በኋላ ትጣላኛለህ አልተውህም፡፡ ማርያምን! በዚህ አማላጅ የለኝም"፡፡ ዘመቻዬም በጥቅምት ነውና የሸዋ ሰው እስከ ጥቅምት እኩሌታ ድረስ ወረይሉ ከተህ ላግኝህ" ብለው አዋጅ አስነገሩ፡፡ ዳግኛም በፈረሶታቸው መጣብር ላይ በጦራቸው አንደበት ላይ የመስቀል ምልክት እንዲያደርጉ ጭፍሮችን አዘዛቸው መስቀል ጠላትን ድል አድራጊ እንደሆነ አስቀድሞ ያውቅ ነበርና። አዋጁን ካስነገሩ በኋላ ከዚያም ተነሥቶ ወደ ትግራይ ክፍለ አገር ዘመቱና ከትግራይ አውራጃ አንዷ የምትሆን ዓድዋ የምትባል አገር ደረሱ፡፡ የሣህለ ማርያም (ዳግማዊ ምኒልክ) ሚስት ወለተ ሚካኤል (እቴጌ ጣይቱም) በንጉሡ ትዕዛዝ ታቦተ ጊዮርጊስን አስይዘው ከሊቀ ጳጳሱ ከአባ ማቴዎስ እንዲሁም ከቀሳውስቱና ከመነኰሳቱ ጭምር ከንጉሡ ጋር ወደ ጦርነቱ ተጓዘች፡፡በዚያም ጊዜ የአክሱም ጽዮን መነኰሳትና ካህናት የእመቤታችንን ሥዕል ይዘው ወደ ንጉሡ ወደ ምኒልክ መጥተው ከሊቀ ጳጳሱ ከነአቡነ ማቴዎስ ጋር ተቀላቀሉ ከዚያም ሌሊቱን ሙሉ ጸሎት ምሕላ ሲያደርሱ አደሩ። ቅዳሜ ማታ ለእሑድ አጥቢያ የካቲት ሃያ ሁለት ቀን ነው ንጉሡ ሣህለ ማርያም (ምኒልክ) የጦር ልብሱን ለብሰው ከሠራዊቱ ጋር ወደ ጦር ግንባር ሄደ፡፡ ከዚያም ከሮማውያን የጠላት ጦር ጋር ተገናኝቶ ከሌሊቱ ዐሥራ አንድ ሰዓት ጦርነቱን ጀመረ፡፡ የንጉሡ የሣህለ ማርያም (የምኒልክ) ሚስት ወለተ ሚካኤል (እቴጌ ጣይቱም) ሌሊት በታቦተ ቅዱስ ጊዮርጊስና በእመቤታችን ሥዕል ፊት በጸሎትና በስግደት እያደረች ሲነጋ ወደጦርነቱ ቦታ በመሄድ እጅግ ለሚያስደንቅ የአነጋገሯ ኃይል ቃል በጦርነቱ መካከል እየተገኘች ለንጉሡ ወታደሮች የሞራልና የብርታት ድጋፍ ትሰጣቸው ነበር። በእውነትም ለተመለከታት ሁሉ እንደ ኃይለኛ ተጋዳይ አርበኛ ትመስል ነበር እንጂ የሴቶች የተፈጥሮ ባሕርይ በእርሷ ላይ አይታይባትም ነበር። የንጉሡም ወታደሮች የንግሥቲቱን የጀግንነት አነጋገር በሰሙ ጊዜ በእሳት ላይ እንደተጣደ የብረት ምጣድ ልባቸው ጋለ ይልቁንም ላም እንዳየ አንበሳና የፍየል መንጋ እንዳየ ነብር እየተወረወሩ በጦርነቱ መካከል በመግባት የጠላትን ጦር በሰይፍ ይጨፈጭፋት ነበር። መጽሐፍ ሹመትን ሽልማትን ያየ አርበኛ ከጦርነት ከሰልፍ ወደኋላ አያፈገፍግም ብሎ ተናግሯልና፡፡ በዚያም ጊዜ ንጉሡ ሣህለ ማርያም (ምኒልክ) በጦርነቱ መካከል ሳለ ሊቀ ጳጳሱ አባ ማቴዎስ እንዲሁም የአክሱም መነኰሳትና ሌሎቹ ካህናት በሙሉ ታቦተ ጊዮርጊስንና ሥዕለ ማርያምን ይዘው ከንጉሡ በስተኋላ በደጀንነት ቆመው ጸሎተ ምህላ ያደርሱ ነበር። ንግሥቲቱ ወለተ ሚካኤል (እቴጌ፡ጣይቱም) በጸሎት ጊዜ በመዓልትም በሌሊትም ከእነርሱ አትለይም ነበር። የጽዮን አገልጋዮችም በእግዚአብሔር የሕጉ ታቦት ፊት መለከት ይነፉ ነበር። በዚህም ዕለት ይኸውም የካቲት ሃያ ሦስት ቀን በሮማውያንና በኢትዮጵያውያን መካከል ከፍተኛ ጦርነት ሆነ በዚህም ጊዜ በሰማይ ታላቅ ተአምር ተደረገ። ማለትም የቀስተ ደመና ምልክት ታየ ከዚያም ከቀስተ ደመናው ውስጥ መልኩ አረንጓዴ የመሰለ ጢስ ይወጣ ነበር፡፡ ከዚህም ጢስ ውስጥ እንደ ክረምት ነጐድጓድ ያለ ድምጽ ተሰማ፡፡ ከዚህም የነጐድጓድ ድምጽ የተነሳ በሮማውያን ወታደሮች ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤና ሽብር ሆነ ለመዋጋት አልቻሉም፡፡ ይልቁኑ ኃያሉ ገባሬ ተአምር ማር ቅዱስ ጊዮርጊስ በአምባ ላይ ፈረሱ ተቀምጦ ከነፋስ ሩጫ ይልቅ እየተፋጠነ በአየር ላይ በተገለጸ ጊዜ በግንባራቸው ፍግም እያሉ ወደቁ፡፡ "የኢትዮጵያ ህዝብ አምላካቸው ሊረዳቸው መጣ እንግዲህ ማን ያድኅነናል" አሉ ምድርም ጠበበቻቸው በዚህን ጊዜ የኢትዮጵያ ሠራዊት የሮምን የጦር ሠራዊት ፈጁዋቸው የተረፉትንም ማረኳቸው ፈጽመውም እስኪያጠፏቸው ድረስ በሮማውያን ላይ በእግዚአብሔር ሥልጣን የኢትዮጵያውያን እጅ እየበረታ ሄደ፡፡ ከዚህም በኋላ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ሣህለ ማርያም (ምኒልክ) በእግዚአብሔር ኃይልና በተአምራት አድራጊው በቅዱስ ጊዮርጊስ ተራዳይነት የሮማውያንን የጦር ሠራዊት ድል አድርገው የድል አክሊል ተቀዳጅተው ተመለሱ፡፡ ስለዚህም በዳዊት የምስጋና ቃል የድል ዘውድ ያቀዳጀኝን እግዚአብሔር "ባለ ዘመኔ ሁሉ አመሰግነዋለሁ ለፈጣሪዬ እዘምራለሁ" አለ ሕዝቡም ሁሉ "በክብር ከፍ ከፍ ያለ እግዚአብሔርን በፍጹም ምስጋና እናመስግነውለን የሮማውያንን ኃይል ቀጥቅጦ አጥፍቷልና ሠረገሎቻቸውንም ሠባብሯልና ሠራዊቱንም ሁሉ በምድር ላይ በትኗልና" እያሉ አመሰገኑ። በፈጣሪው በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል በጦርነቱ መካከል የረዳውን ቅዱስ ጊዮርጊስንም በፍጹም ማድነቅ አደነቁ። የሮማም የጦር ሠራዊት በኢትዮጵያውያን ፊት ተዋረዱ ዳግመኛም በኢትዮጵያ ላይ ራሳቸውን ከፍ ከፍ አላደረጉም። በምኒልክም ዘመነ መንግሥት ኢትዮጽያ ከጦርነት ለዓርባ ዓመት ያህል አረፈች። የኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት ምኒልክ ከአደዋ ጦርነት ከተመለሱ በኋላ በአዲስ አበባ በምትበል ከተማው መካከል በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ቤተክርስቲያን አሠራ። ስሟንም ገነተ ጽጌ ብለው ሰየሟት። ቅዱስ ጊዮርጊስ በጦርነት ቦታ ሁሉ ይረዳው ነበርና። ልመና ክብሩ በኛ ለዘላለሙ በዕውነት ይደረግል። በረከቱ ከእኛ ጋር ትሁን እኛንም በቅዱስ ጊዮርጊስ አማላጅነት ይማረን ለዘለዓለሙ አሜን!!! (ገድለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተአምር 17) @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
6 01131Loading...
39
‹‹ዲያቢሎስ ፕሮጀክቱን ማስተጓጎል ይፈልጋል፡፡ እናም ውዝግብ ካስነሣ በኋላ ወደ አንተ መጥቶ በፍቅርና አንድነት ስም ፕሮጀክቱን እንድታቆም ሊያሳምንህ ይሞክራል፡፡ ማድረግ ያለብህ እንዲህ ነው፡፡ ሒድና ፕሮጀክቱን ቀጥል ፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ ፕሮጀክቱ ወደ መሳካት ሲያመራ ውዝግቡ ያበቃል፡፡›› አሉኝ ብፁእነታቸው፡፡ ያ አጋጣሚ ሳላማክር በራሴ ውሳኔ ላይ እንዳልተማመን ትልቅ ትምህርት ሰጠኝ፡፡ ለእናንተም ይህንኑ እንደሚያስተምራችሁ ተስፋዬ ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ፈቃድ መለየት አንዳንድ ጊዜ አንድ ሰው በቀላሉ ሊወስንበት በማይችለው ሁኔታ ውስጥ ሊገባ ይችላል፡፡ ለምሳሌ በአንድ ጊዜ ሁለት ዩኒቨርሲቲዎች ሊቀበሉህ ይችላሉ፡፡ አንደኛው ዩኒቨርሲቲ በምትኖርበት ከተማ ሲሆን ሌላኛው ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ከከተማ ውጪ ሆኖ የበለጠ ዝነኛ ዩኒቨርሲቲ ይሆናል፡፡ ወይም ደግሞ ሥራ እያለህ በሌላ ከተማ ሌላ ሥራ የመቀጠር እድል አገኘህና ሃሳብህን አንዱ ነገር ላይ ማርጋት አልቻልህም፡፡ በእንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ ላይ ነው እንግዲህ ‹‹እግዚአብሔር ለእኔ ያለው የሚፈቅደው ታዲያ የትኛውን ነው?›› የሚል ጥያቄ የምናነሣው፡፡ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅ በእርግጥ አስቸጋሪ ነው፡፡ የአባቶቻችንን መንገድ ከተከተልን ግን አያስቸግርም፡፡ ወደዚህ ጉዳይ ከመግባታችን በፊት ግን እስቲ ራሳችንን እንጠይቅ ‹‹የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅ ለእኔ ምን ይጠቅመኛል?›› ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ ፲፪፥፪/12÷2 ላይ የእግዚአብሔር ፈቃድ በጎ ፣ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም እንደሆነ ነግሮናል፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ ፍጹም ነው ፤ ምንም ነገር አይጎድለውም ፣ መንፈሳዊ ፣ ሥነ ልቡናዊና ስሜታዊ ፍላጎቶችን ሁሉ ለማሟላት የሚችል ነው፡፡ እግዚአብሔር ወደፊት የሚሆነውን ያውቃል ፣ የትኛው ነገር ለዘለቄታው እንደሚጠቅመኝ ያውቃል፡፡ በሌላ በኩል የእኔ ፍላጎት ፍጹም የሆነ ነገርም ሊሆን ይችላል፡፡ ሆኖም እኔ የዘለቄታውን ጥቅም ሳላስብ የቅርቡን ጥቅም ብቻ ልመለከት እችላለሁ፡፡ የዘለቄታውን ከግምት ውስጥ ላስገባ ብፈልግ እንኳን በሚመጣው ሳምንት እንኳን የሚያጋጥመኝን ነገር መተንበይ የማልችል እስከሆንኩኝ ድረስ ይህንን የማደርግበት ዓቅም የለኝም፡፡ ጠቢብ ሰው ምንም ነገር ሲያደርግ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚጠይቀው ለዚህ ነው፡፡ ሆኖም እግዚአብሔርን ፈቃድ እንዴት ላውቅ እችላለሁ? ባሕታዊው ቴዎፋን እንደነገረን ከሆነ እግዚአብሔር በጎ ፣ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነ ፈቃዱን እንዲገልጽልኝ የምፈልግ ከሆነ የራሴን ፈቃድ መተው አለብኝ፡፡ ይህም ማለት በእውነት የእርሱን ፈቃድ እንደምፈልግ ለእግዚአብሔር ማረጋገጥ አለብኝ ማለት ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ፈቃዱን እንዲያስታውቀን እንጸልያለን በውስጣችን ግን የራሳችንን አቋም ከያዝን ቆይተናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እየምንፈልገው ከእኛ ፈቃድ ጋር እስከተስማማ ድረስ ብቻ ነው፡፡ በዚህ መንገድ የምንመራ ከሆነ እግዚአብሔር ፈቃዱን አይገልጥልንም፡፡ ባሕታዊው ቴዎፋን ይህንን ምሳሌ ሰጥቶናል፡፡ የወይን ጭማቂ ያለበት ብርጭቆ ቢኖርህና በዚያው ብርጭቆ ውስጥ ማር ልታደርግበት ብትፈልግ በመጨመሪያ የወይኑን ጭማቂ መድፋት ፣ ብርጭቆውን ማጠብና የወይኑ መዓዛ እስኪጠፋ ድረስ ለጥቂት ሰዓታት በፀሐይ ላይ ማድረቅ አለብህ፡፡ ከዚያ በኋላ ማሩን ታደርግበታለህ፡ ፡ የወይን ጭማቂ የተባለው ግለኛ ፣ የቅርቡን ብቻ ተመልካች ፣ ከእግዚአብሔር ፈቃድ በተለየ ፍጹምነት የሚጎድለው ፣ በጎ ያልሆነና ደስ የማያሰኝ የሆነው የእኛ ፈቃድ ነው፡፡ ማሩ ደግሞ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፡፡ የራሳችንን ፈቃድ ካላስወገድን እግዚአብሔር ፈቃዱን አይገልጥልንም፡፡ ምክንያቱም የራሳችንን ፈቃድ ወስነን እያለ እግዚአብሔርን ፈቃድህን ግለጥልን ማለት በእርግጥ እንደ መዘበት ነው፡፡ እንዴት ላድርገው ይሆን? መልካም ለዚህ መፍትሔው ፈቃድን ገለልተኛ የማድረግ ልምምድ ነው፡፡ ጽንሰ ሐሳቡ ይሔ ነው፡፡ በአንድ ነገር ላይ በአወንታዊም ይሁን በአሉታዊ መንገድ ላዘነብል እችላለሁ፡፡ ለምሳሌ ተጨማሪ ደሞዝ የሚያስገኝልኝ ሥራ ካገኘሁ ለዚያ ሥራ ላደላ እችላለሁ ፤ ይህም የዚያን ሥራ መጥፎ ጎኖች ከመመልከት ሊከለክለኝ ይችላል፡፡ ወይም ደግሞ የማልፈልገውን ነገር እንድቀበል የሚጋብዝ ሁኔታ ደግሞ ሊያጋጥመኛል ሆኖም ነገሩን ስለማልፈልገው ያሉትን በጎ ጎኖች ለመመልከት አልፈልግም፡፡ እነዚህ መውደድና መጥላቶች ብዙውን ጊዜ ከመጀመሪያ እይታ የሚመነጩ ናቸው፡፡ እናም ብዙ ጊዜ የምንወስደው እርምጃ የገንዘቡን ሌላ ጎን በመዘንጋት ነው፡፡ መፍትሔው ግን የዚህ ተቃራኒ ነው፡፡ እስቲ ምሳሌ እንውሰድ፡፡ አንድ በከተማችን የሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ተቀበለኝ እንበል፡፡ ሆኖም ከከተማ ውጪ ያለ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ጥሪ አደረገልኝ፡፡ ‹ነጻ የመሆን› ፍላጎቴ ከከተማ ወጥቶ በመማር የሚመጡብኝን የጎንዮሽ ጉዳቶች እንድዘነጋቸው አደረገኝ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ፍጹም ፣ በጎና ደስ የሚያሰኝ የሆነው የእግዚአብሔር ፈቃድ የቱ እንደሆነ ለማወቅ ትፈልጋላችሁ? በመጀመሪያ ሆን ብዬ በሩቅ ከተማው ዩኒቨርስቲ ጉዞዬ ምክንያት የሚመጡ ጥሩ ያልሆኑ ነገሮችን ነቅሶ በማውጣትና ቢቻል በማጉላት ለአንዱ ጉዳይ ማድላቴን ትቼ ገለልተኛ /ሚዛናዊ/ መሆን አለብኝ፡፡ አንደኛ ከቤተሰቦቼና ከጓደኞቼ ልርቅ ነው፡፡ ልነጋገር የምችለው ከማላውቃቸው ሰዎች ጋር ስለሆነ ብቸኝነት ይሰማኛል፡፡ በዩኒቨርሲቲው አካባቢ ቤተ ክርስቲያን ስለሌለ ለመሳለም ለሰዓታት ያህል መጓዝ ይኖርብኛል፡፡ እንዲረዱኝ ሁልጊዜ የምቀርባቸውን የንስሐ አባቴንም ከእኔ በመራቃቸው ምክንያት ላጣቸው ነው ወዘተርፈ በእርግጥም እነዚህ ሁሉ አሉታዊ ጎኖች እውነት ሆነው ሳለ ከቤተሰብ ቁጥጥርና ከቤት ውጪ በመሆን ስለምታገኘው ‹ነጻነት› ስትል ንቀህ ትተኸዋል፡፡ ቁርጠኛ የሆነ ሰው ግን ይህንን ልምምድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያደርጋል፡፡ በውጤቱም ራስህን ለሁለቱም ምክረ ሐሳቦች ያላደላ ገለልተኛ ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡ እያንዳንዱም ሐሳብ የየራሱ አወንታዊና አሉታ ጎን አለው፡፡ በሺህ የሚቆጠሩ ዶላሮችን የምታገኝበት ነገር ግን ልጆችህን ከትምህርት ቤታቸው ፣ ከጓደኞቻቸውና ከሰንበት ትምህርት ቤታቸው እንድትለያቸው የሚያደርግህና አንተንም ከቤተ ክርስቲያን አገልግሎትህ እና ከንስሐ አባትህ የሚነጥልህ ሥራ ስታገኝም ይህንኑ መተግበር አለብህ፡፡ የመጀመሪያው ሒደት ስለምታገኘው ነገር መልካም ጎን በምትሰጠው ክብደት መጠን መጥፎ ጎኑንም በትኩረት በመለየት ሚዛናዊ መሆን ነው፡፡ ይህን ጊዜና ይህን ጊዜ ብቻ ነው ወደ እግዚአብሔር ቀርበህ በጎ ፍጹምና ደስ የሚያሰኝ ፈቃዱን እንዲገልጽልህ መለመን የምትችለው፡፡ ቀጣዩ ሒደት ወደ ንስሐ አባትህ መሔድና እንዲጸልዩልህ መጠየቅ ነው፡፡ ይህ ሲሆን ፈቃዱን ይገልጥልሃል፡፡ ይህ ራስህን ለንስሐ አባትህ የማስገዛት ተግባር የትሕትና ሲሆን እግዚአብሔር ፈቃዱን ይገልጽልህ ዘንድ ትልቁ ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡
4 58714Loading...
40
እግዚአብሔር ለአንተ የማይስማማህን ነገር ይፈቅድ ይሆን ብለህ ፍርሃት ፍርሃት የሚልህ ከሆነ የቤት ሥራህን በሚገባ አልሠራህም ፣ ለአንዱ ነገር ማድላትህ አሁንም ድረስ አለ፡፡ ወደ ንስሐ አባትህ ሔደህ እንዲጸልዩልህ ነግረሃቸው እግዚአብሔር ከአንዱ አማራጭ ይልቅ ሌላኛውን እንዲመርጥ የምትመኝ ከሆነ አሁንም የቤት ሥራህን በሚገባ አልሠራህም፡፡ በሚከተለው ምሳሌ እንደምነግርህ አንተ ራስህን ገለልተኛ ከማድረግህ በፊት እግዚአብሔር አንተ ትፈልገው የነበረውን አማራጭ መርጦት ሲሆን ደግሞ መልካም ይሆናል፡፡ ወደ ካናዳ ከመምጣቱ በፊት ግብፅ እያለ የማውቀው አንድ ወጣት ወላጆቹና ወንድም እኅቶቹ ሁሉ ካናዳ የሚኖሩ ቢሆንም እርሱ ግን ወደ ካናዳ ለመምጣት ፈቃድ ለማግኘት በካናዳ ኤምባሲ በኩል ያደረገው ተደጋጋሚ ጥረት እንዳልተሳካለት በማማረር ደብዳቤ ጻፈልኝ፡፡ እኔም ወደ ካናዳ እንድትሰደድ የእግዚአብሔር ፈቃድ አይሆን ይሆናል አልሁት፡፡ ከዚያም የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዴት ለማወቅ መፈለግ እንዳለበትና ራሱን ሚዛናዊ ለማድረግ ምን ማድረግ እንዳለበት አስከትዬ ነገርሁት፡፡ እሱም ምክሬን ተቀብሎ ወደ ካናዳ ባለመሔዱ ውስጥ ስለሚያገኛቸው መልካም ነገሮችም ማሰብ ጀመረ፡፡ ለሚስቱም ‹‹በግብፅ ከቆየን ወላጆቼና ቤተሰቦቼ ግብፅን ለመጎብኘት ቢፈልጉ እንኳን የእኛ ቤት ማረፊያቸው ይሆናል፡፡ እንዲሁም እዚህ ሁለታችንም ጥሩ ሥራ እስካለን ድረስ ወደ ካናዳ ሔደን ሀ ብለን መጀመር አይኖርብንም፡፡ ማመልከቻዎችም የምንጽፈው ካናዳ አልሔዱም ለመባል ብቻ ነው፡፡ በማንኛውም ጊዜ ወደ ካናዳ መሔድና ከቤተሰቦቻችን ጋር ማሳለፍ በሁለቱም ዓለማት ፈለግነውን ማድረግ እንችላለን፡፡›› ብሎም ለሚስቱ ነገራት፡፡ ሁለቱም ይህንን ይህንን አቋም በግብፅ መኖር መጥፎ እንዳልሆነ እስኪያምኑ ድረስ ተከተሉት፡፡ (በተለይም ነገሩ የእግዚአብሔር ፈቃድ እስከሆነ ድረስ) በቀጣዩ ደብዳቤ እንዲህ ብሎ ጻፈልኝ ‹‹ከሀገር ብንወጣም ግብፅ ውስጥ ብንቆይም ምንም ለውጥ አያመጣም ብለን ማሰብ ስንጀምርና ለአንዱ ነገር ብቻ ከነበረን ዝንባሌ ነጻ በሆንበት እለት ከካናዳ ኤምባሲ ተደውሎ እንደተቀበሉንና ቪዛችንን ለመቀበል የህክምና ምርመራ እንድናደርግ ተነገረን፡፡›› ይህንን መንፈሳዊ ልምምድ የማድረግ ውበቱ ሁልጊዜ እንዲህ ዓይነት ነገር ሲገጥምህ ወደ ተመሳሳይ ሒደት ትመጣለህ፡፡ ማድረግ ስለሚገባህ ነገር ከመጠን በላይ አለማሰብ ቀላል ይሆንልሃል፡፡ የራስህን ፍላጎት ቀብረህና ሚዛናዊ ሆነህ በመገኘትም ፍጹም በጎና ደስ የሚያሰኘው የእግዚአብሔር ፈቃድ ሊገለጥልህ ይችላል፡፡ አንዳንድ የማሳሰቢያ ቃላትን ልነግርህ እፈልጋለሁ! ለማታለል እንዳትሞክር! አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ እንፈልጋለን ሆኖም እግዚአብሔር ፈቃዱን ሲገልጥልን በፈቃዱ አንደሰትም፡፡ አንዳንድ ሰዎች የንስሐ አባትን መቀየር የእግዚአብሔርን ፈቃድ ይቀይረው ይሆናል በሚል ተስፋ ሌላ ንስሐ አባት ይቀይራሉ፡፡ ሌላው ችግር የእግዚአብሔር ፈቃድ ፍጹም ዘንግተን እግዚአብሔር የምንፈልገውን ብቻ እንዲሰጠን በመጠየቅ የራሳችንን ፈቃድ ብቻ እንከተላለን፡፡ ይህ በተለይ በጋብቻ ጉዳይ ላይ እጅግ አደገኛ ነገር ነው፡፡ የተቀደሰ ትውስታ የነበራቸው የቀድሞው አቡነ ጴኤሜን ከሚስቱ ጋር ስላለበት የጋብቻ ችግር ለማማከር ሁልጊዜ ወደ እርሳቸው ስለሚመጣ አንድ ወጣት ታሪክ ነግረውኝ ነበር፡፡ ጳጳሱ አንድ ቀን በመታከት ‹‹ይህችን ሴት ከማግባትህ በፊት ጸልየህ ነበር?›› ብለው ጠየቁት፡፡ እሱም ‹‹አዎን ለስድስት ወራት በየቀኑ እጸልይ ነበር!›› አላቸው፡፡ ጳጳሱም ‹‹ምን እያልህ ነበር የምትጸልየው?›› ብለው ጠየቁት፡፡ ወጣቱም ‹‹እግዚአብሔር ሆይ እባክህ ይህችን ሴት እንዳገባት ፍቀድልኝ!›› እያልሁ እጸልይ ነበር አላቸው፡፡ እኔ እጅግ የተሻለ መንገድ የምለው የእግዚአብሔርን ፈቃድ መቀበል ለብዙ ወጣቶች እጅግ አስቸጋሪ ነገር ነው፡፡ አንዲት ወጣት ‹‹ከጋብቻ በስተቀር በሁሉም ነገር የእግዚአብሔርን ፈቃድ እቀበላለሁ!›› አለችኝ፡፡ ለምን እንደሆነም ጠየቅኋት፡፡ መለሰች ‹‹ምክንያቱም እግዚአብሔር የሚፈቅደው አብሮ ለመኖር የሚከብደኝን በሰንበት ትምህርት ቤቶች የሚያስተምር ዲያቆን እንዳገባ ነው!›› አለችኝ፡፡ እኔም ‹‹እግዚአብሔር አብረሽው በመኖርሽ ሊያስደስትሽ የሚችል በሰንበት ትምህርት ቤት የሚያስተምር ዲያቆንንስ ሊመርጥልሽ አይችልም?›› አልኳት፡፡ ‹የእግዚአብሔር ፈቃድ በጋብቻዬ ላይ› በሚል ርእስ በምናደርገው ውይይት ላይ ታዳሚ የነበረ ሌላ ወጣት ደግሞ ባቀረብኩት ነገር ላይ በቁጣ ተቃውሞ ተነሣ፡፡ ‹‹ጋብቻን በተመለከተ የእጣ ፈንታዬ ጌታ እኔ ራሴ መሆን አለብኝ!›› እኔም መለስሁለት ‹‹እጮኛህ በመምረጥ ሒደት ላይ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ንቀህ ከተውህ የጥፋትህም ጌታ አንተው ትሆናለህ!›› ይህንን ምሳሌ ለወጣቶቻችን ሁሉ ለመስጠት እፈልጋለሁ! ሕይወታችሁ ሁለት ሰዎች እንደሚሠሩባት ጀልባ ናት የአንደኛው ሥራ መቅዘፍ ሲሆን የጀልባዋን አቅጣጫ መቆጣጠሪያ (መልሕቅ?) የሚይዝ ነው። ጠቢብ ሰው ‹‹ጌታ ሆይ አንተ አቅጣጫ መቆጣጠሪያውን ያዝ እኔ ደግሞ መቅዘፊያውን ልያዝ!›› ይላል፡፡ እንደ አለመታደል ሆኖ ብዙ ጊዜ እኛ አቅጣጫ ጠቋሚውን ለመያዝ የምንታገል ሲሆን እግዚአብሔር ግን ቀዛፊ እንዲሆን እንፈልጋለን! የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንደ ራስ ምርጫ አድርጎ የመቀበል ጥቅሙ ሕይወት ወዴትም አቅጣጫ ቢያመጣህ እግዚአብሔር እንደፈቀደው ስለምታውቅና እግዚአብሔር የፈቀደልኝ ነው ስለምትል አትፈራም፡፡ በአጭር ቃል ‹‹አልወደውም!›› የሚባል ዓይነት ነገር ቢሆንም እንኳን በእርግጥ በጎ ፣ ፍጹምና ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡ ~ ተ ፈ ጸ መ ~ . . ‹‹ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን!›› ፪ቆሮ. ፪÷፲፬ /2ኛ ቆሮ. 2÷14 "ተግባራዊ ክርስትና" በዚህ ተጠናቋል። ከመጽሐፉ ብዙ ራስን የመግዣ ጥበቦች እንዳገኛችሁበትና እንደተጠቀማችሁበት/እንደምትጠቀሙበት ተስፋ እናደርጋለን። ይህን ድንቅ መጽሐፍ ለጻፉልን ለአቡነ አትናስዮስ እስክንድር እንዲሁም ወደ አማርኛ ለተረጎመልን ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ እግዚአብሔር አምላክ ቃለ ሕይወትን ያሰማልን! በቀጣይ "ሕይወተ ወራዙት" የተሰኘውን የዲ/ን ኅብረት የሺጥላ(አሁን ቀሲስ) ድንቅ መጽሐፍ ወደ እናንተ ማድረስ እንጀምራለን። አስተያየታችሁን በ @Ethiopian_Orthodox_bot በኩል አድርሱን። @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
5 74212Loading...
በገድለ አቡነ ሀብተ ማርያም ላይ ተጽፎ የሚገኝ አንድ መንፈሳዊ ታሪክ አለ፡፡ ከዕለታት በአንድ ቀን የእመቤታችን የድንግል ማርያም በዓል በሚከበርበት ዕለት ቅዳሴ ለመቀደስ የተዘጋጁ አንድ ካህን ነበሩ፡፡ እኚኽ አባት ማታ ተኝተው ሳለ አንድ ጋኔን በሴት አምሳል አብሯቸው በማደር ሕልመ ሌሊት እንዲያገኛቸው አደረገ፡፡ ከመኝታ ሲነቁም ቅዳሴ መግባት የማያስችል እንቅፋት እንደገጠማቸው ስላወቁ በእርሳቸው ቦታ ጻድቁ አቡነ ሀብተ ማርያም ተተክተው ቅዳሴውን አከናውነዋል፡፡ የገድላቸው መጽሐፍም የእመቤታችን ፈቃድ ቅዳሴውን አቡነ ሀብተ ማርያም እንዲቀድሱት ነበረ በማለት በግልጽ ይተርካል፡፡ ይህ ሁኔታ የተፈጸመው ስለ አቡነ ሀብተ ማርያምም ክብር ሲባል ነው። አቡነ ሀብተማርያም በእመቤታችን በድንግል ማርያም ዘንድ ምን ያህል ተወዳጅ እንደሆኑ ያሳያል:: ከዚህ አልፎ ግን “ያኚኽ ካህን ምን በደል ቢገኝባቸው ነው» ማለት አይቻልም፡፡ እንዲህ ማለት በሰው መፍረድ ነውና፡፡ መጽሐፈ ገድሉም ካህኑ እንደዚህ ያለ በደል ነበረባቸው ብሎ የሚጠቅሰው ምንም ነገር የለም፡፡ ያልተጻፈውንና የማናውቀውን መናገር በእግዚአብሔር ሥራ ገብቶ እንደ መተቸት ይቆጠራል፡፡ ይህ ታሪክ በሕልመ ሌሊት በሚፈተኑ ሰዎች ላይ እንዳንፈርድ ይልቁኑም በሌላ አቅጣጫ ማየት የሚገባን ነገር እንዳለ ያስረዳል፡፡ በቀጣይ «ዝንየት»ና መንፈሳዊ ሥርዓቱ ይቀጥላል.... @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
24👍 14🥰 3
በዐፍላ ጉርምስና ወቅት ፈጣን ዕድገት ከሚያሳዩና ከሚለጠጡ የሰውነት ክፍሎች መካከል የድምፅ ጅማቶች ስለሚገኙበት አንዳንድ ጊዜ ሳይታሰብ «ቀጭን» ድምፅ ማውጣትና የድምፅ መጎርነን እንደ ጉርምስና ምልክት ይታያሉ፡፡ የአዳም ፍሬ በመባል የሚታወቀው ‹‹ማንቁርትም» ማደግና መታየት የሚጀምረውም በዚሁ ጊዜ ነው፡፡ ከዚህም ሌላ ብዙ ወንዶች ብጉር የሚያበጉሩ ሲሆን፣ በብብት፣ በደረትና በብሽሽት (በአባለ ዘርዕ) አካባቢ ፀጉር ማብቀል ይጀምራሉ፡፡ እንደዚሁም ከራስ እስከ ጽሕም በግራና በቀኝ የሚወርድ ለጊዜው ለስለስ ያለና ስስ ጠጉር ወይም ሪዝ ማቆጥቆጥ ይጀምራል፡፡ ይህንን ጽሕም (ሪዝ) መከርከምና መቀነስ እንጂ ሴት እስኪመስሉ ድረስ ሙሉ በሙሉ ልጭት አድርጐ ማንሣት የሚገባ አይደለም፡፡ ይህን በተመለከተ ፍትሐ ነገሥት መንፈሳዊና ዲድስቅልያ የተሰኙ መጻሕፍት እንዲህ ብለዋል፡፡ «ወባሕቱ ኢመፍትው ለነ ንላጺ ጽሕመነ ወኢንወልጥ ፍጥረተ ብእሲ ውስተ ካልዕ ግዕዝ - ነገር ግን ጽሕማችንን ልንላጭ የወንድነት መልካችንን ወደ ሌላ ማለትም ሴት ወደ መምሰል እንለውጥ ዘንድ አይገባንም::›› ማለት ነው:: ዲድ.አን.1፤ ፍት.መን.አን .11 የጉልምስና ምልክት የሆነው የዚህ ጠጉር ብዛት ከሰው ሰው ይለያያል:: ሆኖም ምን ያህል <<ወንድ>> መሆንን አመልካች አይደለም:: ሌለቹ የዐፍላ ጉርምስና ምልክቶች ደግሞ የሰውነት ጠረን መለወጥ፣ የዘር ፍሰት ወይም ሕልመ ሌሊት ማየት መጀመር ናቸው፡፡ «ሕልመ ሌሊት» ምንድር ነው? በዐፍላ የጉልምስና ወቅት አባለ ዘርዕ ወደ ሙሉ የዕድገት ደረጃ መድረስ ብቻ ሳይሆን መሥራትም ይጀምራል:: በዚህ ጊዜ ከንዑስ መሌሊት (ኀፍረተ አካል) ዘርዓ ብእሲ የሚባል የአፍንጫ ዛሕል (ንፍጥ) የሚመስል ፈሳሽ ነገር ይወጣል፡፡ ወንድና ሴት ግንኙነት በሚያደርጉበት ጊዜ ወደ ሴቲቱ ማኅፀን በመግባት ፅንስ እንዲፈጠር የሚያደርገው ይህ ፈሳሽ ንጥረ ነገር ነው፡፡ የወንድ ወጣቶች ሰውነት ይነስም ይብዛ በየጊዜው ከላይ ‹‹ዘርዓ ብእሲ›› ወይም «የወንድ ዘር» ተብሎ የተጠቀሰውን ፈሳሽ ንጥረ ነገር ያስወጣል፡፡ ለዘር የበቁ ወጣቶች ዘር የሚከፍሉት ወይም የሚወጣቸው በልዩ ልዩ መንገድ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ግን ተኝተው ሳለ በጠለቀ እንቅልፍ ሆነው ሕልም በሚያልሙበት ወቅት ነው፡፡ ይህ ሲሆን እንደ ጤናማ የተፈጥሮ ሂደት ይቆጠራል። የዚህ ዓይነቱን ሕልም መጽሐፈ መነኮሳት በአንድ ስፍራ «ሕልመ ጽምረት» በሌላ ቦታ ደግሞ «መስቆርርት ሕልም» ሲለው ይገኛል:: ሕልሙን ያየው ሰው ደግሞ «ዝንየት መታኝ» ወይም «ሕልመ ሌሊት» አገኘኝ ይላል፡፡ ይህ በቤተ ክርስቲያን ልጆች ዘንድ የተለመደና በቀላሉ የሚያግባባ የቃል አጠቃቀም ነው:: ወደ አቅመ አዳም እየደረሱ ባሉ ልጆች ላይ ይህ «የዘር ፍሰት» ባልጠበቁት ጊዜ ሲከስት በጣም ሊረብሻቸው ይችላል፡፡ ይልቁኑም ልጆቹ ከዚህ አስቀድሞ ስለ ጉዳዩ በተለያየ መንገድ በቂ ግንዛቤ ያላገኙ ከሆኑ መረበሻቸው በእጅጉ ይጨምራል፡፡ እነዚህ ታዳጊዎች እንዳይረበሹና ስለ ጉዳዮ የተሳሳተ ሐሳብ ይዘው እንዳያድጉ ለነገሩ በቂ ግንዛቤ እንዲያገኙ ከማድረግ ጋራ እንደ አስደሳች ተግባር በመውሰድ እያወቁ ዘራቸውን በራሳቸው እጅ ማፍሰስ እንዳይጀምሩ የነአውናንን በዚህ ተግባራቸው መቀሠፍ እየጠቀሱ ኃጢአትነቱን ኣጥብቆ ማስረዳት ያስፈልጋል:: መጽሐፍ ቅዱስ ስለ <<ዘር መውጣት>> እና በአጠቃላይ <<ፈሳሽ ነገር>> ስላለበት ሰው በዝርዝር ይናገራል፡፡ ዘሌ.15፥16፡ 15፥1-33  ይህንን ጨምሮ የወንድ ዘርን የሚመለከት ሐሳብ የያዙ መንፈሳዊ መጻሕፍቶችን ማንበብ ለወጣቶች የተሻለ ግንዛቤ ይሰጣቸዋል፡፡ ይህን በመሳሰሉ ፆታዊ ጉዳዮች ላይ ወጣቶች ጥያቄ ሲኖራቸው ከማን ጋር መወያየት የተሻለ እንደሚሆን ሊለዩ ይገባል፡፡ ልጆች የሚጓዙበት ተፈጥሮአዊ የሕይወት ጐዳና በሙሉ ጤናማ ወላጆች የተጓዙበት ስለሆነና ሌሎችም ብዙ ተሞክሮዎች ስላሏቸው ለልጆች ፆታዊ ችግር ጉዳት የሌለበት የመፍትሔ ሐሳብ ማቅረብ ይችላሉ፡፡ ካህናትና መምህራነ ቤተ ክርስቲያንንም ማማከር ለወጣቶች መንፈሳዊውን ሥርዓት እንዲያውቁ ይረዳቸዋል፡፡ እኩዮችንና ሌሎች ወጣቶችን ወይም የእግዚአብሔርን ቅዱስ ቃል መሠረት ያላደረጉ ጽሑፎችን መስማትና ማንበብ ጥቂት እውነትና ብዙ የፈጠራ ወሬ ያለበትን የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ወጣቶችን ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ ሊመሯቸው ይችላሉና ሊጠነቀቁባቸው ይገባል፡፡ «ሕልመ ሌሊት» ኃጢአት ነውን? በጠለቀ እንቅልፍ ላይ ሳሉ የሚከሠት ሕልመ ሌሊትን እንደ ኀጢአት እንዲቆጠርና እንዳይቆጠር የሚያደርጉ የተለያዩጨሁኔታዎች አሉ:: ስለዚህ ሕልመ ሌሊትን በጥቅሉ ኀጢአት ነው ወይም አይደለም ማለት አይቻልም፡፡ ነገር ግን እንደ ኀጢአት እንዲቆጠር የሚያደርጉ ሁኔታዎችን በመጠኑ መዘርዘር ይቻላል፡፡ ሀ. አጋንንት የሰው ልጆችን በልዩ ልዩ መንገድ ክፉኛ ይዋጓቸዋል፡፡ የሰው ልጆች ሲያንቀላፉ አጋንንት ግን ለቅጽበት እንኳን እያሸልቡም፡፡ ያንቀላፋውን ሰው እስኪነቃ ድረስ እንኳን አይጠብቁትም: አጋንንት የሰውን ልጅ በተኛበት ክፉ ክፉ ሕልም በማሳየት ይፈትኑታል፡፡ አንድ ጊዜ የተራቆተ የሴት ገላ፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ እንደ ወንድና ሴት አለሌና ባዝራ እየሆኑ ሲጨዋወቱና ሲደራረጉ በምትሐት ያሳዩታል፡፡ በዚህ ጊዜ እርሱም በዝሙት ሐሳብ ይሳብና በሕልሙ ዝሙት ሲፈጽም ያድራል፡፡ በዚህ መልኩ የተከሠተ ሕልመ ሌሊት «ጸዋግ» ወይም «ኅሡም» ሕልም ይባላል፡፡ ክፉ ወይም ጥፉ ሕልም ማለት ነው:: በዚህ መልኩ አጋንንት ሰውን እንደሚዋጉት በመጽሐፈ መነኮሳት እንዲህ ተጽፏል፡፡ «ይትቃተልዎ ሰይጣናት በመዓልት በሕሊናት እኩያት ወበሌሊት በአሕላማት ኅሡማት» በአማርኛ «ሰይጣናት የሰውን ልጅ ቀን ቀን ክፉ ሐሳብ በማሳሰብና በማሠራት በሌሊት ደግሞ ዝሙት የሞላበት አስጸያፊ ሕልም በማሳየት ይዋጉታል» ማለት ነው፡፡ በዚህ መልኩ ሰይጣናት ያቀረቡለትን ረቂቅ ፈተና ከመቃወም ይልቅ ደስ እያለው የሚያጣጥም ማለትም ከመጸጸትና ከመቆጨት ይልቅ በደስታ ስለ ዝሙት የሚያሰላስል፣ የሚዳራ፣ የሚዛለል፣ ወደ ዝሙት ከሚያመሩ ማናቸውም ነገሮች የማይሸሽ ሰው እነዚህ ነቅቶ ሳለ ያልተቃወማቸውን ተግባራት በሕልሙ በሚፈጽማቸው ጊዜ በተግባር እንደፈጸማቸው ያህል ኃጢአት ሆነው ይቆጠሩበታል:: ይህን የሚያስረዳ እንዲህ የሚል የመጻሕፍት ቃል ይገኛል:: «ዘይትቄበል በመዓልት ስሕተታተ ፍትወት ውስተ ልቡ ወኢይከሥታ ወለዝንቱ ሕሊናቲሁ ወአሕላማቲሁ ወፍትወታቲሁ ርኩሰት ትትሐሰብ ሎቱ ኃጢአተ» ይህም ‹‹በቀን ነቅቶ ሳለ ኃጢአትን ወዶ የሚቀበልና ገልጾ የማይናዘባት ለዚያ ሰው የረከሰች ሐሳቡ፣ ሕልሙ ኃጢአት ሆና ትቆጠርበታለች፡፡» ማለት ነው፡፡ በተጨማሪም <<ወኢይጻሙ ውስተ ንስሐ ወኢየኀሥሥ እም እግዚአብሔር ሥርየተ አበሳቲሁ በቀዳሚ ወለዝንቱ አሕላማቲሁ መስቆርርት ትትሐሰብ ሎቱ ኃጢአተ::›› ወደ አማርኛ ሲመለስ <<በንሥሐ ሥራ የማይደክም (ንስሐ የማይገባ)፣ በቀደመው ኃጢአቱ እግዚአብሐርን ይቅር በለኝ የማይለው ለዚያ ሰው የሚያጸይፉ ሕልሞቹ ዕዳ በደል ሆነው ይቆጠሩበታል::» ማለት ሲሆን ይህ የሆነበት ምክንያት ሰውዬው የነዚህ ሥራዎች ተቃዋሚ ባለመሆኑ ነው፡፡ ይህም ንስሐ ባለመግባቱ ይታወቃል:: እነዚህን ኃጢአቶች የማይቃወም ሰው ደጋፊ ስለሆነ በነዚህ ኃጢአቶች ለምን እጠየቃው ለማለት አይችልም፡፡
Show all...
የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot

👍 8 8
ከሥራ ብዛት ሕልም እንደሚታይ ጠቢቡ ሰሎሞን «ሕልም በሥራ ብዛት ይታያል» በማለት የተናገረው ቃል ያስረዳል፡፡ መክ5፥3 እንደዚሁም ሁሉ ከምኞት ብዛትም ሕልም ሊከሠት ይችላል:: ክፉ ምኞት በሕልምም ቢሆን ማርከሱ አይቀርም፡፡ ሐዋርያው ይሁዳ «እያለሙ ሥጋቸውን ያረክሳሉ» በማለት የጻፈው መልእክት እዚህ ቦታ ላይ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ ይሁዳ 1፥ (ቁ8) እንደሚታወቀው ነፍስ እንደ ሥጋ አትተኛም እንቅልፍም በእርሷ ዘንድ የለም:: ስለዚህ ነፍስ በእንቅልፍ ልቤ ነው በማለት ማመካኘት አትችልም፡፡ ነፍስ በረከሠ ሕልም ምክንያት ከተጠያቂነት ነፃ መሆን የምትችለው ሥጋ ከእንቅልፍ ውጭ በሚሆንበት ጊዜ ተግባረ ዝሙትን በመቃወምና በመጥላት ከእግዚአብሔር ጋር መሆኗን ስታስመሰክር ብቻ ነው፡፡ ሌላው ሕልመ ሌሊትን እንደ ኃጢአት የሚያስቆጥረው ሁኔታ አብዝቶ መመገብ ነው:: ጾም ለጽድቅ ሥራ ሁሉ መሠረት እንደሆነ እንደዚሁ አብዝቶ መመገብም የኃጢአት ሁሉ መሠረት ነው:: <<እኅልም ጉልበትን ያጠነክራል>> ተብሏልና፡፡ ሰው ሁሉ ለቁመተ ሥጋ ያህል መመገብ ያሻዋል፡፡ መዝ103፥15 ሆኖም ለልዩ ልዩ የምግብ ዓይነቶች መጐምጀትና ከዚያም አልፎ አብዝቶ መመገብ ነፍስን ለሥጋ ማስገዛት ነው:: ይህ ደግሞ ገዥዋን ተገዥ ማድረግ በመሆኑ ግፍ ነው፡፡ ሊቀ ጳጳስ ለዐቃቢት እንደመገዛት ያህል ነውና፡፡    ለሥጋ መገዛት የሚያሻውንም ሁሉ ጥሮ ግሮ ማቅረብ የገዛ ሰውነትን ማምለክ ነው፡፡ ሐዋርያው «ሆዳቸው አምላካቸው ነው፡፡» በማለት የተናገረው «እንብላ እንጠጣ ነገ እንሞታለን» በማለት ከሞት በኋላ ተከትሎ የሚመጣባቸውን ወቀሳና ፍርድ ችላ ላሉ ሰዎች ነው፡፡ በአዳምና በሔዋን ሊነገር የማይችል ውርደትና ጉስቁልና ያመጣባቸው ለሆዳቸው መገዛታቸው ወይም ለመብል መሳሳታቸው መሆኑ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ ፊልጽ3፥19፣ 1ቆሮ 15፥32፡ ዘፍ3፥ 1-24 ወጣቶች ይልቁኑም በዝሙት ሥራና ሐሳብ በእጅጉ የሚፈተኑ ስዎች በሚገባ መጾም አለባቸው:: በሰውነት ላይ የዝሙት ፆር ጸንቶ ሳለ አብዝቶ መመገብ የሚቃጠል ክርን ሰም እንደ መመገብ (መቀባት) ነው:: ሰም ክሩን የበለጠ እንደሚያቀጣጥለው አብዝቶ መመገብም የዝሙት ፍላጐትን የበለጠ እንዲበረታ ያደርገዋል፡፡ መጽሐፈ መነኮሳትም ይህን ሲገልጽ <<መብዝኀ መባልዕትኒ ምስለ ኃይለ ውርዝውና ያስተዳልው ምጽአተ ሕማማት በኃይል፣ አብዝቶ መመገብ ከወጣትነት ጋር የኃጢአት ሐሳብን በግድ እንዲመጣ ያደርጋሉ» ይላል፡፡ (ማር ይስ አን.20 ምዕ.1) አብዝቶ መመገብና ለመብል መሳሳት የኃጢአት ምንጭ ከመሆናቸው ባሻገር በራሳቸው ኃጢአት ሆነው ይቆጠራሉ፡፡ የሰዶም ኃጢአት አብዝቶ መመገብና ጠግቦ መብላት እንደ ነበር መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር፦ «እነሆ የእኅትሽ የሰዶም ኃጢአት ይህ ነበረ፡ ትዕቢት፣ እንጀራን መጥገብ፣ መዝለልና ሥራ መፍታት በእርስዋና በሴቶች ልጆቿ ነበረ>> ይላል:: «እንጀራን መጥገብ›› ኃጢአት መባሉን ተመለከትክን? ሕዝ16:49 ስለዚህ በልክ ተመገብ እንጂ ለስስት አትሽነፍ፡፡     ሳይጠነቀቅ ቀርቶ አብዝቶ ከመመገቡ የተነሣ ሕልመ ሌሊት ያገኘው ሰው እንደ ኃጢአት ይታሰብበታል፡፡ ምክንያቱም አብዝቶ መመገብ ኃጢአትን እንደሚወልድ እያወቀ ችላ ብለሎ በመመገቡ ነው፡፡ መጽሐፈ መነኮሳት አብዝቶ ከመመገብ የተነሣ ሕልመ ሌሊት ስለሚከሠትበት ሰው እንዲህ በማለት ይተርካል፡፡ «ወመንጸፈ ኅርትምናሁስ ወልብሱ ወትፍግዕተ ሥጋሁ ኩለንታሁ ርሱሕ፡፡ በእንተ ብዝኀ ውኂዝ ርኵስ ዘይውኅዝ እም ሥጋሁ ከመ ዐይነ ማይ አኮ በሌሊት ባሕቲቱ ዘይመጽእ ዝንቱ እስመ ሥጋ ያውኀዝ ወትረ ወያረኩሶ ለሕሊና›› ወደ አማርኛ ሲመለስ «ከሰውነቱ እንደ ምንጭ የሚነቃ ርኩስ ዘር በዝቶ ስለ ፈሰሰ ጎስቋላ ምንጣፉ፣ልብሱ፣በዝሙት ደስ የተሰኘ ሥጋው ሁለንተናው የረክሰ ነው:: ሥጋ ሁልጊዜ ያነቃዋልና ዘሩ የሚፈሰው በሌሊት ብቻ አይደለም፡፡ ሕሊናውንም ያረክሰዋል›› ማለት ነው፡፡ ይህም ለምግብ ከመሳሳትና አብዝቶ ከመመገብ የተነሣ የሚመጣ ሕልመ ሌሊት እንዴት ሰውን እንደሚያረክስና ኃጢአት ሆኖ እንደሚቆጠርበት ያስረዳል:: ማር.ይስ. አን.20 ምዕ.2 አንድ ሰው በንቁ ልቡና ሳለ ወደ ኃጢአት የሚየመሩትን ነገሮች ተግቶ እየተቃወመ ነገር ግን በተኛና ባንቀላፋ ጊዜ ዝንየት ቢያገኘው በተራክቦ፣ ዘር በማፍሰስ ያያት ሕልሙ ዕዳ ሆና አትቆጠርበትም፡፡ መሐሪ የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውዬው ተቃወማት እንጂ ወዶ ወደ እርሷ እንዳልተሳበ ያውቃልና፡፡ አንቀላፍቶ ላለ ዘሩ ቢወርድ ፈልጎ አለመጣውምና ዕዳ አይሆንበትም፡፡ ነገር ግን ተቃውሞ ለማራቅ አልተቻለውም:: ይህ ከዚህ በላይ የሰፈረው ሐሳብ በግዕዙ እንዲህ ይነበባል። <<ወዘሰ ይትጋደል ሕሊናተ እንተ የሀውክዋ ሰይጣናት ውስተ ልቡ በመዓልት ወዝኒ አሕላማቲሁ መስቆርርት ዘበሐሊመ ስዕበት ኢትትሐሰብ ሎቱ ኃጢያተ፡፡ እስመ እግዚአብሔር ጻድቅ ወመሐሪ የአምር እስመ ውእቱ በጊዜ ፈቂዶቱ ኢተሰፍጠ በፍትወት አላ ተቃተላ ወሰደዳ፡፡ ወለእመኒ ወረደት ላዕሌሁ በጊዜ ንዋሙ ኢየሐስባ ላዕሌሁ ኃጢያተ እስመ ውእቱ ኢተቀበላ በፈቃዱ ወኢኮነ ክሀሌ ለተጋድለሎታ ወሰዲዶታ ወአርኅቆታ::>> ኃጢአትን ከልቡ በሚቃወምና በሚጠላ ሰው ላይ ሕልመ ሌሊት እንደ ኃጢአት እትቆጠርበትም፡፡ ይህን ለማስረዳት አረጋዊ በፊልክስዮስ መጽሐፍ እንዲህ የሚል ሐተታ አስፍሯል፡፡ ሰይጣን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን:- የኔን ወገኖች አጋንንትን ባንተ ወገኖች ላይ አሰለጥናቸዋለው፣ ነገር ግን ወገኖቼ የአንተን ወገኖች አይችሏቸውምና ድል ይሆናሉ:: እነርሱ ምንም ባይችሏቸው እኔ ግን «በሕልመ ሌሊት አስሕቶሙ» «በሕልመ ሌሊት አስታቸዋለሁ።» አለው:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ለሰይጣን እንዲህ ሲል መለሰለት <<ለእመስ ድቀት ይወርስ አባሁ ዛቲኒ ትትሐሰብ ኀጢአተ ላዕለ እሊአየ።» ትርጓሜውም <<ጭንጋፍ አባቱን ለመውረስ ከቻለ ሕልመ ሌሊትም በወገኖቼ ላይ ዕዳ ሆና ትቆጠርባቸዋለች» ይህም ማለት ተስዕለተ መልክዕ ያልተፈጸመለት ጭንጋፍ አባቱን መስሎና አህሎ ባለመገኘቱ የአባቱ የሆነውን ነገር መውረስ እንደማይቻለው እንደዚሁም በተግባር ያልተፈጸመች ሕልመ ሌሊትም እንደ ተግባር ኃጢአት ተቆጥራ አታስኮንንም ማለት ነው፡፡ : አረጋዊ እንዲህ ማለቱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስና ሰይጣን ከሕልመ ሌሊት አንጻር ያላቸውን ፈቃድ ለማስረዳት ፈልጐ ነው እንጂ ሰይጣን ደፍሮ ኢየሱስ ክርስቶስን ተናግሮት ኢየሱስ ክርስቶስም እንዲህ ተዋርዶ ለዲያብሎስ መልስ ሰጥቶት አይደለም:: ይህ ቃለ ምልልስ በመጽሐፈ ኢዮብ ምዕራፍ አንድ ላይ እና በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ አራት ላይ ከሰፈረው የሰይጣንና የእግዚአብሔር ንግግር ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡ በሕልመ ሌሊት በተደጋጋሚ የሚፈተን ሰው በቅርብ እናውቅ ይሆናል:: እንዲህ ባሉ ሰዎች ላይ መፍረድ ተገቢ አይደለም፡፡ ለምን ቢባል ጥፋት ሳይገኝባቸው በዚህ መልኩ የሚፈተኑ ብዙ ሰዎች ስለሚገኙ ነው:: እኛም ብንሆን በዚህ ፈተና እንዳንወድቅ መጠንቀቅና መጸለይ ይገባናል፡፡ በሰው መፍረድ ራስን ወደ ወጥመድ ማስገባት ነውና፤ በሰው ከመፍረድ ለሚፈተን ለዚያ ሰው መጸለይ በእጅጉ ይበልጣል፡፡ ሰው ራሱ በራሱ ላይ ይህን የመሰለ ፈተና ማምጣቱን እየመረመረ ኃጢያተኛ ነኝ ቢል ተገቢ ነገር ነው:: ሌሎች ግን በእርሱ ላይ ቢፈርዱበት ኃጢአት ሠሩ ማለት ነው:: ፈጣሪ በሌላው እንድንፈርድ አይፈልግምና፡፡
Show all...
የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot

8👍 6
.                      ምዕራፍ ሦስት              የዐፍላ ጉልምስና ምልክቶች     ዐፍላ የጉርምስና ወቅት የጉልምስናን የመጀመሪያ ወቅት ይሸፍናል፡፡ ጉልምስናና ጉርምስና የሚሉት ቃላት አንድ ናቸው። የዘይቤ እንጂ የምስጢር ልዩነት የላቸውም፡፡ ይህ ወቅት በፆታ የመብሰል ምልክቶች የሚታዩበት ዕድሜ ነው፡፡ ከላይ እንደተጠቀሰው ጉልምስና የሚጀምርበት ዕድሜ እንደየሰዉ ሁኔታ ከፍና ዝቅ ሊል ስለሚችል የኔ ፈጥኗል የኔ ደግሞ ዘግይቷል በማለት ሊጨነቁበት የሚገባ አይደለም፡፡ የሆነው ሆኖ አንድ ሰው በጉልምስና ወቅት ሊከሠቱ ከሚችሉ የአካል ለውጦች ጋር ተያይዘው የሚከሠቱ ሌሎች ለውጦችንበሚገባ ሊያውቃቸውና ሊጠብቃቸው ይገባዋል:: እነዚህም ለውጦች በአጭሩ ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፡፡   በጉልምስና ወቅት ከሚከሠቱ የአጥንቶች ዕድገትና የጡንቻዎች መለጠጥ የተነሣ በወጣቶች ላይ የመፍዘዝና የቅንብር ጉድለቶች ይስተዋላሉ:: በዚህ ምክንያት ለአደጋ መጋለጥ እንዳይኖር ተጨማሪ ጥንቃቄ ቢያስፈልግም ይህ ዓይነቱ የመቅዘዝና ቅስስ የማለት ሁኔታ ጊዜውን ጠብቆ ያልፋልና የሚያሳስብ ጉዳይ አይደለም:: ወጣቶች በብዙኀኑ ዘንድ የሚታወቁበት ገጽታ ንቁነትና ቀልጣፋነት ቢሆንም በአፍላ የጉልምስና ወቅጥ መፍዘዝና ቅስስ የማለት ሁኔታ መከሠቱን ማወቅ ለሚያሳዩት ባሕርይና ያልተለመደ እንቅስቃሴ ሌላ ትርጓሜ ከመስጠት እንድንቆጠብ ይረዳል፡፡
Show all...
6👍 4😢 1
Do you enjoy reading this channel? Perhaps you have thought about placing ads on it? To do this, follow three simple steps: 1) Sign up: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox 2) Top up the balance in a convenient way 3) Create an advertising post If the topic of your post fits our channel, we will publish it with pleasure.
Show all...
2👍 1🔥 1👏 1🤩 1
ምኩራብ የዐብይ ጾም ሦስተኛ እሑድ(ሳምንት) ሦስተኛው ሰንበት ምኩራብ ተብሎ የተሰየመበት ምክንያት በዚሁ ዕለት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ከዋዜማው ጀምሮ እስከ ሰላሙ ድረስ በዕለተ ሰንበት «ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ» «ምኩራብ» ማለትም ቀጥተኛ ፍችው ኮረብታ፣ ተራራ የሚያኸል ታላቅ ሕንጻ ማለት ነው፡፡ ከዚህም የተነሣ የአይሁድ ቤተ ጸሎት ወይም ቤተመቅደስ ማለት ይሆናል፡፡ ዐቢይ ፍሬ ቃሉ ግን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያነ ሥጋን በትምህርቱ፣ ድውያነ ነፍስን በታምራቱ ሲፈውስ በምኩራብ እየተገኘ የፈጸመውን የማዳን ሥራ በኀሊና እያሳሰበ የሚያስተምር ሦስተኛ ሳምንት ነው፡፡ ዮሐ. 2:12 «ኢየሱስ በሰንበት ቀን ወደ አይሁድ ምኩራብ ገባ» እያለ ኢየሱስ በአይሁድ ምኩራብ ማስተማሩን እየጠቃቀሰና እያነሣሣ ስለሚዘምር ይህን ሰንበት ለዚህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምኩራብ እየገባ ለማስተማሩና በምኩራብ የሚሸጡ የሚለውጡ ነጋዴዎችን ለማስወጣቱ ቤተ መቅደሱን ለማስከበሩ መታሰቢያ ሳምንት ነው። የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ) ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ ወመሐረ ቃለ ሃይማኖት ወይቤሎሙ ምጽዋተ አበድር እመሥዋዕት አነ ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት እግዚኣ ውእቱ ለሰንበት ወልደ እጓለ እመሕያው ኢትግበሩ ቤተ አቡየ ቤተ ምስያጥ ቤትየሰ ቤተ ጸሎት ይሰመይ ቦአ ምኩራቦሙ ወገሠፆሙ ያርምሙ አንከሩ ምህሮቶ ሞገስ ቃሉ ወጣዕመ ነገሩ ወሣዕሣዓ አፉሁ፡፡ ትርጉም:- ጌታችን ኢየሱስ ወደ አይሁድ ምኩራብ ገባ፤ የሃይማኖት ቃልን አስተማረ፤ ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወዳለሁ፤የሰንበት ጌታዋ የምሕረት አባቷም እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም የሰንበት ጌታዋ ነው ፡፡ያባቴን ቤት የንግድ ቦታ አታድርጉት፤ቤቴስ የጸሎት ቤት ይባላል (እያለ የሃይማኖትን ቃል አስተማራቸው፡)፡ ወደ ምኩራባቸውም ገብቶ ዝም ይሉ ዘንድ ገሠፃቸው፤ እነርሱም ትምህርቱን፣ የቃሉን ግርማ፣ የአነጋገሩን ጣዕምና፣ የአንደበቱን ቅልጥፍና አደነቁ። ምስባኩም፦ መዝ ፷፰፥፱ "እስመ ቅንዐት ቤትከ በልዐኒ ትዕይርቶሙ ለእለይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ" "የቤትህ ቅናት በልቶኛል የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆብኛልና ነፍሴን በጾም አስመረርኳት" በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ ጥቅሶች፦ -ቆላ ፪፥፲፮ እስከ ፍጻሜ -ያዕ ፪፥፲፬ እስከ ፍጻሜ -የሐዋ ሥራ ፲፥፩-፱ ወንጌሉም፦ ዮሐ ፪፥፲፪ እስከ ፍጻሜ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
👍 18 16
"ምኩራብ" በዲያቆን ዘማሪ ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
👍 11 11🥰 7
"በእጸ መስቀሉ የተከፈለልኝ" ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
42👍 26🥰 3
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!