cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox

Show more
Advertising posts
29 951Subscribers
+1624 hours
+227 days
+58830 days
Posts Archive
በሰሙነ ሕማማት ባሉ ቀናት የግዝት በዓላት(12፣ 21 ወይም 29) ቢያጋጥሙ እንኳ ስግደት ይሰገዳል!! ያዳምጡት! @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
12👍 4👏 3🙏 1
<<የተዋሕዶ ልጆች>> አዲስ ኦርቶዶክሳዊ ቻናል በልዩ አቀራረብ፤ ኑ ተቀላቀሉ። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/Ethiop_tewahido https://t.me/Ethiop_tewahido https://t.me/Ethiop_tewahido
Show all...
👍 7 3
<<የተዋሕዶ ልጆች>> አዲስ ኦርቶዶክሳዊ ቻናል በልዩ አቀራረብ፤ ኑ ተቀላቀሉ። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/Ethiop_tewahido https://t.me/Ethiop_tewahido https://t.me/Ethiop_tewahido
Show all...
"ኒቆዲሞስ" በዘማሪ ዲያቆን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ ኒቆዲሞስ/፪/ክቡር፣/፪/ ሌቱን በብርሃን የሚማር መምህር፣/፪/ በጨለማው ግርማ ኮከብ የደመቀ፣ በመከራው ጽናት ይህን ዓለም ናቀ፣ መምህር ሆኖ ሳለ ከመማር ያልራቀ፣ የትዕቢትን ጅረት : በትህትና : ተዋርዶ አደረቀ። °°°°°°°°°°°°°°✧°°°°°°°°°°°°°°° ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የዓቢ ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ። °°°°°°°°°°°°°°✧°°°°°°°°°°°°°°° ፍርሀትን በሚጥል ፍፁም ፍቅር ያደረ፣ ከመስቀል አውርዶ ጌታውን ቀበረ፣ የመግነዙን በፍታ በሽቱ ያከበረ፣ ከመቅደሱ አንቀጽ : ላይረሳ : አምድ ሆኖ ታጠረ። °°°°°°°°°°°°°°✧°°°°°°°°°°°°°°° ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የዓቢ ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ። °°°°°°°°°°°°°°✧°°°°°°°°°°°°°°° ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ነገረች፣ ህጉን ለሚያስበው ምክር አለኝ እያለች፣ ከጨለማው ኃጢአት ነቅታ ብርሃን ካየች፣ እንደ ኒቆዲሞስ : ነፍስህም : ተምራ ተመለሰ። °°°°°°°°°°°°°°✧°°°°°°°°°°°°°°° ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የዓቢ ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ። @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
👍 22🥰 8 7😢 1
ኒቆዲሞስ የዐብይ ጾም ሰባተኛ እሑድ(ሳምንት) ኒቆዲሞስ ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የነበረው ሰው ነው፡፡ የአይሁድ አለቆች አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን ‹‹ምልክት አሳየን›› እያሉ ይፈታተኑት ነበር፡፡ ጌታችን ስለ ሞቱና ትንሣኤው በምሳሌ እያስረዳ ቢያስተምራቸውም እነርሱ ግን አልገባቸውም ነበር፡፡ ከዚህም አልፎ ጌታችን በተአምራቱ የታመሙትን ሲፈውስ ‹‹ሕጋችን ተሻረ›› ይሉ ነበር፡፡ በዚህ ዅሉ ተአምራትና ትምህርት የአይሁድ አለቆች ክርስቶስን ለመክሰስ በሚፈልጉበት ወቅት ከአይሁድ አለቆች አንዱ ኒቆዲሞስ በቀን እንዳያደርገው አይሁድን ቢፈራ፣ አንድም ጊዜ ባያደርሰው እንደ ባልንጀሮቹ ክርስቶስን ሳይቃወም በሌሊት ወደ ጌታችን ዘንድ እየሔደ ወንጌልን ይማር ነበር፡፡ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በነፍስ የታመሙትን በቃሉ፣ በሥጋ የታመሙትን በተአምራቱ ሲፈውስ ኒቆዲሞስ ሰምቶ፣ ተመልክቶ በመምህርነቱ ሳይኮራ አለቅነቱን መመኪያ ሳያደርግ በልቦናው የተሳለውን እውነትን የመፈለግ ስሜት አንግቦ ከጌታው፣ ከመምህሩ ከክርስቶስ ዘንድ በሌሊት ይገሰግስ ነበር (ዮሐ. ፫፥፩)፡፡ ምስክርነቱንም እንዲህ ሲል መስጠት ጀመረ፤ ‹‹መምህር ልታስተምር ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን፡፡ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከኾነ በቀር አንተ የምታደርገውን ተአምራት ሊያደርግ የሚችል የለምና፤›› (ዮሐ. ፱፥፳፬፤ ሐዋ. ፲፥፴፰)፡፡ ይህን ምስክርነቱን በሚሰጥበት ጊዜም ጎዶሎን የሚሞላ፤ አላዋቂነት በአዋቂነት የሚለውጥ፤ ከምድራዊ ዕውቀት ወደ ሰማያዊው ምሥጢር የሚያሸጋግር አምላክ ‹‹ዳግመኛ ያልተወለደ የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማየት አይችልም፤›› በማለት የአይሁድ መምህር ለኾነው ኒቆዲሞስ ቢያስተምረው ምሥጢሩ አልተገለጠለትም ነበርና ‹‹ሰው ከሸመገለ በኋላ ዳግመኛ መወለድ እንደምን ይቻላል? ዳግመኛ ይወለድ ዘንድ ወደ እናቱ ማኅፀን ተመልሶ መግባት ይችላልን?›› በማለት ጥያቄ አቅርቧል (ዮሐ. ፫፥፮፤ ፩ኛጴጥ. ፩፥፳፫)፡፡ ‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ያልተወለደ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም፡፡ ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፡፡ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነውና፤›› (ኤፌ. ፭፥፳፮) በማለት አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኒቆዲሞስ ቢያስረዳውም ምሥጢሩ ከአቅሙ በላይ ስለ ኾነበት እንደምን ይቻላል? በማለት ጠይቋል፡፡ አበ ብዙኃን አብርሃም ከአምላኩ ሞገስን አግኝቶ የሰዶምና ገሞራ ጥፋት እንዳይደርስ ለመማለድ ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጋገር እንደ ነበረ፤ ኒቆዲሞስም አላዋቂነቱን አምኖ ያልገባውን ምሥጢር ከአምላኩ በጠየቀ ጊዜ ኢየሱስ ክርስቶስም፡- ‹‹አንተ የእስራኤል መምህራቸው ኾነህ ሳለ ይህን ነገር አታውቅምን? በምድር ያለውን ስንነግራችሁ ካላመናችሁ በሰማይ ያለውን ብንነግራችሁ እንደምን ታምናላችሁ? ከሰማይ ከወረደው ከሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም … ሙሴ በምድረ በዳ እባቡን እንደ ሰቀለ የሰው ልጅ እንዲሁ ይሰቀላል፡፡ ያመነበት ዅሉ ለዘለዓለም ሕያው ኾኖ እንዲኖር እንጂ እንዲጠፋ አይደለም ...፤›› እያለ ሰው በመብል ምክንያት የአምላኩን ትእዛዝ አፍርሶ ከእግዚአብሔር ቢለይም የሰው ልጅ ያጣውን ልጅነት ለመመለስ፣ ስመ ክርስትናን፣ ሀብተ ወልድን ለመስጠት ጌታችን መምጣቱን አስረዳው (ዮሐ. ፫፥፲፬)፡፡ ይህን የክርስቶስን የማዳን ሥራና በሥጋ መገለጥም ‹‹ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ አመከርከኒ ወኢተረከ ዐመፃ በላዕሌየ ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ እጓለ እመሕያው፤ ልቤን ፈተንኸው፡፡ በሌሊትም ጐበኘኸኝ፤ ፈተንከኝም፡፡ ምንም አላገኘህብኝም፡፡ የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው፤›› (መዝ. ፲፮፥፫) በማለት ቅዱስ ዳዊት ከኒቆዲሞስ ሕይወት ጋር በማዛመድ አመሥጥሮታል፡፡ በሌሊት ከአምላኩ ተምሮ ምሥጢሩ የተገለጸለት ኒቆዲሞስ ቀድሞ በአደባባይ ሔዶ መማርን ይፈራ እንዳልነበረ ምሥጢሩ ሲገለጽለት ግን አይሁድ ጌታችንን በሰቀሉት ዕለት ፍርኃት ርቆለት ከአርማትያሱ ዮሴፍ ጋር ቅዱስ ሥጋውን ገንዞ ለመቅበር በቃ፡፡ ‹‹ወአልቦ ፍርኃት ውስተ ተፋቅሮትነ፤ ፍጹም ፍቅር ፍርኃትን አውጥቶ ይጥላል›› ተብሎ እንደ ተጻፈ (ማቴ. ፳፯፥፶፰፤ ፩ኛዮሐ. ፬፥፲፰)፡፡ ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ያመነ፣ የተጠመቀ ይድናል፡፡ ያላመነ፣ ያልተጠመቀ ግን ይፈረድበታል›› (ማር. ፲፮፥፮) በማለት በሰጠን ቃል ኪዳን መሠረት በአምላክነቱ አምነን የመንግሥቱ ወራሾች እንኾን ዘንድ ለኒቆዲሞስ ምሥጢሩን እንደ ገለጸ ለእኛም ይግለጽልን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡  በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ ጥቅሶች፦ -ሮሜ ፯፥፩-፱ -፩ኛ ዮሐ ፬፥፲፰ እስከ ፍጻሜ -የሐዋ ሥራ ፭፥፴፬ እስከ ፍጻሜ ምስባኩም፦ መዝ ፲፮፥፫ "ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ አመከርከኒ ወኢተረክበ ዓመጻ በላዕሌየ ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ ዕጓለእመሕያው" "ልቤን ፈተንከው በሌሊትም ጎበኘኸኝ ፈተንኸኝ ምንም አላገኘህብኝም የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው" ወንጌሉም፦ ዮሐ ፫፥፩-፳ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
👍 12 12😢 1
"እግዚአብሔር ያጽናናሽ" እግዚአብሔር ያጽናናሽ                  ዕንባሽን ያብሰው፣ ቤተክርስቲያን ሆይ                  እስከመጨረሻው፣ ካህንሽ በመቅደስ           ከበጎቹ ጋራ ስለታረደብሽ፣ እንደ ራሔል ዕንባ                  እግዚአብሔር ያስብሽ። ስለ ጌታ ፍቅር ማህቧተን ይዛ                       አክሊል ተቀዳጀች፣ በደሙ ከዋጃት ከክርስቶስ ጋራ                        እኖራለሁ አለች፣ የእምነት ሰማዕትነት ሲመጣ በገሃ፣ ይሻሙ ነበረ ከእሳቱ ለመንደድ።         አዝ= = = = = በዚህ በእኛ ዘመን ቅዱሳን ተሻሙ፣ አክሊሉን ለመውሰድ ከሁሉ ሊቀድሙ፣ የተክለሃይማኖት የክርስቶስ ሠምራ ሕፃናት ተነሱ፣ በመሞት ህይወትን ከእግዚአብሔር ሊወርሱ፣         አዝ= = = = = አሕዛብ አትድከም በመግደል አትጸድቅም፣ ነፍሰ ገዳይነት አሸንፎ አያውቅም፣ በበቀል ጭካኔ የሰው ልጅን ማረድ፣ እጅግ የወጣ ነው ከሃይማኖት መንገድ።         አዝ= = = = = ይቺ ቤተክርስቲያን የተገነባችው                              በደም ስለሆነ፣ በሞት ሕይወት ሊያገኝ                           ክርስቲያን ታመነ፣ ምድሪቱ ለእግዚአብሔር የተቀደሰች ናት፣ ሕዝቧም ሊወድቅ ቀርቧል እንደበግ መስዋዕት።                     በሊቀመዘምራን ይልማ ኃይሉ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
👍 24😢 6 5
ሚያዝያ ፲፩ ዝክረ ሰማዕታተ ሊብያ ዘጠነኛ ዓመት አመ ዐሡሩ ወአሚሩ ለሚያዝያ በዛቲ ዕለት አዕረፉ ሰማዕታተ ኢትዮጵያ:: በረከቶሙ የሃሉ ምስሌነ ለዐለመ ዐለም አሜን፡፡ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
22😢 6👍 4🙏 1
ክዕወተ በርዕ ሥር እየሰደደ ሲሄድ ባለበት አይወሰንም፡፡ «አንደኛውኑ ዝሙት ይሻላል›› በማሰኘት ወደ ዝሙትና ግብረ ሰዶም ሊያመራ ይችላል፡፡ ገለልተኝነት፣ ብቸኝነትን መሻትና የሥራ ተነሣሽነትን ማጣት ደግሞ ሌላው የዚህ ክፉ ልማድ ጐጂ ገጽታ ነው። የመሰንጋት ሌላው አደገኛና ጐጂ ገጽታው ደግሞ ተስፋ መቁረጥና አጉል ጸጸት እንዲሁም ከንቱ ትሕትናን ማሳደሩ ነው፡፡ አጉል ጸጸቱ እንደ ይሁዳ ዓይነት ጸጸት በመሆኑ ኀፍረተ አካልን ተናዶ እስከ መቁረጥ ለ.ያደርስ ይችላል:: ይሁዳ ራሱን እስከ መግደል የደረሰው በአጉል ጸጸት ነውና፡፡ የሐዋ 1፥16-20፤ ማቴ 27፥3-5   አጉል ትሕትና ማለት ደግሞ በዚህ ክፉ ልማድ የተመረዙ ሰዎች ዘማርያን፣ ሰባክያን፣ መነኮሳትና በልዩ ልዩ አገልግሎትና መንፈሳዊ ሙያ የተሰማሩ ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ:: መንፈሳዊ አገልግሎት ንጽሕናን የሚፈልግ በመሆኑ ኑሮአቸውና መንፈሳዊ አገልግሎታቸው ሳይጣጣም ሲቀር «ማገልግል አይገባኝም!» በማለት ከትሩፋትና ከበጐ ሥራ ራሳቸውን የሚያሸሹ አሉ:: ነገር ግን ክፉ ሥራን እንጂ የትሩፋት ሥራን መሸሽ በምንም መልኩ አይበጅም፡፡ ከአገልግሎት ጋር ሆነን ያላራቅነውን ክፉ ሥራ ከረድኤተ እግዚአብሔር ተለይተን ልናርቀው አንችልም፡፡ ውሣኔያችንን አየመረመርን ከበላዮቻችን ማለትም ከመንፈሳዊ አባቶች ጋር እየመከርን በምክረ ካህን በፈቃደ ካህን መኖርን መፍትሔ እናድርግ፡፡ ይኸውም ለጊዜው ነው እንጂ አማራጭ የሌለው መፍትሔ ከዚህ ልማድ መለየት ብቻ ነው፡፡   በጋብቻ ሕይወት ውስጥ አንዱ ለሌላው ወገን ደስታና እርካታ ማሰቡ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ ካልሆነ ግን የጋብቻ ግንኙነቶች ይበላሻሉ:: በጋብቻ መሃል ጭንቀትና ቅሬታም ይፈጠራል፡፡ ወጣቶች ከጋብቻ በፊት ያዘወትሩት የነበረው የፆታ ብልትን በመነካካትና በማሻሸት ለመርካት የመሞከር ተግባር ወይም ሴጋ ስለ ራስ ደስታና እርካታ ብቻ የማሰብ ልምድን ያሳድግባቸዋል:: ይህ ልምድ ደግሞ በጋብቻ ውስጥ የሚገኘውን ደስታ አደጋ ላይ ይጥለዋል፡፡ ምክንያቱም ስለራስ እርካታ ብቻ በማሰብ በባልና በሚስት መሃል መተሳሰብ እንዲጠፋ ስለሚያደርግ ነው፡፡ ይህ ችግር ትክክለኛውን መፍትሔ አያግኙለት እንጂ በዓለማዊያኑ ዘንድ በስፋት ለውይይት ይቀርባል፡፡ በመንፈሳዊያን ሰዎች ዘንድ ደግሞ ምንም በሰፊው ባይወያዩበት በጋብቻ ውስጥ ለሚፈጠሩ የግጭት መነሻዎች ዋነኛ ሲሆን የሚመነጨውም ከትዳር በፊት ይዘወተር ከነበረ ክዕወተ ዘርዕ (ሴጋ) አማካኝነት ነው፡፡ አንተ ወጣት ይህ ክፉ ልማድ እስከ ጋብቻ ዘልቆ እንዴት ሊጐዳ እንደሚችል ተረዳህን? ከ«ግብረ አውናን» እንዴት መላቀቅ ይቻላል? ሀ. ግብረ አውናን እንደ ማር ጠብታ ነው:: የማር ጠብታ ልብስ ላይ የወደቀ እንደ ሆነ በፍጹም የሚለቅ አይመስልም፤ ነገር ግን ትንሽ ለቅለቅ ያደረጉት እንደሆነ ወዲያውኑ ይለቃል:: ይህ ክፉ ልማድም እንደ ማር በቀላሉ ባይሆንም ከልብ በመጸጸት በጠንካራ መንፈስ ከተነሡ ሊያስወግዱት ይቻላል:: ተስፋ መቁረጥ ከሁሉ ይከፋልና በመጀመሪያ የሚያስፈልገው ሊወገድ የማይችል አድርጐ በመቁጠር ተስፋ አለመቁረጥ ነው:: ለ. መሰንጋት ልማድ ነው፡፡ ልማድ ደግሞ በልማድ ይሸነፋል፡፡ ጠንክረህ ከተነሣህ ይህን ተግባር በትዝታ ብቻ የምታስብበት ቀን ሩቅ አይሆንም:: ነገር ግን ከዚህ ልማድ ጋር ለመዋጋት ከመነሣትህ በፊት «ይህን ክፉ ልማድ ምን ያህል ከልቤ ጠልቼዋለሁ?» በማለት ራስህን ጠይቅ፡፡ መላልሰህ የምትሰናከለው ሳትጸጸት ቀርተህ ሳይሆን ጣዕሙ በልቡናህ ስላለና ጐጂነቱ ዘልቆ ወደ ልብህ ስላልገባ ነው:: ስለዚህ መፍትሔው በመጀመሪያ ጎጂነቱን አምነህ ይህን ኃጢአት መጥላት መጀመርህ ነው፡፡ ይህ ካልሆነና የዚህን ኃጢአት ጣዕም ከልብህ ሳታወጣ ልታርቀው ብትታገል የአምላክህን ረድኤት አታገኝም። እግዚአብሔር ከኃጢአት ከመለየታችን በፊት መራራነቷን ከልብ እንድናምን ይፈልጋልና፡፡ የኃጢአት ጣዕም ከልብ ካልወጣ ለጊዜው ከኃጢአት በልዩ ልዩ ምክንያት ብንለይ እንኳን ተመልሰን አንድ መሆናችን አይቀርም፡፡ ሐ. ይህን ክፉ ልማድ እንደ እሳት የሚያያይዙት የራስህ ተግባርና በዙሪያህ ያሉ ነገሮች ናቸው:: ከዚህ እኩይ ልማድ ለመላቀቀቅ ከፈለግህ «ተዐቅቦ›› ያስፈልግሃል፡፡ «ተዐቅቦ›› ማለት መከልከል መቆጠብ ማለት ነው፡፡ የምትከለክለውም ወደዚህ መጥፎ ሐሳብ ልቡናህን የሚስቡትን ነገሮች ከማየት፣ ከመስማት፣ ከመንካትና ከመሳሰሉት ነው:: ስለዚህ የሴቶችን ገላ በፊልምም፣ በአካልም ቢሆን በምንም መልኩ ከማየት ተቆጠብ። በመዋኛና በመጠመቂያ ቦታዎች ራስህን ጠብቅ የሴት ልጅን መልክና ቅርፅ መርዘህና አተኩረህ አትመልከት፡፡ ስለ ዝሙት የሚያሳስቡ ስዕሎችን፣ ጽሑፎችንና ወሬዎችን አጥብቀህ ሽሻቸው፡፡ ሥራህ ሁሉ አንተው እያራገብክ ለምን ይቃጠላል? ብሎ እንደ መጠየቅ እንዳይሆንብህ ተጠንቀቅ:: መ. ዘወትር ልቡናህ የሚጠመድበትን ነገር ፈልገህ አድርግ፡፡ ቦዘኔ አትሁን፤ ትጉህ ሠራተኛ ሁን:: ሥራህም በእንቅሳቃሴ የተሞላ ወይም አእምሮን ያለ ዕረፍት የሚያሠራ ይሁን። ነጋዴ ብትሆንና ገበያ ሲመጣ ሽጠህ ብትቀመጥ ከዚያ በኋላ ግን ቁጭ ብለህ ብትውል በሥራ ቦታ በመዋልህ ብቻ አእምሮህ እስካልተያዘ ድረስ በመንፈሳዊ ጎዳና ከተመለከትከው እየሠራኽ ነው አይባልም፡፡ በትርፍ ሰዓትህ የሚነበብ ወይም ሌላ የሚሠራ ሥራ ፈጥረህ ሥራ:: የዝሙት ማራገቢያው የአእምሮ ቦዘኔነት ነውና፡፡ ሠ. «ሁለት ሁለት አድርጐ ላካቸው» የሚለውን የወንጌል ቃል አስብ፡፡ በዚህ ክፉ ልማድ ተጠምደህ ሳለ ለብቻህ መሆንን አትወደድ፡፡ ቢቻልህ አኗኗርህና መኝታህ ከምታፍረውና ከምታከብረው ሰው ጋር ይሁን፡፡ ይህም ጓደኛህ ወይም ከቤተሰቦችህ አንዱ ሊሆን ይችላል:: ከብቸኝነት ይልቅ መወያየትን ይልቁንም መንፈሳዊ ውይይትን ዘወትር አድርግ፡፡ በጸሎት ከሚረዱህ መንፈሳዊያን መምህራንና አባቶች ጋር ጊዜ ማሳለፍን ውደድ፡፡ ከእነርሱ ጋር በመወያየትህ በጸሎታቸው እንዳይረሱህ ከማድረግ ጋር ለነፍስህ ወደብ የሚሆኑ ብዙ መንፈሳዊ ነገሮችን ትማራለህና፡፡ ረ. እንቅልፍ የያዘህ ስለ መሰለህ ብቻ ወደ መኝታ አትሂድ፡፡ በቂ ዕረፍት አግኝቼ የለምን? መኝታ ለምን አስፈለገኝ? ብለህ ራስህን ጠይቅ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ስትተኛ ውለህ እንቅልፍ ያምርሃልና፡፡ ነገር ግን ሰይጣን ሊፈትንህ ከሆነ በምትተኛበት ጊዜ እንቅልፍ ከአይንህ ይርቃል:: ተከትሎም ፈተናው ይመጣና ወደ ዝሙት ሕሊናህ ይሳባል፡፡ ሰውነትህንም በመደባበስ ፍትወትህን ለማርካት ትጥራለህ፡፡ ስለዚህ ከመተኛትህ በፊት በደንብ መድከምህንና ቶሎ ማሸለብ መቻልህን መርምረህ ተኛ፡፡ ሲ ጸሎት ማድረግንም አትርሳ የሚረሳ ነገር አይደለምና፡፡ ስትተኛም በጀርባህ ወይም በሆድህ አትተኛ:: ከዚህ ይልቅ በጎንህ ለመተኛት ሞክር፡ አመጋገብህ በልክ ይሁን ጾምን በተገቢው መንገድ ጹም፡ ቅዱሳት መጻሕፍትን አንብብ፡፡ የመንፈሳዊ ሙያ ባለቤት ከሆንክ የምታወቀውን ዜማ ድምፅ አወጥተህ አንጐራጉር፡፡ ያም ባይሆን የምትችለውን መዝሙር ዘምር። ሽ. እንዲህ ያለ ፈተና ሲነሣብህ አንድ ዓይነት የአካል እንቅስቃሴ (ስፖርት) ሥራ:: ወይም ወዲህና ወዲያ ተንቀሣቀስ፡፡ ከዚህም ሁሉ ይልቅ ደግሞ ከሆነልህ መስገድህ ይመረጣል:: ሽንትን መሽናትም ጥሩ መድኃኒት ሊሆንህ ይችላል:: በየጊዜው ጸበል መጠመቅንም ቸል አትበል፡፡ ነገር ግን ይህን በምታደርግበት ጊዜ ሕዋሳተ አንስትን ከማየት በእጅጉ ተጠንቀቅ፡፡
Show all...
👍 16 6
ቀ. ሰውነትህ ሲበላህ ይልቁኑም ወደ አባለ ዘርዕ አካባቢ ከሆነ ትኩረት ሰጥተህ አታስበው፡፡ ምክንያት እንዳይሆንብህ ተጣጥበህ ንጹሕ ለመሆን ሞክር፡፡ የበላህን ቦታ ግን በምንም መልኩ አትከከው፡፡ ማከክ ሰውነትን ከማቁሰል በቀር ይህን ለመሰለ ፈተና መፍትሔ አይሆንምና፡፡ ከዚያ ይልቅ መጽሐፈ መነኮሳት «ግበር ትእምርተ መስቀል በሕሊናከ ውስተ መካነ ደዌከ› ፤ ‹ሕመም ወይም ማላከክ በተሰማህ ቦታ ላይ በሕሊናህ የመስቀል ምልክት ሥራ» ይላልና። በሚያሳክክህ ቦታ ላይ በሕሊናህ አማትብበት፡፡ በሕሊናም ማለቱ የሚያይህ ሰው ነገር እንዳይመራመርኽ ለማድረግ ነው፡፡ በተረፈ ግን አጥብቀህ ጸልይ፡፡ ሁላችንንም እግዚአብሔር ይርዳን! በቀጣይ ምዕራፍ አምስት <<ምትረተ አስኪት>> በሚል ይቀጥላል..... ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ። @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
29👍 7👏 1
የተመከረ ሰው ምን ፈርቶ ከክፉ ሥራው ይመለሳል?    በኃጢአት ተግባር ላይ ያለ ሰው «ምን ይመጣብኝ ይሆን?›› እያለ ማሰቡ በውስጡ እግዚአብሔርን መፍራት እንዳለ ያሳያል፡፡ ምንም እንኳን ከኃጢአት መላቀቅ ባይችል ይህ ፍርሃቱ እንደ ጽድቅ ሊቆጠርለት ይችላል፡፡ ያላየውን እግዚአብሔርን መፍራት የማመን ምልክት ነውና፡፡ እግዚአብሔር የሚያመጣውን ፍርድ አስቦ መፍራት ከኃጢአት አንጽቶ እንደ ጻድቅ ሊያስቆጥር መቻሉን መጽሐፈ መነኮሳት በዚህ መልኩ ገልጾታል:: «ፍራህ እምእንታክቲ ምግባራት እንተ ትትኄበብ ከመ ባቲ መገሥጽ እስመ ዘከመዝ ግዕዙ ይትበልሃ ከመ ውእቱ የሐውር በአፍኣ እምፍኖታ» : «ቅጣትና ተግሣጽ እንደሚያስከትል ከጠረጠርከው ሥራ ሁሉ ተጠበቅ እንዲህ ሲፈራ የሚኖረው ሰው ከኃጢአት ውጭ ነው ይባላልና›› ማለት ነው:: ማር.ይስ.አን.16 ምዕ 1   ሰው ሁሉ ክእግዚአብሔር ጋር እንድ መሆን የሚችለው ከእነዚህ ከሦስቱ መንገዶች ቢያንስ እንኳን በአንዱ መጓዝ ከቻለ ብቻ ነው:: አንደኛው ያለ ምንም ምክንያት በራሱ ተነሣሥቶ እንደ አብርሃም ፈጣሪውን ፈልጎ ካመነ። ሁለተኛው እንደ ቅዱስ ጳውሎስ በግርማ እግዚአብሔር ተገልጾ ከተመለስ፡፡ ሦስተኛ ደግሞ በክፉ ሥራው ምክንያት የሚመጣበትን ቅጣት አስቦ ከፈራ ነው፡፡ የሐዋ 9፥6፣ ማር ይስ አን 3 ምዕ1 ለምሳሌ:- እንደ ቅዱስ ወቅሪስ፡፡ ቅዱስ ወቅሪስ መልከ መልካም ነበረ። ከዕለታት በአንድ ቀን ከሴት ጋር ተቃጠረ፡፡ በዚያችም ሌሊት ራእይ አየ፡፡ ራእዩም «እርሱ ታሥሮ ከብዙ እሥረኞች ጋር በንጉሡ ፊት ቆሞ እሥረኞቹ እያንዳንዳቸው በተራ ሲመረመሩ እርሱ ግን የቀጠርኳት ሴት ባሏ አሣሥሮኝ ይሆን? እያለ ሲጨነቅና ሲፈራ በዚህ ጊዜ ጠባቂ መልዐኩ ከወዳጆቹ አንዱን መስሎ መጥቶ ይህን ሥራ ሠርተህ እንዳታሲዘኝ ማልልኝና እኔ ልዋስህ እያለ ሲያስምለው›› ነበር። ከዚያ በኋላ ሄላኔ የምትባል ደግ ሴት ነበረች ወደ እርሷ ሄዶ ያየውን ራእይ ነገራት፡፡ እርሷም ተርታ ልብስ ለብሰህ አልባሌ መስለህ ፈጣሪህን አገልግለው ይምርሐል አለችው፡፡ እርሱም እንደነገረችው አድርጐ ከፈጣሪው ታርቋል፡፡ ማር ይስ አን 3 ምዕ 1 እንዲህ ከሆነ ፍርድን አስቦ መፍራት ጻድቅ ያደርጋል ቢባል ምን ይደንቃል?    ከክፉ ሥራ ለመመለስና ንስሐ ለመግባት ጥርጊያ ጎዳናው እግዚአብሔርን መፍራት ነው :: እግዚአብሔርን መፍራት ከእግዚአብሔር ዘንድ ምሕረትንና ርኅራኄን እንደሚያስገኝ ከዚህ በታች የተጻፈው ታሪክ ያስረዳል:: የእግዚአብሔር ነቢይ ኤልያስ <<በእግዚአብሔር ፊት ክፉን ሥራ ለመሥራት ራሱን ለሸጠ>> ለአክዓብ የሚደርስበትን ቅጣት ሁሉ በነገረው ጊዜ አክዓብ «ልብሱን ቀዶ ገላውን ማቅ አለበሰ፥ ጾመም፣ በማቅ ላይም ተኛ ቅስስ ብሎም ሄደ፡፡›› ይላል:: በተለይ «ቅስስ ብሎ ሄደ» የሚለው ዐረፍተ ነገር የአክዓብን ፍርሐትና ድንጋጤ ያመለክታል:: በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር «ኤልያስ ሆይ አክዓብ እንደ ደነገጠ (እንደፈራ) ተክዞም እንደሄደ አየህን? በፊቴ የተዋረደ ስለሆነ በልጁ ዘመን በቤቱ ላይ ክፉ ነገር አመጣለሁ እንጂ በእርሱ ዘመን ክፉ ነገር አላመጣም።›› በማለት በይቅርታ ወደ አክዓብ መመለሱን ተናግሯል:: 2ነገ 20፥27 ሰው በክፉ ሥራው «ምን ይመጣብኝ ይሆን?» እያለ ሲፈራ እግዚአብሐርን መፍራቱ እንጂ ሌላ አይደለም:: ከላይ የተጠቀሰው የአክዓብ ታሪክ እግዚአብሔርን መፍራት የሚያስገኘውን ታላቅ ጥቅምና በእግዚአብሔርም ዘንድም ያለውን ተወዳጅነት ያስረዳል፡፡ ሰይጣን ደግሞ ሰው እግዚአብሔርን በመፍራቱ ብቻ እንኳን የሚያገኘውን ጥቅም ያውቃልና የዓለምን ምሁራን አስነሥቶ በልዩ ልዩ ጐዳና ፍርሐተ እግዚአብሔርን ከሰው ልብ የሚያርቅ ንግግር ያናግራቸዋል፡፡ አንድ ጊዜ ፍርሐትና የበደለኝነት ስሜት ጤናን ሊያቃውስ እንደሚችል ሌላ ጊዜ ደግሞ ፍርሐት በራስ የመተማመን ጉድለትና የብቃት ማነስ ምልክት እንደ ሆነ በማስረዳት ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት በፍርሃት እንዳይመላለሱ ለማድረግ ይጥራሉ፡፡ እኛ ክርስቲያኖች ግን ምንም ከበደል መራቅ ባይቻለን ፍርድን አስቦ መፍራታችን ብቻ እንኳን ዋጋ ያለው መሆኑን እንረዳለን፡፡ ሰይጣን በውጫዊ ማንነታችን ሰልጥኖ ኃጢአት ቢያሠራንም ፍርድን አስበን መፍራታችን በውስጣችን የምንገዛው ለእግዚአብሔር መሆኑን ያመለክታል፡፡ ውጫዊው ኃላፊና ፈራሽ ሲሆን ውስጣዊው ግን ዘለዓለማዊ ነው፡፡ በውጫዊው ሰውነት ከመገዛት በውስጣዊው መገዛት በብዙ ይበልጣል:: እንዲሁም በአፍኣዊ ማንነታችን ኃጢአት እየሠራን ለሰይጣን ከምንገዛው ይልቅ በውስጣችን ለእግዚአብሔር የምንገባው አገዛዝ ይበልጣልና መጨረሻችን የእግዚአብሔር መሆን ነው:: ስለዚህ «ለእግዚአብሔር በፍርሐት እንገዛ›› መዝ 2፡11 ብንበድልም ፍርሐትን ከልባችን አናርቃት። «ግብረ አውና>>ን መፈጸም ሰው መግደል ሊሆን ይችላል?   ብዙ ሰዎች ዘር ሲክፍሉ ወይም ሲፈሳቸው ይልቁኑም አውቀው ያደረጉት ከሆነ «ሰው እንደ መግደል ይቆጠርብኝ ይሆን?» እያሉ ራሳቸውን መጠየቃቸው አይቀርም፡፡ በእርግጥ ግብረ አውናንን እየፈጸሙ ዘርን ማፍሰስ ሰው እንደ መግደል ይቆጠር ይሆን?    ወንድና ሴት ሩካቤ ሲያደርጉ ከወንድ ዘር ከሴት ደግሞ ደም ተከፍለው ተዋሕዶ ባደረጉ ጊዜ ተከፍሎዋ እንደ የብርሃን ፋና ይሁን እንጂ በዚያው ጊዜ ነፍስም አብራ ትከፈላለች:: ነገር ግን ሴቶች በየወሩ ደም ሲያዩ ወንዶችም ዘር ሲወጣቸው ነፍስ እንደ ማጥፋት አይቆጠርባቸውም። እንዴት? ምሥጢሩ እንዲህ ነው:- እነሆ እሳት በእንጨት ውስጥ መኖሩ የታወቀ ነው:: ሆኖም አንድ እንጨት ከሌላ ጋር ሳይሳበቅ ለብቻው እሳት መፍጠር አይችልም:: እሳት በእንጨት ውስጥ ይገኛል ቢባልም ቅሉ እንጨት መስበር እሳት እንደ ማጥፋት አይቆጠርም:: እንጨት ምሳሌነቱ እንደ ሴት ደምና እንደ ወንድ ዘር ሲሆን እሳት ደግሞ እንደ ነፍስ ነውና፤ ሴቶች ለብቻቸው የሚያስገኙት ደም ወንዶችም ለብቻቸው የሚከፍሉት ዘር ነፍስን ሊያስገኝ ስለማይችል ሰው እንደ መግደል ሊቆጠር አይችልም:: ሰው የሚባለው ራሱ አራት ባሕርያተ ሥጋ ሦስት ባሕርያተ ነፍስ ያሉት ፍጥረት ነውና፡፡ ስለ ነፍስና ሥጋ በአጠቃላይ ስለ ሰው ተፈጥሮ የበለጠ ለመረዳት በዚሁ መጽሐፍ የመጀመሪያ ክፍል የሕይወት አጀማመር የሚለውን ንዑስ ክፍል ያንብቡ፡፡ ግብረ አውናንን የሚፈጽሙ ሰዎች በተያያዥ ሊከሠትባቸው የሚችለው ቀጣዩ ጥያቄ ደግሞ ሩካቤ ሥጋ ፈጽመው የማያውቁ ከሆነ ‹‹ከዚህ በኋላ ድንግል ልባል እችላለሁ?» የሚል ነው፡፡ ለዚህ ጥያቄ ምላሽ የሚሆን ሐሳብ ስለ ሴቶች ድንግልና በሚያትተው ንዑስ ክፍል «ድንግል ነኝን?» በሚለው ርዕስ ሥር የሰፈረ በመሆኑ እንዲያነቡት ተጋብዘዋል፡፡    «ግብረ አውናን» የሚያስከትለው ጉዳት    ግብረ አውናን (ሴጋ) ውጥረትን ለፈጠረ አንድ ችግር የተሳሳተ አማራጭን መጠቀም እንደመሆኑ መጠን በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ብርታትና ጥንካሬን የሚጠይቁ መንገዶችን እንድንሸሽ ያለማምዳል:: ይህ ማለት ደግሞ እጅግ ሲበዛ ሰነፍ እንድንሆን ያደርጋል ማለት ነው::    ግብረ አውናን ኃጢአት እንደ መሆኑ መጠን በዚህ ዓለምና በወዲያኛው ዓለም ቅጣትን ያስከትላል፡፡ በዚህ ዓለም ቅጣቱ እንደ አውናን ከመቀሠፍ ሊጀምር ይችላል፡፡ ዘፍ 38÷9 ሰላም ማጣት፣ ቁጭት፣ ጸጸት፣ ጭንቀት፣ መረበሽ፣ ንጹሕ ያለ መሆን ስሜትና የመሳሰሉት የግብረ አውናን እንጻራዊ ጉዳቶች ተደርገው ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡
Show all...
👍 12 2🥰 2
ሕይወተ ወራዙት(የወጣቶች ሕይወት)       ምዕራፍ ፬/4 ክፍል ፪/2 ...........................................................   «ግብረ አውናን»ን በተመለከተ አሳሳች ሐሳቦች     ግብረ አውናንን በተመለከተ ከተለያየ አቅጣጫ የሚሰነዘሩ ሐሳቦች አሉ:: ከነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ ምንም እንኳን በቀጥታ ድርጊቱን ለማበረታታት የተነገሩ ባይመስሉም ብዙዎችን ከዚህ ክፉ ልማድ እንዳይወጡ ለማሰር ኃይል ያላቸው ናቸው:: ከእነዚህም ሐሳቦች መካከል ጥቂቶቹ ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል:: ሀ) ብዙ ሰዎች «አውናን የተቀሠፈው ዘሩን በማፍሰሱ ሳይሆን ለወንድሙ ዘር ማቆምን  ስላልወደደ በምቀኝነቱ ነው» በማለት መሠረት የሌለው ሐሳብ ይሰነዝራሉ፡፡ በእርግጥ አውናን ለወንድሙ ዘር ላለማቆም ማሰቡ ምቀኛ ያሰኘዋል:: ያስቀሠፈው ዋና ምክንያት ምቀኝነቱ ነው ማለት ግን ስሕተት ነው፡፡ ምቀኝነት ሊያስቀሥፍ የሚችል ኃጢአት ቢሆንም አውናን የተቀሠፈው ግን «ዘሩን በማፍሰሱ» እንጂ በምቀኝነቱ አይደለም።
Show all...
👍 6 6
ሰው የራሱን የግል አስተያየት ወደ ጎን አድርጐ እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ ለሕዝቡ የሚናገረውን ማድመጥ ከፈለገ አውናን የተቀሠፈበትን ዋና ምክንያት መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡ ምቀኝነትና ዘርን ማፍሰስ በጣም ይለያያሉ:: ምቀኝነት የልቡና ሐሳብ ነው:: ዘርን ማፍሰስ ግን በግልጽ የሚታይ ተግባር ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ አውናን የተቀሠፈበትን ምክንያት ሲገልጽ «ሥራውም በእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ ሆነበት» ይላል እንጂ ‹‹ምቀኝነቱ›› አይልም:: ታዲያ የአውናን ክፉ ሥራው ምን ነበር ዘሩን በምድር ላይ ማፍሰሱ አልነበረምን? ምቀኝነት በሥራ የሚገለጥ የልቡና ክፋት እንጂ በራሱ «ሥራ» አይባልምና፡፡    ከላይ እንደተብራራው አውናን የተቀሠፈው ዘሩን በማፍሰሱ ሳይሆን በምቀኝነት ብቻ እንደሆነ አድርጐ መናገር መሠረት የሌለው የሰይጣን ትርጓሜ ከመሆኑም ባሻገር «ዘርን ማፍሰስ›› አያስቀጣም ወይም ሊያስቀሥፍ አይችልም እያሉ እንደማወጅ ነው፡፡ እንዲህ ማለት ደግሞ የእግዚአብሔርን ፍርድ ፈርቶ ከክፉ ሥራው ለመለስ ያለውን ወጣት ለምን ትመለሳለህ ግፋበት እንጂ እያሉ እንደመምከር ይቆጠራል፡፡ ክፉን ነገር እንደማያስቀጣ አድርጐ መተርጐም ተሳስቶ ማሳሳት ነውና ሊታረም ይገባል:: በዚህ የተሳሳተ ሐሳብ ተወግተው ክፉውን ልማድ እንደ በጐ ይዘው የሚማቅቁትን ወጣቶች ቤት ይቁጠራቸው፡፡ ለ) በመሰንጋት ራስን በራስ ለማርካት የመሞከር ተግባር በብዙ ወጣቶች ዘንድ የተለመደ ሆኗል:: ይህ ድርጊት ፆታና ዕድሜ አይለይም:: በአጠቃላይ ሲታይ ወንዶች ከሴቶች ቀደም ባለ ዕድሜ ቢጀምሩም ሴቶችም ከዚህ ተግባር ውጭ አይደሉም:: ጥናቱ በኛ ሀገር አይካሄድ እንጂ አንድ በአሜሪካን ሀገር የተደረገ ጥናታዊ ጽሑፍ እንደሚያመለክተው ከሆነ ከአጠቃላይ ወጣት ልጃገረዶች ሁለት ሦሥተኛው እጅ ከአጠቃላይ ወጣት ወንዶች ደግሞ ዘጠና አምስት በመቶ የሚሆኑ ወጣቶች የተለያየ ርዝማኔ ላላቸው ጊዜያት «በማስተርቤሽን› ልማድ ይያዛሉ፡፡ ይህ አኀዝ ለወንዶች ሙሉ በሙሉ እንደማለት ነው:: ከሁሉ የሚያስደንቀው በሰባዎቹ ውስጥ ከሚገኙ አሮጊቶች ሠላሳ ሦስት እጅ ከሽማግሌዎች ደግሞ አርባ ሦስት እጅ የሚሆኑት አሁንም በዚሁ የመሰንጋት (ራስን በራስ ማርካት) ተግባር ውስጥ መገኘታቸው ነው፡፡ (ኢንካርታ ብሪታኒካ ኢንሳይኮሎፒዲያ 2004) በኛም አገር ቁጥሩ ይህን ያህል አይጋነንን እንጂ ብዙ ወጣቶች በዚህ ክፉ ልማድ መመረዛቸው በተለያየ መንገድ ይሰማል:: ከዚህ የተነሣ አንዳንድ ሰዎች «ይህ ድርጊት ጤናማነትን ስለሚያመለክት የሚያሳስበው በዚህ መንገድ የማይጓዙ ሰዎች ሕይወት ነው» እስከ ማለት ደርስዋል::    በዓለም ላይ ሴጋን መፈጸም በብዙኀኑ ዘንድ የተለመደ በመሆኑ ብቻ ድርጊቱ እንደ ተገቢና ጤናማ የሰውነት ተግባር ሊቆጠር አይችልም፡፡ ወጣቶችም በዚህ ሐሳብ በመሳሳት በድርጊቱ የተለከፉ ከሆነ ለመላቀቅ ከመጣጠር ይልቅ «ለካ እኔ ብቻ አይደለሁም!» እያሉ መጽናናት አይገባቸውም:: ይህን ተግባር ሞክረውትም የማያውቁ ከሆነ ለመሞከር ከማነሣሣት ይልቅ ጨርሶ የዚህን ክፉ ኃጢአት ጣዕም አለመቅመስ በሕይወታቸው ያለውን ፋይዳ ተረድተው ከመሞክር መታቀብ ይኖርባቸዋል::    በዓለማችን መፋታት፣ ዝሙት፣ መግደል፣ ውርጃ፣ ባዕድ አምልኮ፣ ውሸትና መሥረቅ በብዙ ሰዎች ዘንድ የተለመዱ ናቸው፡፡ ታዲያ እነዚህ ተግባራት በብዙኀኑ ዘንድ መተግበራቸው ትክክል ቢሆኑ ነው እንጂ ያሰኛቸዋልን? ሴጋ መፈጸምም እንደዚሁ ነው:: ከላይ በፊደል «ሀ» እንደተጠቀሰው ሐሳብ ሁሉ ሰዎች ለክፉ ሥራቸው አጋር እንዳላቸው እያሰቡ እንዲጽናኑ ሰይጣን የዘረጋው የጥፋት ወጥመድ «ብዙዎች የሚፈጽሙት ከሆነ እንዴት ኃጢአት ይሆናል?» የሚል ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ግን «ብዙዎች ኃጢአት ሲሠሩ አይተህ ከእነሱ ጋር አትተባበር ይላል፡፡›› ዘፀ 23÷2 ሐ) ብዙ የሕክምና ባለሙያዎችና የሥነ አእምሮ ጠበብቶች «ክዕወተ ዘርዕ» ብዙ ዓይነት ሥነ ልቡናዊና አካላዊ የጤና ችግር እንደሚያስከትል በአንድ ልብ ይስማማሉ፡፡ እንዲያውም የብዙዎችን ጓዳ ከሚያንኳኳው ከ‹‹ስንፈተ ወሲብ› ጀምሮ የኩላሊትና የልብ በሽታዎች ድረስ በሴጋ አማካኝነት ሊመጡ እንደሚችሉ በሰፊው ተዘግቧል፡፡ ሆኖም ግን የዓለም ጠቢባን ቃላቸው ወጥነት የሚጎድለውና ተለዋዋጭ ነው:: ስለዚህ አንዱ የካበውን ሌላው ሲንደው ይታያል፡፡    <<የዓለም ጠቢባን ቃላቸው ወጥነት ይጎድለዋል>> ለሚለው ሐሳብ ማስረጃ የሚሆነው ብዙ ምሁራን «ሴ.ጋ» ወይም ‹‹ማስተርቤሽን› ለልዩ ልዩ በሽታ ያጋልጣል ሲሉ ሌሎች ደግሞ በጭራሽ አያጋልጥም ማለታቸው ነው:: እንዲያውም ከእነዚህ መካከል ጥቂቶቹ «ሴጋ» ወይም ‹‹ማስተርቤሽን›› ለአንዳንድ በሽታዎች የመጋለጥ ዕድልን ይቀንሳል ሲሉ ይደመጣል፡፡ ለምሳሌ:- በሀገራችን ከሚታተሙት በርካታ የግል ጋዜጦች አንዱ የሆነው ሜዲካል ጋዜጣ በ1995 በመጨረሻዎቹ ሁለት ወራት ውስጥ ካሳተማቸው ጋዜጦች በአንዱ ላይ ‹‹ማስተርቤሽን» በካንሠር የመያዝ ዕድልን እንደሚቀንስ ጥናታዊ መረጃዎችንና የባለሙያዎችን አስተያየት ጠቅሶ አስፍሯል፡፡    እንደ የሕክምና ባለሙያዎች ሁሉ የሥነ አእምሮ ጠበብቶችም «አንድ ሰው ሴጋ በመፈጸሙ ምክንያት ጉዳት ሊያገኘው የሚችለው የአእምሮና የስሜት መረበሽን የሚያስከትል የበደለኝነት ስሜት የሚሰማው ከሆነ ብቻ ነው» በማለት ይናገራሉ፡፡ ይሁን እንጂ ሐኪሞችና የሥነ አእምሮ ጠበብቶች እንደ ሌላው ሰው ሁሉ ለስሕተት የተጋለጡ፣ ደካማ ፍጡራንና ፍጽምና የሌላቸው በመሆናቸው አመለካከታቸው በየጊዜው ይለዋወጣል:: ማን ያውቃል? ዛሬ ጉዳት አያስከትልም ያሉትን ድርጊት ነገ አንድ ያልደረሱበትን ዕውቀት ሲያገኙ ጉዳት የሞላበት ነው ይሉት ይሆናል፡፡ ያን ጊዜ የዛሬ ቃላታቸውን ተቀብለው በክፉ ልማዱ ጸንቶ የተገኘ ወጣት መጨረሻው ምን ይሆን? በዓለም ጠቢባን ቃል ልቡን ከሚያሳርፍ ይልቅ በእግዚአብሔር ሕግና ሥርዓት ጸንቶ የሚኖር ሰው እንዴት የተመሰገነ ነው?    የዚህ መንፈሳዊ መጽሐፍ ዋና ዓላማ ዘርን በገዛ እጅ በማፍሰስ ስሜትን ለማርካት መሞከር ምን ያህል ወይም ምን ዓይነት የጤና መታወክ ይፈጥራል? የሚለውን ማብራራት ሳይሆን ምን ያህል? መንፈሳዊ ጉዳት ያስከትላል ለሚለው ጥያቄ በቂ ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው::    ምንም እንኳን ከዚህ በላይ ምንም ዓይነት የጤና ጉዳት እያስከትልም፡ ጉዳት የሚያስከትለው ድርጊቱን የሚፈጽመው ሰው የበደለኘነት ስሜት የሚሰማው ከሆነ ብቻ ነው::›› በሚል በባለሙያዎች የተሰነዘረው ሐሳብ አስተማማኝነት እንደሌለው ቢገለጽም በዚህ ክፉ ልማድ የተመረዙትንና እየተሳቡ ያሉትን ሰዎች ከድርጊታቸው እንዳይላቀቁ የሚጫወተው ሚና ግን እጅግ የከፋ ነው:: ምክንያቱም ይህ ሥራዬ የጤና መታወክ የሚፈጥርብኝ ስጸጸት ብቻ ከሆነ ጉዳት እንዳያስከትልብኝ ራሴን እንደ ጥፋተኛ እየቆጠርኩ መቆርቆር የለብኝም እያሉ እንዲጽናኑ ስለሚያደርጋቸው ነው::   በዚህ መልኩ በክፉ ሥራቸው እንዳይጸጸቱና እግዚአብሔር የሚያመጣባቸውን የቅጣት ፍርድ እያሰቡ እንዳይፈሩ በጤና ባለሙያዎችና በሥነ አእምሮ ጠበብቶች የተሰጣቸው ምክር ምንም ዓይነት ፍርሃተ እግዚአብሔር በልቡናቸው እንዳይኖር ያደርጋል፡፡ ይህ ደግሞ <<የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነውና›› በእግዚአብሔር ዘንድ የተጣሉና ረድኤት የሌላቸው እንዲሆኑ ከማድረጉም በላይ ከክፉ ሥራቸው እንዳይመለሱ ያደርጋል:: ምክንያቱም ሰው ከክፉ ሥራው የሚመለሰው በዋናነት ክፉ ሥራው የሚያስከትልበትን ፍርድ አስቦ ነውና፡፡ ምንም ክፉ ነገር አያገኝኽም እየተባለ በባለ ሙያ
Show all...
6👍 5
"ገብር ኄር" ቸር አገልጋይ ማነው ለንጉሥ የታመነ መክሊቱን ያልቀበረ አትርፎ የከበረ (፪) ባለ አምስቱ መክሊት መልካም ያደረገው በመውጣት በመውረድ አትርፎ መጥቶ ነው በጥቂቱ ታምኖ በብዙ የተሾመው ባለ አምስቱ መክሊት ሊቀ ጳጳሱ ነው። ሳይሰለች የተጋ ባለሁለት መክሊት የታመነ እረኛ በፍቅርና በእምነት ግባ የተባለው ወደ ጌታው ደስታ አጥምቆ ያቆርባል ካህኑ የጌታ። ለሚበልጠው ጸጋ ተጠርቶ የነበረ መክሊቱን ደብቆ ቆፍሮ የቀበረ ሰነፍ ባርያ ተብሎ ወደ ፍርድ ተጣለ ማኔ ቴቄል ፋሬስ በአምላክ ፊት ቀለለ። ፈቃድህን ማድረግ ነፍሱ ለምትወደው ወንጌልህን መግለፅ የየዕለት ግብሩ ነው ህግህ ለዘለላም ተጽፎ ይኖራል በታላቅ ጉባኤ ጽድቅህ ይነገራል።         በዘማሪ ዲያቆን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
22👍 5
ገብር ኄር የዐብይ ጾም ስድስተኛ እሑድ(ሳምንት) ይህን ሳምንት ቅድስት ቤተክርስቲያን ”ገብርኄር” የሚል ስያሜ ሰጥታዋለች፡፡ ገብርኄር በጎ አገልጋይ ማለት ሲሆን የስያሜውን መነሻ የምናገኘው በዕለቱ ሥርዓተ ቅዳሴ ከሚነበበው የወንጌል ክፍል ማቴ. 25:14-30 ነው፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምሳሌ መስሎ ካስተማራቸው ትምህርቶች መካከል አንዱ የሆነው ይህ የዛሬው ወንጌል አስተማሪ የሆኑ መሠረታዊ ጉዳዮችን በውስጡ ይዟል፡፡ በተለይ ምንም እንኳን የቤተክርስቲያን ሓላፊነት የእገሌና የእገሊት ተበሎ ባይወሰንም ቤተ ክርስቲያን ባላት የአገልግሎት መዋቅር መሠረት የሓላፊነትን ቦታ ይዘው ለሚያገለግሉ ሰዎች አትኩሮት ሊሰጡባቸው የሚገባቸውን ነጥቦች ይጠቁማል፡፡ ይህን ለማየት ያመቸን ዘንድ ከታሪኩ የመጀመያ ክፍል በመነሣት ዋና ዋና የሆኑ ዐሳቦችን በአትኩሮት መመርመር  ጠቃሚ ነው፡፡ በምሳሌያዊው ታሪክ መጀመሪያ ላይ የምናገኘው አንድ መንገድ ሊጀምር ያሰበ ሰው ከመሔዱ በፊት አገልጋዮቹን ጠርቶ ለእያንዳንዳቸው እንደ ችሎታቸው መጠን ለአንዱ አምስት ለአንዱ ሁለት እንዲሁም ለሌላኛው አንድ መክሊት ነግደው ያተርፉበት ዘንድ እንደሰጣቸው ነው፡፡ ገና ከታሪኩ መጀመሪያ እንደምንረዳው የአገልጋዮቹ ጌታ ምንም እንኳን እርሱ ለመንገድ ቢዘጋጅም ሀብቱ ግን በተዘጋ ቤት ውስጥ ተቆልፎበት እንዲቀመጥ አልፈለገም፡፡ በዚህም አገልጋዮቹን ጠርቶ ገንዘቡን በአደራ ተቀብለው እንዲያተርፉበት ማዘዙን እንደማስረጃ ልናቀርብ እንችላለን፡፡ ሆኖም ግን ማትረፍ በመፈለጉ ብቻ ገንዘቡን ያለአግባብ አልበተነም፡፡ ነገር ግን ለእርሱ ቀረቤታ የነበራቸውን አገልጋዮቹን ጠርቶ ያውም እንደየችሎታቸው መጠን ሓላፊነቱ ሳይከብዳቸው እንዲሠሩበት ገንዘቡን አከፋፈላቸው፡፡ ይህ ጌታ ቅንነትና ርኅራኄ የበዛለት እንደሆነ የሚያመላክተን ነገር አለ፡፡ ይኸውም ለአገልጋዮቹ ሓላፊነትን ቢሰጥም እንኳን ከእነርሱ ጋር በነበረው ቀረቤታ ማን ምን መሥራት ይችላል የሚለውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለእያንዳንዳቸው እንደ ሓላፊነት የመሸከም አቅማቸው አምስት ሁለት አንድ እያደረገ መስጠቱ ነው፡፡ ምናልባት ስስት ባልተላቀቀው ስሜት ለሚያስብ ሰው የዚህ ጌታ መክሊት አሰጣጥ አድልዎ ያለበት ሊመስለው ይችላል፡፡ ታሪኩን እስከ መጨረሻው ብንከታተለው ግን የሚያሳየን የባለ መክሊቱን ባለቤት ቅንነት ነው፡፡ ቀጥለን እንደምናነበው ይህ ጌታ ለአገልጋዮቹ አትርፉበት ብሎ መክሊቱን ሰጥቷቸው በሔደበት ሀገር አልቀረም፡፡ ይልቁንም እያንዳንዱ በተሰጣቸው መክሊት ምን እንደሠሩበት ሊቆጣጠራቸው እንደመጣ እናነባለን፡፡ ስለዚህ አገልጋዮቹ በሰጣቸው መክሊት ምን እንደሠሩ እንደሚጠይቃቸው እያወቀ ከአቅማቸው በላይ የሆነ መክሊትን በመስጠት ምን ሠርተው የተሰጣቸውን መክሊት ያህል ማትረፍ እንደሚችሉ በማሰብ እንዲጨነቁ አልፈለገም፡፡ በተቃራኒው የምናየው ያለምንም ጭንቀት ከአእምሯቸው በላይ ሳይሆን ባላቸው ኀይል ተጠቅመው መሥራትና ማትረፍ የሚችሉትን ያህል መክሊት እንደሰጣቸው ነው፡፡ ከብዙ ጊዜም በኋላ የእነዚያ አገልጋዮች ጌታ በሰጣቸው መክሊት ምን እንደሠሩበት ሊቆጣጠራቸው ሲመጣ አምስት መክሊት ተቀብሎ የነበረው ሌላ አምስት እንዲሁም ሁለት መክሊት ተቀብሎ የነበረው ሌላ ሁለት መክሊት አትርፎ ጌታቸው ፊት እንደቆሙ ያ ጌታም በእነዚህ አገልጋዮቹ ታማኝነት ተደስቶ ወደ ደስታው እንዳስገባቸው እናያለን፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ያ አንድ መክሊት ተቀብሎ የነበረው ምድርን ቆፍሮ ያተርፍባት ዘንድ የተሰጠችውን መክሊት እንደቀበረ ከዚህም አልፎ ምን አደረክባት ተብሎ ሲጠየቅ የአመጽ ንግግር እንደተናገረ በዚህ ከፊቱ ያዘነው ጌታውም ያን ክፉ አገልጋይ እንዲቀጣ እንዳደረገው አናነባለን፡፡ በዚህኛው ክፍል ከተጠቀሰው ታሪክ ሦስቱን አካላት ማለት የመክሊቱን ሰጪ ጌታ፣ በጎ የተባሉ አገልጋዮችና ክፉ እና ሰነፍ የተባለውን አገልጋይ በተናጥል እንመልከታቸው፡፡ 1. የአገልጋዮቹ ጌታ፡– ይህ ሰው ለገንዘቡ ጠንቃቃ ከመሆኑ ባሻገር በአገልጋዮቹ ላይ ሙሉ ሥልጣን እንዳለው እናያለን፡፡ በክፉው አገልጋይ ላይ ባለመታዘዙ ምክንያት የፈረደበትን ፍርድ /ልቅሶና ጥርስ ማፏጨት ወዳለበት በውጪ ወዳለ ጨለማ እንደአወጡት/ ስንመለከት የሚያሳየን የአገልጋዮቹን ጌታ ታላቅ ሥልጣን ነው፡፡ ምንም እንኳን ሥልጣኑ ጽኑ ቢሆንም ይህ ጌታ ፍርዱ ግን በእውነት ላይ የተመረኮዘ መሆኑን ደግሞ በድካማቸው ታግዘው በተሰጣቸው መክሊት ላተረፉት በጎ አገልጋዮች የሰጣቸውን ፍጹም ደስታ መጥቀስ ይቻላል፡፡ 2. በጎ አገልጋዮች:- በአገልጋዮቹ ጌታ በጎ አገልጋዮች የተባሉት አምስት መክሊት የተቀበለውና ሁለት መክሊት የተቀበለው ናቸው፡፡ እዚህ ጋር ማስተዋል የሚገባው እነዚህ ሁለቱ አገልጋዮች በጎ አገልጋዮች ለመባል ያበቃቸው አስቀድመው ብዙ ወይንም የተሻለ ቁጥር ያለው መክሊት ለመቀበል መብቃታቸው አይደለም፡፡ ጉዳዩ የመክሊቱ ቁጥር ሳይሆን በተሰጣቸው መክሊት መጠን የሚገባቸውን ያህል ደክመው ማትረፍ መቻላቸው ነው፡፡ ወይንም ያ ባለ አንድ መክሊት አገልጋይ ከሁለቱ ያሳነሰው ከአንድ በላይ መክሊት መቀበል የማይችል መሆኑ ሳይሆን በዚያችው በአንዷ መክሊት እንኳን መሥራት አለመቻሉ ነው፡፡ 3. ክፉና ሰነፍ አገልጋይ:- ይህ ሰው የተጠቀሱ ሦስት መሠረታዊ ችግሮች አሉበት፡፡ የአገልጋዮቹ ጌታ ወደ መንገድ ሊሔድ በተዘጋጀበት ወቅት አገልጋዮቹን ጠርቶ ለእያንዳንዳቸው እንደችሎታቸው ገንዘቡን ሲሰጣቸው አትርፈው እንዲቆዩት ነው፡፡ ከላይ እንደተነገጋገርነው እንደ አቅማቸው መስጠቱም አቅማቸው በሚፈቅደው የሥራ ደረጃ እንዲሰማሩ በማሰብ ነበር፡፡ ይህ ሰነፍ አገልጋይ ግን ያደረገው ከታዘዘበት ዓላማ በተቃራኒው መልኩ ነው፡፡ ሊሠራበት የሚገባውን መክሊት ቀበረው፡፡ ይህም ለጌታው ትዕዛዝ ያለውን ቸልተኝነት ያሳያል፡፡ ጌታው በመጣ ጊዜ አመጽ የተመላበት የሐሰት ንግግር ተናግሯል፡- ከሔደበት ቦታ ተመልሶ ጌታው በተሰጠው መክሊት ምን እንዳደረገ ሲጠይቀው «አንተ ካልዘራህበት የምታጭድ፣ ካልበተንህበትም የምትሰበሰብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንህ አውቃለሁ ስለፈራሁም ሔድሁና መክሊትህን በምድር ውስጥ ቀበርሁ፡፡» ሲል መለሰለት፡፡ ይህ ንግግር ከአመጽ ንግግርነቱ በተጨማሪ ውሸት አለበት፡፡ ምክንያቱም እርሱ እንዳለው ጌታው ካልዘራበት የሚያጭድ ካልበተነበት የሚሰበሰብ ጨካኝ ሰው ቢሆን ኖሮ ያደርግ የነበረው ምንም መክሊት ሳይሰጠው ከነትርፉ ሁለት መክሊቶችን ይጠይቀው ነበር፡፡ ነገር ግን ተጽፎ የምናነበው ትርፉን ከመጠየቅ በፊት አንድ መክሊት ሰጥቶት እንደበረ ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ አስቀድሞ ገንዘቡን ዘርቶ ነበር ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ይህ ጌታ ዘርቷልና ማጨድ ይገባዋል፤ በትኗልና መሰብሰብም መብቱ ነው፡፡ እርሱ መሥራት ሲሳነው እንኳን ዕድሉን ለሌሎች አልሰጠም፡- ይህ ሰው የተሰጠው መክሊት በትርፍ ሊመለስ እንደሚገባው ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ምክንያቱም ገና ሲቀበል ከጌታው የተቀበለው ትዕዛዝ ነውና፡፡ ስለዚህ ምንም እንኳን መውጣት መውረዱ ቢከብደውም ወጥተው ወርደው ማትረፍ ለሚችሉ ሰዎች አለመስጠቱ ተጨማሪ ጥፋቱ ነው፡፡ ይህን እንዳያደርግ ያሰረው ደግሞ ውስጡ የተቀረጸው የአመጽ መንፈስ ነው፡፡ ጌታው መጥቶ ስለ ትርፉ ሲጠይቀው የሚመልስለትን ረብ የለሽ ምክንያት እንደ መከላከያ አድርጎ ማሰቡ አእምሮው ሌላ አማራጭ እንዳያስብ የዘጋበት ይመስላል፡፡
Show all...
14👍 9
የመጽሐፍ ቅዱስ መተርጉማን አባቶች የዚህን ምሳሌያዊ ታሪክ ምስጢር ሲያስተምሩ የአገልጋዮቹ ጌታ የፍጡራን ጌታ የሆነ የእግዚአብሔር ምሳሌ እንደሆነ እንዲሁም ሦስቱ አገልጋዮች በተለያየ ደረጃ ያሉ ምዕመናንን እንደሚወክሉ ያስተምራሉ፡፡ ከዚህ የወንጌል ክፍል ምን እንማራለን? ከተጠቀሰው ታሪክ የምንማራቸው ብዙ ነገሮች ቢኖሩም ዓበይት የሆኑትን ሁለቱን እንመልከታቸው፡፡ ለእያንዳንዳችን ከእግዚአብሔር የተሰጠ ስጦታ እንዳለ እንረዳበታለን እግዚአብሔር እያንዳንዳችን በሃይማኖት ሆነን የምናፈራውን ፍሬ ይፈልጋል፡፡ ምንም እንኳን ከእኛ ፍሬን ቢፈልግም ያን ፍሬ ማፍራት የምንችልበትን ኃይል ግን የእግዚአብሔርን ልጅነት ካገኘንበት ከዕለተ ጥምቀት ጀምሮ እንደሚያስፈልገን መጠን እየሰጠን ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቀበልናቸው ስጦታዎች በቁጥር እጅግ ብዙ ቢሆኑም በዓይነታቸው ግን ለሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ የመጀመሪያው እያንዳንዱ ክርስቲያን ዳግመኛ በመወለድ ምስጢር ያገኘው የእግዚአብሔር ልጅነት ጸጋና ከልጅነት ጋር በተያያዘ የሚሰጡ ስጦታዎች ናቸው (ዮሐ.3፥3)። ሁለተኛው ዓይነት ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድና እንደ ሰውየው አቅም ለተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች ማስፈፀሚያ ይሆኑ ዘንድ በእግዚአብሔር የሚሰጡ ስጦታዎች ናቸው፡፡ ለምሳሌ ትንቢት መናገር ፣ በተለያዩ ልሳናት መናገር ፣ አጋንንትን ማስወጣት … የመሳሰሉት ከዚህኛው ዓይነት ስጦታ የሚመደቡ ናቸው (1ኛ ቆሮ.12፥4)፡፡ በመጀመሪያውም ይሁን በሁለተኛው ዓይነት ስጦታ ተቀባዮች ዘንድ ግን ብዙ የሚያሳዝኑ ችግሮች አሉ፡፡ በዳግመኛ መወለድ ምሥጢር (በ40 ና 80 ቀን ጥምቀት) ስላገኘነው የልጅነት ጸጋ ጊዜ ሰጥቶ የሚያስብ ክርስቲያን ማግኘት በዚህ ዘመን በጣም አዳጋች ነው፡፡ በዓመት ውስጥ ክርስቲያንነቱ ለጥምቀት በዓልና ለመስቀል ደመራ ካልሆነ ትዝ የማይለው ቁጥሩ ቀላል አይደለም፡፡ ከዚህ የከፋው ደግሞ ከቤተ ዘመድ አንድ ሰው ምናልባትም ራሱም ሊሆን ይችላል ነፍሱ ከሥጋው ካልተለየች ወደ ቤተ ክርስቲያን ደጅ ብቅ አይልም፡፡ እግዚአብሔር ለእኛ የልጅነትን ጸጋ በመስጠቱ ለእኛ ያለውን ጥልቅ ፍቅሩን አሳይቶናል፡፡ ምክንያቱም ልጅነታችን ዋጋ ተከፍሎበታልና፡፡ እንዲሁ በቀላሉ አይደለም ልጆች የተባልነው፡፡ እኛ ልጅነትን እንድንቀበል አምላክ መከራን ተቀብሏል፡፡ የጥምቀታችን ውሃ የፈሰሰው በጦር ከተወጋው ከጌታ ጎን ነው (ዮሐ.19፥24)፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ይሄንን ሁሉ ሲያመለክት ”የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደሰጠን እዩ፡፡” (1ኛ ዮሐ.3-1) እኛ ልጆቹ እንሆን ዘንድ እግዚአብሔር ካሳየን የአባትነት ፍቅር በተጨማሪ ልጆቹ ስለመሆናችን የገባልንም ተስፋ ከአዕምሮ በላይ ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለገላትያ ምዕመናን በላከው መልእክቱ ”እንኪያስ እናንተ ልጆች ናችሁ እንጂ ባሮች አይደላችሁም፡፡ ልጆች ከሆናችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሾች ናችሁ፡፡” (ገላ.4:7) በማለት  ስለሚጠብቀን ተስፋ ነግሮናል፡፡ ስለዚህ በጣም ልንጠነቀቅበት የሚገባን የመጀመሪያው መክሊታችን ልጅነታችን መሆኑን መረዳት ያስፈልገናል፡፡ በዚህም መክሊት እንድንሰራ የታዘዝናቸውን ምግባራት እንድናፈራ የሚጠበቅብንን ፍሬዎች ማፍራት አለብን፡፡ ያለበለዚያ መክሊቱን እንደቀበረው ሰው መሆናችን ነው፡፡ እያንዳንዱ ስጦታ እንደሚያስጠይቅ እንረዳለን እግዚአብሔር ያለ አንድ አላማ ለሰዎች ሓላፊነትን የሚያሰከትል ስጦታ አልሰጠም አይሰጥምም፡፡ ማንም ከእግዚአብሔር የተቀበለ ሰው የተሰጠው ስጦታ ለሆነ አላማ ነውና ጥያቄ አለበት፡፡ ጠያቂው ደግሞ የስጦታው ባለቤት ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ ስለዚህ ማንም ይሁን ማን ግን ስለተሰጠው መክሊት ባለቤቱ ከፊቱ አቁሞ እንደሚጠይቀው መዘንጋት የለበትም፡፡እንግዲህ በአጠቃላይ መክሊት የተባለ ጸጋ ስጦታ ሲሆን እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን የተለያየ ስጦታ ሰጥቶናል፡፡ በተሰጠንም ስጦታ ልናገለግልበት ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪ መክሊት ቃለ እግዚአብሔር ነው፡፡ የሰማናትን ቃለ እግዚአብሔር ለሌላው ማሰማት ይገባናል ፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው ማሰማቱ ብቻ ነው፡፡ በልቦናው አድሮ ሥራ የሚሠራ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነውና፡፡ በመሆኑም እርሱ በሰጠን የአገልግሎት በር ጸጋ በታማኝነት በማገልገል በሕይወት ዘመናችን ሁሉ መንፈሳዊውን ሀብት የምናተርፍ እንሆን ዘንድ የተላለፈልን አምላካዊ ምክር ነው፡፡ ምክንያቱም እኛ የተጠራነው ፍሬ ልናፈራና ሌላውንም ልናተርፍ መልካም ሥራን ልንሠራ እንጂ የሥጋችንን ፈቃድ በመከተል የኃጢአት ባሮች ልንሆን አይደለም፡፡ መጽሐፍ እንደሚነግረን  ¨ሁሉ እንደተጠራ እንዲሁ ይኑር” (፩ኛ ቆሮ. ፯፥፳) ይላልና። አሁን ባለንበት ወቅት በጎና ታማኝ አገልጋይ መሆን እንዳንችል ብዙ ችግሮች አሉ፡፡ የችግሮቹም መሠረታዊ ምንጭ በተጠሩበት ጸንቶ መቆም ፈጽሞ አለመቻልና ለሥጋዊ ጥቅም ብቻ በማድላት ሓላፊነትን መዘንጋት ናቸው፡፡ በሥጋዊ አምሮት ፍላጎትና ምርጫ ውስጥ ደግሞ መንፈሳዊ ጸጋንና በረከትን ለማግኘት የሚያስችለንን የታማኝነት ሥራን መሥራት አይቻልምና በታማኝነት ከምናድነው ሰው ይልቅ መክሊታችንን በመቅበር ባለመታመን መሰናክል የምንሆንበት ሰው ሊበዛ እንደሚችል አያጠራጥርም፡፡ በመሆኑም ከእርሱ ዘንድ እንደ ዓቅማችን የተሰጠንን መንፈሳዊ ዕውቀት ሀብትና አገልግሎት ለሌላው በማድረስ መክሊታችንን ልናበዛ የምንችለውና አገልግሎታችን ወይም ክርስትናችን ውጤታማ የሚሆነው ምርጫችንን አውቀን እንደቃሉ ሆነንና ጸንተን ስንገኝ ብቻ ነው፡፡ ይህ ባለመሆኑ ነው ዛሬ ብዙዎቻችን በሕይወታችን ሌላውን ማትረፍ አቅቶን በእግዚአብሔርና በሰውም ዘንድ በሚያስወቅስ የስንፍና መንገድ ላይ ቆመን የምንገኘው፡፡ ስለዚህም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው “ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ” (ማቴ. ፳፬፥፵፪) ብሎናል፡፡ ቃሉን የሰማንና የምናውቅ ሁላችን በሞቱ ላዳነን፣ በልጅነት ጸጋም ላከበረን፣ በትንሣኤውም ላረጋጋን፣ በመስቀሉ ጥልን ገድሎ ከራሱ ጋር ላስታረቀን፣ በውኂዘ ደሙም ሕይወትን፣ ሰላምን፣ ፍቅርን፣ በረከትንና ዘለዓለማዊ ደስታን ለሰጠን አምላካችን በመታዘዝ አቅማችን በሚፈቅደው አገልግሎት ጸንቶ መገኘት ተገቢ ነው፡፡ በአገልግሎት የመጽናት ምልክቱ ደግሞ አትራፊነት ነው፡፡ ቅዱሳን ነቢያት፣ ቅዱሳን ሐዋርያት፣ ቅዱሳን ሊቃውንት በቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ በአትራፊነት ይታወቃሉ፡፡ ለማትረፍ ግን ራሳቸውን ለእውነት ለአገልግሎት ለመከራ አሳልፈው በመስጠት ነው፤ በትንሹ መታመን ሲባል የእኛ አገልግሎት ከፈጣሪ ቸርነት ጋር ስለማይመጣጠን ነው፤ በብዙ እሾምሃለሁ ማለቱም በመንግሥተ ሰማያት ለዘለዓለም ከብሮ መኖርን ነው፡፡ ከቅዱሳን ነቢያትም ሐዋርያትም ሰብአ አርድእትም ሊቃውንትም የሰማነውና ያየነው እውነት ምንጊዜም ትጉህ ሠራተኛ የሚሠራው መልካም ሥራ ሁሉ ለቤተ ክርስቲያንም ለሀገርም የሚሰጠው ጥቅም እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ ዘመን ልዑል እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን፤ ምእመናንን፤ ሀገርንና ሕዝብን ለመምራት የጠራንና የመረጠን፤ በአገልግሎት ዐደባባይ ያስቀመጠን ሰዎች እጅግ ዕድለኞች ነን፤ ምክንያቱም የሕዝብን ችግርና አቤቱታ ሰምቶ ተቀብሎ መፍትሔ መስጠት ትርፋማነት ነውና፤ ትርፋማነት ደግሞ ወደ ትልቁ የሹመት መሰላል መውጣት ነው፤ ይህ ሳይሆን ቀርቶ አገልግሎታችን ተደናቅፎ የሕዝባችን ችግር ሳይፈታ ቀርቶ የአገልግሎታችን ተቆጣጣሪ አምላካችን ቢጎበኘን “አንተ ሰነፍ አገልጋይ”
Show all...
6👍 4
ተብለን ወደ ውርደት አዘቅት እንዳንላክ መጠንቀቁ አይከፋም፡፡ የመሾም የመሻር የማሳደግና የማውረድ ሥልጣን የእግዚአብሔር ነውና፡፡ “ከእናንተ መካከል አንዱን እንኳ እንዳናስቸግር ቀንም ሌሊትም እንሠራ ነበር” (፩ኛ ተሰ. ፪፥፱) በጎና ታማኝ አገልጋዮች ሆነን እንድንገኝ ጠንክረን ልንሠራ ይገባናል፡፡  በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ ጥቅሶች፦ -፪ኛ ጢሞ ፪፥፩-፲፮ -፩ኛ ጴጥ ፭፥፩-፲፪ -የሐዋ ሥራ ፩፥፮-፱ ምስባኩም፦ መዝ ፴፱፥፰ "ከመ እግበር ፈቃድከ መከርኩ አምላኪየ ወሕግከኒ በማዕከለ ከርሥየ ጽድቀከ በማኅበር ዐቢይ" "አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድኩ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው በታላቅ ጉባዔ ጽድቅህን አወራሁ" ወንጌሉም፦ ማቴ ፳፭፥፲፬-፴፩ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
4👍 2
<<የተዋሕዶ ልጆች>> ብዙ የሚተረፍበት አዲስ ኦርቶዶክሳዊ ቻናል በልዩ አቀራረብ፤ ተቀላቀሉ። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/Ethiop_tewahido https://t.me/Ethiop_tewahido https://t.me/Ethiop_tewahido
Show all...
👍 4👏 3
"ኃይልህ ሲገለጽ በሰማይ" በሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ           ኃይልህ ሲገለጽ በሰማይ(፪) አቤት ማን ይቆም ይሆን ከፊትህ ማን ይቆም ይሆን አቤት ቀንደመለከት ሲነፋ አዋጅ ሲታወጅ በይፋ ጻድቃን ሲጠሩ ለተድላ ምን ይሆን የእኛ ተስፋ አዝ____ አቤት መላእክት ሰማዩን ሲያርሱት ቀድመው ሲሰሙ መባርቅት ያልታየና ያልተሰማ ድምጽ ሲሰማ ከራማ አዝ____ አቤት ሰባቱ ነፋስ ተከፍተው ምድርን ሲያውኩት ቀስፈው ሲታዘዝ የባህር ሞገድ ምድሪቱን ሊከድናት ለፍርድ አዝ____ አቤት ሲጠሩ ጻድቃን ቅዱሳን መልካም የሠሩ ብሩካን በምድር የሠሩት ትሩፋት ሲያቀርቡ ለአምላክ ስብሐት አዝ____ አቤት ኃጥአን ለፍርድ ሲጠሩ በጨለማ ዓለም ሊቀሩ የማይጠቅም ዋይታ ሆኖ መዋረድ ይሆናል አስሉ አዝ____ አቤት ሲጠሩ ጻድቃን ቅዱሳን መልካም የሠሩ ብሩካን በምድር የሠሩት ትሩፋት ሲያሰሙ ለአምላክ ስብሐት   " አምላካችን ይመጣል "            መዝ፶፥፫ ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥ የተዋሕዶ ልጆች @Ethiop_tewahido
Show all...
19👍 11😢 7🙏 3
"ኃይልህ ሲገለጽ በሰማይ" በሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ           ኃይልህ ሲገለጽ በሰማይ(፪) አቤት ማን ይቆም ይሆን ከፊትህ ማን ይቆም ይሆን አቤት ቀንደመለከት ሲነፋ አዋጅ ሲታወጅ በይፋ ጻድቃን ሲጠሩ ለተድላ ምን ይሆን የእኛ ተስፋ አዝ____ አቤት መላእክት ሰማዩን ሲያርሱት ቀድመው ሲሰሙ መባርቅት ያልታየና ያልተሰማ ድምጽ ሲሰማ ከራማ አዝ____ አቤት ሰባቱ ነፋስ ተከፍተው ምድርን ሲያውኩት ቀስፈው ሲታዘዝ የባህር ሞገድ ምድሪቱን ሊከድናት ለፍርድ አዝ____ አቤት ሲጠሩ ጻድቃን ቅዱሳን መልካም የሠሩ ብሩካን በምድር የሠሩት ትሩፋት ሲያቀርቡ ለአምላክ ስብሐት አዝ____ አቤት ኃጥአን ለፍርድ ሲጠሩ በጨለማ ዓለም ሊቀሩ የማይጠቅም ዋይታ ሆኖ መዋረድ ይሆናል አስሉ አዝ____ አቤት ሲጠሩ ጻድቃን ቅዱሳን መልካም የሠሩ ብሩካን በምድር የሠሩት ትሩፋት ሲያሰሙ ለአምላክ ስብሐት   " አምላካችን ይመጣል "            መዝ፶፥፫ ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥ የተዋሕዶ ልጆች @Ethiop_tewahido
Show all...
   ይህ ርኩስ መንፈስ ለመጀመሪያ ማሳከክ ሲጀምርና ሰውነትህን እንድትደባብስ ሲያደርግ ከሕዋሳቶችህ የሚመርጠው የለም:: «ወቦ አመ ይበውእ ውስተ አዕይንት፣ ወአዕዛን፣ ወውስተ አእናፍ፣ ወከናፍር፣ ወይሬስዮ ይሕሲ በእደዊሁ» ማለትም «ወደ ዓይን፣ ወደ አፍንጫ፣ ወደ ከንፈር ይገባል፡፡ በእጁም እንዲያሽ ያደርገዋል::» ይህ ሁሉ ሲሆን ሰውዬው የሰይጣን ፈተና መሆኑን ካልተረዳ እንዲያው እንዳሳከከው ወይም ሰውነቱ እንደቆሸሸ ያስባል፡፡ ገፋ ካለም እንደ በሽታ ይቆጥረውና ሐኪም ዘንድ ይሄዳል:: ሁሌም ባይሆን ብዙ ጊዜ የደም መቆሸሽ፣ አለርጂ የሚል ስም የሚሰጣቸው ይህን የመሳሰሉ የሰይጣን ፈተናዎች ናቸው:: ከሁሉ የሚገርመው ይህን ለመሳሰሉና ሐኪሞች በበሽታነት ለሚያውቋቸው ብዙ ፈተናዎች ከምክር፣ ከመጠነኛ ማስታገሻና ከጥንቃቄ በቀር ምንም ዓይነት መድኃኒት አለመገኘቱ ነው፡፡ ችግሩ በቆዳና በሰውነት ላይ በጉልህ ስለሚታይ ሐኪሞች በሽታውን ያውቁታል፡፡ መንሥኤው ግን ርኩስ መንፈስ በመሆኑ መድኃኒቱን አያውቁትም ለምን ቢባል ለርኩስ መንፈስ መድኀኒቱ መንፈሳዊ ነገር እንጂ በሐኪም ቅመማ የተገኘ መድኃኒት አይደለምና:: እርግጥ ነው ይህ ሐሳብ በሕክምና ባለሙያዎች ዘንድ አንድምታ ሊኖረውና ብዙ ትችትም ሊደርስበት ይችላል፡፡ ነገር ግን አንድ መረሳት የሌለበት ነገር እነርሱ የሚታየውንና የዓለሙን ጥበብ ያወራሉ:: እኛ ግን የማይታየውንና ሰማያዊውን ጥበብ እንናገራለን፡፡ ልዩነቱ ይህ ነው በቃ! ከላይ በተገለጸው መልኩ ፈተናውን ሰውነትን በማሳከክ የጀመረው ሰይጣነ ዝሙት ዓላማውን ከግብ ለማድረስ በዚህ ብቻ አይወሰንም:: እንደ መጽሐፈ መነኮሳት ገለጻ ወደ አባለ ዘሩም ይሄድና ያን ሰው ያለመጠን እንዲያክ ያደርገዋል:: ማከክ በሚጀምርበት ጊዜም ዕረፍት ከማግኘት ይልቅ ማሳክክ እየባሰና እየጨመረ ይሄድበታል፡፡ ይህ ሐሳብ በዚህ መልክ ቁልጭ ብሎ ተጽፏል:- «ወዓዲ ይወርድ ዲበ እስኪት ወቁልህ ወይሬስዮ ይህክክ እንበለ ምሒክ።» ትርጓሜው «ዳግመኛም ወደ አባለ ዘርዕ ይወርዳል:: ያለ ርኅራኄም እንዲያክ ያደርገዋል» ማለት ነው፡፡ ይህ ሰይጣነ ዝሙት ያንን ሰው በዝሙት ሐሳብ ተስቦ በዚህ መልኩ ብልቱን እያሻሸ ዘሩን እስኪያፈስ ድረስ ዕረፍት ሳይሰጠው ፈተናውን ይቀጥላል፡፡ በዚህ ዓይነት የዝሙት ዝንባሌ ተይዞ ከእንቅልፍ ውጭ ዘርን እያወቁ ወደ ውጭ ማፍሰስ «ግብረ አውናን›› ይባላል፡፡ «ግብረ አውናን›› የተባለበት ምክንያት አውናን የተባለው ሰው ከሚስቱ ጋር ተኝቶ ሳለ ዘሩን ከሚስቱ ማኅፀን ውጭ ያፈሰው ስለ ነበረ ነው፡፡ ዝሙትን ወዶ ክቡር ዘርን የትም ማፍሰስና የአውናን ዘሩን ከማኅፀን ውጭ ማፍሰስ አንድ ናቸውና:: ዘፍ 38፥9 ይህን ተግባር መንፈሳዊያን መጻሕፍት «ክዒወ ዘርዕ» በማለት ይጠሩታል፡፡ በብዙ የሀገራችን ወጣቶች ዘንድ በአማርኛው «ሴጋ» ወይም ‹‹መሰንጋት» በሚል ሲታወቅ አንዳንዶች ደግሞ በነገረ አፍርንጅ «Masturbation/ማስተርቤሽን» በማለት ይጠሩታል፡፡ «ግብረ አውናን›› ተገቢ ነውን? ግብረ አውናንን በመጽሐፍ ቅዱስ ስንመዝነው ተገቢ ነገር አለመሆኑን እንረዳለን፡፡ አንድ ገበሬ ለዘር የሚያስቀረው ዘር ራሱ ከሚመገበው እንኳን የተሻለውን ምርጥ ዘር ነው፡፡ ስለሆነም ከዘር ወቅት በፊት ተጠንቀቆ በሪቅ (በጐተራ) ያስቀምጠዋል:: በዘር ወቅት ደግሞ አውጥቶ በመልካም ማሳ ላይ ይዘራዋል እንጂ ያለ ቦታው አይበትነውም፡፡ እንደዚሁም ሁሉ የሰው ዘር ከእህል ዘር ይከብራልና በመልካም ጎተራ ማለትም በሰውነት ተጠብቆ መቆየት አለበት፡፡ ከጋብቻ በኋላ ባልና ሚስት ሩካቤ ሲፈጽሙ ደግሞ በመልካሟ ማሳ በሚስት ማኅፀን መዝራት እንጂ በልዩ ልዩ ምክንያት ሆን ብሎ ዘርን እንደ ጉድፍ ከማኅፀን በአፍኣ ማፍሰስ ከባድ ኃጢአት ነው፡፡ (ትዳርና ተላጽቆ ምዕ 7) የሰው ዘር ክቡር በመሆኑ ዘራቸውን በሜዳ ከሚያፈሱ ሰዎች ይልቅ ሰው የመሆን ዕድል የነበራቸው ነገር ግን በየሜዳው ፈሰው የቀሩት ዘሮች የተሻሉ ናቸው፡፡ ምክንያቱም አፍሳሾቹ ከሕገ እግዚአብሔር ወጥተው በኃጢአት ሲኖሩ ፈሰው የቀሩት ዘሮች ግን ምንም ካለመበደላቸውም ባሻገር ቢወለዱ ኖሮ ጳጳስና ንጉሥ የመሆን ዕድል ሊኖራቸው ስለሚችል ነው፡፡ እንዲህ ስለሆነ ዘራቸውን ያፈስሱ የነበሩ ሰዎችን ላፈሰሱት ዘር ራሳቸውን ቤዛ በማድረግ እግዚአብሔር ጊዜ ሳይሰጥ ቀሥፏቸዋል:: እግዚአብሔር እንዲህ በማድረጉ ዘርን ማፍሰስ እንደማይገባና የሰው ዘር ክቡር መሆኑን አስረድቷል፡፡ ዘፍ 38፥9-10 (ትዳርና ተላጽቆ ምዕ 7) አውናን የተባለው ሰው ዘሩን ከማኀፀን ውጭ በማፍሰሱ ምክንያት የደረሰበትን መቅሠፍት መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይተርከዋል፡፡ «አውናንም ዘሩ ለእርሱ እንዳይሆን አወቀ ወደ ወንድሙ ሚስት በገባ ጊዜ ለወንድሙ ዘር እንዳይሰጥ ዘሩን በምድር ያፈሰው ነበር፡፡ ይህም ሥራው በእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ ሆነበት:: እርሱንም ደግሞ ቀሠፈው።» ዘፍ 38፥9-10 ይህ ታሪክ በማንኛውም ምክንያት ከዓዌ ዘርዕ (ዘር አፍሳሽ) መሆን ሊያስቀሥፍ የሚችል ክፉ ሥራ መሆኑን ይገልጻል፡፡ ሰውነትን በመደባበስና ዘርን በማፍስስ ለመርካት መሞክር ተገቢ አለመሆኑን የሚያስረዱ በልዩ ልዩ አገባብ የተጠቀሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ይገኛሉ:: ለምሳሌ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ የጻፈው ክታብ እንዲህ ይላል፡፡ «እንግዲህ በምድር ያሉትን ብልቶቻችሁን ግደሉ እነዚህም ዝሙትና ርኩሰት፣ ፍትወትም ክፉ ምኞትም፣ ጣኦትንም ማምለክ የሆነ መጎምጀት ነው፡፡» ቆላ 3፥5 እዚህ ላይ «ብልቶቻቸሁን ግደሉ» ሲል ቆርጣችሁ ጣሏቸው ማለቱ ሳይሆን አትቀስቅሱ ማለት ነው፡፡ ታዲያ ዘርን በማፍሰስ ለመርካት ብልትን እየነካኩ ማነሣሣት «ብልቶቻችሁን ግደሉ» ከሚለው የሐዋርያው ትእዛዝ ጋር በቀጥታ የሚቃረን አይደለምን? ዘርን ማፍሰስ ከጣዖት አምልኮ፣ ከክፉ ምኞት፣ ከርኩሰት፣ ከመጐምጀት ጋር ተሰልፎ እየተቆጠረ እንዴት ተገቢ ሊሆን ይችላል? ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ደንዝዘውም በመመኘት ርኩሰትን ሁሉ ለማድረግ ራሳቸውን ወደ ሴሰኝነት አሳልፈው ሰጡ።» በማለት የተናገረው ቃል ግብረ አውናንን ለሚፈጽሙ ሰዎች ሊጠቀስ ይችላል:: ኤፌ 4፥19 ምክንያቱም ሴጋ ዝሙትንና ርኩሰትን የመመኘት ዝንባሌ ዋና መገለጫ ነውና፡፡ አስቀድም እንደ ተገለጸውም የመጐምጀት፣ የስግብግብነት፣ የርኩሰት፣ የራስ ወዳድነትና ለሥጋ ማደርንም የሚያመለክት ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በፍትወት ለተቃጠሉ ሰዎች መፍትሔ ሲሰጥ «በምኞት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና ራሳቸውን መግዛት ባይችሉ ያግቡ» ብሏል:: 1ቆሮ 7፥9 ስለዚህ «በዝሙት ለሚቃጠለ» መፍትሔው ማግባት እንጂ መሰንጋት (ሴጋ መፈጸም) አይደለም:: መሰንጋት በምንም መንገድ እንደ መፍትሔ ሊቆጠር አይችልም:: ሐዋርያው ማግባትን እንጂ ግብረ አውናንን እንደ መፍትሔ አድርጐ አልመከረምና፡፡ አምላካችን ሥጋ የፍትወቱን ያህል አግኝቶ እንዲረካ ጋብቻን ሲያሰናዳ ከጋብቻ ጋር አብረው የሚሄዱትንም ኃላፊነቶች ከመቀበልና ከመሸከም ጋር ነው፡፡ ነገር ግን ዘርን በማፍሰስ ራስን በራስ ለማርካት መሞከር ያለ ዋጋ ማለትም ምንም ዓይነት ኃላፊነት ሳይሸከሙ ያንን እርካታ ለማግኘት እንደመሞከር ይቆጠራል፡፡ ይህ ደግሞ የራስ ያልሆነን ነገር ለማግኘት መሞከር እንደመሆኑ መጠን የሚወገዝ እንጂ እንደ ተገቢ ነገር ሊበረታታ አይገባውም፡፡
Show all...
👍 14 9
የምኞት ቃጠሎን ዘርን በማፍሰስ ለማብረድ መሞከር ስሕተት ነው:: ምክንያቱም አንድ ችግር ሲያጋጥም ተቋቁሞ በማለፍ ፈንታ በተሳሳተ ጐዳና በመጓዝ ችግሩን ለማምለጥ መሞከር ሽንፈትንና ደካማነትን የሚያመለክት በመሆኑ ነው:: ይህን ዓይነት አካሄድ የተለማመደ አንድ ወጣት ችግሮችን እንደ አመጣጣቸው ከመመከት ይልቅ ሌላ የተሳሳተ አቋራጭ ሲማትር ይገኛል። በዚህ ምክንያት ብዙ ወጣቶች ላለመማራቸውና ለሥራ አጥነታቸው ወይም በሕይወታቸው ለገጠማቸው አንድ ችግር ተገቢና ጤናማ መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ ዱርዬነትን፣ ሌብነትን፣ ሰካራምነትን፣ ሲጋራ ማጨስንና፣ ጫት መቃምን እንደ አማራጭ ይወስዳሉ፡፡ ታዲያ ይህ የሽንፈትና የደካማነት ምልክት አይደለምን? ፍትወት ሲያስቸግር ራስን በራስ ለማርካት መሞክርስ ከእነዚህ በምን ይለያል?   አንዳንድ ሰዎች «አንድ ሰው ጋብቻ ለመመሥረተ ዕድሜው ያልደረሰ ወይም ሌሎች ችግሮች ያሉበት ከሆነ የጋብቻ ጊዜውን እየተጠባበቀ በዝሙትና በሰዶማዊ ተግባር ከሚሰነካከል ራሱን በራሱ በማርካት ተግባር ቢቆይ አይሻልም?>> እስከ ማለት ደርሰው ግብረ አውናንን ተገቢ ነገር ለማስመሰል ይጥራሉ፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ሕሊናችን ቢመስለውም ግብረ አውናንን ከግብረ ሰዶምና ከዝሙት አሳንሶ የማየት ስልጣን የለንም፡፡ ሁሉም የዝሙት ልዩ ልዩ ገጽታዎች ሲሆኑ በየትኛውም ዓይነት ኃጢአት መሰነካክል የፈጣሪን ሕግ መሻር ነው፡፡ ከሕግጋት ደግሞ አንዱን ማሳነስ ሌላውን ማተለቅ ለሰው አልተሰጠውም:: ማቴ 5፥19 ሰይጣንም ቢሆን ሐሳቡ እስኪፈጸምለት ድረስ በትንሽነቷ ንቀን እንድንፈጽማት ከግብረ ሰዶምና ከዝሙት ታንሳለች በማለት ያሳስበናል እንጂ በዚሁ ኃጢአት የተያዙትን ሰዎች ደግሞ ያልሠሩትን ግብረ ሰዶምና ዝሙት እንዲሠሩለት «አንደኛውኑ ዝሙት ይሻላል፣ ይህን የመሰለ ኃጢአት እየፈጸምህ ዝሙት አልሠራውም ለማለት ነውን?» እያለ ተስፋ ለማስቆረጥ እንደሚያምታታቸው መዘንጋት የለብንም፡፡ ትንሽ ናት ብለህ የምትንቃት ከሆነ መናቅህን ከእርሷ በመለየት አሳይ! ልትለያት ወደህ ከእርሷ መራቅ ካቃተህ ትንሽ ናት ማለትህ የአፍ ብቻ አይሆንምን? በመጨረሻም ከላይ በተዘረዘሩት ዙሪያ ገብ ነጥቦች ግብረ አውናንን ስንመረምረው ክርስቲያኖች ሁሉ ሊጸየፉት የሚገባ እኩይ ምግባር መሆኑን እንረዳለን፡፡ በቀጣይ ምዕራፍ አራት ክፍል ሁለት፦ «ግብረ አውናን»ን በተመለከተ አሳሳች ሐሳቦች በሚል ይቀጥላል.... @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
32👍 15👏 3😱 2😢 2🔥 1
👍 15 2😢 1
ሰይጣነ ዝሙት የሰው ልጆችን የሚፈትንበት መንገድ ረቂቅና ልዩ ልዩ ነው:: አንዳንዶቹ የፈተና ስልቶች ፈጽሞ ከዝሙት ጋር ምንም ግንኙነት ያላቸው አይመስሉም፡፡ ፍጻሜያቸውን ከልብ ያስተዋለ ሰው ግን ረቂቅና ቀጥተኛ ዝምድና እንዳላቸው ለመረዳት ይችላል፡፡ ፆር የለመዱ (የሰይጣንን የፈተና ስልት በደንብ ለይተው ያውቁ) አበው ቅዱሳን ግን ሽንገላ የሞላበትን የሰይጣንን የፈተና አሸንክላ ምን እንደሚመስል መጪ ትውልድ እንዲያውቀው በሕይወታቸው ያዩትንና መንፈስ ቅዱስ ያቀበላቸውን ጽፈው አስቀምጠዋል፡፡ ለምሳሌ:- ሰይጣነ ዝሙት የሰውን ልጅ ወደ ዝሙት ተግባር ከሚስብባቸው መንገዶች አንዱና ዋነኛው ገሢሥ ነው:: ገሢሥ ማለት ማሻሸት፣ መነካካት፣ መዳበስ ማለት ነው፡፡ ነቢዩ ሕዝቅኤል «ወከዐዉ ዝንየቶሙ ዲቤሃ>> ማለትም «ግልሙትናቸውንም አፍስሰውባት ነበር» በማለት እንደተናገረው ለዘር የደረሱ ወንዶች ከሴቶች ጋር ሲላፉና ሲዳሩ ሩካቤ ሳይፈጽሙ ዘራቸው የሚፈስበት ጊዜ አለ፡፡ ሕዝ23፥8 ይህንን ድርጊት እንደ ተድላ በመቁጠር ብዙ ወጣቶች ሆን ብለው ያደርጉታል:: በቅዱስ መጽሐፍ «የድንግልናዋንም ጡቶች ዳብሰው ነበር» እንደ ተባለው ቦታ ሳይመርጡና ሰው ሳይለዩ የሴት ልጅን ገላ በመዳበስ «ግልሙትናን ማፍሰስ›› እንዴት ያሳፍራል? ሕዝ 23፥3፣ 23፥8 ይህ መጥፎ ልማድ የተጣባቸው ስዎች ግርግርና በሰው ብዛት የተጨናነቀ ስፍራ የሴቶችን ገላ እንደ ሐሳባቸው ለመነካካት ምቹ ሁኔታን ይፈጥርላቸዋል፡፡ ከእነዚህ ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ የሥራቸውን አስነዋሪነት ስለሚያውቁ እንዳይነቀፉ ልዩ ልዩ ዘዴ በመፍጠር የተካኑ ናቸው፡፡ ለምሳሌ:- አንዳንዶቹ ምንም ሳያውቁና በእንቅልፍ ልባቸው ያደረጉት ለማስመሰል እንደ ተኛ ሰው እየተገላበጡና እያንኳረፉ በልዩ ልዩ አጋጣሚ አጠገባቸው ለመተኛት የተገደደችውን ሴት ገላ ሲደባብሱ ያድራሉ፡፡ ይህ ድርጊት ያለ ሩካቤ የወንድ ዘር የትም ከሚፈስባቸው ሕገ ወጥ መንገዶች መካከል አንዱ ነው:: ሌሎች ደግሞ በአድካሚ ጉዞ ወቅት ደጋፊ፣ በሕመም ጊዜ ደግሞ አስታማሚ፣… ወዘተ እየመሰሉ ከወሊድ ጋራ ተዛምዶ ያላቸውን አካላት ለመደባበስ የሚሞክሩ ሰዎች ናቸው:: እነዚህ ሰዎች ውጫቸውን ላየ አዛኝና ሌላውን ለመርዳት የሚፋጠኑ ይመስላሉ፡፡ ሰውን መርዳት ባልከፋ ነበር፡፡ ነገር ግን ችግሩ ወንዶቹ ይህን በሚያደርጉበት ጊዜ ልባቸው በፍትወት እሳት እንደ ሰም እየቀለጠና አባለ ዘራቸው እየታለበ መሆኑ ነው:: ሰውን ለመርዳት የሚፋጠኑትም ፍትወታቸው እስክትሟላላቸው ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡ አንዳንዶች ደግሞ እነርሱ ለመነካካት ፈጽሞ እንዳላሰቡ ነገር ግን የተፈጠረው ችግር እንዲጋፉ ወይም እንዲገፋፉ እንዳደረጋቸው ለማስመሰል ይጥራሉ፡፡ ይህም የሚሆነው በአብዛኛው ሕዝባዊ ስብሰባዎች በሚደረጉባቸው ዕለታትና መጨናነቅ በሚኖርባቸው ስፍራዎች ነው፡፡ ለምሳሌ:- እንደ ጥምቀትና መስቀል ያሉ ሕዝብ የሚበዛባቸውን ዕለታት መጥቀስ ይቻላል፡፡ ያለ አግባብ በርካታ ሰዎችን የሚጭኑ የሀገራችንን የሕዝብ ማመላለሻዎችንም (አውቶና ሚኒ ባስስ) እንደ ተጨማሪ ማስረጃ መጥቀስ ይቻላል:: ስለዚህ ጉዳይ በሕዝብ ማመላለሻ መኪና ውስጥ ሳሉ አጠገባቸው በቆመ ጎረምሳ እንደ ቆዳ የለፉ ሴቶች ምስክርነት ቢሰጡ የተሻለ ነበር፡፡ ለካ በመኪና ውስጥና በተጨናነቀ ቦታ ሁሉ መጠንቀቅ የሚገባው ኪስን ከሚበረብር ልባ ብቻ አይደለም፡፡ ታዲያ ሌላ ከምን እንጠንቀቅ የሚል ጠያቂ ካለም መልሱ ሕዋሳትን ከሚደባብስ ሴሰኛ ነዋ የሚል ነው! ሌሎች ደግሞ ውጫዊ ይዘታቸው ሲታይ በዚህ ዓይነት ዘርን በማፍሰስ የመርካት ተግባር የማይጠረጠሩ ዓይነት ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡- ዕድሜያቸው በጣም የገፋ፣ በአስተሳሰብ የበሰሉ፣ በአለባበስና በምጣኔ ሀብት የተከበሩ የሚመስሉ ወይም አስተማሪ የሆነ መንፈሳዊ አቋምና መልካም ስም የያዙ ናቸው፡፡ እንደዚህ ያሉ ሰዎች የሌሎችን ሕዋሳት ለመነካካት የሚያደርጉት ጥረት «ይህን አስበው አይደለም!>> እየተባለ ብዙ ጊዜ በበጎ ይተረጎምላቸዋል፡፡ ይህም እነርሱን ወደ ባሰ የጥፋት ዐዘቅት ይመራቸዋል፡፡ ስለዚህ ክርስቲያኖች ሁሉ ይህን ተገንዝበው አጥፊዎች እንዲታረሙ ከማድረግ ጋራ የራሳቸውን ሕይወት በንጽሕና መጠበቅ አለባቸው፡፡ ዘርን በማፍሰስ የመርካት ልማድ ሩካቤን ከመፈጸም በላይ የሚያስደስታቸው ሰዎች ሌላው ዝንባሌያቸው ታዳጊ ሕጻናትን ማባለግ ነው፡፡ በቅጡ ጡት ያላጎጠጎጡ ሕጻናትም እንኳን የእነዚህ ሰዎች የጥቃት ሰለባ ናቸው፡፡ ሕጻናቱ እነዚህ ሰዎች ምን እያደረጉ እንደሆነ አያስተውሉትም፣ አያውቁትም፣ ቢያውቁትም አይቃወሟቸውም አይከሷቸውምም:: ወይም በትንሽ ነገር በቀላሉ ሊባበሉና ሊታለሉላቸው ይችላሉ:: ስለዚህ እንደዚህ ያሉ ሰዎች እንደ መላእክት ንጹሐን የሆኑ ሕጻናትን ሕይወት ያበላሻሉ፡፡ ሕጻናቱን ያጫወቱና ያሳሳቁ በመምሰል ሲታገሉና ሲላፉ በፍትወት እየተቃጠሉ : ልብሳቸውን በዘር ጭቃ የሚለውሱትን ወንዶች ቁጥር ቤት ይቁጠረው፡፡ ከላይ የተሰጡት ማስገንዘቢያዎች በማንም ሰው ቢሆን ያለ አግባብ እንዳንተማመን የሚረዱ ናቸው፡፡ በተጨማሪም የምንውልበትን፣ የምንጓዝበትንና የምናድርበትን ቦታ ዙሪያውን እየቃኘን ወደ ዝሙት የሚያመሩ ምክንያቶችን ከወዲሁ አውቀን እንድንሸሽ ያግዙናል፡፡ ሌላው ደግሞ ሕጻናቶቻችንን በጥንቃቄ እንድንይዝ የሚያደርጉን ሲሆኑ በዚህ መጥፎ ተግባር የተመረዙትን ሰዎች ደግሞ ሥራቸው በብዙዎች ዘንድ መገለጡን አውቀው አደብ እንዲገዙ ሊያደርጓቸው ይችላሉ፡፡ ሰይጣነ ዝሙት አንድን ሰው ያልተፈቀደለትን የሌላ ሰው አካል በዝሙት መንፈስ ለመንካት እንዲመኝ እንደሚያነሣሣው ሁሉ ሰውዬው የራሱንም ሕዋሳት በዝሙት መንፈስ ሆኖ እንዲደባብስ የሚገፋፋበት ጊዜ አለ፡፡ የራስን አካል በራስ የመደባበስ ተግባር ምን ሊያስከትል እንደሚችል ባለማወቅ የሚደረግበት ጊዜ አለ፡፡ በአንዳንዶች ዘንድ ደግሞ ውጤቱ ቢታወቅም እንደ መልካምና አስደሳች ተግባር እየተቆጠረ ይከናወናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ከልብ ሳይሆኑና ሳያስተውሉ እንዲያው በልማድ ብቻ ኀፍረተ ሥጋቸውን የሚነካኩና የሚደባብሱ ሰዎች እንዳሉ መታዘብ ይቻላል:: ከዚህ ውጭ ደግሞ «ገሢሠ አካል ዘእንበለ ፈቀድ» እንደ ተባለው የሚያስከትለውን መጥፎ ገጽታ ቢያውቁትም ቅሉ ሳይፈልጉ በሰይጣን ማታለልና በሥጋ ፈቃድ ግፊት ሰውነታቸውን በዝሙት ሐሳብ የሚደባብሱ ብዙ ወጣቶች ይገኛሉ፡፡ ሰው የራሱን ሰውነት ያለ ማቋረጥ እንዲያክ፣ እንዲያሻሽና እንዲደባብስ ለማድረግ ሰይጣነ ዝሙት ሰውዬውን የገዛ ሰውነቱ እንዲሻክረውና እንዲኮሰኩሰው በማድረግ ፈተና እንደሚያመጣበት መጽሐፈ መነኮሳት እንዲህ በማለት ይገልጻል፡፡ «ወቦ አመ ያስሕኮ ለሥጋሁ ወይሬስዮ ለብእሲ ይዝሐቅ ሥጋሁ ዘእንበለ አፅርዖ›› ይህም ወደ አማርኛ ሲተረጐም:- «ሰውነቱንም የሚያሻክርበት ጊዜ አለ፣ ያለ ማቋረጥም እንዲያክ ያደርገዋል›› ማለት ነው፡፡ ወጣት እስከ ሆንክ ድረስ ይህ ርኩስ መንፈስ በተመሳሳይ መልኩ አንተንም ይፈትንሃል፡፡ ስለዚህ በቆምክ ጊዜ ሕዋሳትህን ትዳብሳለህ፣ ትንጠራራለህ ወይም ትወጣጠራለህ፣ እግርህንም ታፋትላለህ፡፡ «አመ እንዘ ትቀውም ታረመስስ ዲበ አባላቲከ ወትሰፍሕ እዴከ፡ ወታግደመድም እገሪከ›› ተብሎ ተጽፏልና፡፡
Show all...
👍 12 12🙏 1
🛑 ደብረ ዘይት 🛑 ለዐቢይ ጾም ዐምስተኛ ሳምንት የተዘጋጀ የበገና ዝማሬ እንዳያስቷችኹ 👇👇👇 https://youtu.be/2u0AZgnJeTc?si=XJKRya0PPVvbIgNo https://youtu.be/2u0AZgnJeTc?si=XJKRya0PPVvbIgNo https://youtu.be/2u0AZgnJeTc?si=XJKRya0PPVvbIgNo
Show all...
3
ጥያቄ: በዛሬው ዕለት ዓለም ላይ ባሉ የኢ/ኦ/ተ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የተቀደሰው ቅዳሴ የትኛው ነው? t.me/Ethiopian_Orthodox t.me/Ethiopian_OrthodoxAnonymous voting
  • ቅዳሴ እግዚእ
  • ቅዳሴ ማርያም
  • ቅዳሴ ዘሐዋርያት
  • ቅዳሴ ዘዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ
  • ቅዳሴ ዘሠለስቱ ምእት
  • ቅዳሴ ዘዮሐንስ አፈወርቅ
  • ቅዳሴ ዘአትናቴዎስ
  • ቅዳሴ ዘኤጲፋንዮስ
  • ቅዳሴ ዘዲዮስቆሮስ
  • ቅዳሴ ዘባስልዮስ
0 votes
👏 28 20👍 13🔥 4😢 4
ጥያቄ: በዛሬው ዕለት ዓለም ላይ ባሉ የኢ/ኦ/ተ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የተቀደሰው ቅዳሴ የትኛው ነው? t.me/Ethiopian_Orthodox t.me/Ethiopian_OrthodoxAnonymous voting
  • ቅዳሴ እግዚእ
  • ቅዳሴ ማርያም
  • ቅዳሴ ዘሐዋርያት
  • ቅዳሴ ዘዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ
  • ቅዳሴ ዘሠለስቱ ምእት
  • ቅዳሴ ዘአትናቴዎስ
  • ቅዳሴ ዘዮሐንስ አፈወርቅ
  • ቅዳሴ ዘዲዮስቆሮስ
  • ቅዳሴ ዘኤጲፋንዮስ
  • ቅዳሴ ዘባስልዮስ
0 votes
መጋቢት ፳፱ በዓለ ወልድ (የጌታችን ጽንሰት) መጋቢት ሃያ ዘጠኝ በዚህች ቀን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የከበረ መልአክ ገብርኤል የምሥራች የነገረበት ድኅነትን የተመላች ታላቅ በዓል ናት በዚህም የከበረ ወንጌል ምስክር ሁኗል እንዲህ ሲል፦  ኤልሳቤጥ ከፀነሰች በኋላ በስድተኛው ወር መልአኩ ገብርኤል የገሊላ ክፍል የሆነች ናዝሬት ወደምትባል አገር ከዳዊት ወገን ለሆነ ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ። የድንግሊቱም ስም ማርያም ነው። መልአኩም ወደርሷ ገብቶ ደስተኛ የሆንሽ ደስ ይበልሽ ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው አንቺ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ አላት። እርስዋም አይታ ከንግግሩ የተነሣ ደንግጣ እንዴት እንዲህ ያለ ሰላምታ ይቀበሏል ብላ አሰበች። መልአኩም እንዲህ አላት ማርያም ሆይ በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሻልና አትፍሪ። እነሆ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ እርሱ ታላቅ ነው የልዑል እግዚአብሔር ልጅም ይባላል። እግዚአብሔር አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል ለያዕቆብ ወገንም ለዘላለም ነግሦ ይኖራል ለመንግስቱም ፍጻሜ የለውም።  ማርያምም መልአኩን ወንድ ሳላውቅ ይህ እንደምን ይሆናል አለችው።መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት መንፈስ ቅዱስ መጥቶ ያድርብሻል የልዑል ኃይልም ያጸናሻል ከአንቺ የሚወለደው ከሶስቱ አካል አንዱ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ይባላል። እነሆ ዘመድሽ ኤልሳቤጥም እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ፀንሳለች ወንድልጅም አገኘች ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና። ማርያምም እነሆኝ የእግዚአብሔር አገልጋይ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለችው። ያን ጊዜም ድንግል ስትሆን ረቂቅ ፅንስን ተቀበለች የእግዚአብሔር አካላዊ ቃል ወልድ ዋህድ ለኩነተ ሥጋ ወርዶአልና ይህም አንድ ባሕርይ አንድ ህልውና ሲሆን ከሦስቱ አካላት አንዱ ነው ከዓለም መፈጠር አስቀድሞ የነበረ በማይመረመር ድንቅ በሆነ ተዋሕዶ እንዴትም እንደሆነ በማይታወቅ በቅድስት ድንግል ማርያም ማሕፀን አደረ ፅንስ ሆኖ ኖረ። በዚያን ጊዜም የኋላ ኋላ መለየት ከቶ የሌለውን ፍጹም ሰውነት ነሥቶ ተዋሐደ መለኮቱ ከትስብእቱ ጋራ ያለ መለያየት አንድ ሆኖአልና። ይቺም ዕለት የበዓላት ሁሉ በኵር ናት በእርሷም የዓለም ድኅነት ተጀምሮዋልና። ይሕች ቀን ለቤተ ክርስቲያን በእጅጉ ልዩ ናት:: በዓመቱ ከሚከበሩ በዓላትም አንደኛውን ሥፍራ ትይዛለች:: በተለይም ደግሞ የዛሬዋ ዕለት(29/07/2016 ዓ/ም) በሚከተሉት ድርብርብ በዓላት ምክንያት "ርዕሰ በዓላት"(የበዓላት ራስ)፣ "በኩረ በዓላት" እየተባለች ትጠራለች:: ይኸውም:- ፩. እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ:: ዘፍ.፩/1፥፩/1 ፪. በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት በድንግል ማርያም ማኅፀን አደረ/ተጸነሰ:: በዓሉም "በዓለ ትስብእት" ይባላል:: ይህም "አምላክ ሰው ፤ ሰው አምላክ የሆነበት" ማለት ነው:: ሉቃ.፩/1፥፳፮/26 ፫. የክብር ባለቤት መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ:: ማቴ.፳፰/28፥፩/1 ፣ ማር.፲፮/16፥፩/1 ፣ ሉቃ.፳፬/24፥፩/1 ፣ ዮሐ.፳/20፥፩/1 ፬. ደብረ ዘይት/ጌታችን ዳግመኛ ለፍርድ በዚህች ቀን ይመጣል:: ማቴ.፳፬/24፥፩/1 አምላካችን ከዕለቷ ረድኤትና በረከት ይክፈለን! @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
👍 14 6🥰 1
"ደብረ ዘይት" በዲያቆን ዘማሪ ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
👍 19 12🔥 4🥰 3
🛑 ደብረ ዘይት 🛑 ለዐቢይ ጾም ዐምስተኛ ሳምንት የተዘጋጀ የበገና ዝማሬ እንዳያስቷችኹ 👇👇👇 https://youtu.be/2u0AZgnJeTc?si=XJKRya0PPVvbIgNo https://youtu.be/2u0AZgnJeTc?si=XJKRya0PPVvbIgNo https://youtu.be/2u0AZgnJeTc?si=XJKRya0PPVvbIgNo
Show all...
9👍 3
ደብረ ዘይት የዐብይ ጾም አምስተኛ እሑድ(ሳምንት) (የዐብይ ጾም እኩሌታ) ደብረ ዘይት ማለት የወይራ ዛፍ ያለበት ተራራ ማለት ነው፡፡ቦታው ከኢየሩሳሌም በስተምስራቅ የሚገኝ የወይራ ዛፍ የበዛበት ተራራ ሲሆን ስሙም ከወይራ ዛፉ:- ደብረ ዘይት (የወይራ ዛፍ ተራራ) በመሰኘት ተገኝቷል። በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ደብረ ዘይት በዓልሆኖ የሚከበርበት ምክንያት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረዘይት ተራራ ላይ ሳለ ለቅዱሳን ደቀመዛሙርቱ ስለ ዓለም ፍጻሜ እና ስለ ዳግም ምጽአቱ ስላስተማራቸዉ በጌታችን ትምህርት መሠረት ነገረ ምጽአቱን እንድናስታውስ ወይም እያሰብን እንድንዘጋጅ ለማድረግ ነው። ስለ ዓለም መጨረሻና ስለ ዳግም ምጽአቱ ምልክቶች ምን እንደሆኑ ሐዋርያው ቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል ላይ በሦስት መሠረታዊ ክፍሎች ከፍሎ ጽፎልናል፡፡ ፩. ሃይማኖታዊ ምልክቶች "እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ ብዙዎችንም ያስታሉ" /ማቴ 24፥5/፡፡ ፪. ፖለቲካዊ ምልክቶች “ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ” /ማቴ 24፥6/ “ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና” /ማቴ 24፥7/ ፫. ተፈጥሯዊ ምልክቶች “ራብም ቸነፈርም የምድር መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል” /ማቴ.24፥7/ ከላይ ያየናቸውን ምልክቶች በዓለማችን ላይ ዕለት ተዕለት የምናየው የምንሰማው የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ ጌታችን ለደቀመዛሙርቱ የነገራቸውን ምልክቶች የቤተ ክርስቲያናችን አራት አይና ሊቃውንት የወንጌሉን ገጸ ንባብ እንዲህ ብለው ያመሰጥሩታል፡፡ “እነዚህ ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያዎች ናቸው” /ማቴ.24፥8/ ምጥ ሲመጣ አስቀድሞ የምጡ መጀመሪያ ሕመም (ጣር) እንዳለ ሁሉ የዓለምም ፍጻሜ በጣር ነው የሚጀምረው። ይህንንም ጌታችን በግልጽ አስረድቶናል፦ ጦርና የጦር ወሬ መሰማት፣ ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ መነሳት፣ ርሃብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ መታየት ለዓለም ፍጻሜ የምጥ ጣር መጀመሪያዎች ናቸዉ። እነዚህ ነገሮች በሁሉም ቦታ በአንድ ጊዜ ላይከሰቱ ይችላሉ፤ ነገር ግን በልዩ ልዩ ቦታዎች ለብዙ ዘመናት ታይተዋል፤ እየታዩም ናቸው። “ስለ ስሜ በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ” /ማቴ.24፥9/ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "ስለ ስሜ ክርስቲያኖች በመሆናችሁ በዓለም ዘንድ ትጠላላችሁ" ብሎናል። ዓለም ክፉ ስለሚሠራ የጥሩ ነገር ተቃራኒ ሆኖ ለብዙ ዘመናት ቆይቷል። ጌታችን “ብርሃንም ወደ ዓለም ስለመጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለወደዱ ፍርዱ ይህ ነው። ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፣ሥራዉም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤ እውነትን የሚያደርግ ግን ሥራው በእግዚአብሔር ተደርጎ እንደሆነ ይገለጥ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል” /ዮሐ. 3፥19-21/ እንዳለን በክፉ ሥራ ውስጥ ያለው ይህ ዓለም በጎ ሥራ የሚሠሩትን የክርስቶስን ተከታዮች ይጠላል። ጨለማ ብርሃንን ብርሃንም ጨለማን እንደሚጠላ፤ ይህ ዓለም እኛን እንዲጠላን፣ እኛ ክርስቲያኖች ደግሞ ይህንን ዓለም ልንጠላው ይገባል። አሁን ባለንበት ዘመን ክርስትና እየተጠላ፣ እየተናቀ ነው ያለው። “ባደጉት” ዓለማት ባዶ አብያተ መቅደሶች ቀርተው እነሆ እንመለከታቸዋለን፤ ትውልዱ በዓለም ስሜትና በሥጋ ፈቃድ ብቻ እየሔደ ነው። ክርስቲያን ነን በሚሉትም አውሮፓውያን ዘንድ የአንገት በላይ የማስመሰል ክርስትና እንጂ እንደ ቅዱስ ቃሉ የሚጓዝ አማኝ ማግኘት አይቻልም። እውነተኞች አይወደዱም፤ ይገፋሉ፤ ይናቃሉ። ሁኔታው የዘመኑ ፍጻሜ እጅግ እየቀረበ መምጣቱን በእርግጥ ያስረዳል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዚህም በላይ “ስለ ስሜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤ ይገድሏችሁማል” ብሏል። ክርስቲያን በመሆናቸው ብቻ ማንንም ሳይበድሉ ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ በልዩ ልዩ ሀገራት ክርስቲያኖች ሰማዕትነትን እስከ አሁን ድረስ እየተቀበሉ ነው፡፡ቅዱስ ጳዉሎስ  “ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፤ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን” /ሮሜ 8፥36/ እንዳለው። ይህ በቅዱሱ በክርስቶስ ስም መጠላትና መከራ መቀበል ከዓለም የሚጠበቅ የፍጻሜዉ ዘመን ምልክት መሆኑን አውቀን መዘጋጀትና ከሐዋርያው ጋር “በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን” /ሮሜ 8፥37/ እያልን በእምነታችን ጸንተን መጋደል ይገባናል። የክርስቲያኖች ቁጥር እያነሰ መምጣት፣ የአብያተ ክርስቲያናት መዘጋት፣ ሰው ሰው የሚያሰኘውን ክብርና ሞገስ ትቶ በግብሩ እንስሳትን ሲመስል የቅድስና ሕይወት ሲጠላና ሲናቅ፤ በአንጻሩ ደግሞ የሰው ልጅ ለረከሰው ለዚህ ዓለም ምኞትና ፈቃድ ሲገዛ ስናይ የዚህ ዓለም ፍጻሜ ጊዜው እየደረሰ መሆኑን አውቀን፤ ኖኅ በብዙ ኃጢአተኞች መካከል ቢኖርም ራሱን በቅድስና ጠብቆ እንደኖረ /ዘፍ.6-8/፤ ሎጥም እንዲሁ በብዙ ኃጢአተኞች መካከል ሲኖር በነርሱ ኃጢአት እንዳልተባበረ /ዘፍ. 19/ ከዚህ ዓለም ክፉ ሥራ ተለይተን ራሳችንን በቅድስና በመጠበቅ እንጋደል። ዓለሙ ስለ እምነታችን ቢጠላንም እኛም ስለ ክፉ ሥራው ንቀነው መኖር የግድ መሆኑን እንወቅ እንጂ ስለ እምነት፣ ስለ ቅድስናም ከዓለም በጎ ነገር አንጠብቅ። በተለያዩ ሁኔታዎች የሚደርሱብንን ፈተናዎች ሁሉ በትዕግስት እንቀበላቸው እንጂ በማማረር አንዘን፤ ምክንያቱም ስለ ስሜ በዓለም ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ ተብለናልና። “የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ አንባቢው ያስተውል!” ማቴ.24፥15/ ዓለም ራሱን በማርከስ ብቻ ሳይወሰን በፍጻሜ ዘመን በተቀደሰው ስፍራ እንኳን ሳይቀር የጥፋትን ርኩሰት ያቆማል። የተቀደሰው ስፍራ የተባለው በተቀደሰ ሃይማኖት የሚኖሩትን ሀገራት፣ ሕዝቦች የሚመለከት ነው። እንደ ኢትዮጵያ የመሳሰሉትን ሀገራት ዲያብሎስ በመልእክተኞቹ ላይ አድሮ በብዙ ርኩሰት ተፈታትኗቸዋል፤ እየተፈታተናቸውም ነው። የየሀገራቱን እምነትና ታሪክ ለማጥፋት ጥሯል፤ ብዙውንም የቅድስና ሥርዓት በርዟል፤ የቻለውንም ከነጭራሹ አጥፍቶታል። አሁን እንኳ አምልኮተ እግዚአብሔር በሚፈጸምባቸዉ ቅዱሳት መካናትና ገዳማት ሳይቀር በልዩ ልዩ ምክንያት የጥፋት ርኩሰት አዉጇል። ይህም የፍጻሜ ዘመኑ አንዱ ምልክት ስለሆነ አንባቢዉ ያስተዉል እንደተባለ የዘመኑን መፍጠን የጊዜውን መድረስ በመረዳት መዘጋጀት ይገባናል። “ብዙ ሐሰተኛዎች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ” /ማቴ.24፥11/፡፡ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት በየዘመኑ ተነስተው እውነተኛይቱን ቤተ ክርስቲያን ታግለዋታል፤ ሊያጠፏት ባይችሉም እንኳን ብዙ ልጆቿን ነጥቀው ወስደውባታል። የነዚህን ሐሰተኞች ሠራተኞች አመጣጥ ከባድ የሚያደርገው በተአምራትና በድንቅ ምልክቶች መምጣታቸው ነው። ጌታችን እንደተናገረ “ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳን እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ” /ማቴ.24፥24/ ስለዚህ በምትሐታዊ ምልክቶቻቸው የብዙ የዋሐንን ልብ በማታለል ከተቀደሰ እምነታቸው እያስኮበለሉ አጥፍተዋቸዋል፤ በማጥፋትም ላይ ይገኛሉ። ስለዚህም ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ  “ወዳጆች ሆይ መንፈስን ሁሉ አትመኑ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነዉ እንደሆነ መርምሩ”/1ዮሐ 4፥1-3/ አለን።
Show all...
👍 17 8
ቅዱስ ጳዉሎስም “የክርስቶስን ሐዋርያት እንዲመስሉ ራሳቸዉን እየለወጡ ውሸተኞች ሐዋርያትና ተንኮለኞ ሠራተኞች ናቸው። ይህም ድንቅ አይደለም ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለዉጣልና” ብሏል /2ቆሮ.11፥13-15/። ሐዋርያት ሁሉ በየመልእክቶቻቸው ከሐሰተኞች አስተማሪዎች እንድንጠበቅ ደጋግመው አሳስበዋል። ብዙ ሰው ግን በየዋሕነት ስለሚጓዝ የነዚህ ተኩላዎች ሰለባ ሆኗል። ጊዜው ክፉ ነውና የሐሰተኞች ነቢያት መረብ ጠልፎ ወደ ሐሰተኞች ክርስቶሶች እንዳይወስደን በጥንቃቄ መጓዝ ይጠበቅብናል። ሐዋርያዉ ቅዱስ ይሁዳም በመልእክቱ ቁ3  “ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኳችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ” ሲል እንደመከረን በተቀደሰ እምነታችን እስከመጨረሻ ጸንተን እንጋደል። በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ ጥቅሶች፦ -፩ኛ ተሰ ፬፥፲፫ እስከ ፍጻሜ -፪ኛ ጴጥ ፫፥፯-፲፭ -የሐዋ ሥራ ፳፬፥፩-፳፪ ምስባኩም፦ መዝ ፵፱፥፫ "እግዚአብሔርሰ ገሀደ ይመጽዕ ወአምላክነሂ ኢያረምም እሳት ይነድድ ቅድሜሁ" "እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም እሳት በፊቱ ይቃጠላል" ወንጌሉም፦ ማቴ ፳፬፥፩-፴፮ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
20👍 3🥰 1😱 1
ጌታ ሆይ አይሁድ ዓማፅያን ሰቀሉህ ወይ የዓለም መድኃኒት የዓለም ሲሳይ ሰቀሉህ ወይ(፪) የአዳም በደል አደረሰህ አንተን ለመገደል የሔዋን ስሕተት አበቃህ ለሞት ቸሩ አባት (፪) ንጹህ ክርስቶስ ሆንክ በደለኛ ብለህ ስለኛ መስቀል አሸክመው አሥረው ገረፉህ እያዳፉህ (፪) እጅና እግርህ በብረት ተመታ የዓለም ጌታ የሾህ አክሊል ደፍተህ ጎንህም ተወጋ አልፋ ኦሜጋ (፪) ግብዞች እንደ ራሳቸው መስሏቸው ምራቅ እየተፉ በፊትህ ቀለዱ አንተን ሊጐዱ (፪) በመስቀል ላይ ቃልን አሰምተህ ተጠማሁ ስትል ሐሞት እና ከርቤ ሰጡህ ቀላቅለው ጠጣ ብለው (፪) ይቅር ባይ የሰዎችን በደል ሁሉን ሳታይ አንተ ይቅር በለን በእኛ ሳትከፋ እንዳንጠፋ (፪) @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
23👍 5😢 5🥰 2
የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ይስሐቅ ከሰይፍ ቤዛ የሆነህን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ያዕቆብ በበረሃ የታገለህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኢዮብ በደመና የታየህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ሙሴ ስለ እርሱ ‹እንደእኔ ያለ ነቢይ ይነሣል› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዳዊት ‹‹እነሆ በኤፍራታ ሰማነው፣ በበረሃ ዛፍም አገኘነው›› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኤርሚያስ ‹‹የክቡሩን ዋጋ ሠላሳ ብር ተቀበሉ›› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኢሳይያስ ‹‹ወልድ ሰው ለመሆን ተገለጠልን፣ ሕፃን ተወለደልን፣ ድንቅ መካር ኃያል አምላክ›› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ሕዝቅኤል ‹‹አምላክ ወደ ተዘጋች ደጃፍ ገባ፣ ከተዘጋች በርም ወጣ›› ብለህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዳንኤል ነጭ ሐር ለብሶ ያየኸውን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኤልያስ ከሞት በፊት የሰወረህ በእሳት ፈረሶች ያሳረገህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ሕዝቅያስ የፀሐይ መግባቱን ያሳየህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ምናሴ ችንካሮችህን ከእግር ብረት የፈታ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኢዮስያስ ፋሲካውን ያደረግህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ አናንያ፣ አዛርያና ሚሳኤል ከእሳት ምድጃ ያዳናች የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ኑ፡፡ አብያና ሲላ ፌንቶስ ከመወለዱ አስቀድሞ ያመናችሁበት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ኑ፡፡ የቀድሞ አባቶች ነቢያት ሁላችሁ ከፋራን ተራራና ከቴማን ይመጣል ያላችሁት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ኑ፡፡ አሞፅ በአድማስ ቅጥር ያየኸው የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዘካርያስ በተራራዎች መካከል ያየኸው የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዕዝራ በአርፋድ በረሃ ያየኸው የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ስምዖን በክንድህ የታቀፍከውን ሕፃን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዮሴፍ እንደ አንተ የተሸጠ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ጠራቢ ዮሴፍ በትከሻህ ያዘልከው በክንድህ የተሸከምከው ሕፃን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ ከሕፃንነትህ ጀምሮ በበረሃ ያለ እናት ያለ አባት ያሳደገህ መንገዱንም እንድትጠርግለት ያዘጋጀህና መለኮትን እንድታጠምቅ የመረጠህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኢያቄምና ሐና ሆይ የልጃችሁን ልቅሶዋን የልቧንም መዘንጋት ታዩ ዘንድ ኑ፡፡ ከሔዋን እስከ ፋኑኤል ልጅ እስከ ሐና ያላችሁ ሁላችሁ ቅዱሳት ሴቶች የድንግልን ልቅሶዋን ታዩ ዘንድ ኑ፣ አንድ ልጇ ሙቷልና፡፡ የለመለመ የሥጋ ሞት ሕንፃ የተጀመረበት የአቤል ተከታዩ፣ ከጎኑ የፈሰሰው ደም ሔዋንን ከጥፋት ያዳናት የተገደለ መድኃኒታችን ነው፡፡ የናቡቴ ጓደኛው የተገፋው መድኃኒታችን ነው፡፡ አቤል ስለሚስቱ ሞተ፡፡ ናቡቴም ስለ ወይኑ ቦታ ሞተ፡፡ መድኃኒታችን ግን በቀኙ ያነጻት ዘንድ ስለቤተክርስቲያን ሞተ፡፡ ነፍሳችሁን ይወስዷታልና መውረዱንም አላወቁምና ስለ ወገኖቹ ኃጢአት እስከ ሞት ደረሰ ብሎ ስለ እርሱ የተናገረ አባቱን እንስማው፡፡ ሙሴም እርሱን ያውቁት ዘንድ አላሰቡትም፣ በሚመጣበት ቀንም አላወቁትም አለ፡፡ ዕዝራ በባሕር ጥልቅ ያለውን ማወቅ እንዳይችሉ ወልድንም ማወቅ እንዲሁ ሆነባቸው አለ፡፡ ጳውሎስም ብታውቁትስ ኖሮ የክብርን ጌታ እግዚአብሔርን ባልሰቀላችሁት ነበር አለ፡፡ በመሰደድ፣ ያለምንም በደልም በፍርድ አደባባይ በመቆም መከራ መስቀልን በመሸከም አብነት የሆናችሁ ሰማዕታት ሁላችሁ ኑ የመድኃኔዓለምን የሞቱን ዕለት አስባችሁ በጋራ አልቅሱለት፡፡ ሁሉ የእርሱ ከእርሱ ለእርሱ ተፈጥሮ ሳለ በምድር ላይ ምንም ሳይኖረው ራሱን እንኳን የሚያስጠጋበት ቤት ሳይኖረው አብነት የሆናችሁ ባሕታውያንና መነኮሳት ሁላችሁ ኑ በዛሬዋ ዕለት ስለሞተው አምላካችሁ መሪር ዕንባን አልቅሱለት፡፡ ሕግ ጠብቆ፣ ሥርዓት አክብሮ፣ ነዳያንን በመመገብና ያዘኑትን በማጽናናት 33 ዓመት በምድር ላይ ኖሮ አብነት የሆናችሁ እናንት በዓለም ሆናችሁ ሕግ ጠብቃችሁ፣ አሥራት በኩራቱን አውጥታችሁ፣ ድሆችን በመርዳት የምትኖሩ ክርስቲያኖች ሁላችሁ የመድኃኔዓለምን የሞቱን ዕለት ታስቡ ኑ፡፡ ‹‹የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና›› ብሎ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደጻፈልን (1ኛ ጴጥ 2፡21) እርሱ ንጹሕ ባሕርይ ሲሆን ወደ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ዘንድ ወደ ዮርዳኖስ በመሄድ ለተጠመቅን ለእኛ ለተነሣሕያን ለሁላችን አብነት የሆነን መድኃኒታችን ስለእኛ ሞቷልና ሞቱን እናስብ ዘንድ ኑ በቤቱ ተሰብስበን እናልቅስለት፡፡ መታሰያውንም እናድርግለት፡፡ ጌታችን ሞቶ ተቀብሮ ካረገ በኋላ ለቅዱሳን ሐዋርያትና ለቅዱሳን አባቶቻችን ለእነ አቡነ መባዓ ጽዮን፣ ለእነ አቡነ ዘርዐ ቡሩክ እንደነገራቸው የሞቱን መታሰቢያ የሚያደርግ ኃጠአተኛ እንኳ ቢሆን ሲኦልን አያያትም፡፡ የመድኃኔዓለምን የሞቱን መታሰቢያ የሚያድርግ ቢኖር ሲኦል ራሷ አፍ አውጥታ ‹‹ይህችን ነፍስ ወደኔ አታምጡብኝ›› ብላ ትጮሃለች እንጂ ችላ አትቀበለውም፡፡ የጌታችን ወዳጆቹ ዮሴፍ ኒቆዲሞስ በድርብ በፍታና በመቶ ወቄት ሽቱ ገንዘው በሐዲስ መቃብር ሊቀብሩት ቢሉ ጌታችን ያን ጊዜ ዐይኑን ክፍቶ ‹‹በሰውነቴ መዋቲ ብሆን በመለኮቴ ሕያው ነኝ እንጂ ምነው እንደ እሩቅ ብእሲ ዝም ብላችሁ ትገንዙኛላችሁን?›› አላቸው፡፡ ይህን ጊዜም ዮሴፍ ኒቆዲሞስ በታላቅ ድንዳጤ ሆነው ‹‹አቤቱ ጌታችን ሆይ! እንግዲያስ ምን እያልን እንገንዝህ?›› አሉት፡፡ መድኃኒታችንም እንዲህ እያላችሁ ገንዙኝ አላቸው፡- ‹‹ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተወልደ እማርያም እምቅድስት ድንግል ተሣሃለነ እግዚኦ፡፡ ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተጠምቀ በዮርዳኖስ ወተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል ተሣሃለነ እግዚኦ፡፡ ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተንሥአ እሙታን አመ ሣልስት ዕለት ዐርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት ወነበረ በየማነ አቡሁ ዳግመ ይመጽእ በስብሐት ይኰንን ሕያዋነ ወሙታነ ተሣሃለነ እግዚኦ› እያላችሁ ገንዛችሁ ቅበሩኝ አላቸው፡፡›› ከዚህም በኋላ መድኃኒታችን ለወዳጆቹ ለ12ቱ ሐዋርያት፣ ለ72ቱ አርድእት፣ ለ36ቱ ቅዱሳት አንስት ‹‹እስከ ሦስት ቀን እነሣላችኋለሁ እዘኑ አልቅሱ፣ እህል ውኃ አትቅመሱ በሏቸው›› ብሎ ለዮሴፍና ለኒቆዲሞስ አክፍሎት አስተማራቸው፡፡ ዳግመኛም መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከዕርገቱ በኋላ ለቅዱሳን ሐዋርያት የሞቱን መታሰቢያ እንዲያደርጉ ነግሯቸዋልና፡፡ ሕማሙንና ሞቱንም እንዲዘክሩ አዟቸዋልና አሁንም ያንን ሁሉ የመድኃኔዓለምን ሞቱን ያላሰበና የሞቱን መታሰቢያ በዓል ያላከበረና እርሱንም የማይወደው ቢኖር ዕድል ፈንታው ጽዋ ተርታው ከአይሁድ ጋር ነው፡፡ የአምላካችንን የመድኃኔዓለምን ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ተባብረን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ከእርሱ ለመተባበር ያብቃን። @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
👍 13 6😢 2
"መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በቀራንዮ ስቁል። በለኒ መሐርኩከ/በለኒ መሐርኩኪ በእንተ ማርያም ድንግል። እስመ ኢኀሎ ሔር እንበሌከ ቃል።" "ከአንተ (ከቃል) በቀር ቸር የለምና በቀራንዮ የተሰቀልህ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ሆይ! ስለ ማርያም ድንግል (ስለ እናትህ) ብለህ ምሬሀለሁ/ምሬሻለሁ በለኝ።" (መልክአ መድኃኔ ዓለም) @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
😢 11👍 9 5🙏 4