cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

ወንድም ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!

Show more
Advertising posts
34 328Subscribers
+2224 hours
+3447 days
+71430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ግርዶ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 42፥51 ለሰውም አሏህ በራእይ ወይም ከግርዶ ወዲያ ወይም መልእክተኛን መልአክን የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን ነገር የሚያወርድለት ቢኾን እንጅ በገሃድ ሊያናግረው ተገቢው አይደለም፡፡ እርሱ የበላይ ጥበበኛ ነውና፡፡ وَمَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُكَلِّمَهُ اللَّهُ إِلَّا وَحْيًا أَوْ مِن وَرَاءِ حِجَابٍ أَوْ يُرْسِلَ رَسُولًا فَيُوحِيَ بِإِذْنِهِ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّهُ عَلِيٌّ حَكِيمٌ ጭሮ አዳሪ ከመሆን ይልቅ ጸብ አጫሪ መሆንን ምርጫቸው ያረጉ ክርስቲያን ሚሽነሪዎች "ጸብ በደላላ ካልሆነልን" ብለው ለገላይ በማያመች "ያዙኝ ልቀቁኝ ደግፉኝ ጣሉኝ" በማለት መፎለሉን፣ ማቅራራቱን፣ መሸለሉን፣ መፎከሩን ተያይዘውታል። "አሏህ እንደ እንስት ሒጃብ ይለብሳል" በማለት የሌለ አሻሚ ሕፀፅ"Fallacy of equivocation" ያፅፃሉ። ምሁራን "ውኃን ከጥሩ ነገርን ከሥሩ" እንደሚሉ ስለ ሒጃብ ከሥር መሠረቱ ኢንሻላህ እንመልከት! "ሒጃብ" حِجَاب የሚለው ቃል "ሐጀበ" حَجَبَ ማለትም "ሸፈነ" "ጋረደ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መሸፈኛ"cover" "መጋረጃ"curtain" "ግርዶ"screen" ማለት ነው፥ ለምሳሌ፦ መርየም ያደረገችው መጋረጃ "ሒጃብ" حِجَاب ተብሏል፦ 19፥17 ከእነርሱም "መጋረጃን" አደረገች፡፡ فَاتَّخَذَتْ مِن دُونِهِمْ حِجَابًا እዚህ አንቀጽ ላይ "መጋረጃ" ለሚለው የገባው ቃል "ሒጃብ" حِجَاب እንደሆነ ልብ አድርግ! በተጨማሪ የጀነት ሰዎች እና የእሳት ሰዎች እንዳይገናኙ በመካከል ያለው አዕራፍ "ሒጃብ" حِجَاب ተብሏል፦ 7፥46 በመካከላቸውም ግርዶሽ አለ፡፡ وَبَيْنَهُمَا حِجَابٌ ስለዚህ "ሒጃብ" حِجَاب የሚለው ቃል እንደ ዐውዱ የተለያየ ትርጉም አለው። ለተጨማሪ ግንዛቤ እነዚህ አናቅጽ ተመልከት፦ 17፥45 38፥32 41፥5 ሌላው ሴት ልጅ የምትሰተርበት ጉፍታ "ሒጃብ" حِجَاب ተብሏል፦ 33፥59 አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህ እና ለምእምናን ሚስቶች ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّأَزْوَاجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاءِ الْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَابِيبِهِنَّ ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65 ሐዲስ 312 ዑመር"ረ.ዐ." እንደተናገረው፦ "እኔ የአሏህ መልእክተኛ ሆይ! ሰናይ እና እኩይ ሰዎች ወደ እርሶ ይገባሉ፥ ለምእመናን እናቶች በሒጃብ እንድታሰትራቸው አስጤናለው" አልኩኝ፥ ከዚያም አሏህ የሒጃብ አንቀጽ አወረደ"። قَالَ قَالَ عُمَرُ ـ رضى الله عنه ـ قُلْتُ يَا رَسُولَ اللَّهِ، يَدْخُلُ عَلَيْكَ الْبَرُّ وَالْفَاجِرُ، فَلَوْ أَمَرْتَ أُمَّهَاتِ الْمُؤْمِنِينَ بِالْحِجَابِ، فَأَنْزَلَ اللَّهُ آيَةَ الْحِجَابِ‏.‏ እዚህ ድረስ ከተግባባን አምላካችን አሏህ አንድን ሰው ነቢይ አርድጎ ለማስነሳት በግልጠት ከሚያናግርበት መንገድ አንዱ ከግርዶ ወዲያ ነው፦ 42፥51 ለሰውም አሏህ በራእይ ወይም ከግርዶ ወዲያ ወይም መልእክተኛን መልአክን የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን ነገር የሚያወርድለት ቢኾን እንጅ በገሃድ ሊያናግረው ተገቢው አይደለም፡፡ እርሱ የበላይ ጥበበኛ ነውና፡፡ وَمَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُكَلِّمَهُ اللَّهُ إِلَّا وَحْيًا أَوْ مِن وَرَاءِ حِجَابٍ أَوْ يُرْسِلَ رَسُولًا فَيُوحِيَ بِإِذْنِهِ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّهُ عَلِيٌّ حَكِيمٌ እዚህ አንቀጽ ላይ "ግርዶ" ለሚለው የገባው ቃል "ሒጃብ" حِجَاب ሲሆን አሏህን ሳያዩ በድምፅ ብቻ መስማት ሲሆን ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" በለይለቱል ኢሥራእ ወል ሚራጅ ጊዜ አምስት ወቅት ሶላትን ሲቀበሉ ያዩት ይህ ሒጃብ ብርሃን ነው፦ ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 350 አቢ ዘር እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛን”ﷺ” ጌታህን አይተከዋልን? ብዬ ጠየኳቸው። እርሳቸው፦ "ያየሁት ብርሃን ነው፥ እንዴት እርሱን ማየት እችላለው? አሉ። عَنْ أَبِي ذَرٍّ، قَالَ سَأَلْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم هَلْ رَأَيْتَ رَبَّكَ قَالَ ‏ “‏ نُورٌ أَنَّى أَرَاهُ ‏”‏ ‏.‏ ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 201 አቡ ሙሣ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ “አሏህ አይተኛም፥ እርሱ መተኛት አይገባውም። እርሱ ሚዛኖችን ዝቅ ያረጋል ያነሳልም፥ የእርሱ ግርዶ ብርሃን ነው። أَبِي مُوسَى، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ لاَ يَنَامُ وَلاَ يَنْبَغِي لَهُ أَنْ يَنَامَ يَخْفِضُ الْقِسْطَ وَيَرْفَعُهُ حِجَابُهُ النُّورُ "መንጦላዕት" የሚለው የግዕዙ ቃል "አንጦልዐ" ማለትም "ጋረደ" "ሸፈነ" ከሚል ሥረወ ቃል የመጣ ሲሆን "መጋረጃ" ማለት ነው። የፈጣሪ መጋረጃ ብርሃን ነው፥ ማንም ሊቀርበው በማይችል በብርሃን መጋረጃ ይኖራል፦ መዝሙር 31፥20 በፊትህ "መጋረጃ" ከሰው ክርክር ትጋርዳቸዋለህ። תסתירם בסתר פניך מרכסי איש መዝሙር 4፥6 በጎውን ማን ያሳየናል? የሚሉ ብዙ ናቸው። ያህዌህ ሆይ! የፊትህ "ብርሃን" በላያችን ታወቀ። רַבִּ֥ים אֹמְרִים֮ מִֽי־יַרְאֵ֪נוּ֫ טֹ֥וב נְֽסָה־עָ֭לֵינוּ אֹ֨ור פָּנֶ֬יךָ יְהוָֽה׃ 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፥16 እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፥ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል። አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም። አንድ ሰው እንኳ ያለየው እና ሊያየው የማይቻለው በብርሃን መጋረጃ ስለሚኖር ነው። ከመስማት እና ከመስማማት ይልቅ የመደናቆር እና የመጻረር አባዜ ስለተጠናወታቸው እንጂ በትውፊት እና በአዋልድ መጻሕፍት ውስጥ "ሰባቱ መንጦላይት" የሚባሉት "ሰባቱ የእሳት መጋረጃ" ሲሆኑ አምላክ በእነዚህ ሰባት የእሳት መጋረጃ የተሰወረ ነው፦ ሰይፈ ሥላሴ ዘዓርብ ቁጥር 14 "ሥላሴ "በእሳት መጋረጃ" ውስጥ የተሰወረ ነው"። መዓዛ ቅዳሴ ምዕራፍ 1 ቁጥር 51 "በሱራፌል መካከል "የእሳት መጋረጃ" በፊቱ ጋረደ፥ አሳቡን የሚያውቅ የለም። አኳኃኑን የሚረዳ የለም፥ ስውር በሆነ መሰወሪያው እራሱን ሰወረ"። እንግዲህ ቅንፍጥፍ በማለት ከማዛግ ይልቅ ቅልጥፍጥፍ ብላችሁ በአርምሞ እና በጥሞና ብትመረምሩ እና ብትመራመሩ የአሏህ ምሪት ለማግኘት መደንርደሪያ ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
1. ጥያቄ ካላችሁ፣ 2. መረጃ ከፈለጋችሁ፣ 3. መሥለም ከፈለጋችሁ በዚህ አድራሻ አግኙኝ፦ https://m.me/Wahidapologist
Show all...
"የተደበቀዉ እዉነት" የሚል መጽሐፍ Abdu Book Delivery እኛም ጋር ያገኙታል። አድራሻችን፦ አዲስ አበባ ፒያሳ ለበለጠ መረጃ በ 0929574133 ይደዉሉልን! በዚሁ ስልክ ቁጥር በቴሌ ግራም፣ በዋትሳፕ እና በኢሞ ያነጋግሩን! ክፍለ አገር እና ባሕር ማዶ ላላችሁ የመጻሕፍት ወዳጆች በተመጣጣኝ ዋጋ እና በታማኝነት በያላችሁበት በፍጥነት እንልክላችኋለን። በቴሌግራም👇👇👇 https://t.me/Abdubook በtiktok፦👇??👇👇👇 https://vm.tiktok.com/ZMjLMx7X9
Show all...
እነዚያ ጣዖታውያን በአሏህ ሌላ የሚያጋሩትን ጣዖታት፦ “አማላጆቻችን ናቸው” ይበሉ እንጂ ለእነርሱ ወደ አሏህ የሚያማልድ አማላጅ የላቸው፦ 6፥51 እነዚያንም ከእርሱ ሌላ ረዳት እና አማላጅም የሌላቸው ሲኾኑ ወደ ጌታቸው መስሰብሰብን የሚፈሩትን ይጠነቀቁ ዘንድ በእርሱ በቁርኣን አስጠንቅቅ፡፡ وَأَنذِرْ بِهِ الَّذِينَ يَخَافُونَ أَن يُحْشَرُوا إِلَىٰ رَبِّهِمْ ۙ لَيْسَ لَهُم مِّن دُونِهِ وَلِيٌّ وَلَا شَفِيعٌ لَّعَلَّهُمْ يَتَّقُونَ 40፥18 ለበዳዮች ምንም ወዳጅ እና ተሰሚ አማላጅ የላቸውም፡፡ مَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ حَمِيمٍ وَلَا شَفِيعٍ يُطَاع "ወሊይ" وَلِيٍّ ማለት "ረዳት" "ወዳጅ" ማለት ሲሆን አሏህ ወሊይ ነው፥ ከእሳት ቅጣት የሚያድን ከአሏህ ሌላ ረዳት የለም። በተጨማሪ አሏህ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም፦ 32፥4 ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም እናም አማላጅም ምንም የላችሁም። አትገሰጹምን?። مَا لَكُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا شَفِيعٍ ۚ أَفَلَا تَتَذَكَّرُون “ማ ለኩም ሚን ዱኒሂ ሚን ወሊይ” مَا لَكُمْ مِنْ دُونِهِ مِنْ وَلِيٍّ ማለትም “ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም” ማለት ሲሆን ከአሏህ ውጪ በጀነት ለመጥቀምና በጀሃነም ለመቅጣት የሚችል ማንም እረዳት የላቸውም፥ “ሚን ዱኒሂ” مِنْ دُونِهِ ማለትም “ከእርሱ ሌላ” የሚለው ተሳቢ ተውላጠ ስም ከሰዋስው አንጻር አሏህ ብቻ በመጥቀምና በመጉዳት ረዳት መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። አንቀጹ ላይ፦ “ወላ ሸፊዒን” وَلَا شَفِيعٍ ማለት “እና አማላጅም የላችሁም” ማለት ሲሆን ከመጀመሪያው ሐረግ ለመለየት “ወ” وَ የሚል መስተጻምር ይጠቀማል፥ ያ ማለት “በተጨማሪም አማላጅም የላችሁም” ማለት ነው፤ “ላ” لَا የሚለው “ሐርፉ ነፍይ” በመጀመሪያው ሐረግ ላይ “ማ” مَا የሚለው ሐርፉ ነፍይ ሆኖ ገብቶ በተጨማሪ በሁለተኛው ሐረግ ላይ “ላ” لَا የሚለው ሐርፉ ነፍይ መደገሙ ጣዖታውያን ጣዖቶቻቸውን "ወደ አሏህ በማማለድ ያቀርቡናል" ብለው የሚናገሩላቸውን ጣኦታት አማላጆች አለመሆናቸውን ለማሳየት “አማላጅ የላችሁም” በማለት ዘግቶታል፦ 30፥13 ለእነርሱም ከሚያጋሩዋቸው አማላጆች አይኖሯቸውም። وَلَمْ يَكُن لَّهُم مِّن شُرَكَائِهِمْ شُفَعَاءُ ስለዚህ “አማላጅም ምንም የላችሁም” ማለት “ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ካልሆነ በቀር እናንተ ከምታጋሯቸው የሚያማልድ አንድም አማላጅ የለም” ማለት ነው እንጂ በአሏህ ፈቃድ የሚያማልዱ አማላጆች የሉም ማለትን አሊያም አሏህ አማላጅ ነው ማለትን አያሲዝም። ከአሏህ ሌላ ከቅጣት ሊያድናቸው የሚችል ረዳት የላቸውም፥ እንዲሁ ቅጣት እንዳይቀጡ ወደ አሏህ የሚያማልዱ አማላጅ የላቸውም ማለት ነው። ሙፈሢሮችም የፈሠሩት በዚህ መልክ እና ልክ ነው፦ 36፥23 ”ከእርሱ ሌላ አማልክትን እይዛለሁን? አልረህማን በጉዳት ቢሻኝ ምልጃቸው ከእኔ ለመመለስ ምንም አትጠቅመኝም፥ አያድኑኝምም፡፡ أَأَتَّخِذُ مِن دُونِهِ آلِهَةً إِن يُرِدْنِ الرَّحْمَـٰنُ بِضُرٍّ لَّا تُغْنِ عَنِّي شَفَاعَتُهُمْ شَيْئًا وَلَا يُنقِذُونِ ተፍሢር ኢብኑ ከሲር 32፥4 "ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም” ማለት “እርሱ ብቻ ሉአላዊ የሁሉንም ጉዳዮች ተቆጣጣሪ፣ የሁሉም ነገር ፈጣሪ፣ ሁሉን ነገር አድራጊ ነው፤ ከእርሱ ሌላ ፈጣሪ የለም” ማለት ነው። “እናም አማላጅም ምንም የላችሁም” ማለት “ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም” ማለት ነው። ( ما لكم من دونه من ولي ولا شفيع ) أي : بل هو المالك لأزمة الأمور ، الخالق لكل شيء ، المدبر لكل شيء ، القادر على كل شيء ، فلا ولي لخلقه سواه ، ولا شفيع إلا من بعد إذنه . መላእክት፣ ነቢያት፣ ሙዑሚን ያማልዳሉ ማለት እና እኛ ወደ ፍጡራን በሌሉበት መለማመን፣ መጠየቅ እና መጸለይ ይለያያል፥ ወደ ፍጡራን በሌሉበት መለማመን፣ መጠየቅ እና መጸለይ ምልጃ ሳይሆን ሺርክ ነው። የሁሉንም ፍጥረት ልመና፣ ጥያቄ እና ጸሎት ጊዜና ቦታ ሳይወስነው ሁሉን የሚሰማ፣ ሁሉን የሚያይ እና ሁሉን የሚያውቅ የዐለማቱ ጌታ አሏህ ብቻ እና ብቻ ነው።  "አሏህ አማላጅ ከሆነ ተማላጁ ማን ነው? የሚለው የሚሽነሪዎች ቅጥፈት ውኃ በላው፥ አሏህ ተማላጅ እንጂ አማላጅ አይደለም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
ሸፊዕ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 32፥4 ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም እናም አማላጅም ምንም የላችሁም። አትገሰጹምን?። مَا لَكُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا شَفِيعٍ ۚ أَفَلَا تَتَذَكَّرُون “ሸፊዕ” شَفِيع ማለት “አማላጅ” ማለት ሲሆን በአላህ ፈቃድ የሚያማልዱት መላእክት፣ ነቢያት፣ ሙዑሚን ናቸው፤ ለምሳሌ መላእክት፦ 53፥26 በሰማያት ውስጥ ካለ መልአክም ብዙዎች ሊማለዱለት ለሚሻው እና ለሚወደው ሰው ከፈቀደ በኋላ ቢኾን እንጅ ምልጃቸው ምንም አትጠቅምም፡፡ وَكَم مِّن مَّلَكٍ فِي السَّمَاوَاتِ لَا تُغْنِي شَفَاعَتُهُمْ شَيْئًا إِلَّا مِن بَعْدِ أَن يَأْذَنَ اللَّهُ لِمَن يَشَاءُ وَيَرْضَىٰ 21፥28 በፊታቸው ያለውንና በኋላቸው ያለውንም ሁሉ ያውቃል፡፡ ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም፡፡ እነርሱም እርሱን ከመፍራታቸው የተነሳ ተጨናቂዎች ናቸው፡፡ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلَا يَشْفَعُونَ إِلَّا لِمَنِ ارْتَضَىٰ وَهُم مِّنْ خَشْيَتِهِ مُشْفِقُونَ “ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም” የሚለው ኃይለ ቃል መላእክት ለአማንያን እንደሚያማልዱ ያሳያል፥ ሌላው አማላጆች አሏህ ቃል ኪዳን የገባላቸው ነብያት ናቸው፦ 19፥87 አልረሕማን ዘንድ ቃል ኪዳንን የያዘ ሰው ቢኾን እንጂ ማማለድን አይችሉም፡፡ لَّا يَمْلِكُونَ الشَّفَاعَةَ إِلَّا مَنِ اتَّخَذَ عِندَ الرَّحْمَـٰنِ عَهْدًا 2፥255 ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው?። مَن ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِندَهُ إِلَّا بِإِذْنِهِ 33፥7 ከነቢያትም የጠበቀ ኪዳናቸውን ከአንተም፣ ከኑሕም፣ ከኢብራሒምም፣ ከሙሳም እና ከመርየም ልጅ ከዒሳም ጋር በያዝን ጊዜ አስታውስ፡፡ ከእነርሱም የከበደን ቃል ኪዳን ያዝን፡፡ وَإِذْ أَخَذْنَا مِنَ النَّبِيِّينَ مِيثَاقَهُمْ وَمِنكَ وَمِن نُّوحٍ وَإِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ ۖ وَأَخَذْنَا مِنْهُم مِّيثَاقًا غَلِيظًا ከላይ በግልፅና በማያሻማ መልኩ አሏህ የፈቀደለት አማላጅ እና የሚማለድለት ተመላጅ ሰው እንዳለ ተቀምጧል፦ 10፥3 ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም፡፡ እነሆ! አሏህ ጌታችሁ ነውና አምልኩት! አትገሰጹምን?። مَا مِن شَفِيعٍ إِلَّا مِن بَعْدِ إِذْنِهِ ۚ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ فَاعْبُدُوهُ ۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ “ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም” የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! ነገር ግን ጣዖታውያን ቁሬሾች ከአሏህ ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ያመልካሉ፥ “እነዚህም አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው” ይላሉ። እነዚህም በትንሳኤ ቀን፦ “እነዚያንም እነርሱ በእናንተ ውስጥ ለአሏህ ተጋሪዎች ናቸው" የምትሉዋቸውን አማላጆቻችሁን ከእናንተ ጋር አናይም” ይባላሉ፦ 10፥18 ከአሏህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ያመልካሉ፤ “እነዚህም አሏህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው” ይላሉ፡፡ وَيَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ مَا لَا يَضُرُّهُمْ وَلَا يَنفَعُهُمْ وَيَقُولُونَ هَـٰؤُلَاءِ شُفَعَاؤُنَا عِندَ اللَّهِ 6፥94 እነዚያንም እነርሱ በእናንተ ውስጥ ለአሏህ ተጋሪዎች ናቸው የምትሉዋቸውን አማላጆቻችሁን ከእናንተ ጋር አናይም፤ ግንኙነታችሁ በእርግጥ ተቋረጠ፡፡ ከእናንተም ያ "ያማልደናል" የምትሉት ጠፋ ይባላሉ፡፡ وَمَا نَرَىٰ مَعَكُمْ شُفَعَاءَكُمُ الَّذِينَ زَعَمْتُمْ أَنَّهُمْ فِيكُمْ شُرَكَاءُ ۚ لَقَد تَّقَطَّعَ بَيْنَكُمْ وَضَلَّ عَنكُم مَّا كُنتُمْ تَزْعُمُونَ
Show all...
36፥23 ”ከእርሱ ሌላ አማልክትን እይዛለሁን? አልረህማን በጉዳት ቢሻኝ ምልጃቸው ከእኔ ለመመለስ ምንም አትጠቅመኝም፥ አያድኑኝምም፡፡ أَأَتَّخِذُ مِن دُونِهِ آلِهَةً إِن يُرِدْنِ الرَّحْمَـٰنُ بِضُرٍّ لَّا تُغْنِ عَنِّي شَفَاعَتُهُمْ شَيْئًا وَلَا يُنقِذُونِ ተፍሢር ኢብኑ ከሲር 32፥4 "ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም” ማለት “እርሱ ብቻ ሉአላዊ የሁሉንም ጉዳዮች ተቆጣጣሪ፣ የሁሉም ነገር ፈጣሪ፣ ሁሉን ነገር አድራጊ ነው፤ ከእርሱ ሌላ ፈጣሪ የለም” ማለት ነው። “እናም አማላጅም ምንም የላችሁም” ማለት “ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም” ማለት ነው። ( ما لكم من دونه من ولي ولا شفيع ) أي : بل هو المالك لأزمة الأمور ، الخالق لكل شيء ، المدبر لكل شيء ، القادر على كل شيء ، فلا ولي لخلقه سواه ، ولا شفيع إلا من بعد إذنه . መላእክት፣ ነቢያት፣ ሙዑሚን ያማልዳሉ ማለት እና እኛ ወደ ፍጡራን በሌሉበት መለማመን፣ መጠየቅ እና መጸለይ ይለያያል፥ ወደ ፍጡራን በሌሉበት መለማመን፣ መጠየቅ እና መጸለይ ምልጃ ሳይሆን ሺርክ ነው። የሁሉንም ፍጥረት ልመና፣ ጥያቄ እና ጸሎት ጊዜና ቦታ ሳይወስነው ሁሉን የሚሰማ፣ ሁሉን የሚያይ እና ሁሉን የሚያውቅ የዐለማቱ ጌታ አሏህ ብቻ እና ብቻ ነው። "አሏህ አማላጅ ከሆነ ተማላጁ ማን ነው? የሚለው የሚሽነሪዎች ቅጥፈት ውኃ በላው፥ አሏህ ተማላጅ እንጂ አማላጅ አይደለም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

ወንድም ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!

ሸፊዕ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 32፥4 ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም እናም አማላጅም ምንም የላችሁም። አትገሰጹምን?። مَا لَكُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا شَفِيعٍ ۚ أَفَلَا تَتَذَكَّرُون “ሸፊዕ” شَفِيع ማለት “አማላጅ” ማለት ሲሆን በአላህ ፈቃድ የሚያማልዱት መላእክት፣ ነቢያት፣ ሙዑሚን ናቸው፤ ለምሳሌ መላእክት፦ 53፥26 በሰማያት ውስጥ ካለ መልአክም ብዙዎች ሊማለዱለት ለሚሻው እና ለሚወደው ሰው ከፈቀደ በኋላ ቢኾን እንጅ ምልጃቸው ምንም አትጠቅምም፡፡ وَكَم مِّن مَّلَكٍ فِي السَّمَاوَاتِ لَا تُغْنِي شَفَاعَتُهُمْ شَيْئًا إِلَّا مِن بَعْدِ أَن يَأْذَنَ اللَّهُ لِمَن يَشَاءُ وَيَرْضَىٰ 21፥28 በፊታቸው ያለውንና በኋላቸው ያለውንም ሁሉ ያውቃል፡፡ ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም፡፡ እነርሱም እርሱን ከመፍራታቸው የተነሳ ተጨናቂዎች ናቸው፡፡ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلَا يَشْفَعُونَ إِلَّا لِمَنِ ارْتَضَىٰ وَهُم مِّنْ خَشْيَتِهِ مُشْفِقُونَ “ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም” የሚለው ኃይለ ቃል መላእክት ለአማንያን እንደሚያማልዱ ያሳያል፥ ሌላው አማላጆች አሏህ ቃል ኪዳን የገባላቸው ነብያት ናቸው፦ 19፥87 አልረሕማን ዘንድ ቃል ኪዳንን የያዘ ሰው ቢኾን እንጂ ማማለድን አይችሉም፡፡ لَّا يَمْلِكُونَ الشَّفَاعَةَ إِلَّا مَنِ اتَّخَذَ عِندَ الرَّحْمَـٰنِ عَهْدًا 2፥255 ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው?። مَن ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِندَهُ إِلَّا بِإِذْنِهِ 33፥7 ከነቢያትም የጠበቀ ኪዳናቸውን ከአንተም፣ ከኑሕም፣ ከኢብራሒምም፣ ከሙሳም እና ከመርየም ልጅ ከዒሳም ጋር በያዝን ጊዜ አስታውስ፡፡ ከእነርሱም የከበደን ቃል ኪዳን ያዝን፡፡ وَإِذْ أَخَذْنَا مِنَ النَّبِيِّينَ مِيثَاقَهُمْ وَمِنكَ وَمِن نُّوحٍ وَإِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ ۖ وَأَخَذْنَا مِنْهُم مِّيثَاقًا غَلِيظًا ከላይ በግልፅና በማያሻማ መልኩ አሏህ የፈቀደለት አማላጅ እና የሚማለድለት ተመላጅ ሰው እንዳለ ተቀምጧል፦ 10፥3 ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም፡፡ እነሆ! አሏህ ጌታችሁ ነውና አምልኩት! አትገሰጹምን?። مَا مِن شَفِيعٍ إِلَّا مِن بَعْدِ إِذْنِهِ ۚ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ فَاعْبُدُوهُ ۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ “ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም” የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! ነገር ግን ጣዖታውያን ቁሬሾች ከአሏህ ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ያመልካሉ፥ “እነዚህም አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው” ይላሉ። እነዚህም በትንሳኤ ቀን፦ “እነዚያንም እነርሱ በእናንተ ውስጥ ለአሏህ ተጋሪዎች ናቸው" የምትሉዋቸውን አማላጆቻችሁን ከእናንተ ጋር አናይም” ይባላሉ፦ 10፥18 ከአሏህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ያመልካሉ፤ “እነዚህም አሏህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው” ይላሉ፡፡ وَيَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ مَا لَا يَضُرُّهُمْ وَلَا يَنفَعُهُمْ وَيَقُولُونَ هَـٰؤُلَاءِ شُفَعَاؤُنَا عِندَ اللَّهِ 6፥94 እነዚያንም እነርሱ በእናንተ ውስጥ ለአሏህ ተጋሪዎች ናቸው የምትሉዋቸውን አማላጆቻችሁን ከእናንተ ጋር አናይም፤ ግንኙነታችሁ በእርግጥ ተቋረጠ፡፡ ከእናንተም ያ "ያማልደናል" የምትሉት ጠፋ ይባላሉ፡፡ وَمَا نَرَىٰ مَعَكُمْ شُفَعَاءَكُمُ الَّذِينَ زَعَمْتُمْ أَنَّهُمْ فِيكُمْ شُرَكَاءُ ۚ لَقَد تَّقَطَّعَ بَيْنَكُمْ وَضَلَّ عَنكُم مَّا كُنتُمْ تَزْعُمُونَ እነዚያ ጣዖታውያን በአሏህ ሌላ የሚያጋሩትን ጣዖታት፦ “አማላጆቻችን ናቸው” ይበሉ እንጂ ለእነርሱ ወደ አሏህ የሚያማልድ አማላጅ የላቸው፦ 6፥51 እነዚያንም ከእርሱ ሌላ ረዳት እና አማላጅም የሌላቸው ሲኾኑ ወደ ጌታቸው መስሰብሰብን የሚፈሩትን ይጠነቀቁ ዘንድ በእርሱ በቁርኣን አስጠንቅቅ፡፡ وَأَنذِرْ بِهِ الَّذِينَ يَخَافُونَ أَن يُحْشَرُوا إِلَىٰ رَبِّهِمْ ۙ لَيْسَ لَهُم مِّن دُونِهِ وَلِيٌّ وَلَا شَفِيعٌ لَّعَلَّهُمْ يَتَّقُونَ 40፥18 ለበዳዮች ምንም ወዳጅ እና ተሰሚ አማላጅ የላቸውም፡፡ مَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ حَمِيمٍ وَلَا شَفِيعٍ يُطَاع "ወሊይ" وَلِيٍّ ማለት "ረዳት" "ወዳጅ" ማለት ሲሆን አሏህ ወሊይ ነው፥ ከእሳት ቅጣት የሚያድን ከአሏህ ሌላ ረዳት የለም። በተጨማሪ አሏህ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም፦ 32፥4 ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም እናም አማላጅም ምንም የላችሁም። አትገሰጹምን?። مَا لَكُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا شَفِيعٍ ۚ أَفَلَا تَتَذَكَّرُون “ማ ለኩም ሚን ዱኒሂ ሚን ወሊይ” مَا لَكُمْ مِنْ دُونِهِ مِنْ وَلِيٍّ ማለትም “ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም” ማለት ሲሆን ከአሏህ ውጪ በጀነት ለመጥቀምና በጀሃነም ለመቅጣት የሚችል ማንም እረዳት የላቸውም፥ “ሚን ዱኒሂ” مِنْ دُونِهِ ማለትም “ከእርሱ ሌላ” የሚለው ተሳቢ ተውላጠ ስም ከሰዋስው አንጻር አሏህ ብቻ በመጥቀምና በመጉዳት ረዳት መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። አንቀጹ ላይ፦ “ወላ ሸፊዒን” وَلَا شَفِيعٍ ማለት “እና አማላጅም የላችሁም” ማለት ሲሆን ከመጀመሪያው ሐረግ ለመለየት “ወ” وَ የሚል መስተጻምር ይጠቀማል፥ ያ ማለት “በተጨማሪም አማላጅም የላችሁም” ማለት ነው፤ “ላ” لَا የሚለው “ሐርፉ ነፍይ” በመጀመሪያው ሐረግ ላይ “ማ” مَا የሚለው ሐርፉ ነፍይ ሆኖ ገብቶ በተጨማሪ በሁለተኛው ሐረግ ላይ “ላ” لَا የሚለው ሐርፉ ነፍይ መደገሙ ጣዖታውያን ጣዖቶቻቸውን "ወደ አሏህ በማማለድ ያቀርቡናል" ብለው የሚናገሩላቸውን ጣኦታት አማላጆች አለመሆናቸውን ለማሳየት “አማላጅ የላችሁም” በማለት ዘግቶታል፦ 30፥13 ለእነርሱም ከሚያጋሩዋቸው አማላጆች አይኖሯቸውም። وَلَمْ يَكُن لَّهُم مِّن شُرَكَائِهِمْ شُفَعَاءُ ስለዚህ “አማላጅም ምንም የላችሁም” ማለት “ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ካልሆነ በቀር እናንተ ከምታጋሯቸው የሚያማልድ አንድም አማላጅ የለም” ማለት ነው እንጂ በአሏህ ፈቃድ የሚያማልዱ አማላጆች የሉም ማለትን አሊያም አሏህ አማላጅ ነው ማለትን አያሲዝም። ከአሏህ ሌላ ከቅጣት ሊያድናቸው የሚችል ረዳት የላቸውም፥ እንዲሁ ቅጣት እንዳይቀጡ ወደ አሏህ የሚያማልዱ አማላጅ የላቸውም ማለት ነው። ሙፈሢሮችም የፈሠሩት በዚህ መልክ እና ልክ ነው፦
Show all...
አሥ ሠላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ ያ ጀመዓህ! "የተደበቀው እውነት" የሚለው ስድስተኛው መጽሐፌ በገበያ ላይ ውሏል። "የተደበቀው እውነት" የሚያውጠነጥነው ስለ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" መምጣት በተውራት እና በኢንጂል ተነግሮ የመጽሐፉ ሰዎች ይህንን እውነት እንዴት እንደደበቁት የሚገልጥ እና የሚያጋልጥ ነው። ዝርዝሩን መጽሐፉ ላይ ያንብቡ እና ለሎች የሂዳያህ ሠበብ እንዲሆን አስነብቡ! መጽሐፉን መርካርቶ አንዋር መሥጂድ ኢሥላማዊ መጻሕፍት መደብር ውስጥ ያገኙታል፥ የበለጠ ለመረጃ +251920781016 ዐብዱ ብለው ይደውሉ! መጽሐፉ ተደራሽነት እንዲኖረው ባለው የማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን ሼር በማድረግ ሠበቡል ሂዳያህ ይሁኑ! ወጀዛኩሙላህ ኸይራ! ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom
Show all...