cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴

✞✞✞ በየቀኑ አዳዲስ መንፈሳዊ ፅሁፎች ለማግኘኘት ከፈለጉ ተቀላቀሉን ✞✞✞ @orthodox1 ሁሉም እንዲያነበው share ያርጉ ለማንኛውም መረጃዎች ለመጠየቅ @drshaye ማናገር ይችላሉ 🇪🇹 ✝✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር 🇪🇹 Join Us Today And Lets learn Together ✝✝✝ @orthodox1

Show more
Advertising posts
38 347Subscribers
-2224 hours
-1117 days
-52430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#ያንን_ሰው_ባረገኝ  ፣ #ያቺንም_ሴት_በሆንኩ [፩] 🍁 ላንዴ እስከወዲያኛው ያንን ሰው ባ’ረገኝ  ፣ ያቺንም ሴት በሆንኩ ላልወጣ ገብቼ ፡ ላልመለስ በሔድኩ ~~~~~~~ ምነው እሱን በሆንኩ ያን የቀኝ ወንበዴ ብመስለው ላ’ንድቀን : ባየው መንገዴ ለመስረቅ አይደለም ንብረት ለመቀማት አልያም ለመዝረፍ ሕይወትን ለማጥፋት በዚያ መንገድማ ከሱስ ብበልጥ እንጂ መች ከእርሱ አንስና እኔን ታውቀኝ የለ …  የወንበዴ አለቃ ያ’ጢኣተኞች ዋና ያ … ጸጸት ያዘለ በዚያች የጭንቅ ሠዓት «አስበኝ» እያለ ከመስቀልህ ጥላ ከሥር ስለዋለ ካ’ዳም ቀድሞ ገባ ምሕረት ተቀበለ እኔም እንደ ጥጦስ : ማታዬ እንዲያምር ብትለኝ ምን አለ? … «ከገነት ተጠለል: ዛሬን ከእኔ እደር» 🍁 ላንዴ እስከወዲያኛው ያንን ሰው ባ’ረገኝ  ፣ ያቺንም ሴት በሆንኩ ላልወጣ ገብቼ ፡ ላልመለስ በሔድኩ ~~~~~~~ ደ’ሞ ይህን ተመኘሁ ለንጊኖስን በሆንኩ ያቺን ዕለተ ዓርብ : ቀራንዮ በዋልኩ ለአመጽ አይደለም : ከከአይሁድ ለማበር አልያም ለመውጋት : ያንተን ጎን በጦር በዚያ መንገድማ አንተን ለማሳመም:  ማን እኔን መሰለ ስንቴ እንዳቆሰልኩህ …  ስንቴ እንደወጋሁህ : እኔን ታወቀኝ የለ! ያ …የጲላጦስ ጭፍራ በመስቀል ላይ ሳለህ በሞት በመከራ በጦሩ ቢወጋህ ሳያዝን ሳይራራ  ከቀኝ ጎን አፍስሰህ  ውኃው ከደም ጋራ በፍቅርህ ስታስረው  ዐይኑን ስታበራ ትዕግስትህን ጎትቶት   ባንተ እንደ ተጠራ ምናለ እንደው ’ኔንም … ላንተ ብቻ እንዲያድር : ልቤን ብታበራ 🍁 ላንዴ እስከወዲያኛው ያንን ሰው ባ’ረገኝ  ፣ ያቺንም ሴት በሆንኩ ላልወጣ ገብቼ ፡ ላልመለስ በሔድኩ ~~~~~~~ የበገና መዝሙር ዲ/ን አቤል ተስፋዬ ላንዴ እስከወዲያኛዉ https://youtu.be/GjZf3fPaeDs
Show all...
የበገና መዝሙር ዲ/ን አቤል ተስፋዬ ላንዴ እስከወዲያኛዉ

🍁 ላንዴ እስከወዲያኛው ያንን ሰው ባ’ረገኝ  ፣ ያቺንም ሴት በሆንኩ ላልወጣ ገብቼ ፡ ላልመለስ በሔድኩ ~~~~~~~~~~~~~~~ ምነው እሱን በሆንኩ ያን የቀኝ ወንበዴ ብመስለው ላ’ንድቀን : ባየው መንገዴ ለመስረቅ አይደለም ንብረት ለመቀማት አልያም ለመዝረፍ ሕይወትን ለማጥፋት በዚያ መንገድማ ከሱስ ብበልጥ እንጂ መች ከእርሱ አንስና እኔን ታውቀኝ የለ …  የወንበዴ አለቃ ያ’ጢኣተኞች ዋና ያ … ጸጸት ያዘለ በዚያች የጭንቅ ሠዓት «አስበኝ» እያለ ከመስቀልህ ጥላ ከሥር ስለዋለ ካ’ዳም ቀድሞ ገባ ምሕረት ተቀበለ እኔም እንደ ጥጦስ : ማታዬ እንዲያምር ብትለኝ ምን አለ? … «ከገነት ተጠለል: ዛሬን ከእኔ እደር» 🍁 ላንዴ እስከወዲያኛው ያንን ሰው ባ’ረገኝ  ፣ ያቺንም ሴት በሆንኩ ላልወጣ ገብቼ ፡ ላልመለስ በሔድኩ : ዛሬን ከእኔ እደር» ደ’ሞ ይህን ተመኘሁ ለንጊኖስን በሆንኩ ያቺን ዕለተ ዓርብ : ቀራንዮ በዋልኩ ለአመጽ አይደለም : ከከአይሁድ ለማበር አልያም ለመውጋት : ያንተን ጎን በጦር በዚያ መንገድማ አንተን ለማሳመም:  ማን እኔን መሰለ ስንቴ እንዳቆሰልኩህ …  ስንቴ እንደወጋሁህ : እኔን ታወቀኝ የለ! ያ …የጲላጦስ ጭፍራ በመስቀል ላይ ሳለህ በሞት በመከራ በጦሩ ቢወጋህ ሳያዝን ሳይራራ  ከቀኝ ጎን አፍስሰህ  ውኃው ከደም ጋራ በፍቅርህ ስታስረው  ዐይኑን ስታበራ ትዕግስትህን ጎትቶት   ባንተ እንደ ተጠራ ምናለ እንደው ’ኔንም … ላንተ ብቻ እንዲያድር : ልቤን ብታበራ 🍁 ላንዴ እስከወዲያኛው ያንን ሰው ባ’ረገኝ  ፣ ያቺንም ሴት በሆንኩ ላልወጣ ገብቼ ፡ ላልመለስ በሔድኩ ሰው ባ’ረገኝ  ፣ ያቺንም ምነው በመሰልኳት የቺን አመንዝራ እንደርሷ ላንድ ቀን : ከፊትህ ብጠራ ለዝሙት አይደለም ነፍሴን ለማሳደፍ አልያም ለመርከስ መቅደስክን ለማጉደፍ በዚያ መንገድማ ነውርን በመሸከም : መች ከእርሷ አንሳለሁ ሕግህን በማፍረስ … እኔን ታውቀኝ የለ : ምን እነግርሃለው ያቺን … ድኩም ዘማ በኃጢአቷ ቆስላ በበደሏ ታ’ማ ዓለም ተሰብስቦ ሕይወቷን ሊቀማ እንዲወግሯት ሳትፈርድ ቸርነትህ ቀድማ መሬቱን ስትጭር ድምጽህ ሳይሰማ ነውሯን እንደቀበርክ በከሳሽ ፊት ቆማ ዳግም አትበድዪ : በፍቅር ሂጂ እንዳልካት እንደው የኔንም ነፍስ … ምናለ መልሰህ: እንዲያ በማረካት 🍁 ላንዴ እስከወዲያኛው ያንን ሰው ባ’ረገኝ  ፣ ያቺንም ሴት በሆንኩ ላልወጣ ገብቼ ፡ ላልመለስ በሔድኩ ባ’ረገኝ  ፣ ያቺንም ሴት ✍️๏ በአግናጥዮስ  🖊 ሕዳር ካህናተ ሰማይ ፳፻፲፫ ዓ.ም ተፃፈ ☞ ከምድር ጌጥ ታላቋ ደብረ ሊባኖስ

👍 6 5
🌾 አንተን ማሳዘኔ በደሌ ቢበዛ ባታገኝም ከእኔ የጽድቅ መዓዛ 🌾 በምሕረትህ ብዛት አንተ ይቅር በለኝ ሥራዬን አትይ እኔ ደካማ ነኝ። 🌾 ዘወትር አለቅሳለሁ ድካሜን አውቄ መኖሬ ሲሰማኝ ከቃልህ ርቄ 🌾 በመንገድህ ምራኝ ፊትህን እንዳይ ስለ እናት ብለህ ከኔ አትለይ በዘማሪት ፋሲካ ድንቁ
Show all...
11🙏 3👍 1
የመልአከ ፀሐይ ቀሲስ መኮንን ደስታ ሥርዓተ ቀብርን በማስመልከት የተሰጠ መግለጫ መልአከ ፀሐይ ቀሲስ መኮንን ደስታ ባጋጠማቸው ህመም ምክንያት የህክምና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይቶ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። የመልአከ ፀሐይ ቀሲስ መኮንን ደስታ ክቡር አስከሬንም ከሀገረ አሜሪካ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ገብቶ ስርዓተ ቀብራቸው እሁድ መጋቢት 15/2016 ዓ.ም በፈረንሳይ ለጋሲዮን በሚገኘው ገነተ ኢየሱ ቤ/ክ ከ4- 6 ሰዓት ይፈፀማል:: ይህንንም በማስመልከት ለመልዐከ ፀሐይ ቀሲስ መኮንን ደስታ መታሰቢያ ለማስቀመጥ ጊዜያዊ ኮሚቴ ተቃቁሞ እንቅስቃሴ ተጀምራል:: በዚህም መሰረት ይህንን የተቀደሰ አላማ ለመደገፍ የምትፈልጉ ከዚህ በታች በተጠቀሱት አካውንቶች ገቢ እንድታደርጉ እንጠይቃለን:: 1000614508497 ንግድ ባንክ 179465639 አቢሲኒያ ባንክ መልአከብርሃንሙላት ክበቤ መልአከብርሃን ቄሰ ገበዝ ተቋመ ማህቶት መምህር በላይ ወርቁ የመልዐከ ጸሐይ ቀሲስ መኮንን ደስታ የቀብር አስፈጻሚ አብይ ኮሚቴ
Show all...
👍 3
ምግብ ልብስና ቤታችን የምኞታችን ማረፊያ፣ መድኃኔዓለም መድኃኒት ምግብ ልብስና ቤታችን፣ የኑሯችንም መሠረት ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋ ትጉህ ኖላዊ  ነው ፤  ነቅቶ የሚጠብቅ ከተራራው ወርዶ፣  ከበለስ ለበላች – ላንዷ የሚጨነቅ ከአውሬ እየታደገ ፤ እንዳንመስል ዓለሙን በመስቀል መንበር ላይ፣  አዘጋችቶ ሰጠን – ሥጋውና ደሙን  መድኃኒታችን መድኃኔዓለም   የማያልቀው ምግብ ለተራበው ዓለም  ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋ ጸጋችን ተገ’ፎ ፣ ተራቁተን ብንርቅ በቁም ሞትን ለብሰን ፣ በለስ አገልድመን –በኃጢዓት ብንደርቅ በልጅነት ሥልጣን ከክብር ሊመልሰን ከሸማኔ ጎድጓድ ፣ ከድንግል ተገኝቶ – ራሱን አለበሰን መድኃኒታችን መድኃኔዓለም የማያረጀው ልብስ ለታረዘው ዓለም  ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋ ከንቱ ቃል በመስማት ፣ ማረፊያ ስናጣ  ከገነት ተሰ’ደን ፣  ከሰማዩ መንግሥት–ወደ ምድር  ብንመጣ ተድላና ርስት ሆኖ የምንወርሰው ሀገር መንግስተ ሰማያት፣ ወንጌልና ተስፋ –እርሱ ነው እግዚአብሔር። መድኃኒታችን መድኃኔዓለም የማይፈርስ ጽኑ  ቤት  ለፈላሲው ዓለም  ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋ https://youtube.com/watch?v=uHyymObqHQ0&si=VkH5pu91GUt0g8ki ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋♧ ⇌⇋
Show all...
የሕግ ፍፃሜ 🔴  "መድኃኒታችን" ዲ ዘለዓለም ታከለ (ዘጎላ) || New EP Yiheg Fetsame |  Medhanitachen l D Zelalem Takele

#like #share #subscribe መድኃኒታችን የምኞታችን ማረፊያ፣ መድኃኔዓለም መድኃኒት ምግብ ልብስና ቤታችን፣ የኑሯችንም መሠረት ትጉህ ኖላዊ  ነው ፤  ነቅቶ የሚጠብቅ ከተራራው ወርዶ፣  ከበለስ ለበላች – ላንዷ የሚጨነቅ ከአውሬ እየታደገ ፤ እንዳንመስል ዓለሙን በመስቀል መንበር ላይ፣  አዘጋችቶ ሰጠን – ሥጋውና ደሙን  መድኃኒታችን መድኃኔዓለም የማያልቀው ምግብ ለተራበው ዓለም  ጸጋችን ተገ’ፎ ፣ ተራቁተን ብንርቅ በቁም ሞትን ለብሰን ፣ በለስ አገልድመን –በኃጢዓት ብንደርቅ በልጅነት ሥልጣን ከክብር ሊመልሰን ከሸማኔ ጎድጓድ ፣ ከድንግል ተገኝቶ – ራሱን አለበሰን መድኃኒታችን መድኃኔዓለም የማያረጀው ልብስ ለታረዘው ዓለም  ከንቱ ቃል በመስማት ፣ ማረፊያ ስናጣ  ከገነት ተሰ’ደን ፣  ከሰማዩ መንግሥት–ወደ ምድር  ብንመጣ ተድላና ርስት ሆኖ የምንወርሰው ሀገር መንግስተ ሰማያት፣ ወንጌልና ተስፋ –እርሱ ነው እግዚአብሔር። መድኃኒታችን መድኃኔዓለም የማይፈርስ ጽኑ  ቤት  ለፈላሲው ዓለም  ግጥም መጋቤ ሐዲስ ቴዎድሮስ በለጠ (ዶ/ር) ዜማ  ዘ. ዘውዱ ጌታቸው ክራር ዘ. ዘውዱ ጌታቸው መሰንቆ እንዳልካቸው አዱኛ ዋሽንት ኤልያስ ፈቃዱ ድምጽ አጃቢ ዘማሪት መቅደስ ማርዬ ድምጽ ቅጂ ሚክሲንግና ማስተሪንግ ዘጎላ ሬከርድስ

👍 12
የሕግ ፍፃሜ 🔴  "መድኃኒታችን" ዲ ዘለዓለም ታከለ (ዘጎላ) || New EP Yiheg Fetsame |  Medhan... https://youtube.com/watch?v=uHyymObqHQ0&si=VkH5pu91GUt0g8ki
Show all...

✝️ኑ! ቸርነትን እናድርግ ✝️ መጋቢት 15 ቀን 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ፣ +++ ገቢው በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠመው ማኅበራዊ ቀውስና ድርቅ የተጎዱ ወገኖቻችንን፣ ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ለመደገፍ የሚውል። የመግቢያ ትኬቱን፡- 1. በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ 4ኛ ወለል (ቤተ አብርሃም) 2. በወረዳ ማእከላት ጽ/ቤቶች 3. በማኅበረ ቅዱሳን ንዋያተ ቅድሳት መሸጫ ሱቆች 4. በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ የዕለት ገንዘብ መሰብሰቢያዎች 5. በአሐዱ ባንክ ሁሉም ቅርንጫፎች 6. በሰ/ት/ቤት ጽ/ቤቶች ለበለጠ መረጃ • 09 44 71 82 82 • 09 42 40 76 60 ማኅበረ ቅዱሳን
Show all...
👍 3
«ወኢትምጻእ ቅድመ እግዚአብሔር አምላክከ ዕራቀከ» በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ራቁትህን አትምጣ 【ዘዳ ፲፮፥፲፮】 በዚህ መጻሕፍት ይተባበሩበታል ✧ "ወኢታስተርኢ ቅድሜየ ዕራቀከ ☞ በፊቴም አንድ ሰው ባዶ እጁን አይታይ" 【ዘጸ ፴፬፥፳】 ✧ "ወኢትትረአይ በቅድሜየ ዕራቀከ ☞ በፊቴም ባዶ እጃችሁን አትታዩ። 【ዘጸ ፳፫ ፥፲፭ / ፳፬፥፲፩】 ✧ ሲራክም "ኢትባእ ቅድመ እግዚአብሔር ዕራቀከ ☞ ወደ እግዚአብሔር ማደሪያ ባዶህን አትግባ" 【ሲራ ፴፪፥፮】 በቅድሜየ ወይም በፊቴ ማለቱ ለእግዚአብሔርስ ሁሉ ቅድሙ ወይም ፊቱ ነው፤ በሁሉ ያለና ከፊቱ የሚሸሸግ የሌለ ሆኖ ሳለ መገለጫ መክበሪያውን ሲያይ ፊቴ ይላል። ☞ በዘመነ ብሉይ በደብተራ ኦሪትና በቤተ መቅደስ በረድኤት ያድር ነበርና ☞ ዛሬም በዘመነ ሐዲስ በሥጋውና ደሙ በቤተክርስቲያን ይገለጽባታልና ከሁሉ አብልጦ ማደርያ ቤቱን ቅድሜየ አላት። ይህን ራሱ ሙሴ ሲገልጠው «ቅድመ እግዚአብሔር ፥ ውስተ መካን ዘኀርየ እግዚአብሔር አምላክከ ☞ በእግዚአብሔር ፊት ፥ እርሱ አምላክህ በመረጠው ስፍራ» ሲል አስረድቷል፤ ለሰው አካሉን ገልጦና ሰውነቱን አራቁቶ ለመታየት የታወቀ (በቂ) ምክንያት ያስፈልጋል፤ ሠለስቱ ምዕት ለመታከም «የሚተኮስ» «የሚታገም» አካል ቢኖር አልያም ከጸበል ሊነከሩና ሊታጠቡ እንጂ በሌላውስ መንገድ በማንም ፊት እርቃን መታየት ክልክል ነው ብለዋል። "ወዓዲ ተዐቀብ ከመ ኢትትዐረቅ እምልብስከ ቅድመ መኑሂ ዘእንበለ ዳዕሙ ሶበ ይረክበከ ምክንያት ለተዐርቆ። ☞ ዳግመኛም በማንም ፊት ከልብስህ ራቁትህን እንዳትሆን ተጠበቅ፤ የምትራቆትበት ምክንያት ቢያገኝህ ነው እንጂ" 【ሃይ አበው ፳፥፲፪】 ራቁትነት በውጭ ያለ (አፍኣዊ) ገላን መክደኛ ነውርን መሸፈኛ ከሆነው ጨርቅ ከመራቆት በላይ በሦስት መንገድ ውሳጣዊ እርቃንን የሚያስረዱ ሦስት መንገዶችን እናስቀምጥ ፩ኛ] ራቁት የሚለው በኃጢዓት መመላለስን በበደል መጽናትን ነው። ያንን በንሰሐ ሳያጠሩ በእግዚአብሔር ፊት መቆም የሚገባ አይደለምና። በኃጢዓት ከመውደቃቸው አስቀድሞ የማይተፋፈሩ የነበሩ አዳምና ሴቲቱ ከሕግ ሲወጡ ራቁትነትን አወቁ፤ “የሁለቱም ዓይኖች ተከፈቱ፥ እነርሱም ዕራቁታቸውን እንደ ሆኑ አወቁ፤ የበለስንም ቅጠሎች ሰፍተው ለእነርሱ ለራሳቸው ግልድም አደረጉ።” 【ዘፍ ፫፥፯】 ቅዱስ ዳዊት ይህን ድርጊት «እንሰሳትን መምሰል» ብሎታል 【መዝ ፵፰፥፲፪/፳】 አባ ጊዮርጊስም በመጽሐፈ ምሥጢር እርቃን ከመቅረት በላይ እንሰሳትን መምሰል ወዴት አለ? ብሏል “ምንት ውእቱ ተመስሎ እንስሳ ዘእንበለ ተከሥቶ ዕርቃኑ ማእከለ ዕፀዊሃ ለገነት ሶበ ነፍጸ አጽፈ ብርሃን ዘላዕሌሁ ኀደጎ አጽፈ ብርሃን ⇨ በገነት ዛፎች መካከል ዕርቃኑን ሆኖ ከመተየት በስተቀር እንስሳን መምሰል ምንድ ነው? የብርሃን ልብስ ከበላዩ ላይ በተገፈፈ ጊዜ የብርሃን መጐናጸፊየው ተለየው” ክዶ ከአምላኩ ተለይቶ የነበረው ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታው በፊቱ በቆመ ሠዓት ለጊዜ እርቃኑን በልብስ ደብቆ ከባህር ጠልቆ መታየቱ ነውን በንሰሐ አርቆ ሥጋን በቅጣት አስጨንቆ ድኅነት እንደሚገኝ ማሳያ ነው። “ኢየሱስ ይወደው የነበረውም ደቀ መዝሙር ጴጥሮስን፦ ጌታ እኮ ነው አለው። ስለዚህ ስምዖን ጴጥሮስ ጌታ መሆኑን በሰማ ጊዜ ዕራቁቱን ነበረና ልብሱን ታጥቆ ወደ ባሕር ራሱን ጣለ።” 【ዮሐ ፳፩፥፯】 እንደ ወርቅ የተፈተነ ቃሉን በመያዝ ፣ እንደ ነጭ ልብስ የከበረውን ጸጋ ልጅነት ለማጽናት… ከፊቱ ቀርቦ መያዝ ይገባል “ባለ ጠጋ እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ፥ ተጐናጽፈህም የራቁትነትህ ኃፍረት እንዳይገለጥ ነጭ ልብስን፥ እንድታይም ዓይኖችህን የምትኳለውን ኵል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ።” 【ራእ ፫፥፲፰】 ፪ኛ) ራቁት ማለት ራስን መግለጥ ተርእዮን መሻት እግዚአብሔርን መርሳት አምላከቅዱሳንን ማስረሳት ማለት ነው። ራስን ለመስበክና ስለራስ ለማውራት እግዚአብሔር ፊት መቆም ተገቢ አይደለም። በሰማይ ያሉ አገልጋዮቹ ከመንበሩ ፊት የቆሙ መላእክቱ ፊት እግራቸውን መሸፈናቸው ለዚህ መማርያ ይሆነናል “ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር፥ ለእያንዳንዱም ስድስት ክንፍ ነበረው፤ በሁለት ክንፍ ፊቱን ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ እግሮቹን ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ ይበር ነበር።” 【ኢሳ ፮፥፪】 ራሱን ሲሰብክ ለዋለው "ኢየሱስን ልናይ እንወዳለን ብለው ለመኑት” (ዮሐ 12፥2) የሚል መልእክት ልከው ኋላ ተመልሶ ራሱን ሰውሮ ክብረ ክርስቶስን ቢሰብክላቸው “ጌታን ባዩ ጊዜ ደስ አላቸው።” (ዮሐ20፥20) ብለው አመስግነውታል። ፫ኛ) ራቁት ማለት ባዶ እጅ ምንም ሳይዙ መምጣት ማለት ነው፤ መባዕ፣ ስእለት ፣ ምጽዋት ፣ ዐሥራት፣ በኩራት፣ ቀዳምያት እና መስዋእት ሳይይዙ ወደመቅደሱ መመረጣት የሚገባ አይደለምና። “ስጡ ይሰጣችሁማል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና፥ የተጨቈነና የተነቀነቀ የተትረፈረፈም መልካም መስፈሪያ በእቅፋችሁ ይሰጣችኋል።” 【ሉቃ ፮፥፴፰】 የእግዚአብሔር መልስ መስፈርተ ሠናየ ☞ Good measure ንሕኑሕ ☞ pressed down/deeper ምሉዕ ☞ shaken together ሕዝዙኅ ☞ Running over በስብከት መልእክቱን በተከታዩ አስፈንጣሪ ያድምጡ https://youtu.be/cTghI5q7d20?si=KbkRNZ2IdRq366aI
Show all...
ዲ ን ዶ ር ቴዎድሮስ በለጠ በእግዚአብሔር ፊት ዕራቁትህን አትምጣ ዘዳ16፥16

✝️✝️✝️የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ በጸሎት ያግዙን✝️✝️✝️አዲሱን የማኅበራችንን የዩቱዩብ ቻናል +++SUBSCRIBE +++ እያደረጋችሁ ትምህርቶችን እና መዝሙሮችን እንዲደርሶት እና ለሌሎች እንዲደርሳቸው ሼር በማድረግም ይተባበሩን:: ከዚህ በፊት የተለቀቁ ትምህርቶችንና ዝማሬዎችን ለማግኘት ከስር የሚገኘውን ሊንክ ይጠቀሙ

https://www.youtube.com/channel/UCol_BHX6I-EjDdHv2Mbfsdw/videos

እግዚአብሔር ያክብርልን

👍 7 4
እግዚአብሔርን መውደድ የእ’ሱ የሆነውን ሁሉ በመውደድ ይገለጣል! ይልቁንም የእርሱ ከሆነው ሁሉ  እርሱ የወደደውንና የሞተለትን ክቡር የሰው ልጅ መውደድ እርሱን ወደ መውደድ ያደርሳል! ሰውን መግፋት እግዚአብሔርን መርሳት ነው። አበው «ተዘክሮተ እግዚአብሔር እና ተዛውኦተ አኃው ካለው ሰው በላይ እግዚአብሔርን ከቶ ማን ይመስለዋል?»  ይላሉ! ለዐቢይ ጾም ዐቢይ ትዕዛዝ የሚያስተምር ዐበይት ሕግጋቱን የሚናገር ዝማሬ እነሆ "የሕግ ፍጻሜ" ዲያቆን ዘለዓለም ታከለ (ዘጎላ)  ዝማሬ መላእክት ያሰማልን 🙏 #ሕግጋተ_ወንጌል ከፍቅረ ቢጽ ጋራ ፍቅረ እግዚአብሔር አጽና ኦሪትና ወንጌል በሁለቱ ትዕዛዛት ተሰቅለዋልና በባልንጀራህ ላይ በከንቱ አትቆጣ የእግዚአብሔር ሰላም ከቤትህ እንዳይወጣ አድመኝነት ቁጣ ጠብና ክርክር ፀሐይዋ ሳትገባ ትተህ በፍቅር ኑር አዝ (ከፍቅረ ቢጽ ጋራ) ወደሴቲቱ አይቶ ልቡ ‘ሚያመነዝር ምኞቱ ኃጢዓት ወልዳ ከሞት ጋር የሚኖር ያለዝሙት ምክንያት ሚስቱን የሚፈታ ከሰማዩ መንግሥት የለው እድል ፈንታ አዝ (ከፍቅረ ቢጽ ጋራ) እውነት ከሆነ  አዎን ፡  ካልሆነ አይደለም በል በሰማይም በምድር  ፡ ፈጽሞ አትማል ክፉውን በክፉ ፡  ተቃውመህ አትመልስ መልካም የሆነውን በሰው ሁሉ ፊት ያዝ አዝ (ከፍቅረ ቢጽ ጋራ) እግዚአብሔርን መምሰል ራስህን አስለምድ ላሳዳጆች ጸልይ ጠላትህን ውደድ የሚረግሙህንም መርቅ እንጂ አትርገም ይህ ነው ሕገ ወንጌል  ፡ ልዝብ ቀሊል ሸክም አዝ (ከፍቅረ ቢጽ ጋራ) https://youtu.be/ERbbNT-RkOE?si=6GS0X04qOY15ikcO
Show all...
የሕግ ፍፃሜ 🔴  "ሕግጋተ ወንጌል" ዲ ዘለዓለም ታከለ (ዘጎላ) || New EP Yiheg Fetsame |  Hegegate wongel D Zelalem Takele

#like #share #subscribe ሕግጋተ ወንጌል ከፍቅረ ቢጽ ጋራ ፍቅረ እግዚአብሔር አጽና ኦሪትና ወንጌል በሁለቱ ትዕዛዛት ተሰቅለዋልና በባልንጀራህ ላይ በከንቱ አትቆጣ የእግዚአብሔር ሰላም ከቤትህ እንዳይወጣ አድመኝነት ቁጣ ጠብና ክርክር ፀሐይዋ ሳትገባ ትተህ በፍቅር ኑር ወደሴቲቱ አይቶ ልቡ ‘ሚያመነዝር ምኞቱ ኃጢዓት ወልዳ ከሞት ጋር የሚኖር ያለዝሙት ምክንያት ሚስቱን የሚፈታ ከሰማዩ መንግሥት የለው እድል ፈንታ እውነት ከሆነ  አዎን ፡  ካልሆነ አይደለም በል በሰማይም በምድር  ፡ ፈጽሞ አትማል ክፉውን በክፉ ፡  ተቃውመህ አትመልስ መልካም የሆነውን በሰው ሁሉ ፊት ያዝ እግዚአብሔርን መምሰል ራስህን አስለምድ ላሳዳጆች ጸልይ ጠላትህን ውደድ የሚረግሙህንም መርቅ እንጂ አትርገም ይህ ነው ሕገ ወንጌል  ፡ ልዝብ ቀሊል ሸክም ግጥም መጋቤ ሐዲስ ቴዎድሮስ በለጠ (ዶ/ር) ዜማ ዘ. ዘውዱ ጌታቸው ክራር ዘ. ዘውዱ ጌታቸው መሰንቆ እንዳልካቸው አዱኛ ዋሽንት ኤልያስ ፈቃዱ ድምጽ ቅጂ ሚክሲንግና ማስተሪንግ ዘጎላ ሬከርድስ

6👍 4
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!