Add channel
  • Support
Stay updated with our news!
Best analytics service

Add your telegram channel for

  • get advanced analytics
  • get more advertisers
  • find out the gender of subscriber
Channel location and language
መረጃዎችን ለመላክ  @Fikerassefa  
168 752+23
~17 201
~12
10.20%
Telegram general rating
Globally
6 099place
of 3 620 016
3place
of 901
In category
54place
of 2 511
Posts archive
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የፌደራል ፖሊሶችን ለማስመረቅ ጦላይ ገቡ። የኢትዮጵያ ፓሊስ ዩኒቨርሲቲ በጦላይ በሚገኘው የመሰረታዊ የፓሊስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ግቢ ያሰለጠናቸውን የፓሊስ አባላት በማስመረቅ ላይ ሲሆን ፖሊሶቹ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በተገኙበት በስልጠና ወቅት ያካበቱትን የተኩስ ችሎታ በመስክ ላይ ትርዒት በተግባር አሳይተዋል። ዩኒቨርሲቲው አገራቸውን በፓሊስ ሙያ ለማገልገል ፍላጎት ያላቸውን ወጣቶች በ2013 ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች መልምሎ በማሰልጠን በ20ኛው ዙር እያስመረቀ ይገኛል። Via Walta @YeneTube @FikerAssefa
5 805
3
አሜሪካ አንድን ከፍተኛ የአልቃይዳ መሪ መግደሏን አስታወቀች! በሶሪያ በፈጸመችን የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃት አንድን ከፍተኛ የአልቃይዳ መሪ መግደሏን አሜሪካ አስታወቀች፡፡ጥቃቱ በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ የተፈጸመ ነው ያለው የአሜሪካ መከላከያ መስሪያ ቤት (ፔንታጎን) አብዱል ሃሚድ አል ማታር ይባላል ያለውን አንድን ከፍተኛ የአልቃይዳ አመራር መግደሉን አስታውቋል፡፡እንደ አረብ ኒውስ ዘገባ ፔንታጎን አልቃይዳ ሶሪያን እንደገና ለመደራጀት፣ ራሱን ለመገንባት፣ የውጭ አጋሮቹን ለማስተባበር እና የውጭ ሥራዎችን ለማቀድ እንደ አስተማማኝ መሸሸጊያ እየተጠቀመ ይገኛልም ነው ያለው፡፡ Via Alain @YeneTube @FikerAssefa
6 913
3
ለ 12ተኛ ክፍል ተማሪዎች የኢንትራንስ መፈተኛ ቀን ተቃርቧል በዚህ ወቅት ከማጥናት ባሻገር ያለፉትን ዓመት ጥያቄዎች መስራት ጉልህ ሚና አለው። ለዚህም በኢትዮጵያ ከ100,000 በላይ ተጠቃሚዎች ያሉት EthioMatric አፕሊኬሽን ቀርቦላችኋል። - EthioMatric ከ2008-2012/13 ዓ.ም የ4 እና የ5 ዓመት የኢንትራንስ ፈተናዎች ከነመልሶቻቸው እና ከነማብራሪያቸው በየምዕራፉ ከፋፍሎ አስቀምጧል፡፡ EthioMatric አፕሊኬሽን ለማውረድ 👇👇 https://play.google.com/store/apps/details?id=com.addismatric.addismatric ለበለጠ መረጃ @ethiomatric
6 526
16
በዐይነቱ ለየት ያለ አንድሮይድ ፕሮጀክተር (Borrego Smart Android Projector) ለተለያዩ አገልግሎቶች: - DStv (ዲኤስ ቲቪ) - Seminar (ስብሰባ) - Bar and Restaurants (መዝናኛ ቦታ) - Home theater (ለፊልም ቲያተር) Higher resolution projector - 2800 Lumens - Image Tech TFT LCD - Color 16.7K - Light source LED - Lamp 30000hr - 1gb RAM 8gb Storage - Project size 36-150 inch - Aspect ratio 4:3 16:9 16:10 - you can connect to your wifi Installed apps - Youtube - Google playstore - Mirror cast - Chrome - Other browsers Price... 12000Birr Location:-Bole medihanialem Call : 251911516533
Show more ...
6 641
2
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ወደ ትግራይ ዋና ከተማ መቀሌ የሚያደርጋቸውን በረራዎች በሙሉ ዛሬ ማገዱን አስታወቀ። ድርጅቱ በረራዎቹን ያገደው 11 መንገደኞችን ያሳፈረ ዛሬ ከአዲስ አበባ የተነሳ አንድ አውሮፕላኑ መቀሌ እንዳያርፍ ከተከለከለ በኋላ መሆኑን የድርጅቱ ቃል አቀባይ ሽቴፋን ዱጃሪክ አስታውቀዋል።ዱጃሪክ እንዳሉት ይኽው የተባበሩት መንግሥታት ሰብዓዊ የአየር አገልግሎቶች በምህጻሩ ዩ ኤን ኤች ኤ ኤስ በረራ ከፌደራል መንግሥት ባለስልጣናት ፈቃድ ያገኘ ቢሆንም በመቀሌ አውሮፕላን ማረፊያ የበረራ ተቆጣጣሪዎች መቀሌ እንዳያርፍ ትዕዛዝ ተስጥቶታል።አውሮፕላኑ አዲስ አበባ ተመልሶ በሰላም ማረፉን የተናገሩት ዱጃሪክ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅቶች የሆነውን በጥንቃቄ እያጠኑ መሆኑንም ተናግረዋል። [DW] @YeneTube @FikerAssefa
14 362
23
የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የሁለት ዳኞችን ያለመከሰስ መብት አነሳ! የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የሁለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞችን ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ውሳኔ ማሳለፉን የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ጽ/ቤት ገለጸ፡፡ የጉባዔው ጽ/ቤት እንደገለጸው የኢፌዲሪ ፍትህ ሚኒስቴር ሁለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች በወንጀል መጠርጠራቸውን በመጥቀስ ምርመራ ለማድረግ ያስችል ዘንድ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ለጉባዔው ጥያቄ አቅርቧል፡፡ ይህንንም ተከትሎ የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጥቅምት 12 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በቀረበው ጥያቄ ላይ ተወያይቶ በአዋጅ ቁጥር 1233/2013 አንቀጽ 34(2) መሰረት የሁለቱንም የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ወስኗል፡፡ [የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ] @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
14 330
6
አቶ ኦርዲን በድሪ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተመረጡ! አዲሱ የሐረሪ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው የመጀመሪያ ጉባኤ አቶ ኦርዲን በድሪ በድጋሚ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ በአብላጫ ድምፅ መርጧል። ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ኦርዲን የክልሉን ሕዝብን በቅንነት ለማገልገል ቃለ-መሐላ መፈፀማቸውን መምረጡ የክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታውቋል።አቶ ኦርዲን በድሪ ላለፉት ሦስት ዓመታት የሐረሪ ክልልን በርዕሰ መስተዳድርነት መርተዋል። @YeneTube @FikerAssefa
15 020
7
መቀሌ ለማረፍ ተችግራ ተመለሰች ስለተባለችው የተመድ አውሮፕላን ጉዳይ ሮይተርስ ሁለት የሰብአዊ እርዳታ ሰራተኞችን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ የተመድን የሰብአዊ እርዳታ የጫነ አውሮፕላን መንግስት በትግራይ ባካሄደው የአየር ድብድባ ምክንያት መቀሌ ማረፍ አልቻለም ብሏል።ሮይተርስ በዚህ ጉዳይ ሁለት ሰማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሰዎችን ማናገሩን ጠቅሷል። ጉዳዩን በተመለከተ አል ዐይን ኒውስ ከመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ጋር የሥልክ ቆይታ አድርጓል።ዶ/ር ለገሰ እንደገለጹት በራሳቸው ምክንያት ካሆነ በስተቀር የአየር ድብደባው እና የሰብአዊ እርዳታ ጫኝ አውሮፕላን እንቅስቃሴ አይገናኝም ብለዋል። “አንደኛ ሰዓቱ የተለያየ ነው” ያሉት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶ/ር ለገሰ፤ “መዳረሻዎችም የተለያዩ ናቸው” ሲሉም ተናግረዋል።መንግስት በአስቸኳይ ጊዜ መረጃ ማጣሪያ ዛሬ ገጹ ባወጣው መግለጫ “ሌላው የአሸባሪው የህወሓት ማሰልጠኛ ማዕከል ዛሬ የአየር ጥቃት ዒላማ ሆኗል” ብሏል። Via Alain @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
15 625
8
የአገር መከላከያ ሰራዊት በዛሬው የአየር ድብደባው የሕወሓት የወታደራዊ መሰልጠኛ ማዕከልን ዒላማ እንዳደረገ መንግሥት አስታወቀ፡፡ የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ ገጽ እንዳስታወቀው ማዕከሉ ከዚህ ቀደም የአገር መከላከያ ሰራዊት ማሰልጠኛ የነበረ ስፍራ ነው፡፡ ሆኖም ቡድኑ አሁን ላይ ቦታውን በሕገ ወጥ መንገድ ለሚመለምላቸው ሰዎች ማሰልጠኛ አድርጎታል፡፡ ስፍራው ከማሰልጠኛ ማዕከልነቱ ባሻገር ቡድኑ የጦር አውድ የመረጃ መለዋወጫ ማዕከል ሆኖ እያገለገለ መሆኑንም የመረጃ ማጣሪያው አስታውቋል፡፡ @YeneTube @FikerAssefa
16 728
13
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፍአለ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ተወያዩ! የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፍአለ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውውይት አድርገዋል፡፡ በውይይቱ ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፍአለ(ዶ/ር) የህወሓት የሽብር ቡድን ወረራ በፈፀመባቸው አካባቢዎች ንፁሃን ላይ ኢሰብዓዊ ድርጊት መፈፀሙን፣የመንግስትና የግለሰብ ንብረት ማውደሙንና በዚህ ሳቢያ በርካታ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን አስረድተዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ ተፈናቃዮቹ በተለያዩ ጊዚያዊ መጠለያ ጣብያ ተጠልለው እንደሚገኙና ድጋፍ እንደሚሹ ለአምባሳደሯ አብራርተዋል።አምባሳደር ጊታ ፓሲ ለተፈናቃዮች አሜሪካ ድጋፍ እንደምታደርግ ገልፀዋል፡፡ Via EBC @YeneTube @FikerAssefa
16 695
6
የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ዛሬ አዲስ መንግስት ይመሰርታል፡፡ ምክር ቤቱ በሚያደርገው ጉባዔ አፈ ጉባኤና ምክትል አፈ ጉባኤ እንደሚሠይም ይጠበቃል።በተጨማሪም የሚቀርቡለትን የክልሉን ርዕሰ መስተዳድርና ምክትል ርዕስ መስተዳድር ጨምሮ ሌሎች የክልሉን አስፈፃሚ አካላት ሹመት እንደሚያፀድቅም የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ነገኦ መግለጻቸው ይታወሳል።የሀረሪ ክልል ምክር ቤት 36 ወንበሮች ያሉት ምክር ቤት ነው። [AMN] @YeneTube @FikerAssefa
16 101
3
ፌስቡክ የኦሮሞ ነጻነት ጦር(ኦነግ ሸኔን) አገደ! የዓለማችን ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር መድረክ የሆነው ፌስቡክ የኦሮሞ ነጻነት ጦር የተባለውን ታጣቂ ቡድን ከገጹ ማገዱን ለቢቢሲ አረጋገጠ።ፌስቡክ የኦሮሞ ነጻነት ጦርን ከፌስቡክ ያገድኩት 'አደገኛ ድርጅቶች' በሚለው መመሪያው መሠረት እንደሆነ ገልጿል።"የኦሮሞ ነጻነት ጦር ከፌስቡክ የታገደው 'አደገኛ ድርጅቶች' በተለይ ደግሞ 'መንግሥታዊ ያልሆኑ ሁከት ፈጣሪ አካላት' በሚለው ፖሊሲ ሥር ነው" ሲሉ የኩባንያው ቃል አቀባይ ለቢቢሲ በኢሜይል በሰጡት ምላሽ አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት አሸባሪ ሲል የፈረጀውን የኦሮሞ ነጻነት ጦር በምዕራብ፣ በመካከለኛው እና በደቡብ ኦሮሚያ የትጥቅ እንቅስቃሴ የሚያደረግ ቡድን መሆኑ ይነገራል።ፌስቡክ የኦሮሞ ነጻነት ጦርን ከፌስቡክ አግጃለሁ ማለት፤ በኦሮሞ ነጻነት ጦር ወይም ጦሩን ወክለው የሚከፈቱ ወይም የተከፈቱ የፌስቡክ አካውንቶች እንዲኖሩ አይፈቀድም። "ለዚህ ቡድን ድጋፍ የሚሰጥ ወይም ቡድኑ የሚፈጥረውን ሁከት የሚያወድስ" ይዘት ከፌስቡክ የማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር መድረክ ላይ ይጠፋል።የፌስቡክ ቃል አቀባይ ኩባንያው ድርጅቶችን በተለያየ ጎራ ከመፈረጁ በፊት ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ባለሙያዎች ጋር ዝርዝር ሥርዓቶችን እንደሚከተል ጨምረው ገልጸዋል። ቢቢሲ የፌስቡክ ውሳኔ ተከትሎ የኦሮሞ ነጻነት ጦር ቃል አቀባይን አስተያየት ጠይቆ በተሰጠው ምላሽ፣ በፌስቡክ በቡድኑ ላይ የወሰደውን እርምጃ እንደሚያውቅ ገልጾ፤ ይህም ውሳኔ በተለያዩ ቡድኖች "የኦሮሞ ሕዝብን እና ሌሎች የተጨቆኑ ቡድኖችን ድምጽ ለማፈን" በተካሄደ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ተጽእኖ ነው ብሏል።ጨምሮም በአገሪቱ ውስጥ ያሉ ሌሎች "የሰብአዊ መብት ጥሰትና ጭፍጨፋዎች የፈጸሙና ማስረጃ የሚቀርብባቸው ቡድኖች" በነጻነት ፌስ ቡክን እየተጠቀሙ የኦሮሞ ነጻነት ጦርን በመሠረተ ቢስ ፕሮፓጋንዳ ማገድ "የፌስቡክን ፖሊሲ ማን ተጽእኖ እያደረገበት እንደሆነ ግልጽ ነው" ብሏል። ሌሎች ቡድኖችና ድርጅቶችን በተመለከተ በኢትዮጵያ ውስጥ ከፌስቡክ መመሪያ በተቃራኒ የተለያዩ መልዕክቶችን የሚያስተላልፉ ሌሎች በርካታ ቡድኖችና ግለሰቦች መንግሥታዊ ባልሆኑ ሁከት ፈጣሪ አካላት ወይም በሌሎች ዘርፎች ውስጥ ተካተው እገዳ እንደተጣለባቸው የፌስቡክ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ ገልጸዋል። Via BBC @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
15 673
9
ቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተመልሷል! የጨዋታ ውጤቶችን #ከዛሬ ጀምሮ በመገመት ነጥብዎትን ይሰብስቡ። ከፍተኛ ነጥብ ለሚያገኙ ገማቾች የተለያዩ አጓጊ ሽልማቶች ተዘጋጅተዋል። - DSTV ዲኮደር ከ1 ወር ነፃ ፓኬጅ ጋር - ኳስ እና የሚወዱትን ክለብ መለያ - Wireless Mouse - ብሉቱዝ ስፒከር እና - ፍላሽ ዲስክ እና ሌሎች አጓጊ ሽልማቶች ተዘጋጅተዋል። ቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን በቀጥታ የሚከታተሉበት ምርጥ የሞባይል አፕ። መረብ ስፖርት | Mereb Sport ----------------==------------------- ከPlay Store ዳውንሎድ ያድርጓት 👇 ዛሬውኑ ይገምቱ! https://play.google.com/store/apps/details?id=com.adika.merebsport የውድድር ህጎችን ለማንበብ - https://merebsport.net/gamerules/
Show more ...
15 039
7
ለ 12ተኛ ክፍል ተማሪዎች የኢንትራንስ መፈተኛ ቀን ተቃርቧል በዚህ ወቅት ከማጥናት ባሻገር ያለፉትን ዓመት ጥያቄዎች መስራት ጉልህ ሚና አለው። ለዚህም በኢትዮጵያ ከ100,000 በላይ ተጠቃሚዎች ያሉት EthioMatric አፕሊኬሽን ቀርቦላችኋል። - EthioMatric ከNaN/13 ዓ.ም የ4 እና የ5 ዓመት የኢንትራንስ ፈተናዎች ከነመልሶቻቸው እና ከነማብራሪያቸው በየምዕራፉ ከፋፍሎ አስቀምጧል፡፡ EthioMatric አፕሊኬሽን ለማውረድ 👇👇 https://play.google.com/store/apps/details?id=com.addismatric.addismatric ለበለጠ መረጃ @ethiomatric
15 904
41
ዛሬ በመቀሌ ተጨማሪ የአየር ድብደባ መካሄዱን መንግስት አስታወቀ! የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዛሬ ከቀትር በኋላ በመቀሌ ከተማ በሚገኘው የቀድሞው የሰሜን እዝ ዋና መቀመጫ ግቢ ላይ የአየር ድብደባ ማካሄዱን መንግስት ይፋ አደረገ። የመንግስት ኮሚንኬሽን አገልግሎት ኃላፊ የሆኑት ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) የአየር ድብደባው ከቀትር በኋላ መካሄዱን ለሪፖርተር አረጋግጠዋል። የአየር ድብደባው የተካሄደው ቀደም ሲል የአገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን እዝ ዋና መቀመጫ በነበረው እና በአሁኑ ወቅት የህወሓት ኃይል ለወታደራዊ አገልግሎት በሚጠቀምበት ግቢ ላይ መሆኑን ገልጸዋል። @YeneTube @FikerAssefa
19 814
16
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን 700 ሚሊየን ብር ፈሰስ ከሚያደርግ የመኪና አምራች ድርጅት ጋር የስምምነት ውል ተፈራረመ፡፡ ኮርፖሬሽኑ ኤልአውቶ ኢንጂነሪንግ እና ትሬዲንግ ከተሰኘ የመኪና አምራች ድርጅት ጋር በድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ መኪና በመገጣጠም ለሀገር ውስጥ እና ለውጪ ገበያ ለማቅረብ ዛሬ በኮርፖሬሽኑ ፅ/ቤት የውል ስምምነት ፈፅሟል፡፡የውል ስምምነቱን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ እና የኤልአውቶ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ በቀለ አበበ ተፈራርመዋል፡፡ ዛሬ በነበረው የፊርማ ስነ-ስርዓት ላይ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ ካለፈው በጀት አመት ጀምሮ የሀገር ውስጥ ድርጅቶችን ወደ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለማስገባት ጠንከር ያሉ ስራዎች እንደተሰሩ የገለፁ ሲሆን የዛሬው የውል ስምምነትም የጥረቱ አካል ውጤት ነው ብለዋል፡፡ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም ድርጅቱ እስካሁን በፓርኮቻችን ላይ እየሰሩ ካሉ ድርጅቶች በይዘቱ ለየት ያለ መሆኑን ገልጸው በታቀደው ግዜ ወደ ስራ እንደሚገባ ተስፋ አደርጋለሁ ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የኢልአውቶ ኢንጂነሪንግ እና ትሬዲንግ ኃ/የተ/ የግል ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ በቀለ አበበ በበኩላቸው ድርጅታቸው ባገኘው እድል ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው የመረጡት የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተሟላ አገልግሎቶች ስላሉት ለምርት ሂደታቸው ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ሲሆን ፓርኩ ከጅቡቲ ወደብ ያለው ርቀትም አጭር በመሆኑ ለስራ ቅልጥፍና ትልቅ ፋይዳ አለው ሲሉ ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ በቀለ አበበ ተናግረዋል፡፡ ድርጀቱ በ700 ሚሊዮን ብር የሚያቋቁመው የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር ለ400 ዜጎች ጊዜያዊ እና ቋሚ የስራ እድል በመፍጠር በዓመት 9000 መኪኖችን ለሀገር ውስጥ አና ለውጪ ገቢያ እንደሚያቀርብ ተገልጿል፡፡ኤልአውቶ ኢንጂነሪንግ እና ትሬዲንግ 11ሺ ካ.ሜ ስፋት ያለው ሼድ ለመውሰድ የኪራይ ውል ስምምነት ያደረገ ሲሆን 50 በመቶ ምርቶቹን ለውጪ ገበያ (ኬኒያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ታንዛኒያ፣ ጅቡቲ እና ሶማሌ ላንድ) የሚያቀርብ ሲሆን ከፊሉን 50 በመቶ ምርቶቹን ደግሞ ለሀገር ውስጥ ገበያ የሚያቀርብ ይሆናል፡፡ @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
19 831
16
እስክንድር ነጋ በደረሰበት ድብደባ ምክንያት ችሎት አለመቅረቡ ተገለፀ! በእነ እስክንድር ነጋ ላይ ምስክሮችን ማሰማት የጀመረው የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፀረ ሽብር እና ሕገ-መንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ከትላንት የቀጠለ ቀጠሮ ለዛሬ ሰጥቶ የነበረ ሲሆን በጠዋቱ ውሎ አንደኛው ተከሳሽ ስንታየሁ ቸኮል ባቀረበው ሪፖርት መሰረት እስክንድር ነጋ በትናንትናው እለት ምሽት እስር ቤት ውስጥ በደረሰበት ድብደባ ምክንያት ችሎቱ ላይ ሊገኝ መገኘት አለመቻሉ ተጠቅሷል። ሪፖርቱ እንደተሰማ የእነ እስክንድርን ችሎት ለመከታተል የመጡት ታዳሚዎች ተቃውሞ በማሰማት ችሎቱን አቋርጠው መውጣታቸውን እና ችሎቱ መቋረጡንም የባልደራስ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ በቃሉ አጥናፉ(ዶ/ር) ለአዲስ ዘይቤ አረጋግጠዋል። አያይዘውም እስክንድር ላይ የደረሰውን ድብደባ መንስዔ እና ተጠያቂ አካላቱን ጉዳይ ለማጣራት ጠበቃዎቹ ወደ እስር ቤት መሄዳቸውን የገለፁልን ሲሆን ችሎቱን አቋርጠው የወጡት ታዳሚዎች በፖሊስ ተይዘው ወደ አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዳቸውንም ነግረውናል። [@AddisZeybe] @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
18 321
11
አርቲስት መሰረት መብራቴ ለልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማዕከል ያሰባሰበችውን 6 ሚሊዮን ብር አስረከበች! አርቲስት መሰረት መብራቴ በአሜሪካን ሀገር በነበራት ቆይታ ያሰባሰበችውን 6 ሚሊዮን ብር ለልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማዕከል በዛሬው ዕለት አስረክባለች፡፡ ገንዘቡ የልብ ህመም ላለባቸው 60 ህጻናት ህክምና የሚውል እንደሆነም ተገልጿል። አርቲስቷ ላለፉት 3 ዓመታት በማዕከሉ በአምባሳደርነት እያገለገለች የምትገኝ ሲሆን ሕክምናን ለማግኘት ወረፋ እየጠበቁ የሚገኙ ህጻናትን ለመታደግ የተለያዩ የገቢ ማሰባሰብ ስራዎችን እየሰራች ትገኛለች። በ1981 ዓ.ም የተመሰረተው የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማዕከል ላለፉት 32 ዓመታት ከ9 ሺ 500 በላይ ህጻናት ህክምና እንዲያገኙ ማድረጉን መረጃዎች ያሳያሉ። [EBC] @YeneTube @FikerAssefa
17 200
6
💯JOBS UPDATES CHANNEL Get Daily Job Updates For Ethiopia Country. Willing to work in Ethiopia ? 👉Then click to Join our channel here! All Jobs are Legit and fowarded direct from AjiraNawe Website to the Channel. Remember: We do not ask for money for you to get a job, we are just your helping hand to keep you updated with open vacancies released everyday. Join Now and Thank Us Later. Channel Link 👉 https://t.me/jobs_ethiopia
16 700
18
ግብፅ እና ሱዳን የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ማካሄድ ጀመሩ! የግብፅ እና የሱዳን ወታደራዊ ኃይሎች ከትናንት በስትያ ማክሰኞ የግብፅ ድንበር ጠባቂዎችና የሱዳን እግረኞችን ያካተተ የጋራ ልምምዶች መጀመራቸውን የግብፅ ጦር አስታወቋል።የጋራ ወታደራዊ ልምምዱ በሜድትራኒያን ግዛት በማትሮህ ግዛት በመሐመድ ናጉይብ የጦር ሰፈር መካሄዱም ተገልጿል። ወታደራዊ ልምምዱ እስከ ጥቅምት 29 ድረስ እንደሚቀጥል የግብፅ ወታደራዊ ቃል አቀባይ ገብር አብደል ሃፌዝ መናገራችውን ሲጂቲን በድረገጹ አስነበቧል። የመጀመሪያ ደረጃ ንድፈ ሃሳባዊ ንግግሮችን ጨምሮ ተግባራዊ ልምምዶችን እንዲሁም የድንበር ደህንነትን ለመጠበቅ እና ሰርጎ ገብነትን ለመዋጋት የሚያገለግሉ የጦር መሳሪያዎች የሚያጠቃልል ነው።አሁን የሚካሂደው የጋራ ልምምድ የሁለቱን ሃገራት የጋራ ዕድገት የማጠናከር ዓላማ ያለው ሲሆን ግብጽ ከወዳጅ አገራት ጋር ወታደራዊ ትብብርን ለማሳደግ ያላት ዕቅድ አካል ነውም ተብሏል። ✍Asham @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
15 872
14
ከቡና ወጪ ንግድ ከእቅድ በላይ ተጨማሪ 120 ሚሊየን ዶላር ተገኘ! በበጀት አመቱ የመጀመሪያ ሩብ ከቡና ወጪ ንግድ 330 ሚሊየን ዶላር በገኘቱን የቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) ለካፒታል ጋዜጣ ተናገሩ፡፡የገቢ መጠኑ በተጠቀሰው ጊዜ ይገኛል ተብሎ ከተጠበቀው መጠን ከግማሽ በላይ ጭማሪ የታየበት ነው፡፡ በሩብ አመቱ ልናሳካ ካቀድነው ተጨማሪ 120 ሚሊየን ዶላር አግኝተናል በዚህ ከቀጠልን በበጀት አመቱ በቀላሉ የአንድ ቢሊየን ዶላር ገቢን እናሳካለን፤ ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ አክለዋል፡፡ የብራዚል የቡና ምርት በአየር ንብረት ምክንያት መጎዳት የአለም የቡና ዋጋ እንዲያሻቅብ እያደረገው መሆኑ ይጠቀሳል፡፡ይህም ለገቢ ማደግ አስተዋፅኦ እንደነበረው የተገለጸ ሲሆን ፤በተጨማሪም ኢትዮጵያ የምትልከውን ቡና በከፍተኛ መጠን እየጨመረች ከመሆኑ ጋር ተያዞ የገቢ መጠኑን እያሳደገው ነው፡፡ [Capital] @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
15 690
7
በትግራይ ክልል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ያላቸው ደንበኞች ላይ የተጣለው እገዳ መነሳቱ ተነገረ! በትግራይ ክልል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የባንክ ሂሳብ ከፍተው ከጦርነቱ በኋላ ሂሳባቸው የታገደባቸው ደንበኞች አሁን እገዳው እንደተንሳላቸውና ሂሳባቸውን ማንቀሳቀስ እንዲችሉ መፈቀዱን ዋዜማ ራዲዮ ሰምቻለሁ ብላለች። አንድ ዓመት ሊሆነው የተቃረበው ጦርነት መጀመሩን ተከትሎ በትግራይ ክልል ያለው የባንክ አገልግሎት ሲቋረጥ በትግራይ ክልል የተከፈቱ የባንክ ሂሳቦች እንደይንቀሳቀሱ አብረው መታገዳቸው ይታወሳል።ለእገዳው ምክንያት የነበረው ከፀጥታ ስጋት ጋር የተያያዘ የገንዘብ ዝውውርን መግታት ነበር። አንድ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፍተኛ የስራ ሀላፊ ለዋዜማ እንደተናገሩት ትግራይ ክልል ሂሳብ የከፈቱ ደንበኞቹ የታገደባቸውን ሂሳብ ለማንቀሳቀስ ከፈለጉ አቅራቢያቸው ባለ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ቀርበው የታገደባቸውን ሂሳብ ማንቀሳቀስ እንዲፈቀድላቸው የሚጠይቅ ማመልከቻ በመጻፍና ከማመልከቻው ጋርም ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያን እንዲሁም የሂሳብ ደብተራቸውን በማያያዝ ጥያቄያቸውን ማቅረብ ይችላሉ።ባንኩም አስፈላጊውን ማጣሪያ አድርጎ ደንበኞቹ ሂሳባቸውን እንዲያንቀሳቅሱ ያደርጋል። ትግራይ ክልል ተከፍተው በጦርነቱ ሳቢያ መንቀሳቀስ ያልቻሉ ሂሳቦችን እንዲንቀሳቀሱ የማድረጉን ስራ ግን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውጭ ሁሉም የግል ንግድ ባንኮች ስለመጀመራቸው ዋዜማ ራዲዮ ማረጋገጥ አልቻለችም። ያነጋገርናቸው የአንድ የግል ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት ስለ ጉዳዩ መረጃ እንደሌላቸው ተናግረዋል። Via Wazema @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
16 732
95
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ 'ትሩዝ ሶሻል' የተባለ አዲስ ማኅበራዊ ሚዲያ ሊመሠርቱ መሆኑን አስታወቁ። ትራምፕ ማኅበራዊ ሚዲያው በአሜሪካ የተቃዋሚ ድምጾችን ዝም በማሰኘት የሚታወቁ "ታላላቅ የቴክኖሎጂ ጭቆና ያስቆማል" ብለዋል።ትራምፕ የሚመሩት ትራምፕ ሚዲያ እና ቴክኖሎጂ ቡድን (ቲኤምቲጂ) በደንበኝነት ምዝገባ ቪዲዮ-በፍላጎት የሚሰጥ አገልግሎት ለማስጀመር አስቧል።በጥር ወር ደጋፊዎቻቸው የአሜሪካን ምክር ቤት ህንጻን ካፒቶል ሂልን በመውረራቸው ምክንያት ትራምፕ እንደ ትዊተር እና ፌስቡክ ካሉ ታዋቂ የማኅበራዊ ሚዲያ ትስስር መድረኮች በጊዜያዊነት ወይም በቋሚነት ታግደዋል። እሳቸው እና አማካሪዎቻቸው ከዚያ በኋላ ተፎካካሪ የማኅበራዊ ሚዲያ ለመፍጠር ስለማቀዳቸው ፍንጭ ሰጥተዋል።በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ 'ከዶናልድ ጄ ትራምፕ ዴስክ' የሚባል ድረ-ገጽ ጀምረው ነበር።ድረ-ገጹ ከተጀመረ ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ እስከወዲያኛው ተዘግቷል። በቲኤምቲጂ መግለጫ መሠረት 'ትሩዝ ሶሻል' በሚቀጥለው ወር ለተመረጡ ሰዎች ብቻ ክፍት ሆኖ በአውሮፓውያኑ 2022 የመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት ደግሞ በአገር አቀፍ ደረጃ ይለቀቃል ተብሏል።ትራምፕ "ታሊባን በትዊተር ላይ ትልቅ ቦታ ኖሮት ተወዳጁ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዝም እንዲል በተደረገበት ዓለም ውስጥ እየኖርን ነው" ሲሉ ጽፈዋል።"ሁሉም ሰው ለምን ትልልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን አትገዳደሩም ብሎ ይጠይቀኛል? ደህና፣ በቅርቡ ይሆናለን!" በማለት አክለዋል። አዲሱ ኩባንያ የሚሠራ ገጽ እንዳለው የሚጠቁም ነገር የለም። Via BBC @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
15 183
8
ቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተመልሷል! የጨዋታ ውጤቶችን #ከዛሬ ጀምሮ በመገመት ነጥብዎትን ይሰብስቡ። ከፍተኛ ነጥብ ለሚያገኙ ገማቾች የተለያዩ አጓጊ ሽልማቶች ተዘጋጅተዋል። - DSTV ዲኮደር ከ1 ወር ነፃ ፓኬጅ ጋር - ኳስ እና የሚወዱትን ክለብ መለያ - Wireless Mouse - ብሉቱዝ ስፒከር እና - ፍላሽ ዲስክ እና ሌሎች አጓጊ ሽልማቶች ተዘጋጅተዋል። ቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን በቀጥታ የሚከታተሉበት ምርጥ የሞባይል አፕ። መረብ ስፖርት | Mereb Sport ----------------==------------------- ከPlay Store ዳውንሎድ ያድርጓት 👇 ዛሬውኑ ይገምቱ! https://play.google.com/store/apps/details?id=com.adika.merebsport የውድድር ህጎችን ለማንበብ - https://merebsport.net/gamerules/
Show more ...
15 114
7
ለ 12ተኛ ክፍል ተማሪዎች የኢንትራንስ መፈተኛ ቀን ተቃርቧል በዚህ ወቅት ከማጥናት ባሻገር ያለፉትን ዓመት ጥያቄዎች መስራት ጉልህ ሚና አለው። ለዚህም በኢትዮጵያ ከ100,000 በላይ ተጠቃሚዎች ያሉት EthioMatric አፕሊኬሽን ቀርቦላችኋል። - EthioMatric ከNaN/13 ዓ.ም የ4 እና የ5 ዓመት የኢንትራንስ ፈተናዎች ከነመልሶቻቸው እና ከነማብራሪያቸው በየምዕራፉ ከፋፍሎ አስቀምጧል፡፡ EthioMatric አፕሊኬሽን ለማውረድ 👇👇 https://play.google.com/store/apps/details?id=com.addismatric.addismatric ለበለጠ መረጃ @ethiomatric
16 381
60
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ረቂቅ ሕገ መንግሥት የክልል መቀመጫን ሳይጠቅስ ማለፉ አወዛገበ! መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም. የተከናወነውን ሕዝበ ውሳኔ ተከትሎ በክልልነት ለመደራጀት የሚያስችለውን ድምፅ ያገኘው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ረቂቅ ሕገ መንግሥት፣ በተለያዩ ዞኖች ውይይት እየተደረገበት ቢሆንም፣ የክልል ከተማን በግልጽ ባለማስቀመጡ ውዝግብ እያስነሳ ነው፡፡ የክልሉ ረቂቅ ሕገ መንግሥት የክልል መቀመጫ አንድ ብቻ እንደማይሆንና በርካታ ከተሞች እንደሚኖሩ የሚደነግግና በስብሰባዎቹ የተገኙ ታዳሚዎች፣ የክልል ከተሞች በርካታ ቢሆኑም፣ የርዕሰ መስተዳድር መቀመጫ የሚሆነው የት ነው የሚለው ጥያቄ እያወዛገበ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ረቂቅ ሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ ስድስት ላይ ርዕሰ ከተማን የሚመለከት ድንጋጌ የያዘ ሲሆን፣ ‹‹የክልሉ መንግሥት ከአንድ በላይ ከተሞች ይኖሩታል፡፡ ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል፤›› ሲል ይደነግጋል፡፡ Via Reporter @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
18 791
21
የፌደራሉ ዓቃቤ ሕግ ዛሬ በባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች ለመሠረተው የሽብር ክስ ዛሬ በግልጽ ችሎት ምስክሮቹን ማሰማት መጀመሩን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል። ዓቃቤ ሕግ ለዛሬ ከጠራቸው 9 ምስክሮች ዛሬ ችሎት ያቀረበው ሁለቱን ብቻ ነው። ከዘጠኙ ምስክሮች ሁለቱ የሚመሰክሩት በፓርቲው ሊቀመንበር እስክንድር ነጋ ላይ እንደሆነ ዓቃቤ ሕግ ለችሎቱ አስረድቷል። ዓቀቤ ሕግ የቀሪዎቹን 12 ምስክሮቹን ስም ዝርዝር ዛሬ ለመገናኛ ብዙኀን በይፋ እንዲገልጽ ትናንት በችሎቱ ታዞ የነበረ ቢሆንም፣ ስም ዝርዝራቸውን ግን ዛሬ ሳይገልጽ ቀርቷል። [Wazema] @YeneTube @FikerAssefa
18 085
10
በቡራዩ ከተማ ከደለሳ ፒ ኤል ሲ የምንጣፍና ፕላስቲክ ፋብሪካ 2 ነብጥ 7 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ንብረት በቡድን የዘረፉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡   ግለሰቦቹ ገፈርሳ ቀበሌ ኖኖ ልዩ ቦታው ታጠቅ በተባለ ቦታ ከምሽቱ በግምት 3 ሰዓት ተኩል ላይ ዝርፊያ መፈጸማቸውን የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡የወረዳ 2 ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ሃላፊ ሳጅን ሙሉነህ ቀንኣ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ዘረፋው የተፈጸመው በዕለቱ ጥበቃ ላይ ከነበረው ግለሰብ ጋር በመመሳጠር እና ከተዘረፈ በኋላ እንደሚገዛቸው ከተስማማው ግለሰብ ጋር በጋራ በማቀድ ነው፡፡   ጥበቃው ወደ ፋብሪካው ቅጥር ግቢ ካስገባቸው በኋላ ውስጥ የነበሩ ግለሰቦችን በማፈን ዘረፋው መፈጸሙን የገለጹት ሳጅን ሙሉነህ ÷ ለዚህም ሁለት መኪናዎችን ተጠቅመዋል ነው ያሉት፡፡በዚህም 92 ካርቶንሲሲቲቪ ካሜራ፣ ቴሌቪዥን እና ሰነዶች መዘረፋቸውን አረጋግጠናል ብለዋል፡፡ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትም በኤግዚቢትነት የተያዙትን ንብረቶች በቦታው ተገኝቶ ተመልክቷል፡፡   ፓሊስ ባደረገውም ክትትል ንብረቱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ካኦጄጄ አካባቢ ወደ ሌላ መኪና ሲጫን እጅ ከፈንጅ መያዝ ተችሏል ነው ያሉት፡፡ከወንጀሉ ጋር ተያይዞም 11 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው ያሉት ሳጅን ሙሉነህ ÷ እየተደጋገመ ለመጣው የቡድን ዘረፋ አስተማሪ ቅጣት ይጠብቃቸዋል ብለዋል፡፡ Via Fana @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
18 706
7
በአዲስ አበባ ከተማ የቋሚ ንብረት መሻሻጥን የሚከለክለው መመሪያ በቅርቡ ይነሳል ተባለ፡፡ እንደ መኖሪያ ቤት ያሉ ቋሚ ንብረቶችን መሸጥና መግዛት ተከልክሎ እንደነበር ይታወሳል፡፡በዚህም ምክንያት የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲም የስም ዝውውር እና ሥጦታን የተመለከቱ አገልግሎቶችን መስጠት ካለፈው ሐምሌ ወር ጀምሮ አቋርጦ ቆይቷል፡፡ አሁን ግን፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዲስ መልኩ በመዋቀሩ እና የከተማዋ የመሬት ማኔጅመንትም አዲስ ኃላፊዎች ተሰይመውለት እንደገና በመደራጀቱ በዚህ ወር ውስጥ ከልካዩ መመሪያ ይነሳል ተብሎ ይጠበቃል መባሉን ሸገር ሰምቷል፡፡ ሸገር ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ እንዳገኘው መረጃ ከኾነ፣ ምናልባትም እስከ ጥቅምት ወር መጨረሻ ቋሚ ንብረቶችን መሻሻጥና በሥጦታ የማስተላለፍ አገልግሎት ዳግም ይጀመራል፡፡ በመሆኑም ዜጎች ሕጋዊ ባለሆነው የመንደር ውል ቋሚ ንብረት ከመሸጥ እና ከመግዛት እንዲቆጠቡ እና አገልግሎቱ ዳግም እስኪጀመር በትዕግስት እንዲጠብቁ ኤጀንሲው አሳስቧል፡፡ Via Sheger FM @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
20 234
122
መከላከያ ሠራዊት ያካሄዳቸው የአየር ድብደባዎች ኢላማቸውን የመቱ መሆናቸው ተገለጸ! የመከላከያ ሠራዊት ያካሄዳቸው የአየር ድብደባዎች ዒላማ ያደረጉት የህወሓት የጦር መሣሪያ ማምረቻ እና የጦር ትጥቅ ጥገና ጣቢያዎች ላይ ብቻ እንደሆነና ኢላማቸውን የመቱ መሆናቸው ተገለጸ፡፡   የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች የመረጃ ማጣሪ ባወጣው መግለጫ፤ የመከላከያ ሠራዊት ያካሄዳቸውን የአየር ድብደባዎች በተመለከተ የተዛባ ግንዛቤ ቢኖርም፣ በተቃራኒው ጥቃቶቹ ዒላማ ያደረጉት የህወሓት የጦር መሣሪያ ማምረቻ እና የጦር ትጥቅ ጥገና ጣቢያዎችን ብቻ ነው ብሏል።   የመከላከያ ሠራዊት የሚያከውናቸው እነዚህ ሥራዎች የሽብር ድርጅቱ ከባድ የጦር መሣሪያዎችን እና ሌሎች ሕገወጥ የጦር መሣሪያዎችን ለመሸሸግ የሚጠቀምባቸውን እና ወደ ወታደራዊ መገልገያነት የቀየራቸውን የተወሰኑ ቦታዎች ከጥቅም ውጭ ለማድረግ ያለመ ነው ሲልም አስታውቋል። [FBC] @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
18 087
14
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚካሄደውን ምርጫ አስመልክቶ ጊዜያዊ የጊዜ ሰሌዳ ለፓርቲዎች እና ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ይፋ አደርገ! የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው አጠቃላይ ምርጫን በአብዛኛው የአገራችን ክፍሎች አከናውኖ እጠናቋል።በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ በሚገኙ 17 ምርጫ ክልሎች (በአብዛኛው የክልል ምክር ቤት) ምርጫ ሳይካሄድ ቀርቷል።በክልል የሚያስፈልገው የጸጥታ ፍላጎቶች ከተሟሉ ምርጫው ሊከናወንበት የሚችልበትን ጊዜያዊ ሰሌዳ ለፓርቲዎች እና ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ይፋ አድርጓል። @YeneTube @FikerAssefa
17 355
4
ፌስቡክ የስያሜ ለዉጥ ሊያደርግ መሆኑ ተሰማ! ግዙፉ ማህበራዊ ሚዲያ ተቋም ፌስቡክ ከሚቀጥለዉ ሳምንት ጀምሮ የስያሜ ለዉጥ ለማድረግ ማቀዱን ቨርጅ የተሰኘዉ የዜና ምንጭ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸዉ ሰዎች መስማቱን ጠቅሶ ዘግቧል። አዲሱ ስያሜ በመጭዉ ማክሰኞ ጥቅምት 16፤ 2014 ዓ.ም በኩባንያው ዓመታዊ ኮንፈረንስ ላይ በድርጀቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማርክ ዙከርበርግ ይፋ ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ዘገባዉ ያመላከተ ሲሆን ፌስቡክ በምላሹ በጉዳዩ ላይ አስተያየት አለመስጠቱም የተጠቀሰ ሲሆን የስያሜ ለውጥ ዜናው የተሰማው በኩባንያው የንግድ አሰራር ላይ ከአሜሪካ መንግስት የሚደረግበት ቁጥጥርና ወቀሳ እያየለ በመጣበት ወቅት መሆኑን ዘገባው አስታዉሷል። በሲሊከን ቫሊ የቴክኖሎጂ መንደር ውስጥ የሚገኙ ኩባንያዎች አገልግሎታቸዉን በማስፋፋት በሚያደርጉት የንግድ ውድድር ስያሜያቸውን መቀየር ብዙም የተለመደ አይደለም።ከወራት በፊት ፌስቡክ የአገልግሎቱን ትኩረት ሜታቨርስ ወደተሰኘ ሰዎች የተለያዩ መሣሪያዎችን በመጠቀም በምናባዊ እውነታ (ቨርቹዋል ሪያሊቲ) ውስጥ ተሳትፎ የሚያደርጉበትን አሰራር ለማስተዋወቅ መዘጋጀቱን ይፋ አድርጎ ነበር። ✍Addis Zeybe @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
16 566
21
ሞሮኮ 310 ህገወጥ ስደተኞች ባህር ሊያቋርጡ ሲሉ መያዟን ገለጸች! የሞሮኮ የባህር ኃይል 310 የሚሆኑ ህገወጥ ስደተኞች በሜድትራኒያንና በአትላንቲክ ባህር ዳርቻዎች አድርገው ወደ አውሮፓ ሊያቀኑ ሲሉ መያዙን አስታውቋል፡፡አብዛኞቹ ስደተኞች ከሰሀራ በታች የመጡ የመጡ ሲሆን ከስደተኖቹ ውስጥ 23 ሴቶችና 9 ህጻናት ይገኙበታል፡፡ስደተኞቹ በሚንቀሳቀሱበት ጉዜ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ማለፋቸውን የሞሮኮ መንግስት አስታውቋል፡፡ [Alain] @YeneTube @FikerAssefa
15 700
8
በሶማሌ ክልል የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ተገለጸ! ከመሀል አገር በሶማሌ ክልልን አቋርጦ ወደ ጎረቤት አገሮች የሚጓጓዝ የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ ባለፉት ሦስት ዓመታት ከደቡብ ክልልና ከመሀል አገር ተጭኖ ወደ ጎረቤት ኬንያ፣ ሶማሊያና ሌሎች መዳረሻ አገሮች ሊጓዝ ሲል በቁጥጥር ሥር የሚውለው የአደንዛዥ ዕፅ መጠን እየተበራከተ መምጣቱን የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ረዳት ኮሚሽነር መሐመድ አሊ አስታውቀዋል፡፡ ኮሚሽነሩ አጠቃላይ የክልሉን የፀጥታ ጉዳይ አስመልክተው ማክሰኞ ጥቅምት 9 ቀን 2014 ዓ.ም. በጅግጅጋ ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በየቀኑ በመኪና ተጭኖ ከአገር ሊወጣ ሲል የሚያዘው የዕፅ መጠን ከፍተኛ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ Via Reporter @YeneTube @FikerAssefa
15 118
7
ለ 12ተኛ ክፍል ተማሪዎች የኢንትራንስ መፈተኛ ቀን ተቃርቧል በዚህ ወቅት ከማጥናት ባሻገር ያለፉትን ዓመት ጥያቄዎች መስራት ጉልህ ሚና አለው። ለዚህም በኢትዮጵያ ከ100,000 በላይ ተጠቃሚዎች ያሉት EthioMatric አፕሊኬሽን ቀርቦላችኋል። - EthioMatric ከ2008-2012/13 ዓ.ም የ4 እና የ5 ዓመት የኢንትራንስ ፈተናዎች ከነመልሶቻቸው እና ከነማብራሪያቸው በየምዕራፉ ከፋፍሎ አስቀምጧል፡፡ EthioMatric አፕሊኬሽን ለማውረድ 👇👇 https://play.google.com/store/apps/details?id=com.addismatric.addismatric ለበለጠ መረጃ @ethiomatric
14 304
109
🥾🥾🥾 It gives our team a great pleasure letting you all know that, we are now collaborating with @shegerhive @Cheenahiking organized a Camping trip to Ajora Waterfalls on October 30 & 31, 2021. The two day trip will allow participants a camping opportunity at the twin waterfalls. The package includes meals, BBQ, Campfire, entrance fees, guide fees, trekking and more for only 2,750 ETB. 👉Note that Package fee must be paid upon registration to secure a spot and discounts are available until Oct 16 Saturday. For booking, contact 0951 10 19 07/09. Make sure to register now! #Shegerhive #hiking #AddisAbaba #Ethiopia
Show more ...
13 857
5
🎁 #ArtLand_Gifts 🎁 ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ✿ "እማይረሱ ስጦታዎችን ለሚወዷቸው 🎁 " ✔️የወደዱትን "ፎቶ ወይም ምስል" እንጨት እና ቆዳ(ሌዘር) ላይ እንሰራለን👌 🏷ለልደት 🏷ለምርቃት 🏷ለሰርግ 👰🤵 🏷ለፍቅረኛዎ❤️ 🏷ለቤተሰቦ 👪 🏷ለቢዝነስ ካርድ 🏷 ለቤት, ለካፌ እና ለተለያዩ ነገሮች ማሳመሪያ የሚሆኑ ምስሎችን እንደሚወዱት አርገን እንሰራለን 👍 ከአዲስ አበባ ውጪ ላሉ ደንበኞቻችን በ EMS / DHL እናደርሳለን 📦 🔘ስልክ : 📞(093) 146-5618 🔘For Order @artlandgifts 🚚 ይዘዙን ያሉበት ድረስ እናደርሳለን🏍🏍 Join our channel👇 @artlandengraving @artlandengraving
16 369
7
ዘ ቴሌግራፍ በጠ/ሚር አብይ ንግግር ዙርያ የሰራው የተሳሳተ ዘገባ! የእንግሊዙ ዘ ቴሌግራፍ "የኢትዮጵያው ጠ/ሚር የእርዳታ ምግብ ወደሀገራቸው መግባቱን አስቆማለሁ ብለው ዛቱ" የሚል ዘገባ ትናንት ሰርቶ አስነብቧል። ሚድያው አክሎም ጠ/ሚሩ ይህንን ያሉት የአለም አቀፍ ጫናን ለመቀነስ አስበው እንደሆነ ፅፏል። ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ አጭር ማጣራት ያረገ ሲሆን ጠ/ሚር አብይ አህመድ በአማርኛ የተናገሩት ንግግር "... በደንብ ሰርተን ስንዴ የሚባል ነገር እንዳይገባ ካደረግን 70 ፐርሰንት የኢትዮጵያ ችግር ይራገፋል" የሚል እንደሆነ ተመልክቷል። ጠ/ሚሩ በዚሁ ንግግራቸው "ሁሉም የኢትዮጵያ ክልል በቀጣይ አመት የስንዴ ክላስተር 30 እና 40 ፐርሰንት ከተገበረ አንድ ኪሎ ስንዴ ኢትዮጵያ አይገባም" ብለው ነበር። ይህንንም ያሉት በቅርብ ቀናት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በመሄድ የግብርና እንቅስቃሴዎችን በጎበኙበት ወቅት ነበር። ይህም በግልፅ እንደሚያሳየው "...ስንዴ የሚባል ነገር እንዳይገባ..." የሚለው አገላለፅ ራስን በምግብ ከመቻል ጋር ተያይዞ የቀረበ እንጂ የእርዳታ ምግብ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ለማድረግ ከመዛት ወይም ከማስፈራራት ጋር የተያያዘ አይደለም። Via @EthiopiaCheck @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
19 526
17
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ትናንት ከመቀሌ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው መሶቦ ስሚንቶ ፋብሪካ አካባቢ በፈጸመው ጥቃት 3 ሕጻናት መሞታቸውን እና አንድ ሰው መቁሰሉን የተመድ ሰብዓዊ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ መናገሩን ሮይተርስ ዘግቧል። በከተማዋ ማዕከላዊ ክፍል በተፈጸመው ሁለተኛው ድብደባ ደሞ 9 ሰዎች እንደቆሰሉ ቢሮው የሕክምና ባለሙያዎችን ዋቢ አድርጎ ተናግሯል። የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የአየር ድብደባ እጅጉን እንዳሳሰባቸው በቃል አቀባያቸው በኩል አስታውቀዋል። ጉተሬዝ ሁሉም የግጭቱ ተፋላሚ ወገኖች ሲቪል ሰዎችንና መሠረተ ልማቶችን ዒላማ ከማድረግ እንዲቆጠቡ ጠይቀዋል። [Wazema] @YeneTube @FikerAssefa
18 616
9
በመንግሥት ተቋማት የተያዙ መሬቶችን ለቤት ልማት ማዋል መጀመሩ ተጠቆመ! በፌዴራልና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር ባሉ መንግሥታዊ ተቋማት የተያዙ ክፍትና ሥራ ላይ ያልዋሉ ቦታዎች፣ ለቤቶችና ሌሎች ልማት እንዲውሉ የተቀመጠውን አቅጣጫ ተግባራዊ ማድረግ ተጀምሯል ተባለ፡፡ መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) አዲስ ለተቋቋመው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የተነሱ ጥያቄዎችን ሲመልሱ እንደገለጹት፣ በመንግሥት ተቋማት የተያዙ መሬቶች ለአገልግሎት ሳይውሉ፣ በአንጻሩ ዜጎች በመኖሪያ ቤት እጥረት መሰቃየታቸው ከሀብት አስተዳደር አንጻር ያለውን ክፍተት በግልጽ ያሳያል፡፡ በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳነሱት በአዲስ አበባ፣ በቦሌና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍላተ ከተሞች ብቻ በድምሩ 600 ቢሊዮን ብር የሚገመት መሬት በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ያለአግባብ ተይዟል፡፡ [Reporter] @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
19 230
14
በሕወሓት ኃይሎች ቁጥጥር ስር የነበረችውን የውጫሌ ከተማ የመንግስት ወታደሮች እና አጋሮች ትናንት ሰኞ መቆጣጠራቸውን የአካባቢው ነዋሪ ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። በአካባቢው እየተካሄደ ባለው ጦርነት ደሴና አካባቢዋ በተፈናቃዮች ከመጨናነቅ ውጪ ሰላማዊ መሆኑን የደሴ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል፡፡አንድ የውጫሌ ከተማ ነዋሪ በስልክ እንዳረጋገጡት የሕወሓት ተዋጊዎች ትናንት ለጥቂት ሰዓታት ተቆጣጥረዋት የነበረችውን ታሪካዊዋን የውጫሌ ከተማ የመከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የመንግስት ኃይሎች በጋራ በወሰዱት እርምጃ ከተማውን አስለቅቀዋል። “ውጫሌ በመከላከያ መልሶ ተይዟል ፣ ትናንትናማ ይዘውት 10 ሰዓት በዚህ ሰዓት ነው ኮማንዶ ገብቶ ያስለቀቀው፣ በአንፃራዊነት ጥሩ ነው፡፡ቆርጠው የገቡት ወደዚህ ጎልቦ የምትባል ታውቃት ከሆነ ወደዚያ፣ እዛ አካባቢ የተወሰኑ ቆርጠው ነበር የት እንደገቡ አይታወቅም፣እነሱ ናቸው አሁን እያሰጉ ያሉት፣ ሌላ ሰላም ነው ” የባሕርዳሩ የዶይቸ ቨለ ዘጋቢ ያነጋገራቸው የደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አበበ ገ/መስቀል በበኩላቸው በደሴ ከተማ ከተፈናቃዮች ቁጥር መጨመር ውጪ በከተማዋ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መኖሩን ተናግረዋል።“ሰላም ነው፣በሰላም ነው።ሁሉም ነገር የተረጋጋና መደበኛ ስራው እንደቀጠለ ነው፣ ሆቴሎች፣ ሱቆች፣ ካፌዎች ፣ ትራንስፖርት ሁሉም በልዩ ሁኔታ ጥሩ ነው”። Via DW @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
18 865
23
በቡና ገበያ ተቋማት እየተወዛገቡ ነው! ባሳለፍነው ሰኞ ጥቅምት 1 የኢትዮጵያ ምርት ገበያ (ECX) በቡና ግብይት ላይ አዳዲስ ለውጦች ማድረጉን ካሳወቀ በኋላ ከቡና እና ሻይ ባለስልጣን ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብቷል።ECX በማስታወቂያው የቡና ግብይት የመዋዠቅ መቶኛ ቀደም ሲል ከነበረው የ5 በመቶ መጠን ወደ 10 በመቶ እንዲሰፋ ሲወስን፤ የቡናን ደረጃ ከቀድሞው 9 ደረጃዎች እና UG ወደ 5 እና UG ያወረደ ነው። ሆኖም ይህን ውሳኔ የቡና እና ሻይ ባለስልጣን ክፉኛ ኮንኖ ግብይቱን ችግር ውስጥ የሚከት ነው ብሏል።ባለስልጣኑ ማክሰኞ ጥቅምት 2 ለክልሎች በፃፈው ደብዳቤ አዲሱ የECX አሰራር ባለድርሻዎችን ሳያማክር በተናጠል የተወሰ ነው ሲል ቅሬታውን ገልፆ ተግባራዊ እንደማይደረግም በአፅንኦት ገልጿል። በተመሳሳይ ECX ሀሙስ ጥቅምት 4 ለግብርና ሚኒስቴር በፃፈው ደብዳቤ የባለስልጣኑን ውሳኔ አጣጥሎታል። በተጨማሪም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የቡና እና ሻይ ባለስልጣን ውሳኔውን የሚቀለብስ ደብዳቤ እንዲያወጣ እንዲያደርግለት ጠይቋል።በምላሽ ደብዳቤው ECX ያሳለፈው ውሳኔ ቡና እና ሻይ ባለስልጣንን ጨምሮ በባለድርሻዎች ምክክር ተደርጎበት የተወሰነ ነው ሲል ገልጿል። Via Capital @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
17 810
14
በደሴ ከተማ የተፈናቃዮች ቁጥር መጨመር ለጸጥታ ስራው እንቅፋት እንደሆነበት የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ! በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል አሸባሪው ህወሓት የከፈተውን ግጭት በመሸሽ በርካታ ቁጥር ያላቸው ተፈናቃዮች ወደ ደሴ ከተማ እየገቡ ይገኛል፡፡ይህም በከተማዋ ላይ የጸጥታ ሀይሉ ለሚያደርገው የሰላም እና የጸጥታ ስራ ፈተና እንደሆነበት የደሴ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ቢሮ አስታውቋል፡፡ በከተማዋ በሚገኙ ሁሉም የግል እና የመንግስት ትምህርት ቤቶች፣ የመምህራን ማሰልጠኛ ተቋማትና ኮሌጆች በተፈናቃዮች መያዛቸውን የደሴ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ሀላፊ ዋና ኢንሲፔክተር ሀሰን መሀመድ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡ሆኖም ከተፈናቃዮች ቁጥር አንጻር ይህም በቂ ባለመሆኑ በየቦታው ተፈናቃዮች በመኖራቸው የጸጥታውን ሁኔታ ለመቆጣጠር አስቸጋሪ አድርጎብናል ብለዋል፡፡ የደሴ ከተማ አስተዳደር የተፈናቃዮች ቁጥር መጨመር ከአቅሜ በላይ ነው የተወሰኑትን ወደ ሌሎች ከተሞች ለመውሰድ ለክልሉ ቢሮ ጥያቄ ቢያቀርብም እስካሁን መልስም ሆነ መፍትሄ አለማግኘቱን ዋና ኢንሲፔክተር ሀሰን ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡ ሆኖም እንደ ደሴ ከተማ አስተዳደርም የተለያዩ ዕቅዶችን በማዘጋጀትና ከደቡብ ወሎ ዞን፣ በዙሪያው ከሚገኙ የከተማ አስተዳደሮችና ወረዳዎች ጋር በየዕለቱ የጸጥታውን ሥራ ተቀናጅተን እየሠራን እንገኛለን በህዝቡና በጸጥታ ሀይሉ አማካይነት በተለያዩ ኬላዎችን፣ አልጋ ቤቶች፣ የእግረኛና ተሸከርካሪዎች ላይ ጥብቅ ፍተሻ እየተደረገ ይገኛል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ [ዳጉ ጆርናል/Bisrat FM] @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
17 698
7
ለተማሪዎች ሰርቪስ የሚሰጡ ታክሲዎች አገልግሎት እንዳይሰጡ ታግደዋል በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑ ተገለጸ! ለተማሪዎች ሰርቪስ የሚሰጡ ታክሲዎች አገልግሎት እንዳይሰጡ ታግደዋል በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ለተማሪዎች ሰርቪስ የሚሰጡ ታክሲዎችን በተመለከተ አገልግሎት እንዳይሰጡ የሚከለክል መመሪያ እንደተዘጋጀ የሚዘዋወረው መረጃ ትክክል አይደለም ብሏል፡፡ ሕጋዊ ፈቃድ የሌላቸው ታክሲዎች በተማሪዎች የሰርቪስ አገልግሎት ላይ በመሰማራታቸው በትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እየፈጠረ እንደሚገኝ ቢሮው መግለጹን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡ በቀጣይም የትራንስፖርት እጥረቱን በተመለከተ ግምገማ ተደርጎ የመፍትሔ አቅጣጫ የሚቀመጥና ዝርዝር መረጃም የሚወጣ ይሆናል ተብሏል፡፡ በመሆኑም የተማሪዎች ሰርቪስን በተመለከተ አዲስ መመሪያ እስኪወጣ ከዚህ ቀደም አገልግሎቱን ሲሰጡ የነበሩ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው ታክሲዎች በነበሩበት ሥራ እንዲቀጥሉ ቢሮው ጥሪ አቅርቧል፡፡ @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
18 293
11
በኢትዮጵያ በሁሉም አካባቢዎች የፖሊዮ ቫይረስ መኖሩ ተረጋግጧል ተባለ፡፡ በዚህም ከመጪው ጥቅምት 15 ጀምሮ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ እንደሚካሄድ ተነግሯል፡፡የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩ እና የጤና ሚኒስቴር ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን ከመጪው ጥቅምት 12 እስከ 15፣ 2014 ዓ.ም በዘመቻ ይሰጣል ተብሏል፡፡ ክትባቱ የሚሰጠው በሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች የፖሊዮ ቫይረስ ታማሚዎች ሪፖርት በመደረጉ ነው ተብሏል፡፡የክትባት ዘመቻው በሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ለሚገኙ እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ላሉ ከ17 ሚሊየን በላይ ህፃናት እንደሚደርስ ተነግሯል፡፡ ክትባቱን ለመስጠት የሚያገለግሉ አስፈላጊ ግብዓቶች መሰራጨታቸው ተነግሯል፡፡ክትባቱ የሚሰጠው በሰለጠኑ የክትባት ባለሙያዎች ቤት ለቤት ሲሆን በሚመጡበት ጊዜ አስፈላጊውን ትብብር አድርጉላቸው ሲል የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳስቧል፡፡ Via Sheger FM @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
18 405
16
በትግራይ እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተወሰነ፡፡ በሀገራችን የሰሜኑ ክፍል በህወሃት አሸባሪ ቡድን በተፈጠረው ችግር ምክንያት በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎችና በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች በጊዜያዊነት ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እና ወልዲያ የኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲ በጊዜያዊነት ለመመደብ የመመዝገቢያ ገፅ ተከፍቶ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ እና ምደባ እንደሚካሄድም ተገልጿል፡፡ በዚህም በዩኒቨርስቲዎቹ ትምህርትቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች አስፈላጊውን የትምህርት ማስረጃቸውን በማዘጋጀት ከ ዛሬ ጀምሮ መመዝገብ እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡ ለመመዝገብ https://forms.gle/wYpZtTqpdQ417Bxx8 በመጠቀም የተቀመጠውን ፎርም እንዲሞሉ እና ምዝገባ እንዲያካሂዱ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡ Via MoE @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
18 514
113
በውጫሌ ከተማ በተፈጸመ የከባድ መሣሪያ ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ! በአማራ ክልል፣ በደቡብ ወሎ ዞን፣ በአምባሰል ወረዳ በምትገኘው ውጫሌ ከተማ በተፈጸመ የከባድ መሣሪያ ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ።የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት በሽብርተኛ ቡድንነት ከተፈረጀው ህወሓት ጋር እያካሄደ ያለው ጦርነት ከተጀመረ አንድ ዓመት ሊሞላው ጥቂት ሳምንታት የቀሩት ሲሆን ጦርነቱ ወደ አፋርና አማራ ክሎች ተስፋፍቶ ይገኛል።ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ በአማራና በአፋር ክልሎች ውስጥ መልሶ ባገረሸው ጦርነት ወቅት የህወሓት ኃይሎች በውጫሌና በጭፍራ አካባቢዎች ላይ በፈጸሙት የከባድ መሳሪያ ጥቃት ከ30 በላይ ሰዎች መገደላቸውን መንግሥት አሳውቋል። የአምባሰል ወረዳ ኮምዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ሀብቴ መለሰ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የህወሓት አማጽያን በውጫሌ ከተማ ላይ በፈጸሙት የከባድ መሣሪያ ጥቃት ሁለት ወንድማማቾችን ጨምሮ በአጠቃላይ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት አልፏል።"እሁድ ዕለት ወደ ከተማዋ ከባድ መሣሪያ ተተኩሶ የዘጠኝ ሰው ሕይወት አልፏል። ከአንድ ቤት ሁለት ወንድማማቾች ሞተዋል። መደበኛ ሥራ ላይ የነበሩ እና በመሸሽ ላይ የነበሩም ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል" ብለዋል።በተጨማሪም አራት ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል ገብተው ሕክምና በመከታተል ላይ እንደሚገኙም አክለዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እየተካሄደ ያለውን ጦርነት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ላይ አማጺያኑ በአማራና በአፋር ክልል ውስጥ የሚገኙ አዋሳኝ አካባቢዎችን ዒላማ በማድረግ "ሰላማዊ ሰዎች ላይ ተቀባይነት የሌለው ጥቃት" ፈጽመዋል ብሏል።አዲስ የተዋቀረው የኮምዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኀን ሰኞ ዕለት በሰጡት መግለጫ፣ የህወሓት ኃይሎች በውጫሌና ጭፍራ አካባቢዎች ላይ ፈጸሙት ባሉት ጥቃት ከ30 በላይ ንጹኀን ሰዎችን መግደላቸውንና በርካቶችን መፈናቀላቸውን ተናግረዋል። Via BBC @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
15 942
10
ቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተመልሷል! የጨዋታ ውጤቶችን #ከዛሬ ጀምሮ በመገመት ነጥብዎትን ይሰብስቡ። ከፍተኛ ነጥብ ለሚያገኙ ገማቾች የተለያዩ አጓጊ ሽልማቶች ተዘጋጅተዋል። - DSTV ዲኮደር ከ1 ወር ነፃ ፓኬጅ ጋር - ኳስ እና የሚወዱትን ክለብ መለያ - Wireless Mouse - ብሉቱዝ ስፒከር እና - ፍላሽ ዲስክ እና ሌሎች አጓጊ ሽልማቶች ተዘጋጅተዋል። ቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን በቀጥታ የሚከታተሉበት ምርጥ የሞባይል አፕ። መረብ ስፖርት | Mereb Sport ----------------==------------------- ከPlay Store ዳውንሎድ ያድርጓት 👇 ዛሬውኑ ይገምቱ! https://play.google.com/store/apps/details?id=com.adika.merebsport የውድድር ህጎችን ለማንበብ - https://merebsport.net/gamerules/
Show more ...
14 856
3
🎁 #ArtLand_Gifts 🎁 ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ✿ "እማይረሱ ስጦታዎችን ለሚወዷቸው 🎁 " ✔️የወደዱትን "ፎቶ ወይም ምስል" እንጨት እና ቆዳ(ሌዘር) ላይ እንሰራለን👌 🏷ለልደት 🏷ለምርቃት 🏷ለሰርግ 👰🤵 🏷ለፍቅረኛዎ❤️ 🏷ለቤተሰቦ 👪 🏷ለቢዝነስ ካርድ 🏷 ለቤት, ለካፌ እና ለተለያዩ ነገሮች ማሳመሪያ የሚሆኑ ምስሎችን እንደሚወዱት አርገን እንሰራለን 👍 ከአዲስ አበባ ውጪ ላሉ ደንበኞቻችን በ EMS / DHL እናደርሳለን 📦 🔘ስልክ : 📞(093) 146-5618 🔘For Order @artlandgifts 🚚 ይዘዙን ያሉበት ድረስ እናደርሳለን🏍🏍 Join our channel👇 @artlandengraving @artlandengraving
17 667
2
🥾🥾🥾 It gives our team a great pleasure letting you all know that, we are now collaborating with @shegerhive @Cheenahiking organized a Camping trip to Ajora Waterfalls on October 30 & 31, 2021. The two day trip will allow participants a camping opportunity at the twin waterfalls. The package includes meals, BBQ, Campfire, entrance fees, guide fees, trekking and more for only 2,750 ETB. 👉Note that Package fee must be paid upon registration to secure a spot and discounts are available until Oct 16 Saturday. For booking, contact 0951 10 19 07/09. Make sure to register now! #Shegerhive #hiking #AddisAbaba #Ethiopia
Show more ...
14 267
2
የሕወሓት ታጣቂዎች ሰሞኑን በአማራ እና አፋር ክልሎች ከፍተውታል በተባለ "መጠነ ሰፊ የማጥቃት ዘመቻ" ከሰላሳ የማያንሱ ንፁሃን ዜጎች መገደላቸውን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ። ኃላፊ ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሠ ቱሉ እንዳሉት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው ቡድን በሁለቱ ክልሎች ላይ ከባድ መሣሪያ በመተኮስ ሲቪል የከተማ ሕብረተሰብን ከመግደል ባለፈ እንዲሸበርና እንዲፈናቀል አድርጓል። ጦርነቱ የማይመለከተው የኢትዮጵያ ክፍል እንደሌለ የገለፁት ኃላፊው ሕወሓት የከፈተው የሕዝብን ማዕበል መሠረት ያደረገ ጦርነት በመሆኑ መከላከል የሚቻለው ጦርነቱ ባለበት ቀጣና አካባቢ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ሕዝባዊ ማዕበል በማድረግ ነው ብለዋል። [DW] @YeneTube @FikerAssefa
24 312
12
የኢፌዲሪ አየር ሃይል በመቀለ ህወሃት ሲጠቀምባቸው በነበሩ የመገናኛ አውታሮችና መሳሪያዎች ላይ የተሳካ እርምጃ ወስዷል ተባለ! የኢፌዲሪ አየር ኃይል ዛሬ በመቀሌ ከተማ ህወሓት ለሽብር ተግባር ሲጠቀምባቸው በቆዩ የመገናኛ አውታሮችና መሳሪያዎች ላይ እርምጃ ወስዷል። አየር ኃይሉ የወሰደው እርምጃ የፈደራል መንግስት ይዞታ በነበሩና አሸባሪው ህወሓት አገር ለማፍረስ እየተጠቀመባቸው በቆዩ ይዞታዎች ላይ መሆኑ ተገልጿል። በዚህ መሰረት የአየር ድብደባው እንደ ፋና በመሰሉ የሚዲያና የኢንሳ ታወሮች እና መሳሪያዎች ላይ ያነጣጠረ እንደነበረና ተልዕኮውም በስኬት መጠናቀቁ ታውቋል። የኢፌዲሪ አየር ኃይል ዛሬ በፈጸመው ድብደባ ንጹሃን ዜጎች እንዳይጎዱ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረጉንና ይህም በተሳካ ሁኔታ መፈጸሙ ተገልጿል። Via EPA @YeneTube @FikerAssefa
20 350
32
የኢፌዲሪ አየር ሃይል በመቀለ አሸባሪው ሲጠቀምባቸው በነበሩ የመገናኛና አውታሮችና መሳሪያዎች ላይ የተሳካ እርምጃ ወስዷል ተባለ! የኢፌዲሪ አየር ኃይል ዛሬ በመቀሌ ከተማ አሸባሪው ህወሓት ለሽብር ተግባር ሲጠቀምባቸው በቆዩ የመገናኛ አውታሮችና መሳሪያዎች ላይ እርምጃ ወስዷል። አየር ኃይሉ የወሰደው እርምጃ የፈደራል መንግስት ይዞታ በነበሩና አሸባሪው ህወሓት አገር ለማፍረስ እየተጠቀመባቸው በቆዩ ይዞታዎች ላይ መሆኑ ተገልጿል። በዚህ መሰረት የአየር ድብደባው እንደ ፋና በመሰሉ የሚዲያና የኢንሳ ታወሮች እና መሳሪያዎች ላይ ያነጣጠረ እንደነበረና ተልዕኮውም በስኬት መጠናቀቁ ታውቋል። የኢፌዲሪ አየር ኃይል ዛሬ በፈጸመው ድብደባ ንጹሃን ዜጎች እንዳይጎዱ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረጉንና ይህም በተሰካ ሁኔታ መፈጸሙ ተገልጿል። Via EPA @YeneTube @FikerAssefa
1
0
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቐለ ዛሬ ሰኞ የአየር ድብደባ መፈጸሙን የግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ሰራተኞች እና ዲፕሎማቶች ተናገሩ። የትግራይ ቴሌቭዥን ጣቢያ በፌስቡክ ገጹ ባሰፈረው ጽሁፍ በአየር ድብደባው ሶስት ሰዎች መገደላቸውን እና በ10 የሚቆጠሩ መቁሰላቸውን ገልጿል።የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ተፈጸመ የተባለውን የአየር ድብደባ አስተባብሏል። በከተማው የሚገኙ ሁለት የግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ሰራተኞች የአየር ድብደባው መፈጸሙን በአጭር የጽሁፍ መልዕት ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት (AFP) ገልጸዋል።ሌሎች ሁለት ዲፕሎማቶችም ጥቃቱ መፈጸሙን እንደተናገሩ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። በዘገባዉ መሠረት የመጀመሪያው ድብደባ ዛሬ ሰኞ ጠዋት በመቐለ ዳርቻ ስሚንቶ ፋብሪካ ከሚገኝበት አካባቢ ተፈጽሟል። ሁለተኛዉ ድብደባ ዛሬ ዕኩለ-ቀን በመቐለ ማዕከላዊ ክፍል ባለሥልጣናት የሚያዘወትሩት ፕላኔት ሆቴል አካባቢ እንደተፈጸመ የዜና ወኪሉ ዘግቧል። የህወሓት ቃል-አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በተረጋገጠ የትዊተር ገጻቸው የአየር ድብደባው መፈጸሙን አረጋግጠው "ሰኞ በመቐለ የገበያ ቀን ነው። [የጥቃቱ] ዓላማ ግልጽ ነው" ብለዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የኢትዮጵያ መንግሥት እስካሁን በጉዳዩ ላይ የሰጡት መግለጫ የለም። በጥቃቱ የደረሰው ጉዳትን በተመለከተ በመቐለ ከሚገኙ የሕክምና ተቋማት ማረጋገጫ አልተገኘም። የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ተፈጸመ የተባለውን የአየር ድብደባ አስተባብሏል። የመንግሥት ኮምዩንኬሽን አገልግሎት ኃላፊ ለገሰ ቱሉ "መንግሥት ለምን የራሱን ከተማ ያጠቃል? መቐለ የኢትዮጵያ ከተማ ነች" ሲሉ ለሬውተርስ ተናግረዋል። [DW] @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
19 971
15
በኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ክትባት በግሉ ዘርፍ መሰጠት ተጀመረ! በኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ክትባት በሜዲቴክ ኢትዮጵያ እና በዋሽንግተን የህክምና ማዕከል የጋራ ትብብር መሰጠት ተጀመረ።የግል ተቋሞቹ ክትባቱን በክፍያ መስጠት መጀመራቸውን በመግለፅ፤ ከቻይናዉ የክትባት አምራች ሲኖፋርም ጋር የኹለት ሚሊዮን ዶዝ ዉል መፈራረማቸውንም አስታውቀዋል። ክትባቱን ከቻይናው ድርጅት ለማግኘት ከስድስት ወር በላይ እንደፈጀ የሚዲቴክ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር መሃመድ ኑሪ የገለጹ ሲሆን፣ ክትባቱን ሜዲቴክ ኢትዮጵያ በአቅራቢነት እንዲሁም፤ ዋሽንግተን የህክምና ማዕከል ደግሞ ለተጠቃሚዎች የማድረስን ስራ ይሰራሉ ተብሏል።የመጀመሪያ ዙር 200 ሺሕ ዶዝ ክትባት ዛሬ አዲስ አበባ መግባቱም ተገልጿል። [Addis Maleda] @YeneTube @FikerAssefa
20 531
17
አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተመረጡ! የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ መረጠ።አቶ ሙስጠፌ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በመቀበል ቃለ-መሓላ ፈፅመዋል። @YeneTube @FikerAssefa
19 575
6
የሶማሌ ክልል የመንግስት ምስረታውን በጅግጅጋ ከተማ እያከናወነ ይገኛል። በስነስርአቱ ላይ የማእከላዊው መንግስት እና የክልላት የስራ ሃላፊዎች የተገኙ ሲሆን። የ ጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ሶማልያ እና ሶማሌላንድ ከፍተኛ ባለስልጣናትም በመንግስት ምስረታው ተገኝተዋል።በ6ኛው የክልሉ ምርጫ ያሸነፈው ብልፅግና ሙስጠፌ ሞሃመድን ፕሬዝደንት አድርጎ ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል። አዲስ የሚቋቋመውም ካቢኔ አዳዲስ ተሿሚዎችን ሳያካትት እንደማይቀር ተገምቷል። [Capital] @YeneTube @FikerAssefa
18 464
4
ቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተመልሷል! የጨዋታ ውጤቶችን #ከዛሬ ጀምሮ በመገመት ነጥብዎትን ይሰብስቡ። ከፍተኛ ነጥብ ለሚያገኙ ገማቾች የተለያዩ አጓጊ ሽልማቶች ተዘጋጅተዋል። - DSTV ዲኮደር ከ1 ወር ነፃ ፓኬጅ ጋር - ኳስ እና የሚወዱትን ክለብ መለያ - Wireless Mouse - ብሉቱዝ ስፒከር እና - ፍላሽ ዲስክ እና ሌሎች አጓጊ ሽልማቶች ተዘጋጅተዋል። ቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን በቀጥታ የሚከታተሉበት ምርጥ የሞባይል አፕ። መረብ ስፖርት | Mereb Sport ----------------==------------------- ከPlay Store ዳውንሎድ ያድርጓት 👇 ዛሬውኑ ይገምቱ! https://play.google.com/store/apps/details?id=com.adika.merebsport የውድድር ህጎችን ለማንበብ - https://merebsport.net/gamerules/
Show more ...
16 841
9
🎁 #ArtLand_Gifts 🎁 ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ✿ "እማይረሱ ስጦታዎችን ለሚወዷቸው 🎁 " ✔️የወደዱትን "ፎቶ ወይም ምስል" እንጨት እና ቆዳ(ሌዘር) ላይ እንሰራለን👌 🏷ለልደት 🏷ለምርቃት 🏷ለሰርግ 👰🤵 🏷ለፍቅረኛዎ❤️ 🏷ለቤተሰቦ 👪 🏷ለቢዝነስ ካርድ 🏷 ለቤት, ለካፌ እና ለተለያዩ ነገሮች ማሳመሪያ የሚሆኑ ምስሎችን እንደሚወዱት አርገን እንሰራለን 👍 ከአዲስ አበባ ውጪ ላሉ ደንበኞቻችን በ EMS / DHL እናደርሳለን 📦 🔘ስልክ : 📞(093) 146-5618 🔘For Order @artlandgifts 🚚 ይዘዙን ያሉበት ድረስ እናደርሳለን🏍🏍 Join our channel👇 @artlandengraving @artlandengraving
18 011
3
🥾🥾🥾 It gives our team a great pleasure letting you all know that, we are now collaborating with @shegerhive @Cheenahiking organized a Camping trip to Ajora Waterfalls on October 30 & 31, 2021. The two day trip will allow participants a camping opportunity at the twin waterfalls. The package includes meals, BBQ, Campfire, entrance fees, guide fees, trekking and more for only 2,750 ETB. 👉Note that Package fee must be paid upon registration to secure a spot and discounts are available until Oct 16 Saturday. For booking, contact 0951 10 19 07/09. Make sure to register now! #Shegerhive #hiking #AddisAbaba #Ethiopia
Show more ...
15 154
5
እንኳን ለ1496ኛው የነቢዩ መሐመድ (ሠዓወ) የልደት በዓል(መውሊድ) በሰላም አደረሳችሁ! መልካም በዓል!
19 573
30
በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ለተቸገሩ ወገኖች ከ27 ሺህ 900 ኩንታል በላይ እህል ተከፋፈለ! በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ለተቸገሩ ወገኖች ከ27 ሺህ 900 ኩንታል በላይ እህል ለተጎጂዎች መድረሱን የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደበበ ዘውዴ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ በአካባቢው ባጋጠመው የዝናብ እጥረት ሳቢያ በተከሰተው ድርቅ ነዋሪዎች ለችግር ተዳርገዋል።ይህንንም ተከትሎ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ችግረኞችን ለመርዳት በተለይም አስቸኳይ የምግብ እህል አቅርቦት እንዲያገኙ አድርጓል ብለዋል። በአገሪቱ ቆላማና ድርቅ በተከታታይ ከሚያጠቃቸው አካባቢዎች መካከል የቦረና ዞን አንዱ መሆኑን ገልፀው ኮሚሽኑ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።በዚህም በዞኑ በተከሰተው ድርቅ ለተቸገሩ ወገኖች ከ27 ሺህ 900 ኩንታል በላይ እህል ለተጎጂዎች መድረሱን ገልጸዋል።ከዚህ ውስጥ 12 ሺህ 400 ኩንታል በላይ ስንዴ፣ ከ6 ሺህ ኩንታል በላይ ሩዝ፣ 6 ሺህ ኩንታል ዱቄት እና ከ3 ሺህ 500 ኩንታል በላይ አልሚ ምግብ መሆኑን አቶ ደበበ አብራርተዋል። ድጋፉ የመጀመሪያ ዙር መሆኑን ገልጸው በዘላቂነት ለማቋቋም እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።የድርቅ አደጋው በዞኑ አሁን ያለበትን ሁኔታ፣ የተጎጂዎችን ቁጥርና ሌሎች ተዛማች ጉዳዮችን የሚያጠና ቡድን ወደ ስፍራው ተልኮ መረጃ በማሰባሰብ ላይ መሆኑንም የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው ጠቁመዋል።ኢትዮጵያ ለተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ አደጋ ከተጋለጡ ዜጎቿ መካከል 70 በመቶ የሚሆኑትን በራሷ አቅም እየረዳች መሆኑ ይታወቃል። Via FBC @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
21 624
14
19 874
5
በዛሬው ዕለት በተለያዩ ከተሞች በተካሄዱ የማራቶን ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል! በዕለቱ በአምስተርዳም በተካሄደ የወንዶች የማራቶን ውድድር አትሌት ታምራት ቶላ ርቀቱን በ2:03.38 በመሮጥ አሸንፏል፣ ሰዓቱም የሻምፒዮናው አዲስ ክብረ ወሰን ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ሌላው ኢትዮጵያዊ ልዑል ገብረ ስላሴ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቋል፡፡ በሊዝበን ማራቶን አትሌት አንዷለም በላይ በ2:05.52 በመግባት ያሸነፈ ሲሆን፤ ይሁንልኝ አዳነ እና ባለው ይሁኔ 3ኛ እና 4ኛ ወጥተዋል፡፡ በተመሳሳይ በፓሪስ የሴቶች ማራቶን ኢትዮጵያውያኑ ትዕግስት ማሙዬ፣ የኔነሽ ድንቂሳ፣ ፋንቱ ጂማ እና ዋጋነሽ መካሻ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል፡፡ትዕግስት ርቀቱን የሮጠችበት ሰዓት 2:26.12 ነው፡፡በፓሪስ የወንዶች ማራቶን ደግሞ ኃይለማርያም ኪሮስ 2ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቋል፡፡ Via EBC @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
21 864
12
የ2014 ቤትኪንግ ዛሬ ይጀመራል! የ2014 የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ይጀምራል። በዛሬው የመክፈቻ ጨዋታ ሐዋሳ ከተማ ከጅማ አባጅፋር 8 ሰዓት ጨዋታቸውን ሲያደርጉ÷ ድሬዳዋ ከተማ ከወላይታ ዲቻ ደግሞ 12 ሰዓት ይጫወታሉ፡፡ Photo: Soccer Ethiopia @YeneTube @FikerAssefa
21 503
8
Buy cheap the latest software with great discounts from SoftwareDeal.store. Rated #1 Software Provider for Microsoft Licensing, SQL Licensing, Windows, Office for Mac, Exchange, Windows Server, Visio, Adobe, Autodesk, Antivirus and more cheapest OEM Software! https://softwaredeal.store/
6 454
7
በትግራይ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች በመድሃኒት እና ምግብ እጥረት ምክንያት እየተፈጠረ ነው ያሉት የዜጎች ሞት በማውገዝ መቐለ በሚገኙ የተባበሩ መንግስት ድርጅት መስርያ ቤቶች በራፍ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ። ዛሬ ቅዳሜ ጠዋት በመቐለ በተደረገው የሀኪሞች የተቃውሞ ሰልፍ ወደ ትግራይ የሚያስገቡ መንገዶች በመዘጋታቸው መድሃኒት፣ የህክምና ቁሳቁስ እና ምግብ እየገባ እንዳልሆነ ጠቅሰው፥ በዚህ በትግራይ የዜጎች ሕይወት በሰው ሰራሽ ምክንያት እያለፈ ነው ብለዋል። Via DW @YeneTube @FikerAssefa
22 568
16
የብሪታኒያ የአፍሪካ ጉዳዮች ምኒስትር ቪኪ ፎርድ በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ለተቸገሩ ሰዎች አገራቸው 29 ሚሊዮን ፓውንድ እንደምትሰጥ ይፋ አደረጉ።በኢትዮጵያ የተፈጠረው "ሰው ሰራሽ ቀውስ" ነው ያሉት በብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ምኒስትሯ ቪኪ ፎርድ ሰብዓዊ ዕርዳታ ለተቸገሩ ሰዎች እንዲደርስ ውጊያ የገጠሙ ኃይሎች በአፋጣኝ የተኩስ ማቆም ሥምምነት ላይ እንዲደርሱ ጥሪ አቅበዋል። Via DW @YeneTube @FikerAssefa
21 234
6
የአማራ ክልል መንግሥት ማምሻውን በኮምንኬሽን ቢሮው በኩል ባወጣው መግለጫ በክልሉ ላይ ወረራ የፈጸመውን አማጺው ሕወሃትን ጨርሶ መቅበር ቀዳሚው ዓላማው መሆኑን አስታውቋል። አማጺው በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች በርካታ ሰላማዊ ነዋሪዋችን እየጨፈጨፈ እና ሃብትና ንብረት እያወደመ መሆኑን የጠቀሰው መግለጫው፣ የአማራ ሕዝብ እና የኢትዮጵያ ሕልውና የሚረጋገጠው በሕወሃት መቃብር ላይ ብቻ ነው- ብሏል። የሰሜን ጎንደር፣ ሰሜን ወሎ እና ዋግኽምራ ዞኖችን ከሕወሃት ወረራ ነጻ ለማውጣት አቅም ወይም ሃብት ያለው የክልሉ ነዋሪ ሁሉ በሙሉ ኃይሉ እንዲረባረብ መግለጫ ጥሪ አድርጓል። [Wazema] @YeneTube @FikerAssefa
20 331
16
የሱዳን ጦርን የሚደግፉ በሺሕዎች የሚቆጠሩ የመንግሥት ተቃዋሚዎች ዛሬ ቅዳሜ በኻርቱም አደባባይ ወጡ። በዋና ከተማዋ በሚገኘው ፕሬዝደንታዊ ጽህፈት ቤት ደጃፍ የተሰበሰቡ ተቃዋሚዎች "የረሐብ መንግሥት" ያሉት የጠቅላይ ምኒስትር አብደላ ሐምዶክ አስተዳደር ከሥልጣን እንዲለቅ ጥሪ ማቅረባቸውን ሬውተርስ ዘግቧል።የተቃውሞ ሰልፉ የቀድሞው የሱዳን መሪ ኦማር አል በሺርን ከሥልጣን ለማውረድ ያመጹ ቡድኖችን ጨምሮ ለጦሩ በሚወግኑ የነፃነት እና የለውጥ ኃይሎች ስብስብ አንድ አንጃ የተጠራ ነበር። "ወታደራዊ መንግሥት ያስፈልገናል።አሁን ያለው መንግሥት ፍትኅ እና እኩልነት ሊያመጣልን አልቻለም" ሲሉ በተቃውሞ ሰልፉ የተሳተፉት የ50 አመቱ አባውድ አሕመድ ተናግረዋል። ተቺዎች ሰልፉ በጦሩ እና በጸጥታ ኃይሎች ግፊት የተደረገ እና የቀድሞው መንግሥት ናፋቂዎች የተካተቱበት ነው ሲሉ ይወነጅላሉ።ተቃዋሚዎቹ መንግሥት እንዲበተን የሚጠይቁ መፈክሮች ይዘው የታዩ ሲሆን "አንድ ጦር፤ አንድ ሕዝብ" እንዲሁም "ጦሩ ዳቦ ያመጣልናል" ሲሉ መደመጣቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። ኢናም መሐመድ የተባሉ የኻርቱም ነዋሪ የቤት እመቤት "ሰላማዊ ተቃውሞ ለማሰማት ነው የወጣነው። ወታደራዊ መንግሥት እንፈልጋለን" በማለት ከአባውድ አሕመድ የተስማማ አስተያየት ሰጥተዋል።ከተቃውሞው በፊት ማንነታቸው ያልተለየ ታጣቂ ቡድኖች በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ዙሪያ ለጸጥታ ጥበቃ የተዘጋጁ ማገጃዎችን ማንሳታቸውን እና ፖሊስ እና የጸጥታ ኃይሎች ወደ ሥራ እንዳይሔዱ መከልከላቸውን የኻርቱም ግዛት አስተዳዳሪ አይማን ኻሊድ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ትናንት አርብ የሱዳኑ ጠቅላይ ምኒስትር አብደላ ሐምዶክ አገራቸው ወደ ሲቪል አስተዳደር የምታደርገው ሽግግር "የከፋ ቀውስ" እንደገጠመው አስጠንቅቀው ነበር። [DW/Reuters/AFP] @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
20 465
10
አፕል በቻይና ከባለሥልጣናት የቀረበለትን ጥያቄ ተከትሎ በዓለም ታዋቂ የሆነውን የቁርዓን መተግበሪያ አነሳ። 'ቁርዓን ማጂድ' የተባለው መተግበሪያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በአፕ ሰቶር [የመተግበሪያዎች መገኛ] ላይ የሚገኝ ሲሆን 150 ሺህ የሚጠጉ አስተያቶች ያሉት ነው።ቢቢሲ መተግበሪያው የተነሳው ሕገ ወጥ የሆኑ ሐይማኖታዊ ጽሁፎችን በማዘጋጀት እንደሆነ ለመረዳት ችሏል።የቻይና መንግሥት በዚህ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ ከቢቢሲ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ አልሰጠም። መተግበሪያው መጀመሪያ ላይ እንዲነሳ መደረጉ የታወቀው በዓለም አቀፍ ደረጃ አፕል 'አፕ ስቶር' ላይ ያሉትን መተግበሪያዎች በሚቆጣጠረው ድረ ገጽ -አፕል ሴንሰርሽፕ ነበር።መተግበሪያውን የሠራው ፒዲኤምኤስ ባወጣው መግለጫም "እንደ አፕል ድርጅት ከሆነ 'ቁርዓን ማጂድ' መተግበሪያ ከቻይና ባለሥልጣናት ተጨማሪ መረጃዎችን የሚጠይቁ ይዘቶችን በማካተቱ ምክንያት በቻይና ካለው አፕ ስቶር ተነስቷል" ሲል ገልጿል። ድርጅቱ ችግሩን ለመፍታትም ከቻይና የሳይበር ስፔስ አስተዳዳር እና ከሚመለከታቸው የቻይና ባለሥልጣናት ጋር ለመነጋገር እየሞከርኩ ነው ብሏል።ድርጅቱ እንዳለው መተግበሪያው መነሳቱ በቻይና አንድ ሚሊየን የሚጠጉ ተጠቃሚዎችን እንዳይገለገሉበት አድርጓል።የቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ በአገሪቷ እስልምናን እንደ ሐይማኖት በይፋ የተቀበለ ቢሆንም፤ ቻይና በዢንጂያንግ የሚገኙ የዊጋ ሙስሊም ማኅበረሰቦች ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ብሎም የዘር ማጥፋት በመፈፀም ይከሰሳል። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ በቻይና ዢንጂያንግ የዊጋ የሐይማኖት መሪዎች (ኢማሞች) ኢላማ እንደተደረጉ ቢቢሲ ዘግቧል።አፕል ስለ መተግበሪያው መውረድ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም።ነገር ግን ቢቢሲ "በአገሪቷ ሕጎች እንገዛለን፤ አንዳንድ ገዜ ግን ከመንግሥት ጋር የማንስማማባቸው ውስብስብ ጉዳዮች ይኖራሉ" የሚለውን የሰብዓዊ መብቶች ፖሊሲውን እንዲመለከት መርቷል።ይሁን እንጂ መተግበሪያው በቻይና የትኛውን ሕግ እንደጣሰ ግልጽ አይደለም። Via BBC @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
19 284
19
የዘንድሮው 1496ኛው የመውሊድ በዓል የፊታችን ሰኞ ጥቅምት 8 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚከበር የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ሞክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።ነቢዩ መሐመድ የተወለዱት መልካም ነገሮችን ሊያስተምሩና መጥፎ ነገሮችን ደግሞ ሊቃወሙ፤ ሰውን ወደጀነት ለመምራት በመሆኑ ይህንኑ መልካም ስራቸውን በማየት በእስልምና እምነት ተከታዮች መውሊድ ይከበራል ብለዋል። ነቢዩ መሐመድ የተወለዱበትን፣ የተላኩበትንና ያረፉበትን ቀን በዓል ማክበር ተገቢ መሆኑንም የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ሙፍቲ ሀጅ ጠቅሰዋል።በቀጣዩ ሰኞ የሚከበረውን የመውሊድ በዓል ህዝበ ሙስሊሙ ሲያከብር የሌላቸውን በመጎብኘት እንዲሆንም ጥሪ አቅርበዋል።ተፈናቅለው በተለያየ ችግር ላይ ያሉ ዜጎቻችንም መደገፍና ድጋፉም ለተጎዱ መድረሱን መንግሥት እንዲያረጋግጥ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ ጠይቀዋል። Via EBC @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
19 182
77
የዘንድሮው 1496ኛው የመውሊድ በዓል የፊታችን ሰኞ ጥቅምት 8 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚከበር የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ሞክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።ነቢዩ መሐመድ የተወለዱት መልካም ነገሮችን ሊያስተምሩና መጥፎ ነገሮችን ደግሞ ሊቃወሙ፤ ሰውን ወደጀነት ለመምራት በመሆኑ ይህንኑ መልካም ስራቸውን በማየት በእስልምና እምነት ተከታዮች መውሊድ ይከበራል ብለዋል። ነቢዩ መሐመድ የተወለዱበትን፣ የተላኩበትንና ያረፉበትን ቀን በዓል ማክበር ተገቢ መሆኑንም የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ሙፍቲ ሀጅ ጠቅሰዋል።በቀጣዩ ሰኞ የሚከበረውን የመውሊድ በዓል ህዝበ ሙስሊሙ ሲያከብር የሌላቸውን በመጎብኘት እንዲሆንም ጥሪ አቅርበዋል።ተፈናቅለው በተለያየ ችግር ላይ ያሉ ዜጎቻችንም መደገፍና ድጋፉም ለተጎዱ መድረሱን መንግሥት እንዲያረጋግጥ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ ጠይቀዋል። Via EBC @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
3
0
በኦሮሚያ ክልል ሦስት ነጥብ አራት ሚሊዮን ሔክታር መሬት በኩታ ገጠም መታረሱን የክልሉ ኘሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ! በኦሮሚያ ክልል ሦስት ነጥብ አራት ሚሊዮን ሔክታር መሬት በኩታ ገጠም መታረሱን የክልሉ ኘሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንና ሚኒስትሮችን ያካተተ ልዑክ በምስራቅ ሸዋ የግብርና ምርት እየጎበኘ ይገኛል።እስካሁንም በአደአ ወረዳ በኩታ ገጠም የተዘራ ጤፍና የአቦካዶ እርሻን ጎብኝተዋል። ጉብኝት በተካሄደበት ወቅት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እንደገለጹት፤ በክልሉ ለግብርና ምርት ትልቅ ትኩረት በመሰጠቱ፤ በኩታ ገጠም ካለው ስድስት ነጥብ ሦስት ሚሊዮን ሔክታር መሬት ውስጥ፤ ሦስት ነጥብ አራት ሚሊዮን ሄክታር መሬት ታርሷል።ቀደም ብሎ ክልሉ በ2013/14 የምርት ዘመን ከሦስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በኩታ ገጠም ለማልማት አቅዶ ሲንቀሳቀስ እንደነበር ኢዜአ መዘገቡ ይታወሳል።ይህም ክልሉ የግብርና ምርት ሂደቱን ለማዘመን የኩታ ገጠም እርሻ በስፋት ለማከናወን አቅዶ የሚንቀሳቀስ መሆኑን እንደሚያሳይ ያመለክታል። ባለፉት ሶስት ዓመታት የኩታ ገጠም እርሻ 300 ሺ ሔክታር መሬት ላይ እንደነበር አስታውሰው፤ አሁን ወደ ሦስት ነጥብ አራት ሚሊዮን ሔክታር መሬት ማደግ መቻሉን አብራርተዋል።በመስኖ እርሻ ረገድም 15 የውሃ ፓምፖችን ለአርሶ አደሮች በማሰራጨት 200 ሺ ሔክታር መሬት በመስኖ መልማቱን ተናግረዋል።በቀጣይም በግብርና ዘርፍ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የግብርና ምርቶችን ወደ ውጪ ለመላክና ሰፊ የስራ እድል ለመፍጠር እንደሚሰራም ገልፀዋል። ማሳቸው የተጎበኘ አርሶ አደሮችም በመንግስት እየተደረገላቸው ባለው ድጋፍ ከቀደመው የተሻለ ምርት እያገኙ መሆኑን አስረድተዋል።ከሰሞኑ በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ የተመራ ልዑክ በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች የተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር የግብርና ስራዎችን መጎብኘቱ ይታወቃል ሲል ኢዜአ ዘግቧል። @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
18 373
5
የቀዳማዊት እመቤት ፅ/ቤት በአዲስ አበባ ያስገነባውን የዳቦ ፋብሪካ አስመረቀ! ፋብሪካ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ፅ/ቤቱ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ6 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያስገነባውን መርቀዋል።ፋብሪካው ለከተማዋ ነዋሪዎች አገልግሎት መስጠት እንዲያስችልም ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስረክበዋል። በቀን 1 ሚሊየን ዳቦ የሚያመርተው የዳቦ ፋብሪካው ጎን ለጎንም በቀን 72 ቶን ዱቄትም እንደሚያመርት ተገልጿል። ግንባታው በ217 ሚሊዮን ብር ወጭ የወጣበት ሲሆን ለ450 ሰዎች የስራ እድል የሚፈጥር እንደሆነም ነው የተገለፀው። የቀዳማዊት እመቤት ፅ/ቤት በቀጣይ በ10 ከተሞች በተመሳሳይ የዳቦና ዱቄት ፋብሪካዎችኝ ለማስገንባት ሂደት ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል።በነዚህ ከተሞች የሚገነቡት የዳቦ ፋብሪካዎችም እያንዳንዳቸው በቀን 400 ኩንታል ዱቄት የማምረትና 300 ሺህ ዳቦ የመጋገር አቅም ይኖራቸዋል ተብሎም ይጠበቃል። Via EBC @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
18 035
7
ከሳዑዲ አረቢያ 428 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመለሱ! በተለያዩ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ አገራቸው ለመመለስ እየተደረገ ባለው ጥረት ከሳዑዲ አረቢያ፣ ሪያድ 172 ህጻናትን ጨምሮ 428 ዜጎች ዜጎች በትናንትናው ዕለት ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል። የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ተወካይ ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። @YeneTube @FikerAssefa
16 574
5
የወለደችውን ህጻን ሽንት ቤት የከተተችዉ ግለሰብ በእስራት ተቀጣች! በምስራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ከተማ 01 ቀበሌ ውስጥ ነዋሪ የሆነችው ለምለም ዋለ የተባለች ግለሰብ ከተወለደ 15 ቀን የሆነውን ህጻን ልጇን ጥቅምት 3 ቀን 2014 ዓም ከጥዋቱ አስራ ሁለት ሰዓት ሲሆን ከአንድ ግለሰብ ሽንት ቤት ውስጥ ከታው ትሰወራለች፤ ወድያውኑ ሽንት ቤት ለመጠቀም የገባ ሰው የህጻን ለቅሶ በሽንት ቤቱ ውስጥ ይሰማና የአካባቢውን ማህበረሰብ በማሰባሰብ ህጻኑን ከሽንት ቤት በማውጣት ለፓሊስ ሪፓርት ያደርጋሉ፤ መረጃው የደረሰው የደጀን ከተማ ፓሊስም ህጻኑን በደጀን ጤና ጣቢያ የህክምና እርዳታ እንዲደረግለት ካደረገ በኋላ ክትትል በማድረግ ተጠርጣሪዋን ወዲያውኑ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራወን በማጣራት ለሚመለከተው የፍትህ አካል ይልካል። ክሱ የቀረበለት የደጀን ወረዳ ፍርድ ቤትም ተከሳሿ በተከሰሰችበት ወንጀል ጥፋተኛ መሆኗን በሰውና በህክምና ማስረጃ በማረጋገጡ ጥቅምት 4 ቀን 2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ለምለም ዋለ በሁለት አመት ከሰባት ወር ጽኑ እስራት እንድትቀጣ የወሰነባት መሆኑን የወረዳው ፓሊስ ገልጿል። [ምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ] @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
15 793
14
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ በኦሮሚያ ክልል የግብርና ስራዎችን እየጎበኘ ነው! በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ በኦሮሚያ ክልል የግብርና ስራዎችን እየጎበኘ ነው። በጉብኝቱ የፌዴራል እና የክልል መንግስታት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል። የልዑኩ አባላት በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን አደአ ወረዳ ውስጥ የሚገኘው ደንካካ ቀበሌ የጤፍ ሰብል ክላስተር እየጎበኙ ሲሆን፤ ጉብኝቱ ዛሬና ነገ እንደሚቀጥል ይጠበቃል። ከሰሞኑ በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ የተመራ ልዑክ በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች የተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር የግብርና ስራዎችን መጎብኘቱ ይታወቃል። Via AMN @YeneTube @FikerAssefa
15 393
7
አሜሪካ በካቡል ያደረሰችው የድሮን ጥቃት ስህተት መሆኑን አምና ተቀበለች ፤ ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተሰቦች ካሳ እንደምትከፍልም አስታውቃለች! በአፍጋኒስታን መዲና ካቡል ፤ በአሜሪካ ወታደሮች በድሮን በስህተት ህይወታቸው ለተቀሙት 10 ቤተሰቦች የዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ካሳ ለመክፈል መዘጋጀቱን ገልጿል። በጥቃቱ ህይወታቸውን ከተቀሙት ከሟቾቹ መካከል ህፃናት እንዲሁም የድጋፍ ሰጪ ሰራተኛ ይገኝበታል ተብሏል።ፔንታጎን እንዳለችው ከካሳው በተጨማሪ የቤተሰቡን አባላት ወደ አሜሪካ በመውሰድ ህይወታቸውን በዛው እንዲያደርጉ ተመቻችቷል።የአሜሪካ ወታደሮች ከአፍጋኒስታን ከመውጣታቸው ቀደም ብሎ ባሉት ቀናት ነበር ጥቃቱ የተሰነዘረው። የታሊባን አስተዳደር ወደ ስልጣን ከመምጣቱ በፊት በካቡል ኤርፖርት አቅራቢያ የኢስላሚክ ስቴት አልያም አይኤስ ቡድኑ ላይ ኢላማውን ያደረገ እንደነበርም ነው የአሜሪካ ባለስልጣናት የገለፁት።የክትትል ድሮኑ ሰዎች ወደ ድጋፍ ሰጪ መኪናው ተቀጣጣይ ነገሮችን እየጫኑ መመልከቱ ቢገለፅም የውሃ ማጠራቀሚያ ነበር።ከሟቾቹ መካከል አህመድ ናስር የተባለው ለአሜሪካ ወታደሮች በማስተርጎም ይሰራ ነበር። [ዳጉ ጆርናል] @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
14 476
7
ቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተመልሷል! የጨዋታ ውጤቶችን #ከዛሬ ጀምሮ በመገመት ነጥብዎትን ይሰብስቡ። ከፍተኛ ነጥብ ለሚያገኙ ገማቾች የተለያዩ አጓጊ ሽልማቶች ተዘጋጅተዋል። - DSTV ዲኮደር ከ1 ወር ነፃ ፓኬጅ ጋር - ኳስ እና የሚወዱትን ክለብ መለያ - Wireless Mouse - ብሉቱዝ ስፒከር እና - ፍላሽ ዲስክ እና ሌሎች አጓጊ ሽልማቶች ተዘጋጅተዋል። ቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን በቀጥታ የሚከታተሉበት ምርጥ የሞባይል አፕ። መረብ ስፖርት | Mereb Sport ----------------==------------------- ከPlay Store ዳውንሎድ ያድርጓት 👇 ዛሬውኑ ይገምቱ! https://play.google.com/store/apps/details?id=com.adika.merebsport የውድድር ህጎችን ለማንበብ - https://merebsport.net/gamerules/
Show more ...
13 778
6
🎁 #ArtLand_Gifts 🎁 ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ✿ "እማይረሱ ስጦታዎችን ለሚወዷቸው 🎁 " ✔️የወደዱትን "ፎቶ ወይም ምስል" እንጨት እና ቆዳ(ሌዘር) ላይ እንሰራለን👌 🏷ለልደት 🏷ለምርቃት 🏷ለሰርግ 👰🤵 🏷ለፍቅረኛዎ❤️ 🏷ለቤተሰቦ 👪 🏷ለቢዝነስ ካርድ 🏷 ለቤት, ለካፌ እና ለተለያዩ ነገሮች ማሳመሪያ የሚሆኑ ምስሎችን እንደሚወዱት አርገን እንሰራለን 👍 ከአዲስ አበባ ውጪ ላሉ ደንበኞቻችን በ EMS / DHL እናደርሳለን 📦 🔘ስልክ : 📞(093) 146-5618 🔘For Order @artlandgifts 🚚 ይዘዙን ያሉበት ድረስ እናደርሳለን🏍🏍 Join our channel👇 @artlandengraving @artlandengraving
16 971
5
🥾🥾🥾 It gives our team a great pleasure letting you all know that, we are now collaborating with @shegerhive @Cheenahiking organized a Camping trip to Ajora Waterfalls on October 30 & 31, 2021. The two day trip will allow participants a camping opportunity at the twin waterfalls. The package includes meals, BBQ, Campfire, entrance fees, guide fees, trekking and more for only 2,750 ETB. 👉Note that Package fee must be paid upon registration to secure a spot and discounts are available until Oct 16 Saturday. For booking, contact 0951 10 19 07/09. Make sure to register now! #Shegerhive #hiking #AddisAbaba #Ethiopia
Show more ...
13 399
7
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን የከምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የሰዓት እላፊ አዋጅ ማወጁን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። አዲሱ መመሪያ ከምሽቱ 2 ሰዓት በኋላ ከጸጥታ አስከባሪዎች ውጭ ሌሎች ሰዎች እና ተሽከርካሪዎች በከተማዋ እንዳይንቀሳቀሱ የሚያግድ ነው። አስተዳደሩ ሰዓት እላፊውን ያወጀው፣ በአማጺው ሕወሃት ወረራ ከሌሎች አካባቢዎች የተፈናቀሉ በርካታ ተፈናቃዮች በከተማዋ ዙሪያ ስለሚገኙ እና ለከተማዋ ነዋሪዎች ደኅንነት ሲባል እንደሆነ ገልጧል። [Wazema] @YeneTube @FikerAssefa
19 673
11
በሕዳሴ ግድብ ጉዳይ አረብ ሊግ ያለውን የተሳሳተ አቋም ለማስተካካል እንደምትሰራ አልጄሪያ አስታወቀች! በአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ እየተካሄደ ባለው 39ኛው የአፍሪካ ህብረት መደበኛ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ የተገኙት የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ራማታኒ ናማምራ ሀገራቸው ቀጣዩ የአረብ ሊግ ሊቀመንበርነቱን ቦታ ስለምትይዝ ፣ የአረብ ሊግ አባል ሀገራት በሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ ያላቸውን የተሳሳተ አቋም ለማስተካካል እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ይህንን ያሉት እየተካሄደ ባለው 39ኛው የአፍሪካ ህብረት መደበኛ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን ከምክትል ጠቅላይ ሚንስቴርና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ጋር ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት ላይ እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃልአቀባይ ዛሬ ከቀትር በፊት በሰጡት መግለጫ ላይ ነው፡፡ ከበፊትም ጀምሮ ከአልጄሪያ ጋር መልካም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዳለን ያነሱት ቃል አቀባዩ በህዳሴው ግድብ ላያ የሊጉ አባል አገራት ያላቸውን የተሳሳተ አቋም ለማስተካካል የበኩላቸውን እንደሚወጡ መናገራቸውን ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም የህዳሴ ግድብ ጉዳይ በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር በውይይት እንዲፈታ አልጄሪያ እንደምትደግፍም ናማምራ አክለው መግለጻቸው ታውቋል።ራማታኒ ናማምራ በአፍሪካ ህብረት የሰላምና ደህንነት ኮሚሽነር በመሆን መስራታቸው ይታወሳል፡፡ [Ethio FM] @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
19 369
10
የአውሮፓ ህብረት በቅርቡ ያቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ሚዛናዊነት የጎደለውና ተቀባይነት የሌለው ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ። ከስሎቬኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንዤ ሎጋር ጋር የስልክ ውይይት ያካሄዱት አቶ ደመቀ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ እና በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ እንዲሆን እየተደረገ ያለውን ጥረት በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።ህወሃት በአማራና አፋር ክልሎች በፈጸመው ጥቃት የንጹሐን ዜጎችን የኑሮ መሰረቶችን ማውደሙን አስረድተዋል። አሸባሪው ቡድን የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ ትግራይ ክልል የገቡ 420 ተሽከርካሪዎችን አስቀርቶ ለወታደራዊ አገልግሎት እየተጠቀመባቸው እንደሆነም ገልጸዋል።የኢትዮጵያ መንግስት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ሰባት ሰራተኞችኝ ከአገር እንዲወጡ ያደረገበትን መነሻ ምክንያት አብራርተዋል። የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ በቅርቡ ኢትዮጵያን በተመለከተ ያዘጋጀው የውሳኔ ሀሳብ ሰነድ መሬት ላይ ያለውን ሀቅ ያላገናዘበና ሚዛናዊነት የጎደለው ስለመሆኑ ገልጸዋል።የስሎቬኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንዤ ሎጋር በበኩላቸው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ላደረጉላቸው ገለጻ አመስግነው፤ የወቅቱ የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር እንደመሆናቸው በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ ሁኔታና ግጭት እንደሚያሳስባቸው ተናግረዋል። @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
18 504
3
በኢትዮጵያና ኢንዶኔዥያ በተከሰከሱት አውሮፕላኖች ምክንያት የቦይንግ ኩባንያ የቀድሞ የሙከራ በረራ ሀላፊ ማርክ ፎርክነር ለእስር ተዳረጉ! የቦይንግ የቀድሞው የሙከራ በረራ ዋና ሀላፊ ማርክ ፎርክነር በቴክሳስ ግዛት ውስጥ የኩባንያው 737 ማክስ አውሮፕላን ደህንነት የአሜሪካ ተቆጣጣሪዎችን በማታለል ተከሰዋል። በ 2011 አ.ም የ 157 ሰዎች ህልፈት መክንያት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የነበርው የበረራ ቁጥሩ ኢቲ 302 ቦይንግ 737 አደጋ ከተከሰተ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ሁሉም 737 ማክስ አውሮፕላኖች በዓለም አቀፍ ደረጃ አገልገሎት እንዲይቆሙ ተድርጎ ነብር። የፍርድ ቤት ሰነዶች ሀላፊው የአውሮፕላኑን የበረራ መቆጣጠሪያ ስርዓት ክፍል ሐሰተኛና ትክክል ያልሆነ እና ያልተሟላ መረጃ ለፌዴራል አቪዬሽን አስተዳደር እንዲሰጠ አድርገዋልም ተብሏል። የኢትዮጵያና ኢንዶኔዥያ አየር መንገዶች ንብረት በነበሩት 737 ማክስ አውሮፕላኖች ላይ ለደርሰው የመከስከስ አድጋም ተጠያቂ ሆነዋል።ማርክ ፎርክነር በተከሰሱበት ወንጀል ጥፋተጋ ከተባሉ እስከ 20 ዓመት የሚደርስ እስር እንደሚጠብቃቸው ቢቢሲ ዘግቧል። ✍BBC/Asham @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
17 810
8
ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለጸ። ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል በሔራዊ ፈተናን ከጥቅምት 29 እስከ ሀዳር 2 ቀን 2014 አ.ም ለመስጠት በያዘው መርሃግብር መሰረት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ ባዘጋጀው የንቅናቄ ሰነድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው፡፡ውይይቱም የ2012 ዓ.ም አፈጻጸምና በዋናነት የ2013 ፈተና ዝግጅት ላይ ያተኮረ ነው፡፡ የኤጀንሲው የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት፣ ከ617 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለፈተና ዝግጁ ሆነዋል። ፈተናው የጸጥታ ችግር ባለባቸው የአማራና የአፋር ክልል አካባቢዎችም እንደ ወላጆችና ተማሪዎች ፈቃድ እንዲሁም እንደ አካባቢው ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ሊከናወን እንደሚችል ገልጸዋል። ፈተናው በአስር የትምህርት አይነቶች መዘጋጅቱና የኢኮኖሚክስ ፈተና በዘንድሮው መርሀ ግብር አለመካተቱ ተናግረዋል፡፡ፈተናው የሚወስዱት ተማሪዎች ካለፈው ዓመት በእጥፍ መጨምሩን የተናገሩት ዳይሬክተሩ ዘግጀቱም በዚያው ደረጃ መደረጉን መናገራቸውን ኢፕድ ዘግቧል። ከጸጥታ አንጻር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል። አስፈላጊ ቁሳቁሶች ባለመድረሳቸው ምክንያት የዘንድሮው ፈተናም ቀደም ሲል እንደነበረው በወረቀት የሚከናወን እንደሆነ ተመላክቷል። @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
17 352
41
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሕወሓት በወረራ ይዞ በኃይል በለቀቃቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ከ1500 በላይ ትምህርት ቤቶችን በሙሉና በከፊል በማውደሙ በትምህርት አጀማመር ላይ ከፍተኛ ጫና መፈጠሩን ዐስታወቀ፡፡ የቢሮው የጽ/ቤትና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት በጦርነት ቀጠና ውስጥ ያሉ 1 ሚሊዮን 500ሺህ ተማሪዎችም ከትምህርት ውጪ ናቸው፡፡በደሴ፣ በደባርቅና በእብናት ከተሞች በርካታ ትምህርት ቤቶች በተፈናቃዮች በመያዛቸው ትምህርት ለማስጀመር ሌላው ፈተና እንደሆነባቸውም ነው አቶ ጌታቸው ያስረዱት፡፡ በሌሎች ሰላማዊ እንቅስቃሴ ባለባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ግን 4 ሚሊዮን የሚጠጉ ተማሪዎች ተመዝግበው ትምህርታቸውን ጀምረዋል ብለዋል፡፡ @YeneTube @FikerAssefa
15 357
5
በዐይነቱ ለየት ያለ አንድሮይድ ፕሮጀክተር (Borrego Smart Android Projector) ለተለያዩ አገልግሎቶች: - DStv (ዲኤስ ቲቪ) - Seminar (ስብሰባ) - Bar and Restaurants (መዝናኛ ቦታ) - Home theater (ለፊልም ቲያተር) Higher resolution projector - 2800 Lumens - Image Tech TFT LCD - Color 16.7K - Light source LED - Lamp 30000hr - 1gb RAM 8gb Storage - Project size 36-150 inch - Aspect ratio 4:3 16:9 16:10 - you can connect to your wifi Installed apps - Youtube - Google playstore - Mirror cast - Chrome - Other browsers Price... 12500Birr Location:-Bole medihanialem Call : 251911516533
Show more ...
15 257
6
በዝናብ እጥረት ምክንያት በተከሰተ ድርቅ ለችግር መጋለጣቸውን የቦረና ዞን ነዋሪዎች ተናገሩ! በዝናብ እጥረት ምክንያት በተከሰተ ድርቅ ለውሀ፣ለምግብና ለጤና ችግር መጋለጣቸውን የቦረና ዞን ነዋሪዎች ተናገሩ።በዞኑ በ2013 ዓ.ም የበልግ ዝናብ በቂ አለመሆኑና የ2014 ዓ.ም የመኸር ዝናብ በወቅቱ ባለመዝነቡ ምክንያት በሰውና በእንስሳት ላይ ጉዳት እየደረሰ መሆኑንም የቦረና ዞን አስተዳደር ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሬባ ኦዳ ገልፀዋል። በደረሰው ድርቅም 539 ሺህ 679 የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የውሀ እጥረት እንዳጋጠማቸው የገለፁት ሀላፊው÷ ከዚህም ውስጥ 177 ሺህ 553 ለሚሆኑት ብቻ በቦቴ ውሀ እንዲያገኙ ማድረግ መቻሉን አንስተዋል። እስካሁን በደረሰው የምግብ እጥረትም 6 ሺህ 398 ህፃናት ፣9 ሺህ 78 እናቶችና 2 ሺህ 226 አዛውንቶች ላይ የጤና ችግር መታየቱ ገልፀዋል።እስካሁንም ለ118 ሺህ 864 ሰዎች የምግብ እርዳታ የተደረገ መሆኑን የገለፁት ሀላፊው 166 ሺህ 136 የሚሆኑት ደግሞ ተጨማሪ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው አንስተዋል።በተከሰተው ድርቅም 7 ሺህ 540 ከብቶች የሞቱ ሲሆን÷13 ሺህ 641 የሚሆኑት ደግሞ በሰው ድጋፍ የሚንቀሳቀሱ መሆኑ ተገልጿል። እንስሳቶቹን ከአደጋው ለማትረፍም 2 ሚሊየን 463 ሺህ 214 ቤል ሳር ከመንግስት ተጠይቋል።አሁን ላይ በመንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች እየተደረጉ ያሉ ድጋፎች እንደቀጠሉ ቢሆንም ከችግሩ ስፋት እና አሳሳቢነት አንፃር ግን በቂ ባለመሆኑ የሚመለከተው አካል ሁሉ ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።በሌላ በኩል ከ200 በላይ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶችም ሮቶዎችንና በቂ ውሀ የሚፈልጉ መሆኑን የገለፁት አቶ ሬባ ÷በዞኑ በ2009 ዓ.ም ተመሳሳይ ችግር አጋጥሞ የነበረ መሆኑን ገልፀው በመንግስት፣ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች እና በህዝብ ትብብር ማገገም ተችሎ እንደነበር አስታውሰዋል። Via FBC @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
15 129
7
በጦርነት በምትታመሰው የመን 20 ሚሊዮን ሰዎች ለሰብአዊ እርዳታ ፈላጊነት እንደተጋለጡ የተባበሩት መንግስታት ምክትል ዋና ፀሐፊ ተናገሩ፡፡ ምክትል ዋና ፀሐፊው ራሜሽ ራጃሲንግሐም እንደተናገሩት በጦርነቱ ምክንያት የየመን አጠቃላይ ምጣኔ ሐብት እንዳለ ተንኮታኩቷል፡፡በዚህም የተነሳ ከአገሪቱ አጠቃላይ ሕዝብ ሁለት ሶስተኛው ሰብአዊ እርዳታ የሚያሻው ሆኗል፡፡ ሳውዲ አረቢያ መራሹ የአካባቢው አገሮች የጦር ጥምረት ከሰንዓ የተባረሩትን ፕሬዝዳንት አብዱራቡ መንሱር አል ሃዲን ወደ መንበራቸው ለመመለስ አልሞ የሁቲ ታጣቂዎችን መውጋት ከጀመረ ወደ 6ኛ ዓመቱ እየተቃረበ ነው፡፡ ጦርነቱ ሰብአዊ ቀውሱን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያባባሰው ነው ተብሏል፡፡የረድኤት ድርጅቶች ደግሞ እጅ እያጠራቸው መምጣቱን አልጀዚራ ፅፏል፡፡ጦርነቱ ያለ አንዳች ሁነኛ መፍትሄ እንደቀጠለ ነው፡፡ [Sheger] @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
15 959
4
ለጠ/ሚ ዐቢይ የሰሜን ኮሪያው ጠ/ሚ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ! ኢትዮጵያ መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ ምዕራፍ የጀመረችበትን አዲስ መንግስት መመስረቷን እንዲሁም ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድጋሚ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መመረጣቸውን ተከትሎ በርካታ ሀገራት የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት እያስተላለፉ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ ሀገራት መካከል ሰሜን ኮሪያ አንዷ ሆናለች፡፡ የሰሜን ኮሪያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪም ቶክ ሁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በድጋሚ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመመረጥዎ እንኳን ደስ አለዎት ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም በስልጣን ዘመንዎ ለሀገርዎ ልማት፣ ብልጽግና እና ሰላም እንዲመጣ በሚያደርጉት ጥረት ሁሉ ስኬትን እመኝሎታለሁ ካሉ በኋላ፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የሁለትዮሽ ግንኙነት፣ ወዳጅነት እና በትብብር የመስራት ፍላጎት እናጠናክራለን ብለዋል፡፡ በተመሳሳይ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪ ሰን ግዎን በበኩላቸው፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንም እንዲሁ በድጋሚ በመመረጥዎ የእንኳን ደስ አለዎት መልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡ @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
16 633
24
በሰኔ 14ቱ ሀገራዊ ምርጫ ወቅት አንዲት የፖለቲካ ፓርቲ እጩን ጨምሮ በሰባት ሴቶች ላይ ወሲባዊ ትንኮሳ ደርሷል! የኢትዮጵያ ህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ፤ በኢትዮጵያ በሰኔ ወር በተከናወነው 6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ በሴቶች ላይ የደረሱ ጥቃቶችን በተመለከተ ዝርዝር ሪፖርት አዉጥቷል። ማህበሩ ለብስራት ራዲዮ በላከዉ መረጃ እንደተመላከተዉ ፤ በሴቶች ላይ የተፈፀሙ ዛቻ አልያም ማስፈራሪያ በተመለከተ 41 ክስተቶችን ታዝበዋል። "ከምርታማ የሴፍቲኔት ፕሮግራም እንሰርዛችኋለን" በማለትም ፤ የአካባቢ ሹማምንቶች ሴት መራጮችን እነርሱ በሚፈልጉት ሁኔታ ድምፅ እንዲሰጡ ጫና በመፍጠር ሴት መራጮችን ሲያስፈራሩ አንደነበር ተጠቅሷል። በአማራ ፣ በኦሮሚያ ክልል እና በድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር አብዛኞቹ ጥቃቶች ሲፈፀሙ ፤ በቤኒሻንጉል ፣ ጋምቤላ እና አዲስ አበባ ከተማ በተወሰነ መልኩ ችግሩ መስተዋሉን ማህበሩ አስታውቋል። በተጨማሪም 7 ወሲባዊ ትንኮሳዎች በምርጫው ወቅት በሴቶች ላይ ደርሷል። በሴት መራጮች ላይ 3 ፣ ለመምረጥ በመመዝገብ ላይ በነበሩት 2 ፣ የፖለቲካ ፓርቲ አባል እንዲሁም የፓርቲ ደጋፊ ላይ 2 በድምሩ 7 ወሲባዊ ትንኮሳዎች በምርጫው ወቅት በሴቶች ላይ እንደደረሱ ሪፖርቱ አትቷል። የኢትዮጵያ ህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ታዛቢዎች ፣ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እና የአካባቢ መስተዳድር ተወካዮች ፤ የሴት መራጮችን ድምፅ ለማግኘት የተደረጉ ሙከራዎችን በሚመለከት 10 ክስተቶችን ማግኘቱን ብስራት ከሪፖርቱ ተመልክቷል። Via Bisrat FM @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
15 890
7
የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ህልፈት ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ጉዳት የደረሰባቸው ኢትዮጵያውያንን ለመደገፍ የጀመረው መርሃ ግብር መጠናቀቁን የክርስቲያን በጎ አድራጎትና የልማት ማህበራት ህብረት CCRDA ተናገረ፡፡በድጋፉ ከ3,200 በላይ ዜጎችን ማገዝ ተችሏልም ተብሏል፡፡ Via Sheger FM @YeneTube @FikerAssefa
15 122
7
በሌባኖስ መዲና ቤይሩት በተከፈተ ተኩስ ሰዎች ተገደሉ! በሌባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት በተከፈተ ጥቃት ቢያንስ ስድስት ሰዎች ሲገደሉ 32 ሰዎች ደግሞ ደግሞ ክፉኛ መቁሰላቸው ተሰምቷል።ጥቃቱ የተከሰተው የሺያ ሙስሊም ቡድኖች የሆኑት ሄዝቦላህ እና አማል ባለፈው ዓመት የተከሰተውን ፍንዳታ ተከትሎ የተከፈተውን ምርምራ የሚያዩትን ዳኛ እየተቃወሙ ባሉበት ወቅት ነው።ሄዝቦላህ እና አማል እንደሚሉት የሌባኖስ ኃይሎች የተባለው ፓርቲ አባላት የሆኑ የክርስትና እምነት ተከታይ አልሞ ተኳሾች ናቸው ወደ ሕዝቡ ተኩሰው አመፅ ያስነሱት። የሌባኖስ ኃይሎች ይህን የሄዝቦላህና አማል ክስ ያጣጥላል።ባለፈው ዓመት የተከሰተውንና የ219 ሰዎች ሕይወትን የቀጠፈውን ፍንዳታ ተከትሎ እየተደረገ ያለው ምርመራ ቤይሩት ውስጥ ውጥረት ፈጥሯል።ሄዝቦላህና አጋሮቹ እንደሚሉት ችሎቱን የሚያዩት ዳኛ የሚያዳሉ ቢሆኑም የሟች ቤተሰቦች ግን ዳኛው ንፁሕ ነው ብለው ያስባሉ።ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ነሐሴ ለተከሰተውን የበርካቶችን ሕይወት ላጠፈው አደጋ እስካሁን ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም።ሐሙስ ዕለት የተከፈተውን ተኩስ ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ናጂብ ሚካቲ ዕለተ አርብ የሐዘን ቀን ሆኖ እንዲውል መልዕክት አስተላልፈዋል።ፕሬዝደንት ማይክል አውን በበኩላቸው "ማንም ሰው ሃገሪቱን እንዲያግታትና የራሱ እንዲያደርጋት አንፈቅድም" ብለዋል። Via BBC @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
15 461
9
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና የኬንያው አቻቸው ኡሁሩ ኬንያታ በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፡፡ ሌሊት የነበረውን ውይይት አስመልከቶ አጭር መረጃን በፌስቡክ ገፃቸው ያሰፈሩት ፕሬዝዳንት ባይደን ‹‹የኬንያውን ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኋይት ሃውስ በመቀበሌ ደስተኛ ነኝ›› ብለዋል፡፡‹‹የአሜሪካ-ኬንያ ስልታዊ አጋርነት ቁልፍ የቀጣናዊና ዓለም ዐቀፍ ፈተናዎችን ለመፍታት እጅግ አስፈላጊ ነው›› ሲሉም አክለዋል፡፡ የሁለቱን አገራትም ሆነ ከአጠቃላይ አፍሪካ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማላቅ እንደሚተጉም ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስታውቀዋል፡፡ ኡሁሩ ለፕሬዝዳንት ባይደን የመጀመሪያው የአፍሪካ መሪ እንግዳ ሆነው በነጩ ቤተ መንግሥት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡ሁለቱ መሪዎች ዴሞክራሲንና የሰብኣዊ መብቶችን እንዲሁም ሰላምና ደኅንነትን ማስከበር ላይ አትኩረው መምከራቸው ተሰምቷል፡፡በምጣኔ ሃብት ጉዳዮችና የአየር ንብረት ለውጥ አጀንዳዎች ላይም ተነጋግረዋል ነው የተባለው፡፡ [Walta] @YeneTube @FikerAssefa
Show more ...
15 252
10
🥾🥾🥾 It gives our team a great pleasure letting you all know that, we are now collaborating with @shegerhive @Cheenahiking organized a Camping trip to Ajora Waterfalls on October 30 & 31, 2021. The two day trip will allow participants a camping opportunity at the twin waterfalls. The package includes meals, BBQ, Campfire, entrance fees, guide fees, trekking and more for only 2,750 ETB. 👉Note that Package fee must be paid upon registration to secure a spot and discounts are available until Oct 16 Saturday. For booking, contact 0951 10 19 07/09. Make sure to register now! #Shegerhive #hiking #AddisAbaba #Ethiopia
Show more ...
14 499
6
ለስፖርት አፍቃሪዎች በሽልማት የሚንበሸበሹበት አዲስ የሞባይል አፕ። የጨዋታ ውጤቶችን በመገመት የሞባይል ካርድ እንዲሁም - DSTV ዲኮደር ከ1 ወር ነፃ ፓኬጅ ጋር - ኳስ እና የሚወዱትን ክለብ መለያ - Wireless Mouse - ብሉቱዝ ስፒከር እና - ፍላሽ ዲስክ እና ሌሎች አጓጊ ሽልማቶች ተዘጋጅተዋል። ቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን በቀጥታ የሚከታተሉበት ምርጥ የሞባይል አፕ። መረብ ስፖርት | Mereb Sport ----------------==------------------- ከPlay Store ዳውንሎድ ያድርጓት 👇 ዛሬውኑ ይገምቱ! https://play.google.com/store/apps/details?id=com.adika.merebsport
13 927
17
🎁 #ArtLand_Gifts 🎁 ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ✿ "እማይረሱ ስጦታዎችን ለሚወዷቸው 🎁 " ✔️የወደዱትን "ፎቶ ወይም ምስል" እንጨት እና ቆዳ(ሌዘር) ላይ እንሰራለን👌 🏷ለልደት 🏷ለምርቃት 🏷ለሰርግ 👰🤵 🏷ለፍቅረኛዎ❤️ 🏷ለቤተሰቦ 👪 🏷ለቢዝነስ ካርድ 🏷 ለቤት, ለካፌ እና ለተለያዩ ነገሮች ማሳመሪያ የሚሆኑ ምስሎችን እንደሚወዱት አርገን እንሰራለን 👍 ከአዲስ አበባ ውጪ ላሉ ደንበኞቻችን በ EMS / DHL እናደርሳለን 📦 🔘ስልክ : 📞(093) 146-5618 🔘For Order @artlandgifts 🚚 ይዘዙን ያሉበት ድረስ እናደርሳለን🏍🏍 Join our channel👇 @artlandengraving @artlandengraving
17 716
9
@shegerhive DO YOU WANT TO TRAVEL & MAKE GAMES? ChewataCon 2021_ Gaming Convention brings you the TRAVEL JAM! Travelam is a type of gamejam that incorporates travelling to a selected location where the theme of the jam revolves around and making an actual game during a gamejam after coming back from your travel. The selected travel location meets all safety requirements. During your travel, you will be hosted in farmers' homes where the GIZ knows well for 3 days & 2 nights. Once your travel is done, you will attend a 40hr gamejam to build your game idea. Date & Time: Travel Dates: Beginning Tuesday, Oct, 19 2021 - Thursday, Oct, 21 2021 GameJam Dates: Beginning Friday, Oct, 22nd 6pm and Ending Sunday, Oct, 24th 6pm Venue: Travel Homestead (Farmer's Homes: you will be assigned), GameJam in Addis: IceAddis Powered by : Deutsche Gesellschaft für Internationale Zusammenarbeit (GIZ) Application Process: Fill out the form until end of October 13, 2021 and you'll be hearing from us. https://bit.ly/2YmXH2g
Show more ...
2
0
Privacy Policy