cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ወርቃማ ንግግሮች

ሰው የለበስክ ሰው እንጂ ልብስ የለበስክ ሰው አትሁን.. ሰውነት የአለም ምርጡ ጌጥህ እሱ ነውና። አስተያየት እንቀበላለን.. @Golden_SpeechBot https://youtube.com/channel/UCgP-E0miz3BhJ0YAGJ2zCHg

Show more
Advertising posts
16 121Subscribers
-1624 hours
+3527 days
+1 12030 days
Posts Archive
📢 ታላቅ የሙሀደራ ድግስ ♦️ተጋባዥ እንግዶቻችን 📍ኡስታዝ አቡ አዩብ  ርዕስ፦ ጥሩ ሂወት (الحياة السعيدة) 📍ኡስታዝ አብዱ አረዛቅ ርዕስ፦ የኢእቲካፍ እና የዘካቱል ፊጥር ህግጋት 📍ወንድማችን አቡ ሱፍያን ርዕስ፦ የረመዳን የመጨረሻ አስር ዉድ ቀናቶችን እንዴት እናሳልፍ ዛሬ ጁመዓ ከተራዊህ ሶላት ቡኋላ መቅረት ቀርቶ ማርፈድ ያስቆጫል! 📲ፕሮግራሙ የሚተላለፈው ለታላቁ ሸይኻችን ሸይኽ ያሲን ሙሳን እናሳክማቸው በተከፈተው የቴሌግራም አድራሻ ➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘ https://t.me/+FCoJ8Aqxga1mZmI0 https://t.me/+FCoJ8Aqxga1mZmI0
Show all...
Abdulbasit kimbado shifa
Show all...
ከፍርስራሽ ስር የወደቁ በድሮን ተመተው ከህንፃው ስር የተጋደሙ ፍልስጤማዊያንን በመፈለግ ላይ የተሰማሩት የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ከአንድ ጥግ የ16 አመትን ወጣት አገኙ። ሰውነቱ በደም ተጨማልቆ እስትንፋሱ ተቋርጧል። ከፍነው ለመቅበር እንዲያመቻቸው ወደ ሆስፒታል ሊወስዱት አንከፍክፈው አነሱት። አንድ ሁለት እንደተራመዱ አነስተኛ ደብተር ከኪሱ በኩል ወደቀች። አነሷት። የእለት ተግባሩን የሚመዘገበበት ማስታወሻ ነበረች። ገልጠው ተመለከቱት በእርግጥም ዓይናቸው ያየውን ማመን አቃተው። ለአንድ ሳምንት የፈፀመውን ኃጢያት በደብተሩ ላይ አስፍሯል። ቅዳሜ:- ዉዱእ ሳላደርግ ተኝቻለሁ ይላል። ዝቅ አሉ እሁድ:- በሰዎች ፊት ጮክ ብዬ ስቄያለሁ ሰኞ:- ወደ ወራሪዋ ጦር የተኮስኩት ኢላማውን ጠብቆ ሲያርፍ በራሴ በመገረም ኩራት ተሰማኝ ማክሰኞ:- የሌሊት ሰላቴን ስሰግድ ሱጁድና ከሩኩኤን ማስረዘም ሲገባኝ በፍጥነት ነበር የተነሳሁት። ረቡዕ፡- የጦር አዛዣችን በሰላምታ ቀደመኝ። በአጅር በለጠኝ። ሐሙስ:- የቀን ዚክሬንና ቂርአቴን ረሳሁ ጁሙዐ:- በረሱል ላይ 1,000 ሰለዋት መጨረስ ተስኖኝ 700 ላይ ተገታሁ" ይላል በደብተሩ አጂብ ተሰኙ። በእርግጥም በዘመናችን ይህን መሰል ማየታችን ያስገርማል። ይህ ወጣት ያሳካው ላይ ለመድረስ እኛስ ምን ያህል ዕድሜ ያስፈልገናል? ከዛሬ ለመጀመር አታቅዱምን?! እርሱ 16 አመቱ ነበር። ረህመቱላሂ አለይሂ። Mahi Mahisho https://t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch
Show all...
እውነት /ሀሰት 🖋ትክክለኛው መልስ ስታገኙ  እጅግ ጠቃሚ  ስጦታዎች  ይሰጣችኋል 👇👇👇👇 1// የሀቅ መመዘኛ የሸሪአ ትምህርትን ነው  በእኛ ላይ ደግሞ መማር  ግዴታ ነው ?
Show all...
👍 8
እውነት
ሀሰት
~ አእምሮህን ዘግተህ አትቀበል { የሚነገረንን እውነት ትኩረት ሰጥተን) የምንሰማና በአእምሯችን የምንጠቀም (የምናስብ) ቢሆን ኖሮ ከእሳት ሰዎች ባልሆንን ነበር።} (አል ሙልክ ) ‹‹አል-ዐታቢ የተባለው የሻም አገር ገጣሚና ባለቅኔ አንድ ዕለት ወደ ከተማዋ በሚያስገባው ዋና በር ላይ ሆኖ በሰዎች መካከል ይመገባል። ጓደኛው ‹ወይ ጉድህ!! ትንሽ እንኳ እፍረት አይሰማህምን!?› አለው። እርሱም ስማ አንተ በቤትህ ውስጥ ከብቶች እያዩህ ብትበላ ታፍራለህን?› ሲል ጥያቄውን በጥያቄ መለሰለት። ጓደኛውም በከብቶች መካከልማ ከሆንኩ መመገብ አላፍርም አለ። ‹መልካም! እንግዲያውስ እነዚህም ሰዎች ከብቶች እንዴት እንደሆኑ አሳይሃለሁ፥ ትንሽ ጊዜ ብቻ ታገሰኝ አለው፡፡ ከዚያም ብድግ ብሎ ለሰዎቹ ትምህርት መስጠት፣ ምክር መምከር ፣ ታሪክ መተረክና ዱዓ ማድረግ ጀመረ። ሰዎቹም እርሱን ለማዳመጥ ከዚያም ከዚህም ተመሙ። ቦታው ጠቦመጋፋት እስከሚጀምሩም ድረስ በዙ። በዚህ ጊዜ በንግግሩ መካከል እንዲህ አላቸው ከአንድ በላይ በሆነ ሰነድ የደረሰን ዘገባ እንደሚያመለክተው (የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ሐዲስ ማለቱ ነው።) “በምላሱ ጫፍ የአፍንጫውን ጫፍ መንካት የቻለ ሰው ሁሉ ጀሀነም አይገባም” ተብሏል አላቸው። የዚህ ጊዜ አብዛኛዎቹ ሰዎች ምላሳቸውን እያወጡ መንካት እንደሚችሉና እንደማይችሉ ለማረጋገጥ መሞከር ጀመሩ፡፡ ከዚያም ዘወር አለና ለጓደኛው ‹‹አየህ? እነዚህ ሰዎች አእምሮአቸውን የማይጠቀሙ ከብቶች ናቸው ብዬ አልነገርኩህምን? አለው።›› (ሙሓደራቱ አል-ኡደባእ ገ/31) ብዙዎቻችን በብዙ ነገሮች ላይ አገናዝበን ፣ አብላልተን ፣ በራሳችን የደረስንበትን ድምዳሜ የመያዝ ልምዱ አለን ለማለት አንችልም። ከዚህ ይልቅ ብዙ የተጮኸለትንና የመናገር ወይም የመጻፍ ዕድል ያገኘውን ነገር በደፈናው የመሸመት ነገር ይቀለናል። ከዚህም የተነሳ በብዙ የሕይወት ጉዳዮቻችን ላይ የምንከተላቸው ሃሳቦች የኛ ሳይሆኑ የሌሎች ናቸው። ይህን የሚያሳየው ስሜቶቻችንን የሚያነሳሳው የሌሎች ሰዎች አባባል መሆኑ ነው። እንዲሁም በዙሪያችን ያለው ማኅበረሰብ የሚወደውና የሚጠላው ነገርም በቀላሉ ይዘውረናል። እንዲያውም በድፍረት እንናገር ከተባለ የአንዳንዶቻችን አእምሮ በርካታ የስሜት ባርነቶችንም ያቀፈ ነው። ይህን የሚያስረዳን ደግሞ በውስጣችን ያሉት ብዙ ነገሮች ለመጀመሪያ ጊዜ በአጋጣሚ የሰማናቸው፣ ያየናቸው፣ የወረስናቸውና እንድንሆናቸው በሌሎች የተነገሩን፥ ሆነው መገኘታቸው ነው። ሆኖም ግን እነዚህ ነገሮች አብረውን በቆዩ ቁጥር ከስሜቶቻችን ጋር ስለሚዋሃዱ ነገሩን ትክክል ለማድረግ ምክንያቶችን እንፈልግላቸዋለን። ከዚያም የእኛው እናደርጋቸዋለን። ምክንያት የማናገኝለትን ደግሞ በሌላ ከመጠየቅም ሆነ ሌላን ሰው ከመጠየቅ እንሸሻለን። በዚህ መንገድ እኛው ጋር እድሜያቸውን ያስረዘሙና ሽግግራቸውን ያስቀጠሉ የመፈተሸ እድል ያላገኙ በርካታ ማንነቶች እንዳሉን እሙን ነው። እንደሚታወቀው አንድን ሰው ትልቅ የሚያደርገው በቃል የሸመደደው እውቀት ብዛትና የመረጃ ማከማቻ መሆኑ አይደለም። ያ መልካም ቢሆንም ብቻውን ግን በቂ አይደለም። ይልቁንም ትልቅነት እውነትን ፈላጊ፣ ፈታሽና ነገሮችን በጥልቀት የማየት ልምምድ ነው። ይሁንና ብዙዎቻችን ያደግንበት ማኅበረሰብ በብዙ ነገሮች ላይ “ይህን ተዉት፥ ያንን ያዙት ማለት የሚያበዛ በመሆኑ የሰጠው ጥቅም ሊኖር ቢችልም፥ ንቃተ ሕሊናችን ከፍታውን እንዳያገኝ እንቅፋት ሆኖታል። ከዚህም የተነሳ አንድን ነገር ከመገንዘባችን በፊት የሌሎችን ሃሳብ በደፈናው መቅዳትን እንመርጣለን። ይህ ደግሞ በሕይወት እውነታዎች ላይ ግልብ ዕይታ እንዲኖረን ወይም በሌሎች ብቻ እንድንመራ፥ እልፍም ሲል የመሃይም ማጎብደድ እንድናጎበድድ ያደርገናል። የዚህ ዋና ምክንያቱ ባሕላችን ነው። ገና ልጆች ሳለን ወላጆቻችን የአንድ አመለካከት እስረኛ አድርገው የመቅረጽ ሚናን እንዲድጫወቱ ስለሚያበረታታ ነው። ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ የበላይነት እንዳላቸው የሚታሰቡት ማኅበረሰቦች ወይም ግለሰቦች የሚደግፉትንና የሚጮሁለትን ነገር በጭፍኑ የመከተል አባዜያችን ነው። እርግጥ በወላጆች መቀረጽም ሆነ የሌሎችን ዕይታ መውሰዱ በራሱ ችግር የለውም። ምክንያቱም የነገሩ ትክክለኝነት እንጅ እውነት የትላንት ወይም የዛሬ የሚባል ነገር የለውም። ነገር ግን ችግር የሚሆነው እነርሱ ያመኑበት እንጅ በራሱ ትክክል ያልሆነ በሚሆንበት ጊዜ ነው። አእምሮን በሚገባ አለመጠቀም የመጀመሪያ ምልክቱ የሌሎችን ዕይታ ለመስማት ፍቃደኛ የማይሆኑ ጠባብ ሰዎችን መፍጠሩ ነው። በታሪክ ውስጥ በአስተሳሰብ መስመር (በመዝሀቦች) መካከል ያለውን ልዩነት በማጉላት በታላቁ በኒ ኡመያ መስጊድ ውስጥ አንድ ወቅት ሶላትን አራት ጊዜ የተለያየ የአስተሳሰብ መስመር ባላቸው ኢማሞች ተሰግዶ እንደነበር ታሪክ ያስታውሳል ። እውነቱን ለመናገር የትኛውም ዓይነት ጭፍንነት የሚገነውና ጽንፍ የሚይዘው አእምሮን ካለመጠቀምና ከማመዛዘን እጥረት ነው። ~ ሰው ምክንያታዊነቱን ሲዘጋ የለመደውን ወይም የወረሰውን ነገር በመደጋገም ግትር ይሆናል። የኔ ሃሳብ ብቻ ትክክል ነው ብሎ መከራከር የተከላካይነት ጠባይን ያመጣል። ቡድንተኝነቱን በሚያጠናክሩ ነገሮች ላይ ብቻ ያተኩራል። የሚያምንበትን ነገር በኃይል ለማሳካትም ይሞከራል። ከዚህም የተነሳ ለበርካታ ምድራዊም ሆነ ሰማያዊ ጉዳቶች ተጋላጭ ይሆናል። የሆነ ሆኖ ግን ታላቁ ቁርኣን የትኛውንም ነገር ለመገንዘብ አእምሮን መጠቀም እንደሚገባና ሌሎችንም በጭፍኑ መከተል ከመስመር እንደሚያወጣ በብዙ አንቀጾቹ ላይ በግልጽ አስፍሯል። ለአብነትም የሚከተሉትን እንመልከት… وَقَالُوا لَوْ كُنَّا نَسْمَعُ أَوْ نَعْقِلُ مَا كُنَّا فِي أَصْبِ السَّعِيرِ "የምንሰማ፥ ወይም የምናስብ፥ በነበርንም ኖሮ በነዳጅ እሳት ጓዶች ውስጥ ባልኾን ነበር ይላሉ።" (አል-ሙልክ፡ 10)
Show all...
👍 13 4🥰 2🤔 2
ይህ ግሩፕ የሸኻችንን ሸኽ ያሲን ሙሳን ለማሳከም የተከፈተ ነው  በዚህ በተከበር ወር ከኸይር ስራ ልንሰላች አይገባም  ይህ እንደ ተራ ነገር ቆጥረነው scroll አድርገን ልናልፈው ፈፅሞ ተገቢ አይደለም ተቀላቀሉ 👇👇👇 t.me/+FCoJ8Aqxga1mZmI0 t.me/+FCoJ8Aqxga1mZmI0
Show all...
بسم الله الرحمن الرحيم { وَٱلۡعَصۡرِ } { إِنَّ ٱلۡإِنسَـٰنَ لَفِی خُسۡرٍ } { إِلَّا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّـٰلِحَـٰتِ وَتَوَاصَوۡا۟ بِٱلۡحَقِّ وَتَوَاصَوۡا۟ بِٱلصَّبۡرِ } [Surah Al-asr ] ሰለፎች ተገናኝተው ሲለያዩ ከላይ ያለው ማለትም Surah Al-asr  አንደኛው  ላንደኛው በየተራ ይቀሩት ነበር ። ግን ዛሬ ላይ ይህን የሰለፍች መንገድየተረሳ የተዘነጋ ይመስላል ከኛ ውስጥ አንዳችን ለጓደኛችን ይህን ሱራ አስቁመን ብንቀራለት  ስቆብን ሁላ ሊያልፍ ይችላል አልያም ድምፅ ያምራል ብሎ ያሾፍብናል ለዚህ ሁሉ ምክንያት ግን👇 1/ ዲናዊ የሆኑ እውቀቶችን ካለመገንዘብ 2/ ለቁርአን ያለን ክብር የወረደ ስለመሆኑ 3/ የቀልባችን መድረቅ 4/ጓደኝነታችን ለአላህ ብሎ የተዋደዱ ከሚባሉት ውስጥ የማይመደብ እና ለጥቅም የተገናኘን ስለመሆኑ እንዲሁ ለዱኒያዊ አላማ የተገናኝን        በመሆኑ ነው ሼር ሼር ቻናል t.me/tdar_ina_islam ተቀላቀሉ
Show all...
👍 1
በተፈጥሮ እንግዳ ቸኮላ ነው በር በር ነው የሚያየው ከመቀመጣቸው ይልቅ ለመሄድ ለመሰናበት ይቸኩላሉ። ረመዷናችን እንግዲህ እንዲሁ ነው። እንግዶቻችን እንደቸኮሉ ነው ነፍሶቻችን አንድሱ ፣ ቁርዓን አንብቡ ፣ ጉድለቶቻችሁን ሙሉ ፣ ስግደታችሁን አስረዝሙ ፣ የሱና ሰላትን ስገዱ ፣ ዱዓአችሁንም በማብዛት ፣ ነፍሶቻችሁን በማጣት የረመዳንን ህይወት ለልባችሁ አድርጉ። ዛሬ ረመዷን ⑦ ነው።
Show all...
👍 16
「𑁍📲አዲስ አፕ | ተለቀቀ 𑁍」 ╭┈⟢🎁የረመዷን ስጦታ │ │❏መጃሊሱ ሸህሪ ረመዷን │ │ሊሸይኺል ዑሰይሚን ╰─────────────────╯    ╭🎙የደርሱ አቅራቢ:- ├─┈┈┈ │✑አቡ ዐብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ ╰────────────── ╭⧿⧿⛉ ├⎙አሁኑኑ ዳውንሎድ በማድረግ │ይጠቀሙ! │ ┝ለሌሎችም ሼር በማድረግ የአጅሩ │ተቋዳሽ ይሁኑ! ╰─────────── ╭╼╺╼╺╼╺╼╺╼ ╺╼╺╼ ┢⎘  ለመሰል ስራዎች ይቀላቀላሉን ┃ ┡🖇http://t.me/Yusuf_App1 ╰─╼╺╼╺╼╺╼╺╼╺╼╺╼
Show all...
👍 2
ጥያቄ 👇 ትክክለኛው መልስ ስታገኙ እጅግ ጠቃሚ ስጦታዎች ይሰጣችኋል 👇👇👇👇እውነት /ሀሰት 1// የሀቅ መመዘኛ የሸሪአ ትምህርትን ነው   በእኛ ላይ ደግሞ መማር  ግዴታ ነው ?
Show all...
እውነት
ሀሰት
የሱና ቻናል  በአጭር ግዜ እንዲያድግ እና ተደራሽ እንዲሆን የምትፈልጉ በውስጥ መሥመር ሊንክ ላኩለት   ቻናሉ ከሱናን የወጣ አልቀበልም 👇 ከ 1500 member በታች ያሉት ለግዜው አልቀበልም Link መላከያ 👇👇 @twhidfirst1 @twhidfirst1
Show all...
ረመዷንን ለላቀ ስብእና የውሳኔ ሰው ሁን فإذا مات متوكل على الله ) (አንዳች ነገር ለመፈጸም) ከወሰንክ በአላህ ተመካ።" (እለ ዒምራን፤ 59) ‹‹በሂጅራ ሁለተኛ ዓመት ላይ የመካ ቁረይሾች መዲናን ለማጥቃት ወስነው ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ነብዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) መረጃ ደረሳቸው። ወዲያውኑም ባልደረቦቻቸውን ሰብስበው በጉዳዩ ዙሪያ ለመመካከር ወሰኑ። አጀንዳው ፥ ጦርነቱ የማይቀር ከሆነ በከተማው ውስጥ የሚገኙ ግንቦችን ተጠቅሞ መዋጋት ወይስ ከመዲና ውጭ መግጠም፥ የቱ ይሻላል? የሚለው ነው። በመጨረሻም የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ምርጫ ባይሆንም የብዙሃኑ ወጣት ምርጫና ጉጉት ከመዲና ውጭ ጠላትን መግጠም ይሻላል የሚል ሆነ። ይህን ሃሳብ ከደገፉ ሰዎች መካከልም ገናናው ጀግና አጎታቸው ሐምዛ ይገኙበታል። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የውይይቱን የመጨረሻ ውጤት ተቀብለው ለጉዞ ዝግጅታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ሰዎች የአላህን መልዕክተኛ ሃሳብ ተቃወማችሁ እናንተ የራሳችሁን ሃሳብ አቀረባችሁ፤› በመባባል እርስበ ርሳቸው ተወቃቀሱ፡፡ ከዚያም ሰዎቹ ውሳኔያቸውን ቀልብሰው- ሐምዛ ሆይ! የአላህ መልዕክተኛን እርሳቸው የመረጡትን ሃሳብ ለመከተል ዝግጁዎች ነን› በልልን በማለት ሃሳባቸውን ማጠፋቸውን ተናገሩ። ሐምዛም ሁኔታውን ለነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሲገልጹላቸው፦ አንድ ነብይ ዘመቻ ለመውጣት ወስኖ የጦር ልብሱን ከለበሰ በኋላ እስኪዋጋ ድረስ አያወልቅም።› በማለት በውሳኔያቸው እንደሚጸኑ ቁርጠኝነታቸውን ገለፁለት።›› (ኢብን ሂሻም 3/71) ነብዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) ጉዳዩ በወሕይ የተወሰነ ነገር ስላልሆነ ወደ ውይይት አመጡት። በወሕይ የተገለጸ ቢሆን ኖሮ ለውይይት አይቀርብም ነበር። በመጨረሻም ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የብዙሃኑን ምርጫ ወደ ተግባር ለመለወጥ ከወሰኑ በኋላ ሰዎች የነብዩን (ሰዐወ) ሃሳብ መጋፋታቸው ተሰማቸው። ነገር ግን ይህ ምርጫቸው ሆኖ ሳይሆን እርሳቸውን ለማክበር ሲሉ ያደረጉት ነው። ከዚህም የተነሳ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ይህን የሁለተኛውን ሃሳብ ውድቅ አደርገዋል። ይህ የሚያሳየው አንድን ነገር አስቀድሞ ዙሪያውን ማጥናትና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ጋር መወያየት ከዚያም መወሰን በመጨረሻም በውሳኔ መጽናት እንደሚያስፈልግ ነው። የውሳኔ ሰው ማለት አንድን ነገር ለመጀመርም ሆነ ለመጨረስ ኃላፊነትን የሚወስድ ነው የውሳኔ ሰው ማለት ለመሆን ወይም ላለመሆን የሚያስችለውን ጠንካራ የስሜት ዝግጅት ማድረግ የሚችል ነው። የውሳኔ ሰው ማለት መጥፎና ደካማ ልምዶቹን አሸንፎ የማለፍ ብቃትን ያዳበረ ነው። የውሳኔ ሰው ማለት ስሜት በሁኔታዎች ከፍና ዝቅ በሚልበት ጊዜ ዓላማ ካደረገው ነገር ሳያፈገፍግ ወደፊት የመቀጠል ልምምድ ያለው ነው። የውሳኔ ሰው ማለት ግትርነትም ሆነ ልምጥምጥነት ባህሪ የሌለው ነው። የውሳኔ ሰው ማለት በስሜት የማይነዳ አስቦ ለመወሰንም የማይቸገር ነው። ሁላችንም በውስጣችን ብዙ ሃሳቦች አሉን፡፡ ነገር ግን ወደ ተግባር ለመለወጥ እንቸገራለን። ምክንያቱም ሁሉም ነገር በሃሳብ ደረጃ እያለ ቀላል ነው። ዳሩ ግን ያሰብነውን ወደ ተግባር ለማምጣት የሚያስፈልገው የትእግስት ወጭ ቀላል አይደለም። የዚህ አንዱ ምክንያት ተግባር ከእኛ ውጭ ከሆኑና ከማንቆጣጠራቸው ነገሮች ጋር የሚነካካ በመሆኑ ነው። ሌላው ምክንያት ደግሞ አንዳንዶቻችን የውሳኔ ሰው የማንሆነው በመጥፎ ልምዶቻችን ሳቢያ በጽናት ወደፊት የመሄድ ችግር ስለሚገጥመን ነው። አንዳንዶቻችን ከልክ ያለፈ ማኅበራዊ ፣ ቤተሰባዊና የጓደኛ ግንኙነቶች ስላሉን በእነርሱ ሳቢያ ድርጊቶቻችንና ውሳኔዎቻችን ፈተና ላይ ስለሚወድቁብን ነው።አንዳንዶቻችን ከምቾት ቀጠናዎቻችን ላለመውጣት ስንል መወሰን ስለምንቸገር ነው። አንዳንዶቻችን ከልክ ያለፉ ጥንቃቄዎችን ፈላጊዎች ስለሆንን ነው። አንዳንዶቻችን የማመንታት አባዜ ስላለብን ነው። በአንጻሩ ደግሞ አንዳንዶቻችን ያለምንም አስተውሎ በወሳኝ ጉዳዮች ላይ ሳይቀር ፈጥነን በስሜት የምንወስንም አለን። ትክክለኛውን ነገር በትክክለኛው ጊዜና ቦታ የምንወስን ጥቂቶች ነን አንድ ሰው የመወሰንና የድርጊት አቅም እንዲኖረው የሚያደርጉት ሁለት ወሳኝ ነገሮች መኖራቸውን ጠበብት ይናገራሉ፡፡ እነርሱም ውሳኔ በሚያስፈልገው ነገር ላይ በቂ እውቀት ማግኘትና የፍላጎት መኖር ናቸው ሰው በቂ እውቀት ኖሮት ፍላጎት ከሌለው እውቀቱ ብቻውን የውሳኔ ሰው አያደርገውም። እንዲሁም ግልጽ ባልሆነ ነገርም መወሰን አስቸጋሪ ነው። ብዙ ጊዜ ግን የድርጊት አቅምና የውሳኔ ቁርጠኝነትን የምናጣው ካለን ነገር የበለጠ በጎደሉን ነገሮች ላይ ስለምናተኩር ነው። ምክንያቱም እንዲህ ዓይነት በራስ ላይ ያለ ዕይታ በራስ መተማመንን በፍጥነት ያጠፋል። በራስ መተማመንን ማጣት ደግሞ የራሳችን የሆነ ግንዛቤ ሳይኖረን በሌላ ሰው ሃሳብ ላይ ብቻ ጥገኛ እንድንሆን ያደርገናል። ብዙ ሰዎች በቂ እውቀትም ሆነ የድርጊት አቅም እያላቸውም በጉድለታቸው ላይ ስለሚያተኩሩ ብቻ ከተለምዷዊና ከተርታ ሕይወታቸው ከፍ ያለ ድርጊት ወይም የመሆን ቁርጠኝነትን ያጣሉ።
Show all...
👍 17 3🥰 2
ስናፈጥር የምንለው ዱአ ለመሸምደድ እንዲመች ቀለል ባለ መልኩ የተዘጋጀ ነው ቪዲዮውን ሼር አድርጉት ይህ ነገር የማያውቁ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ ሼር ቻናሉ ተቀላቀሉ👇👇 t.me/tdar_ina_islam t.me/tdar_ina_islam
Show all...
👍 2
~ ክፍል አንድ ~ የሞራል ከፍታ ይኑርህ ( رِجَالٌ صَدَقُوا مَا عَهَدُوا اللَّهَ عَلَيْهِ ) "ለአላህ የገቡትን ቃል የፈጸሙ ወንዶች (ጀግኖች) አሉ።" (አል-አሕዛብ፡ 23) «የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ከአንድ ጉዞ ሲመለሱ በአንድ የገጠር ሰው ቤት አጠገብ አለፉ፡፡ ባላገሩም የእንግዳ አቀባበል አደረገላቸው። ከተስተናገዱ በኋላ መዲና ስትመጣ ጎራ ብለህ ጐብኘኝ አሉት። ባላገሩም ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወደ መዲና መጣ። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንደ እንግዳ ካስተናገዱት በኋላ አንድ ነገር ላበረክትልህ እሻለሁና ጠይቀኝ አሉት። እርሱም የምጋልባት እንሰሳ እፈልጋለሁ, አላቸው፡፡ ስጡት አሉ። ~ አሁንም ጠይቀኝ አሉት። እርሱም ለቤተሰቦቼ አገልጋይ እፈልጋለሁ, አላቸው፡፡ ‹ሰጡት አሉ፡፡ ~ አሁንም ‹ጠይቀኝ አሉት። ‹ፍየሎቼን የሚጠብቅልኝ ውሻ እፈልጋለሁ, አላቸው። ~• ይህ አጋጣሚ በጣም ከፍ ያለ ነገር የሚጠየቅበት ነበር ፤ እርሱ ግን ተራ በሆኑ ነገሮች ላይ አተኮረ። የዚህ ጊዜ) ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)- እንደ በኒ ኢስራኢሏ አዛውንት መሆን ተሳናችሁን አሉ። በሁኔታው ሰሐቦች ተገረሙ። የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! የበኒ ኢስራኢሏ አዛውንት ታሪኳ ምንድን ነው?› አሏቸው። ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) ‹ሙሳ ከግብጽ ሕዝቦቹን ይዞ ሲወጣ በጉዞ ላይ እያሉ ድቅድቅ ያለ ጨለማ አጋጠማቸው። ሙሳም በተከሰተው ነገር ተገረመ። ሕቦቹም እንዲህ አሉት- “ከአንተ በፊት የነበረው ነብይ ዩሱፍ ቃል ኪዳን አስይዞናል። እርሱም ከግብጽ ምድር ስንወጣ ከቀብሩ አውጥተን ይዘነው እንድንሄድ ነበር” አሉት። ~ ሙሳም “ቀብሩን አሳዩኝ? የት ነው ያለው?" አላቸው። እነርሱም “አንዲት አዛውንት እንጅ የሚያውቀው ሰው የለም” አሉ። ሙሳ “አዛውንቷን አምጡልኝ?” አለ። ስትመጣ “የዩሱፍ ቀብር የትነው? አሳይኝ” አላት። እርሷም “ጥያቄዬን እስክትመልስልኝ ድረስ አላሳይህም” አለችው። “ጥያቄሽ ምንድን ነው?” አላት። “በጀነት ውስጥ ከአንተ ጋር አብሬ መሆን ነው (በጀነት ውስጥ በነብይነት ደረጃ መሆን እፈልጋለሁ)” አለች። ~ ሙሳ ጥያቄዋ ከብዶ ታየው። (ምክንያቱም ሙሳ የጠየቋት የተለመደ መረጃ ነው፤ ነገር ግን አዛውንቷ የጠየቀችው ዋጋ ያልተለመደ ከመሆኑ ጋር በሙላ እጅም ላይ የሌለ ነው። ዳሩ ግን) አላህ በሙሳ 'ጥያቄዋን ተቀበላት' የሚል ራዕይ ላከለት። ሙሳም “ተቀብዬሻለሁ” አላት። ከዚያም አንድ ውሃ ያለበት ቦታ ጠቆመችው። ውሃውን ቀድቶ ባዶ እንዲያደርገውም ነገረችው። ሲጨርሱም “እዚህ ቦታ ላይ ቆፍረው” አለች። ቆፈረና የዩሱፍን አስክሬን አወጣ።›› (ኢማም አሕመድ የዘገቡት) ሁሌም የሞራል ከፍታ የሌለው ሰው ዝቅ ባሉ ነገሮች ላይ ይወሰናል። የሞራል ከፍታ ያለው ሰው ግን የተራ ነገሮች አያረኩትም። በአዛውንቷና በባላገሩ መካከል የሆነው ይኸው ነው። አዛውንቷ ከነብዩ ሙሳ (ዐ.ሰ) ያገኘችውን ዕድል ተጠቅማ ወጣትነቴ እንዲመለስልኝ እሻለሁ ማለት ትችል ነበር። ይሁንና አጋጣሚው ከዚህ በላይ የሚፈቅድ በመሆኑ ከነብይ ጋር በጀነት የመሆን መታደልን አግኝታለች። ~ አዛውንቷ ምን ያህል ብልህ ፣ አማኝና የላቀ የሞራል ከፍታ እንዳላት ግልጽ ነው። የሞራል ከፍታ ማለት በእያንዳንዳችን የሚወሰን የመሆን ጥጋችን ነው። ዳሩ ግን ሁላችንም ከአንድ ሰማይ በታች ብንሆንም አንድ ዓይነት የሞራል ከፍታና የተነሳሽነት ፍቅር የለንም። ከዚህም የተነሳ ከፊሎቻችን በተራው ነገር የምንረካ ነን። ከፊሎቻችን ያሰብነውን ወደ መሆን ለማምጣት የሰዎችን ቅስቀሳና ጉትጎታ የምንፈልግ ነን። ከፊሎቻችን ደግሞ በተነሳሽነት ፍቅር የተሞላን ነን። “ሰው በውስጡ ወደ ፈጠረው ምናባዊ ዓለም ጉዞ ሲጀምር ስሜቶቹ፣ አካሎቹ፣ አእምሮውና መንፈሱ ንቁ የሆነ ተሳትፎ እንደሚያደርጉ' ጥናቶች ያሳያሉ። እነዚህ ጥናቶች የሚነግሩን ቁም ነገር በሕይወት ዘመናችን ልናሳካው የምንሻውን ነገር በሃሳባችን ውስጥ ልናሳድረውና ልናቀጣጥለው እንደሚገባን ነው። ምክንያቱም በአእምሮአችን በሚገባ የተሳለውን ነገር ወደ መሆን የማምጣት አቅማችን ከፍ ያለ ነው። እንደሚታወቀው የሁሉም ነገር መጀመሪያ ጥሩ ሃሳብ ፥ ከዚያም ያሰቡትን ወደ መሆን ማምጣት ነው። ከውስጥ ስንፍና ርቀን አንድን ነገር እንድንጀምር ከዚያም እንድናዘልቅ የሚያደርገን በነገሩ ላይ ያለን ልምምድና ችሎታ ወሳኝነት ቢኖራቸውም የአንበሳውን ድርሻ የሚይዘው ግን የተነሳሽነት ፍቅራችን ነው። ምክንያቱም የሞራል ከፍታና የተነሳሽነት ፍቅር ከሌለን አንድን ነገር የማስቀጠል አቅማችን ፈተና ላይ ይወድቃል። የሰው ልጅ የተነሳሽነት ፍቅርና የሞራል ከፍታ ሊኖረው የሚችለው ደግሞ የሁለቱን ወሳኝ ጥያቄዎች መልስ አጥብቆ ፈላጊ ሲሆን ነው። ማለትም በዚህች ምድር ላይ ሕይወቴን አንዴት ቀጣይ ማድረግ አችላለሁ' እና በሕይወት የምኖርበት ፋይዳ ምንድን ነው የሚሉትን ጥያቄዎች መልስ ሲፈልግ ነው። እነዚህ ሁለት ጥያቄዎች በሁሉም ሰው ነፍስ ውስጥ የተዘሩ መሰረታዊና ተፈጥሯዊ ጥያቄዎች ናቸው። የነዚህ ጥያቄዎች መልሶችም እየተዘረጋጉ የሰውን ሁለመናና ፍላጎትን ይመራሉ። ~ በየቅጽበቱ በሚያደርጋቸው እርምጃዎችም ይተረጎማሉ። በሌላ አባባል ሰው ሕይወቱን በሙሉ አሳልፎ የሚሠጠው ለነዚህ ጥያቄዎች መልስ ፍለጋ ነው፡፡ ይሁንና አንዳንዱ ሰው ይበልጥ የሚጨነቀው እንዴት እኖራለሁ' እንጅ “ለምን እኖራለሁ' በሚለው ጥያቄ ላይ አይደለም። የዚህ ዋና ምክንያቱ በልቡ ላይ የተፈጠረበትን ያላዋቂነትና የክህደት ግርዶሽ ማስወገድ አለመቻሉ ነው።
Show all...
👍 10🥰 2👏 1
ነሺዳ + መንዙማ = ዘፈን በየአመቱ ረመዷን ጠብቀው ይህን ኢስላማዊ  የሚል ቅብ ቀብተው የሚለቁ አሉ  ረመዳንን በመንዙማና በነሺዳ  ሞቅ ሞቅ ለማድረግ ያስባሉ  የሚያስቀውና የሚያሳዝነው እነኚህ መንዙማ እና ነሺዳ ከታዋቂ ዘፋኞች ሳይቀር  ግጥም እየሰረቁ ነው የሚሰሩት ግን አንሳሳት ሁላችንም ቆም ብለን ልናስብበት ይገባል መንዙማ በማዳመጥ ወደ አላህ የምንቃረብ አይምሰለን ፆመኛ ሆነን የሽርክ መንዙማ እየሰማን እንዴት           ወደ አላህ እንቃረባለን ረመዷን ላይ መንዙማ ከረመዷን ውጪ ዘፈን?? ኢስላማዊ ስለተባለ ብቻ አናሰልመውም  ረመዳን የቁርአን ወር ነው ። ረመዳን የኢባዳ ወር ነው ። ረመዳን የዚክር ወር ነው ። አላህ ከምንም ግዜ በላይ የምናስታውበት የምንለምንበት የምናመሰግንበት ወር ነው ረሱል ሰለላሁአለዪሂ ወሰለም የወደደ እኮ  እነሱን ነው ሚከተለው። ሱናቸውን ነው በአቅሙ ልክ እግር በእግር የሚከተለው እንጂ በሳቸው ስም እየነገድ ኪሱን እየሞላ ኡማውን ኢስላማዊ የሚል ስም ሰይሞ በዘፈን አያጠምም አላህ ይምራን አላህ ከአውቆ አጥፊዎች አያድርገን ሼር በማድረግ አሰራጩት ✍a.k ቻናሉ ተቀላቀሉ👇👇 t.me/tdar_ina_islam t.me/tdar_ina_islam
Show all...
👍 15 1
በቀላሉ እጅግ ጠቃሚ ቻናሎች ተቀላቀሉ 👇👇
Show all...
1
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
ለማግኘት 🔉🔊
በመቀጠል ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ርዕስ: ሰለ አህባሽ እና ተያያዥ ጉዳዮች ቀጥታ ስርጭት👇👇 t.me/tdar_ina_islam t.me/tdar_ina_islam
Show all...
ታላቅ የሙሀደራ ፕሮግራም በtelegram 🌴               ይታደሙ በአካል መገኘት ያልቻላችሁ ✅በታላቁ የረመዷን ወር ዋዜማ ዛሬ  በዓይነቱ ልዩ የሆነ የረመዷን ኢስቲቅባል ሙሀደራ ፕሮግራም ተሰናድቶ ይጠብቆታል። ፕሮግራሙን ለየት የሚያደርገው ነገር ከአዲስ አበባ የሚመጡ እንቁ የሱና ዱዓቶች ይታደሙበታል። በፕሮግራሙ ከሚታደሙ ዱዓቶች መካከል:- 1ኛ-ዑስታዝ ኢብኑ ሙነወር (አቡ ሁዘይፋ) 2ኛ-ዑስታዝ ሙሀመድ ሲራጅ 3ኛ-ዑስታዝ አብዱናስር መኑር 4ኛ-ዑስታዝ ሙሀመድ ሱልጣን እንዲሁም በዕለቱ የ ጥያቄና መልስ ፕሮግራም ይኖረናል። 🗓ቅዳሜ /ማለትም  ዛሬ 🕰 ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ
N.B ቀጥታ ስርጭት የሚተላለፍበት
ቻናል 👇👇 ገባ ገባ እያላችሁ ጠብቁ ፕሮግራሙ እስኪጀመር 👇 t.me/tdar_ina_islam t.me/tdar_ina_islam
Show all...
ጥያቄ 👇 1✍ ከሚከተሉት ውስጥ የረመዳን ወር ከሌሎቹ 11 ወራቶች ለየት የሚያደርጉት የራሱ የሆኑ መለያወች መካከል የሆነው የቱ ነው?? 👍 መልሱ ስታገኙ የሚሰጣችሁ ስጦታ ንኩለት
Show all...
1
ሀ// የጀነት በሮች የሚከፈቱበት ወር መሆኑ
ለ//የኀጢዓት ማሰረዣ ወር በመሆኑ
ሐ// በዚህ ወር የኡምራ ደረጃ ከፍ ማለቱ
መ// ቁርአን የወረደበት ወር መሆኑ
ሠ// ለይለቱል ቀድር በውስጡ የያዘ ወር በመሆኑ
ረ// ቂያሙ ረመዷን (ተራዊህ)የሚገኝበት ወር በመሆኑ
ሰ// ሁሉም መልስ ነው
🎉ታላቅ ሙሓደራ እና ጥያቄ መልስ . . . በታላላቅ መሻይኾች . . . ☑️ ዛሬ ጁሙዓ #በአህሉ-ተውሂድ ኢስላሚክ ሴንተር ቻናል ላይ ታላቅ ሙሀደራ እና ጥያቄናመልስ ይዘጋጃል- - ● ተጋባዥ እንግዶች ● - - 🎙 الشيخ رشاد الورد الحبيشي <ሼይኽ ረሻድ አል-ሁበይሺይ - ከሳዑዲ > 🎙الشيخ أول بن أحمد الخميسي < ሼይኽ አወል አህመድ አል-ከሚሲይ> 〰〰〰〰〰〰 🔁ፕሮግራም መሪ : ኡስታዝ አቡ-ረይስ 🔺 ይህንን ደማቅ ምሽት አብረውን እንዲያሳልፉና ረመዳን ሊገባ ቀናቶች ብቻ ስለሆነ የቀሩት ወቅቱን ያገናዘበ ● ምክር ሸምተው ● ብዥ ያለቦትን ጠይቄው ይህንን የተከበረ ወር እንዲቀበሉት ተጋብዘዋል ። ⏰ሰዓት : 2:40 በኢትዮ 🖇የሚተላለፍበት ቻናል ሊንክ👇t.me/sefinetunuh t.me/sefinetunuh
Show all...
ጥያቄ 👇 1✍ ከሚከተሉት ውስጥ የረመዳን ወር ከሌሎቹ 11 ወራቶች ለየት የሚያደርጉት የራሱ የሆኑ መለያወች መካከል የሆነው የቱ ነው?? 👍 መልሱ ስታገኙ የሚሰጣችሁ ስጦታ ንኩለት
Show all...
👍 5
ሀ// የጀነት በሮች የሚከፈቱበት ወር መሆኑ
ለ//የኀጢዓት ማሰረዣ ወር በመሆኑ
ሐ// በዚህ ወር የኡምራ ደረጃ ከፍ ማለቱ
መ// ቁርአን የወረደበት ወር መሆኑ
ሠ// ለይለቱል ቀድር በውስጡ የያዘ ወር በመሆኑ
ረ// ቂያሙ ረመዷን (ተራዊህ)የሚገኝበት ወር በመሆኑ
ሰ// ሁሉም መልስ ነው
ቀጥታ ስርጭት من هم الخاسرون؟             ከሳሪዎች ማን'ናቸው?   🎙 በወንድማችን AbuOubeida (አቡ ዑበይዳ) 👇👇👇ቀጥታ ስርጭት        ተ             ጀ                    ም                         ሯ                                ል      ሺርርርር እያደርጋችሁ t.me/+kKY_gazIcRoyNWQ0 t.me/+kKY_gazIcRoyNWQ0
Show all...
👍 2
                  📍ማስታወሻ📍 📲የሙሀደራ ፕሮግራም ምሽት 3:30 ስአት ⏰                                                ላይ ይኖረናል            ➽ሳትርቁ ጠብቁን 💺💺💺💺💺💺 🎙በወንድማችን አቡ ዑበይዳ ሰዒድ            ➽ርዕስ ፦ من هم الخاسرون؟ ከሳሪዎች ማን'ናቸው?   ➽የሚተላለፍበት የቴሌግራም አድራሻ           ትዳር እና ኢስላም https://t.me/+JZhIBzu2bKU2OTU0 https://t.me/+JZhIBzu2bKU2OTU0
Show all...
👍 3
0ረብ ሃገር ያላችሁ ወገኖች ! ~ 1- ቤተሰቦቻችሁን እርዱ። መሆንም ያለበት ነው። ግን ድጋፋችሁ የሚጠቀሙበት እንጂ የሚጎዱበት እንዳይሆን ተጠንቀቁ። ለአጉል ሱሶች የሚጠፋ አይሁን። 2- ራሳችሁን አትርሱ። ተቀማጭ ይኑራችሁ። ዛሬ ሰው ተጨካክኗል። እድሜ ልካችሁን ስትልኩ ኖራችሁ በህመም የወደቃችሁ እለት የሚያነሳችሁ እንኳ ላይኖር ይችላል። 3- ብድር ስትሰጡ በሚገባ ተዋዋሉ። መካካድ በዝቷል። አማና የምታስቀምጡበትንም ለዩ። 4- በማይረቡ ሰበቦች የሚወጡ ወጭዎችን ቀንሱ። 5- ጥሩ ክፍያ አላገኘንም እያላችሁ ለወራት ያለ ስራ አትቀመጡ። 6- "አገባሻለሁ" ለሚሉ ጩልሌዎች የዘመናት ጥሪታችሁን አሟጣችሁ አትስጡ። ለትዳር ሲባል ገንዘብ መውጣቱ ችግር የለውም። ገንዘባችሁን እንጂ እናንተን በማይፈልጉ ሰዎች አትሸወዱ ማለቴ ነው። = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor
Show all...
👍 27
መልዕክተኛው ሰዐወ ተቀምጠው ንግግር ያደርጋሉ። ዙርያቸውን ከበው የተቀመጡ የመልዕክተኛው ሰዐወ ባልደረቦች በተመስጦ እና በስስት የመልዕክተኛውን ንግግር እያዳመጡ ነው። ፍፁም እርጋታ ፍፁም ስክነት ስፍራው ላይ ሰፍኗል። ድንገት ከየት መጣ ያልተባለ አንድ አይሁድ ዘሎ ወደ መሀል በመግባት ነቢን ሰዐወ በሀይል አናቃቸው። ‹‹ሙሀመድ ሆይ! ገንዘቤን መልስልኝ፤ ድሮም ገንዘብ ተበድሮ መጥፋት የዘራችሁ ነው ›› ብሎ ጮኸባቸው። ይህ ሰው በርግጥ ብድር ለነቢ ሰዐወ አብድሮ ነበር፤ ግና መክፈያ ግዜው አልደረሰም። ሰሀባው የነቢን መታነቅ ሲመለከት በጥድፍያ ሰይፉን መዘዘ፦‹‹ነቢ እባክዎን ይህን አንገት ልቀንጥሰው ይፍቀዱልኝ›› አለም። ነቢ ሰዐወ ሰከኑ፣ ታገሱ፣ ንዴታቸውን ዋጡ፣ እንዲህም አሉ፦‹‹በስርዐት ብሩን እንዲጠይቀኝ ለርሱ ንገረው፤ ለኔ ደግሞ ብድሬን እንድመልስ ምከረኝ እንጂ አንገት መቁረጥን ምን አመጣው!›› የሁዲው ተናገረ፦‹‹በዝያ በዕውነት በላከህ ጌታ እምላለሁ፤ ብድሬን ልጠይቅህ አልመጣሁም። መክፈያ ግዜውም አልደረሰም። ብዙ ሰለልኩህ፣ ብዙ ፈተንኩህ ግና ያ በኦሪት ይወራለት የነበረው ነቢይ አንተ ሁነህ አገኘሁህ። ትዕግስተኛ ስለመሆንህ ኦሪት ነገረኝ። ዛሬ ልፈትንህ ሽቼ በአክባሪዎችህ ፊት አነቅኩህ ትዕግስትህን ተመለከትኩ። እነሆ! የአላህ መልዕክተኛ መሆንህን እመሰክራለሁ። የነበረብህንም እዳ ለነዳያን ትመፀውተው ዘንድም ይቅር ብያለሁ ›› ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም
Show all...
👍 32 1🥰 1
የሟችና አልቃሽ አስገራሚ ገፅታ አንድ ቀን አላህን በጣም የሚያመልክ ሰው ወደ ሞት እየተቃረበ መጣ በዙሪያው ያሉ ቤተሰቦቹ ማልቀስ ጀመሩ...ከዛም ይህ ሊሞት የተቃረበ ሰው ለቤተሰቦቹ "ቁጭ አድርጉኝ " አላቸው ደግፈው አስቀመጡት ..ከዛም ወደ አባቱ ዞረና ለምን ታለቅሳለህ ብሎ ጠየቀው አባቱም አንተን ማጣቴ ከአንተ በኋላ ብቸኛ መሆኔ ነው የሚያስለቅሰኝ ብሎ መለሰ ..ወደ እናቱም ዞረና እናቴ ለምንድነው የምታለቅሺው አላት እናትየውም "የልጅ ማጣት መሪር ሀዘን ነው የሚያስለቅሰኝ " አለችው ..ወደ ሚስቱ ዞረና ባለቤቴ ምንድነው የሚያስለቅስሽ አላት እሷም " የአንተን መልካም ነገር ስለማጣ ፤ወደሌላ ስለምከጅል ሸክም ስለምሆን ነው አለችው ወደ ልጆቹም ዞረና ምንድነው የሚያስለቅሳችሁ አላቸው እነሱም " ካሁን በኋላ ወደ የቲምነት ወደ ውርደትና ደጋፊ ወደማጣት ስለምንጓዝ አሉት....ይህን ሁሉ ከሰማ በኋላ በጣም አለቀሰ ቤተሰቦቹም ለምን ታለቅሳለህ አሉት እሱም ሁላችሁም ለኔ ብላችሁ ሳይሆን ለራሳችሁ ጥቅም ነው የምታለቅሱት ከናንተ ውስጥ ...ለጉዞዬ መርዘም ለስንቄ ማነስ የሚያለቅስልኝ የለም??....ከናንተ ውስጥ ከዚህ በኋላ መኝታዬ ለብቻዬ አፈር ለመሆኑ የሚያለቅስልኝ የለም ?? ከናንተ ውስጥ ከዚህ በኋላ ስለሚጠብቀኝ አስደንጋጭ ጥያቄዎች የሚያለቅስልኝ ሰው የለም ?? ከናንተ ውስጥ የአለማት ጌታ ፊት መቆሜን አስታውሶ የሚያለቅስልኝ የለም ??......አለና በፊቱ ወደቀ ቢያንቀሳቅሱትም ህይወቱ አልፋለች 💔💔😭
Show all...
👍 35 12😢 8
ቀጥታ ስርጭት آثار الذنوب والمعاصي على العبد           የ ወንጀል መዘዞች በ ባሪያ ላይ 🎙አቡ ሱፊያን 👇👇👇ቀጥታ ስርጭት        ተ             ጀ                    ም                         ሯ                                ል      ሺርርርር እያደርጋችሁ t.me/+kKY_gazIcRoyNWQ0 t.me/+kKY_gazIcRoyNWQ0
Show all...
1
🔊 እጅግ ጠቃሚ የሙሀደራ ፕሮግራም                     እርዕስ آثار الذنوب والمعاصي على العبد           የ ወንጀል መዘዞች በ ባሪያ ላይ        ሁላችሁም እንደምትገኙ አልጠራጠርም ርዕሱ  ይበልጥ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ስለሆነ ሰአት ዛሬ  ምሽት ልክ 3:30  ይጀመራል በአላህ ፍቃድ   🎙 በወንድማች አቡ ሱፊያን   ቀጥታ ስርጭት የሚተላለፍበት ቻናል:-  👇👇👇 t.me/+kKY_gazIcRoyNWQ0 t.me/+kKY_gazIcRoyNWQ0
Show all...
5
የአዛውንቱ ማስታወሻ ለአቅመ አዳም ስደርስ ማግባት እመኝ ነበር'ና በርግጥም ደርሼ አገባሁ። ግና ትዳር ያለ ልጆች አይጥምም ነበር። ልጅ ተመኘሁ፤ ልጆችንም ወለድኩም። ለኔም ለልጆቼም ሚበቃን ቪላ እንዲኖረን ተመኘሁ። ተግቼ ሰርቼ ገንዘብ ያዝኩ'ና ቪላውን ገነባሁ። ልጆቼ አድገው ጎረመሱ። ልድራቸው እና የልጅ ልጅ እንዲያሳዩኝ ተመኘሁ፤ በርግጥም ዳርኳቸው። ግና አሁን ሰውነቴ ይደክም ጀመር፤ እድሜዬም ስራ ትቼ ቤት እንድቀመጥ ያስገድደኝም ያዘ። ስራዬን ሰው ተክቼ ቤት ጠቅልዬ ለመግባት ተመኘሁ፤ በርግጥም ቤት ገባሁ። ያኔ ስራ አጥ ሆኜ ቤት እውል እንደነበረ ሁላ በተመሳሳይ መልኩ በስተርጅናዬም ላይ ቤት መዋል ጀመርኩ። ግና ምኞት አሁንም ያማልለኝ ይዟል። ቁርአንን መሐፈዝ ተመኘሁ፤ ግና አዕምሮዬ ዝሏል። የሱና ፆሞች ላይ ለማተኮር ተመኘሁ፤ ግና ጤንነቴ ከድቶኝ ኑሯል። የለይል ሰላት ላይ ለመበርታት ወሰንኩ፤ ግና እግሮቼ ሊሸከሙኝ ተሳናቸው። ነቢዩ ﷺ  ያሉት ነገር አሁን ገባኝ። 5 ነገር ሳይቀድምህ በ5 ነገር ተጠቀም - ወጣትነትህን እርጅና ሳይቀድምህ - ጤንነትህን በሽታ ሳይቀድምህ - ሀብትህን ድህነት ሳይቀድምህ - ነፃ ግዜህን የግዜ እጥረት ሳይገጥምህ - ህይወትህን ሞት ሳይቀድምህ
Show all...
👍 55 11
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!