cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

"زاد المعاد" ዛዱልመዓድ- የነገው ስንቅ

በኡስታዝ አሕመድ ኣደም የሚዘጋጁ ተከታታይ ቋሚ ትምህርቶች፣ ፈትዋዎች፣ ሙሓደራዎችና አጫጭር ምክሮች የሚቀርቡበት ቻናል القناة التعليمية الرسمية لأبي عبد الله أحمد بن آدم الشراري دروس في القرآن والعقيدة والفقه وفتاوى ومقالات متنوعة باللغة الأمهرية http://www.youtube.com/c/ZadulMaad

Show more
Advertising posts
56 833Subscribers
+5324 hours
+6287 days
+2 23930 days
Posts Archive
🌳የቁርኣን ተፍሲር🌳           ክ/217 🔹تفسير سورة ق 🔮 የሱረቱ ቃፍ ተፍሲር         ቁ/3 (ከ 30-35)    የዕለተ ጁሙዓ ረመዷን 19/9/1445 ዓ.ሂ          የቁርኣን ትምህርት 🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም     የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ          ⬇ ⬇ ⬇ ⬇ 🔎 https://tinyurl.com/2b6qxxtw       🔸🔹🔸🔹🔸🔹 🌐https://telegram.me/ahmedadem ~~~~ 🔗https://www.facebook.com/yenegew/j ~~~~l 📶  http://www.youtube.com/c/ZadulMaad 📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!" አል-ኢማሙ ማሊክ
Show all...
🌴የረመዷን ልዩ  መልዕክት🌴           ቁ/15 ☄አማናን ያለመጠበቅ መዘዞች        ሀሙስ ረመዷን 18/1445ዓ.ሂ 🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም     የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ          ⬇ ⬇ ⬇ ⬇ 🔎  https://tinyurl.com/2bg44mc3       🔸🔹🔸🔹🔸🔹 🌐https://telegrgam.me/ahmedadem ~~~~ 🔗https://www.facebook.com/yenegew/ ~~~~ 📶  http://www.youtube.com/c/ZadulMaad 📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!" አል-ኢማሙ ማሊክ
Show all...
🏷️የዛዱል መዓድ ፈታዋ 🌾 فتاوى زاد المعاد           ቁ/247 ረቡዕ 17/9/1445 ዓ.ሂ 🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ ⏬  ⏬   ⏬   ⏬   ⏬  ⏬ 🔎https://tinyurl.com/2a2282d3       🔹 🔸 🔹 🔸 🔹 1/ እኔ አመት ባመት የረመዷን መጀመሪያና መጨረሻ  የወር አበባ ላይ እሆናለሁ ረመዷንን ንፁህ ሁኘ ባለመቀበሌ እንድሁም የኢድ ሶላት ባለመስገዴ አላህ ስለማይወደኝ ነው እያልኩ እጨናነቃለሁ እስኪ አንድ በሉኝ ጀዛኩሙላህ ኸይር 2/ ሀይድ በረመዳን መጣ እና  አራት  ቀን ብቻ ፈሶ ቆመ  ከዛ እኔ በስድስተኛው ቀን ሶላት ሰገኩ ፆምም ፆምኩ ሁለት ቀን አሳልፎ በሶስተኛው ቀን መጣ ያ ፆም እዴት ይታያል 3/ረመዷን ላይ የአንድ ወር ከሀያ ቀን ፅንስ  ውጭ ሀገር ለመሄድ ብየ አስወርጄ ነበር በጊዜው በዚሁ ምክኒያት አምስት ቀን አፍጥሪያለሁ ከፋራው ምንድን ነው? 4/ሱጁድ በምንወርድበት ግዜ እጃችን  ቀጥታ ወደ መሬት ነው ወይሥ ጉልበታችንን ይዘን ነው የምንወርደው 5/ለምንድነው አላህ ራሱን እኛ እያለ ቁርዓን ላይ የሚጠቅሰው 6/ ሰለምቴ ነኝ አልሀምዱሊላህ   እሰግዳለሁ እፆማለሁ ከሰለምኩ  4 አመት ሁኖኛል እና  የሰለምኩት  እስልምና በልጅነቴ  ጀምሮ አልሀምዱሊላ  ሲሉ  ደስ  ይለኝ  ነበርና  አረብ ሀገር  ሂጀ  መፆም መስገድ ጀመርኩ  ቁራአንም ተማርኩ አልሀምዱሊላ  ነገር ግን ሸሀዳ  በራሴ  እንጅ  ሸሀዳ  ያስያዘኝ  ሰው  የለም  ስጠይቅ  እስልምናሽ ውድቅ ነው  አሉኝ  ምንድን ነው  ማድረግ  ያለብኝ  የምሰራባቸው  ሰወች ጥሩ ሙስሊሞች  ስለነበሩ  ቁርአን  በአማረኛም  ትርጉም በአረበኛም  ይገዙልኝ  ነበር  በዛው ቁርአንን ተማርኩ  እስልምናየ   በልቤ  ተዋህዶል   የስካሁኑ  እስልምናየ  ውድቅ  ነው በጣም ጨንቆኛል 7/የረመዷን ወቅት እንደመሆኑ አንድ ከእሱ ጋር ተያያዥነት የሚኖረው ጥያቄ ነበረኝ፦እሱም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሐገራችን ረመዷን አጋማሽ ላይ የአደባባይ ላይ ኢፍጣር የሚል ነገር ተጀምሯል፣ ይህ ነገር ለብዙ አልባሌ ነገራቶች ሰበብ እንደመሆኑ ከሸሪዓ አንፃር ቢያብራሩት?ጀዛኩሙልላሁ ኸይር 8/  ጓዴኛየን  አዛን  የሰማሁ  መስሎኝ  አዛን  አለ  አፍጥሪ ብያት  አፈጠርች  ከዛ ከ2ደቂቃ በሀላ  አዛን  አለ  ልጅቷም  በጣም ተናደደችብኝ   እና እኔ  ጫጫታም  ስላለ  አዛን  ያለ መስሎኝ ነው  አፍጥሪ  ያልኩት  እና አሁን የሷ ፆም  ትክክልሽነው አይደለም  ከ2ዴቂቃበሀላነው  አዛን  ያለው  ጀዛኩሙላህ  ኸይር 9/ለልጇ ስትል  ወይም ከፆምኩ ጡቴ ይደርቃል ብላ ያልፆመች ሴት ቀዳውን ብቻ ነው ማውጣት እሚጠበቅባት ወይስ ተጨማሪ ከፋራ አለባት? 10/ እኔ የቲቢ ታማሚ ነበርኩ ለአመት  ያህል ነበር መድኃኒት  የታዘዘልኝ  ቀዷ ሳለወጣ  ሁለት ረመዳን ፆምኩኝ እንዴት ነዉ ማዉጣት ያለብኚ ቢብራሩልኝ 11/የስኳር በሽታ መርፌ አዛን ካለ በኋላ ቢወሰድ  ፆም ያበላሻል? 12/የዛሬ 6 አመት  ከባሌ ጋር  በረመዳን  ግንኝነት አድርገናል ፈልጌ አይደለም አስገድዶኝ ነው ስለ ዲንም ምንም አላቅም ነበር  ልጅ ነበርኩኝ የ16 አመት ልጅ ነበርኩኝ አሁን ግን ከልጁ ተለያይተናል   ከፋራ አለብኝ ? እንዴት ማደረግ አለብኝ? 13/ለተራዊህ ለሶላት መስጂድ ስገባ ዒሻ ተሰግዶ ተራዊህ ላይ ደረስኩ መጀመሪያ መስገድ ያለብኝ ተራዊህን ነው ወይስ ዒሻን ነው መስገድ ያለብኝ? 14/እኔ ልጆች አሉኝ በስደት ነው ያለሁት ልጆቼ ከእናቴ ጋር ናቸው አባታቸው ስራ የለውም  ዘካ እኔ ለነሱም ለራሴም አገር ልኬ ማውጣት እችላለሁ? 15/ተራዊህ ወይም ተሀጁድ ቤት ውስጥ ስሰግድ ቁርአን ይዤ ነው  ላማስረዘም ስል ማለት ነው። በጫጭር ሱራዎች  መስገዱ ይሻላል ወይስ ቁርአን እያነበቡ ከመስገድ የቱ ይበልጣል? ጀዛኩሙላህ ኸይረን 16/ዘካል ፊጥራችንን አሰባስበን ወደ ሀገር ልከን ለሚስኪኖች እንድሰጥ እናደርጋለን ግን የምንሰጣቸው ሰዎች ሶላት አብዛኞቹ አይሰግዱም ዘካተል ፊጥር ሶላት ለማይሰግድ አይሰጥም ሲባል ሰማን  እና ምን እናድርግ? 17/አሰሪወቻችን ለኛ ዘካተል ፊጥር ሲሰጡን መቀበል እንላለን ? ~~ 💥 ተጨማሪም የተለያዩ ትምህርቶችን ለማግኜት ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ 🔸🔹🔸🔹🔸🔹 🌐https://telegram.me/ahmedadem ~ 🌐https://t.me/zad_qirat ~~~~ 🔗https://www.facebook.com/yenegew/ ~~~~ 📶  http://www.youtube.com/c/ZadulMaad አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:- 🔅وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ "ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ" ሱረቱል በቀራ /197
Show all...
የተራዊሕና ተሃጁድ አሰጋጆች ሆይ፥ 🔹ለሰዎች የአላህን ቃል ማሰማትና የቁርኣንን መልዕክት ማድረስ መቻል ትልቅ ዕድልና ጸጋ መሆኑን አውቃችሁ በስራችሁ ተደሰቱ፤ ስራን አላህ ዘንድ ዋጋ ከሚያሳጡ ተግባራትና ኒያዎችም ተጠንቀቁ። ♦️ከኋላችሁ ካሉ ሰጋጆች (ደካማ መኽሉቆች) ይልቅ ከፊታችሁ ያለውን ኀያሉን አላህን እያሰባችሁ አሰግዱ። የማንንም አድናቆት አትከጅሉ፣ የማንንም ወቀሳ አትፍሩ። ♦️የቁርኣን ንባብ ላይ ድምጻችሁን ስታሳምሩ ኒያችሁን ቀድማችሁ አሳምሩ። ድምጹ ሲያምር እንዲባልለት ፈልጎ ድምጹን የሚያሳምር ሰው የጀሀነም ማገዶ ይሆናል! ይልቅ የአላህን ቃል ባማረ ድምጽ ቀርቶ ሰዎች ይበልጥ የጌታቸውን ንግግር እንዲሰሙና እንዲመከሩበት ማሰብና መነየት ነው የሚገባው። በቁርኣን ድምጽን በማሳመር ክብርና ዝና መፈለግ፣ ድምጽን የሚያሳምሩትን ያክል ስራና ስነምግባርን አለማሳመር ውጤቱ ነገ አላህ ዘንድ መክሰርና እያደረ ሰዎች ዘንድም ከክብር በኋላ መዋረድ፣ ከመወደድ በኋላ መጠላት ነው የሚሆነው:: ♦️ የምታነቡትን ቁርኣን ተፍሲሩን ለማወቅ ጥረት አድርጉ፤ ሙሉ አቅሙ እንኳ ባይኖራችሁ አጫጭር የተፍሲር መጽሐፍትን አንብቡ፣ በሚገባችሁ ቋንቋ የተዘጋጁ ተፍሲሮችን አዳምጡ። ልብ የሚገሰጸው የሚነበበውን ሲረዳ ነውና። ከኋላችሁ ያሉ ሰጋጆችም ቀድሞ በሚያነበው አንቀጽ ከተገሰጸ ሰው አንደብት የሚወጣ ንባብ ይበልጥ ይገስጻቸዋል። ♦️ቀን ላይ በቂ ዝግጅት ማድረግን በመተው በተደጋጋሚ ትልልቅ ስህተቶችን መሳሳት የተሰጠን አደራ በአግባቡ አለመወጣት ከመሆኑም ባሻገር ሰጋጆች የልብ መረጋጋትን እንዲያጡ ያደርጋል። ይህ እንዳይሆን ቀን ላይ በቂ ዝግጅት አድርጉ። ይህን ከማድረጋችሁም ጋር ቁርኣን አሸናፊ ነውና ከተሳሳታችሁ ቆም ብላችሁ ለሚያርማችሁ ሰው ዕድል ስጡ! መሳሳት ነውር አይደለምና። ይሳሳታል ላለመባል እየጣራችሁና እየደጋገማችሁ ሰዓት አታባክኑ! ♦️አትዋሹ! ሳል ሳይኖር ሲሳሳቱ ማሳልና ያልተሳሳቱ ለመምሰል መሞከር ተገቢ አይደልም! ♦️የሰላትና የአስጋጅነትን ህግጋት ጠንቅቃችሁ እወቁ። ሰላትን የሚያበላሹ ነገሮችን፣ የሰላት መስፈርትና ማዕዘናትን፣ ከኢማም የሚጠበቁ ነገሮችን ሳያውቁ ቁርኣን በቃል ስለሸመደዱ፣ ወይም ጥሩ ድምጽ ስላለ ብቻ ወደ ሚሕራብ መግባት (አሰጋጅ መሆን) ትልቅ ስህተት ነው። ኢማም ከኋላው ተከትለው በሚሰግዱ ሰዎች ሰላት መበላሸት ወይም መጉደል አላህ ዘንድ እንደሚጠየቅ ጠንቅቃችሁ እወቁ። ♦️ሚዛናዊ ሁኑ፤ ሩጫም ይሁን ዝግመት፣ ድምጽ ማነስም ይሁን መብዛት ሳይኖር  (በይነ ዛለኪ) የሆነ አካሄድ ሂዱ። አላህ ያግዛችሁ፤ ስራችሁንም ወዶ ይቀበላችሁ። ✍️ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም ረመዳን 16/ 1445ዓ.ሂ 💥 በተጨማሪም የተለያዩ ትምህርቶችን ለማግኘት   ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ 🔸🔹🔸🔹🔸🔹 🌐https://telegram.me/ahmedadem ~ የኪታብ ደርሶችን ብቻ ለማግኘት 🌐https://t.me/zad_qirat ~~~~ 🔗https://www.facebook.com/yenegew/ ~~~~ 📶  http://www.youtube.com/c/ZadulMaad 📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!" አል-ኢማሙ ማሊክ
Show all...
📮ተራዊሕ በመስገድ ከሚገኙ  ጥቅሞች... 🔹ተራዊሕ የረመዷን ወር ምሽቶች ላይ በጋራም ይሁን በተናጠል የሚሰገድ ነቢዩ صلى الله عليه وسلم እና ሰሓቦቻቸው ያደረጉት ተወዳጅ ዒባዳህ ነው። የተራዊሕ ሰላት በርካታ ጠቀሜታዎችና ምንዳዎችም አሉት፤ ከነዚህም በጥቂቱ:- ① ቀኑን በጾም፣ ሌሊቱን በሰላት በማሳለፋችን ከደጋግ የአላህ ባሪያዎች መሆን ያስችላል። ② ቁርኣን በብዛት በማድመጣችን የአላህን እዝነት እናገኝበታለን። ③ ተራዊሕ በዛ ያለ ሩኩዕና ሱጁድ ስላለበት ሰፊ የዱዓና የዚክር እድል እናገኛለን። ④ ከወንጀልና ከማይጠቅሙ ነገሮች ርቀን ጊዜያችንን በመልካም ስራ እናሳልፋለን። ⑤ ዒባዳህ ላይ መታገስን እንማርበታለን። ⑥ አመቱን ሙሉ ሰላተል-ለይል ለመስገድ ልምምድ እናደርግበታለን። ⑦ በተደጋጋሚ ከኢማምና ከማእሙሞች ጋር "ኣሚን" በማለታችን ወንጀላችን ይማራል። ⑧ መስጂድ ስንሄድና ስንመለስ በእርምጃችን ልክ ወንጀሎች ተራግፈው መልካም ስራዎች ይጻፉልናል። ⑨ ሰላት እየጠበቀን በምናሳልፋቸው ጊዜያቶች መላኢካዎች ምህረት ይጠይቁልናል። ①∅ የሙስሊሞችን ጀማዓ በማብዛት ሸይጣንና አጋዦችን እናስቆጫለን። ①① ከመልካም ሰዎች ጋር በመቀላቀላችን መልካም ስራዎቻችን ወደ ሰማይ እንዲወጡና ተቀባይነት እንዲያገኙ እድል ይፈጥራል። ①② ከአልባሌ ነገሮች ለመራቅና ዲን ላይ ቀጥ ማለት ለሚፈልገው ወጣት መልካም አርዓያና ማበረታቻ እንሆናለን። ①③ ካመኑበትና ጥቅሙን ካወቁት ሁሉም ነገር ቀላልና የሚቻል መሆኑን በተጨባጭ እንረዳበታለን። ①④ ቁርኣንን በብዛት በመስማታችን እንገሰጻለን፤ እንዲሁም የተለያዩ አንቀጾችን በተደጋጋሚ በመስማታችን ትክክለኛውን የቁርኣን አቀራር ለማወቅም ይረዳናል። ①⑤ በቁኑት ዱዓ ወቅት ብዙ እኛ ያላሰብናቸውና መግለጽ የማንችላቸው ነገሮች ዱዓ ተደርጎ "ኣሚን" በማለታችን ትርፋማ እንሆናለን። ①⑥ ከኢማሙ ጋር እስከሰላቱ ፍጻሜ ድረስ አብረን እየሰገድን ከቆየን ሌሊቱን በሙሉ ሲሰግድ ያደረን ሰው እጅር /ምንዳ እናገኛለን። ①⑦ ለሰላት ረጅም ጊዜ መቆማችን የቂያማ ቀን መቆምን ያቀልልናል፤ ዱኒያ ላይ ለጌታው ብሎ ረጅም ሰዓት የቆመ የቂያማ ቀን መቆም አይከብደውምና። ①⑧ ሰግደን ስንመለስ አላህ የሚወደውን ስራ በመስራት የሚገኘውን የውስጥ ደስታና እፎይታ እናገኛለን። 💠ሌሎችንም የዱኒያም የኣኺራህ በርካታ ጥቅሞችን እናገኛልንና ተራዊሕን መቼም አንተው! አላህ ያግራልን። اللهم أعز الإسلام والمسلمين وأذل الشرك والمشركين ووحد صفوفنا وقنا شرور أنفسا يارب العالمين ✍ኡስታዝ አሕመድ ሼኽ ኣደም @ዛዱል መዓድ ረመዷን 1444 ዓ.ሂ 🔸   🔹  🔸  🔹  🔸  🔹 🌐https://telegram.me/ahmedadem
Show all...
🌾የጁሙዓ ኹጥባ በአማርኛ  🌾              ቁ/256 🔆 ከሐራም መጾም (2)      እሁድ ረመዷን 14/1445 ዓ.ሂ 🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም        የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ           ⬇ ⬇ ⬇ ⬇ 🔎  https://tinyurl.com/murmr55t 🔹 🔸 🔹 🔸 🔹 🔸 🌐https://telegram.me/ahmedadem 📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!" አል-ኢማሙ ማሊክ
Show all...
🌴የረመዷን ልዩ  መልዕክት🌴           ቁ/14 🔆የጾም ዓላማ/3 ☄መልካም ስነ-ምግባሮችን መማር        ሀሙስ ረመዷን 9/1445ዓ.ሂ 🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም     የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ          ⬇ ⬇ ⬇ ⬇ 🔎  https://tinyurl.com/2dpyobcz       🔸🔹🔸🔹🔸🔹 🌐https://telegrgam.me/ahmedadem ~~~~ 🔗https://www.facebook.com/yenegew/ ~~~~ 📶  http://www.youtube.com/c/ZadulMaad 📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!" አል-ኢማሙ ማሊክጁ
Show all...
🌳የቁርኣን ተፍሲር🌳           ክ/216 🔹تفسير سورة ق 🔮 የሱረቱል ቃፍ ተፍሲር         ቁ/2 (ከ 16-29)    የዕለተ ጁሙዓ 12/09/1445 ዓ.ሂ          የቁርኣን ትምህርት 🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም     የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ          ⬇ ⬇ ⬇ ⬇ 🔎 https://tinyurl.com/2s48zs83       🔸🔹🔸🔹🔸🔹 🌐https://telegram.me/ahmedadem ~~~~ 🔗https://www.facebook.com/yenegew/j ~~~~l 📶  http://www.youtube.com/c/ZadulMaad 📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!" አል-ኢማሙ ማሊክ
Show all...
🌴የረመዷን ልዩ መልዕክት🌴 ቁ/13 🔆የጾም ዓላማ/2 🔹 የሙስሊሞችን አንድነትና እኩልነት ማስረጽ ሀሙስ ረመዷን 9/1445ዓ.ሂ 🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ ⬇ ⬇ ⬇ ⬇ 🔎 https://tinyurl.com/2xqsruwp 🔸🔹🔸🔹🔸🔹 🌐https://telegrgam.me/ahmedadem ~~~~ 🔗https://www.facebook.com/yenegew/ ~~~~ 📶 http://www.youtube.com/c/ZadulMaad 📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!" አል-ኢማሙ ማሊክጁ
Show all...
ኢብኑ ዐባስ የቁርኣን እና ሸሪዓዊ ትምህርት ማዕከል በአዳማ ከተማ የሚገኝ ሲሆን ከ 2004 ዓ. ል ጀምሮ ቁርኣን እና ሸሪዓዊ ትምህርቶችን እያስተማረ ቆይቷል። ማዕከሉም ያረፈበት ቦታ 100 ካሬ የማይሞላ ቢሆንም ከ200 በላይ ተማሪዎችን እያስተማረበት ይገኛል። ሴቶች ህብረተሰቡ ውስጥ ያላቸውን ወሳኝ ሚና በመገንዘብ በተለየ መልኩ የቁርኣን ሒፍዝ እና ሸሪዓዊ ትምህርቶችን ለእነርሱ በመስጠት በእነዚህ አመታት ውስጥ ጥሩ ስነ ምግባር ያላቸው የቁርኣን እና ሸሪዓዊ ትምህርት ብዙ ሴት አስተማሪዎችን አፍርቷል። ነገር ግን አሁን ያለበት ተጨባጭ መናገር በሚከብድ መልኩ ምስሉ ላይ እንደምንመለከተው ቤቱ ፈራርሶ መማር ማስተማር ላይ አዳጋች ሆኗል። ሰለዚህም አሁን ማዕከሉ ያለበት ቦታ አካባቢ ላይ ለመማር ማስተማር ሂደቱ አመቺ ቦታን በማግኘቱ ይህንንም ቦታ ለመግዛት ከተማው ውሰጥ ባደረገው እንቅስቃሴ ከህብረተሰቡ 9,000,000 ብር ገደማ አግኝቷል። ይሁንና የሚያስፈልገው የብር መጠን 15,000,000 ስለሆነ ለመግዛት በቂ አልሆነለትም። ስለሆነም የተቀረው የብር መጠን ላይ በመረባረብ "ሰደቀተል ጃሪያህ" ላይ በመሳተፍ ማዕከሉ የጀመረውን እንቅሰቃሴ በመደገፍ አስተዋፀኦ እናበርክት ሲል ለመላው ሙስሊም ጥሪውን ያቀርባል።
Show all...
ጾምና ሙቀት 🔅ሙቀት በበረታበት ጊዜ እየተቸገሩ መጾም ምንዳን ከፍ ያደርጋል። ደጋግ የአላህ ባሮች ዱኒያ ላይ መቆየትን እንዲመኙና እንዲወዱ ከሚያደርጉ ነገሮች መካከልም አንዱ ጾም በሚከብድበት ጊዜና ቦታ ላይ ችግሩን ተቋቁሞ መጾም ነው። 🔅አቡ አድ'ደርዳእ رضي اللہ عنہ "በሙቀት ጊዜ (በረሃ ውስጥ) ጥምን ተቋቁሜ መጾም፤ የሌሊት ሰላት ላይ የሚደረግ ሱጁድና እውቀትን አዋቂዎች ዘንድ ተንበርክኮ መማር ባይኖር ኖሮ ዱኒያ ላይ መቆየትን አልፈልግም ነበር" ሲሉ፤ ታላቁ ሰሓቢይ ዓሊይ ኢብኑ አቢ ጣሊብ رضي اللہ عنہ ደግሞ ምን ትመኛለህ ተብለው ሲጠየቁ "በጋ ላይ መጾም፤ በአላህ መንገድ እየታገልኩ ጠላትን በሰይፍ መምታትና እንግዳን በክብር ማስተናገድ " ብለዋል። 🔅ስለዚህ የዘንድሮ ጾም የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ሙቀት በበረታበት ወቅት ላይ መሆኑ ይበልጥ ሊያስደስተን ይገባል። 🔅ከመሆኑም ጋር የሙቀትን ድካም የሚያቀንሱ ነገሮችን ማድረግ ይፈቀዳል። ለምሳሌ፥ በማንኛውም ሰዓት ገላን በቀዝቃዛ ውኃ መታጠብ፣ ፊት እና ጸጉር ላይ ውኃ ማፍሰስ፣ አፍን በውኃ መጉመጥመጥና መልሶ መትፋት፣ ከጸሐይ መሸሽ፣ አናትና ደረት ላይ የረጠበ ፎጣ ማስቀመጥ ወዘተ። 💥 የዱኒያው ቀላል ሙቀት የጀሀነሙን ከባድ ግለት አስታውሷቸው ከርሱ የሚድኑበትን መልካም ስራ ለመስራት ደፋ ቀና ከሚሉ ባሮች አላህ ያድርገን! 🔅ማታ ማታ ተራዊሕ ላይም ሙቀት አልችልም ብሎ ሰላት ትቶ ከመሄድ ይልቅ ታግሶና የጀሀነምን ግለት እያስታወሱ አላህን ከጀሀነም ጠብቀኝ ብሎ መማጸን በላጭና ብልሕነት ነው። ✍ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም ረመዷን 10/1445 ዓ.ሂ @ዛዱል መዓድ   🔹🔸🔹🔸🔹🔸 💥 በተጨማሪም የተለያዩ ትምህርቶችን ለማግኘት   ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ 🔸🔹🔸🔹🔸🔹 🌐https://telegram.me/ahmedadem ~ የኪታብ ደርሶችን ብቻ ለማግኘት 🌐https://t.me/zad_qirat ~~~~ 🔗https://www.facebook.com/yenegew/ ~~~~ 📶  http://www.youtube.com/c/ZadulMaad 📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!" አል-ኢማሙ ማሊክ
Show all...
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!