cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር

مشاركات الإعلانات
2 406
المشتركون
+824 ساعات
+857 أيام
+49330 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Repost from N/a
Photo unavailableShow in Telegram
✳️ የተወለዱበትን ወር በመምረጥ ኮከቦን ይመልከቱ ✳️
إظهار الكل...
❇️ መስከረም ❇️
❇️ ጥቅምት ❇️
❇️ ህዳር ❇️
❇️ ታህሳስ ❇️
❇️ ጥር ❇️
❇️ የካቲት ❇️
❇️ መጋቢት ❇️
❇️ ሚያዝያ ❇️
❇️ ግንቦት ❇️
❇️ ሰኔ ❇️
❇️ ሀምሌ ❇️
❇️ ነሀሴ ❇️
❇️ ጷግሜ ❇️
[ ስንክሳር ሰኔ - ፳፬ - ] .mp37.64 MB
🕊 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ †   እንኳን አደረሳችሁ   † [ †  ሰኔ ፳፬ [ 24 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት † ] 🕊 † ቅዱስ ሙሴ ጸሊም [ ጥቁሩ ሙሴ ] † 🕊 ግብጻውያን ስማቸውን ጠርተው ከማይጠግቧቸው ቅዱሳን መካከል አንዱ ኢትዮዽያዊው አባ ሙሴ ጸሊም ነው:: በእኛ ኢትዮዽያውያን ግን ይቅርና በወርኀዊ በዓሉ [በ፳፬ [24] ] በዓመታዊ በዓሉ እንኩዋ ሲከበር ብዙም አይታይም:: ቅዱሱ ሰው በትውልዱ ኢትዮዽያዊ ሲሆን ያደገውም እዚሁ ሃገራችን ውስጥ እንደሆነ ይታመናል:: ገና በወጣትነቱ አገር የሚያሸብር ሽፍታ ነበር:: ሙሴ ጸሊም ወደ ግብጽ የሔደበት ምክንያት በግልጽ ባይታወቅም መምለክያነ ጣዖት [ፀሐይን ከሚያመልኩ ሰዎች] ጋር ይኖር ስለ ነበር ምናልባት እነርሱ ወስደውት ሊሆን ይችላል:: ቅዱስ ሙሴ በምድረ ግብጽም በኃይለኝነቱ ምክንያት የሚደፍረው አልነበረም:: ፀሐይን ያመልካል: እንደ ፈለገ ቀምቶ ይበላል: ያሻውን ሰው ይደበድባል:: ነገር ግን በኅሊናው ስለ እውነተኛው አምላክ ይመራመር ነበርና አንድ ቀን ፀሐይን "አምላክ ከሆንሽ አናግሪኝ?" አላት:: እርሷ ፍጡር ናትና ዝም አለችው:: ቅዱስ ሙሴ ምንም አስቸጋሪ ሰው ቢሆንም ፈጣሪን መፈለጉን ግን ቀጥሏልና አንድ ቀን ተሳካለት:: መልካም ክርስቲያኖችን አግኝቶ . . . ወደ ገዳመ አስቄጥስ ቢሔድ በዛ ያሉ መነኮሳት ወደ እውነት እንደሚመሩት ነገሩት:: እርሱም ሰይፉን እንደታጠቀ ወደ ገዳም ገባ:: መነኮሳቱ ፈርተውት ሲሸሹ ታላቁ አባ ኤስድሮስ ግን ተቀብለው አሳረፉት:: "ምን ፈለግህ ልጄ?" አሉት:: "እውነተኛውን አምላክ ፊት ለፊት ማየት እፈልጋለሁ" የሙሴ ጸሊም መልስ ነበር:: አባ ኤስድሮስም "የማዝህን ሁሉ ካደረግህ ታየዋለህ" ብለው ወደ መነኮሳት አለቃ ቅዱስ መቃርስ ታላቁ ወሰዱት:: መቃሬም ክርስትናን አስተምረው አጠመቁትና ለአባ ኤስድሮስ መለሱላቸው:: ከዚህ ሰዓት በሁዋላ ነበር የአባ ሙሴ ጸሊም ሕይወት ፍጹም የተለወጠው:: በጻድቁ እጅ ምንኩስናን ተቀብሎ ይጋደል ጀመር:: በጠባቧ በር ይገባ ዘንድ ወዷልና ያ በሽፍትነት የሞላ አካሉን በገድል አረገፈው:: ከቁመቱ በቀር ከአካሉ አልተረፈለትም:: ወገቡን በአጭር ታጥቆ መነኮሳትን አገለገለ:: አጋንንት በቀደመ ሕይወቱ በሕልም: አንዳንዴም በአካል እየመጡ ይፈትኑት ነበር:: እንዳልቻሉት ሲረዱ ተሰብስበው መጥተው በእሳት አለንጋ ገርፈው አቆሳስለውት ሔዱ:: እርሱ ግን ታገሰ:: በበርሃ ለሚኖሩ አበው መነኮሳት ሁሉ ብርሃን በሆነ ሕይወቱ ሞገስ ሆነላቸው:: ለኃጥአን ደግሞ መጽናኛ ሆነ:: "በተራራ ላይ ያለች ሃገር ልትሠወር አይቻላትምና ስም አጠራሩ በመላው ዓለም ተሰማ:: ሁሉም "ሙሴ ጸሊም ይል ጀመር ፡፡" በየበርሃው ያሉ አበው ብቻ ሳይሆነ ዓለማውያን መኩዋንንት ሳይቀሩ ሊያዩት ይመኙ ነበር:: እርሱ ግን ራሱን "አንተ ጥቁር ባሪያ ስለ ኃጢአትህ አልቅስ" እያለ ይገስጽ: ከውዳሴ ከንቱም ይርቅ ነበር:: ከቆይታ በኋላም በመነኮሳት ላይ እረኛ [አበ ምኔት] ሆኖ ተሾመ:: እንደሚገባም አገለገለ:: የበርካቶችን ሕይወት ጨው በሆነ ሕይወቱና ምክሩ አጣፍጦ: ድርሳናትንም ደርሶ እያረጀ ሔደ:: ከቁመቱ መርዘም የጽሕሙ ነጭነትና አወራረዱን ያዩ ሁሉ ሲያዩት ያደንቁት ነበር:: በመጨረሻም በ፫፻፸፭ [375] ዓ/ም በርበረሮች [አሕዛብ] ገዳመ አስቄጥስን ሲያጠፉ ሌሎች መነኮሳት ሸሹ:: እርሱ ግን አልሸሽም ብሎ ከ፯ [7] ደቀ መዛሙርቱ ጋር በዚሕች ቀን ተሰይፎ በሰማዕትነት አልፏል:: ቅዱስ ሙሴ ጸሊምን ለርስቱ ያበቃ ጌታ ለእኛም ዕድሜ ለንስሃ: ለዘመን ለፍስሃን አይንሳን:: ከበረከቱም ፈጣሪው ያድለን:: 🕊 [ †  ሰኔ ፳፬ [ 24 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም [ ኢትዮዽያዊ ] ፪. "፯ቱ [ 7ቱ ] " ቅዱሳን መነኮሳት [ ደቀ መዛሙርቱ ] ፫. አባ ኤስድሮስ ታላቁ [ †  ወርኃዊ በዓላት ] ፩ ፡ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ፪ ፡ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ፫ ፡ ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ ፬ ፡ ቅዱስ አጋቢጦስ ፭ ፡ ቅዱስ አብላርዮስ ፮ ፡ አቡነ ዘዮሐንስ ዘክብራን ፯ ፡ ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ " መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ ዘጠና ዘጠኙን በበርሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሔድ ከእናንተ ማን ነው? ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል:: ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ "የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ" ይላቸዋል:: እላችሁአለሁ: እንዲሁ ንስሃ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሃ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል::" [ሉቃ.፲፭፥፫-፯] (15:3-7) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
إظهار الكل...
[ የእግዚአብሔር ሕግ - ፲፩ - ] .mp311.24 MB
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
                       †                          [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]   🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒                [  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ] [   ሳምንታዊ መርሐ-ግብር   ] 🕊                            ❝ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ፤ ነፍስን ይመልሳል ፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው ፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል። የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው ፥ ልብንም ደስ ያሰኛል ፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው ፥ ዓይንንም ያበራል። ❞ [ መዝ . ፲፱ ፥ ፯  ] ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [ ❝ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ! ❞  ]                [   ክፍል - ፲፩ -  ]           💖   ድንቅ ትምህርት  💖 [ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ] ❝ የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ]          †              †               † ▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬                        👇
إظهار الكل...
Repost from N/a
Photo unavailableShow in Telegram
💔 ️የተወለዱበትን ወር ቶሎ ይምረጡ እና በ Zodiac ሳይንስ ስለራስዎ በደንብ ይወቁ 😍😍😍 የፍቅር ሁኔታዎንም ይጠቁማል 👏 100% ትክክል የሆነ ✅ ➕ Add your channel
إظهار الكل...
💧 መስከረም 💧
🔥 ጥቅምት 🔥
⚡️ ህዳር ⚡️
🌪 ታህሳስ 🌪
☀️ ጥር ☀️
💨 የካቲት 💨
🌦 መጋቢት 🌦
🌧 ሚያዚያ🌧
🌩 ግንቦት 🌩
☔️ ሰኔ ☔️
🌊 ሀምሌ 🌊
☃️ ነሀሴ ☃️
😍 ጷግሜ 😍
Photo unavailableShow in Telegram
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [       ከመንፈሳዊ መጻሕፍት ቅኝት        ] 🔔 [     ል ሳ ን !       ] አንድ ኢትዮጵያዊ ካህን ከባሕር ማዶ ለትምህርት ተልኮ ሳለ ክርስቲያን ነን የሚሉት ነጮች በአንድ አዳራሽ ተሰብስበው እንደ ሀገር ቤቱ ዛር ቤት ሲጯጯሁ ይሰማና የጤና ስላልመሰለው ጠጋ ብሎ ይጠይቃል፡፡ ተጠያቂዎቹም ፦ "መንፈስ ቅዱስ ወርዶላቸው በልሳን እየተናገሩ ነው፡፡" ሲሉ ይመልሳሉ፡፡ ሻሽ ባለመጠምጠሙ ትኩረት ሰጥቶ የሚከታተለው ስለሌለ እስኪ ጉዳቸውን ልይ ከበረታሁም ፈተና አቀርብላቸዋለሁ ብሎ ወደ አዳራሹ ይዘልቃል፡፡ መሪ የለ ተመሪ ከመድረኩ ላይና ከመድረኩ በታች ግማሹ ሽር ሽር እያለ ከፊሉ ምድር ላይ እየተንፈራፈረ ..... ከሰውነት ባህርይና ሥርዓት  ውጪ በሆነ መልኩ ይጯጯሃል፡፡ ኢትዮጵያዊው ካህን አንድ ነገር አሰበ አስቦም አልቀረ ፈጸመው፡፡ ከመዝሙረ ዳዊት ውስጥ መዝሙር አንድን በግእዝ ልሳን ልበለውና መተርጎም አለመተርጎማቸውን ልፈትን ብሎ መድረካቸው ላይ ወጣና ከመዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ አንድ ላይ ወስዶ በቅድሚያ እየደጋገመ ፍካሬ ፍካሬ ፍካሬ! አለ፡፡ ቀጠለና ፦ ፍካሬ ዘጻድቃን ወዘኃጥኣን መዝሙር ዘዳዊት ሃሌ ሉያ ብፁዕ ብእሲ ዘኢሖረ በምክረ ረሲአን ወዘኢቆመ ውስተ ፍኖተ ኃጥኣን ...... እያለ እስከ ፍጻሜው ዘለቀውና ሲጨርስ ቀጥ ብሎ ቆመ፡፡ የመድረኩ መሪ ጮሌ ፈረንጅ ሮጦ መጣና ለአዳራሹ ህዝብ ፦ "ሃሌ ሉያ ጌታ የተመሰገነ ይሁን" ብሎ ካስጮሃቸው በኋላ "ትርጉሙን ስሙ" አለና ይተረጉም ጀመር፡፡ እንዲህ ሲል ፦ "እኔ አንድ ጥቁር አፍሪካዊ በነጮች መካከል ተገኝቼ ጌታን በመቀበሌና በልሳን በመናገሬ እጅግ በጣም ተደስቻለሁ፡፡ ይላል" ብሎ ተረጎመው፡፡ አዳራሹ በጩኸትና በጭብጨባ አስተጋባ፡፡ ይኼኔ ኢትዮጽያዊው ቄስ አዝኖ ተሳልቆባቸው ወጥቶ ሄደ፡፡ 🔔 ወገኖቼ በዚህ አይነት የማታለያ ድርጊት የጠፉ ወገኖቻችን ብዙ ናቸው፡፡ ለእነዚህ ነፍሳት መጥፋት ተጠያቂዎቹ ደግሞ አይታወቅብንም ብለው ባፈጠጠ ውሸት በሃይማኖት ስም በሕዝባችን ላይ የሚጫወቱት ጊዜ የሰጣቸው መናፍቃን ናቸው፡፡ መንፈስ ቅዱስ የእውነት መንፈስ ነው፡፡ መንፈስ ተሞላን እያሉ መዋሸት ፣ አረፋ እስኪደፍቁ መንፈራገጥ ፣ ቅዱሳንን መንቀፍና መሳደብ የነዚህ የመናፈቃን ተግባር ነው፡፡ ከእኛ ዘንድ ከቶ ይራቅ፡፡ ይልቁንም የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እንዲህ ያስታውሰናል ፦ "ወዳጆች ሆይ! መንፈስን [ መምህራንን ] ሁሉ አትመኑ ነገር ግን መናፍስት [ መምህራን ] ከእግዚአብሔር ሆነው እንደሆነ መርምሩ፡፡ [ ፩ኛ ዮሐ.፵፩ ] [ ምጥን ቅመም ዲ/ን ምትኩ አበራ ] 💖 " ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ። ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል ፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል። " [ መዝ . ፩ ፥ ፩ ] ይቆየን ! †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.