cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

AbuTolhaAhmedmusa

ከቻናሉ ይቀላቀሉ በአላህ ፍቃድ ጠቃሚነጥቦችንያገኛሉ ⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️ https://t.me/joinchat/SBf-mUs1ixjO31Gc ”ሙብተዲዕ (መጀመሪያ) ቤቱን ከውስጥ ያበላሻል። ከዛም ለጠላት በሩን ከፍቶ ግባ ይለዋል” ሸይኽ ረቢዕ ቢን ሃዲ አልመድኸሊ [المجموع صـ (።

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
425
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
+430 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

👉  ሺዓዎችና ዓሹራእ     ዓሹራእ ሲታወስ በዋነኝነት የሚታወሰው የሑሰይን ኢብኑ ዐልይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ ከርበላእ ላይ መገደል ነው ። ሑሰይን ከርበላእ ላይ የተገደለው ሙሐረም 10/61ኛው አመተ ሂጅሪያ ላይ ነበር ።     የሑሴይን መገደል መንስኤ የነበረው ለየዚድ ኢብኑ ሙዓዊያ ኢብኑ አቡ ሱፍያን ሙባየዓ አላደርግም ማለቱ ነበር ። በኢስላም ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው የሐሰን ኢብኑ ዐልይ ለሙዓዊያ የመሪነቱን ቦታ መልቀቁ ( ተናዙል )  ማድረጉ ነው ። ዑስማን ኢብኑ ዐፋን በዐብዱላሂ ኢብኑ ሰበእ አል የሁዲይ የተንኮል መረብ ከተገደለ በኋላ ዐልይ የኸሊፋነቱን ቦታ በሶሓቦች ግፊትና ውትወታ ተረክቦ ሁኔታዎችን ለማረጋጋት እየሰራ ባለበት ወቅት ሙዓዊያ የሻም ዋሊ ( አስተዳደር ) ነበርና ለዐልይ የዑስማን ገዳዮች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጥያቄ ያቀርባል ። ዐልይም መጀመሪያ ሙባየዓ ማድረግ እንዳለበትና ሁኔታዎች ከተረጋጉና ገዳዮቹ በህዝብ ውስጥ ተደብቀው ስላሉ መለየት በሚቻልበት ወቅት ለፍርድ እንደሚቀርቡ ይገልፅለታል ። ሙዓዊያም ምናልባት መዲና ያለው ሁኔታ ካልተረጋጋና አቅም ከሌለው ሀላፊነቱን ለሱ እንዲሰጠውና እሱ ገዳዮቹን ለፍርድ ሊያቀርብ በሚችልበት አቅምና አቋም ላይ መሆኑን በመግለፅ ይህ ሳይሆን ሙባየዓ እንደማያደርግ ለዐልይ ያሳውቃል ። ይህ አለመግባባት ሳይፈታ ዐልይ ኢብኑ አቢጧሊብ ዐብዱራሕማን ኢብኑ ሙልጂም በሚባል ኻሪጂ ይገደላል ። በቦታው ሐሰን ኢብኑ ዐልይ ሙባየዓ ተደረገለት ኸሊፋም ሆነ ።  ነገር ግን ከሙዓዊያ ጋር የነበረው አለመግባባት በቀላሉ የሚፈታ አልነበረምና ሐሰን ለሙዓዊያ መሪነቱን አስረከበ ።      ይህ የሐሰን ተግባር ለሑሰይን አላስደሰተውም ። ነገር ግን ታላቁ ነውና ምንም ማድረግ አልቻለም ለሙዓዊያ ሙባየዓ አደረግ ። በዚህም ሀገር ሰላም ሆነ ሙስሊሞች ኡፈይ አሉ ። በዚህ ሁኔታ ነገሮች እየሄዱ እያሉ ሙዓዊያ መሪነቱን ለልጁ የዚድ አሳልፎ ሰጠ ። የዊላያት መሪዎችና የጦር አዛዦች እንዲሁም ታዋቂ ሶሓባዎች ለልጁ ሙባየዓ እንዲያደርጉ ጠየቀ ። ሑሰይን ኢብኑ ዐልይ ለየዚድ ሙባየዓ እንደማያደርግ ግልፅ አደረገ ። በዚህን ጊዜ የዚድ ለመዲናው አስተዳዳሪ ከሑሰይን ሙባየዓ እንዲቀበልለት ትእዛዝ አስተላለፈ ። ሑሰይንም ሁኔታው ስላላማረው መዲናን ትቶ ወደ መካ ተሰደደ ። የዚህን ጊዜ ኢራቅ ያሉ የሙዓዊያ ተቋዋሚ ፋርሳዊያን ( ሺዓዎች ) ሑሰይንን ወደ እነርሱ እንዲመጣና መሪያቸው እንዲሆን መወትወት ጀመሩ ። ሑሰይንም ለመውጣት አሰበ የኩፋ ሰዎች በየቀኑ ወደ ሑሰይን ይልካሉ ። ይህ ሁኔታ ያላማረው የዚድ የሑሰይንን እንቅስቃሴ መከታተል ጀመረ ።     ሑሰይንም የአጎቱን ልጅ ሙስሊም ኢብኑ ዓቂልን ወደ ኩፋ ሄዶ ነገሮችን እንዲያጣራ ላከው ። ሙስሊም ኩፋ እንደደረሰ በጣም ጥሩ አቀባበል ተደረገለት ለሑሰይን ሙባየዓ አደረጉ ። የዚህን ጊዜ ለሑሰይን መምጣት እንዳለበትና ሙባየዓ እንደተደረገለት ገልፆ ላከለት ።      የዚድ የሙስሊም ኢብኑ ዐቂል ኩፋ መግባትና ሰዎች ( ሺዓዎች ) ለሑሰይን ሙባየዓ እያደረጉ መሆኑን በሰማ ጊዜ ዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድን የበስራና የኩፋ መሪ አድርጎ በመሾም ወደ ኩፋ እንዲሄድና የሆነውን ነገር አጣርቶ እርምጃ እንዲወስድ ላከው ። ወደ መዲናና መካ የሚገኙ ትላልቅ ሶሓቦችም ሑሰይንን ወደ ኩፋ እንዳይወጣ እንዲመክሩትና ሙባየዓ እንዲያደርግ እንዲነግሩት መልእክት ላከ ።     ዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድ ወደ ኩፋ እንደመጣ ለወታደሮች በጣም ከፍተኛ ስጦታ ሰጠ ። ታዋቂ ሰዎችን አስጠርቶ ከሱ ጋር እንዲሆኑ የፈለጉት ነገር እንደሚያደርግላቸው ካልሆነ ግን አይቀጡ ቅጣት እንደሚቀጣቸው ገለፀላቸው ። ማንኛውም ሰው አዲስ ሰው እንዳያስጠጋ አስጠግቶ የተገኘ እርምጃ እንደሚወስድበት ተናገረ ። ቀጥሎ በስራና ኩፋ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ አዘዘ ። ማንኛውም አዲስ ሰው ከተገኘ ወደርሱ እንዲቀርብ ትእዛዝ ሰጠ ። ቀጥሎ አሉ የተባሉ ታዋቂ ሰዎችን በተለያየ ጥቅማጥቅም በመያዝ ሙስሊም ኢብኑ ዐቂል ያለበት እንዲያደርሱትና ከሱ ጎን የቆሙ ሰዎችን እንዲለዩለት አደረገ ።    ወዲያውኑ ሙስሊም ኢብኑ ዐቂል ያለበት ቦታ ጦቀሙት ። ወደ ሙስሊም ኢብኑ ዐቂል ጉዞ ቀጠለ ደረሰበትም ። ሙስሊም ኢብኑ ዐቂል የተከሰተው ነገር ሲያይ ማመን አቃተው እነዚያ ቃል የገቡና ሑሰይንን እንዲያስመጣ ያዘዙት ሺዓዎች ክደውታል ። ዑበይዱላህ እጅ እንዲሰጥ ጠየቀው አላደረገውም ተገደለ ። የሚቀጥለው ስራ የሑሰይንን መምጣት መጠበቅ ነው ። በተለያዩ መንገዶች ጠባቂ አደረገ ። ስለሙስሊም መገደል እንዳይደርሰው አደረገ ።     ሑሰይን ከመካ ወደ ኩፋ እንቅስቃሴ ጀመረ ። ትላልቅ ሶሓቦች እንዳይሄድ ከለከሉት ። ከእነዚህ ውስጥ : – – ዐብዱላሂ ኢብኑ ዐባስ – ዐብዱላሂ ኢብኑ ዑመር – ጃቢር ኢብኑ ዐብዱላሂ – ዐብዱላሂ ኢብኑ ዙበይር – አቡ ሰዒድ አል ኹድርይ     እና ሌሎችም ግን አልተሳካም ።     የሑሰይን መንቀሳቀስ ተሰማ ዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድ 1000 ፈረሰኛ እሱን ለመጠባበቅ ላከ ። ሌላ ጦር ደግሞ ዑመር ኢብኑ ሰዕድን መሪ አድርጎ ላከ ። ለዚህ ጦር እጅ ከሰጠ ይዘው እንዲያቀርቡት ካልሆነ እንዲገሉት ትእዛዝ ሰጠ ። ሑሰይን ወደ ኩፋ በቀረበ ጊዜ የአጎቱ ልጅ መገደል ፣ የኩፋ ሰዎች ከዑበይዱላህ ኢብኑ የዚድ ጎን መቆማቸውንና የአጎቱን ልጅና እሱንም እንደካዱዋቸው የሙስሊም ኢብኑ ዑቅባ ደጋፊዎች ሀኒእ ኢብኑ ዑርዋን ጨምሮ ሁሉም መገደላቸውን ሰማ ። ብዙም ሳይቆይ ከዑመር ኢብኑ ሰዕድ ጦር ጋር ተገናኘ ። እነዚያ ወትውተው ከመካ ያስወጡት ሺዓዎች አዘጋጅተው ለጅብ ሰጥተውታል ።      የዚህን ጊዜ ከሱ ጋር ያሉትን ማስጨረስ አልፈለገም ሙሉ በሙሉ ሀሳቡን ቀይሮ ሶስት አማራጭ ለዑመር ኢብኑ ሰዕድ አቀረበለት ። አማራጮቹ የሚከተሉት ነበሩ : – – እንዲተውትና ወደ መካ እንዲመለስ – ወደ ድንበር ሄዶ እንደማንኛውም ሙስሊም ድንበር እንዲጠብቅ ( ሀገር ጠባቂ ወታደር እንዲሆን ) – ወደ ሻም ሄዶ ከየዚድ ጋር ተነጋግሮ እንዲግባባ የሚል ነበር ።      ዑመር ይህን ሲሰማ በጣም ደስ ብሎት ለዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድ ላከለት ። ይሁን እንጂ በሙስሊሞች ደም የሚታጠበው ዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድ እጅ ካልሰጠ እንዲገድለው አዘዘ ። ዑመር ለሑሰይን እጅ እንዲሰጥ ጠየቀው ሑሰይንም አይደረግም አለ ። በሙሐረም 10 ኛ ቀን በ61ኛው አመተ ሂጅሪያ ሺዓዎች ከመካ መሪያችን ሁን ብለው አውጥተው ከርበላእ ላይ እንዲገደል አደረጉት ።     ይህን ቀን ነው ሺዓዎች ከርበላእ ላይ ራቁታቸውን ሆነው ራሳቸው እየገረፉ ለሑሰይን ሞት ሐዘን እያሉ  ያ ሑሰይን ብለው የሚጮኹት ።       https://t.me/bahruteka
إظهار الكل...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

👉 ዓሹራእና ምንዳውዓሹራእ ማለት የሙሐረም ወር 10ኛ ቀን ሲሆን ከነብዩላሂ ሙሳ አስገራሚ ታሪኮች አንዱን የሚያስታውሰን ቀን ነው። ➧ ነብዩላሂ ሙሳ ፊርዓውን ህፃናቶችን በሚያርድበት ዘመን ተወልደው በራሱ ቤት እንዲያድጉ አላህ ያሻውን ሰሪ የሆነው ጌታ አደረገ። ይህም ፊርዓውን በይተል መቅዲስ አካባቢ የተነሳ እሳት የግብፅን ምድር ሲያጠፋ በህልሙ ያይና ለጠንቋዮቹና ድግምተኞቹ ሲነግራቸው ከእስራኤላዊያን የሚወለድ ህፃን የንግስናው  መጥፊያ ሰበብ እንደሚሆን ነግሩት። ፊርዓውንም ከሚወለዱት ህፃናት ሴቶቹ ቀርተው ወንዶቹ እንዲታረዱ አዘዘ።ይህ ነገር አገልጋይ እንዳያሳጣቸው የፈሩት ግብፃዊያን ፊርዓው ዘንድ ሄደው አቤቱታ ሲያቀርቡ አንድ አመት የሚወለደው ተትቶ በሌላኛው አመት የሚወለደው እንዲታረድ አዘዘ። የአላህ ፍላጎት ሆነና ነብዩላሂ ሙሳ ወንድ ህፃናቶች በሚታረዱበት አመት ተወለዱ። የእስራኢላዊያን ህፃናት መወለድ የሚጠባበቁ ሰራዊቶች በመኖራቸው የነብዩላሂ ሙሳ እናት ጊዜዋ በመድረሱና አመቱ ወንድ ህፃናት የሚታረዱበት በመሆኑ ጭንቅ ውስጥ ገባች። የተፈራው አልቀረም ህፃኑ ተወለደ። እናት ምን ይዋጣት!!!? ↪️ አላህ ሁሉን ቻይ መሆኑን ሊያሳያት በሳጥን አድርገሽ ወደ ቀይ ባህር ወርውሪው የሚል መልእክት እንዲመጣላት አደረገ። ወረወረችውም። ወደ አላህም ፍፁም ተማፀነች። አላህም ልጇን እንደሚመልስላት ቃል ገባላት። ባህሩ ሳጥኑን ወደ ፊርዓውን ቤተመንግስት እየነዳ አደረሰው። የፊርዓው አገልጋይ ሴቶች ሳጥኑን አገኙት ሲከፍቱት የሚያምር ህፃን ነው!!!። ወደ ቤተመንግስት ተወሰደ። ኣሲያ የፊርዓው ባለቤት የአይናችን ማረፊያ ይሆናል ልጅ አድርገን እንያዘው አትግደለው አለችው ተቀበላት።     ➲ ረሃብ ይዞት ሲያለቅስ የሚቀርብለት ጡት በሙሉ እንቢ አለ። ምናልባት የሚስማማው ጡት ከተገኘ ብለው ሴቶችን ሲፈለጉ እህታቸው ማንነቷን ደብቃ አንድ ህፃናት በሙሉ ጡቷን የሚጠቡላት ሴት ላመላክታችሁ ወይ ብላ ጠየቀች አው አሉ። እናታቸው ወደ ቤተመንግስት መጣች!!!። ሱብሃናላህ በፊርዓውን ቤተመንግስት በእሱ ተንከባካቢነት በእናታቸው ጡት እንዲያድጉ አላህ አደረገ። በወቅቱ እስራኤላዊያን በቂብጦች የመከራ ገፈት ይጎነጩ ነበር። አላህ በሙሐረም 10ኛ ቀን ፊርዓውንን ከነሰራዊቱ አጥፍቶ እሳቸውንና ህዝቦቻቸውን ነጃ አወጣ። የአላህ መልእክተኛ ነብዩ ሙሐመድ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም – ወደ መዲና ሲሄዱ አይሁዶች ይህን ቀን ሲፆሙ አገኙዋቸው። ለምንድነው የምትፆሙት ብለው ሲጠይቁዋቸው ይህ ቀንማ አላህ ፊርዓውን አጥፍቶ ሙሳን ያዳነበት ቀን ነው። ለዚህ ነው የምንፆመው አሉዋቸው። እሳቸውም ለሙሳማ እኔ ከናንተ የቀረብኩኝ ነኝ ብለው መፆም ጀመሩ ተከታዮቻቸውንም እንዲፆሙ አዘዙ። ያለውንም ምንዳ ሲናገሩ እንዲህ አሉ:– "صِيَامُ يَوْمِ عَرَفَةَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ وَالسَّنَةَ الَّتِي بَعْدَهُ وَصِيَامُ يَوْمِ عَاشُورَاءَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ"     رواه مسلم   ( 1162). "የዓረፋ ቀንን መፆም ያለፈውንና የሚመጣውን አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። የዓሹራእ ቀንን መፆም ደግሞ ያለፈውን አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።" ♻️ አዩዶችን ለመኻለፍ አላህ ካቆየኝ የሚመጣውን አመት ዘጠነኛውን የሙሐረም ቀን እፆማለሁ ብለው ነበር። ከዚህ በመነሳት የሙሐረምን ዘጠነኛና አስረኛ ቀን መፆም ይወደዳል። አብዛኛዎች ፉቀሃዎች ዘጠነኛ አስረኛና አስራ አንደኛውን ቀን መፆም ሱና ነው ይላሉ። ነገር ግን ከመረጃ አንፃር ዘጠነኛና አስረኛው ነው። ይህ ካልተቻለ አስረኛና አስራ አንደኛውን በመፆም አይሁዶችን መኻለፍ ይቻላል።         አላህ ይወፍቀን። ከተወሰነ ማስተካከያ ጋር በድጋሚ የተለቀቀ። http://t.me/bahruteka
إظهار الكل...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

ካሚል ሸምሱ፣ ኢልያስ አህመድ እና ሳዳት ከማል ============> ↪️ ❝ ተመዩዕ ዳር የሌለው ባህር ነው ! ❞ ↩️ ❞ التمييع بحر لا ساحل له! ❝ ♻️ የተመይዕ ቢድዓ ልክ ዳር እንደሌለው ባህር ነው ከገባህበት በኋላ ለመውጣት ብትሞክር አትችልም ምክንያቱም ባህሩ ዳርቻ የለውምና። ወደ ተመዩዕ Ideology የተነከሩ ሰዎች በቆዩ ቁጥር ባህሩን ያንቦጫርቃሉንጂ አይሻሻሉም። ➲ ከታች በቅደም ተከተል የምንጠቅሳቸው ሰዎች በተለዬ እርከን የሚገኙና የተለያዩ ስህተቶችን የሚፈፅሙ ናቸው። እንመልከት፦ ❶ኛ 🎙 ካሚል ሸምሱ፦ ➲ ❝ሱፊይ ሰለፍይ የሚለው በእስልምና አስተምህሮት ጥንት ያልነበረ አሁን የመጣ ቢሆንም ሱፍይ ነን ከሚለው ቡድንም በፊደራልም በአድስ አበባም በተለያዩ ክልል መጅሊሶችም የተካተቱበት የተወከሉበትም ተጨባጭ ነው ያለው።❞ ➘➴➘ ማዳመጥ ይችላሉ https://t.me/AbuImranAselefy/7523 ✅ መልስ፦ እጅግ በጣም ሰቅጣጭ ሀሳብ ነው። እንደት ሰው «...ሰለፍይ የሚለው በእስልምና አስተምህሮት ጥንት ያልነበረ አሁን የመጣ ቢሆንም...» ብሎ በድፍረት ይናገራል!? በእርግጥ ኢኽዋንዮች ምንም ለማለት የማይጨንቃቸው በተለያዩ አጋጣሚዎች የሻቸውን የሚናገሩ ሸይኽ እንዳሻዎች መሆናቸውን በደንብ እናውቃለን። ቢሆንም ግን እንዲህ አይነት ግልፅ ጥፋት እንግዳ ሊሆን ይችላል። ካሚል ሸምሱ ሰለፍይ ስለሚለው ፅንፀ-ሀሳብ ምንም አይነት ግንዛቤ እንደሌለው መገንዘብ ይቻላል። ለመሆኑ ሰለፍይ ማለት የሰለፎች (የደጋግ ቀደምቶች) ተከታይ አይደለምን!? ሰሃቦችን እና እነሱን በመልካም የተከተሉትን መከተል አይደለምን!? ነውንጂ ወሏህ وَالسَّابِقُونَ الْأَوَّلُونَ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ وَالْأَنصَارِ وَالَّذِينَ اتَّبَعُوهُم بِإِحْسَانٍ رَّضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ وَأَعَدَّ لَهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي تَحْتَهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا ۚ ذَٰلِكَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ ከስደተኞቹና ከረዳቶቹም ሲኾኑ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸው አላህ ከእነሱ ወዷል ከእርሱም ወደዋል፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲኾኑ ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ ይህ ታላቅ ዕድል ነው፡፡   [ሱረቱ አል-ተውባህ - 100] ♻️ ሰለፍያን መጤ ማለት ከባድ አደጋ እንደሆነ ብንገነዘብ ኖሮ ምን ያክል በጨነቀን ነበር። ለማንኛውም ይህ ለሱና ሰዎች ግልፅ ስለሆነ መደጋገም አልፈልግም። ካሚል ቀጥሎ እንዲህ ይላል፦ ➲ ❝አሁን ያለው መጅሊስ መውሊድን ኮሚቴ አዋቅሮለት በጀት በጅቶለት መውሊድ እንዲከበር እያደረገ ያለ መጅሊስ ነው።❞ ✅ መልስ፦ አዎ እንዲህ ሰዎች ማንነቱን እንዲገነዘቡ በዚህ መልኩ መናገሩ ጥሩ ነው። ለመውሊድ ይሄን ያክል ቦታ ከሰጡ የታለ ቢድዓን መቃወም እ? መጅሊሱን አስተካክለናል የሚሉት ሰወችስ ምን እየሰሩ ነው!? ❷ኛ 🎙 ኢልያስ አህመድ፦ ➲ ❝ይህ (መጅሊስ) የተለያዩ አመለካከት ያሏቸው ከተለያዩ background የመጡ ስብስቦች በአንድ ... የሚመሰርቱት ህብረት ነው❞ ✅ ማዝገንዘቢያ፦ ኢልያስ እንዳለው መጅሊስ የተለያዩ ሰዎች ስብስብ ነው። በህብረቱ ድብን ያሉ ከባባድ ልዩነቶች ያሏቸው አካላት የተጠራቀሙበት ነው። በዚህ መጅሊስ የተለያዩ የቢድዓ ባለቤቶች ተከማችተዋል። ከንግግሩ እንደምንገነዘበው እነዚህ የቢድዓ ሰዎች በጋራ እየሰሩ ነው። ታዲያ የሱና ሰው ነኝ የሚል አካል እንደት ከነዚህ አጥፊዎች ጋር በጋር ለአመታት ይቀጥላል!? የባሰው ደግሞ ከነዚህ የጥፋት አካላት ጋር በመሆን የሀቅ ሰዎችን መዋጋት ነው። 🎞 ቀጥሎም የሚከለክለውን መልዕክት ያዘለ ንግግር ያስተላልፋል፦ ➲ ❝ሌሎችን የምንገፋ ከሆነ ለሌሎች እውቅና የማንሰጥ ከሆነ....❞ ✅ ጉድኮ ነው! አሉ በኢልያስ ሙግት ከሆነ ሌሎች መገፋት የለባቸውም እውቅና መሰጠት አለበት ማለት ነው። አይይይ ሰው አውቆ ያላወቁትን ያህል ሲያጠፋ ይሰቀጥጣል። እርግጥ ነው ሰዎች ከንግግሩ የሚረዱት በዚህ መልኩ የተናገረው ለሆነ አላማ ሲባል ነው በማለት ነው። አላማውም መጅሊስ ገብቶ አንዳንድ ጥቅሞችን ማስገኘት ነው በማለት ይሞግታሉ! ⁉️ የኛ ጥያቄ የታለ ጥቅሙ? ⁉️ ለመውሊድ ከተበጀተ ሰለፍያ ልክ እንደሱፍያ መጤ ከተደረገ የታለ ጥቅሙ!? ⁉️ የሚገኘው ጥቅም በግልፅ የሚታየው መች ነው!? ⁉️ የአሁኑ መጅሊስ ከድሮው በምን ይለያል!? እንደውም እነ ኡመር ገነቴ ሰለፍይ ነኝ ያላለ ይከፍራል አሉንጅ ሰለፍያህ መጤ ነው አላሉም። ትክክለኛውን ሱና የፈለገ ይፁምንጅ እየበላ እየጠጣ መውሊድ ማክበር የለበትም ነው ያሉት! የነኢልያስ ካሚሎች ግን ለመውሊድ አብይ ኮሚቴና ከመጅሊሱ በጀት አውጥተው ይደግሱና በድፍረት ተግባራቸውን ይነግሩናል። የታለ የድሮውና የአሁኑ መጅሊስ ልዩነት!??? ❸ኛ 🎙 ሳዳት ከማል፦ ➲ ❝የመጅሊሱ ሰዎች ከእኛ በእድሜ የጠገቡ ናቸው❞ ✅ መልስ፦ ሳዳት ከማል ከተመዩዕ በሽታ በፊት የመጅሊስ ሰዎችን ጥፋቶች እየለቃቀመ ማስተካከያ ያደርግ ነበር። ያኔ ጥፋታቸውንጅ እድሚያቸው አልታየውም ነበር። በጥፋታቸው ሙስሊሙን የሚጎዱ እንጂ ጥቅማቸው አልተገለፀለትም ነበር። ምክንያቱም ያኔ በሹብሃ ሳይበከል በንፁህ አስተሳሰብ ላይ ነበር። ሰው ካጠፋ ትልቅ ነው ጠቃሚ ነው ወዘተ እየተባለ ጥፋቱ አይሸፍንም። መነገር ባለበት ልክ መነገር አለበት። ግን ሳዳት ዳርቻ ወደሌለው የተመዩዕ ባህር ከሰመጠ በኋላ ሀሳቡን ቀየረ። እንዲህም ይላል፦ ➲ ❝እንዳንተ ልጅ አይደሉም ጅል አይደሉም፤ ልጅና ጅል ቶሎ አይበስልም❞ ✅ መልስ፦ በዚህ ንግግሩ ምክንያት አንድ ድምፅ ትዝ አለኝ። ዶክተር ጀይላን በአንድ ወቅት ስለነሳዳትና መሰሎቹ እንዲህ ብሎ ነበር «ተዋቸው ልጅ ስለሆኑ ነው ይመለሳሉ ታገሱ» በማለት እስኪበስሉ ጠብቁ ብሎ ነበር እናም ዛሬ ሳዳት በስለናል እያለ መሆኑ ነው። አይ ጨዋታ ጉድ! ➲ ❝ስትሸብት መብት እያለህ እንደሌለህ ሆነህ መንግስት ቤት ሆነህ ትለምናለህ። ፈሪነት ግን አይደለም።❞ ✅ መልስ፦ ስንትና ስንት ሰዎች ሸብተው ሀይማኖታችንን ለመበረዝ ጥረት ያደርጋሉ። ተፈላጊው ነገር በትክክለኛው መንገድ መሆን እንጂ መሸበት አይደለም። ሳጠቃልል ♻️ እነዚህ ሰዎች ተሳስረው እየተጓዙ ነው። ከመንጫጫታችሁ በፊት ነገሮችን ለአላህ ብላችሁ ለማስተዋል ሞክሩ! እነ ኢልያስም ሆነ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ እነሳዳትም በኢክዋኖች ላይ ደራርበው ተኝተዋል። ይህ የሚካድ አይደለም። በዚህ አመት ብቻ የሀገራችን ኢኽዋኖች ስንቱን ቀባጠሩት ማነው ትንፍሽ ያለው!? የሳዳት ወዳጆች ረድ የምትመስል ነገር ካገኙ ይሄው ረድ አደረገ ይሄው ዝም አላለም በማለት ይንጫጫሉ። ይህ የሚያሳየው ረዱ ብርቅ ሆኖባቸዋል። በቃ እንደበፊቱ አይደለም። ወደድክም/ሽም ጠላህም/ሽም 📝 ➷➘➴ https://t.me/AbuImranAselefy
إظهار الكل...
Abu Imran Muhammed Mekonn

ካሚል ሸምሱ፣ ኢልያስ አህመድ እና ሳዳት ከማል ============> 🎙 ካሚል ሸምሱ፦ ➲ ❝ሱፊ ነን የሚሉት በፊደራልም በአድስ አበባም በተለያዩ ክልል መጅሊሶችም እንዲካተት አድርገናል።❞ ➲ ❝አሁን ያለው መጅሊስ መውሊድን ኮሚቴ አዋቅሮለት በጀት በጅቶለት መውሊድ እንዲከበር እያደረገ ያለ መጅሊስ ነው።❞ 🎙 ኢልያስ አህመድ፦ ➲ ❝ይህ (መጅሊስ) የተለያዩ አመለካከት ያሏቸው ከተለያዩ background የመጡ ስብስቦች በአንድ ... የሚመሰርቱት ህብረት ነው❞ ➲ ❝ሌሎችን የምንገፋ ከሆነ ለሌሎች እውቅና የማንሰጥ ከሆነ....❞ 🎙 ሳዳት ከማል፦ ➲ ❝የመጅሊሱ ሰዎች ከእኛ በእድሜ የጠገቡ ናቸው❞ ➲ ❝እንዳንተ ልጅ አይደሉም ጅል አይደሉም፤ ልጅና ጅል ቶሎ አይበስልም❞ ➲ ❝ስትሸብት መብት እያለህ እንደሌለህ ሆነህ መንግስት ቤት ሆነህ ትለምናለህ።❞ ጊዜ ሳገኝ በማብራሪያ እመለሳለሁ 📝 ➷➘➴ ጠብቁኝ!!!

https://t.me/AbuImranAselefy

የጁሙዓ ኹጥባ (ምክር) ርዕስ" ሃራምና ሃላል ግልፅ ነው 🎤በሸይኽ ሙሐመድ ሃያት [ሃፊዘሁሏህ] https://t.me/SheikMohmmedHyatHara 🕌 መስጅደ ሶፋ ሃራ ውላጋ ሐምሌ ቀን /05/2016/የጁሙዓ/ምክር https://t.me/hussenhas
إظهار الكل...
የጁሙአ_ኹጥባ_በሸይኽ_ሙሀመድ_ሀመያት_.mp36.03 MB
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ، عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ : " إِنَّ اللَّهَ تَعَالَى يَقُولُ : يَا ابْنَ آدَمَ، تَفَرَّغْ لِعِبَادَتِي أَمْلَأْ صَدْرَكَ غِنًى، وَأَسُدَّ فَقْرَكَ، وَإِلَّا تَفْعَلْ مَلَأْتُ يَدَيْكَ شُغْلًا، وَلَمْ أَسُدَّ فَقْرَكَ ". رواه الترمذي (2466) و ابن ماجه (4107) واحمد (8696) https://t.me/AbuToIhaAhmedmusa
إظهار الكل...
AbuTolhaAhmedmusa

ከቻናሉ ይቀላቀሉ በአላህ ፍቃድ ጠቃሚነጥቦችንያገኛሉ ⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️

https://t.me/joinchat/SBf-mUs1ixjO31Gc

”ሙብተዲዕ (መጀመሪያ) ቤቱን ከውስጥ ያበላሻል። ከዛም ለጠላት በሩን ከፍቶ ግባ ይለዋል” ሸይኽ ረቢዕ ቢን ሃዲ አልመድኸሊ [المجموع صـ (።

👉 ታላቅ ቡሽራ ለኩቱቡ ሲታ ቂራኣት ፈላጊዮች ለሰሜን ወሎና አካባቢዋ ጧሊበል ዒልሞች ልዩ የምስራች ። ኩቱቡ ሲታ ፣ ሙስጠለሐል ሐዲስ ፣ ተፍሲር ፣ ነሕውና ሰርፍ በሰለፍይ ዑለሞች ። የማይታመን እድል ነው የት አላችሁ ተጠቃሚዮች ተሽቀዳደሙ ። https://t.me/bahruteka
إظهار الكل...
ታላቅ ቡሽራ ለኩቱቡ ሲታ-WPS Office.docx0.10 KB
👉 የኒቃብ ጥላቻ በሽታ ሲሆን የታሪክ መዛግብቶች እንደ ሚያስነብቡት የአላህ መልእክተኛ ከመላካቸው በፊት አዩሁዶችና ነሳራዎች ( ክርስቲያኖች ) ዘንድ ኒቃብ የንፁህነትና የክብር ራስን የመጠበቂያ ምልክት እንደነበር ነው ። በዛን ዘመን አንድ ክብሯን የምትጠብቅና ከፀያፍ ተግባር ለመራቅ የፈለገች ሴት ሙሉ ልብስ ከነኒቃቡ ጋር ትለብስ እንደነብርና የዚህ አይነት ልብስ የምትለብስ ወጣት በማህበረሰቡ የተከበረች እንደነበረች መዛግብቶቹ ያስረዳሉ ። አላህ ነብዩ ሙሐመድን ሲልክ ሴትን ልጅ የክብር ማማ ላይ በማስቀመጥ የመጀመሪያ መለኮታዊ የህይወት መመሪያ በሆነው ሕያው ቃሉ ስለ ሒጃብ በሚቀጥለው ቃሉ አስቀምጧል ። « وَقُل لِّلْمُؤْمِنَاتِ يَغْضُضْنَ مِنْ أَبْصَارِهِنَّ وَيَحْفَظْنَ فُرُوجَهُنَّ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا مَا ظَهَرَ مِنْهَا ۖ وَلْيَضْرِبْنَ بِخُمُرِهِنَّ عَلَىٰ جُيُوبِهِنَّ ۖ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا لِبُعُولَتِهِنَّ أَوْ آبَائِهِنَّ أَوْ آبَاءِ بُعُولَتِهِنَّ أَوْ أَبْنَائِهِنَّ أَوْ أَبْنَاءِ بُعُولَتِهِنَّ أَوْ إِخْوَانِهِنَّ أَوْ بَنِي إِخْوَانِهِنَّ أَوْ بَنِي أَخَوَاتِهِنَّ أَوْ نِسَائِهِنَّ أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُهُنَّ أَوِ التَّابِعِينَ غَيْرِ أُولِي الْإِرْبَةِ مِنَ الرِّجَالِ أَوِ الطِّفْلِ الَّذِينَ لَمْ يَظْهَرُوا عَلَىٰ عَوْرَاتِ النِّسَاءِ ۖ وَلَا يَضْرِبْنَ بِأَرْجُلِهِنَّ لِيُعْلَمَ مَا يُخْفِينَ مِن زِينَتِهِنَّ ۚ وَتُوبُوا إِلَى اللَّهِ جَمِيعًا أَيُّهَ الْمُؤْمِنُونَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ » النور (31) " ለምእምናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ ፡፡ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ ፡፡ ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልጽ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ ፡፡ ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ ፡፡ (የውስጥ) ጌጣቸውንም ለባሎቻቸው ወይም ለአባቶቻቸው ወይም ለባሎቻቸው አባቶች ወይም ለወንዶች ልጆቻቸው ወይም ለባሎቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለወንድሞቻቸው ወይም ለወንድሞቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለእህቶቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለሴቶቻቸው ወይም እጆቻቸው ለያዙት (ባሪያ) ወይም ከወንዶች ለሴት ጉዳይ የሌላቸው ለኾኑ ተከታዮች ወይም ለነዚያ በሴቶች ሐፍረተ ገላ ላይ ላላወቁ ሕፃኖች ካልኾነ በስተቀር አይግለጹ ፡፡ ከጌጣቸውም የሚሸፍኑት ይታወቅ ዘንድ በእግሮቻቸው አይምቱ ፡፡ ምእመናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ (በመመለስ) ተጸጸቱ ፡፡ በእነዚህ አንቀፆች ሴት ልጅ የውበቷ መገለጫዎች ለማን ግልፅ ማድረግ እንዳለባትና ከማን መሰተር እንዳለባት አስቀምጧል ። በመሆኑም ኒቃብ ኢስላም ሴት ልጅ ክብሯን መጠበቅ ስትፈልግ እንድትለብሰው ሳይሆን ለብሳው ክብሯን መጠበቅ እንዳለባት አዟል ። ኒቃብ በኢስላም ክብንና ንፅህናን የሚጠብቁበት ብቻ ሳይሆን ወደ አላህ የሚቃረቡበት የአምልኮ ክፍል ነው ። ምክንያቱም አምልኮ ( ዒባዳ) ማለት የአላህንና የመልእክተኛውን ትእዛዝ መፈፀም ስለሆ ነው ። በመሆኑም ኒቃብ በሁለቱም ሀገር እጅግ በርካታ ቱሩፋቶች ያሉት መሰተሪያ ሲሆን ከእነዚህ ቱሩፋቶቹ ውስጥ ጥቂት በቅርቢቱ ዓለም ካሉት ውስጥ እንመልከት : – አንደኛና ሁለተኛው – ተለይተው እንዲታወቁና ጎንታይ ባለጌዎች እንዳይጎነትሏቸው እንዳያስቸግሩዋቸውም ይረዳል ። ይህን አስመልክቶ አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ያላል : – « يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّأَزْوَاجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاءِ الْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَابِيبِهِنَّ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا » الأحزاب ( 59 ) " አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም ፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው ፡፡ ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው ፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው ፡፡" ሶስተኛው – ክብራቸውን ይጠብቁበታል ። አራተኛው – አላህን የመፍራታቸው ምልክት ነው ። አምስተኛው – ልባቸው በተቃራኒ ፆታ ፍላጎት የታመሙ ሰዎች በእነርሱ ምክንያት እንዳይሳሳቱ ያደርጋል ። ስድስተኛ – ዝሙት እንዳይስፋፋ ያደርጋል ። እነዚህ ከብዙ ጥቂት ቱሩፋቶቹ ናቸው ። በመሆኑም ኢስላም ሴትን ልጅ ከወርቅ በላይ ቦታ የሰጣት ስለሆነ አንድ ሴት ጌጥ የሆነው ወርቋን ደብቃ ከምትጠብቀው በላይ ራስዋን ደብቃ ለሚገባው አካል ብቻ እንድታስረክብ ያዛታል ። ይህን ስትፈፅም የክብሩ ማማ ላይ ትወጣለች ። በጣም የሚያሳዝነው ግን አብዛኛው ሙስሊም ማህበረሰብ ኒቃብ የኋላ ቀርነት ምልክት አድርጎ ያየዋል ። ከዚህም በላይ አንዳንዶች ልጃቸው ዝሙት ሰርታ በዝሙት አርግዛ ሲያዩ የማይደነግጡትና የማይበሳጩት አይነት ብስጭት ኒቃብ ለብሳ ሲያዩ ይበሳጫሉ ።‼ ይህ በርግጥ ትልቅ በሽታ ነው ። ከዚህም በላይ ደግሞ ልጃችሁ ከፍራለች ቢባሉ በብስጭት የማይታመሙትን ያክል ታመው ሆስፒታል ይገባሉ ። ይህ ምናባዊ ሀሳብ ሳይሆን በገሀዱ ዐለም ያለ እውነታ ነው ። በቅርቡ ሶስት ኒቃብ የለበሱ እህቶቻችን ቤተሰቦች ላይ ከታየው አሳፋሪ ተግባር ውስጥ የአንደኛዋ እህት እናትና አባት በብስጭት ታመው አባትየው ሆስፒታል ይገኛሉ ። ‼ በእነዚህ እህቶች ላይ ከተማም ገጠርም ያለ ዘመድ አዝማድ በሙሉ ኒቃቡን ለማስወለቅ የሚችለውን ያደረገ ሲሆን የሁለቱ እስካሁን አልተሳካም ። በተለይ ቤተሰቦቿ በዚህ ምክንያት የታመሙት ፀንታ ነው ያለችው ። ከሁለቱ እህቶቿ አንደኛዋ በጣም አሳፋሪና አሳዛኝ በሆነ መልኩ መብትሽ ነው እኔ ጋር ነይ ብሎ ከዘመዶቿ አንዱ ወደ ማታውቀው ከተማ እንድሄድ ካደረገ በኋላ መንገድ ላይ ጠብቆ ከመኪና ስትወርድ የምታወልቂ ከሆነ ልውሰድሽ ካልሆነ አዚሁ ጥዬሽ ነው ምሄደው ብሎ የቀን ጨለማ ውስጥ እንድትገባ አድርጎ አስሆልቋቷል ። ‼ አላህ ይድረስልን እንጂ ኒቃብ ለበሽታ ሰበብ የሚሆንባቸው ሙስሊሞች ያሉበት ዘመን ላይ ነው ያለነው ። ለእህቶቻችን ፅናቱን ለቤተሰቦቻቸው አላህ ሂዳያ እንዲሰጣቸው ዱዓእ እናድርግ እላለሁ ። https://t.me/bahruteka
إظهار الكل...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

👉 የነጅድ አንበሶች ለተውሒድ የከፈሉት ዋጋ ክፍል ሶስት የመጨረሻው ኢብራሂም ባሻ ዲርዒያን ካወደመና ዐብዱላሂ ኢብኑ ሙሐመድ ኢብኑ ስዑድንና መማክርቶቹን እንዲሁም ጠባቂዮቹን ካስረሸነ በኋላ ዲርዒያን ሙሉበሙሉ ለማፅዳት ባደረገው ዑለሞችን የማደን ሂደት ሸይኽ ሱለይማን ኢብኑ ዐብዲላህ ኢብኑ ሙሐመድ ኢብኑ ዐ/ወሃብን በቁጥጥር ስር አደረጋቸው ። ሸይኽ ሱለይማን ማለት ተይሲሩል ዐዚዚል ሐሚድ ሸርሕ ኪታቡ ተውሒድን እየፃፉ የነበሩ ታላቅ ዓሊም ሲሆኑ የሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐ/ወሃብ የልጅ ልጅ ናቸው ። የጀመሩት ኪታብ የአጎታቸው ልጅ ዐ/ራሕማን ኢብኑ ሐሰን ፈትሑል መጂድ በሚል ጨርሰውታል ። ኢብራሂም ባሻ ስልጣናችን ተነካ ባሉ የቱርክ ኤምፓየር መሪዮች የፈለገውን ሰርቶ ስልጣናቸውን ከስጋት እንዲከላከልላቸው በአባትየው አማካይነት ስልጣን የተሰጠው አረመኔ ነውና የቁርኣንና ሐዲስ ዓሊም ክብር ምኑም አይደለም ። ሸይኽ ሱለይማንን የፊጥኝ አስሮ ወደ መቃብር ቦታ ወሰዳቸው ። እዛ ከመረሸንና ከረሀብ የተረፈውን ህዝብ ሰብስቦ የግብፅ የሙዚቃ ባንድ እያስጨፈረ በከባድ መሳሪያ እንዲመቱ አደረገ ። የሸይኽ ሱለይማን ስጋ ተቆራርጦ ተበታተነ ።‼ ጀናዛቸው ታጥቦ ተከፍኖ ሊቀበር ይቅርና አካላቸው እንኳን መሰብሰብ አዳጋች ሆነ ። በዚህ አላበቃም ኢብራሂም ባሻ ወደ ሱለይማን አባት ሄዶ በግብፅ አነጋገር ያ አጉዝ ( አጁዝ ) ( አንተ ሽማግሌ ሆይ) ቀተልና ኢብነክ ( ልጅህን ገደልኩት ) አለው ። የሸይኽ ሱለይማን አባት ግን ታሪክ የማይረሳው መልስ ሰጡት ። መልሱ የኢብራሂም ባሻን አእምሮ እንደ ኤሌክትሪክ ሞገድ ሰርስሮ ገባ ። አባትየው እንዲህ ነበር ያሉት : – ኢን ለም ተቅቱልሁ ማተ ( ባትገድለውም ኖሮ ሟች ነበር ። !!!!! ከዚህ በኋላ ኢብራሂም ባሻ ዲርዒያ ላይ አሻንጉሊቶቹን አስቀምጦ ወደ ግብፅ ተመለሰ ። ግብፅ ላይ ሹማምንቶች ፣ የጦር አበጋዞችና ዑለሞች ተሰብስበው እየጠበቁት መሆኑን ተነገረው ። እሱም በትካዜ የኋልዮሽ ተመልሶ እያየ ዑለሞችማ የዲርዒያ በረሀ ላይ ቀሩ አለ ። የሸይኽ ሱለይማን አባትም ዓሊም መሆናቸውን ያውቅ ነበርና ንግግሩ ከአእምሮ አልወጣ ብሎት ። በቱርክ ኤምፓየርና በመምለካ ተዋጊዮች መካከል የነበረው ጦርነት ለስልጣንና ለተውሒድ የተደረገ ጦርነት ነበር ። የአላህ ስራ አስገራሚ ነውና አላህ ያን ግዙፍ የኢስላሙን ዐለም ሲመራ የነበረው የቱርክ ኤምፓየር ስርወ መንግስ ከአምስት አመት በኋላ ዲርዒያ ላይ ዳግም ላይመለስ ገርስሶ ከእነዚያ የተውሒድ መሪዮች ጋር ተቀብሮ የነበረው የተውሒድ ችግኝ እንቡጥ በደማቸው በዐብዱላሂ ልጅ ቱርኪ አማካይነት ዳግም እንዲያብብ በማድረግ የተውሒዷን ሀገር እስከ ዛሬ እንድትቀጥል አድርጓል ። የቱርክ ኤምፓየር ግን በዛው ማብቂያው ሆኗል ። ለአላህ የሆነ ይቀራል የሚባለው ለዚህ ነው ። ተፈፀመ ክፍል አንድን ለማግኘት 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/bahruteka/5079 ክፍል ሁለትን ለማግኘት 👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/bahruteka/5081 https://t.me/bahruteka
إظهار الكل...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

🔷 የነጅድ አንበሶች ለተውሒድ የከፈሉት ዋጋ ክፍል አንድ ነጅድ ማለት በሳውዲ ዐረቢያ የሚገኙ ሰፊ ቦታዎችን የሚያካልል ግዛት ስም ነው ። የሳውዲ ዋና ከተማ ሪያድ ነጅድ ውስጥ ነው ያለው ። እንደ ሓኢል ፣ ዲርዒያ ፣ ዑየይናና ፣ ሑረይሚላእ እንዲሁም አሕሳእ የመሳሰሉ ከተሞች ያሉበት አካባቢ ነጅድ በመባል ይታወቃል ። የነጅድ አንበሶች በማለት የፈለግሁበት የሸይኽ ሙሐመድ ዐ/ወሃብ የልጅ ልጆችና የሙሐመድ ኢብኑ ስዑድ የልጅ ልጆችን ነው ። የሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዱል ወሀብ የልጅ ልጆች የነጅድ ዑለሞች ሲባል ቅድሚያ ዪዛሉ ። ሳውዲ ( መምለከቱል ዐረቢያ ሱዑዲያ) የሚባለው ሀገር የተመሰረተው በሙሐመድ ኢብኑ ሱዑድና በሸይ ሙሐመድ ኢብኑ ዐ/ወሃብ ነው ። ሸይኽ ሙሐመድ ዐ/ወሃብ ዳዕዋቸውን ሲጀምሩ ሑረይሚላእ ከሚባለው ከተማ ወደ ዑየይና ከዛ ወደ ዲርዒያ እየተሰደዱ መጥተው ዲርዒያ ላይ የሙሐመድ ኢብኑ ሱዑድ ባለቤት በወቅቱ የጎሳ መሪ ለነበረው ባልዋ ይህን ሰው ተቀበለው አላህ ወዳንተ የላከው ስጦታ ነው ብላው ሸይኽ ሙሐመድን ተቀብሎ አክብሮ በነፃነት ዳዕዋ እንዲያደርጉ አደረገ ። በየቦታው ተደብቆ የነበረው የተውሒድ ዳዕዋ የተጠማ በሙሉ የተውሒድ ዳዕዋ ነፃነት ሲሰማ ወደ ዲርዒያ ጎረፈ ። ሸይኽ ሙሐመድ ከየቦታው የሚመጣውን የተውሒድ ተማሪ በማስተማርና ዳዕዋ በማድረግ ዲርዒያን ከፅልመት አውጥተው ወደ ተውሒድ ብርሀን ቀየሯት ። የተውሒድ ባንዲራ ዲርዒያ ላይ ከፍ ብሎ መውለብለብ ጀመረ ። ሙሐመድ ኢብኑ ስዑድ በእውኑ አይደለም በህልሙም ይሆናል ብሎ ያልጠቀው ክስተት ማየት ጀመረ ። ማህበረሰቡ ተቀየረ ። ቀብር አምልኮ እየመነመነ ሄደ ። በጎሳ ህግ ሲተዳደር የነበረው ገበሬ በቁርኣንና ሐዲስ መመራት ጀመረ ። ሙሐመድ ኢብኑ ስዑድ…

🔷 የነጅድ አንበሶች ለተውሒድ የከፈሉት ዋጋ የቱርክ ኤምፓየር ሱዑዲያ የምትባለውን ሀገር ማጥፋትና መካና መዲናን ማስመለስ ጊዜ የማይሰጠው ዋናው ስራ አደረገው ። ግዙፍ ጦር አዘጋጅቶ ወደ ዐረቢያ ግዛት ላከ ። ጦሩ ወደ መዲና ለመድረስ በሚያደርገው ግስጋሴ ያገኘውን ሁሉ ከምድር በታች እያደረገ ጉዞ ቀጠለ ። መዲና ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ አካሂዶ ህፃን አዋቂ ፣ ሽማግሌ አሮጊት ሳይል እየረሸነ መዲናን ተቆጣጠረ ። መዲና የነበሩ ታሪካዊ ቅርሶችን ወደ ኢስታንቡል ጫነ ። እነዚህ ታሪካዊ ቅርሶች አሁንም በቱርክ ዋና ከተማ ሙዘየም ላይ ይገኛሉ ። አላማው የመምለካን መሪዮች የሱዑዲ ዋና ከተማ የነበረችው ዲርዒያን ወሮ መሪዮቹን ማርኮ መቀጣጫ ማድረግና የተውሒድዋን ሀገር ማፈራረስ ነበርና መገስገስ ጀመረ ። ጉዞውን ወደ መካ ያደረገው ይህ ጦር ማውደሙንና መረሸኑን በመቀጠል መካ ደረሰ ። መካ ላይም የተለመደውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ በማድረግ በቁጥጥሩ ስር አደረጋት ። ሒጃዝን ( መካና ነዲናን) በቁጥጥሩ ስር ካደረገ በኋላ ጉዞውን ወደ ነጅድ አደረገ ። የዚህን ትልቅ ሀላፊነት መወጣት ለሚስር ( ግብፅ ) መሪዮች አስረከበ ። በወቅቱ የነበረው ሙሐመድ ዐሊ ባሻ ጦሩን እየመራ ወደ ዲርዒያ አቀና ። ከመጀመሪያ የባሰ ዘግናኝ ጭፍጨፋ በተለያዩ ከተሞች እያደረሰ ቢሄድም ዲርዒያን መቆጣጠር አልቻለም ። መሪነቱን ለልጁ ኢብራሂም ባሻ አስረክበ ። ኢብራሂም ባሻ በአዲስ መልኩ ጦሩን አደራጅቶ ሳር ቅጠሉን እያነደደ የህፃንና አዋቂን የአረጋዊያንን ጀናዛ ለአሞራ እየተወ ወደ ዲርዒያ ገሰገሰ ። ዲርዒያን ለሰባት ወር አካባቢ ከበባት ። ምንም ነገር እናዳይገባና እንዳይወጣ ከለከለ ። ረሀቡና ጥሙ ህፃናትና አረጋዊያንን ማርገፍ ሲጀምር የሳውዲ ( የሱዑዲ ) መሪ የነበረውን ዐብዱላሂ ኢብኑ ሙሐመድ ኢብኑ ሱዑድ ከበባው እንዲያበቃና ዋስትና ከሰጠው እጁን እንደሚሰጥ መልእክት ላከ ። ኢብራሂም ባሻ ጥያቄውን የተቀበለው መሆኑና ምንም ጉዳት እንደማያደርስ መልስ ሰጠ ። ዐብዱላሂ ኢብኑ ሙሐመድ ከነመማክርቱና ጠባቂዮቹ እጅ ሰጠ ። አሳፋሪው ኢብራሂም ባሻ ግን ቃሉን አፍርሶ ዲርዒያን አነደዳት ። ‼ በህዝቡ ላይ የተለመደውን አረመኔያዊ ጭፍጨፋ አካሄ ። ሙርከኛቹን ወደ ግብፅ ላካቸው ። ከግብፅ ወደ ቱርክ ተላኩ ። ቱርክ ላይ ዐብዱላሂ ኢብኑ መሐመድ ተገሎ አንገቱ ተቆርጦ ወደ የቱርክ ኤምፓየር መሪ ተላከ ። የተቀሩትም ተረሸኑ ። ኢብራሂም ባሻ ዲርዒያን ለማፅዳት ዑለሞቹን ማደን ጀመረ ። አላህ ካለ ይቀጥላል ። https://t.me/bahruteka
إظهار الكل...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

🔷 የነጅድ አንበሶች ለተውሒድ የከፈሉት ዋጋ ክፍል አንድ ነጅድ ማለት በሳውዲ ዐረቢያ የሚገኙ ሰፊ ቦታዎችን የሚያካልል ግዛት ስም ነው ። የሳውዲ ዋና ከተማ ሪያድ ነጅድ ውስጥ ነው ያለው ። እንደ ሓኢል ፣ ዲርዒያ ፣ ዑየይናና ፣ ሑረይሚላእ እንዲሁም አሕሳእ የመሳሰሉ ከተሞች ያሉበት አካባቢ ነጅድ በመባል ይታወቃል ። የነጅድ አንበሶች በማለት የፈለግሁበት የሸይኽ ሙሐመድ ዐ/ወሃብ የልጅ ልጆችና የሙሐመድ ኢብኑ ስዑድ የልጅ ልጆችን ነው ። የሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዱል ወሀብ የልጅ ልጆች የነጅድ ዑለሞች ሲባል ቅድሚያ ዪዛሉ ። ሳውዲ ( መምለከቱል ዐረቢያ ሱዑዲያ) የሚባለው ሀገር የተመሰረተው በሙሐመድ ኢብኑ ሱዑድና በሸይ ሙሐመድ ኢብኑ ዐ/ወሃብ ነው ። ሸይኽ ሙሐመድ ዐ/ወሃብ ዳዕዋቸውን ሲጀምሩ ሑረይሚላእ ከሚባለው ከተማ ወደ ዑየይና ከዛ ወደ ዲርዒያ እየተሰደዱ መጥተው ዲርዒያ ላይ የሙሐመድ ኢብኑ ሱዑድ ባለቤት በወቅቱ የጎሳ መሪ ለነበረው ባልዋ ይህን ሰው ተቀበለው አላህ ወዳንተ የላከው ስጦታ ነው ብላው ሸይኽ ሙሐመድን ተቀብሎ አክብሮ በነፃነት ዳዕዋ እንዲያደርጉ አደረገ ። በየቦታው ተደብቆ የነበረው የተውሒድ ዳዕዋ የተጠማ በሙሉ የተውሒድ ዳዕዋ ነፃነት ሲሰማ ወደ ዲርዒያ ጎረፈ ። ሸይኽ ሙሐመድ ከየቦታው የሚመጣውን የተውሒድ ተማሪ በማስተማርና ዳዕዋ በማድረግ ዲርዒያን ከፅልመት አውጥተው ወደ ተውሒድ ብርሀን ቀየሯት ። የተውሒድ ባንዲራ ዲርዒያ ላይ ከፍ ብሎ መውለብለብ ጀመረ ። ሙሐመድ ኢብኑ ስዑድ በእውኑ አይደለም በህልሙም ይሆናል ብሎ ያልጠቀው ክስተት ማየት ጀመረ ። ማህበረሰቡ ተቀየረ ። ቀብር አምልኮ እየመነመነ ሄደ ። በጎሳ ህግ ሲተዳደር የነበረው ገበሬ በቁርኣንና ሐዲስ መመራት ጀመረ ። ሙሐመድ ኢብኑ ስዑድ የሸይኽ ሙሐመድና የዳዕዋቸው ሁኔታና የተከታያቸው ብዛት ሲያይ ሶስት ነገር ቃል እንዲገቡለት ጠየቃቸው ። 1ኛ — የያዝከው ነገር አላህ ከፍ ሲያደርገው ጥለኸኝ ላትሄድ 2ኛ – በየአመቱ የምቀበለው ግብር አለ ላትከለክለኝ 3ኛ – የዲን ጉዳይ እሳቸው ሊመሩና የዱንያዊው ስልጣን ለሱ እንዲሆን ሸይኽ ሙሐመድ ጥሎ መሄድን በተመለከተ ደሜ ከደማችሁ ጋር ነው ጥዬህ አልሄድም ። የግብሩን በተመለከተ አላህ በምርኮ ይተካልሀል ። የዱንያው ስልጣን ያንተ ነው አሉት ። ከዚህ ስምምነት በኋላ ሙሐመድ ኢብኑ ስዑድ በስልጣን ዲኑን እየረዳ ሸይኽ ሙሐመድ ዲኑን እየመሩ ዳዕዋው ቀጠለ ። በጋራ ሆነው የሚመለኩ ቀብሮች ላይ የተሰሩ ዶሪሖችን መናድ ጀመሩ ። ሸሪዓ በስራ ላይ ዋለ ። ዝሙት የሰራ እየመጣ ሸሪዓዊ ቅጣት ልቀጣ ማለት ጀመረ ። ሽርክና ቢዳዓ አንገታቸውን ደፉ ። ወንጀል መክሰም ጀመረ ። የተውሒዱ ብርሀን አድማሱን እያሰፋ በአራቱም አቅጣጫ ይኖግድ ጀመር ። ሳውዲ ( መምለከቱል ዐረቢያ ስዑዲያ) የሚባለው ሀገር በሙሐመድ ኢብኑ ስዑድ አባት ስም ተመሰረተ ። ሳውዲ ከመመስረቷ በፊት ነጅድና አል ጀዚራ አል ዐረቢያ የሚባሉ ግዛቶች በወቅቱ የኢስላሙን ዐለም ሲመራ የነበረው የቱርክ ኤምፓየር አያውቀውም ነበር ። እነዚህ አካባቢዮች በአብዛኛው በጎሳ መሪዮች የሚመሩ የነበሩ ስለሆኑና እንዳጠቃላይ በረሀማ ግመል አርቢ ዘላኖች የሚበዙበት ለስርኣቱ የሚያስገኘው ብዙ ጥቅም ስላልነበረ ከዑስማንዮች ትኩት ተነፍጓቸው የቆዩ ነበሩ ። በተወሰነ መልኩም ቢሆን ትኩረት የሚሰጠው ለመካና ለመዲና ነበር ። ይህም የዐለም ሙስሊሞች ልባቸው የሚንጠለጠልባቸውና ለሐጅና ዑምራ እንዲሁም ለነብዩ መስጂድ ዚያራ የሚፈለጉ ስለነሩ ነው ። በፍቅ የሻፍዕይ መዝሀብ በዐቂዳ ሱፍይ የነበረው የቱርክ ኢምፓየር ስርኣት የሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐ/ወሃብና የሙሐመድ ኢብኑ ስዑድ ሳውዲን መመስረትና የተውሒድ ዳዕዋ ማወጅ የቀብር አምልኮ ማስወገድና ሸሪዓ በስራ ላይ ማዋል የራስ ምታቱ ሆነ ። መስራቾቹ ለትውልድ አስረክበው ሄደዋል ። ማግኘት አይቻልም ። የተመሰረተውን ሀገር ማፍረስና መሪዮቹን ማጥፋት የቱርክ ኤምፓየር ትልቅ የቤት ስራ ሆነ ። አላህ ካለ ይቀጥላል ። https://t.me/bahruteka
إظهار الكل...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.