cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Bekulu Entertainment

ትኩስ መረጃወች በየደቂቃ የሚለቀቁበት channel እዲሁም:- ፠ አጫጭር ታሪኮች ፠ስፖርት እና ወቅታዊ ጉዳዮች ይዘገቡበታል። https://t.me/joinchat/AAAAAEdTBZdXx8xrHyomTg ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info_bot

إظهار المزيد
Ethiopia1 896Amharic1 529الفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
10 390
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام
أرشيف المشاركات
Photo unavailableShow in Telegram
Breaking : 70% የትግራይ ክልል በመከላክያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ሆኗል። በትግራይ ክልል አገልግሎቶች ዳግም እየጀመሩ ነው አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በትግራይ ክልል አገልግሎቶች ዳግም እየጀመሩ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ እና የሰላም አማራጭ ዐቢይ ኮሚቴ አባል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለጹ። በክልሉ 70 በመቶ በሚሆኑ አካባቢዎች ዕርዳታው ከመቼውም ጊዜ በላይ እየደረሰ መሆኑንም ጠቁመዋል። ዕርዳታውን በሌሎች ቀሪ አካባቢዎችም ለማዳረስ በ35 ተሽከርካሪዎች ምግብ እና በ3 ተሽከርካሪዎች መድኃኒት ተጭኖ ሽሬ ገብቷል ብለዋል። ወደ ክልሉ በረራ መፈቀዱን የገለጹት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ የሰብአዊ ዕርዳታን በተመለከተ ምንም ዓይነት መሰናክል አይፈጠርም ብለዋል። አንዳንድ አካላት የአፍሪካውያን ዕውቀት በፕሪቶሪያ ባመጣው ስኬት ደስተኛ እንዳልሆኑ ጠቁመው፣ ይህንን መልካም መንፈስ ለማወክ ሲጥሩ ይታያሉ ሲሉም ገልጸዋል። ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
የቻይና “J-20” ስውር ተዋጊ ጄቶችን ምን የተለየ ያደርጋቸዋል? የ2022 የቻይና የአየር ትርኢት በደቡባዊ የሀገሪቱ ከተማ ዡሃይ መካሄድ ላይ ሲሆን፤ “J-20” ስውር ተዋጊ ጄት ለእይታ ቀርቧል። ለቻይና ኤር ሾው ላይ የቻይና አየር ሃይል ተዋጊዎች እና "የአየር ኤሮባቲክስ" ቡድን በዙሃይ ታላቅ የአየር ትርኢት ቢያቀርቡም አራት ጄ-20 ስውር ተዋጊዎች የተመልካችን አይን ስበዋ ነው የተባለው። በሰዓት እስከ 2 ሺህ 100 ኪሎ ሜትር ድረስ መብረር ይችላል የተባለለት “J-20” ተዋጊ ጄት፤ 19 ሺህ 390 ኪሎ ግራም ክብደት አለው ተብሏል። Via Al ain ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
እስራአል ዳንሳ በጥይት ተመታ ሐዋርያው እስራአል ዳንሳ ከአዲስ አበባ 590 ኪሜ የምትገኘው በኦሮሚያ ክልል የምትገኘው ነጌሌ ቦረና ኮንፍረስ አገልግሎ ሲመለስ ለአዲስ አበባ 140 ኪሜ ርቀት ያላት መቂ ከተማ  አካባቢ ሲደርስ ባልታወቁ የታጠቁ ሰዎች በአካባቢው በከፈቱት የተኮስ ሩምታ በሐዋርያ እስራኤል ዳንሳ ላይ እግሩ ላይ በጥይት ተመቷል። መቂ አካባቢ በታጠቁ ሰዎች በተከፈተው ተኮስ የሞቱ ሰዎች እና በርካታ መኪናዎች ተቃጥለው ነበር ። ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
#Somalia #Eritrea የሶማሊያው ፕሬዜዳንት በ3 ወር ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ  ወደ ኤርትራ አቅንተዋል። የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ ለ4 ቀን የስራ ጉብኝት ዛሬ ኤርትራ፣  አስመራ መግባታቸው ታውቋል። የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አስመራ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው የሶማሊያ አቻቸውን ተቀብለዋቸዋል። ፕሬዝዳንት ሙሀሙድ ወደ ፕሬዜዳንትነት የስልጣን መንበር ከመጡ በኃላ ወደ ኤርትራ በስራ ጉብኝት ሲያቀኑ ይህ ሁለተኛቸው ነው። ከሶስት ወር በፊት ነበር ለስራ ጉብኝት ወደ ኤርትራ ሄደው የነበር። በወቅቱ በዛው በኤርትራ ያሉ የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር አባላትን (ከፕሬዜዳንት ኢሳያስ ጋር) እንደጎበኙ ፣ ከጉብኝቱ በኃላ ወታደሮቹን ወደ ሀገራቸው ሶማሊያ ለመመለስ በሚቻልበት መንገድ ላይ እየሰሩ መሆኑን ፤ በኤርትራ ከነበራቸው ቆይታ በኃላ ወደ አሜሪካ በሄዱበት ወቅትም በኤርትራ ያሉትን 5,000 የሶማሊያ ጦር አባላትን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የአሜሪካን ድጋፍ እንደጠየቁ አይዘነጋም። ፕ/ት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ ፤ የሶማሊያ ወታደሮች ከኤርትራ ያልተመለሱበት ምክንያት ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሀገሪቱ ውስጥ (በሶማሊያ) ባለው የፖለቲካ ልዩነት ምክንያት ሊመልሷቸው ፈቃደኛ ባለመሆናቸው መሆኑን መግለፃቸው እና ኤርትራ የሶማሊያ ወታደሮችን ማሰልጠን ብቻ ሳይሆን እያስታጠቀችም እንደሆነ መግለፃቸው ይታወሳል። ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
#Ethiopia #EU #UNICEF የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የ31.5 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አደረገ። ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ላይ የተቋረጡ የጤና አገልግሎቶች እንደገና እንዲጀምሩ ለማድረግ የአውሮፓ ህብረት (EU) የ31.5 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉን ያደረገው የማስጀመር እና የአቅም ግንባታ ስራ እንዲሰራ ለማስቻል ለተመድ የህፃናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) መሆኑን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል። የተደረገው ድጋፍ የህፃናትና ሴቶች ኑሮ ለማሻሻልና በግጭቱ ሳቢያ ከደረሰባቸው ጉዳት እንዲያገግሙ እንዲሁም የጤና አገልግሎቶች እንዲጀምሩ ለማድረግ ነው። ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በ100 ሺሕ ብር ዋስትና እንዲፈታ ተወሰነ! የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት 2ኛ ይግባኝ ሰሚ ወንጀል ችሎት ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በ100 ሺሕ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈታ ወስኗል። ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ከዚህ ቀደም በ20 ሺሕ ብር ዋስትና እንዲወጣ የፈቀደለት ቢሆንም፤ ዐቃቤ ህግ በውሳኔው ቅር መሰኘቱን በመግለጽ ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ መጠየቁ ይታወሳል። በዚህም በጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ 3 ተደራራቢ ክሶች ስለቀረቡበት ፍ/ቤቱ ይግባኝ ያስቀርባል በማለት ሂደቱ እንዲቀጥል ያዘዘ ሲሆን፤ ጥቅምት 30/2015 ፍ/ቤት ቀርቦ መዝገቡ ለውሳኔ በሚል ለዛሬ ህዳር 1/2015 መቀጠሩ አይዘነጋም። Via Ethio FM ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
በአዲስ አበባ ከተማ ከአራት ወራት በላይ ተቋርጦ የነበረው የመታወቂያ እድሳት አገልግሎት በዛሬው ዕለት ጀምሯል። የመታውቂያ ዕድሳት አገልግሎት አሰጣጡ ለሕግ ወጥ ድርጊት ተጋልጦ የነበረ በመሆኑ እና የተለያዩ የሰላምና ፀጥታ ስጋት ጭምር በመፍጠሩ አገልግሎቱ መቋረጡ ይታወሳል። አገልገሎቱ ተድቅኖበት የነበረውን ችግር በማረም እና በማስተካከል ዳግም የመታውቂያ እድሳት በዛሬው ዕለት ተግባራዊ መደረግ መጀመሩን ኤ ኤም ኤን ዘግቧል። Photo: EBC ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
በጅቡቲ ወደብ ከመርከብ ላይ በቀጥታ መጫን የሚያስችል አዲስ ቴክኖሎጂ ሊተገበር ነው የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ከጅቡቲ የወደብ አገልግሎት ጋር በመሆን ቀደም ሲል በጭነት ማራገፍና ማጓጓዝ ረገድ ያጋጥሙ የነበሩ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ አሰራሮችን ሊተገብሩ መሆኑ ተገለጸ። የኢትዮጵያ ባህር ትራንሰፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅትና የጅቡቲ ወደብ ተናበው በመስራታቸው በመርከብ ጭነት አገልግሎት እና በሎጀስቲክስ ዘርፍ ውጤታማ ስራ መስራት አስችሏል ሲሉ የዶራህሌ መልቲፐርፐዝ የስራ ኃላፊ ገልጸዋል፡፡ የዶራህሌ መልቲፐርፐዝ የኦፕሬሽን ምክትል ዋና ኦፊሰር ኢድሪስ ዶሆር አህመድ የኢትዮጵያ ባህር ትራንሰፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅትና የጅቡቲ ወደብ ግንኙነት ከጀመረበት ካለፉት 30 ዓመታት ጀምሮ በትብብር እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ባህር ትራንሰፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅትና የጅቡቲ ወደብ ተናበው መስራታቸው በመርከብ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ዘርፍ ውጤታማ ስራ እንዲከናወን አድርጓል ሲሉም ኃላፊው አስታውቀዋል። ስራው በየሰዓታቱ እንድንገናኝ የሚያስገድድ እንደመሆኑ የመርከቦችን መድረሻ፣ የመርከብ ላይ ጭነት ማራገፍ፣ የየብስ ከባድ ተሽከርካሪ ጭነቶችን እና የባቡር ጭነቶችን አንድ ላይ አቅደን መስራታችን ክንውናችንን ውጤታማ አድርጎታል ብለዋል፡፡ በቀጣይ ከመርከብ ላይ በቀጥታ መጫን የሚያስችል አዲስ ቴክኖሎጂ ዕውን እንደሚያደርጉ አስረድተው የ2015 የአፈር ማዳበሪያ ቀደም ሲል ሲወስደው ከነበረው ባጠረ ጊዜ ወደ ሚፈለግበት ስፍራ ማድረስ የሚያስችል አሰራሮችን መዘርጋታቸውን ገልፀዋል፡፡ Via:- ዋልታ ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
ትላንት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ ፓርቲዉ በመግለጫዉ ካነሳቸዉ ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል፡- ፩. በሰላም ሥምምነቱ በተቀመጠው አግባብ የሽብር ቡድኑ ትጥቁን እንዲፈታ መንግስት በሙሉ አቅሙ እና ትኩረት እንዲሰራ፤ ፪. የ “ነጻ አውጭ ግንባሮች” ፖለቲካዊ ኅልውና ሕጋዊ እውቅና በሚያገኝበት ሀገር ፣ የሀገር ሉዐላዊነት ፣ የግዛት አንድነት እና ሀገራዊ አንድነት ማረጋገጥ የማይቻል በመሆኑ ፤ መንግስት ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጭ እያለ የሚጠራው ቡድን እና መሰል “ነጻ አውጭ” ቡድኖች የፖለቲካ ኅልውናቸው እንዲከስም እንዲሰራ እና የሕግ ክልከላ ስራ ላይ እንዲያውል፤ ፫. የአማራ ሕዝብ ክፋይ የሆኑት እና ከ30 ዓመት በላይ በአማራዊ ማንነታቸው ምክንያት የዘር ማጥፋት ወንጀል የተፈጸመባቸው የወልቃይት እና የራያ አካባቢዎች አሁን ባሉበት አማራ ክልል ሥር ሕጋዊ እውቅና እንዲያገኙ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና የፌዴራሉ መንግስት በአፋጣኝ የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ፣ እና ፬. በአሸባሪው ትሕነግ ጀማሪነት በሶስት ተከታታይ ዙር በተካሄደው የወራራ ጦርነት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን የአማራ፣ አፋር እና ትግራይ አካባቢዎች መልሶ የመገንባት እና የማቋቋም ሥራ የፌደራል መንግሥቱ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት እንዲመራና እንዲያስተባብር፣ መላው ኢትዮጵያውያንም ለመልሶ ግንባታው እና መቋቋሙ ሥራ ድጋፍ እንዲያደርጉ ንቅናቄዉ ጠይቋል፡፡ ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
በትግራይ ክልል የሚገኙ ቅርሶች ያሉበትን ሁኔታ ለማጣራት መታቀዱ ተነገረ! ከሳምንት በፊት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ለአስር ቀናት ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጲያ መንግስት እና የህወኃት ቡድን ውይይት የሰላም ስምምነት ፊርማ በማኖር መጠናቀቁን እንዳስደሰታቸው የኢትዮጲያ ቅርስ ባለአደራ ማህበር አስታውቋል፡፡የማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መቆያ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ከእዚህ ቀደም የኢትዮጲያ ቅርስ ባለአደራ ማህበር በአፋር እና በአማራ ክልል አንዳንዳ አከባቢዎች በጦርነቱ ሳቢያ ውድመት የደረሰባቸው ቅርሶች ያሉበትን ሁኔታ ሲያጣራ መቆየቱን አንስተዋል፡፡ ያም ሆኖ ግን አስተማማኝ ሰላም ባለመኖሩ በክልሎቹ በተለይም በአማራ ክልል የሚገኙ ቅርሶች በጦርነቱ ሳቢያ ከፍተኛ ውድመት እንዳጋጠማቸው ያነሱ ሲሆን አንዳንዶቹ በአስጊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ሃላፊው ጠቁመዋል፡፡የደሴ ሙዚየምን ጨምሮ ሌሎች የጦርነቱ ሰለባ የሆኑ ቅርሶችን ለመጠገን እና ታሪካዊ ይዞታቸውን መልሰው እንዲይዙ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ በአሁን ሰዓት በፌደራል መንግስቱ እና በህወኃት መካከል የተፈጠረውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በትግራይ ክልል የሚገኙ ቅርሶች ያሉበትን ሁኔታ የማጣራት እና አስፈላጊውን ድጋፍ የማድረግ ስራ እንደሚሰራ አቶ መቆያ ማሞ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡ ከእዚህ ቀደም የነበረው አለመረጋጋት በመሰረተ ልማት ላይ ውድመት በማድረሱ እና የሰላም ሁኔታው አስማማኝ ባለመሆኑ ቅርሶች ያሉበትን ሁኔታ ለማጣራት እና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ እንቅፋት ሆኖ ነበር ሲሉ ሃላፊው በተጨማሪነት አንስተዋል፡፡ [ዳጉ ጆርናል] ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ታደሰ ወረደ፣ ብርሃኑ ጁላ እና ባጫ ደበሌ ሰናይ ምሽት🇪🇹🇪🇹 ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
በዝቋላ ከተማ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተመለሰ! በዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዞን ኤሌክትሪክ ተቋርጦባቸው ከቆዩት ከተሞች መካከል አንዷ የሆነችው የሳህላ ወረዳ ዝቋላ ከተማ በዛሬው ዕለት ኤሌክትሪክ አግኝታለች፡፡ ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ መንግሥትና የሕወሃት ወታደራዊ አመራሮች ናይሮቢ ላይ በዝግ እያካሄዱት ያለው ውይይት እስከ ዓርብ ድረስ እንደሚቀጥል ከዲፕሎማቲክ ምንጮች መስማቱን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል። ውይይቱ ዛሬ እንደሚጠናቀቅ አንዳንድ የውጭ ዜና ወኪሎች ዘግበው ነበር። ውይይቱ የሕወሃት ታጣቂዎች ትጥቅ በሚፈቱበት፣ ሰብዓዊ ዕርዳታ ለትግራይ በሚቀርብበትና መሠረታዊ አገልግሎቶች በሚጀምሩበት ሁኔታ ዙሪያ እንደሆነ ቀደም ሲል ተገልጧል። የሁለቱ ወገኖች ውይይት ባለፉት ሦስት ቀናት ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ የውይይቱ አስተባባሪ አፍሪካ ኅብረት የሰጠው ነገር የለም። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በኬንያጉብኝት ላይ ያሉት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ራማፎዛና የኬንያው ሩቶ ሁለቱ ወገኖች የፕሪቶሪያውን የግጭት ማቆም ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገብሩ ዛሬ በጋራ ጠይቀዋል። Via Wazema ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ከሕዳር 15 ጀምሮ ኢትዮጵያ ለኬንያ 500 ኪሎ ቮልት የኤሌትሪክ ኃይል መላክ እንደምትጀምር ተገለጸ! ከሕዳር 15/2015 ጀምሮ ኢትዮጵያ ለኬንያ 500 ኪሎ ቮልት የኤሌትሪክ ኃይል መላክ እንደምትጀምር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለሰ አለም በሳምንቱ በተከናወኑ ዲፕሎማሲያዊ ኹነቶች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ኢትዮጵያ ከተለያዩ የጎረቤት አገራት ጋር የኤሌትሪክ ኃይል ለመሸጥ ስምምነት ማድረጓ የሚታወቅ ሲሆን፤ ወደ ኬንያ የሚላከው የኤሌትሪክ ኃይልም በተደረገው ስምምነት መሰረት መሆኑን አምባሳደሩ በማብራሪያቸው መናገራቸውን ዋልታ ዘግቧል። የኢትዮ- ኬንያ የማስተላለፊያ መስመርና ኮንቨርተር ስቴሽን ፕሮጀክት በ334 ነጥብ 5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጪ የተገነባ ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ 214 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላሩ ለኮንቨርተር ስቴሽኑና ለግራውንድ ኤሌክትሮድ መስመር የግንባታ ሥራ እንዲሁም 120 ሚሊዮን ዶላሩ ደግሞ ለማስተላለፊያ መስመሩ የዋለ ነው፡፡ የግንባታ ሥራው በ2008 የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት እስከ 2000 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፍ አቅም እንዳለው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ አምባሳደር መለሰ አለም አክለውም በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረው ግጭት በደቡብ አፍሪካ የሰላም ስምምነት ላይ መደረሱን ተከትሎ የተለያዩ የኢትዮጵያ ወዳጅ አገራትና ድርጅቶች በመልሶ ግንባታውና በሰብአዊ እርዳታ ላይ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ማሳወቃቸውን ገልጸዋል። ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
የደራሲ በአሉ ግርማ ባለቤት አልማዝ አበራ አረፉ የታላቁ ደራሲና ጋዜጠኛ የበአሉ ግርማ ባለቤት አልማዝ ዛሬ ጥቅምት 30/2015 ማረፋቸውን ቤተሰቦቻቸው አርድተውኛል ሲል ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ አስታውቋል። አልማዝ ባለቤታቸውን የበአሉ ግርማን ሞትና መሰወር አልቀበል ብለው የቆዩ ሲሆን፤ ሁልግዜ ጠዋት ላይ ቤታቸውን አፀዳድተው በር ከፍተው በአሉ ግርማን ይመጣል እያሉ ሲጠብቁት ኖረው በዛሬው ዕለት ህይወታቸው አልፏል። አልማዝ አበራ ከደራሲ በአሉ ግርማ ያፈሯቸው የሦስት ልጆች እናት ነበሩ። ፈጣሪ ነፍሳቸውን ይማርል። ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
300 የአየር ኢላማዎችን የመለየት ችሎታ ያለው የሩሲያው “በራሪ ራዳር” በራሪው ራዳር “ዶራ” በአንድ ጊዜ ከ300 በላይ የአየረ ላይ ኢላማዎችን የመለየት እና የመከታተል አቅም ያለው መሆኑ ተነግሯል።“ዶራ” አውሮፕላን በ600 ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ የአየር ኢላማዎችን በመከታተል እና በመለየት ተዋጊ ጄቶችን ወደ ኢላማዎቹ የመላክ አቅም ያለው መሆኑም መረጃዎች ይጠቁማሉ።"በራሪው ራዳር" ለሩሲያ ተዋጊ ተዋጊ ጄት አብራሪዎች ብዙ ጠቀሜታ አለው የተባለ ሲሆን፤ የሩሲያ አየር ኃይል የጠላት የአየር ዒላማዎችን ለማጥፋት አስፈላጊ መረጃዎችን በመስጠት ከፍተኛ ግልጋሎት ይሰጣል። Via Al ain ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም 2ኛው ምዕራፍ ግንባታ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው። በመርሃ ግብሩ ላይ ርዕሠ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ፣  የባህል እና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጀላ መርዳሳ፣ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል ተመስገን ጥሩነህ ፣ የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይን ጨምሮ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ባለሀብቶች እና የስፖርት ቤተሠቦች የተገኙበት ነው። የአማራ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ እርዚቅ ኢሳ፣ ስታዲየሙ ሳይጠናቀቅም አገልግሎት እየሠጠ የሚገኝ ባለድል ስታዲየም መሆኑን ገልፀው፣ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአማካይ 40 ጨዋታዎችን ማስተናገዱን አንስተዋል። ስታዲየሙ የካፍን ማሟያዎች ባለማሟላቱ ተጥሎበት የነበረውን እገዳ ማስነሳትን ጨምሮ ከጣራው ውጭ ሁሉንም የስታዲየሙ ቀሪ ግንባታዎችን ለማጠናቀቅ 1.1 እስከ 1.8 ቢሊየን ብር የሚጠይቀውን ግንባታ በክልሉ መንግስት እና ባለድርሻ አካላት ትብብር የግንባታ ስምምነቱ የሚፈፀም መሆኑን ገልፀዋል። የአማራ ክልል ለባህርዳር ስታዲየም ማጠናቀቂያ ከ700 ሚሊየን ብር በላይ መመደቡን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ በሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ 300ሚሊየን ብር ተጨማሪ ድጋፍ ነው ግንባታው የተጀመረው። 52ሺ ሠዎችን የሚያስዲያስተናግደው ግዙፉ የባህርዳር ስታዲየም ግንባታ በ2002 ዓ.ም በ780 ሚሊየን ብር በጀት የተጀመረ ሲሆን ሳይጠናቀቅ በመቆየቱ ሁለተኛው ዙር ግንባታ በሜድሮክ ኮንስትራክሽን እና በኤም ኤች አማካሪ ድርጅት የሚከናወን ነው። ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
የአማራ ክልል መንግስት ለባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ማጠናቀቂያ 700 ሚሊዮን ብር መደበ! ዛሬ የማጠናቀቂያ ሥራው ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) በተገኙበት እንደሚጀመር የአማራ ሚድያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) ዘግቧል። ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
የቶሌ ቀበሌ የአማራ ተወላጆች አካባቢያቸውን ጥለው ወጡ! ባለፈው ዓመት ሰኔ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በታጣቂዎች የተገደሉባት ቶሌ ቀበሌ ነዋሪዎች ዳግም ተመሳሳይ ጥቃት ሊፈፀምብን ይችላል በሚል ስጋት አካባቢያቸውን ለቀው መውጣታቸውን ገለጹ። ባለፈው ዓመት ሰኔ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በታጣቂዎች የተገደሉባት ቶሌ ቀበሌ ነዋሪዎች ዳግም ተመሳሳይ ጥቃት ሊፈፀምብን ይችላል በሚል ስጋት አካባቢያቸውን ለቀው መውጣታቸውን ገለጹ። ከአራት ወራት በፊት ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ውስጥ መንግሥት በሽብርተኛ ቡድንነት ሰይሞ ሸኔ በሚል የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 400 የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸውን የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሂዩማን ራይትስ ዎች ገልጾ ነበር። በአብዛኛው የአማራ ብሔር ተወላጆች የሆኑ ነዋሪዎችን ኢላማ አድርጎ በነበረው ጥቃት በርካታ ሴቶችና ህጻናት ሰለባ በሆኑበት በዚያ ጥቃት የተገደሉት ነዋሪዎች ቁጥር 338 መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ መግለጹ ይታወሳል።   በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው ይህ ጥቃት ከተፈጸመ ከጥቂት ወራት በኋላ የአማር ብሔር ተወላጅ የሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ተመሳሳይ ጥቃት ሊፈጸም ይችላል በሚል የደኅንነት ስጋት ከቶሌ ቀበሌ ተፈናቅለው መውጣታቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የቀበሌው ነዋሪዎች በአካባቢው የነበረው የፌደራል መንግሥቱ የፀጥታ ኃይሎች እንዲወጡ እንደነገሯቸውና አርብ ሌሊት ዘጠኝ ሰዓት ተነስተው ለሰዓታት በመጓዝ በምሥራቅ ወለጋ በሚገኘው አርጆ ጉደቱ ወደተባለ አካባቢ መሸሻቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።  የሁለት ልጆች እናት የሆነች ሴት ከዚህ ቀደም ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ በስፍራው የፌደራል ፖሊስ ተሰማርቶ እንደነበረ ገልጻ፣ ባለፈው ዓርብ ጥቅምት 25/2015 ዓ.ም. ከቦታው እንደሚለቁ ነግረውን “ሕይወታችሁን ለማትረፍ ውጡ እንሸኛችሁ” አሉን ስትል ትናገራለች። ሌላኛው የቶሌ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው እና የአራት ልጆች አባት የሆነው ግለሰብ እንደገለጸው፣ በስፍራው ሰፍረው የነበሩት የፌደራል ፖሊስ አባላት ከእኩለ ለሊት በኋላ 9 ሰዓት ላይ መኖሪያ ቤታቸው ድረስ በመምጣት አካባቢውን ጥለው እንዲወጡ እንደነገሯቸው ለቢቢሲ ተናግሯል። “ከእንቅልፍ ቀስቅሰው ተነሱ አሉን። የምናውቀው ነገር የለም በእግር ተጉዘን አምስት ሰዓት አርጆ ደረሰን” የሚለው ነዋሪው ከቀያቸው በድንገት በመውጣታቸው ምንም ነገር ሳይዙ መውጣታቸውን ያስረዳሉ። ከስድስት የቤተሰብ አባላቷ ጋር ከቶሌ ቀበሌ የወጣች ሌላ እናት ደግሞ “ከዚህ በፊት ብዙዎች እዚያው ከፊታችን ታርደውም፣ ተቃጥለውም ሲገደሉ ስላየን ሕይወታችንን ለማዳን ስንል ወጣን” ስትል ትናገራለች።  ከዚህ በፊት በቶሌ ቀበሌ በንጹሃን ዜጎች ላይ ግድያ የተፈጸመው የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ጥቃቱን ለመከላከል በቂ ጥበቃ ባለማደረጋቸው ነው ተብሎ ነበር።      ( ቢቢሲ አማርኛ ) ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
#ቤንሻንጉል! ከአሶሳ ወደ ህዳሴ ግድብ መሄጃ በሲርባ ወረዳ በህዳሴ ግድብ ቃንቁር ካምፕ በሚባል የቤህነን አማፅያን  በወሰዱ እርምጃ ብያንስ 3 በላይ የፀጥታ ሃይሎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል። አሶሳ ከተማ ከወትሮ በተለየ አኳሃን ቁጥራቸው ከነዋሪው በማይተናነስ ኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይል እና የመከላከያ ሃይል ብዛት ተጨናንቃለች። ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
የወልድያ ከተማ ከንቲባ ፅ/ቤት ለኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ደብዳቤ ፃፈ! የወልዲያ ከተማ አስተዳደር የከተማዋ አስፓልት መንገድ ስራ ትኩረት ተሰጥቶት በአስቸኳይ እንዲጀመር ሲል ጠየቀ። ከተማ አስተዳደሩ ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ.ም ለኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በፃፈው ደብዳቤ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሀገሪቱን የመንገድ አውታር ለማሻሻል በአዋጅ ቁጥር 80/1989 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ከሚያሰራቸው መንገዶች መካከል የወልዲያ አስፓልት መንገድ ከሀገር ውስጥ ስራ ተቋራጭ ዉል በመግባት የግንባታ ሰራው ከ4 ዓመት በፊት ተጀምሮ በተቋራጩ ውስንነትና አካባቢው በወረራ በመያዙ ምክኒያት ስራው ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ መቆየቱ እንደሚታወቅ ገልጿል ። ከወራ በኋለም ባቀረብነው ጥያቄ ስራውን የጀመረው ኮንትራክተር በነበረበት የአቅም ውስንነትና በሌሎችም ምክኒያቶች የስራ ውሉ ተቋርጦ ስራው ለሰሜን ሪጅን ኮምቦልቻ አካባቢ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጅመንት ጽ/ቤት እንደተሰጠ ቢነገረንም እስካሁን ስራው አልተጀመረም ብሏል ። ስራው በወቅቱ ባለመጀመሩም በአስፓልት ስራው መክኒያት ከይዞታቸው የተነሱ ባለይዞታዎች የካሳ ክፍያ ባለመጠናቀቁ ለችግር እየተዳረጉ መሆኑና አካባቢው ከፍተኛ የትራንስፖርት መዳረሻ በመሆኑ በዝናብ ወቅት ለጭቃ በበጋ ወቅት በሚፈጥረው አቧራ የከተማዋ ማህበረሰብ ለተለያዩ በሽታዎች እየተዳረገ መሆኑን በመጥቀስ ስራው ቅድሚያ ተሰጥቶት በአስቸኳይ እንዲጀመርልን ሲል የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደርን ጠይቋል። ለኢፊድሪ የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ሚኒስተር፣ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እና መንገድ ቢሮም አሳውቋል። ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
የድርድሩ ስምምነት ወደ ትግበራ ከመግባቱ በፊት በፓርላማው ለውይይት ጸድቆ እንዲቀርብ እናት ፓርቲ ጠየቀ! ባለፈው ሳምንት አጋማሽ በመንግሥት እና በሕወሓት መካከል የተፈረመው ስምምነት ወደ ትግበራ ከመግባቱ በፊት በፓርላማው ለውይይት ጸድቆ አእንዲቀርብ እናት ፓርቲ የጠየቀው ዛሬ ጥቅምት 29፣ 2015 ባወጣው መግለጫ ነው፡፡ ፓርቲው በመግለጫው በሁለት ፓርቲዎች መካከል የተደረገ ነው ባለው በድርድሩ ያልተወከሉና በጦርነቱ ቀጥተኛ ተጎጂ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች “ኢትዮጵያ አሸንፋለች” ብሎ ደጋግሞ በመናገር ለማሳመን ከመጣር ይልቅ የሚያመጣላቸውን በረከት፣ የሚያመጣባቸውን መዘዝ በተለይ የችግሩ ገፈት ቀማሽ የሆነውን ማኅበረሰብ በግልጽና በዝርዝር ቀርቦ ማናገር እንደሚያስፈልግ ገልጧል፡፡ ሁለት ዓመት ያስቆጠረውን የመንግሥት እና ሕወሓት ጦርነት በሠላም ለመቋጨት የሚያስችለው የስምምነት ፊርማ ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ጥቅምት 23 በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ እንደተፈረመ ይታወቃል፡፡ የቀዳሚው ስምምነት አካል የሆነው ተከታይ ውይይት ትላንት ጥቅምት 28፣ 2015 በኬንያ ናይሮቢ በጦር ጀነራራች መካከል የተደረገ ሲሆን፣ ውይይቱ እስከ ነገ ረቡዕ እንደሚቀጥል ተነግሯል፡፡ ከሰሞኑ ከተደርጉ ስምምነቶች በኋላ የአገር መከላከያ ሠራዊት እና የሕወሓት ወታደሮች በአንዳንድ ቦታዎች በጋራ ምግብ አንደተመገቡ እንዲሁም የሞቱትን በጋራ መቅበራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሑሴን ተናግረዋል፡፡ ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
የባህርዳር ስታዲየም የጣራ ማልበስ ስራ ሊጀመር ነው። ስታዲየሙ ሲጠናቀቅም ለከተማዋ ተጨማሪ ድምቀትና ውበት እንደሚጨምርላት ተገልጿል። ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ዋይ-20ኤ" የተሰኘው ግዙፉ የቻይና ወታደራዊ አውሮኘላን ዋይ - 20ኤ" የሚል ስያሜ የተሰጠው ቤጂንግ ሰራሽ የጦር አውሮፕላን በተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ ሀገራት ድጋፍን አድርሷል።የ2022 የቻይና የአየር ትርኢት በደቡባዊ የሀገሪቱ ከተማ ዡሃይ መካሄድ ሲጀምርም ግዙፉ አውሮፕላን ለእይታ ቀርቧል።ቻይና በራሷ አቅም የሰራችው ግዙፍ አውሮፕላን ረጅም ክንፎቹን ዘርግቶ መብረር ጀምሯል። የ2022 የቻይና የአየር ትርኢት በደቡባዊ የሀገሪቱ ከተማ ዡሃይ ከተማ ዛሬ ሲከፈት አውሮፕላኑ ትኩረትን ስቧል።ከ43 ሀገራት ከ740 በላይ ኩባንያዎች በትርኢቱ ላይ ተሳታፊ ሆነዋል።ከ100 በላይ አውሮፕላኖችም ለእይታ መቅረባቸው ነው የተነገረው። በተለይ ቻይና ስሪት የሆነው "ዋይ - 20ኤ" ግዙፍ አውሮፕላን የበርካቶችን ቀልብ መሳቡ ተገልጿል።የዚህ አውሮፕላን ክንፎች ከዋናው የአውሮፕላን ክፍል ወይም ቦዲ በላይ የተሰራ ነው።ራሳቸውን ችለው የሚንቀሳቀሱት ክንፎችም አውሮፕላኑን በአስቸጋሪ ሁኔታ መነሳትም ሆነ ማረፍ ያስችሉታል ተብሏል። ፓኪስታን በያዝነው የፈረንጆቹ 2022 ነሃሴ ወር በጎርፍ አደጋ ስትጠቃ ይሄው ግዙፍ አውሮፕላን ከ3 ሺ በላይ ድንኳኖችን ጭኖ ጉዞ አድርጓል።በዚሁ አመት ሰኔ ወር ላይም አፍጋኒስታን በርዕደ መሬት ስትጠቃ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ነፍስ አድን ድጋፎችን አድርሷል "ዋይ - 20ኤ"።በቶንጋ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ በደረሰበት ወቅትም ከ30 ቶን በላይ የምግብና የመጠጥ ውሃ ድጋፎችን በማመላለስ የጭንቅ ጊዜ ደራሸ ሆኗል። ቻይና በዚህ አውሮፕላን የቴክኖሎጂ እድገቷን እና ቀጣይ አቅሟን አሳይታበታለች።አንዳንዶች ስለ አዲሱ የቤጅንግ አውሮፕላን አድናቆታቸውን ለመግለፅ ቻይናውያን በአፈታሪክ ከሚጠቅሱት ግዙፍ ወፍ ጋር እያገናኙት ነው።ዋይ - 20ኤ" የቻይና መከላከያ ሃይል በትልቅ መሰረት ላይ መቀመጡንም ያሳያል የሚሉ ባለሙያዎች በርካታ ናቸው። እስያዊቷ ሀገር ከምዕራባውያን በተለይ ከአሜሪካ ጋር በገባችው የንግድ ጦርነት ሊገጥማት የሚችለውን ፈተና በቴክኖሎጂው ዘርፍ ራሷን ለመቻል የጀመረቻቸው ጥረቶች ተስፋ ሰጪ መሆናቸው ይነገራል።በዛሬው እለት የተጀመረው አለም አቀፍ ትርኢትም አዳዲስ ፈጠራዎቿን እንደምታስተዋውቅበት ይጠበቃል። Via Al ain ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
ማሊ ሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል በታጣቂዎች እጅ ዉስጥ ገብቷል መባሉን አስተባበለች የማሊ ጦር ሃይሎች በነሀሴ ወር የፈረንሳይ ወታደሮች ሀገሪቱን ለቀው ከወጡ በኋላ የሰሜን ምስራቅ ሜናካ ግዛት በአይ ኤስ ቡድን ታጣቂዎች እጅ ዉስጥ ወድቋል የሚለውን ዘገባ ውድቅ አድርጓል።"ይህ እውነት አይደለም እነዚህ የውሸት ወሬዎች የፕሮፓጋንዳ ሙከራዎች ዋንኛ ዓላማቸዉ የማሊ ታጣቂ ሀይሎችን ለማተራመስ ነዉ ፤ ሜናካ አልተከበበም” ሲሉ የማሊ ጦር ሀይሎች የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ጄኔራል ኮለኔል ሱለይማን ዴምቤሌ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። ሰራዊቱ በተደጋጋሚ በክልሉ በመዘዋወር ጥበቃ እያደረገ እንደሚገኝ አክለዋል፡፡ ተናግረዋል። በጋኦ የሚገኙ የሰራተኛ ማህበራትን  እየጨመረ ያለውን የታጣቂዎች ጥቃት በመቃወም የማሊ ወታደራዊዉን መንግስት ጥቃቱን ማስቆም አልቻለም በሚል የሁለት ቀን የስራ ማቆም አድማ ለማድረግ እቅድ መያዛቸዉን ተከትሎ የማሊ ጦር ሀይሎች መግለጫ ለማዉጣት ተገዷል፡፡ በታጣቂዎቹ የተነሳ በማሊ ድንበራማ አካባቢዎች አፈና፣ የታጠቁ ወንበዴዎች ዝርፊያ  እና የእንስሳት ስርቆት በየዕለቱ እየጨመረ ይገኛል፡፡ታዋቂው የመንግስት ደጋፊ ሚሊሻ የኢምጋድ ቱዋሬግስ እና አጋሮቻቸው ማሊ የሚገኙ የቱዋሬግ ማህበረሰብ አባላት እና አጎራባች ሀገራት አይኤስን በመዉጋት እንዲተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የቱዋሬግ ሚሊሻዎች ከመጋቢት ወር አንስቶ በሜናካ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎችን በጅምላ ገድሏል ከተባለዉ የአይ ኤስ ቡድን ጋር በመዋጋት ግንባር ላይ ይገኛሉ። Via:- ዳጉ ጆርናል ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
የአርቲስት አሊ ቢራ አስክሬን የትውልድ ቦታ በሆነች ድሬዳዋ ከተማ ደርሷል! የክቡር ዶክተር አርቲስ አሊ ቢራ አስከሬን በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ አባገዳዎች፣ የእምነት አባቶች፣ የአርት ባለሙያዎች፣ የአርቲስቱ አድናቂዎች በተገኙበት ሽኝት ከተደረገለት በኋላ ድሬደዋ ገብቷል።በአሁኑ ጊዜ አስክሬኑ ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ የደረሰ ሲሆን የድሬዳዋ ህዝብ፣ የእምነት አባቶች ለአርቲስቱን አስክሬን የክብር አቀባበል አድርገዋል።ከደቂቃዎች በኋላ የክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ የቀብር ስነስርአት የሚፈጸም ይሆናል። Via EPA ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ሹመት! ▪️የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ የሆኑት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ለሶስት ተከታታይ ጊዜ በቦርድ በአባልነት በመሾም ብቸኛው ሆነዋል። ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
የዩክሬን የጦር መሳሪያ ክምችት እየተመናመነ እንደሆነ ተገለጸ ምዕራባዊያን ደግሞ ለዩክሬን የጦር መሳሪያ መስጠት ሩሲያን የባሰ ጥቃት እንድትሰነዝር ሊያደርጋት ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው ተገልጿልhttps://am.al-ain.com/article/ukraine-weapon-is-dwindling ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ሹመት! ▪️የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ የሆኑት ዶ/ር ለገሠ ቱሉ የኢቢሲ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾመዋል። ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን 9 አባላት ያሉት አዲስ የስራ አመራር ቦርድ አባላት ሹመት በዛሬው ዕለት አፅድቋል፡፡ በዚሁ መሰረት ምክር ቤቱ ብዝሃነትን እና የትምህርት ዝግጅትን መሰረት ያደረጉ ዕጩዎች ከቀረቡ በኋላ የስራ አመራር ቦርዱን ሹመት አፅደቋል፡፡ በዚሁ መሰረት 1. ዶ/ር ለገሰ ቱሉ የቦርድ ሰብሳቢ 2. አቶ መሳፍንት ተፈራ 3. ዶ/ር አብዱልዋሳ አብዱላሂ 4. አቶ ታረቀኝ ቡልቡልታ 5. አቶ ጃፋር በድሩ 6. ዶ/ር ንጉሴ ተፈራ 7. አቶ ዩሱፍ ኢብራሂም 8. ወ/ሮ አመለወርቅ ህዝቅኤል 9. ዶ/ር ሙና አቡበክር የኢቢሲ ስራ አመራር ቦርድ አባላት ሆነው ተሹመዋል፡፡ ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ሹመት! ዶክተር ምሕረት ደበበ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ቦርድ ሰብሳቢ ሆነዋል፡፡ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቅራቢነት የዶክተር ምሕረትን የቦርድ ሰብሳቢነት ያጸቀደው ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 29፣ 2015 ባካሄደው ስብሰባ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የግል ተማሪዎች ክፍያን በእጥፍ መጨመሩ ቅሬታ አስነሳ! አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለግል ተማሪዎች የትምህርት ክፍያ ላይ የ100 በመቶ ጭማሪ ማድረጉ ከተማሪዎች ቅሬታ ቀርቦበታል። በዚህም ከፍተኛ ቅሬታ አድሮብናል ያሉት ተማሪዎቹ፣ በተለይ በዚህ ዓመት ለመማር እቅድ ይዘው የነበሩ አዲስ ተመዝጋቢዎች፣ የመግቢያ ፈተናውን ከተፈተኑ በኋላ የዋጋ ጭማሪውን ሲመለከቱ ብዙዎች ማቋረጣቸውን ተናግረዋል። በማኅበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ኹለተኛ ዲግሪዋን ለመማር የተመዘገበች ተማሪ እንደገለጸችው፣ ተማሪዎች የመጀመሪያውን መግቢያ ፈተና 600 ብር ከፍለው ከተፈተኑ በኋላ፣ ያለፉት ኹለት ወር ገደማ ጠብቀው ለዲፓርትመንት መግቢያው ድጋሜ ከፍለው ይፈተናሉ። ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...
" ... ከጌታቸው ጨምሮ ከራሳቸው ከTPLF ሰዎች አጣርቻለሁ ያ የተነገረው የድሮን ጥቃት የሚባለው ውሸት ነው " - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከሰላም ስምምነቱ በኃላ የተፈፀመ " የድሮን ጥቃት " የለም ሲሉ የኢትዮጵያ መንግስት ተደራዳሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ተናግረዋል። ይህን የተናገሩት " የኢትዮጵያ ሚዲያ ሰርቪስ (ኢ ኤም ኤስ) " ለተባለና በኢንተርኔት ላይ ለሚሰራጭ ሚዲያ ነው። " በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ አንዳንድ ክስተቶች ተፈጠሩ ሲባል መረጃ እንለዋወጣለን። ስምምነት ተፈራርመናል ስለዚህ የስልክ ችግር የለብንም። " ያሉት አምባሳደር ሬድዋን በኬንያ ናይሮቢ ፤ ከእነ አቶ ጌታቸው ረዳ እና ከወታደራዊ አዛዦቹም ጋር መነጋገራቸውን እና የድሮን ጥቃት ተፈፀመ የተባለው ውሸት መሆኑን  ገልፀዋል። " #ስምምነት_ከመፈረሙ_በፊት የነበረ (incident) ክስተትን ከስምምነት በኃላም ለማምጣት የሚሞክሩ አሉ። በዚህ ግጭት ውስጥ ገንዘብ ይከፈላቸው የነበሩ ጥሩ ሃብት ያፈሩበት ሰዎች አሁንም ግጭት እንዲቀጥል የማቀጣጠል ፍላጎት ያላቸው እንዳሉ እናያለን ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ፤ ከውስጥም በተለያየ መንገድ ስሜታዊ የሆነ ሰው ሊያራግበው ይችላል የትግራይ ሚዲያም ፤ የወያኔ ቴሌቪዥንም ሰርተውት ነበር" ብለዋል። " በእኛ በኩል #ንግግሮችን ለማስተካከል ሞክረናል " ያሉት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን " አሁን ሰው ተስፋ እንዳያድርበት ወደፊትም ይሄን ነገር እንዲያመጣ ነው እንጂ ቁርሾውን በ 'Transitional Justice' በሂደት ይሄዳል ፣ በምህረት የሚታለፈው ይታለፋል መፀፀቱ ከታየ እውነት ከተናገረ ፤ የግድ በፍርድ ቤት ማለቅ ያለበት ከባድ ወንጀል የሆነ ወደ ፍርድ ቤት ይሄዳል፣ ተጠያቂነትንም የማህበራዊ ህክምናንም ትስስርንም እኩል የሚያማክል መንገድ አለን እሱ ይደረሳል " ሲሉ ተናግረዋል። " ያልነበረ ነገር እያጋጋሉ የውሸት ሚፅፉ አሉ ከራሳቸው ከTPLF ሰዎች አጣርቻለሁ ጌታቸውን ጨምሮ ያ የወጣው መግለጫ (የGSTS መግለጫ ማለታቸው ነው) የጋራቸው አቋም እንዳልሆነ፣  የተባለው የድሮን ጥቃትም ውሸት እንደሆነ አጣርቻለሁ " ብለዋል። በስናይፐር ፣ በድሽቃ አልፎ አልፎ የተኩስ ልውውጥ ሊያጋጥም እንደሚችል የጠቆሙት አምባሳደሩ " ይሄ የተለመደ ነው፤ የሰላም ፊርማ ሲፈረም የተወሰኑ ቀናት እየሞተ እስከሚሄድ ድረስ የሰማም በስሜት ተውጦ እምቢ ብሎ ሊያደርገው ይችላል፣ ሳይሰማ የሚቀርም ያደርገዋል፤ ነገር ፈልጎ ነገሩ እንዲበላሽ  የሚፈልግም ሊያደርገው ይችላል በታንክ እና በመድፍ እንድካልሆነ ድረስ በድሽቃ እና በስናይፐሮች የሚደረግ አንዳንድ የተኩስ ምልልሶች እዚህም እዚያም ያጋጥማሉ " ሲሉ አስረድተዋል። " ሰው ይሄንን (አንዳንድ ቦታዎች ላይ የሚያጋጥሙትን የተኩስ ልውውጦችን ማለታቸው ነው) ለመዘገብ የሚቸኩለውን ያህል ከTPLF ካምፕ ወደኛ ወታደር መጥቶ አብሮ በልቶ ፣ ... ፣ ተጫውቶ ፣ ፎቶ ተነስቶ የሚመለሰውን ለመዘገብ ፍላጎት የላቸውም እኛ ነን መግፋት ያለብን የሚል ነገር በሁለቱም በኩል አለ ካማንደሮቹ ይሄን ጉዳይ መልክ ካስያዙት በኃላ ሁሉ። የራሳቸውን Discipline ያሲዛሉ " ሲሉ ተደምጠዋል። ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡ @ethio27info_bot @ethio27info
إظهار الكل...