cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

azyrot አዚሮት

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
161
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام
أرشيف المشاركات
ጋዜጠኛው የሲኦል ቦታ ስለሌለን ገሃነም ሲከፈት ና ተብሏል #Ethiopia | አንድ ጋዜጠኛ ይሞትና ወደ ሲኦል ይላካል። የሲኦል ጠባቂ ፋይሉን ያይና "ላንተ የሚሆን ቦታ አላዘጋጀንም፤ ያዘጋጀነው እኛ ላሳሳትናቸው ነው። አንተ ደግሞ አሳሳች እንጂ ተሳሳች ስላልሆንክ ቦታ የለንም" ይለዋል። ጋዜጠኛው ከሲኦል ተባርሮ ሲመለስ የወሰደው መልአክ ያገኘውና "ለምን ተመለስክ? አታለህ ገነት ልትገባ ነው አይደል? እዚህም ማታለል ትፈለጋለህ" አለው። ጋዜጠኛውም መልሶ" ኧረ እንደዚያ አይደለም፤ ለአንተ የሚበቃ መቅጫ የለንም ብሎኝ ነው" ይለዋል። መልአኩም መልሶ ይዞት ሄደና የሲኦልን ጠባቂ " ይሄን ጋዜጠኛ ለምን መለስከው" አለው። "ለርሱ የሚሆን ቦታ እንድናዘጋጅ ቀድማችሁ አልነገራችሁንማ" አለው። " እዚህ ካሉት በምን ይለያል" አለው መልአኩ ወደ ሲኦል እያመለከተ። " እነዚህ ሰዎች ናቸው" አለው። "ይሄስ" አለው መልአኩ። "ይሄማ የሲኤንኤን ጋዜጠኛ ነው" አለው። " እና ምን ይሻላል" አለው መልአኩ። " ገሃነም ሲከፈት ይዘህው ና" አለው። የሲኤንኤን ጋዜጠኞች በዚህ የተነሣ ነው ምድር ላይ የቆዩት። ሙሃዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት
إظهار الكل...
ሽንፈት ተከናንቦ ወደ ትግራይ የሸሸው የህወሓት ወራሪ ኃይል የድል አድራጊ አቀባበል እንዲደረግለት ቢሞከርም ተቃውሞ እየገጠመው ነው በተለያዩ ግንባሮች ሽንፈት ተከናንቦ ሙት፣ ቁስለኛና ምርኮኛ ከሆነው የህወሓት ወራሪ ኃይል የተራረፈው ታጣቂ ወደ ትግራይ ሲገባ የድል አድራጊ አቀባበል እንዲደረግለት ቢሞከርም ተቃውሞ እየገጠመው መሆኑን ታማኝ የመረጃ ምንጮቻችን ገልጸውልናል፡፡ እንደ መረጃ ምንጮቻችን ከሆነ አሸባሪው ቡድን የፈጸመው ወረራ ተቀልብሶ ክፉኛ ሽንፈት አጋጥሞት ወደ ትግራይ ክልል እየገባ ነው፡፡ ሽንፈቱ ሊዋጥላቸው ያልቻለው የቡድኑ አመራሮች ወራሪ ኃይሉ ከፍተኛ ድል አስመዝግቦ የመጣ በማስመሰል የድል አድራጊ አቀባበል እንዲደረግለት እየመከሩ ነው፡፡ ታጣቂዎች ወደ ከተማ ሲገቡ ጥይት ወደ ላይ በመተኮስ በከበሮና በጡሩንባ እንዲታጀቡ ጥረት ቢደረግም በርካታ ልጆቹን መስዋዕት ያደረገውና ወደ ‹‹አዲስ አበባ ለመግባት ጫፍ ደርሰናል›› በሚል የሀሰት ፕሮፕጋንዳ እየተጭበረበረ እንደነበር የተገነዘበው ህብረተሠብ አጋጣሚውን ተቃውሞውን ለመግለጽም እየተጠቀመበት ይገኛል፡፡ በድል እንደተመለሱ ለማስመሰል የሚሞክሩት የአሸባሪው ቡድን አመራሮች ሽንፈታቸውን ለማድበስበስ እንዲሁም አሁንም የሀሰት ዘመቻውን በማቀጣጠል ህብረተሠቡ ምንም መረጃ የለውም በሚል ንቀት ለተጨማሪ እኩይ አላማቸው ለማነሳሳት ‹‹ከፍተኛ ድል አስመዝግበናል።ጠላትን ስበን ወደምንፈልገው ቦታ ያመጣነው በመሆኑ አሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ መስዋዕትነት የሚጠይቅ ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡የመጣውን ጠላት ለመደምሰስ ተጨማሪ ኃይል ስለሚያስፈልግ ሁሉም ትግራዋይ የድሉ ተቋዳሽ እንዲሆን ወደ ግንባር መቀላቀል አለበት፡፡ሁሉም ሰው ያለውንም ሀብትና ጥሪት ለዘመቻው ማዋል ይጠበቅበታል›› በማለት ቅስቀሳ እያደረጉ መሆናቸውን ምንጮቻችን አረጋግጠውልናል፡፡ #FBC
إظهار الكل...
#እንድታውቁት ለንግድ ወደ ሀገር የሚገቡ እቃዎች የሚባሉት የትኞቹ ናቸው ? ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት በስተቀር ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ማናቸውም ዕቃዎች ለንግድ የሚውሉ ዕቃዎች ናቸው። 1. በፌደራል እና በክልል የፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ መሰረት ለመንግስት መ/ቤት በተሰጠው ትርጉም ውስጥ የተካተቱ የፌደራል መንግስት መ/ቤቶች እና የክልል መንግስታት መ/ቤቶች የሚያስገቧቸው ዕቃዎች፣ 2. ለትርፍ ያልተቋቋሙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ማህበራት የሚያስገቧቸው እቃዎች (ከተቋቋሙበት አላማ ውጭ በንግድ መልክ የሚያስገቧቸውን ዕቃዎች አይጨምርም)፣ 3. በዲፕሎማቲክ እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሰረት ከንግድ ትርፍ ግብር ነፃ የሆኑ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ የውጭ ዲፕሎማቲክ ወይም ኮንሱላር ሚሲዮኖችና የእነዚሁ አባላት የሚስገቧቸው ዕቃዎች፡፡ 4. የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ ቁጥር 51/2010 መሰረት የግል መገልገያ እቃዎችን ከቀረጥ ነፃ ወይም ቀረጥና ታክስ ከፍለው እንዲያስገቡ የተፈቀደላቸው ግለሰቦች የሚያስገቧቸው እቃዎች፣ 5. በጉምሩክ ታሪፍ ደንብ 2ኛ መደብ (ለ) ተጠቃሚ ሆነው እቃዎችን የሚያስገቡ ግለሰቦችና ድርጅቶች፣ 6. በፌደራልና በክልል ኢንቨስትመንት ባለስልጣን ከገቢ ግብር ነፃ የመሆን መብት የተፈቀደላቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች በእፎይታው ጊዜ ውስጥ የሚያስገቧቸው እቃዎች፣ 7. የአምራችነት ፍቃድ ያላቸው ሰዎች ወይም ድርጅቶች ለሚያመርቷቸው ዕቃዎች በግብዓትነት የሚጠቀሙባቸው ጥሬ ዕቃዎች እና ለካፒታል ዕቃዎች የሚያገለግሉ መለዋወጫዎች ፣ 8. ኢንዱስትሪዎችን ለማቋቋም ወይም ለማስፋፋት ወይም ለሃይል ማመንጨት ወይም የመገናኛ አገልግሎት ለመዘርጋት ወዘተ ወደ አገር የሚገቡ የካፒታል ዕቃዎች ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ወይም ጉዳዩ ከሚመለከተው አካል የካፒታል ዕቃዎች መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከቀረበ፣ 9. የንግድ ትርኢት ለመሳተፍ የሚመጡ የውጪ አገር ድርጅቶች ምርታቸውን ለማስተዋወቅ ወደ ውስጥ ይዘውት የሚገቡት እቃዎች፣ 10. በማዕድን እንዲሁም በፔትሮሊየም ስራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ለነዚህ ስራዎች አገልግሎት እንዲሰጡ የማያስገቧቸው እቃዎች እና 11. ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውሉ እቃዎች ከላይ ከተዘረዘሩት ውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ሌሎች ማናቸውም እቃዎች ለንግድ የሚውሉ ዕቃዎች ተብለው ይታያሉ፡፡ ወደ አገር ከሚገቡ ለንግድ ከሚውሉ ዕቃዎች የቅድሚያ ግብር ስለመሰብሰብ ፦ 1. ዕቃዎቹ ወደ አገር በሚገቡበት ጊዜ በቅድሚያ ግብር የሚከፈለው በጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤቶች በኩል ይሆናል ፡፡ 2. በጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤቶች ለንግድ ከሚውሉ እቃዎች የቅድሚያ ግብር ሲሰበስቡ የግብር ከፋዩን ሥም፤ አድርሻ እና የግብር ከፋዩን መለያ ቁጥር በመጠቀም መመዝገብና ሂሰቡን በዚሁ መሠረት መያዝ አለባቸው። 3. በጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤቶች ከተከፋይ ሂሣቦች ላይ በቅድሚያ ተቀናሽ የሚደረገው የቅድመ-ታክስ ክፍያ ገቢ ባለቤት ለሆኑት ገቢ ሰብሳቢ አካላት በተዘረጋው ሥርዓት መሠረት ይተላለፋል፡፡ ምንጭ፦ የገቢዎች ሚኒስቴር
إظهار الكل...
አብኣላ ልክ እንደ ደሴ በነዋሪ ጁንታ ነበር የተካደችው!!! የአፋሯ አብኣላ ከተማ ህዝብ ለዘመናት አብሯቸው በኖሩና ባመኗቸው ጎረቤቶች ነው የተካዱት ልክ እንደ ደሴ ከተማ።በከተማው ብዙ ሆቴሎች ይገኛሉ ሁሉም በሚባል መልኩ ሆቴሎቹ የትግራይ ተወላጆች ናቸው። እናም በአብኣላ ከተማ የሚኖሩ ከሃዲ ጁንታዎች ከተማዋ በተራራ የተከበበች በመሆንዋ በተለያዩ መንገዶች የጦር መሳሪያ ወደ ከተማ በማስገባት ነቀር ያመናቸውን ህዝብ ለማጥቃት ተዘጋጅተው ነበር የውጭ ወራሪውን መምጣት የሚጠባበቁት። የውጭ ወራሪውም አልቀሩም በአስተኳሾች ወደ ከተማ መድፍ መተኮስ ጀመሩ።በዚህ ጊዜ ከሃዲዎቹ ጁንታው በተደናገጠ ህዝብ ላይ ነበር የደበቁትን መሳሪያ እየመዘዙ ተኩስ የከፈቱት። በሰአቱ መስዋዕት መክፈሉ ባይቀርም ። የአፋር ህዝባዊ ሰራዊት በፍጥነት በተደረጀ መልኩ ቦታ ቦታ ይዘው መጀመሪያ ከተማ ውስጥ የነበረውን ጁንታ አሳደው ደመሰሱ። በመቀጠልም በተራሮች የተመሸገውን የውጭ ወራሪውን ሃይል ሙሉ ለሙሉ በመደምሰስ ከተማቸውን በቁጥጥር ስር አውለው በአሁን ሰአት የአብኣላ ከተማ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ተመልሳለች። ትዝብት ነው እንጂ ጥፊ ሰው አይጎዳም አይደል የሚባለው። Via Ahmed Habib Alzarawi
إظهار الكل...
ታማኝ በየነ የአፋር ህዝብ የክብር አምባሳደር ተደርጎ ተሾመ። "ከዚህ በኋላ ታማኝን የነካ የአፋርን ህዝብ እንደነካ ይቆጠራል።'' የተከበሩ ሀጂ አወል አርባ የአፋር ብሄራዊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አርቲስት እና አክቲቪስት ታማኝ በየነ የአፋር ህዝብ የክብር አምባሳደርነት ማዕረግን ያገኘው ዛሬ በሰመራ ከተማ ነው። ግሎባል አላይንስ ለኢትዮጵያውያን ሰብአዊ መብቶች በሰሜን አሜሪካን የተለያዩ ስቴቶች ከሚገኙ አጋሮቹ ጋር በመሆን በአፋር ክልል በጦርነቱ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ባደረሰበት ጊዜ ነው ይህንን ክብር ብለዋል! "አፋር ኢትዮጵያዊነትን ከንግግር ባለፈ በተግባር የገለጠ ልዩ ህዝብ ነው።የአፋር ህዝብ ሰውን በሰውነቱ ብቻ የሚለካ እና ያለምንም ልዩነት እንግዳውን ተቀብሎ የሚያስተናግድ ኩሩ ህዝብ ነው። ኢትዮጵያ ጉሮሮዋን ታንቃ ፈታኝ የሞት ሽረት ትግል በገጠመችበት ጊዜም የምድር ድሮኖቹ አፋሮች የታነቀውን የኢትዮጵያ ጉሮሮ በማስለቀቅ እና ኢትዮጵያ እንድትቀጥል በተግባር የተፈተነ ጀብድ በመፈጸም ማንነታቸውን አሳይተዋል።"ያለው አርቲስት እና አክቲቪስት ታማኝ በየነ "በዚህ በተከበረ ህዝብ ፊት መቆም ለእኔ ክብር ነው።" ሲል ፍቅሩን ገልጧል። በወራሪው የትግራይ ሀይል ምክንያት በአፋር ክልል የተፈናቀሉ ኢትዮጽያውያንን ለመደገፍ እና ከጎናችሁ ነን ለማለት ያላቸውን ይዘው የመጡትን የግሎባል አልያንስ እና ተባባሪዎቻቸውን ተወካዮች ያመሰገኑት ርዕሰ መስተዳድሩ ሀጂ አወል አርባ "የአፋር ህዝብ በችግሩ ወቅት ከጎኑ የቆሙትን በሙሉ በልዩ ፍቅር ያያቸዋል። የሰው ልጅ በተግባር በሚፈተንበት በዚህ ወቅትም ታማኝ በየነ እንደዚህ ቀደሙ ሁሉ አሁንም ከአፍር ህዝብ ጎን ለመቆም ከሰሜን አሜሪካን ድረስ በመምጣት ወዳጅነቱን አሳይቶናል።" ብለዋል። "የአፋር ህዝብ በጦርነቱ ብዙ መከራን ተቀብሏል። በዚህም በንብረት ውድመት ብቻ ከአስር ቢልዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሞበታል። በዚህ አስቸጋሪ ወቅትም ወዳጅ እና ጠላቱን ለይቷል" ካሉ በኋላ "እአፋሮች ድጋፍ ለማድረግ በመሀከላችን የተገኘው አርቲስት እና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ከድምጻችን ይሰማ ጀምሮ በነበሩን እንቅስቃሴዎች አብሮን እንደነበር አልዘነጋነውም። ለአፋር ክልል ህዝብ ላደረገው ከፍተኛ አስተዋጽኦም የአፋር ህዝብ የክብር አምባሳደር አድርገን ሾመነዋል ካሉ በኋላ ታማኝ ከዚህ በኋላ እንደ አንደ የአፋር ልጅ ነው። ታማኝን ያጠቃ እና የተተናኮለ የአፋርን ህዝብ እንደ ደፈር ይቆጠራል።" ብለዋል። በግሎባል አሊያንስ አስተባባሪነት የተላኩትን ድጋፎች ለርዕሰ መተዳድሩ ያስረከበው ታማኝ በየነም የአፋር ህዝብ እና መንግስት አመስግኖ የክብር ሹመቱን መቀበሉን አረጋግጦ ለዚህ ክብር ያበቃውን የአፋር ህዝብ አመሰግኗል። #Befekadu_Abay
إظهار الكل...
"የደፈሩኝ ይፈሩ‼ "እኔን አንገት ማስደፋት አይቻላቸውም‼" - በአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች የተደረፈረችው የ14 አመት ታዳጊ **************** (ኢ ፕ ድ) ‹‹እኔ የሚያሳፍር ነገር አልሰራሁም አልፈራም። እንዲያውም የእነርሱ ሀጢያት በዓለም ዓደባባይ ይታይላቸው። እኔ የሚያሸማቅቅ ነገር አላደረኩም፡፡ ፈልጌ አድርጌው ቢሆን እውነትም ላፍር ይገባኝ ነበር። ሚዲያዎች ሲቀርፁኝ ፊቴ ለእኔ በማሰብ እንዳይታይ ይፈልጋሉ፡፡ ያለፍላጎቴ እንዲህ ዓይነት ስቃይ ውስጥ የጣሉኝ እነርሱ ይፈሩ፤ ግፋቸውም ይታወቅ እኔ ምንም አይሰማኝም›› ትላለች በአሸባሪው ሕወሓት ታጣቂዎች ተደፍራ የሰቀቀን ቀናትን እየገፋች ያለችው የ14 ዓመት የሸዋሮቢቷ ታዳጊ፡፡ የ14 ዓመቷ ታዳጊ ሀዊ ሲራጅ (ሥሟ የተቀየረ) በሸዋሮቢት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ9ኛ ክፍል ተማሪ ናት፡፡ አሸባሪው ሕወሓት ከተማዋን ሲወር ከእናቷ እና ከሦስት ዓመት ወንድሟ ጋር ህዳር 10 ቀን 2014 ዓ.ም በሸዋሮቢት አቅራቢያ ወደምትገኝ ቆቦ ወደተባለች የገጠር መንደር ሸሹ፡፡ ነገር ግን ታጣቂዎቹ የከተማዋን ነዋሪ አንነካም፤ ሴቶችና ሕፃናት ከቤታችው አይውጡ እኛ የምንፈልገው መሳሪያ የታጠቀ ሰው ብቻ ነው” በሚል ያስተላላፉት መልዕክት እውነት መስሏቸው ወደቤታቸው መመለሳቸውን ታዳጊዋ ትናገራለች። ዳሩ ግን ነገሮችን የአሸባሪው ታጣቂዎች ታዳጊ ሴቶች ያሉባቸውን ቤቶች ሲለዩ ቆይተው፤ ህዳር 17 ቀን 2014 ዓ.ም አምስት ሆነው ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የእነሀዊን ቤት በር ሰብረው ገቡ.... የዚህን ዜና ሙሉ መረጃ ለማግኘት ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ https://www.press.et/ama/?p=62502
إظهار الكل...
የሰሜን ወሎ ዞን ሀገረ ስብከት ዋና አስተዳዳሪ ጳጳስ አባ ኤርሚያስ ዝየራችን እና የርሳቸው ለመላው ሀገራችን ያስተላለፉት መልዕክት !!! »»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»» እኔ ፣ ሻለቃ ሹመት እና የአማራ ፋኖ የራሳ አንበሶች ጋር ወደ አባታችን የገባነው አላማው ስለ እርሳቸው ለህዝባችን ያደረጉትን መልካምነት ለማመስገን እና ጤንነታቸውን ለመጠየቅ ነበር። እርሳቸውም በደስታ ጥያቄያችነን ተቀብለው ወደ ውስጥ አስገቡን ኦርቶዶክስ አማንያኖቹን አሳልመው እኔን እና ሻለቃ ሹመትን ስመው ተቀበሉን። ከዚያም የመጣነው ደህንነተዎን ለመጠየቅ እና ለማመስገን ነው እንደት እንዳሳለፉ ይንገሩን አልናቸው። እርሳቸውም ደስ በሚል አንደበታቸው እንድህ አጫወቱን ፦ " በመጀመሪያ ደረጃ ፈጣሪን አመሰገኑ ከዚያም የወልድያን ህዝብ አመሰገኑ ቀጥሎም የሰሜን ወሎን ህዝብ አመሰገኑ ምክኒያቱም ያዘዝናቸውን ፈጽመዋልና አሉን ፤ እንደት ስንላቸው ህዝባችን በተቸገረ ሰዓት ሙስሊም ክርስቲያን ሳንል የሰላም ኮሚቴ አዋቀርን ከዚያ በዚህ ሰላም ኮሚቴ አማካኝነት ለሁሉም መልዕክት ላክን፤ ይህም መልዕክት በየቤቱ ያስቀመጣችሁት ፣ የቀበራችሁት ብር ካለ ስለነገ መኖራችን ፈጣሪ ነው የሚያውቀውና ወደቤተክርስቲያን አምጡልን ቀን ሲወጣ ቤተክርስቲያኗ ዋስ ትሆናለች ትከፈላላችሁ ብለን በጠየቅነው መሰረት 5.7 ሚልየን ብር ሰበሰብን ፤ ይህነንም ብር እስላም ክርስቲያን ሳንል እስከ መርሳ ፣ ቆቦ ጉባላፍቶ ድረስ አከፋግለናል። ከዚያ መድሃኒቶችን አሰባስበን አከፋፍለናል። እህል ሲያልቅብን ወደ ገበሬው ወርደን መርሳ እና ቆቦ ድረስ እየሰበሰብን እያለ መንግስት ገባልን ብለዋል። ወደ ከተማው ይውገባውም ወራሪው ሃይል ስንገስጻቸው ያለ ማንገራገር ሰምተውናል ፣ ምክራችነንም ይቀበሉ ነበር ብለውናል አባታችን። ነገር ግን ለመላው ህዝብ ያስተላለፉት መልዕክት አለ በተለይ ወልድያ 1/ ማንም ሰው በስሜት እና በጥላቻ ያለ ማስረጃ እንዳይገደል 2/ ገና ለገና የትግራይ ተወላጅ ስለሆኑ ተብለው ግፍ እና በደል እንዳይደርስባቸው። ገንዘብ በቸገረን ጊዜ ገንዘጋቸውን ስማችን እንዳይጠቀስ ብለው ለግሰውልናል። 3/ ጥፋተኛ እና ተጠርጣሪ ካለ ለመንግስት እንድቀርብ እና መንግስት ህጋዊ ፍትህ እንድሰጠው 4/ መንግስት እነዚህን ነገሮች በመከታተል እና በአስቸኳይ ወሰ ስራው እንድመለስ እና የተጎሳቆለውን ወገናቸው እንዲያረጋጋ ጥሪያቸውን ለሁሉም እንዲደርስ አስተላልፈዋል። እንደ አባ ኤርሚያስ አንደበተ ርቱኡ ቅን አባቶችን ያብዛልን። ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሰላም እንዲሰፍንልን ጸሎት አድርገው እኛንም ልንጠይቃቸው ስለመጣን ዱዓ አድርገውልን ተሰነባብተናል። @zementeshagariw
إظهار الكل...
አሸባሪው ሸኔ በቄለም ወለጋ ዞን አንፊሎ ወረዳ የ900 ሚሊዮን ብር ቁሳዊ ውድመት አደረሰ ************************** አሸባሪው ሸኔ በቄለም ወለጋ ዞን አንፊሎ ወረዳ ብቻ ግምታዊ ዋጋው 900 ሚሊዮን ብር የሆነ ቁሳዊ ውድመት ማድረሱ ተገለፀ። የሽብር ቡድኑ የመንግሥት ደጋፊዎች ናችሁ ሲል ንፁሃንን በግፍ ገድሏል ሲሉ የወረዳው አስተዳዳሪ ጌታቸው ገመቹ ለዋልታ ገልጸዋል። የአምሳያው ሕወሓት ተላላኪ የሆነው አሸባሪው ሸኔ በዞኑ ሸበል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘውንና ለጊዜው ባለቤትነቱ ባልታወቀው የብዙኃን መገናኛ የስርጭት ማቀባበያ ሰርቨር እና የቴሌኮም ማማ ላይ ጥቃት መፈጸሙ ታውቋል። የቡድኑ የጥፋት እጆች በጤና ጣቢያ፣ ትምህርት ቤት፣ ፓሊስ ጣቢያ፣ የመዘጋጃና የአስተዳደር ተቋማት ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት በመሰንዘር ከመዝረፍና አቃጥሎ መሄድ አልታቀቡም። ሸኔ ይህንን መሰሉን ጥቃት በሕዝብ መገልገያ ተቋማት ላይ በመፈፀም እታገልለታለሁ በሚለው ሕዝብ ላይ የጭካኔ እና አረመኔያዊ ድርጊት አድርሷል። የወረዳው አስተዳዳሪ የሽብር ቡድኑ ሸኔ ኦሮሞን እየዘረፈና እየገደለ መልሶ የኦሮሞ ጠበቃ ነኝ ማለቱ በሕዝቡ ስም እየነገደ እንደሆነ ግልፅ ማሳያ ነው ብለዋል። የኦሮሞን ሕዝብ ሲገድል ከነበረው አሸባሪው ሕወሓት ጋር እርኩስ ጋብቻ የፈፀመው አሸባሪውና ፅንፈኛው ሸኔ በአሳዳጊው ወያኔ የጭካኔ መንገድ ላይ እንደሚገኝም ዋልታ ዘግቧል።
إظهار الكل...
ወላጅ አባቱን በጦር ሜዳ ያጣው ህፃን ቢንያም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዛሬው እለት ባለሁለት መኝታ ኮንደሚኒየም የመገልገያ ቁሳቁሶች የተሟላለት መኖሪያ ቤት አስረክበውታል። https://www.facebook.com/100003793791660/posts/2410501699086266/?app=fbl
إظهار الكل...
#ያንብቡ በኢትዮጵያ በሚገኙ የተለያዩ የፖለቲካ እና የሃሳብ መሪዎች እንዲሁም የኅብረተሰብ ክፍሎች መካከል እጅግ መሠረታዊ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የሃሳብ ልዩነት እና አለመግባባት የሚታይ በመሆኑ ይህን ልዩነት እና አለመግባባት ለማርገብና ለመፍታት ሰፋፊ አገራዊ የሕዝብ ምክክሮችን አካታች በሆነ መንገድ በማካሄድ አገራዊ መግባባት መፍጠር አስፈላጊ እንደሆነ ተገልጿል። መሠረታዊ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ አካታች አገራዊ ምክክሮችን ማካሄድ የተሻለ አገራዊ መግባባትን ለመገንባትና በሂደትም የመተማመንን እና በወሳኝ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ተቀራርቦ የመሥራት ባህልን ለማጎልበት፣ እንዲሁም የተሸረሸሩ ለማሳለጥ የሚያስችል ሥርዓት በሕግ መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ተብሏል። አገራዊ ምክክሮች ተቀባይነት እና ተዓማኒነት ያላቸው እንዲሆኑ ከሚያስችላቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ምክክሮቹን የሚያመቻቸውና የሚመራው አካል ብቃትና ገለልተኝነት በመሆኑ፤ ምክክሮቹን በብቃትና በገለልተኝነት ለመምራትና ለማስተባበር የሚችል ሰፊ ቅቡልነት ያለው ተቋም ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራስያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀፅ 55(1) መሠረት ከላይ የተያያዘው አዋጅ ታውጇል። ይህ ኮሚሽኑ በሀገሪቱ ለዘመናት የቀጠለውን ያለመግባባት አዙሪት በማስወገድ አገራዊ አንድነት እንደሚያረጋገጥ ተስፋ እንደተጣለበት ተነግሯል። የህ/ተ/ምክር ቤት በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ ዜጎች ረቂቅ አዋጁን አንብበው ም/ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ ሊያየው ይገባል የሚሉትን ሀሳብ እንዲሰጡ ጠይቋል። (እንደ ዜጋ ከላይ የተያያዘውን ረቂቅ አዋጅ አንብበው በም/ቤቱ ገፅ https://www.facebook.com/599208023518983/posts/4270721263034289/ ገብተው ሀሳቦትን ያካፍሉ) ✍️Tikvahethiopia
إظهار الكل...
የኢትዮጵያ_አገራዊ_ምክክር_ኮሚሽን_ማቋቋሚያ_አዋጅ_Amhaic.doc1.43 KB
#ከሚሴ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የቀድሞው ዋና አሰተዳዳሪ አቶ አሕመድ ሐሰን እና አዲሱ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሕመድ አሊ የስልጣን ርክክብ አድርገዋል። ምክር ቤቱ የዞኑ ካቢኔ አባላትን ሹመት ያፀደቀ ሲሆን እነሱም፤ 1ኛ) አቶ አብዱ እንድሪስ - ምክትል አስተዳዳሪ እና የሰላምና ደኅንነት መምሪያ ኀላፊ 2ኛ) ወ/ሮ አሚናት ሁሴን - የገቢዎች መምሪያ ኀላፊ 3ኛ) አቶ አብዱ መሄ ኡመር - የፋይናንስ መምሪያ ኀላፊ 4ኛ) ወ/ሮ ጦይባ አሕመድ - የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኀላፊ 5ኛ) አቶ ኡስማን አልይ - የጤና መምሪያ ኀላፊ 6ኛ) አቶ ታሪኩ አብዲሳ - የውኃ መምሪያ ኀላፊ 7ኛ) አቶ ሰይድ አብዱ - የትምህርት መምሪያ ኀላፊ 8ኛ) ወ/ሮ ፋጡማ ሰይድ-የኢንቨስትመንት መምሪያ ኀላፊ 9ኛ) አቶ ጀማል እንድሪስ - የመሬት አስተዳደር መምሪያ ኀላፊ 10ኛ) አቶ መሀመድሷቢር ሀጂ - የሲቪል ሰርቪስ መምሪያ ኀላፊ 11ኛ) አቶ አሜ ጠያር - የባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኀላፊ 12ኛ) አቶ መሀመድሲራጅ ሙስጠፋ - የመንገድና ትራንስፖርት መምሪያ ኀላፊ ባሉበት የሚቀጥሉት ደግሞ 13ኛ) አቶ ጀማል ሐሰን - የኮምዩኒኬሽን መምሪያ ኀላፊ 14ኛ) ኢንጅ. ሐሊማ ኡመር - የከተማ ልማት መምሪያ ኀላፊ 15ኛ) አቶ አዲሱ ቡላ - የግብርና መምሪያ ኀላፊ 16ኛ) አቶ መሐመድ አሚን - የንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኀላፊ 17ኛ) አቶ ሙሉጌታ ተሾመ - የፍትሕ መምሪያ ኀላፊ 18ኛ) ወ/ሮ ባይሴ ሚጅና - የቴክኒክና ሙያ መምሪያ ኀላፊ 19ኛ) አቶ ሰለሞን ይትባረክ - የወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኀላፊ በተጨማሪም የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ አቶ ከድር አሊን የዞኑ ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ፣ አቶ ጀማል ሐሰንን የዞኑ ፖለቲካ ዘርፍ ኀላፊ እና አቶ መሐመድ ሙሳን የዞኑ አደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ አድርጎ ሹሟል። አሚኮ
إظهار الكل...
አቶ አብርሃ ደስታ ከእስር ተፈቱ። የዓረና ትግራይ ለሉአላዊነትና ዴሞክራሲ ፓርቲ (ዓረና) አመራር የሆኑትና በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ያገለገሉት አቶ አብርሃ ደስታ ዛሬ ከእስር ተፈተዋል። አቶ አብርሃ ከእስር የተፈቱት በ10 ሺ ብር ዋስ መሆኑ ታውቋል። አቶ አብርሃ ደስታ በተረጋገጠው የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ " ከ82 ቀናት በኋላ በፍርድ ቤት የአሰር ሺ ብር የዋስትና ብይን መሰረት ከእስር ተለቅቄያለሁ " ሲሉ ፅፈዋል። (ቲክቫህ)
إظهار الكل...
#የሽብር_ቅስቀሳ_ጀምረዋል! በዚህ ቪዲዮ ላይ የሚናገረው የመለስ ዜናዊ ጠባቂ የነበረና በውጭ የሚኖር የትግሬ ወራሪ አባል ነው። ከትግርኛ በእንግሊዘኛ ተተርጉሞ የተፃፈው በግልፅ እንደሚያሳየው ሰውዬው በግልፅ የሽብር ቅስቀሳ እያደረገ ነው። <<በድሮን ዘመን መደበኛ ውጊያ ስለማያዋጣ ስልታችን በመቀየር፣ የተወሰኑ ግለሰቦችን በያዙ ቡድኖች፣ ብቃት ባላቸው ኮማንዶዎች ሽብር መፍጠር አለብን ይላል። ጠላት ካላሸበርነው ያሸብራናልና ቀድመን ልናሸብረው ይገባል እያለ ይቀሰቅሳል። አዲስ አበባ ድረስ ሄደን ማሸበር አለብን፣ እንቅልፍ ሊተኙ አይገባም፣ ህንፃዎችን፣ ቤተ መንግስቱን ወደ አመድነት መቀየር አለብን>> እያለ በይፋ ይናገራል። ☞የሚናቅ መረጃ የለም።በየአካባቢው የተበታተነ የወራሪው ኃይልን ለሽብር ስራ ሊዘጋጅ እንዳይችል ሆኖ መፅዳት ይኖርበታል። Credit :Getahew Shiferaw
إظهار الكل...
4.59 MB
የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገራት እንዲገኙ አልተፈለገም። ከዚህ በፊት ስለኢትዮጵያ ጉዳይ ከአስር ጊዜ በላይ ስበስባ የተቀመጠው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ትላንት ሰኞ በኢትዮጵያ ጉዳይ ለመነጋገር ስብሰባ እንደሚቀመጥ ታውቋል። ምክር ቤቱ ዛሬ በ “any other business” ስር በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ የሚወያይ ሲሆን ስብሰባው እንዲካሄድ የጠየቁት ፦ 🇪🇪 ኢስቶኒያ 🇫🇷 ፈረንሳይ 🇮🇪 አየርላንድ 🇳🇴 ኖርዌይ 🇬🇧 ዩናይትድ ኪንግደም 🇺🇸 አሜሪካ ናቸው። የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች የአስቸኳይ ጊዜ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ማርቲን ግሪፊትስ በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ እርዳታ ጉዳይን በተመለከተ ለፀጥታው ም/ ቤት አባላት አጭር ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሏል። በትግራይ ክልል ውስጥ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ጊዜ አንስቶ የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት ስለኢትዮጵያ ጉዳይ ከአስር ጊዜ በላይ ስብሰባ የተቀመጠ ሲሆን የዛሬው ስብሰባ ባለፈው ሳምንት የተመድ የሰብአዊ መብቶች ም/ቤት ልዩ ስብሰባ አካሂዶ ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ የተከሰቱ የመብት ጥሰቶችን የሚመረምር ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች አካል እንዲቋቋም በድምጽ ብልጫ ከወሰነ በኋላ ነው። ( https://www.securitycouncilreport.org/whatsinblue/2021/12/ethiopia-meeting-under-any-other-business.php
إظهار الكل...
የአገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ ግብዓት ማሰባሰብ ተጀምሯል። በህ/ተ / ም/ቤት የህግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቶ የተለያዩ ግብዓቶችን አሰባስቧል፡፡ በይፋዊ የውይይት መድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የሰብኣዊ መብት ኮሚሽን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤትና የተለያዩ የሲቪክ ማህበራት የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈውበታል፡፡ በውይይቱ መግቢያ የፍትህ ሚንስቴር ሚንስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ማቋቋሚያ አዋጁን አስመልክተው አጭር ገለጻ ያቀረቡ ሲሆን፤ የማቋቋሚያ አዋጁን አስፈላጊነት፣ እስካሁን ያለፈባቸውን ሂደቶች እንዲሁም የኮሚሽኑ ተግባርና ኃላፊነት ላይ ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡ ለሀገራዊ መግባባት የሚጠቅሙ አጀንዳዎች መለየት፣ የሚሳተፉ አካላትን መለየት፣ የምክክር መድረኮችን ማሳለጥ፣ ከምክክር መድረኮቹ የተገኙ ምክረ ሀሳቦችንና የአተገባበር ስልታቸውን የሚጠቁም ሰነድ ማዘጋጀት እንዲሁም ተግባራዊነታቸውን መከታተል ከሚቋቋመው ኮሚሽን የሚጠበቁ ዋና ዋና ተግባራት ስለመሆናቸው ጠቁመዋል፡፡ ከየተቋማቱ የመጡት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ለሚቋቋመው ኮሚሽን ይጠቅማል ያሉትን መልካም ተሞክሮዎቻቸውን በማጋራት ሊገጥም ይችላል ያሉትን ስጋት ጠቁመዋል፡፡ በሚቋቋመው ኮሚሽን ተግባርና ኃላፊነት እንዲሁም የኮሚሽነሮች አሰያየም ላይ ተደጋጋሚ አስተያየቶች የቀረቡ ሲሆን፤ በረቂቅ አዋጁ አንቀጽ 9/10 ስር ኮሚሽኑ ዝርዝር ሪፖርት በማዘጋጀት ለመንግስት ያቀርባል የሚለው ሀሳብ ኮሚሽኑን በመንግስት ተጽእኖ ስር ሊከተው ይችላል የሚሉና ተመሳሳይነት ያላቸው የገለልተኝነት ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን በዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ Via HPR
إظهار الكل...
ስዊዘርላንድዊው የኢትዮጵያ ወዳጅ ግለሰብ የ5 ሺህ የአሜሪካን ዶላር የቦንድ ግዥ ፈጸሙ ******************* ነዋሪነታቸው በሎዛን ስዊዘርላንድ የሆኑት የኢትዮጵያ ወዳጅ ሚስተር ጉሴፔ አንቶኒዮ ማሪኖ የተባሉ ግለሰብ የ5 ሺህ የአሜሪካን ዶላር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቦንድ ግዥ ፈጽመዋል። በተጨማሪም 3715 ኪግ የሚመዝኑ ልዩ ልዩ አዳዲስ ልብሶችን እና ጫማዎችን በአረመኔው የህወሓት ታጣቂ ቡድን ጉዳት ለደረሰባቸው እና ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች አገልግሎት እንዲውሉ ጀኔቫ በሚገኘው ሚሲዮን በአካል በመገኘት ለግሰዋል። በወቅቱም ከኢትዮጵያ ጎን በመቆምም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ሚስተር ጉሴፔ አንቶኒዮ ማሪኖ ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ አመልክቷል።
إظهار الكل...
አቶ ካሳሁን እምቢአለ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ ሆነው ተሾሙ፡፡   የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄው 4ኛ ዙር 9ኛ ዓመት 32ኛ አስቸኳይ ጉባኤ አቶ ካሳሁን እምቢአለን የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ አድርጎ ሾሟል፡፡   የተቀዳሚ ከንቲባው ሹመት በደብረ ብርሃን ከተማ ብልፅግና ጽህፈት ቤት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ በአቶ ቃሉ ተፈራ ለምክር ቤቱ ቀርቦና በምክር ቤት አባላቱ ሀሳብና አስተያየት ተሰጥቶበት በሙሉ ድምጽ ጸድቋል፡፡
إظهار الكل...
በጋሸና ግንባር የሰሜን ምዕራብ ዕዝ የፈፀመው አኩሪ ገድል ሲዘከር ይኖራል ሲሉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ፡፡   ዛሬ በጋሸና ግንባር ለመከላከያ ሰራዊቱ የምስጋና መርሃ ግብር የተዘጋጀ ሲሆን÷ አሸባሪው ህወሓት ለጦርነት ቁልፍ ቦታ የሆነችውን ጋሸናን ለአምስት ወራት በመቆጣጠር በህዝቡ ላይ ሰቆቃዎችን እና ግፎችን ሲፈፅም መቆቱን ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ ተናግረዋል።ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት በወሰደው የተቀናጀ ጥቃት የሽብር ቡድኑ አከርካሪው ተመቶ ወደ መቀሌ ፈርጥጧል ነው ያሉት።   ዛሬ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ለፈፀመው ገድል ለማመስገን የተገኙት ጀኔራል ብርሃኑ÷ ዕዙ በቀላል መስዋዕትነት የተለያዩ ግዳጆችን በመወጣት በሽብር ቡድኑ ላይ በወሰደው የማጥቃት ዘመቻ በርካታ ምሽጎች ተደምስሰዋል፣ ከእነዚህ ውስጥ የጋሸና እና የሀሙሲት ምሽጎች ይጠቀሳሉ ብለዋል።ላለፉት አርባ እና ሃምሳ ዓመታት በውሸት የቆየው የሽብር ቡድኑ አሁንም ሽንፈቱን አምኖ ከመቀበል ይልቅ ተመሳሳይ ቅጥፈቱን ዳግም ለትግራይ ህዝብ እየነዛ ይገኛልም ነው ያሉት ጄነራል ብርሃኑ።   ሰላምን አልቀበልም በማለት ተከታታይ ጥቃቶችን በመከላከያ ሰራዊቱ እና በህዝቡ ላይ አስነዋሪ ተግባርን የፈፀመው ቡድኑ፥ የትግራይ ወጣቶችን በማስጨረስ የጭካኔ ተግባሩን አሳይቷል፤ ለዚህ ደግም በየአውደ ውጊያው ለጦርነት ያሰለፋቸው ወጣቶች ወድቀው ቀርተዋል ብለዋል።ይህ የመጨረሻው ድል አይደለም ያሉት ጄኔራሉ÷ መከላከያ ሰራዊቱ ለኢትዮጵያ አለኝታ ሆኖ ይቀጥላል፤ የህዝቦቿን ሰላምን ያስጠብቃል ሲሉም ገልጸዋል።   በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ፥ “በወራሪው ቡድን ተወረው የነበሩ አብዛኛው የአማራ ክልል አካባቢዎች በእናንተ መስዋዕትነት ነፃ ሆነዋል፤ ለዚህም በእኔ እና በክልሉ ህዝብ ስም ምስጋና ይገባችኋል” ብለዋል።“የገጠመን ወራሪ ሃይል ቀላል የሚባል አይደለም ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ በአንድነታችን ላይ በመምጣት በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ ጭፍጨፋ በመፈጸም የጀመረውን ጥፋት ላከሸፈው የመከላከያ ሰራዊት የአማራ ህዝብ ትልቅ ክብር አለው” ነው ያሉት።   በዝግጅቱ ላይ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ጌታቸው ጉዲናን ጨምሮ የዕዙ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች፣ የሃገር የሽማግሌዎች እና አርቲስቶች ተገኝተዋል።በዕዙ ስር ከጋሳይ ፣ጋሸና እስከ ድልብ ድረስ ከፍተኛ ተጋድሎ ለፈፀሙ ለ 34ኛ እና 51ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች እና አባላት ክብር ይገባቸዋል ተብሏል።ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን በመሆን ለተፋለሙት እና ለተዋደቁት የአማራ ልዩ ሐይል፣ ፋኖ እና ሚሊሻ እንዲሁም በደጀንነት ከመከላከያው ጎን ለቆሙት የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይ ለደቡብ ጎንደር ህዝብ እና አመራር ምስጋና ይገባዋልም ነው ያሉት። [FBC]
إظهار الكل...
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2021 የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ ሽልማትን አሸነፈ! የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2021 የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድነት ሽልማትን በድጋሚ አሸነፈ። ሽልማቱን የሰጠው መቀመጫውን ብሪታኒያ ያደረገው እና በአቪዬሽን ኢንዱስትሪ አገልግሎት ጥራት፥ የሚሸልመው ስካይ ትራክስ የተሰኘው ተቋም መሆኑን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ የደቡብ አፍሪካ እና ኬኒያ አየር መንገዶችም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ በመቀጠል የሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
إظهار الكل...
አሜሪካ ቃል ለገባችበት ጉዳይ የማትታመን ሀገር ናት-ፑቲን የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) በምስራቅ አውሮፓ የሚያደርገውን መስፋፋት እንዲያቆም የሚደረገው ውይይት በአሜሪካ አለመታመን ምክንያት እንደማይሳካ ስጋታቸውን ገልጸዋል።ፕሬዚዳንቱ አክለውም አሜሪካ ለቃሏ የማትታመን ሀገር መሆኑን አንስተው፥ይህ ክህደቷ የተፈረመ ስምምነትን እስከመቅደድ ሊደርስ ይችላል ነው ያሉት። ፑቲን ለሩሲያ ወታደራዊ መኮንኖች ሞስኮ ውስጥ ባደረጉት ንግግር ''ምዕራባውያን እምነት የሚጣልባቸው አጋሮች አይደሉም'' ሲሉም ተሰምተዋል። “ሩሲያ በድንበሯ አቅራቢያ የአሜሪካ ወታደሮች እና የጦር መሳሪያዎች ስለመታየታቸው የተፃፈ ማረጋገጫ እንዲሰጣት ትፈልጋለች፤ ሆኖም አሜሪካ ቃሏን እንደማታከብር እኔም እናንተም እናውቃቸዋለን” ብለዋል ለወታደራዊ መኮንኖቹ። አሜሪካ ከዚህ ቀደም የፈረመቻቸውን ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ስትጥስ እና ከአንዳንዶቹ የትብብር ድርጅቶችም ስታፈነግጥ በተግባር መታየቷን ጠቅሰዋል። ለአብነትም አሜሪካ በፈረንጆቹ በ1972 የፀረ ሚሳኤል መሳሪያ ማጎልበትን በተመለከተ ከተፈረመው ስምምነት ማንንም ሳታማክር በ2002 መውጣቷን አስታውሰዋል። ከዚህ ባሻገር ምዕራባውያንና አሜሪካ ለራሳቸው ደህንነት ሲሉ በዓለም አቀፍ ተቋማት የወጡ ህግጋትን በመናቅ በሺዎች ኪሎሜትር አቋርጠው በሌሎች ሀገራት የፀጥታና ደህንነት ጉዳይ ጣልቃ ሲገቡ መታየታቸውን አብራርተዋል ፑቲን።ሩሲያ ደህንነቷን ለማስጠበቅ ስትል በአሜሪካ የሚዘወረው ኔቶ ለሚወስዳቸው ማንኛውም ተገቢ ያልሆኑ እንቅስቃሴዎች ወታደራዊ እርምጃዎችን ለመውሰድ በተጠንቀቅ ላይ መሆኗን ፕሬዚዳንቱ ስለመናገራቸው አር ቲ ዘግቧል። ✍Asham
إظهار الكل...
ለ2022 የካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ ከስምንት አመታት በኋላ መሳተፋቸዉን ያረጋገጡት ዋልያዎቹ ዝግጅታቸውን ከሀገር ዉጭ ለማድረግ እሁድ ወደ ካሜሩን እንደሚያቀኑ ታዉቋል! ከዚህ ቀደም ዋልያዎቹ ዝግጅታቸዉን ከሀገር ወጥተዉ ለመከወን ማሰባቸዉን እና ከሚመለከተዉ የመንግስት አካል ጋርም በዝግጅታቸዉ እና ተያያዥ ጉዳይ ዙሪያ በጥልቀት መወያየታቸዉን ማስነበባችን ይታወሳል። አሁን ደግሞ ዋልያዎቹ ለአፍሪካ ዋንጫዉ የሚኖራቸውን ዝግጅት ለመከወን አፍሪካ ዋንጫው ወደ ሚደረግባት ካሜሩን እሁድ በ17/2014 ዓ.ም እንደሚጓዙ እንዲሁም በዝግጅታቸዉ ወቅት ከሁለት ሀገራት ብሔራዊ ቡድኖች ጋር የወዳጅነት ጨዋታ እንደሚያደርጉ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።በተያያዘም ዋልያዎቹ በባህል ልብስ አጊጠዉ ጉዟቸውን እንደሚያደርጉ ሲገለፅ ከዚህ በተጨማሪም በካሜሩን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ለብሔራዊ ቡድኑ አቀባበል ለማድረግ ከወዲሁ በዝግጅት ላይ መሆናቸዉ ተሰምቷል። Via Hatric Sport
إظهار الكل...
በሶማሌ ክልል በድርቅ ምክንያት ከ146 ሺሕ በላይ እንስሳት መሞታቸው ተገለፀ! በሱማሌ ክልል በሚገኙ 78 ወረዳዎች ላይ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በሁለት ወራት ተኩል ጊዜ ውስጥ ከ146 ሺሕ በላይ ከብት፣ ግመልና ፍየሎች መሞታቸውን የክልሉ አደጋ ሥጋት አመራር ቢሮ አስታወቀ፡፡ በክልሉ ከሚገኙት 11 ዞኖች ውስጥ በዘጠኙ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎችና በሲቲ ዞን ውስጥ በሚገኙ አምስት ወረዳዎች ውስጥ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት፣ በክልሉ የሚገኙ ዕርዳታ ፈላጊ ዜጎች ቁጥር ወደ 3.4 ሚሊዮን ከፍ እንዳለ ተገልጿል፡፡
إظهار الكل...
በሠመራ እና አንዳንድ የአፋር ክልል ከተሞች ላይ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም ጀመረ! አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በአፋር ክልል ወረራ ባደረገበት ወቅት የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ውድመት በማድረሱ በክልሉ ከኮምቦልቻ ሰብስቴሽን የሚያገኙት 7 አገልግሎት መስጫ ማዕከላት መሉ በሙሉ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሳያገኙ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡ ሆኖም የአፋር ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት አመራርና ሠራተኞች ባደረጉት ርብርብና የጥገና ሥራ ከትላንት ጀምሮ ሠመራ፣ ሎጊያ፣ ዱብቲ፣ አይሳኢታ፣ ሚሌ፣ ዲችኦቶ፣ ኤሊዳኣር እና ጋላፊ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም አግኝተዋል፡፡ ኤሌክትሪክ በከተሞቹ የማገናኘቱ ሥራ የመዘግየቱ ምክንያት ከኮምቦልቻ ሰብስቴሽን ላይ የኃይል መዋዠቅ በማስከተሉና የኦፕቲካል ፋይበር ጥገና ባለመጠናቀቁ ምክንያት መሆኑን የአፋር ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡ በመሆኑም በከተሞቹ አልፎ አልፎ የኃይል መቆራረጥ ችግር ሊያጋጥም እንደሚችል መገለጹን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
إظهار الكل...
<<መልካም ዜና የሀይቅ ሆስፒታል ዛሬ ጠዋት አገልግሎት መስጠት ጀምሯል! የሀይቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የድንገተኛ ህክምና ፣ የተመላላሽ ህክምና ፣ የወሊድ አገልግሎት ፣ የድንገተኛ ኦፕሬሽን አገልግሎት ፣ የላቦራቶሪ እና የመድሀኒት አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ ሆኗል።>> ዶ/ር ያሬድ አግደው የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ
إظهار الكل...
ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ 2 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ አድርጋለች። ድጋፉ በሰሜናዊው የአገሪቱ ክፍል፣ በሦስቱ ክልሎች ሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸዉ ሰዎች ተጠቃሚ እንደሚያደርጋቸው በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ኤምባሲ አሳውቋን። (ቲክቫህ)
إظهار الكل...
ደሴ ከተማ ትናንት ከሰዓት በኋላ ወሎ ዩኒቨርስቲ አካባቢ በአንድ የመኖሪያ ቤት ግቢ ውስጥ የግለሰቡን ልጆች አግተው በመያዝ ተደብቀው የነበሩ 16 የሽብር ቡድኑ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰምቷል።ይህ የሚያመለክተው በተለያዩ ቦታዎች ተበታትኖ የሚገኝን የወራሪ ኃይል አባላት መኖሩን ነው።አካባቢያችን ከመሰል የሽብር ቡድኑ አባላት ማፅዳት ይገባል።
إظهار الكل...
ወልድያ ከተማ ተንቀሳቃሽ ስልክ አገልግሎት ጀምሯል።
إظهار الكل...
ዘ ጆርዳን ታየምስ የፃፈውን ሱሌማን አብደላ ወደ አማርኛ መልሶታል . ቱርክ ኢትዮጵያን ሀያል ለማድረግ ልምዷንና ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጠል አስታቃለች አለ። ዘጆርዳን ታየምስ ጋዜጣ ኢትዮጵያ የምዕራባውያን ጫና የሚቋቋም ሀገር በቀል ኢኮኖሚ ላይ አትኩራ እንድሰራና ኢትዮጵያን የአፍሪካ ቀንድ ሀያል አገር ለማድረግ ቱርክ አበክራ ትሰራለች ሲል ስሙ መጠቀስ ያልፈገን የቱርክ ባለስልጣናት ምንጭ ጠቅሶ ዘግቧል። ከአፍሪካ ሁለተኛው የህዝብ ብዛት ያላትና የአለም መጋቢ እርሻ መሬት ያላት ኢትዮጵያ ከህዝቧ የአልገዛም ባይነት ባህልና አስተሳሰብ ጋር ለቱርክ የምንግዜም አጋሯ ሆና ትቀጥላለች ብሏል ዘገባው። እዚህ ላይ የምታውቁት ነገር እኛ ሱዳን ይሄንን እድል አግኝ አበላሽታው ነው። ወላዋይ መሆን አይቅምም። በድህነታችን ላይ ለማንም የማንገዛ ህዝቦች መሆናችንን እንዲህ ስናረጋግጠም ክብራችን እንዲህ እየናየ ይመጣል። ኢትዮጵያዊ መሆን ማለት ይሄ ነው !
إظهار الكل...
”ኢትዮጵያ ሰላሟ ተጠብቆ በአፍሪካ ጠንካራ ሀገር ሆና እንድትቀጥል እስራኤል የበኩሏን ድጋፍ ታደርጋለች” -በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ኢትዮጵያ ሰላሟ ተጠብቆ በአፍሪካ ጠንካራ ሀገር ሆና እንድትቀጥል እስራኤል የበኩሏን ድጋፍ እንደምታደርግ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ገለጹ። አምባሳደሩ ይህን ያሉት በአማራና አፋር ክልሎች በጦርነቱ ሳቢያ ለተፈናቀሉ ዜጎች የዓይነት ድጋፍ ባደረጉበት ወቅት ነው። በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ እና ሶሎሞን ፋውንዴሽን በትብብር 14 ሺህ ኪግ ቁሳቁስ፣ አልባሳት፣ ዊልቸሮችና የተለያዩ የንጽህና መጠበቂያዎችን ያካተተ ድጋፍ አድርገዋል። ድጋፉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ተረክበዋል። በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፥ ሁለቱ ሀገራት ረጅም ዘመን ያስቆጠረ የታሪክ፣ የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ግንኙነት አላቸው። ኢትዮጵያ ሰላሟና አንድነቷ ተጠብቆ በአፍሪካ ጠንካራ ሀገር ሆና እንድትቀጥል እስራኤል የበኩሏን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። በተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው ለሚገኙ ዜጎች የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አምባሳደር አለልኝ አክለዋል። የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በበኩላቸው፣ በአማራና አፋር ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል። የሁለቱ ሀገራት ህዝብና መንግስት ያላቸው የረጅም ጊዜ ወዳጅነትና ቤተሰባዊነት ዘመን የሚሽረው አይደለም ብለዋል። በቀጣይም የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ከእስራኤል ህዝብና መንግስት ጋር ተቀራርበው እንደሚሰሩ ሚኒስትሯ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። (ኢዜአ)
إظهار الكل...
ለወልዲያ ከተማና አካባቢው አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ተንቀሳቃሽ ማከፋፈያ ጣቢያ በህውሀት ሀይል ተነቅሎ ተወስዷል ተባለ! ዶሮ ግብር በተባለው ቦታ ለወልዲያ ከተማና አካባቢው አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ተንቀሳቃሽ ማከፋፈያ ጣቢያ በአሸባሪው የህውሀት ሀይል ተነቅሎ መወሰዱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል፡፡ የባለሙያዎች ቡድን በስፍራው ተገኝቶ እንዳረጋገጠው ተንቀሳቃሽ ማከፋፈያ ጣቢያው ለስም የቀረ ነገር ሳይኖር በአሸባሪው የህወኃት ቡድን ተነቃቅሎ ተወስዷል። ማከፋፈያ ጣቢያው ከወልዲያ ነባር ባለ 66 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ ጋር በመሆን ለወልዲያ ከተማ፣ ለወልዲያ ዪኒቨርሲቲ፣ ጭፍራ፣ ሲሪንቃ፣ ሳንቃ፣ ኡርጌሳ፣ ውጫሌ፣ ጉባላፍቶ፣ቃሊም፣ ጉብዬ፣ ሀራ፣ሮቢት ቆቦ ጊራና ከተሞችና አካባቢያቸው የሚሄዱ መስመሮች ነበሩት። የሽብር ቡድኑ ተንቀሳቃሽ ማከፋፈያ ጣቢያውን ጨምሮ ከነባሩ የወልዲያ ማከፋፈያ ጣቢያ የሥርጭት ትራንስፎርመሮችን ነቅሎ መውሰዱን እና የትራንስፎርመር ዘይት ገልብጦ መውሰዱን ማረጋገጥ ተችሏል። የዓይን እማኞቸ እንደገለፁት የሽብርተኛው የህወኃት የዘረፋ ቡድን ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የተዋቀረና ትራንስፎርመሩ ችግር አለበት ወይስ የለውም የሚለው እየተፈተሸ ነው የተወሰደው ብለዋል። በባለሙያዎች ቡድኑ የሚቀርበውን መነሻ መሰረት አድርጎ የጥገና ቡድኑ ከነሐሴ 2 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ የተቋረጠውን የወልዲያና አካባቢው ኤሌክትሪክ ለማገናኘት ፣ በፍጥነት የጥገና ሥራውን እንደሚጀምር ይጠበቃል ስለመባሉ ብስራት ራዲዮ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
إظهار الكل...
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ428 ቦታዎችን ይዞታ አመከነ! የወቅቱን ሁኔታ እንደ አጋጣሚ በመጠቀም ከነባር ይዞታቸው ውጭ መሬት በህገወጥ መንገድ አስፋፍተው የያዙ ግለሰቦችን እና ድርጅቶችን ካርታ ማምከኑን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡የመንግስት ትኩረት ወደ ህልውና ዘመቻው መሳቡን ተከትሎ የህገወጥ የመሬት ወረራ እና የጨረቃ ቤት ግንባታ በከተማዋ ማስፋፊያ ቦታዎች ላይ መታየቱን ያስታወሰው የከተማ አስተዳደሩ የህገወጦችን እንቅስቃሴ ለመግታት እና በህገወጥ መንገድ የተያዙ መሬቶችን የማስመለስ ስራ በስፋት መሰራቱን የከተማ አስተዳደሩ በተቀናጀ ሁኔታ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡ እንደ ቦሌ፣ ለሚ ኩራ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ እና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች ካሉ ከማስፋፊ ቦታዎች ወረራ በተጨማሪ ህገወጦች አጋጣሚውን በመጠቀም በከተማ መሃል ሳይቀር ህገወጥ የመሬት ማስፋፊያ እና ወረራ መፈፀማቸውን ከተማ አስተዳደሩ አስታውሶ፤ በህገወጦች ላይ የማያዳግም እርምጃ መውሰዱን እርምጃውም ይቀጥላል ብሏል።እስካሁን በመሃል ከተማ ከህጋዊ ቦታቸው በተጨማሪ በህገወጥ መሬት አስፋፍተው የያዙ 428 ግለሰቦች እና ድርጅቶች የይዞታ ካርታ መምከኑ ታውቋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዚህ እርምጃ ቅሬታ አለኝ የሚል አካል ችግሩ እንደ ወትሮው በክፍለ ከተማ የሚታይ አይሆንም ይልቁንም ለከተማ አስተዳደሩ ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል ብሏል፡፡የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ሃላፊዎች ያለበት እና በከንቲባዋ የቅርብ ክትትል የሚደረግበት እና የህገወጥ እንቅስቃሴውን እና የሚወሰደውን እርምጃ የሚመራ ልዩ ኮሚቴ ያቋቋመ ሲሆን፤ ቅሬታ አለኝ የሚል ካርታው የመከነበት ወገን ለዚህ ኮሚቴ ቅሬታውን ማቅረብ የሚችል መሆኑ ተነግሯል፡፡ [Capital]
إظهار الكل...
ኦሎምፒያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በማዳበርያ የተጠቀለለ በርካታ ፎርጂድ ዶላር ተገኘ! በቂርቆስ ክፍለከተማ ወረዳ 01 ልዩ ስሙ ኦሎምፒያ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በማዳበርያ የተጠቀለለ በርካታ ፎርጅድ ዶላር መገኘቱ የክፍለ ከተማው ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል፡፡ ታህሳስ 9 ቀን 2014 ዓ.ም በክፍለ ከተማው ወረዳ 01 ልዩ ቦታው ኦሎምፒያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በርካታ የአሜሪካን ፎርጂድ ዶላር በማዳበሪያ መሰል ነገር ተጠቅልሎ መገኘቱን የኮሚኒኬሽ ቢሮ ሀላፊው አቶ አብዱ ሰይድ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል። ፎርጂድ ዶላሩ የተገኘው በህብረተሰቡ ጥቆማ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን በቀጣይም በየአካባቢው አጠራጣሪ የሆኑ ነገሮችን ህብረተሰቡ ሲመለከት በአቅራቢያው ወደሚገኝ የፖሊስ ተቋም በመሄድ ወይም ለጥቆማ ተብለው በተከፈቱ የስልክ መስመሮች ደውሎ ለፀጥታ ሀይሉ ጥቆማ እንዲጠቁም ጥሪ ቀርባል፡፡ [Bisrat FM]
إظهار الكل...
በቄለም ወለጋ ዞን አንፍሎ እና ጋዎ ቄቤ ወረዳዎች የሸኔ አባላት ከዘረፉት ሀብት እና ከተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል። ቡድኑ ዘርፎት ከነበረው 56 ኩንታል ቡና እና 16 የተለያዩ ጠመንጃዎች ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል። በቁጥጥር ስር የዋሉት የሸኔ አባላት ቡድኑ ህብረተሰቡን በመዝረፍና በማሰቃየት ላይ እንደተሰማራ ገልጸው፣ በጫካ የቀሩት የቡድኑ አባላት እጅ እንዲሰጡ ጠይቀዋል። የአንፍሎ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ ሳጂን ተካልኝ ባሩ፣በአካባቢው ዛላቂ ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ ህብረተሰቡ ከጸጥታ ኃይሎች ጋር የሚያደርጉትን ትብብር አጠናክሮ መቀጠል አለባቸው ማለታቸውን ከኦሮሚያ ኮሚዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
إظهار الكل...